ኬር አውድ ፕሬስ Kere-Awed Press

የጉራጌን ባህል የማስተዋወቂያ እና በተለያዩ ጠቃሚ ጉዳዮ ዙሪ

20/11/2023

አዝናኝ ፈጠራ😁

20/11/2023

በሠላም ዋሉ!

Photos from DireTube's post 13/11/2023
06/11/2023

በጉራጌ ዞን ከ18ሺህ በላይ ህጻናት ለምግብ እጥረት መጋለጣቸው ተነገረ
።።።
የምግብ እጥረት ችግር የገጠማቸው ህጻናቱ በአሁኑ ሰዓት ለተለያዩ ተላላፊ በሽታዎች እየተጋለጡ ይገኛሉ ነው የተባለው።
የጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ አየለ ፈቀደ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፣ በዞኑ ለምግብ እጥረት ችግር የተጋለጡትን ህጻናት ልየታ በማድረግ ድጋፍ እየተደረገላቸው ይገኛል።
ከምግብ እጥረት ጋር በተያያዘም በአሁኑ ሰዓት 36 ህጻናት ለበሽታ መጋለጣቸውን ነው ሃላፊው የተናገሩት።
በዞኑ እየተስተዋሉ ያሉ የድንገተኛ ወረርሽኝ አደጋዎች በአፋጣኝ ለመከላከል ኮሚቴ ተቋቁሞ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
በምግብ እጥረት ምክንያት ትውልዱ የከፋ ችግር ላይ እንዳይወድቅ ሁሉም ድጋፍ እንዲያደርግም ጠይቀዋል።
በዞኑ በአሁን ሰዓት ድንገተኛ በሽታዎች፣ የኮሌራና የወባ በሽታዎች እና በስነ ምግብ እጥረት ሊከሰቱ የሚችሉ በሽታዎች ለመከላከል ሰፊ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ሃላፊው ተናግረዋል።
ምንጭ፡- ETHIO FM 107.8

Photos from ኬር አውድ ፕሬስ Kere-Awed Press's post 16/10/2023

ምድረ-ከብድ (ከባድ ስፍራ)
***
በየዓመቱ ጥቅምት 5 በርካታ ቁጥር ያላቸው የኦሮቶዶክስ ዕምነት ተከታዮች ወደ ምድረ ከብድ አቦ ገዳም መንፈሳዊ ጉዞ በማድረግ የአቡነ መንፈስ ቅዱስ ዓመታዊ ክብረ በዓል ይታደማሉ፡፡ ይህ ጥንታዊ ገዳም በጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ ከአዲስ አበባ በ122 ኪ.ሜትር ርቀት ላይ ከጢያ ትክል ድንጋይ መካነ ቅርስ አቅራቢያ ይገኛል፡፡ ጻድቁ አቡነ መንፈስ ቅዱስ በጾምና ፀሎት መንፈሳዊ ተጋድሎ አድርገው በዚሁ ገዳሙ እንዳረፉ የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ፡፡

26/09/2023

#በደምሰው በንቲ

25/09/2023
Photos from ኬር አውድ ፕሬስ Kere-Awed Press's post 24/09/2023

የአረቅጥ ሀይቅ የቱሪስት መዳረሻነት የሚጨምር ሎጅ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ
***
በጉራጌ ዞን አረቅጥ ሀይቅን ለመጎብኘት የሚመጡ ቱሪስቶችን አገልግሎት ለመስጠት ታቅዶ የተገነባው ሙሉወርቅ ሎጅ ተመረቀ።
ሎጁ 221 ሚሊዮን ብር ፈሰስ ተደርጎበታል።

22/09/2023

በወረዳው ከ14 ሄክታር በላይ ሰብል በግሪሳ ወፍ መጠቃቱ ተገለፀ
****
የሶዶ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት እንዳስታወቀው በወረዳው በሰባት ቀበሌያት 14.5 ሄክታር ሰብል በግሪሳ ወፍ ተጠቅቷል።

15/09/2023

''ሴራና'' ፊልም በሴራና አዳራሽ ሊመረቅ ነው
፡፡፡፡፡፡
የጉራጌ ባህል ላይ ትኩረቱን ያደረገው ''ሴራና'' የተሰኘው ፊልም በቡታጅራ ከተማ ሴራና አዳራሽ መስከረም 5 2016ዓ.ም ይመረቃል።
የፊልሙ ደራሲ ዘሪሁን ደነቀ እንደሆነ ከዘቢደር ቲዩብ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።

//ውሎ// "ከአሜሪካ ተመልሼ ሀገሬ ላይ ወጣት ገበሬ ሆኛለሁ" በረከት የምሩ /እሁድን በኢቢኤስ/ 15/09/2023

https://www.youtube.com/watch?v=nxlWASxJRRo

//ውሎ// "ከአሜሪካ ተመልሼ ሀገሬ ላይ ወጣት ገበሬ ሆኛለሁ" በረከት የምሩ /እሁድን በኢቢኤስ/ An infotainment program on Sunday afternoon with EBS’ own Asfaw Meshesha , Mekdes Debesay, Lula Gezu, Kalkidan Girma, Lea Samuel & Tinsae Berhane . It includ...

30/08/2023

የእኛ ሰው በቡዳፔስት ሃንጋሪ

25/08/2023

ተፈጥሮን የመንከባከብ ባህል ያለው ህዝብ!
Not only impressive, but it also highlights a dedication to environmental conservation.

24/08/2023

አትሌት ጥላሁን ሀይሌ በቡዳፔስቱ የአትሌቲክስ ውድድር ያለመሰለፉ ብዙዎችን እያነጋገረ ነው
….
አትሌት ጥላሁን በ5 ሺ ሜትር ወንዶች ባስመዘገበው ምርጥ ሰአት ኢትዮጵያን እንዲወክል ወደ ሀንጋሪ ቡዳፔስት በውድድሩ እንዳይሳተፍ ተደርጓል።
በ10 ሺ ሜትር ተካፍሎ አራተኛ የወጣውን በሪሁ አረጋዊ በድጋሚ ለማሳተፍ ሲባል በ5 ሺ ሜትር ወንዶች ጥላሁን ሀይሌ እንዲቀነስ መደረጉ የስፖርት ቤተሰቡን አሳዝኗል።

Photos from ኬር አውድ ፕሬስ Kere-Awed Press's post 11/08/2023

ጎጎት ለጉራጌ አንድነት እና ፍትሕ ፓርቲ የጉራጌ የክልል አደረጃጀት ጥያቄ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጠው ለፌዴሬሽን ምክር ቤት አቤቱታ አስገባ
የአቤቱታው ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

11/08/2023

ዳሙ ገነት

ሃምሳ ብር ህይወት ቀጠፈ | DW | 24.07.2023 28/07/2023

ሃምሳ ብር ህይወት ቀጠፈ
DW

ሃምሳ ብር ህይወት ቀጠፈ | DW | 24.07.2023 "ጥቂት እንደተጓዝን ተሸከርካሪውን በማቆም እኔም ሆንኩ ሌሎች መንገደኞች ደንግጠን ወረደን መሮጥ ጀመርን ፡፡ በዚህ ሁኔታ ውስጥ እሱን በጥይት መትተው ጣሉት"

Photos from ኬር አውድ ፕሬስ Kere-Awed Press's post 25/07/2023

ጉቦ የለመዱት ትራፊክ ፖሊሶች ነፍስ ወደ ማጥፋት ተሽጋገሩ
፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ባለፈው ዓርብ (ሐምሌ 14/2015 ዓ.ም) ተሳፋሪ ጭኖ ከአዲስ አበባ ወደ ቡታጅራ በመጓዝ ላይ እያለ በትራፊክ ፖሊስ አባላት የተጠየቀውን ጉቦ አልሰጥም በማለቱ የ33 ዓመቱ ሳሙኤል መረተ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን የትራፊክ ፖሊስ አባላት በጥይት ተደብድቦ ተገደለ፡፡ የሟች ቤተሰቦች ፍትህ እየጠየቁ ነው፡፡
ዶቼቬለ እንደዘገበው ተጠርጣሪዎቹ በህግ ቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

19/12/2022

የኦነግ ሽኔ ታጣቂዎች ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኘው የጉራጌ ዞን ውስጥ ሰርገው ገብተው ጥቃት መፈጸም እንደጀመሩ የመረጃ ምንጮቻችን ጠቁመዋል
፡፡፡፡፡፡፡፡
የኦነግ ሽኔ ታጣቂዎች በጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ ሱተን እና አማውቴ ላሊጌ ተብለው የሚጠሩ አካባቢዎች እንዲሁም ወልቂጤ ሰርገው ገብተው የጸጥታ ኃይሎች ላይ እና ሰላማዊ ሰዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት መፈጸማቸው የመረጃ ምንጮቻችን ያመለክታሉ፡፡
የቀንድ ከብት የጫነ ተሽከርካሪ አስቁመው ተሽከርካሪውን እንዳቃጠሉና በተጠቀሱት አካባቢዎች ቅኝት ሲያደርግ የነበረ የጸጥታ ኃይል የጫን ተሽከርካሪ ላይም ጥቃት እንደፈጸሙ ተጠቁሞዋል፡፡ በጥቃቱ ምን ያህል ሰው እንደተጎዳ የመረጃ ምንጮቻችን ያሉት ነገር የለም፡፡
ታጣቂዎቹ በዞን ውስጥ መመሸጋቸውም ተገለጾአል፡፡
Photo credit: Ethiopia Insight

16/12/2022

[የትራንስፖርት ታሪፍ ጉዳይ]
አንድ ሰው ከአዲስ አበባ ጢያ-ሱተን-ቡኢ-ኬላ መሄድ ቢፈልግ የቡታጅራን ሂሳብ ከፍሎ እንዲወርድ ይደረጋል።
ይህ አነስተኛ የገቢ አቅም ላለው ሰው ከባድ ነው።
ለ80 ኪሎ ሜትር 250 ብር?
ቢያንስ ቡኢ ወይ ኬላ ከተማ የራሳቸው ታሪፍ (መስፈርቱን የሚያሟሉ ይመስለኛል ) ሊወጣላቸው ይገባል።
: S**o Lema

16/12/2022

``ባከቶ፣
ይበሎት ዬከቶ``
ማለት ምን ማለት ነው?

Photos from ኬር አውድ ፕሬስ Kere-Awed Press's post 05/12/2022

ት/ቤቱ ከ300ሺህ ብር በላይ ግምት ያላቸው የተለያዩ ማጣቀሻ መጻህፍት እና ኮምፒውተር ድጋፍ ተደረገለት
:::::::
የሶዶ ቡኢ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የቀድሞ ተማሪዎችና ወዳጆች ህብረት የአዲስ አበባ ኮሚቴ አባላት ከ100ሺህ ብር በላይ ግምት ያላቸው ማጣቀሻ መጻሕፍት እና በ200ሺህ ብር 15 DELL Core I3 ኮምፒውተር በተሰበሰበው ገንዘብ ግዢ በመፈጸም ለሶዶ ቡኢ ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት አስረከበዋል።

01/12/2022

አማውቴ!
ታዳጊ ማዘጋጃ ቤት እንዲሆን ከተፈቀደ ወዲህ የልማት ጅምሮቹ የሚበረታታ ነው፡፡ ቦታው ለማታውቁት ዳዮ አቦ ቤተክርስቲያን አካባቢ ይገኛል፡፡ ከአዲስ አበባ በቀጥታ የህዝብ ትራንስፖርት የሚመደብለት በተሬ ከተማ ወይም በጢያ ከተማ በኩል ከአዲስ አበባ የሚያገናኝ መንገድ አለው፡፡

Photos from ኬር አውድ ፕሬስ Kere-Awed Press's post 27/11/2022

የክስታኒኛ መዝገበ-ቃላት መግዛት ይፈልጋሉ?!
።።።።።፡።።።
የክስታኒኛ ቋንቋን ለማሳደግ ከተሰሩ ስራዎች ውስጥ ዋነኛው የመዝገበ ቃላት ዝግጅት ነው። መዝገበ ቃላቱን ያልገዛችሁ በመግዛት ለቋንቋችን ዕድገት አስተዋጽኦ ብታደርጉ መልካም ነው። የት እንደሚሸጥ በ0938407116 ደውላችሁ መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ።

23/11/2022

ደስታ ጋርመንት የሚባል ድርጅት 340 ሙሉ የስፓርት ትጥቅ ለጢያ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ድጋፍ አደረገ::
# Gordena Media

የዎስጠደ-የሙሽሪት ሽኝትና በቀጣይ ለትዳር የሚታጭ ሰው ማብሰሪያ ስነስርዓት 21/11/2022

የዎስጠደ
ያማተ…

የዎስጠደ-የሙሽሪት ሽኝትና በቀጣይ ለትዳር የሚታጭ ሰው ማብሰሪያ ስነስርዓት “የዎስጠደ” በክስታኔ ጉራጌ ዘንድ የሠርግ ዕለት ሙሽሪት ከተሸኘች በኋላ የሚከናወን ስነስርዓት ነው፡፡ ሴቶች የዛፍ ቅጠል ይዘው “የዎሰጠደ ያማተ” እያሉ ጨፍረው ስጦታ የሚጠይቁበት .....

08/11/2022

ስራ መስራት ብቻ ሳይሆን አካባቢያቸውንም መንከባከብ ያውቁበታል-My ጉራንስ ፒውፕል

30/10/2022

የእርዳታ ጥሪ🚨
🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ወ/ሮ ሉሊት ጌታሁን ትባላለች፤ በቡታጅራ ከተማ የሲቪል ሰርቪስ ፅ/ቤት ሰራተኛ ነች።
የማህፀን ካንሰር ስላጋጠማት በአስቸኳይ የህክምና ክትትል እንድታደርግ በሀኪሞቿ ተነግሯታል።
ወ/ሮ ሉሊት የህክምናውን ወጪ የመሸፈን አቅም ስለሌላት የእኛ ድጋፍ ትሻለች።
ሉሊትን መደገፍ ለምትፈልጉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት
1000056870095 ሉሊት ጌታሁን ወይም በእህቷ
የዳሽን ባንክ አካውንት 5026903600006 ጥበቧ ጌታሁን ገንዘብ ማስተላለፍ ትችላላችሁ።

30/10/2022

ውቢቷ ቡታጅራ

23/10/2022

ባህላዊ እና ዘመናዊ የቤት አሰራር የተጣመሩበት

15/10/2022

ምድረከብድ

15/10/2022

ምድረከብድ የተገኛችሁ የኬርአውድ ቤተሰቦች የዛሬው የአቡዬ ዓመታዊ ክብረበዓል የሚገልጹ ምስሎች ካላችሁ በአስተያየት መስጫው ላይ አስቀምጡልን።

ጉዞ ወደ ክስታኔዎች መንደር 14/10/2022

https://www.youtube.com/watch?v=GOo4GeJH0iI

ጉዞ ወደ ክስታኔዎች መንደር አጭር ቆይታ በጉራጌዎች መንደር-መስቀል በጉራጌ -አዳብና

13/10/2022

[እሰይ ነጋ]
ፕሮፌሰር ብርሀኑ ላይ ትንሽዬ ቂም ቋጥሬ ነበር፡፡ ይህም ከተለየ የፖለቲካ አመለካከት የመነጨ ወይም ከገዢው ፓርቲ ጋር አብሮ በመስራቱ ምክኒያት ሳይሆን፡~
ታስታውሱ እንደሆን ለውጡ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ወደ ሀገር ቤት ገብተው ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል እንዲያካሂዱ ሲፈቅድና ግንቦት ሰባትም በዚህ ጥሪ መሰረት ወደ ሀገር ቤት ሲገባ ብርሀኑ ነጋ በቦሌ አየር ማረፊያ በተደረገላቸው አቀባበል አንድ ልቤን የነካ ንግግር ለጋዜጠኞች ተናግረው ነበር፡፡ “ከዚህ በኋላ በሰፊው መስራት የምፈልገው በወጣቱ ላይ ነው፡፡ ወጣቱ ሞራሉ ላሽቋል፣ ስነምግባር ጠፍቷል፣ የሀገር ፍቅር የሌለው ሀላፊነት የማይሰማው ሆኗል፡፡ ስለዚህ በወጣቱ ላይ አተኩሬ መስራት እፈልጋለሁ” ሲሉ ተናግረው ነበር፡፡
እውነት ልንገራችሁ በዚያ በፖለቲካ ወሬዎች ብቻ በተጨናነቀ ወቅት፣ በዚያ በዘርና በብሄር ክፍፍሉ እንደ ብረት ግሎ መቅለጥ በጀመረበት ወቅት ብርሀኑ ነጋ አንድ የሀገር ስብራት አንጓ መዞ “ወጣቱን ማከም እፈልጋለሁ” ብሎ ሲናገር ፍጹም የተለየ ስሜት ነበር የተሰማኝ፡፡ ስለ ክልል፣ ስለ ብሄር፣ ስለ መገንጠል፣ ስለ ምርጫና ስልጣን እየተፎከረ ወደ ሀገር በሚገባበት በዚያ የእብጠት ዘመን ይህን ታላቅ አላማ አንግቤ ነው ወደ ሀገር የተመለስኩት ሲል ስሰማው ነፍሴ በሀሴት ለምልማ ነበር፡፡
ይሁንና ቀን እያለፈ ቀን እየተተካ ሲሄድ ፕሮፌሰር ብርሀኑን በገባው ቃል ዙሪያ ፈልጌ አጣሁት፡፡ ይህንንም ይዤ በየጊዜው እወቅሰው ገባሁ፡፡ ..........
እነሆ ዘንድሮ ቃሉን በተግባር ተርጉሞ አየሁት፡፡ “ሌብነት እስካልተያዙ ድረስ ስራ ነው” የሚል መሪ በነበረባት ሀገር ተወልደው ያደጉ ልጆች ስርቆትን እንደ ስራ እያሰቡ የፈተናን ስርቆት እንደ መለማመጃ ቆጥረውት ያዳበሩትን የሞራል ዝቅጠት አፈራርሶ ልጆች በራሳቸው ተማምነው መስራትን፣ አውቆ መፈተንን፣ በእውቀት መመዘንን፣ በሁለት እግር መቆምን እንዲያውቁ ለማስቻል ብዙ የተባለለትን የብሄራዊ ፈተና አዘምኖ ለትውልዱ ደርሶ አየሁ፡፡ እነሆ ብርሀኑ ነጋ ! እሰይ ነጋ!!!
Tadele

Want your business to be the top-listed Advertising & Marketing Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Videos (show all)

ዛሬ የአሜሪካ ኤምባሲ በር ላይ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ👉ቪዲዮውን ይመልከቱ
https://www.youtube.com/watch?v=wu-KnTGkKN4&t=126s
ዝ
Kids song
ዝ!
እንሾሽላ
COVID_19
Corona privention
corona
Alemayehu Wosen
Documentary

Website

Address


Addis Ababa
Other Social Media Agencies in Addis Ababa (show all)
Kida Digital Solutions Kida Digital Solutions
Addis Ababa, 1874

Kida Digital Solutions is a full-service digital marketing agency.

Dubakko Dubakko
Addis Ababa

welcome to our official page. In this page you will learn more about content marketing and advertisi

እፎይ Advertising Ethiopia እፎይ Advertising Ethiopia
Bole
Addis Ababa

ሽያጭዎን ለማሳደግ ከእኛ ጋር ይስሩ፡፡ ለመሸጥ የፈለጉትን እቃ ወይም አገልግልዎት እኛ ለትክክለኛ ደምበኛ በተመጣጣኝ ዋጋ እናስተዋዉቅልዎታለን ፡፡

WDO Kolfee/Kolfe OUA WDO Kolfee/Kolfe OUA
Ethiopia � Hachalu Street
Addis Ababa

Volunteers

Tesloach Riek Jikany Tesloach Riek Jikany
Addis Ababa, 1000

https://youtube.com/channel/UCwI5ou16JhT7-ew--eaB0Pw

Sololo Intercept Sololo Intercept
Addis Ababa

Social media is the ultimate equalizer. It gives a voice and a platform to anyone willing to engage. Amy Jo Martin Amy Jo Martin

Ethioline Ethioline
Bole Roads
Addis Ababa, 251

ኢትዮላይን

Jossy Man Jossy Man
Addis Ababa

Speak the Truth

Ethio Boost Marketing Ethio Boost Marketing
Addis Ababa
Addis Ababa, 1000

A leading digital marketing agency in Ethiopia, dedicated to helping small businesses and individuals

EwketJobs EwketJobs
Addis Ababa

Pluto Agency Pluto Agency
Addis Ababa

Social Media Marketing Agency -Facebook,IG Ads -Youtube,tiktok ads -Social media automation -web devt