ዳን ዘኢትዮጵያ

ዳን ዘኢትዮጵያ

Social, Cultural, and Religious

22/11/2023

ቅዱስ ሚካኤል ምስክሬ ነው ኢትዮጵያ ታሸንፋለች✊✊✊❤
የጌዲዮን ችቦዋ ፋኒት ታቸንፋለች✊✊✊❤

*****

ኦ****ሮ*****ማ*****ይ***❤

22/11/2023

ቅዱስ ሚካኤል አባቴ...ሥምህ ብቻውን አለኝታዬ መከታዬ ነው!!!

ቅዱስ ሚካኤል ሆይ ኢትዮጵያን ጠብቅልን እባክህን 🤲🤲🤲

22/11/2023

ህዳር ፲፪❤
**********

"ኦ ሚካኤል፣ ኦ ሚካኤል፣ ኦ መተንብል፣ ካህነ አርያም ትሰመይ ቢጸ ሱራፌል፣ ዘእምርዑሳን ርዑስ ወዘእምልዑላን ልዑል፣ ጊዜ ጸዋዕኩከ ቅረበኒ በምሕረት ወሣህል።" ❤❤❤.....ይሄንን ብሎ ቅዱስ ሚካኤል ምሽግ አድርጎ መኖር እንጂ....🤲🤲🤲አሜን🤲🤲🤲

21/11/2023

"ኦ ሚካኤል፣ ኦ ሚካኤል፣ ኦ መተንብል፣ ካህነ አርያም ትሰመይ ቢጸ ሱራፌል፣ ዘእምርዑሳን ርዑስ ወዘእምልዑላን ልዑል፣ ጊዜ ጸዋዕኩከ ቅረበኒ በምሕረት ወሣህል፡፡"

"አማላጃችን ሚካኤል ሆይ ፈጥኖ ደራሻችን ሚካኤል ሆይ የጌታን ዙፋን ከሚያጥኑ ሱራፌል ካህናት አንዱ ሰማያዊ ካህን አንተ ነህ እኮን። የሰማያውያን ሊቃነ መላእክት ሁሉ አንተ አለቃቸው ነህ እኮን። ይልቁንም የልዑላንም ልዑል አንተ ነህና በጠራሁህ ጊዜ ሁሉ በይቅርታና በቸርነት ድረስልኝ አትራቀኝ።"

መልክአ ሚካኤል

21/11/2023

ቅዱስ ሚካኤል ፈጥኖ ደረሰልኝ
ከሳሼን ረግጦ አዋረደልኝ.....❤❤❤

21/11/2023

መጽሐፍ በዚያ ዘመን ያለው የትኛውን ዘመን ይሆን?...እኛስ እንደዚህ ዘመን መከራ አስጨንቆን አያውቅምና...ለእኛስ የመከራ ዘመን ሆኖብናልና....እባክህን ቅዱስ ሚካኤል ሆይ ናና❤
እንኳን አደረሳቹህ🤲🤲🤲...አደረሰን 🤲

21/11/2023

LOVE OF THE PEOPLE Vs. LOVE OF $(USD)🙊🙊🙊

21/11/2023

“ብርሃንሽ መጥቶአልና፥ የእግዚአብሔርም ክብር ወጥቶልሻልና ተነሺ፥ አብሪ።”— ኢሳይያስ 60፥1

******
"ብርሃንካ መጺኡ፡ ክብሪ ኣምላኽውን ካባኻ ወጺኡ እዩ እሞ፡ ተንስእ፡ ብርሃን" - ኢሳይያስ 60፡1

*****

"Ifni kee dhufeera, ulfinni Waaqayyoos si keessaa ba'eera" - Isaayaas 60:1

******
"Arise, shine, for your light has come, and the glory of God has gone out from you." - Isaiah 60:1

*******

ኦ...ሮ...ማ...ይ...❤❤❤

20/11/2023

ይሁዳስ ጌታውን እጅግ ይወደው ነበረ❤😭
***********************************

እንዴት አላቹህ መልካም❤

*****

እኔ ግን ደጋግሜ ምንም የቤተ ክህነት ትምህርት የሌለኝ አይነ ስውር መሆኔን አምኜ....እንዴት የሚለውን...የሆነ ጊዜ...የሆነ ቦታ...ያነበብኩትን የማስታውሰውን ሀሳብ በድፍረት ላካፍላቹህ....ግን በልጅነት በሕፃንነት ድፍረት❤

*****

ይሁዳ አባቱ ነጋዴ ነበርና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ተሃምር ዕለት ዕለት ዕያየ...አብሮት ነበርና...የሮማውያን የቀኝ ገዢነትም ያናድደው ነበርና....ኢየሱስ ክርስቶስን አይሁዶች ችለው አይገሉትም ብሎ በማሰብ....እርሱም የእስራኤል ንጉሥ ሊሆን የአባቱን ቤት ከፍ አርጎ አገሩ እስራኤልን ነፃ ለማውጣት...አቅዶስ ቢሆን....እሺ ኸረ ፍፁም ይቅርታ የማያሰጥ ኃጢያት ሠርቷል...ጌታውን በሠላሳ ዲናር ሸጧል ብለን እንፍረድ እና እንቀጥል......

*****

ይሁዳ ጌታውን ለሞት አሳልፎ እንደሰጠና ጌታውም በእርሱ ምክንያት እንደሞተ ባየ ግዜ....እኔስ ከእንግዲህ ሰው ሆኜ ቆሜ ምድር የሚያስኬደኝ ምንም በጎ ሥራ የለኝ ብሎ.... ተስፋ ቆርጦ......

*****

እራሱን ሊሰቅል ቢል ሁለቴም ዛፏ ተሰብራ እምቢ ብትለው እርሱ የዛፏን እምቢታ እምቢ ብሎ...በሥስተኛው እራሱን ሰቅሎ ሞተ...አፄ ቴዎድሮስ አትልም...ፍቅሩን ጌታውን በረከቱን ተሃምራቱን፣ የእውሮች ዐይንን ማብራቱን፣...ሙታን ማስነሳቱን....ፍቅሩን ጌታውን አጥቶታል እና...ስለ አንድ ኃይማኖታቹህ ተጋደሉ ብሎ ፅፎ...በአንድ ይሁን በሁለት ዐረፍተነገር ብቻ ፅፎልን ሞተ....

*****

እና ይሁዳ ጌታውን ባይወደው ነውን?...አፄ ቴዎድሮስስ ኢትዮጵያን ባይወዳት ነውን?...እራሱን የሰዋለት!❤...የሰውላት❤

****

ይሁዳስ ኃይማኖቱን የት ዐይቷት ነው ተጋደሉላት የሚለነ❤

*****

ኦ...ሮ...ማ...ይ...❤❤❤

20/11/2023

ዘይትገርም😂
************

እኔ እራሴው ስሰርቅ ኖሬ አሁንም እየሰረኩ ነገም ለመስረቅ ጥልቅ ዕቅድ ኖሮኝ ሳበቃ...ይሁዳን ሌባ እያልኩ ስንቴ ፈረድኩበት....ኸረ የይሁዳ አምላክ ሆይ ይሁዳስ የአንተን ሥራ ለመስራት ብሎ ተሳስቶስ ቢሆን...ወይ ጉዴ....አይ ፍርጃዬ...ፈራጅነቴ❤❤❤

20/11/2023

ሰውን አትከተሉ...እግዚአብሔርን እንጂ...በቅዱሳኑ ቃል ኪዳን ታመኑ!.......ሰውማ ምን?......እኔ እራሴን አውቃለው እና ሰውን በፍጹም አልከተልም....ሰው የተሳሳተ ቢመስለኝም አልገረምም...እኔም ትሪሊዮን ጊዜ በኃጢያት ወድቄ በራሴ ተገርሚያለውና....ሰውስ ደካማ ሊሆን ይችላልና ተውት...ተውኝ...

*****

መቻል ግን ለዘለአለሙ የእግዚአብሔር ነውና...እግዚአብሔር ይችላል...ወላዲተ አምላክ ትችላለች...ቅዱስ ሚካኤል ይችላል....ቅዱስ ገብርኤልም በደንብ ይቻለዋል❤❤❤.....
✊✊✊✊✊✊✊✊✊✊✊✊✊✊✊✊✊✊

******

ኦ....ሮ...ማ...ይ...❤❤❤

20/11/2023

ኢትዮጵያ ሁል ጊዜ በምናቤ ውስጥ ልዩ ቦታ አላት እና ኢትዮጵያን የመጎብኘት ተስፋዬ እና ፍላጎቴ ከወደ ፈረንሳይ፣ እንግሊዝ እና አሜሪካ ካደረኩት ጉዞ የበለጠ በዕድሜ ዘመኔ ሁሉ ይስበኛል። ሁሌም ኢትዮጵያን ስጎበኝ የሚሰማኝ የራሴን ዘፍጥረት እየጎበኘሁ እንደሆነ ነው፣ አፍሪካዊ ያደረገኝን ነገር ከስር እንዳውቀው እረድቶኛልና...እኔንም አፍሪካዊ አድርጎኛል። ማንዴላዬ እኮ ነው❤

*****

Itoophiyaan yeroo hunda yaada koo keessatti bakka addaa kan qabdu yoo ta’u, imala gara Faransaay, Ingilizii fi Ameerikaa walitti qabame caalaa abdiin Itoophiyaa daawwachuu cimsee na hawwate. Hundee waan Afrikaa na taasise qotuudhaan, uumama mataa kootii daawwachaa akkan jiru natti dhaga’ame.❤❤❤

20/11/2023

"I HAVE A DREAM tooooo"✊
*****************************

The whole world has contributed all its best to break this poor nation called Ethiopia. , , America BACKUP THE MOST CORRUPTED AND KILER LEADERS IN AFRICA AND ALL OVER THE WORLD😂......

*****

WHY DOES ENGLAND AND America HATE ANCIENT POWER AND Civilization..while they categorize themselves as G7😂...
most developed?🙊🙊🙊

******

Sometimes i wonder so much, .....are we Ethiopians poor?......if so, why are we always stolen by rich nations and nationalities (eg. England, can you return back the covenant of Tewodros son ALEMAYEW body)...i know, i have heard your answer is no...NO...NO...NO...never..in the history OF England,

*****
...then why are you so cruel?....🕺🕺🕺..., don't you know i am human tooooo.......anyway....i am going to continuously asking you..... plus.....i am going to mary her anyways😂🙊🙊🙊MAGIC...RUDE(OV)

*****

Leave alone all the gold and diamond you are still stealing from us, Cross with gold and precious stone on it....etc....rich thief that robes from the poor (3rd world nations) 🙊🙊🙊🙊...🙊...G7😂

*****

Do you know what you always do, if you think it is enough for a regime of your collonized nation, you just blame that government and you want to change with the new one, EVERYTHING IS UNDER CONTROL OF YOURS, and then you wash your hand with water, as if you have done nothing for the death of Million Ethiopian civilian....

*****

E.g. What was the role of and and others for the death of Million Tigrayans...YOU WERE THE ONE THAT WAS PUSHING AND PULING THEM FOR SUCH A TRAGEDY IN THE History OF HUMANKIND.

*****

፦ washing your hands with water.... and continue your gamble on Ethiopian civilians life again....as if you are not the one that brought ABIYE AHMED to power....SHAME ON YOU✊

"What goes around comes around" JT

*****

I can see from here that all the civilian bloods are in your dirty hands....i wish you, to spend one of the hardest summer seasons of all time...in the history of human being....so that you know you are human toooo....I WISH YOU THAT WITH ALL MY HEART...
"HEARTLESS"...The Weeknd...wicked 😂

*****

😂😂😂
THE SHOCKING PART, YOU WANT US TO PERCEIVE YOUR IDEA AND GOT BLIND AND Believe AFRICAN are CURSED....

*****

NICE!...If you concluded that we Africans are cursed but the colonizers are one of the great favoured children of the creator, ......that does not make a sense.....or gives you a green light to drive your corrupted fruit called V8, on our body after you kill us while we stood on our two feets and alive, .......

corrupted African children...the blame goes to you toooo.....SHAME ON YOU!✊

******

IF CIVILIZED COUNTRY SEND THERE 'IDEA' & 'WEAPON' TO KILL CIVILIANS, it must be because they are not civilized as they said they did, ....... because the word Civilization drives from civilian rights and freedom, ....CIVILIANS✊

******

WHAT I AM WITNESSING ALL OVER THE WORLD, OF WHAT HAVE YOU DONE?...YOU HAVE BECOME HEARTLES SOCIETY....YOU ARE SO CARLESS ABOUT CIVILIAN LIFE...."THEY DON'T Really CARE ABOUT US"...Micheal Jackson.❤

*****

If i able to speak all i know my head and stomach will be empty, i rather not....BECAUSE YOU KNOW WHAT YOU HAVE DONE AFTERALL✊

good bye by the song called......

"After All" Cher and Peter Cetera😂🕺🕺🕺🕺🕺

*****

ኦ...ሮ...ማ...ይ....❤❤❤

20/11/2023

እግዚአብሔር የሰው ችግር የለበትም...
እንኳን ሕፃናትን ቀርቶ ድንጋይንም እንዲናገር ያደርጋል።✊

19/11/2023

በትዳራቸው ጸንተው (ሓማራና ኦሮሞ ተጋብተው)...ሲያበቁ...የልጅ ልጅ አይተው በኢትዮጵያዊነት አልደመቁም ወይ...ከሆነስ የታሉ...ከሌሉስ ውሸት ነው በሉኛ❤...ነው እውነት ይሆን አሉን❤

*****

Yoo bultii isaanii keessa hafan (Hamara fi Oromoon wal fuudhan)...yeroo xumuran...ilma ilma hin argine?

******

ኦ...ሮ...ማ...ይ...❤❤❤✊

19/11/2023

ነጋቲ ቡላ!❤...
*************

❤❤❤..........ፍ ቅ ር ያ ሸ ን ፋል..........❤❤❤

❤❤❤.........Jaalalli ni injifata.......❤❤❤

****🤲🤲🤲Galgala gaarii obboleewwan koo Oromoo...🤲🤲🤲..❤

*****

ኦ...ሮ...ማ....ይ...❤❤❤

19/11/2023

ወላሂ...ወላሂ ...ወላሂ...ከእንግዲህ ሁለተኛ ሓማራ አልሆንም......
እንደውም ኦሮሞ እስላም ነኝ...በቃ ተውኛ አይ❤✊

*****

Wolahi...Wolahi...Wolahi...kana booda Hamara lammaffaa hin ta'u......Dhugaa dubbachuuf ani Muslima Oromooti...❤✊

*****

welahī...welahī ...welahī...from now on i will never be AMHAR, please don't kill me🤲..... Just don't kill me from now on i am ISLAMIC OROMO RACE....just allow me to live the life of my creator have given me to live, please!......
❤✊....LIVE AND LET LIVE ...LOOOVVEEE❤

*****

ኦ...ሮ...ማ...ይ...❤✊

19/11/2023

እስቲ መልስልኝ አንተ ኃይማኖተኛ ሰው፣ በድንጋይ ከተቀረጸው የእግዚአብሔር የእጅ ሥራ ከሆነው ....ከሙሴ ከቃል ኪዳኑ ጽላት እና ከሰው..... ማን ይበልጥ በእግዚአብሔር ዘንድ ውድ ይመስልሃል?.....

******
....ሰው✊

********

እሺ.....ስንት ሚሊዮን ኢትዮጵያዊ የሥላሴ ሕንፃ ሲፈርስ እንዴት ብለህ ቻልከው...ካልቻልከውስ...ይህንን ወቀሳስ ምን ትችለው?❤

*****

ፋኖ!!❤....

*****

ኦ...ሮ...ማ...ይ...❤✊

19/11/2023

ይሄ ልጅ በቃ ለየለት ሓማራ ፋኖ ሆኗል አላቹህ መልካም❤
**********************************************
**********************************************
**********************************************

እኔ ኢትዮጵያን ለመውደድ እና ለማፍቀር ግዴታ ሓማራ ፋኖ ተብዬ መፈረጅ አለብኝ እንዴ?....የዘር ፍርጃ...የነገድ ፍርጃ....ሆ❤

*****

ቆይ አንቺ እንግሊዝ ስሚኝማ....ወላዲተ አምላክን አክብሮና ወዶ ሲያበቃ...አይደለም የሰው ዘርን የአዳምን...ይኖርስ ይሆን ወይ የሚጠላ...የሔዋንን ዘር??...???...ሔዋኒና❤❤❤

*****

እንግሊዝ ሙቺ ነው የምልሽ...I LOVE YOU VERY MUCH❤...

I am 100% sure you will say I LOVE YOU TOOO❤

*****

ኦ...ሮ...ማ...ይ..❤❤❤

19/11/2023

የዕልውና ትግል✊
***************

እኔ ብዙ አንቢቢያለው፤ ብዙ የህልውና ትግል ተራኪ ፊልሞችንም በፍቅር እከታተላለው...በተለይ የአልጄዚራ ዶክመንተሪዎች በጣም አድናቂ ነኝ...በተመስጦ!....ግና....ግና....ግና....እንደ ሓማራ...እንደ ፋኖ አይነት ታላቅ የዕልውና ተጋድሎ ዐይቼም ሰምቼም አላውቅም....አይ .....hi...አልጀዚራ አሁን የእውነት የሆነ የኢትዮጵያን ሕዝብ መከራና ሰቆቃ ዶክመንተሪ ፊልምህን ትሰራለህ ወይስ አትሰራም...ዋ!✊....❤❤❤

18/11/2023

You may watch me laughing in my whole day to day life, if i may act as if i forget it፤ but the fact on the ground tells me otherwise, do i have enough heart larger enough to swallow and forgive all of theseeee...&..that..❤

18/11/2023

❤ፀሐዬ❤
**********

ፀሐዬ..........ዲዲዲ....
ደመቀች .....ዲዲዲ...
ደመቀች!............
ብርሃኗን.....
ለእኛ ማለት ...
አዎ .....አወቀች.......አወቀች.....አዎ.... አወቀች....
ፀሐይ ብርሃን ፈንጥቃ ......ዲዲዲ
ከአድማስ ወደ እኛ መጥታ...ዲዲዲዲ..
ጊዜ...ዲዲዲዲ...
ጊዜ....ዲዲዲዲ...
ደመቀች በራች ፀሐይ...
ለእኛ ማለት አወቀች........

******
❤❤❤...ፀሐዬ...❤❤❤

******

ኦ....ሮ....ማ....ይ.....❤

18/11/2023

ወላዲተ አምላክ ምስክሬ ናት ኢትዮጵያ ታቸንፋለች✊✊✊

18/11/2023

"ኢሱ ጭሱ"....✊
************

ምንጭ ሳይጠቅስ ምናምን እንዳትሉ ምንጭ ልጥቀስ...❤

የአዲስ አበባ ወጣት ወዶዎት ያወጣልዎት ሥም ነው።....ለምን ቢሉ ሰው አክብረው ፍቅርን ምህረትን አብሮ መኖርን ..ሰላም..... ሰላም... ሰላም.. ...(እዚህ ጋር ያቺን የርህሶም ተ/ጊዮርጊስ...ሰላም...ሰላም ..ሰላም...የምትለዋን ኤርትራዊ ዘፈን ያዳምጡ።).......ስንቀጥል...ወዲ አፎሞ...ወደው ነውና...ከነበርዎ ታላቅነት ዝቅ ብለው መሸነፍዎ....ፍቅር የሚገዛው ሰው..ዛሬም አሁንም ታላቅ ክብር ቢገባው እንጂ ሌላ ምን?....ኢሱ ጭሱ✊

*****

ኦ....ሮ....ማ...ይ....❤

18/11/2023

አንዴ ውጪ አገር ሰላም ለማስከበር ሄጄ!✊
********************************

የት አላቹህ....ኮሪያ...በዘመቻ መምሪያ ማሰልጠኛ ክፍል ኃላፊው...አንድ ፈረንጅ ግድንግድ ጄኔራል...የሌሎች አገራትን ወዶ ዘማቾችን ሲያመናጭቅ ይውልና...እኔ ጋር ሲደርስ አናቱን ዝቅ አድርጎ አክብሮቱን ይገልጻል።

*****

በኋላ ይሄ ድርጊቱ ገርሞኝ፦ "why are you mistreat the others but not me, why?"..."ሌላውን ሁሉ አመናጭቀህ ስታበቃ ለምን እኔን ታከብረኛለህ?"...ብዬ ጠየኩት....and then he replied back..."because you are Ethiopian, you know how to fight until death for your right...stil i have a strong believe that you have the blood of your forefathers...may be i need something to learn from you"...ብሎ መለሰልኝ...እና የምኒልክ ልጆች ናቹህና...እኛ ከእናንተ ስለ ጀግንነት እንማራለን እንጂ እኛ ጀግና መስለን ኢትዮጵያን ልናስተምራት አንችልም...እያለ ውይይታችን ቀጠለ...

*****

ግርም ድንቅ ያለኝ ግን ......አሜሪካ ወታደራዊ ማሰልጠኛቸው ውስጥ..... የምኒልክ የዓድዋ ዘመቻ የክተት አዋጅ..............እንደ አንድ ትልቅ ማስተማሪያ...ትንታኔ የሚሰጥበትና...የጦር መኮነኖችም የሚማሩበት እንደሆነ እና እርሱም ጠንቅቆ እንዳጠናው ሲነግረኝ...ልቤን ሞቅ ሞቅ አለኝ!✊✊✊

*****

ኦ...ሮ...ማ...ይ...✊❤

18/11/2023

ቱርክዬ .......ያኔ መሬት ስትከዳሽ....... እኛ ኢትዮጵያውያን ግን ሳንከዳሽ ......ለቅሶሽን አብረን ባላቀስንሽ...... ድሮን ነው ወይ ለኢትዮጵያውያን ዕንባ የአጸፋው መልስሽ። አይ ቱርክዬ.... ኢትዮጵያስ ስለአንቺ ጭምር ፈጣሪዋን ምህረቱን እንደምትማጸን .....ግን...ግን....
ታውቂ ኖሯል ቱርክዬ❤🙊

*****

ኦ...ሮ...ማ...ይ...❤

18/11/2023

በዚህ ምድር ጸንተው ከቆሙ እውነቶች መካከል፦ አንዱና ዋነኛው....ኢትዮጵያ የበደልን ቀንበር ከጀርባዋ አውርዳ ቀና ያለች ጊዜና ሁሌም ኀሸናፊ ነች፦ እውነት ነው የዘለአለም...እውነት✊

"ኢትዮጵያ ሁሌም ኀሸናፊ ነች"

✊✊✊✊✊✊✊✊✊✊✊✊✊✊✊✊✊✊

ኀይል የእግዚአብሔር ነው፤ ድል የኢትዮጵያ ነው።

******

ኦ....ሮ...ማ...ይ...❤

18/11/2023

እኔ ማነኝ?❤❤❤....ኦ...ሮ....ማ....ይ....✊✊✊

17/11/2023

ህዳር ፯ ቅዱስ ጊዮርጊስ ❤
********************

❤በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በቅዱሳኑ ስም ለምናመሰግንበት ለሰማእቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ዓመታዊ ቅዳሴ ቤቱ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን ፦❤

*****

ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት - ዘብሔረ ጎንደር (ዲ/ዮርዳኖስ አበበ):

*****

❤መጽሐፈ ገድሉ እንደሚለው የሰማዕታት አለቃቸው አንድም ሞገሳቸው ታላቅና ክቡር ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ7 ዓመታት ስቃይ በሁዋላ ተሰይፏል ይሕስ ጥንተ ነገሩ እንደምን ነው ቢሉ፦

*****

❤ቅዱሱ የተወለደው ከአባቱ ዘረንቶስ (አንስጣስዮስ) እና ከእናቱ ቴዎብስታ የድሮው ፋርስ ግዛት ፍልስጥኤም (ልዳ) ውስጥ ነው የተባረኩ ወላጆቹ ክርስትናን ጠንቅቀው አስተምረውት አባቱ ይሞታል

*****

❤ቅዱስ ጊዮርጊስ 20 ዓመት ሲሞላው የአባቱን ስልጣን እጅ
ለማድረግ ሲሔድ የቢሩት ቤይሩት ወይም ሊባኖስ ሰዎች ዘንዶ (ደራጎን) ሲያመልኩ አገኛቸው እርሱ ግን የከተማውን ሕዝብ አስተምሮ አሳምኖ ደራጎኑንም በፈጣሪው ኃይል ገድሎ መንገዱን ቀጥሏል

*****

❤ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ዱድያኖስና 70 ነገሥታት ዘንድ ሲደርስ ክርስቶስ ተክዶ ለጣዖት ይሠገድ ነበር በዚያች ሰዓት ድንግል እመቤታችን ወደ ሰማዕቱ መጥታ መከራውንና ክብሩን ነገረችው እርሱም በክርስቶስ ስም መሞት ምርጫው ነበርና ከእመቤታችን ተባርኮ ወደ ምስክርነት አደባባይ ደረሰ

******

❤ከዚያም ለተከታታይ 7 ዓመታት ብዙ ጸዋትወ መከራዎችን ተቀበለ 3 ጊዜ ሙቶ ተነሳ ከሰው ልጅ የተፈጥሮ ትዕግስት በላይ የሆነ ስቃይን ስለ ቀናች ሃይማኖት ሲል በመቀበሉ "የሰማዕታት አለቃቸው ፀሐይና የንጋት ኮከብ" በሚል ይጠራል

*****

❤ከ7 ዓመታት መከራ በሁዋላም ከብዙ ተዓምራት ጋር ተሰይፎ ደም ውሃና ወተት ከአንገቱ ፈሷል 7 አክሊላትም ወርደውለታል ይህቺ ዕለት ለቅዱስ ጊዮርጊስ ኃያል ቅዳሴ ቤቱ ናት እርሱ በ390ዎቹ አካባቢ ሰማዕት ከሆነ ከጥቂጥ ዓመታት በሁዋላ በዚያው በሃገሩ ደብር አንጸው አጽሙን አፍልሠው በዚህች ቀን ቀድሰዋታል

*****

❤ቅዱሱ ሰማዕት ከሰማዕትነቱ በፊትም ሆነ በሁዋላ ተአምረኛ ነውና አንዷን እንመልከት በዘመኑ የክርስቲያኖችን ደም ሲያፈሱ ከነበሩ ነገሥታት መካከል አንዱ የሆነው ዲዮቅልጢያኖስ ርጉም የ47 ሚሊዮን ክርስቲያኖችን ደም አፍስሶ ነበርና ፈጣሪ ደመ ሰማዕታትን የሚበቀልበት ጊዜ ደረሰ

*******

❤በ305 ዓ/ም አካባቢ አረመኔው ንጉሥ ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ተአምረኛነት ሰምቶ እንዲያፈርሱት ሠራዊት ላከ የሠራዊቱ አለቃም ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ገብቶ በቅዱስ ጊዮርጊስ ስዕል ላይ ተሳለቀ

******

❤ከፊቱ የነበረውን ቀንዲል በሰይፍ እመታለሁ ሲል ቀንዲሉ ተገልብጦ መሐል አናቱን መታው እንደ እብድ ሆኖ ሞተ ሠራዊቱም ሰምቶ ወደ ንጉሡ ሸሸ ይሕን ሰምቶ የተበሳጨው ዲዮቅልጢያኖስ ግን ራሱ ሊያፈርሰው ሔደ ከቤተ ክርስቲያኑ በር ላይ ሲደርስ ሚካኤልና ገብርኤል ዐይኑን አጠፉት

*****

❤እገባለሁ ሲል ቅዱስ ጊዮርጊስ ከላይ መረዋውን (ደወሉን) ለቀቀበት ራሱን ቢመታው ደነዘዘ የብዙ ቅዱሳንን ደም የጠጣው ርጉሙ ንጉሥም አብዶ ለ7 ዓመታት ፍርፋሪ ሲለምን ኑሮ ሰይጣን ከገደል ጫፍ ወርውሮ ገድሎታል

*****

❤❤❤አምላካችን እግዚአብሔር ከኃያሉ ሰማዕት ጽናትና ትዕግስት ከበረከቱም ያሣትፈን "አሜን" 💒 💚 💛 ❤ 💒

*****

ኦ...ሮ...ማ...ይ...❤❤❤✊

16/11/2023

አንበሳ ፒኮኳን ሲበላ አስሬ ለምን መፖሰት ትወዳለህ???🙊

**********************************************

በቃ እሺ አንበሳውን ተውት .....እና..... ኩንጉፉ ፓንዳ ፒኮኳን ሲያናፍጣት የሚያሳየውን..... ኩንጉፉ ፓንዳ ፓርት ቱ...ይመልከቱ!✊

*****

for those of you that perceive me as a black lion lover, please, i would like to motivate you to watch the season (Kung FU panda part Ii).....and picture how the peacock was kicked by the kungfupanda..😂😂😂

16/11/2023

በአቡነ ተክለ ሃይማኖት ሥም ስንቱ ጠላት እራቀ መሰለህ ጃል....እስቲ ስለ አቡነ ተክለሃይማኖት ሥም ስትሉ እናንት ኢትዮጵያውያን ሁሉ በአንድነት እንደ ዐለት ጸንታቹህ ቁሙ!!❤

*****

ኦ...ሮ....ማ...ይ.....❤❤❤

16/11/2023

የጽዮን ልጅ ሆይ!.....አይዞሽ✊

16/11/2023

ገስጥ ተጫኔ❤..........***......❤❤❤.....***
************

16/11/2023

መልህክት ለምስር✊
***************

ምስር ወጥ ይሻላል ወይስ ኢትዮጵያዊነት?....?..?...ትትትት!

*****

ምስር ወጥ ያላቹህ..... በዚህ ተሰለፉና .....ምሳቹሁን ብሉ (ኤሳውዬ)...እሺ ኢትዮጵያን ያላቹህ በዚህ በኩል ቁሙ....ኢትዮጵያ እኮ ያንተ የአንድ ጩጬ ልጅ አይደለችም...ኢትዮጵያ እኮ...የአባ ጅፋርም ናት....የአብዲሳ አጋም ናት...ስንቶች ጀግነው ተወልደው ያደጉባት የተማሩባት...ጦር የመሩባት....ኢትዮጵያ ናት✊

*****

bytheway....እስቲ ስንቶቻቹህ ታውቃላቹህ የጅማ ልጆች....ዳግማዊ አጼ ምኒልክ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ዘምነገደ ይሁዳ .....ዓድዋ ሊዘምቱ...ስንቁን...ሠራዊቱን በሥርዓት አሰልፈው ሲያበቁ...ጣሊያንን ሊወቁ...ወደ ዓድዋ ጉዞ ከመጀመራቸው በፊት አባ ጅፋርን ከጅማ አስመጥተው አራት ኪሎ ቤተ መንግሥት አስቀምጠው..."በል አባ ጅፋርዋ የጦርነት ነገር አይታወቅምና እኔ ጦርሜዳ ሄጄ በጣሊያን እጅ ከወደኩና ከሞትኩኝ...አገር ታላቅ የፍቅር ሰው የጥበብ ሰው ትፈልጋለች እና ና አልጋዬ ዙፋኔ ላይ ቁጭ ብለህ አገሬን አስተዳድር"...ብለው ወደ ዓድዋ እንደዘመቱ ስንቶቻችን የጅማ ልጆች እናውቃለን.....

*****

ችግር የለውም..... እውነት እውነት ናትና የማንም እገዛ አትፈልግም... አሁን የተናገርኩት እውነት ከሆነ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከተራ ጎጠኝነት .....የአህምሮ ባርነት አጥር.... አውሬ.... እንስሳ..... ከሚያደርግ ሰይጣናዊ አሠራር ወጥተን....ሰፋ ሰፋ ባለ ልብ መምከር ይሻላል!❤

*****

ለማንኛውም የምስር መኳንንትም ለኢትዮጵያ ይሠግዳሉ✊

*****

“መኳንንት ከግብጽ ይመጣሉ፤ ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።”
— መዝሙር 68፥31

*****

ኦ...ሮ...ማ...ይ...❤❤❤

15/11/2023

የዋቢሸበሌ ወንዝ ስድብ🤣
**********************

አንተ ዋቢሸበሌ ደግሞ አፍ ኖሮት ነው የሚሳደብ...ዋቢሸበሌስ በወንዛዎንዙ በሜዳው በጎርጁ ለምንስ አይሳደብ..?

*****

እንዲህ እያለ ነዋ የሚሳደብ....እናንተ ኢትዮጵያውያን ግን የሆናቹህ እንከፍ ነገሮች ናቹህ ልበል...ለም አፈር እንዳትሉ ....አፈሩ ለም...ውሀ አጣን እንዳትሉ ውሀ ተሸክሜ ከተፍ...ሐበሻ...ለወሬ አንጂ...በነገር ጦዞ ....ሌላውን ለማጦዝ...በዘር በሐይማኖት ተከፋፍሎ ለመጨራረስ...አንደኞች ናቹህ ማንም እሮጦ አይዛቹህ.....እያለ አዋሽ አፍ አውጥቶ ኢትዮጵያውያንን ይሳደብ...

*****

አንተ የአባይ ግድብ ግንባታ...የኢትዮጵያ ትንሳኤ ግድብን ልማት ትቃወማለህ ማለት ነው....ዋ...ዋ...ዋቢሸበሌ የምትለው?

*****

ኸረ አባይንስ አልቃወምም በምን አቅሜ ችዬ🙊

*****

ግን ሐበሻ ሲተርት ነው አሉ ተረተረት...የላምበረት...የመሠረት...

እንቁላሎችህን ሁሉ ሰብስበህ አሰባስበህ ተበድረህ ተረድተህ...ያጠራቀምከውን እንቁላሎችህን በአንድ ቅርጫት ውስጥ አታስቀምጥ...ለምን ቢሉ ድንገት እንኳን ፍንግል ቢል ቅርጫቱ...ኪሳራው መብዛቱ....

******

ታዳ ፈረንጅ እንዲህ እያለነ do not put all your eggs in one basket...የልማት ድገፋ እና እርዳታም ሆነ ብድራችንን ሲፈቅዱልነ ለምን ይህንን ትምርታቸውን እረስተውት ይሆነ?....በዛች አንዲቱ ቅርጫት የዓባይ ግድብ ጦር ሰብቀው ጦር ባያሰብቁን..ባያጨራርሱነ..ህ...ልበ!✊

****

ዋቢሸበሌ ስድቤን ካልሰማቹህ ከአገር ሳልወጣ እዛው አገር ውስጥ ሰምጦ የቀረው ውሀዬ ይስደባቹህ ብሏል ዋ ቢ ሸ በ ሌ

*****

ኦ...ሮ...ማ...ይ...❤

15/11/2023

ጥያቄ?
******

ከጆንያ ሙሉ ቀይ ዕንቁና ከአንድ ፍሬ የጤፍ ዘር ማን ይበልጣል?

*****

እኔ መልሴ አንድ የጤፍ ዘር ትበልጣለች ነው!✊

*****

እሺ አንተ አንድ ሙሉ ኩንታል ቀይ ዳይመንድን መረጥክ እንበል...እንበል ነው ደግሞ...ማንም አልመረጠም አሉ!

*****

እሺ....የምንበላው አጣን አንተም ተቸገርሃል አሉ....
በል መረሬ አፈር የሆነ.... የጤፍ መሬትን አርሰህ አለምልመህ ስታበቃ ኩንታል ሙሉውን ዳይመንድህን ዝራው... ማዳበሪያ...አክለህ... ተንከባከበው...ኮትኩተው...አረሙን አርመህ ከምረህ ስታበቃ....ውቂያህን...ስትወቃ....በጎተራህ ከተከማቸው... የእንክርዳድ የአረም ዘር ፍሬ....ምን ትበላ?...ምንስ ትቅም?...

*****

ኸረ ባክህ ሞኝህን ፈልግ ከኩንታሌ ካከማቸዋት አንዷን ቀይ እንቁ ሸጬ ሳበቃ መርከብ ሙሉ ጤፍ እሸምታለው እንኳን አንዷን ፍሬ ጤፍ።....መልካም መልሰሃል...አሉ...አሎሎሎሎ....

*****

ስለዚህ ያለ ጤፍ ዳይመንድህን ብትዘራው እንደ ማያበቅል አውቀሃል ማለት ነው....ስንቋጨው...ጤፏ ውስጥ ለሺህ ዓመታት የሚቀጥል ሕይወት አለ ማለት ነው!..ዳይመንድ ግን የከበረ ድንጋይ ነው....ውድ የተወደደ...የትም የማይገኝ....ግን...ግን...ግን...

*****

ታዳ ይህቺ ደቃቃ የጤፍ ፍሬ በአፈር ተቀብራ ስታበቃ ሺህ...ሚሊዮን...በቢሊዮን...ትሪሊዮን....ወዘተረፈ ከሆነች....ለአንተ ክብሯን የገለጠች....ንገረኝ ሰውስ...ተራ የባዮልጂ የሴል ክፍልፋይ አንድ ሴል ተባዝቶ ከዝንጀሮው ቅም ቅም ሃያቱ🤣 ነው የመጣው ብለህ በዘመናዊ ትምህርትህ ንቀህ ብታስንቀው..... ብታዋርደው....መቼም ከጤፍ አታሳንሰውምና🙊....ከሰውና ከጤፍ ማን ይበልጣል....

******

ሰው አላቹህ...መልካም መልሳቹሃል ተማሪዎች....ስለዚህ በትምህርታችን መሰረት...ሁሌም ሰውን ማክበር ለመከበር መሆኑን እንዳትረሱ እሺ ልጆች....
ሰው > (መሬት+ፀሐይ+ኮከብ+ጨረቃ+...) ...እንዴት የሚለውን የሒሳብ ስሌት አሁን መቼም ማስላት የሚከብዳቹህ አይመስለኝም እና...በሉ ደህና እደሩ ልጆች....የዛሬ አበባዎች የነገ ፍሬዎች...ደህና ሁኑ ልጆች!❤

******

ኦ...ሮ...ማ...ይ...❤

15/11/2023

አንቺ መከረኛ አገር መቼም የማትሻገሪው የለምና ተስፋ አልቆርጥብሽም.....በፍፁም...በፍፁም...ወደፊት ሂጂ✊

15/11/2023

፭......፭.....፭
***********

እንኳን ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አደረሰን አደረሳቹህ❤

******

ኦ....ሮ....ማ...ይ...❤

14/11/2023

አንተ ልጅ አብደሃል ልበል ይላሉ😂

**************************

እና ለምን አናብድ...ጥሽሽሽሽሽ አንል በኢትዮጵያ ሲመጡብነ?❤

*****,,,

ኦ....ሮ...ማ...ይ....❤❤❤

14/11/2023

አላህዋ ክበር!....አሏህ ዋክበር....በልጅነታች በሰማነው በእያዮ ማንያዘዋል ውብ መንዙማ ቅላጼ ነውና ነገሩ!❤❤❤✊
***********

Want your organization to be the top-listed Non Profit Organization in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address

Six Killo, Addis Ababa
Addis Ababa
Other Charity Organizations in Addis Ababa (show all)
imagine1day imagine1day
2Q3W+XV2 Imagine1day, Gabon Street
Addis Ababa, 1000

Educating people to transform themselves, their communities, and the world.

Organization for Welfare & Development in Action - OWDA Organization for Welfare & Development in Action - OWDA
Meskel Square , Lion Building , 9th Floor
Addis Ababa, 1502A.A

OWDA is a charity organization that Promotes conditions of sustainable human development through implementing programs on basic service delivery, economic opportunities, livelihood...

Women and Children Empowerment Organization-WCEO Women and Children Empowerment Organization-WCEO
Addis Ababa. Ethiopia
Addis Ababa

WCEO is Charity Society Organization (CSOs) founded to engage in empowering the community particularly women and children through designing different interventions that create econ...

Jaldu Page Jaldu Page
Addis Ababa, ###X

This page is where Jaldu Woreda people will share their ideas, views and discuss on what ever agendas raised

Relief Organization for South Sudan Addis Ababa, Ethiopia Relief Organization for South Sudan Addis Ababa, Ethiopia
Addis Ababa

To coordinate humanitarian assistance to save lives, restore dignity through psycho-socio rehabilita

waldah qurana waldah qurana
Addis Ababa, 1000

الجمعية الخيرية لخدمة القرآن في إثيوبيا �

ኑስራ የበጎ አድራጎት ድርጅት/ Nusra Charitable organization ኑስራ የበጎ አድራጎት ድርጅት/ Nusra Charitable organization
Mesalemia
Addis Ababa

በበጎነት ማህበረሰቡን እናብቃ!!

ANI SIIF JIRAA CHARITy ANI SIIF JIRAA CHARITy
Addis Ababa

Hojii gaarii dhaloota dhufuuf !

Abdellah Ibnu Umi Mekhtum-አብደላህ ኢብኑ ኡሚ መኽቱም Abdellah Ibnu Umi Mekhtum-አብደላህ ኢብኑ ኡሚ መኽቱም
Around 6kilo
Addis Ababa

Abdellah Ibnu Umi Mektum Qur’an Association is a certified religious non-governmental organization

Ashagari Ashagari
Bole Friendship Building 6th Floor Office Number 604
Addis Ababa, 2260/1110

Ashagari is a Learning and Development Company whose chief aim is to see transformed generation. ‘አሻጋሪ’ is an Amharic word that means ‘The one who helps transform’.