NIB International BANK S.C
the bank that strives to stimulate growth! Nib International Bank (NIB) was established on 26 May 1999 under license no.
LBB/007/99 in accordance with the Commercial Code of Ethiopia and the Proclamation for Licensing and Supervision of Banking Business Proclamation no. 84/1994 with the paid up Capital of birr 27.6 million and authorized capital of Birr 150 million by 717 Shareholders. The Bank commenced the operation in 28 October 1999 by 27 employees. Currently, the authorized and paid up Capital reached birr 2.0
Choose and do what’s right for you.
Use NIB ATM cards to ease your life hustles.
የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ አ/ማ ዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምልመላና አስመራጭ ኮሚቴ ከሰኔ 15 ቀን 2012 ዓ.ም. እስከ መስከረም 12 ቀን 2013 ዓ.ም. ድረስ የዳይሬክተሮች ቦርድ እጩ አባላትን ጥቆማ ይቀበላል፡፡
በመሆኑም የባንኩ ባለአክሲዮኖች ለባንኩ የላቀ ውጤት ለማበርከት ብቃቱ ያላቸውን በባንክ ሥራ አዋጅ ቁጥር 592/2008 እና 1159/2019 /የተሻሻለው/ በብሔራዊ ባንክ መመሪያ SBB/70/2019 እና SBB/71/2019 ላይ የተዘረዘሩትን የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ዕጩ የቦርድ አባላትን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ብቻ እንድትጠቁሙ ጥሪ ያቀርባል፡፡
ለዳይሬክተሮች ቦርድ አባልነት የሚያስፈልጉ መመዘኛዎች
የባንኩ ባለአክሲዮን የሆነ፣
ቢያንስ የመጀመሪያ ዲግሪ ወይም በከፍተኛ ትምህርት ተቋም ዕውቅና ያለው ተመጣጣኝ ትምህርት ደረጃ ያጠናቀቀ፣
ዕድሜው 30 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆነ፣
በባንኪንግ፣ ፋይናንስ፣ አካውንቲንግ፣ ማኔጅመንት፣ ኢኮኖሚክስ፣ ህግ፣ ቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን፣ ኢንቨስትመንት ማኔጅመንት፣ ኦዲቲንግ፣ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የትምህርት ዝግጅትና አግባብነት ያለው የሙያ ልምድ ያለው ቢሆን ይመረጣል፣
በሌላ የፋይናንስ ድርጅት የዳይሬክተሮች አባል ወይም የማንኛውም ባንክ ሠራተኛ ያልሆነ፣
ሀቀኛ፣ ታማኝ፣ ጠንቃቃ እና መልካም ስብዕና እና ዝና ያለው በተለይም በማጭበርበር፣ እምነት በማጉደል፣ ትክክለኛ ያልሆነ የሂሳብ መግለጫ በማቅረብና በመሳሰሉት ተከሶ በፍርድ ቤት የጥፋተኝነት ውሳኔ ተሰጥቶበት የማያውቅ፣
በራሱ ወይም ዳይሬክተር፣ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወይም የበላይ ኃላፊ በመሆን በሚመራው ድርጅት ላይ የመክሰር ክስ ያልቀረበበት ወይም የኪሳራ ውሳኔ ያልተሰጠበት፣
በኪሳራ ምክንያት ንብረቱ ለዕዳ ማቻቻያ ያልዋለበት፣
የባንክ ብድር ባለመክፈሉ ምክንያት ንብረቱ በሐራጅ ያልተሸጠ፣ ተከሶ ያልተፈረደበት ወይም የቦርድ ዳይሬክተር፣ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወይም የበላይ ኃላፊ በመሆን የሚመራው ድርጅት ከገንዘብ ተቋማት የተበደረውን ገንዘብ ባለመክፈሉ ብድሩ ወደ ጤናማ ያልሆነ የብድር ደረጃ ያልዞረበት ወይም ያልገባበት፣
በቂ ስንቅ/ገንዘብ ሳይኖር ቼክ ሰጥቶ ሂሳቡ ያልተዘጋበት፣
ታክስ እና ግብር ባለመክፈል ተከሶ ጥፋተኛ ያልተባለ፡፡
ማሳሰቢያ፡-
በተባዕታይ ጾታ የተገለፀው ለአንስታይ ጾታም ያገለግላል፣
መስፈርቱን የሚያሟሉ ሴት ዕጩዎች ይበረታታሉ፣
ጥቆማው በውክልና የቀረበ ከሆነ ውክልናው ጥቆማውን ለማቅረብ የሚያስችል ሆኖ የውክልና ፎቶ ኮፒው ከመጠቆሚያው ቅፅ ጋር ተያይዞ መቅረብ አለበት፣
ጠቋሚው ባለአክሲዮን ግለሰብ/ማህበር ወይም ድርጅት የተጠቋሚውን ፈቃደኝነት አስቀድሞ ማረጋገጥ አለበት፣
የመጠቆሚያው ቅፅ የኮሚቴው ጽ/ቤት ከሚገኝበት 4 ኪሎ በቱሪስት ሆቴል እና ቶታል ነዳጅ ማደያ መካከል በሚገኘው የባንኩ አዲሱ ህንፃ 4ኛ ፎቅ፣ በባንኩ ቅርንጫፎች ወይም ከባንኩ ድረ-ገፅ www.nibbanksc.com ማግኘት ይቻላል፣
ለጥያቄና ማብራሪያ በኮሚቴው ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ ወይም በኮሚቴው ጽ/ቤት ስልክ ቁጥር +251111265427 ወይም +251111265634 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፣
የመጠቆሚያ ቅፁ በአግባቡ ተሞልቶና ተፈርሞበት ማህበር/ድርጅት ከሆነ ደግሞ ማህተም ተደርጎበት አራት ኪሎ በሚገኘዉ የባንኩ ህንጻ 4ኛ ፎቅ ላይ ባለዉ የአስመራጭ ኮሚቴ ጽ/ቤት፤ በባንኩ ሁሉም ቅርንጫፎች ወይም በኮሚቴው የኢሜል አድራሻ [email protected] ወይም በባንኩ ፖስታ ሳጥን ቁጥር 2439 መላክ ይቻላል፤
የመጠቆሚያ ቅፁ መመለሻ የመጨረሻ ቀን መስከረም 12 ቀን 2013 ዓ.ም. ነው፣
ከመስከረም 12 ቀን 2013 ዓ.ም. በኋላ የሚቀርቡም ሆነ የሚደርሱ ጥቆማዎች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
የዕጩ ቦርድ ጥቆማ ቅፅ
የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ አ/ማህበር
የዳይሬክተሮች ቦርድ ምልመላና አስመራጭ ኮሚቴ
https://www.nibbanksc.com/news
በኢትዮጵያ የግል ባንኮች ታሪክ ቀደምት አሻራቸውን ካሳረፉት መካከል አንዱ የሆነው ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ፣ ከምስረታው ጀምሮ ለተከታታይ ሃያ ዓመታት የትርፍ መጠኑን እያሳደገ መጥቶ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት (እ.አ.አ 2019/20) ከታክስና ከተለያዩ ቅንስናሾች በፊት ከ1.4 ቢሊዮን ብር በላይ በማትረፍ በሀገሪቱ በትርፍ ቀዳሚ ከሚባሉ ባንኮች አንዱ መሆኑን በድጋሚ አረጋግጧል፡፡
በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በአገርና በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተው የኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ በፋይናንስ ኢንዱስትሪው ላይ ያሳደረውን ተግዳሮት ተቋቁሞ ይህንን ትልቅ ትርፍ ለማስመዝገብ ችሏል፡፡ የተመዘገበው የትርፍ መጠን ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በብር 378.3 ሚሊዮን ወይም 36.9 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡ በቀጣይም ከዚህ የተሻለ አመርቂ ትርፍ ለማስመዝገብ ተግቶ እንደሚሠራ ከባንኩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ከባንኩ በተገኘው ግርድፍ የሂሣብ መረጃ መሠረት የባንኩ ጠቅላላ ተቀማጭ ገንዘብ 33.2 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን ከአምናው 27.6 ቢሊዮን ብር ጋር ሲነጻጸር የ21.5 በመቶ ዕድገት ለማሳካት ተችሏል፡፡ የባንኩ አጠቃላይ ሐብት 42 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን ከአምናው 33.5 ቢሊዮን ብር ጋር ሲነጻጸር የ25.1 በመቶ ብልጫ አሳይቷል፡፡ የተከፈለ ካፒታል ከብር 2.6 ቢሊዮን ወደ ብር 3.4 ቢሊዮን ያደገ ሲሆን አጠቃላይ ካፒታልና መጠባበቂያም ከብር 4.4 ቢሊዮን ወደ ብር 5.8 ቢሊዮን በማሳደግ መሪ ከሆኑት የግል ባንኮች መካከል አንዱ የመሆን ዕቅዱን ለማሳካት ጥረቱን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ ተደራሽነቱን በማስፋትና የቅርንጫፎቹን ቁጥር ከሶስት መቶ በላይ እንዲሁም የደንበኞቹን ቁጥር ከአንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሺህ በላይ አድርሷል፡፡ ለበርካታ ደንበኞችም የፋይናንስ ችግራቸውን በመቅረፍ በአገሪቱ የኢንቨስትመንት ተሳትፎ ላይ አዎንታዊ ሚናውን በመጫወት ለዕድገት ጉልህ ድርሻ በማበርከት ላይ ይገኛል፡፡ ባንኩ፣ በአገሪቱ የባንክ ኢንዱስትሪ የተለያዩ የቁጠባ አይነቶችን በማስተዋዋቅ በርካታ ደንበኞችን አፍርቷል፡፡
ባንካችን፣ የኮረና ቫይረስን ለመከላከል በሀገር ደረጃ እና በአዲስ አበባ በሁሉም ክፍለ ከተሞች በኩል ለሚደረገው ጥረት እንዲያግዝ ከብር 5.1 ሚሊዮን በላይ የለገሰ ሲሆን ለባንኩ ተበዳሪዎችና ሌሎች ደንበኞች የወለድ ምጣኔን፣ እንዲሁም የተለያዩ ክፍያዎችን በመቀነስና አንዳንዶቹንም በመሰረዝ ከእነዚህ በአጠቃላይ ሊያገኝ ይችል የነበረውን ከብር 113 ሚሊዮን በላይ ገቢ በመተው ሀገራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት ረገድ በታላቅ ደረጃ አጋርነቱን አሳይቷል፡፡
አካላዊ መቀራረብ እንዳይኖር ደንበኞች በባንኩ የቴክኖሎጂ መሣሪያዎች በኤቲኤም፣ ፖስ፣ ሞባይልና ኢንተርኔት ባንኪንግ እንዲጠቀሙ የተመቻቸ ሲሆን ይህንንም ለማበረታታት የኤቲኤም የአገልግሎት ክፍያ ነጻ እንዲሆን ከማድረጉም ባሻገር በዚሁ ቴክኖሎጂ በመጠቀም እስከ ብር 10,000.00 ማውጣት እንዲሁም በሞባይል እስከ ብር 30,000.00፣ በኢንተርኔት ለመደበኛ ደንበኞች ብር 100,000.00 እና ለኮርፖሬት ደንበኞች ብር 500,000.00 ማስተላለፍ እንዲችሉ ተደርጓል፡፡
ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን ከመወጣት አንጻር ለሸገር ማስዋቢያ ፕሮጀክት ብር 10 ሚሊዮን፣ ለአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች የትምህርት መሣሪያ ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉ ይታወሳል፡፡
ባንኩ “ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!” የሚለውን መሪ ቃል ያነገበ የ5 ዓመት ስትራቴጂክ ፕላን አዘጋጅቶ በትግበራ ላይ የሚገኝ ሲሆን በዚህም የኮር ባንኪንግ ስርአቱን እጅግ ዘመናዊ በሆነው የT24 Version 2020 ቴክኖሎጂ፣ Tier 3 data center እና ሌሎች ቴክኖሎጂዎችንም በመጠቀም ለደንበኞች የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅቱን እያጠናቀቀ ይገኛል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ለመዲናችን አዲስ አበባ ብሎም ለሀገራችን የገጽታ ግንባታ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሊያደርግ የሚችለውን ከፍታው ባለ 4B+G+M+32 የሆነው የዋናው መሥሪያ ቤት ሕንጻ በቅርቡ ለመጨረስ እየተዘጋጀ ሲሆን፤ ለአራት ኪሎ አካባቢ ውበት ያጎናጸፈው ባለ 2B+G+7 የሆነው የአራት ኪሎ ሕንጻውን በማጠናቀቅና በዚሁ ሕንጻ ላይ የፕሪሚየም ቅርንጫፉን በመክፈት ደንበኞቹን በላቀ ደረጃና ክብር ለማገልገል ተግቶ በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡
ባንኩ የዕድገት ጉዞውን በፈጣን ሁኔታ እያከናወነ ሲሆን ለዚህ ውጤት እንዲበቃ ላደረጉት ለባንኩ የቦርድ አመራሮች፣ ማኔጅመንትና መላው ሠራተኞች እንዲሁም ለውድ ደንበኞቹ ከፍተኛ ምስጋና እያቀረበ፤ ወደፊትም ከዚህ በበለጠ በመሥራት ለሀገርና ለወገን አኩሪ ተግባር ለመፈጸም እየተዘጋጀ መሆኑን ገልጿል፡፡
ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ
ይሠሯል ከልብ እንደ ንብ!
https://www.nibbanksc.com/news/
News – Nib International Bank NIB has launched modern electronic payment products using ATM & POS machines. Our ATMs are located at convenient places for our NIB CARD holders. With our ATMs, you can make
መልካም በዓል!
https://www.youtube.com/watch?v=obvL4X4juSw
Nib International Bank - Arefa Advert Happy Eid Al-Adha holiday!
እንኳን ደስ አለን!
Nib International Bank has opened a new Premium Branch at its 4 Kilo Building for the first time today June 26, 2020.
!
Use these E-channel transaction methods that will at least decrease your chance of being infected by Coronavirus!
Mobile banking - Internet Banking - ATMs - POS Machines!
photo credit
Nib InternationalBank S.C
እንኳን ለ ኢድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
መልካም በዓል!
ሁሌም ምርጫችሁ ስላደረጋችሁን እናመሰግናለን
Internet Banking
- Anywhere, anytime, anyplace
- Your transaction is available at the tip of your fingers
- For regular customers, up to ETB 100,000.00 – for
corporate customers, available up to ETB 500,000.00
for more inf www.nibbanksc.com
We are opening soon to provide you with comprehensive premium banking services around 4 Kilo at our building - a convenient & most accessible venue.
Protect yourself
Protect your family
Protect your community
Protect your country
# staysafe
Today's Currency exchange rate
Currency Buying Selling
USD 28.8459 29.4228
EURO 32.4776 33.1272
POUND 36.4583 37.1875
for more information please visit www.nibbanksc.com/
we always care for your satisfaction, We focus every day on the quality of our products and services to make them match your needs and requirements.
Thank you for choosing NIB!
the bank that strives to stimulate growth!
Nib InternationalBank S.C
እንኳን ለ1440ኛው ኢድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
መልካም በዓል!
ሁሌም ምርጫችሁ ስላደረጋችሁን እናመሰግናለን
የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ከፍተኛ የሥራ አመራሮች ሹመት ጸደቀ
በቅርቡ በንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዲሬክተሮች ቦርድ ለከፍተኛ ስራ አመራርነት ማለትም ለፕሬዚደንትነትና ለም/ል ፕሬዚደንትነት ታጭተው ሹመታቸው እንዲጸድቅ ለብሔራዊ ባንክ መቅረቡ ይታወቃል፡፡
በዚሁ መሰረት ብሔራዊ ባንክ በቁጥር ፋኢሱ/ባሱዳ/244/19 በቀን መጋቢት 03/2011 ዓ.ም ለባንካችን በላከው ደብዳቤ መሠረት አቶ ገነነ ሩጋ የባንኩ ፕሬዚደንት፣ አቶ ልዑልሰገድ ንጉሤ - የስትራቴጂና ትራንስፎርሜሽን ዘርፍ ም/ፕሬዚደንት፣ አቶ ሰይፉ አገንዳ - የባንኪንግ ኦፕሬሽንስ ዘርፍ ም/ፕሬዚደንት እና አቶ ከድር በደዊ - የከስተመርስ ቻናልስ ም/ፕሬዚደንት መሆናቸውን አጽድቋል፡፡
ቀድም ሲል የባንኩ ሪሶርስና ፋሲሊቲስ ዘርፍ ም/ፕሬዚደንት የነበሩት አቶ ሰለሞን ጎሽሜ - የዚሁ ዘርፍ ኃላፊ ሆነው እንዲቀጥሉ የባንኩ ዲሬክተሮች ቦርድ መወሰኑ የሚታወቅ ነው፡፡
Nib international bank assigned the new president
Mr. Genene Ruga.
Click here to claim your Sponsored Listing.
Videos (show all)
Contact the business
Telephone
Website
Address
Addis Ababa
2439