CBE NOOR
Interest Free Banking (CBE NOOR) The history of Commercial Bank of Ethiopia (CBE) dates back to the establishment of the State Bank of Ethiopia in 1942.
CBE was legally established as a share company in 1963. Since then, it has been playing significant roles in the development of the country. Currently CBE has more than 38.9 million account holders in its more than 1879 branches and the number of Mobile and Internet Banking users also reached more than 6 million and 39K. Active ATM card holders reached more than 8.8 million and 17 million CBE Birr users.
ነዳጆትን በ ‘ ነዳጅ’ መተግበሪያ ይቅዱ!
******************
ከመቶ ሺዎች በላይ የሚጠቀሙትን ቀላል እና ምቹ የነዳጅ ክፍያ መተግበሪያ አሁኑኑ ከPLAY STORE እና APP STORE በማውረድ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብዎ ጋር ያስተሳስሩ!
መልካም መንገድ!!
#ነዳጅ #ክፍያ #ምቹ # ሂሳብ
‘ነዳጅ’ መተግበሪያን ለመጫን፡
- ለአንድሮይድ ስልኮች:
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.eaglelionsystems.nedaj
- ለአፕል ስልኮች:
https://apps.apple.com/us/app/nedaj/id1639807926
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሞባይል ባንክ አገልግሎት መተግበሪያ በሚያዘምኑበት ጊዜ ይህን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ይመከራል፡፡
*************** *******
ደንበኞች የእጅ ስልካቸውን የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲኖረው በማድረግ ብቻ ካለምንም ተጨማሪ ሰው እገዛ የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት መተግበሪያቸውን ለማዘመን ይችላሉ፡፡
የባንኩን የሞባይል ባንክ አገልግሎት እና የሲቢኢ ብር መተግበሪያዎችን ለማዘመን እና ለማውረድ Play Store ወይም App Store ብቻ መጠቀም አለባቸው።
ደንበኞች የሞባይል ባንክ አገልግሎን ለማዘመን በስልክ ተደውሎ የሚሰጥ አገልግሎት እንደሌለ በማወቅ ተመሳሳይ መልእክቶች ሲደርሳቸው ወደ ባንኩ ቅርንጫፍ በመሄድ አሊያም ወደ 951 በመደወል ማሳወቅ ይኖርባቸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ !
https://youtu.be/2ss5SOrfmD8
#ሞባይልባንኪንግ #ደንበኞች #ማዘመን #መተግበሪያ
ለ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሞባይል ባንክ አገልግሎት ደንበኞች መተግበሪያችሁን ስለማዘመን ማሳሰቢያ ፡፡ ደንበኞች የሞባይል ባንክ አገልግሎን ለማዘመን በስልክ ተደውሎ የሚሰጥ አገልግሎት እንደሌለ ማወቅ አለባቸው፡፡ ደንበኞች የእጅ ስልካቸውን የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲኖረው በማድረ...
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን አምበል ሎዛ አበራ የአሜሪካው እግር ኳስ ክለብ በይፋ ተቀላቀለች፡፡
==================================
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ካስ ቡድን ስኬታማ ቆይታ የነበራት ሎዛ አበራ በዘርፉ በነበራት ተሳትፎና ጥረት ለስኬት መብቃቷ ለሌሎች ተምሳሌት መሆን የቻለች፤ የራሷንም አሻራ በማስቀመጥ በሃገራችን የሴቶች እግር ኳስ ታሪክ ስሟን በደማቅ ብዕር ማፃፍ የቻለች ብርቱ ተጫዋች ናት፡፡ በዚህም የክለቧ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስም እና የሃገሯን የኢትዮጵያን ስም በተደጋጋሚነት በአሸናፊነት ማስጠራት ችላለች፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የሴቶች እግር ኳስ ቡድን አምበል ሎዛ አበራ በአንድ ወቅት ከባንካችን የቴሌቪዥንና የሬድዮ ክፍል ጋር በነበራት ቆይታ የኢትዮጵያ እግር ኳስን ለማሳደግ ሁሉም ድርሻውን በጥምረት ሊወጣ ይገባል በማለት ወደፊት በዘርፉ ከሚሰሩ ዓለም ዓቀፍ ተቋማት ጋር ሃገሯን ወክላ በሚኖራት ተሳትፎ በእግር ኳሱ ዘርፍ የሚታየውን ችግር ለመቅረፍ የበኩሏን እንደምትወጣ ምኞቷን ተናግራ ነበር፡፡
በዚህም ምኞቷ በተለያዩ አገሮች በሚገኙ ክለቦች የመጫወት እድል አግኝታ በርካታ ተመክሮ እና ልምድ ያካበተች ተንካራ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ናት።
ሎዛ ከወራት በፊት ወደ አሜሪካ በማቅናት የልምምድና የሙከራ ጊዜያዋን ያሳለፈች ሲሆን የሙከራ ጊዜዋን በስኬት በማጠናቀቋ በአሜሪካ “USWL” ሊግ የሚሳተፈው ማራውደርስ እግርኳስ ክለብን በይፋ መቀላቀሏን ክለቡ ይፋ አድርጓል።
በእግር ኳስ ህይወቷ የከፍተኛ ጎል አስቆጣሪነት እና የምርጥ ተጫዋችነት ክብርን በተደጋጋሚ የተጎናፀፈችው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን አምበሏ ሎዛ አበራ በአሜሪካው ክለብ ማራውደርስ “USWL” ሊግ ስኬታማ እንዲሁንላት እንመኛለን፡፡
እንኳን ለ128ኛ ዓመት የአድዋ ድል በዓል
አደረሳችሁ!
#አድዋ #ድል #በዓል
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ !
Exchange Rate Applicable for, Friday, 01 March 2024.
For more information:
https://combanketh.et/en/exchange-rate
ጁምዓ ሙባረክ!
ለሐጅ መንገደኞች ልዩ መስተንግዶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
*************
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ም/ቤት ጋር በጋራ በመሆን ለሐጅ መንገደኞች የቅድመ ጉዞ ሂደቱን የተቀላጠፈ ለማድረግ ፤ ልዩ መስተንግዶ በሁሉም ቅርንጫፎቻችን እየሰጠን እንገኛለን፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ !
Exchange Rate Applicable for, Thursday, 29 February 2024.
For more information:
https://combanketh.et/en/exchange-rate
የትም የትም ሳይሄዱ ክፍያዎን
በሲቢኢ ብር ባሉበት ይክፈሉ!
ከ260 በላይ ተቋማት ጋር ትስስር ፈጥረናል!
*************
#ሲቢኢ ብር #ክፍያ #ተቋማት
የሲቢኢ ብር መተግበሪያን ለማውረድ፡
• ለአንድሮይድ ስልኮች፡ https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr
• ለአፕል ስልኮች፡ https://apps.apple.com/us/app/cbebirr/id1600841787
Exchange Rate Applicable for, Wednesday, 28 February 2024.
For more information:
https://combanketh.et/en/exchange-rate
#ዜና
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰራተኞች ማኅበር የባንኩን ራዕይ እና ስትራቴጂዎች ለማስፈጸምና ሰላማዊ የሥራ ኢንዱስትሪ እንዲኖር አበክሮ መሥራት እንዳለበት ተገለጸ፡፡
****************************
ከተመሰረተ 55 ዓመታትን ያሰቆጠረው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማኀበር ከምሥረታው ጀምሮ የኢንዱስትሪው የተረጋጋ ሰላማዊ እንዲሆን የራሱን እገዛ አድርጎል፡፡
https://youtu.be/iolVcNDMCS8
#ሠራተኞች ማኀበር #ሰራተኛ #ማኅበር #ሰላማዊ
International Competitive
***********
Commercial Bank of Ethiopia (CBE) Request for expression of interest LEASING AND PROPORTY MANAGENENT CONSULTANCY SERVICE FIRMS SELECTION.
Leasing and property Management Consultancy service of the CBE New Headquarter Building. Bid Number 101/2023/24.
Interested bidders can get the full information on our website using the following link: https://combanketh.et/cbeapi/uploads/Consultancy_service_of_the_CBE_New_Headquarter_a228b2b91c.pdf
Exchange Rate Applicable for, Tuesday, 27 February 2024.
For more information:
https://combanketh.et/en/exchange-rate
ካርድዎን ሳያስገቡ፤ ገንዘብዎን ያውጡ!
***
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ካርድዎን ኤቲኤም ማሽን ውስጥ ሳያስገቡ በማስጠጋት ብቻ
የይለፍ ቁጥርዎን አስገብተው ገንዘብ ማውጣት ይችላሉ፡፡
የያዙት ካርድ እና ATM ማሽኑ ያለንክኪ እንደሚሠሩ የሚያሳየውን የሞገድ ምልክት (የዋይፋይ ምልክት) ልብ ይበሉ፡፡
#ዜና
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የውጭ ምንዛሪ የሚያስፈልጋቸው አገልግሎቶችን በማገዝ አበረታች ውጤት ማስመዝገቡ ተገለጸ፡፡
***************************
ባንኩ ባለፉት 6 ወራት ለተለያዩ ዘርፎች ያቀረበው የውጭ ምንዛሪ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ13.8 በመቶ ብልጫ አሳይቷል፡፡
የቀረበው የውጭ ምንዛሬ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ላልሆኑ የአገልግሎት ዘርፎች ውሏል፡፡
#የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ #የውጭ ምንዛሬ #አገልግሎቶች
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የውጭ ምንዛሪ የሚያስፈልጋቸው አገልግሎቶችን በማገዝ አበረታች ውጤት ማስመዝገቡ ተገለጸ፡፡ ባንኩ ባለፉት 6 ወራት ለተለያዩ ዘርፎች ያቀረበው የውጭ ምንዛሪ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ13.8 በመቶ ብልጫ አሳይቷል፡፡ የቀረበው የውጭ ምንዛሬ መንግስታዊ እና መንግ....
Exchange Rate Applicable for, Monday, 26 February 2024.
For more information:
https://combanketh.et/en/exchange-rate
በሲቢኢ ኑር አገልግሎት ላይ የተደረጉ የአሠራር ማሻሻያዎች የሙስሊሙን ማህበረሰብ በከፍተኛ ደረጃ ተጠቃሚ ማድረግ መቻላቸውን የኢ.ን.ባ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ገለፁ፡፡
የሲቢኢ ኑር 10ኛ አመት ክብረ-በዓል የማጠቃለያ ፕሮግራም በዛሬው ዕለት ባበንኩ ዋና መሥሪያ ቤት በልዩ ልዩ መርሃ-ግብሮች ተከናውኗል፡፡
********************************************************
በመርሃ- ግብሩ ላይ የኢ.ን.ባ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ እንደተናገሩት ባንኩ ከአስር ዓመት በፊት ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት መስጠት የጀመረው በወለድ ምክንያት ከባንክ የራቀውን የህብረተሰብ ክፍል ተጠቃሚ ለማድረግ ነው ብለዋል፡፡
እንደ አቶ አቤ ገለፃ በተለይ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የፋይናንስ ዘርፉ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ እምርታ በማሳየቱና መንግስትም ዘመኑን የዋጀ ጠንካራ የማሻሻያ እርምጃዎችን መውሰዱ ዘርፉን ወደ ተሻለ ምዕራፍ አሸጋግሯል ብለዋል፡፡
መንግስት ስራ ላይ ያዋላቸውን የአሰራር ማሻሻያዎች ተከትሎ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክም ይሰጥ በነበረው ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግት ላይ የመዋቅር፣ የአሰራር እና የአገልግሎት አሰጣጥ ለውጦችን አድርጓል ያሉት አቶ አቤ እነዚህ የአሠራር ማሻሻያዎችና ለውጦችም የሙስሊሙን ህብረተሰብ በከፍተኛ ደረጃ ተጠቃሚ ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡
ባንኩ ባደረጋቸው ማሻሻያዎች የዛሬ አስር ዓመት በ23 ቅርንጫፎች ብቻ ይሰጥ የነበረውን ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት አሁን ላይ በመላው ሀገሪቱ ከ1ሺ 939 ማድረስ መቻሉን የጠቆሙት አቶ አቤ ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ብቻ የሚሰጡ ቅርንጫፎችንም 156 ማድረስ ችሏል ብለዋል፡፡
እንደ ፕሬዚዳንቱ ማብራሪያ ሲቢኢ ኑር የተጠቃሚ ደንበኞቹን ዕድሜ፣ ጾታ እና ፍላጎት መሠረት ያደረጉ ከ40 በላይ የሚሆኑ የተለያዩ የተቀማጭ ሒሳብ አገልግሎቶችን በማቅረብ፣ የደንበኞቹን ቁጥር ከ6 ነጥብ 8 ሚሊዮን በላይ አድርሷል፡፡ ከሲቢኢ ኑር ደንበኞች የተሰበሰበው የተቀማጭ ገንዘብ መጠንም ከ107 ቢሊዮን ብር በላይ ደርሷል ያሉት አቶ አቤ፤ 34 ቢሊዮን ብር ደግሞ ፋይናንስ ተደርጓል ብለዋል።
ሲቢኢ ኑር ባለፉት አስር ዓመታት በርካታ ውጣ ውረዶችን አልፎ አስረኛውን ዓመት በደመቀ መልኩ ማክበር በመቻሉ ሁሉንም የባለድርሻ አካላት እንኳን ደስ ያላችሁ ያሉት አቶ አቤ በቀጣይም በአጋርነታቸው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የሲቢኢ ኑር10ኛ አመት ክብረ-በዓል ባለፉት ሦስት ወራት በልዩ ልዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብሮች መከበሩን ያስታወሱት የሲቢኢ ኑር ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ኑሪ ሁሴን በበኩላቸው መርሃ- ግብሮቹ ስኬታማ ነበሩ ብለዋል፡፡
የሲቢኢ ኑር አገልግሎትን ስኬታማ ምዕራፎች በማስተዋወቅ የተሰሩ አበይት ተግባራትን ያብራሩት አቶ ኑሪ፤ ቀጣዩን የተስፋ ምዕራፍ በጋራ ለመወጣት ሁሉም የባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው እንዲሰሩም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በመርሃግበሩ ላይ ለሲቢኢ ኑር ዕድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱ እና የሲቢኢ ኑር የሸሪዓ አማካሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሆነው ለመሩት ለዶ/ር ጀይላን ከድር እንዲሁም የሸሪዓ አማካሪ ኮሚቴ አባል በመሆን ላገለገሉት ለኡስታዝ አወል አብዱልዋሂብ አሸኛኘት ተደርጓል፡፡
የሲቢኢ ኑር አገልግሎት ዛሬ ካለበት እንዲደርስ አስተዋፅኦ ያበረከቱ ተቋማትና ግለሰቦችም ከዕለቱ የክብር እንግዳ ከብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥ ከአቶ ሰለሞን ደስታ እጅ እውቅናና ሽልማት ተቀብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአለማቀፉ የ9ኛ ኢስላሚክ ሪቴል ባንኪንግ ተሸላሚ ሆነ፡፡
==================================================
ሰሞኑን በሳውዲአረቢያ ጂዳ በተካሄደው የሽልማት ስነ-ሥርዓት ባንኩ ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት 2023 በሪቴል ኢስላሚክ ባንኪንግ በኢትዮጵያ ተስፋ የተጣለበት ባንክ ተብሎ ነው ሽልማት የተበረከተለት፡፡
ሽልማቱንም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሲቢኢ ኑር ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ኑሪ ሁሴን በስፍራው በመገኘት ተቀብለዋል፡፡ ከሽልማቱ በኋላ የሲቢኢ ኑር ም/ፕሬዚዳንት አቶ ኑሪ ሁሴን በተለይ ለባንኩ የሬዲዮና ቴሌቭዥን ክፍል እንደገለፁት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለዚህ ሽልማት የበቃው በሲቢኢ ኑር የባንክ አገልግሎት ባለፉት ዓመታት በፋይናንስ አፈፃፀም የኢስላሚክ ባንኪንግ አገልግሎትን ሳይሸራረፍ ተግባራዊ በማድረግ እንዲሁም ለሸሪዓ መርሆች ተግባራዊነት ላሳየው ቁርጠኝነት ተገዢ በመሆን ባስመዘገበው የላቀ አፈፃፀም ነው ብለዋል፡፡
ሽልማቱ በተለይም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሲቢኢ ኑር አገልግሎት የተመሰረተበትን 10ኛ ዓመት እያከበረ ባለበት ወቅት የተበረከተለት በመሆኑ ልዩ እንደሚያደርገው ገልፀው የተገኘው ውጤት ከባንኩ ጋር የሚሰሩ መላው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሲቢኢ ኑር ደንበኞች፣ የባንኩ ሠራተኞች፣ የማኔጅመንት አባላት፣ የቦርድ አመራሮችና የሸሪዓ አማካሪዎች ድምር የስራ ውጤት መሆኑንም ነው የገለፁት፡፡ እናም ሁሉንም አካላት እንኳን ደስ አላችሁ ያሉት አቶ ኑሪ አገልግሎቱን ከዚህ የበለጠ ለማሳደግ የሁሉም ወገን የጋራ ጥረት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡
የኢትዮጵያን ንግድ ባንክን በመወከል ሽልማቱን የተቀበሉትን የሲቢኢ ኑር ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ኑሪ ሁሴንም የኸንኑ ሽልማትም ለባንካችን ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ በዛሬው ዕለት በቢሮአቸው በመገኘት በክብር አበርክተዋል ።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ በበኩላቸው የሲቢኢ ኑር አገልግሎት ባለፉት 10 ዓመታት ላስመዘገበው ውጤት ሽልማት መሸለሙ ተገቢ መሆኑን ገልፀው የሲቢኢ ኑር የወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት በኢኮኖሚ ውስጥ ያለውን አስተዋፅኦ ለማጠናከርና እስካሁን የተፈጠረውን ግንዛቤ ወደተጨባጭ ተግባራዊ ለውጦች ለማሸጋገር ባንኩ የሚጠበቅበትን ሁሉ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከ 2 ዓመት በፊት ጅቡቲ በተካሄደው 12ኛ ዓለም ዓቀፍ የኢስላሚክ የፋይናንስ ሽልማት የክብር እንግዳ በመሆን በዘርፉ ኢትዮጵያ ላበረከተችው አስተዋፅኦ ሽልማት መቀበላቸው ይታወሳል፡፡
ከአጭበርባሪዎች ይጠንቀቁ !
*****************
ሰሞኑን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሞባይል ባንክ አገልግሎት መተግበሪያን ደንበኞች እንዲያዘምኑት ማሳሰቡ ይታወቃል፡፡ በዚህ አጋጣሚ አጭበርባሪዎች የባንኩን መተግበሪያ እናዘምናለን በማለት ስርቆት እየፈጸሙ ስለሆነ ደንበኞች ጥንቃቄ እንድታደርጉ እናሳስባለን፡፡
የባንኩን የሞባይል ባንክ አገልግሎት እና የሲቢኢ ብር መተግበሪያዎችን ለማዘመን እና ለማውረድ ከ Play Store ወይም App Store ብቻ በማውረድ እንዲጠቀሙ ለማሳሰብ እንወዳለን።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ !
ሲቢኢ ሪሕላ የቁጠባ ሂሳብ
==============
ደንበኞች በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገራት ሊያደርጉ ላሰቡት ጉብኝታዊ ጉዞ ወጪ መሸፈኛ ገንዘብ አስቀድመው መቆጠብ እንዲችሉ የተዘጋጀ የቁጠባ ሂሳብ ነው፡፡
የቁጠባ ሂሳቡ የተለያዩ ጥቅሞች ያስገኛል፡
• ቆጣቢዎች በሀገር ወስጥ ጉዟቸው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ዲጂታል የክፍያ አማራጮች ተጠቅመው ለአየር ትኬት፣ ለቱሪስት መዳረሻዎች መግቢያ፣ ለሆቴል አገልግሎት ለመሳሰሉት ክፍያ በሚፈፅሙበት ወቅት ተመላሽ ያገኛሉ፤
• ዳያስፖራዎች ወይም የውጭ ሀገር ዜጎች ሲቢኢ ቱሪስት ካርድን ሲጠቀሙ እስከ 7 በመቶ የሚደርስ ተመላሽ ያገኛሉ ፤
• ሌሎች ተጨማሪ ጥቅሞችንም ያስገኛል፡፡
ሲቢኢ ሪሕላ ወዲዓህ የቁጠባ ሂሳብ
**********
• ከብር 1000 ጀምሮ ይከፈታል፡፡
ሲቢኢ ሪሕላ ሙዳራባህ የቁጠባ ሂሳብ
*********
• ከብር 1500 ጀምሮ ይከፈታል፡፡
• አስቀማጮች ከትርፍ ላይ 67 በመቶ ከባንኩ ጋር ይጋራሉ፡፡
ሂሳቡን በአቅራቢያዎ በሚገኝ የሲቢኢ ኑር ቅርንጫፍ ወይም በማንኛውም የባንኩ ቅርንጫፎች ይክፈቱ፤ ለበለጠ መረጃ ወደ 951 ይደውሉ!
#ሲቢኢ ሪሕላ # ወዲዓህ #የቁጠባ #ሂሳብ
#ይቆጥቡ፤ #ይጓዙ!
Exchange Rate Applicable for, Friday, 23 February 2024.
For more information:
https://combanketh.et/en/exchange-rate
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኢንተርኔት ባንኪንግ አገልግሎት ይጠቀሙ፡፡
*******
ቀላል አማራጭ በሆነው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኢንተርኔት ባንኪንግ ይጠቀሙ፡፡
በኢንተርኔት ባንኪንግ አገልግሎት በማንኛውም ሰዓት፣ በየትኛውም ቦታ እና ሀገር ሆነው ግብሮን ይክፈሉ ፣ የአየር ትኬት ይቁረጡ፡፡
አገልግሎቱን ለመጠቀም የሚከተለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ፡- https://www.cbeib.com.et/ARCIB-4/servlet/BrowserServlet
#ኢንተርኔት ባንኪንግ #ግብር # ገንዘብ #ሰዓት #የአየር ትኬት
በኑር ስትመሩ
በሀላል ፈለግ ወደ ስኬት ታመራላችሁ!
****************
ለእሴትዎ ተጠንቅቀን የሸሪዓ መርሆዎችን አክብረን
እንደ ፍላጎታችሁ ልናገለግላችሁ ዛሬም ተዘጋጅተናል
ሲቢኢ ኑር የተሟላ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት!
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ !
#ሲቢኢ ኑር #ኑር #ሀላል # ስኬት
በኑር_ስትመሩ_በሀላል_ፈለግ_ወደ_ስኬት_ታመራላችሁ! ሲቢኢ_ኑር_የተሟላ_ከወለድ_ነፃ_የባንክ_ አገልግሎት! Copyright © CBE (Commercial Bank of Ethiopia)Follow us on:☞Facebook: https://www.facebook.com/combanketh/☞Twitter: https://www.twitter.com/combankethiopia☞Li...
Exchange Rate Applicable for, Thursday, 22 February 2024.
For more information:
https://combanketh.et/en/exchange-rate
ለተሻለ ነገ...
የትምህርት ቁጠባ!
**************
የትምህርት ቁጠባ ሂሳብ ደንበኞች በቁጠባቸው የነገ የከፍተኛ ትምህርት ወጪያቸውን ያለስጋት መሸፈን ያስችላቸዋል፡፡
የርስዎንም ሆነ የልጆችዎን የከፍተኛ ትምህርት ወጪ ለመሸፈን
የትምህርት ቁጠባ ሒሳብ ተጠቃሚ ይሁኑ!
#ትምህርት #ቁጠባ #ለተሻለ ነገ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታል አገልግሎት እና ከተለያዩ ተቋማት ጋር የፈጸመውን ስምምነት እና ፋይዳው አስመልክቶ ከባንኩ የሥራ ኃላፊ ጋር የተደረገ ቆይታ፡፡
***************** #የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቴሌቨዠን ፕሮግራም
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ ከ 10 ዓመት በላይ ሆኖታል፡፡ ሕብረተሰቡ የዲጂታል ባንክ አገልግሎትን ተጠቅሞ ወደ ባንክ መሄድ ሳይጠበቅበት እጁ ላይ በሚገኘው የዲጂታል አማራጮች ክፍያዎችን ቢፈጸም ጊዜውን እና ጉልበቱን ይቆጥባል ከሥርቆትም ይድናል፡፡
https://youtu.be/hp1x4fvVeOA
#የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ #የዲጂታል #ባንክ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታል ባንክ አገልግሎት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታል ባንክ አገልግሎት እና ከተለያዩ ተቋማት ጋር የፈጸመውን ስምምነት እና ፋይዳው አስመልክቶ ከባንኩ የሥራ ኃላፊ ጋር የተደረገ ቆይታ፡፡ የኢትዮጵያ ንግ.....
ፔይ ባንድ (Payband) ምንድነው?
**********
ፔይ ባንድ በእጅ ላይ የሚጠለቅ ንክኪ አልባ ክፍያን መፈጸሚያ ነው፡፡ ደንበኞች በፔይ ባንድ ክፍያን ለመፈጸም ወደ ሽያጭ መፈጸሚያ ማሽን (POS) እጃቸውን ጠጋ አድርገው በፍጥነት እንዲከፍሉ፤ ከአውቶማቲክ የክፍያ ማሽን (ኤቲኤም) ደግሞ ጠጋ በማድረግ ገንዘባቸውን ማውጣት የሚያስችላቸው ነው፡፡ በአጠቃላይ አጠቃቀሙ ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ፣ ደህንነቱ አስተማማኝ ንክኪ አልባ የክፍያ መፈጸሚያ ዘዴ ነው፡፡
Exchange Rate Applicable for, Wednesday, 21 February 2024.
For more information:
https://combanketh.et/en/exchange-rate
ሎያሊቲ ፕሮግራም ለታማኝ ደንበኞች የሚበረከት ሥጦታ፡፡
********* #የቴሌቨዠን ፕሮግራም
ውድድር በዛበት የንግድ ዓለም ደንበኞችን ለማፍራት እና ይዞ ለማቆየት ለደንበኞችን የሚበረከት ሥጦታ መስጠት እንደሚያስፈልግ በዘርፊ ጥናት ያደረጉ ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡
ባንክ ኦፍ አሜሪካ/ Bank of America/ ደንበኞቹን ለማበረታታት ከ20 ሺህ ዶላር እስከ 50 ሺህ ዶላር ተቀማጭ ሲኖራቸው የ ወርቅ ደረጃ ፤ 50ሺህ ዶላር እስከ 100 ሺህ ዶላር ተቀማጭ ያላቸው የ ፕላቲንየም ደረጃ፤ ከ100ሺህ ዶላር በላይ ተቀማጭ ያላቸውን ደግሞ ልዩ ፕላቲንየም ደንበኛ በማለት በደረጃ ለይቶ ማበረታቻ ይሰጣል፡፡
https://youtu.be/NO5SLtx2_MY
#ሎያሊቲ #ደንበኞች #ሥጦታ #እውቅና #ሽልማት
ጉርሻና ማበረታቻ ለታማኝ ደንበኞች!
ሎያሊቲ ፕሮግራም ለታማኝ ደንበኞች የሚበረከት ሥጦታ፡፡ ባንክ ኦፍ አሜሪካን ለደንበኞቹን ለማበረታታት ከ20 ሺህ ዶላር እስከ 50 ሺህ ዶላር -ተቀማጭ ሲኖራቸው የ ወርቅ ደረጃ ፤50ሺህ ዶላር እስከ 100 ሺህ ዶላር ተቀማጭ ያላቸው የ ፕላቲንየም ደረጃ፤.....
Click here to claim your Sponsored Listing.
Videos (show all)
Telephone
Website
Address
Addis Ababa
WARYT BUILDING
Addis Ababa
WARYT Mulutila International PLC, IN ETHIOPIA is a company established in 1989 by the members of the
Adiss Ababa
Addis Ababa
Where innovation meets legacy, Girum Interior Designs & Furnishings creates timeless interiors
Namibia Street
Addis Ababa
The #1 lifestyle brand empire of Abyssinia. Living and dreaming in color. We provide a world of colors and comfort.
Addis Ababa
Manufacturing custom-made sofa, interior furniture and import furnitures
Summit
Addis Ababa
ቡሎ ፈርኒቸር የትኛውንም የእንጨት ስራ በአስተማማኝ ጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ ያቀርብሎታል : ኪችን ካቢኔት ፣ ቁም ሳጥን ፣ በሮች ፣ አልጋ ፣ ሶፋ
Century Mall, Gurd Shola
Addis Ababa, 1000
SNS Furniture Your home for stylish affordable furniture. Let’s create your dream home together.
Gerji Mebratyl
Addis Ababa
We are Designing and constructing a very modern and classic interior designs & also the construction