Entoto PTC.tms

Entoto PTC.tms

Founded in 1917 E.C as Teferi Mekonen School, Entoto Poly Technic College provides outcome-based training in 11 departments.

Join us for quality education and a bright future!

Photos from Entoto PTC.tms's post 03/08/2024

" አንድ ሞያ ለአንድ ዜጋ"
ዕለተ ዓርብ ሐምሌ 26/2016ዓ.ም

" አንድ ሞያ ለአንድ ዜጋ" በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው የስልጠና መርሃ-ግብር ሃሳብ አፍላቂ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር ) ባስቀመጡት አቅጣጫ መሰረት ይህንን የተቀደሰ ተግባር እውን ለማድረግ ኮሌጁ ባወጣው ማስታወቂያ መሠረት በተለያዩ የሙያ መስኮች ለመሠልጠን 271 ስልጠና ፈላጊዎች የተመዘገቡ መሆናቸውን ከቀረበው የምዝገባ መረጃ ለማወቅ ተችሏል።

በስልጠናው መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ ዲን አቶ ተሾመ ፈይሳ በዋናነት የስልጠናውን አስፈላጊነት ሲያብራሩ ዜጎች ካላቸው ሙያ በተጨማሪ የአንድ ሙያ ባለቤት ሆነው ራሳቸውንና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን በማረጋገጥ የተሻለ ኑሮ ለመምራት የሚያስችል በመሆኑ ከስልጠናው ማጠናቀቅ በኃላ ብቃታቸውን በምዘና አረጋግጠውና ተደራጅተው ለሚመጡት ወደስራ የሚገቡበትን መንገድ ኮሌጁ ባለው አቅም ዕድሉን የሚፈጥርና የሚያመቻች
መሆኑንም አረጋግጠዋል።

በተመሳሳይ የስልጠናውን ሰዓትና ከስልጠና በኋላ የሚኖሩ ሂደቶችን አስመልክቶ የኮሌጁ ስልጠናና አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ዲን አቶ ደመላሽ ተስፋዬ በቂ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በመጨረሻም ከቤቱ ለተነሱ አንዳንድ ብዥታዎች እና ጥያቄዎች ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፤ስልጠናው በሚቀጥለው ሳምንት የሚጀመር መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል።

ኮሙኒኬሽን ቡድን

Photos from Entoto PTC.tms's post 16/05/2024

ዕለተ ሐሙስ ግንቦት 8/2016 ዓ.ም

ተግባራዊ ጥናትና ምርምር (Action research) ውድድር ተካሄደ።

በትናንትናው ዕለት ተግባራዊ ጥናትና ምርምር ውድድር የተካሄደ ሲሆን ውድድሩ ላይ የስለጠና ዘርፍ ሀላፊዎች፣ የጥናትና ምርምር አወዳዳሪዎችና ተወዳዳሪ አሰልጣኞች በተገኙበት አራዳ መኒፍክቸሪንግን ጨምሮ ስድስት ተግባራዊ ጥናትና ምርምር ለውድድር ቀርቧል።

የውድድሩ ዓላማ ኮሌጆች በስልጠና እና በኢንደስትሪ ኤክስቴንሽን እንዲሁም በቴክኖሎጂ ሽግግር ዙርያ የአሰራር ስርአታቸውን ለማዘመንና ቀልጣፍ አገልግሎት መስጠት ያስችላቸው ዘንድ መነሳሳትን መፍጠርና ከዚህም ባሻገር በኮሌጆች ውስጥ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን መፍታት የሚያስችል አቅም መፍጠር ላይ ያለመ ነው።

በዚህም በዛሬው ዕለት በተካሄደው የክላስተር ውድድር በትናንትናው ዕለት ከቀረበው ተግባራዊ ጥናትና ምርምር ውስጥ 1ኛ የወጣው በክላስተር ደረጃ የሚወዳደር ሲሆን ከዚህ ውድድር አንደኛ የሚወጣው ተግባራዊ ጥናትና ምርምር በቀጣይ በከተማ እና በተዋረድ በሀገር አቀፍ ጀረጃ የሚቀርብ መሆኑን የኢንደስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ዲን ወንድምሲያምረኝ መኮንን ገልፀዋል።

ኮሙኒኬሽን ቡድን

10/05/2024

ለአረንጓዴ ፈጠራ ላብ ያመልክቱ

በአዲስ አበባ ለምትገኙ እና ለወጣቶች እና ለሴቶች የስራ እድል የሚፈጥር አዳዲስ አረንጓዴ ፈጠራዎች ውጤታማ እና ጠንካራ መስመር መገንባት
Address:Leghar, ORDA Bldg, 15th Floor Addis Ababa, Ethiopia Tel.Number:+251942494949 :+251911010160

Photos from Entoto PTC.tms's post 08/05/2024

ዕለተ ረቡዕ ሚያዝያ 30/2016 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ጠልሰም ሠዓሊ ሔኖክ መልካምዘር የህይወትና የስራ ልምዳቸውን ለስነ-ጥበብ ት/ክፍል ሰልጣኞች አካፈሉ።

የእንጦጦ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሥነ-ጥበብ ትምህርት ክፍል ማስተማር ከተጀመረበት ጊዜ ማለትም 1999 ዓ.ም አንስቶ ከመደበኛው የመማር ማስተማር ሂደት ባሻገር በሥነ-ጥበብ ዘርፉ አንጋፋ ባለሙያዎችን በመጋበዝ የሕይወትና የሥራ ልምዳቸውን ለሰልጣኞች እንዲያካፍሉ በማድረግ መዝለቁ ይታወሳል። በመሆኑም የዚህ ወር እንግዳ የሆኑት በኢትዮጽያ የጠልሰም ሥዕል ጥበብ አንጋፋ የሆኑት ሠዓሊ ሔኖክ መልካምዘር ናቸው።

በመረሀ-ግብሩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የስነ-ጥበብ ስልጠና ዘርፍ መምህር ሀይሉ ክፍሌ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈው በኢትዮጵያ የጠልሰም ሥዕል ጥበብ አንጋፋ የሆኑት ሠዓሊ ሔኖክ መልካምዘር ለሰልጣኞች የህይወትና የስራ ልምዳቸውን ሊያካፍሉ በመምጣታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልፀው ለፕሮግራሙ መሳካት ያላሰለሰ ጥረት ላደረጉ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በተያያዘም የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ ተሾመ ፈይሳ ለኮሌጁ 99ኛ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈው በኢትዮጵያ የጠልሰም ሥዕል ጥበብ አንጋፋ የሆኑት ሠዓሊ ሔኖክ መልካም ዘር የተደረገላቸውን ጥሪ አክብረው በምጣታቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል። አክለውም ከዚህ ቀደም የነበ ሩ የስነ-ጥበብ ስልጠና ዘርፍ ሰልጣኞች ከኮሌጁ 100ኛ ዓመት ክብረ በዓል ጋር በተያያዘ ዘመን ተሻጋሪ ሰራዎቻቸውን ለተመልካች የሚቀርቡበትን መንገድ እንደያመቻቹ ጥሪ አስተላልፈዋል።

በኢትዮጽያ የጠልሰም ሥዕል ጥበብ አንጋፋ የሆኑት ሠዓሊ ሔኖክ መልካምዘር የኮሌጁ ዲኖች፣ ተጋባዥ እንግዶችና ሰልጣኞች በተገኙበት ተወልደው ካደጉበት አዲስ አበባ ልዩ ስሙ ጃን ሜዳ ፣ አስተዳደጋቸውን እና ከልጅነታቸው ጀምሮ ክረምት ላይ ትምህርት ሲዘጋ የቅኔ መምህር የነበሩት አያታቸው ጋር ጎጃም ክፍለ ሀገር እንደሚሄዱና በእርሳቸው አማካኝነት ከስድስተኛ ክፍል ጀምረው የጠልሰም ትምህርት እንደ ጀመሩ እንዲሁም ለ18 ዓመታት ያለማቋረጥ እንደ ተማሩ ገለፀዋል። የመጀመሪያ የጠልሰም ስራቸውን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኤግዚቢሽን ማዕከል በ1984 ዓ.ም እንዳቀረቡና ከዘህም ባሻገር በተለያዩ ዓለማት የስዕል ስራዎታቸውን እንዳቀረቡና አሁንም በዶ/ር ኤልሳቤት ወ/ጊዮርጊስ አማካኝነት በሻርጃህ አርት ፋውንዴሽንና ሙዝዬም 120 የስዕል ሥራዎቹ እየቀረቡ እንደሆነ እንዲሁም የተለያዩ ወርክሾፖችን እንደተካፈሉ አመላክተዋል። በተያያዘም ስለ ጠልሰም ምንነት፣ ጠልሰም ለመስራት የሚያስፈልጉ ነገሮች፣ ስለ ጠልሰም አይነቶች ሰፊ ማብራራያ ሰጥተዋል በተያያዘም ከታዳሚዎች ለተነሱላቸው ሃሳብ፣ አስተያየት እና ጥያቄዎች እንደየ አጠያየቃቸው ምላሽ ሰጥተዋል።

በመቀጠል በሻርጃህ አርት ፋውንዴሽንና ሙዝዬም የስዕል ስራዎችን ለማቅረብ በር ከፋች የሆነውን በዶ/ር ኤልሳቤት ወ/ጊዮርጊስ የተዘጋጀ የስድስት ደቂቃ ቪዲዮ ለታዳሚ የቀረበ ሲሆን በተያያዘም የበገና መምህር በሆኑት ኤርሚያስ አማረ ስለ በገና ምንነትና አደራደር አጭር ገለፃ በመስጠት ዝማሬ ቀርቧል።

በመጨረሻም በት/ክፍሉ የተዘጋጀውን እና የተሳታፊዎች ፊርማ ያረፈበት ማስታወሻ በሰዓሊያን ማህበር ፕሬዝደንት ሰዓሊ አክሊሉ አማካኝነት በስጦታ መልክ ተበርክቶላቸዋል።

ኮሙኒኬሽን ቡድን

Photos from Entoto PTC.tms's post 03/05/2024

ዕለተ ሀሙስ መጋቢት 24/2016 ዓ.ም

የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ ማዕድ
የማጋራት መርሀ-ግብር ተካሄደ።

ኮሌጁ የበጎ አድራጎት ማዕድ ማጋራት መርሀ ግብርን በተለያዪ ጊዚያት ተግባራዊ እያደረገ የመጣ መሆኑ ይታወቃል ፡፡ በዛሬው ዕለትም አነስተኛ ደመወዝ ተከፋይ ለሆኑ የኮሌጁ ሠራተኞች እና በአካባቢው ነዋሪ የሆኑ አቅመደካሞችን በማካተት የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ በቀድሞ ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ተማሪዎች ህብረት አማካኝነት የማዕድ ማጋራት ፕሮግራም ተካሂዷል።

በፕሮግራሙ ላይ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን ያስተላለፉት የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ ተሾመ ፈይሳ የማዕድ ማጋራት ፕሮግራም በበዓል ወቅት የመተሳሰብና ተካፍሎ መብላትን እንዲሁም የአብሮነት ባህልን የሚያዳብር መሆኑን በመግለፅ ይህንን መርሀ-ግብር ላዘጋጁ የቀድሞ ተፈሪ መኮንን ተማሪዎች ህብረት ምስጋናቸውን አቅርበዋል። አክለውም ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች መልካም የትንሳኤ በዓል በማለት መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።

በተያያዘም የቀድሞ ተማሪ የነበሩ አቶ ፍቅረማርያም ፀሀይ ለኮሌጁ ማህበረሰብ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈው በውጭ ሀገር ሆነ ሀገር ውስጥ ያሉ የቀድሞ ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ተማሪዎች ይህንን ማዕድ የማጋራት መርሀ-ግብር እንዳዘጋጁ ገልፀው መልካም የፍሲካ በዓል በማለት መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።

ኮሙኒኬሽን ብድን

Photos from Entoto PTC.tms's post 30/04/2024

ዕለተ ማክሰኞ ሚያዝያ 22/2016 ዓ.ም

ለኮሌጁ ማኔጅመንና አካዳሚክ ኮሚሽን አባላት
ስልጠና ተሰጠ።

እንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከኢትዩጰያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት ጋር አይሶን ለመተግበር ባደረገው ስምምነት መሠረት በታስክ ፎርሱ /የሥራ ግብረ ኃይሉ አማካኝነት ወደ ስራ መግባቱ ይታወሳል፤ ትግበራውን በተጠናከረ ሁኔታ ለማስኬድ ይረዳ ዘንድ በዛሬዉ ዕለት ለኮሌጁ ማኔጅመንትና አካዳሚክ ኮሚሽን አባላት ስልጠና ተሰጥቷል።

የዚህ ስልጠናው ዓላማ የሥራ ግብረሀይሉ አባለት ግንዛቤን በማዳበር ለአይሶ ትግበራው የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዳያበረክቱ በማስቻል ዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና በማግኘት ኮሌጁን ተወዳዳሪ ሊያደርግ የሚያስችል የአሰራር ስርዓት መዘርጋትና ለቴክኖሎጂ ሽግግር ምቹ ሁኔታ መፍጠር እንዲሁም የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መሰጠት ላይ ያለመ ነው።

ኮሙኒኬሽን ቡድን

Photos from Entoto PTC.tms's post 30/04/2024

ዕለተ ማክሰኞ ሚያዝያ 22/2016 ዓ.ም

ለኮሌጁ አሰልጣኞች እንዲሁም ፅዳትና ጥበቃ
ሠራተኞች ስልጠና ተሰጠ።

ስልጠናው ከትናንት የቀጠለ እና በጥቅም ግጭት ላይ ትኩረት ያደረገ ሲሆን በሥነ-ምግባርና ፀረ ሙስና መከታተያ ዳሬክቶሬት አማካኝነት የተዘጋጀ ነው።

የስልጠናው ዓላማ በተቋማት ውስጥ የሚስተዋሉ የጥቅም ግጭቶችን ለመከላከልና ለማስተዳደር የሚያስችል ግንዛቤ በመፍጠር አሰራርን በመርህ ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ማድረግ ላይ ያለመ ነው።

ስልጠናውን የሰጡት ከአዲስ የአበባ ሥነ-ምግባርና ፀረ- ሙስና ኮሚሽን የስልጠና ዳሬክቶሬት አቶ ደረጀ ግርማ ሲሆኑ ስልጠናው ትኩረት ያደረገባቸው ርዕሰ ጉዳዮች፦
- የጥቅም ግጭት መሰረታዊ ሀሳቦች
- የጥቅም ግጭት ለመከላል ህጋዊ መነሻዎች
- የጥቅም ግጭት ሊፈጥሩ የሚችሉ ተጋላጭ መስኮች
- የጥቅም ግጭት መንስኤዎች
- የጥቅም ግጭት መከላከያና ማስተዳደርያ መንገዶች
- የጥቅም ግጭት መከላከል ላይ የተለያዩ አካላት ሚና በዝርዝር ተዳሰዋል።

ኮሙኒኬሽን ቡድን

Photos from Entoto PTC.tms's post 30/04/2024

ዕለተ ሰኞ ሚያዝያ 21/2016 ዓ.ም

ለኮሌጁ አሰልጣኞች እንዲሁም ፅዳትና ጥበቃ በሥነ-ምግባር እና መልካም አስተዳደር ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና ተሰጠ።

የስልጠናውን መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ ተሾመ ፈይሳ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈው በሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳሬክቶሬት አዘጋጅነት መልካም አርአያነት ያለው ብልሹ አሰራርን የሚጠየፍ የተሻለ ተቋማዊ አፈፃፀም የሚያመጣ ማህበረሰብን ለመገንባት በኮሚሽኑ አማካኝነት ተከታታይነት ያለው ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን ገልፀዉ የተሻለ ተቋምን ለመገንባት የመልካም አስተዳደር ግንዛቤን ይዘን የጥቅም ግጭትን ለማስወገድ ያስችል ዘንድ ስልጠናውን በአግባብ መከታተል እንደሚገባ በማመላከት መልካም የስልጠና ግዜን ተመኝተዋል።

ስልጠናዉ በሥነ-ምግባርና ፀረ ሙስና መከታተያ ዳሬክቶሬት አማካኝነት የተዘጋጀ ሲሆን የስልጠናው ዓላማ መልካም ሥነ-ምግባር ለመልካም አስተዳደር ግንባታ ያለውን ፍይዳና አስፈላጊነት በሚመለከት መሰረታዊ እዉቀትንና ክህሎቶችን ማስጨበጥ እና በኮሌጅ ውስጥ ሥነ-ምግባራዊ አገልግሎት እንዲሁም መልካም አስተዳደርን ማጎልበት ላይ ያለመ ነዉ።

ስልጠናውን የሰጡት ከአዲስ የአበባ ሥነ-ምግባርና ፀረ- ሙስና ኮሚሽን የስልጠና ዳሬክቶሬት አቶ ደረጀ ግርማ ሲሆኑ ስልጠናው ትኩረት ያደረገባቸው ርዕሰ ጉዳዬች፦
- የመልካም አስተዳደር መሰረታዊ መርሆች
- የመልካም አስተዳደር አስፈላጊነት
- የመልካም አስተዳደር ተግዳሮቶች
- ሥነ-ምግባርና መልካም አስተዳደር
- ሥነ-ምግባርዊ ፈታኝ ሁኔታዎች እና መልካም አስተዳደር በዝርዝር ተዳሰዋል።

ኮሙኒኬሽን ቡድን

Photos from Entoto PTC.tms's post 30/04/2024

ዕለተ ሰኞ ሚያዝያ 21/2016 ዓ.ም

ለኮሌጁ አሰልጣኞች ISO ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።

በ"ISO 21001:2018 Educational quality management system" በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና በማግኘት ኮሌጁን ተወዳዳሪ ሊያደርግ የሚያስችል የውል ስምምነት ከኢትዩጰያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት ጋር ፈፅሞ ወደ ስራ መግባቱ ይታወሳል።

በመሆኑም የዚህ ስልጠና ዋና ዓላማ ኮሌጁ የትግበራውን ሂደት ዕውን ለማድረግ ያስችል ዘንድ ለኮሌጁ አሰልጣኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መሰጠት ላይ ያለመ ሲሆን ስልጠናዉ ትኩረት ያደረገባቸው ርዕሰ ጉዳዮች፦
- ISO ምንነት
- ISO ትግበራ ጠቀሜታ
- የISO መለኪያዎች (standard) ምንድናቸው
- ISO የምንተገብርበት ምክንያት
- የትግበራው ሂደት ምን ይመስላል
- የትግበራው ጠቀሜታና በትምህርት ተቋማት የISO ትግበራ በዝርዝር ተዳሷል።

ኮሙኒኬሽን ቡድን

Photos from Entoto PTC.tms's post 27/04/2024

የተፈሪ መኮንን ት/ቤት 99ኛ ዓመት ልደት በዓል

የዛሬ 99 ዓመት ሚያዝያ 19,1917 በዕለተ ሰኞ በ10 ሰዓት በአገራችን በዕድሜ 2ተኛ የሆነው ተፈሪ መኮንን የአዳሪ ት/ቤት በልዑል አልጋወራሽ ተፈሪ መኮንን ተመርቆ ተከፈተ፡፡ መጀመሪያ የተመዘገቡት 32 አዳሪዎችና 40 ያህል ተመላላሾች ነበሩ። እስካሁንም የተማሪዎች ቁጥር በየቀኑ እያደገ የሚሄድ ሲሆን በእነዚህ ዘመናትም ብዙ የዕድገት ደረጃዎችን ማለፉን የተለያዩ የመረጃ ምንጮች ያስረዳሉ ፡፡ ከዚህም ባሻገር በዕድሜ አንጋፋ፣ በተሞክሮ የዳበረ፣ በአሠራር የደረጀው የእንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዛሬም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰልጣኞችን በዕውቀት እና በሙያ እያበቃ ለሃገር በማበርከት 99ኛውን የልደት በዓል ያከብራል።

የ,ኋላው ከሌለ የለም የፊቱ ነውና የተማሪ ቤቱ መስራች ተፈሪ መኮንን የወለዷቸውን ልጆች ብሎም ት/ቤቱ ያፈራቸው አንጋፍ የቀድሞ ተማሪዎችን እያሰበ ሲያከብር የመከበሩ ስኬት የተቋሙ ብቻ ሳይሆን የሀገር ብሎም የቀድሞ ተማሪዎችና ቦርድ አባላት እንዲሁም በኮሌጁ ውስጥ በሰራተኝነት አልፈው የነበሩና እያገለገሉ ያሉ በሙሉ በመሆኑ እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን።

ኮምንኬሽን ክፍል

Photos from Entoto PTC.tms's post 25/04/2024

ዕለተ ሐሙስ ሚያዝያ 17/2016 ዓ.ም

የኮሌጁን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ያደረገው
የሌማት ትሩፋት።

ያለ አቅምን አሟጦ በመጠቀም ማህበረሰብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራትን ማከናወን መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራበት ያለ ጉዳይ መሆኑ ይታወቃል። በዚህም የከተማ አስተዳደሩ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የኮሌጁን ማህበረሰብ የሌማት ትሩፍት ተጠቃሚ ለማድረግ ብሎም የኮሌጁን የውስጥ ገቢ ማሳደግ የቀጣይ አቅጣጫ መሆኑ ተጠቁሟል።

በኮሌጁ የሚገኙ ማሽነሪዎችን እና አቅምን በማቀናጀት ለረጅም ዓመታት ያለስራ የተቀመጡ የዳቦ መጋገርያ ማሽኖችን አስጠግኖ ወደስራ በማስገባት በተመጣጣኝ ዋጋ ለኮሌጁ ማህበረሰብ ዳቦ ማቅረብ ተችሏል።

የዚህ አገልግሎት ተጠቃሚ ከሆኑ የዝግጅት ክፍላችን ካነጋገራቸዉ የኮሌጁ ሰራተኞች መካከል የሬጀስትራል ባለሙያ የሆኑት ወ/ሪት መስከረም መኮንን በአገልግሎቱ ደስተኛ እንደሆኑና ውጪ ካለው ዋጋ፣ መጠን እና ጥራት አንፃር የተሻለ ሆኖ እንዳገኙት ገልፀው ነገር ግን የአቅርቦት መጠኑ ዝቅተኛ በመሆኑ የፈለጉትን ያህል መግዛት እንዳልቻሉና ይህም ትኩረት ተሰጥቶ ቢሰራበት መልካም ነው ሲሉ ሀሳባቸውን ገልፀዋል።

ተጨማሪ አስተያየት ከሰጡን የኮሌጁ ማህበረሰብ መካከል በኮሌጁ ፍይናንስ ሰነድ ክፍል ባለሙያ ወ/ሮ ብርሀኔ ዘርይሁን መውጫም ሆነ መግቢያ ሰዓት ላይ ሰርቪስ እንዳያመልጣቸው ሲሉ ለልጆቻቸው ዳቦ መግዣ ግዜ አጥተው እንደነበርና ኮሌጁ የዚህ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ስላደረጋቸው ግዜያቸውን ሆነ ገንዘባቸውን መቆጠብ ያስቻለ የተሻለ ጥራት ያለው ትኩስ ዳቦ መግዛት እንደቻሉ ገልፀዋል። አክለውም የዳቦው መጠን ማለትም ግራሙ ላይ ማስተካከያ ቢደረግ መልካም ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ኮሙኒኬሽን ቡድን

Photos from Entoto PTC.tms's post 24/04/2024

ዕለተ ረብዕ ሚያዝያ 16/2016 ዓ.ም

በሆቴልና ቱሪዝም የስልጠና ዘርፍ የቱር ጋይድ
ት/ት ክፍል ሠልጣኞች ጉብኝት አካሄዱ።

ቱሪዝም ለሀገር ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት ሆኖ በተለያዩ ዘርፎች ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል የሚፈጥር መሆኑ ይታወቃል። በማህበራዊ እና አካባቢያዊ ዕድገት ውስጥም አዎንታዊ ተፅዕኖ የሚፈጥር ዘርፍ ነው።
ለውጪ ሀገር እና ለሀገር ውስጥ እንግዶች በሀገሪቱ ስላለው የተፈጥሮና ሰውሰራሽ መስህቦችን በማስተዋወቁ ረገድ የቱርጋይድ ሚና የጎላ ነው ።

በእንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ይህንን ወሳኝ ሚና በሚጫወተው በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ የሚሰማራውን የሰው ሀይል እውቀትና ክህሎት ለማሳደግ የሚያስችል ስልጠና በሆቴልና ቱሪዝም የስልጠና ዘርፍ ቱር ጋይድ ት/ክ የሚሰጥ ሲሆን በቀደሙት ግዚያት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍል የሚገኙ ታሪካዊና የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎች ላይ በመሄድ በቲዎሪ የተማሩትን በተግባር ቦታው ላይ በመገኘት ልምምድ የሚያደርጉና በተግባር የተደገፈ ት/ት የሚወስዱ መሆኑ ይታወቃል። በዘንድሮው ዓመት በአዲስ አበባና በዙሪያው ሰፊ የመስህብ ስራዎች የተሰሩ በመሆናቸው በእንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በሆቴልና ቱሪዝም ስልጠና ዘርፍ በቱር ጋይድ ትምህርት ክፍል በደረጃ ሁለት እና በደረጃ ሶስት ያሰለጠናቸውን ሰልጣኞች ለሁለት ቀናት የዘለቀ ጉብኝት አደርገዋል።

የጉብኝቱ ዋና ዓላማ በመዲናችን አዲስ አበባ የሚገኙን የቱሪስት መዳረሻ ሰፍራዎችን በመጎብኘት በንድፈሀሳብ የተማሩትን ወደ ተግባር መለወጥ ላይ ያለመ ነው። በከተማችን የቱሪስት መዳረሻ ከሆኑት ስፍራዎች መካከል፦
- እንጦጦ ማርያም ሙዝየም
- እንጦጦ ፖርክ
- አንድነት ፖርክ
- አድዋ ፖርክ
- አዲስ አበባ ሙዝየምን ያካተተ ጉብኝት በአሰልጣኞቻቸው በመታገዝ አድርገዋል።

ኮምንኬሽን ቡድን

13/11/2022
Photos from Entoto PTC.tms's post 09/09/2020

እንጦጦ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

ኮሌጁ ኮቪድ-19ን ለመከላከል የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን ሰርቶ አስተዋጽኦ ከማድረግ በተጨማሪም የዜጐችን የኑሮ ሁኔታ ሊያግዝ በሚችል መልኩ ከዚህ በፊት በሁለት ዙር ለ250 ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ላሉት የማህበረሰብ ክፍሎች የማዕድ ማጋራት ማድረጉ ይታወቃል፡፡
አሁን ለ3ተኛ ጊዜ 210 የማህበረሰብ ክፍሎች ከሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ ከተፈሪ መኰንን የቀድሞ ት/ቤት /TMS/ ተማሪዎች ጋር በመተባበር 300,000/ሦስት መቶ ሺህ ብር/በላይ በመሰብሰብ
አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ የማዕድ ማጋራት ፕሮግራም የከተማ;ክ/ከተማ አመራሮች፤የኮሌጁ አመራሮችና ማህበረሰብ በተገኙበት ረቡዕ ጳጉሜ 4/2012 ዓ.ም ተከናውኗል፡፡

“የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን እንግታ”
ነገን ለመኖር ዛሬ እንጠንቀቅ!

Photos from Entoto PTC.tms's post 16/03/2020

ማርች 8ን አስመልክቶ በሽሮ ሜዳ ካምፓስ የጽዳት ዘመቻ ተካሂዷል፣

Photos from Entoto PTC.tms's post 16/03/2020

የሥርዓተ-ፆታ ክበብ
በኮሌጁ ከተቋቋሙ የተለያዩ ክበባት መካከል አንዱ የሆነው የሥርዓተ-ፆታ ክበብ ሃገራዊ ትኩረት ከሚሹ ጉዳዮች አንዱ በሆነው በሥርዓተ-ፆታ ጉዳዮች ላይ በክፍሉ በአባላቱ ምን ይሰራል ፣እንዴትስ ይሰራል ፣ከእያንዳንዳችን የሚጠበቁ ሁኔታዎችን አንስቶ ስራውን የጋራ አድርጎ መንቀሳቀስ እንዲቻል የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም ተካሄደ፡፡

Photos from Entoto PTC.tms's post 16/03/2020

ዓለማቀፍ የሴቶች ቀን /ማርች 8/
የእንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዓለማቀፍ የሴቶች ቀን /ማርች 8/ን ምክንያት በማድረግ በተለያዩ ዝግጅቶች አከበረ፡፡ ከዝግጅቶቹ መካከል የደም ልገሳ፣
መረከብ ኳስ ውድድር ኬካ ኢንደስትሪያል ኮሌጅ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ፣
በሽሮ ሜዳ ካምሽ የጽዳት ዘመቻ፣
የግንዛቤ መፍጠሪያ ውይይትና
ከ20ዓመት በላይ በተለያዩ መስኮች አገልግሎት ያለቸው ሴት ሰራተኞችን ጀግኖቻችን ናችሁ እናመሰግናለን፡፡ ወልዶ በማሳደግ በሃገር ደረጃ ለሚኖረው ለውጥ የእናንተ ድርሻ ከፍተኛውን ደረጃ ይይዛል፤እናትነትነት ወልዶ ማሳደግ ከወንዱ ባልተናነሰ አንዳንዱም በበለጠ በተለያዩ ዘርፎች በመንግስት ስራ ላይ ላደረጋችሁት አስተዋጽኦ እናመሰግናለን በማለት በደመቀ ሁኔታ በአሉ ተከብሮ ውሏል፡፡ በዚህ መልኩ በዓሉ መከበሩ ከምንግዜውም በላይ ጠንክረን እንድንሰራ ያበረታታናል ሲሉም እናቶች ገለጹ፡፡

Photos from Entoto PTC.tms's post 16/03/2020

እንጦጦ በሰራ እድል ፈጠራው ዘርፍ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በአዲስ አበባ ውስጥ ያለውን የስራ አጥነት ቅነሳ እና የህብረተሰቡን የዳቦ አቅርቦት ችግር ለማቃለል የተጀመረው ፕሮጀክት አንዱ የሆነው አገልግሎታቸውን ጨርሰው የቆሙ አውቶብሶችን አሁን ለሚፈለገው አላማ በሚውሉበት መልኩ ኮሌጃችን በተሰጠው ተልእኮ መሰረት 13 አውቶብሶችን አጠናቆ ለጉለሌ ክፍለከተማ የስራ እድል ፈጠራ ጽ/ቤት አስረከበ፡፡
በርክክቡ ወቅት የኮሌጁ ዲን አቶ ስሜነህ ሀበሻ ስራውን ስንሰራ ከልብ ደስ ብሎን ነው፤በቀጣይም ከዚህ ያሰባሰብነውን ተሞክሮ አክለን የተሻለ እንሰራለን ኮሌጁ በሚፈለግበት አግባብ ሁሉ የድርሻውን ሊወጣ ከጎናችሁ መሆኑን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ በማለት ሲገልጹ የጉለሌ ክ/ከተማ የስራ እድል ፈጠራ ቢሮ ሃላፊ አቶ ኃ/ማርያም አባይነህ ኮሌጁ ላደረገው አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን ገልጸው ወጣቶች ይህንን እድል ተጠቅመው ወደ ስራ እንዲገቡ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

Photos from Entoto PTC.tms's post 16/03/2020

10ኛው የቴክኒክና ሙያ ሳምንት
10ኛው የቴክኒክና ሙያ ሳምንትን አስመልክቶ የተለያዩ ውድድሮች በተለያዩ መስኮች ተከናውነዋል በመዝጊያው ዕለት በተከናወነ ስፖርታዊ ውድድር ኮሌጃችን በገመድ ጉተታና በጆንያ ውስጥ ሩጫ የነሃስ ሜዳልያ ተሸላሚ ሆኖዋል ፡፡ ኮሌጃችን በቀጣይ ደረጃውን የሚያሳድግበትና እንደሃገርም ትኩረት በተሰጠው በቴክስታይል ጋርመንት ከተማ አቀፍ በሆነው የፋሺን ዲዛይን ሁለተኛ ደረጃ ይዞ ፉክክሩን አጠናቋል፡፡

04/03/2020

10ኛው የቴክኒክና ሙያ ሳምንት በኤግዚቢሽን ማዕከል
ከየካቲት 26-30/2012ዓ.ም በሚቆየው የቴክኒክና ሙያ ሳምንት ዝግጅትን እንዲጎበኙ ተጋብዘዋል፡፡ ቦታው ኤግዚቢሽን ማእከል፤ መግቢያ በነጻ

Photos from Entoto PTC.tms's post 04/03/2020

ጋዜጣዊ መግለጫ
10ኛው የቴክኒክና ሙያ ሳምንትን አስመልክቶ የእንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ስሜነህ አበሻ ለአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ መግለጫ ሰጡ፡፡
በመግለጫቸው ‹‹ቴክኒክና ሙያ ወይም የሙያ ስልጠና የወጣቱ የስኬት በር ነው››፡፡ በኮሌጃችን 62 ቴክኖሎጂዎች የተሰሩ ሲሆን በአብዛኛው በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የተሰሩ ናቸው ከነዚህም መካከል አብላጫው ቁጥር ወደ ኢንተርፕራይዞች ተሸጋግረዋል፤ አንዳንዶቹም ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ናቸው፡፡ ወጣቶች ይህንን እድል በመጠቀም በሃገር ግንባታ ላይ የራሳቸውን ሚና ሊጫወቱ ይገባልም ብለዋል፡፡

Photos from Entoto PTC.tms's post 04/03/2020

የእንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ክላስተር
10ኛው የቴክኒክና ሙያ ሳምንትን አስመልክቶ በክላስተር ደረጃ የሚገኙ ኢንተርፕራይዞች ምርታቸውን ፣የመንግስትና የግል ኮሌጆች በሠልጣኞችና አሠልጣኖች የተሰሩ የተለያዩ ስራዎች ለእይታ ቀረቡ ፡፡

04/03/2020

የድል በዓል
እንኳን ለ124ኛው የዓድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ፡፡ ቀደምት አባቶች ወራሪውን ድል እንዳደረጉት ሁሉ በዚህ ዘመን ያለው ትውልድ ግዜው የሚጠይቀውን የኢትዮጲያን አንድነት በማስጠበቅ ድህነትን ታሪክ በማድረግ የበኩሉን ሊወጣ ይገባል፡፡ ‹‹የወጣቱ የስኬት በር በሙያ ብቁ ሆኖ መገኘት ነው፡፡››

Photos from Entoto PTC.tms's post 28/02/2020

የፓናል ውይይት
10ኛው የቴክኒክና ሙያ ሳምንትን አስመልክቶ ከሚከናወኑ የተለያዩ ዝግጅቶች መካከል ከቴክኒክና ሙያ ስትራቴጂ አንዱ በሆነው የትብብር ሥልጠናና ምዘናን አስመልክቶ ከሠልጣኞች፣ከወላጆች፣ ከኢንተር ፕራይዝና ከካምፓኒ ተወካች ጋር በክላስተር ደረጃ የተዘጋጀ የፓናል ውይይት ከየካቲት 19/2012ዓ.ም -20/6/2012ዓ.ም በእንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ተካሄደ፡፡

Photos from Entoto PTC.tms's post 21/02/2020

የድጋፍና ክትትል የጋራ መድረክ
ከአዲስ አበባ ቴ/ሙ/ት/ሥ/ቢሮ የእንጦጦ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የድጋፍና ክትትል ባለሞያ ሆነው እየሰሩ ያሉት ወ/ሮ ፀዳለ ተክሉ በኮሌጁ ተገኝተው ባደረጉት የክትትለና ድጋፍ ስራ በኮሌጁ የተጀማመሩት ስራዎች ጥሩ ደረጃ ላይ ያሉ መሆኑን ገልፀው በተለይ ከቴክኒክና ሙያ ሳምንት ዝግጀት ጋር የተያያዙ ስራዎች በትኩረትና በአፋጣኝ መጠናቀቅ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

Photos from Entoto PTC.tms's post 21/02/2020

የእንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ክላስተር
13/6/2012ዓ.ም በእንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ክላስተር የሚገኙ የግል ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ውይይት አካሄዱ፡፡ ይህ ውይይት የመንግስትና የግል ኮሌጆች በጋራ መስራታቸው በሃገር ግንባታና ሃገሪቱ የምትፈልገውን በመካከለኛ ደረጃ የሠለጠነ የሠው ሃይል ከማፍራት ረገድ ለሚያደርጉት አስተዋጽኦ አወንታዊ ሚና እንዳለው ከስምምነት የተደረሰበት ጉዳይ ሆኗል፡፡ በቀጣይ በየወሩ እየተገኛኙ ስራዎችን የጋራ በማድረግና በመደጋገፍ መስራት እንዳለባቸው መግባባት ላይ ተደርሶበታል፡፡

21/02/2020

በተጨማሪ በክላስተር ደረጃ የሚደረገው የክህሎት ውድድር ከየካቲት 13 -15/2012 ድረስ በኢንተር ፕራይዞች፣ በሰልጣኞች እና በአሠልጣኞች መካከል በተለያዩ የሥልጠና መስኮች የሚደረግ ሲሆን የውድድር ቦታ እንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ፡፡ ለተወዳዳሪዎቻችን መልካም ምኞታችንን እንገልጻለን፡፡
በተመሳሳይ ይህንን ዝግጅት አስመልክቶ ከቴክኒክና ሙያ ስትራቴጂ አንዱ የሆነው የትብብር ሥልጠናና ምዘና በክላስተር ደረጃ ለሠልጣኞች፣ለወላጆች፣ ለኢንተር ፕራይዝና ካምፓኒዎች ከየካቲት 19/2012 - 20/2012 ለሁለት ቀናት የሚቆይ የፓናል ውይይት መድረክ መዘጋጀቱን ከክፍሉ ከተገኘ መረጃ ለማወቅ ተችሏል፡፡
በተጨማሪ በክላስተር ደረጃ የሚገኙ ኢንተርፕራይዞች ምርታቸውን ፣ የመንግስትና የግል ኮሌጆች በሠልጣኞችና አሠልጣኖች የተሰሩ ቴክኖሎጂዎችን የሚያስተዋውቁበት መድረክ ከየካቲት 23-24/2012ዓ.ም በ4ኪሎ ሚኒሊክ መሰናድኦ ትምህርት ቤት ፊትለፊት የሚቀርብ በመሆኑ እንድትጎበኙ ተጋብዛችኋል፡፡

Photos from Entoto PTC.tms's post 21/02/2020

የቴክኒክና ሙያ ሳምንት
የቴክኒክና ሙያ ሳምንትን ታሳቢ ያደረጉ የተለያዩ ዝግጅቶች መካከል ቴክኖሎጂን መቅዳትና ማሻሻል ፣የክህሎት ውድድር ፣አክሽን ሪሰርች ተጠቃሽ መሆናቸውን የኢንደስትሪ ኤክስቴንሽን ም/ዲን አቶ ወንደሰን ለሜሳ ያብራራሉ ፡፡
የዝግጅቱ አንድ አካል የሆነው በኮሌጅ ደረጃ በኢንተር ፕራይዞች፣ በሰልጣኞች እና በአሠልጣኞች መካከል ክህሎት ውድድር ተከናውኗል፡፡

Photos from Entoto PTC.tms's post 21/02/2020

ምቹ የስራ አካባቢ
በእንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የሽሮ ሜዳ ካምፓስ የስራ ቦታዎችን ከማስዋብና ደህንነትን ከማስጠበቅ አንጻር በካምፓሱ የተለያዩ ቦታዎች ላይ በአሠልጣኞችና በሠልጣኞች ትብብር የስራ አካባቢን ምቹ ከማድረግ አኳያ ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል

Address


Gulele
Addis Ababa
1033