Addis Ababa Youth Federation

Addis Ababa Youth Federation

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Addis Ababa Youth Federation, Charitable organisation, janmeda, Addis Ababa.

Photos from Addis Ababa Youth Federation's post 22/07/2022

# #የወጣቶች ፌዴሬሽን አረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ተካሄደ #
የ4ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር ወሰን ተሻጋሪ በለገጣፎ ተጀመረ በቀጣይም ይቀጥላል።
በዛሬው መርሀግብር የአዲስ አበባ ወጣቶች ፤የለገጣፎ ወጣቶች ከኦሮሚያና አዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ጋር በመተባበር፣በማስተባበር ለመትከል ተችሏል።
በቀጣይነት ወሰን ተሸጋሪ የችግኝ ለመትከል ቅድመ ዝግጅቶች እየተደረገ ነው።
✍️ወጣቶች ፌዴሬሽን
🗒15/11/2014
አዲስ አበባ

12/03/2021

ከተማ አቀፍ የአከባባ ፅዳት ፕሮግራም ላይ ወጣቶች በየአከባቢያቸው መሳተፍቸው የሚመሰገን መሆኑን ተገለፀ።

12/03/2021

መልካም ቀን

Photos from Addis Ababa Youth Federation's post 06/03/2021

እኔ አከባቢዬን በማፅዳት የከተማዬ ውበት አምባሳደር ነኝ በሚል ከተማ አቀፍ የፅዳት
ንቅናቄ ተጀመረ።
ወጣቶች አከባቢያቸውን በማፅዳት ሀላፊነታቸውን
በአግባቡ እንዲወጡ ጥሪ ቀርቦላቸዋል።

መልካም የስራ ቀን ይሁን

Photos from Addis Ababa Youth Federation's post 05/03/2021
Photos from Addis Ababa Youth Federation's post 06/12/2020

ዜና ወጣቶች ፌዴሬሽን
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባዘጋጀው የብሔር ብሔረሰቦች በዓል ላይ የከተማው ወጣቶች በክብር እንግድነት ለተገኙት ለክቡር አቶ ሙስጠፌ የሱማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዲሁም ለከተማ አስተዳደራችን ም/ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የአጋርነት ስጦታ አበርክተዋል።

30/11/2020

የአዲስ አበባ ወጣቶች ፌዴሬሽን የዕውቅና ሰርተፍኬት

26/11/2020

መልካም የስራ ጊዜ ተመኘን
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወጣቶችና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ ኃላፊ
ባጫ ጅሬኛ አዲሱ

Photos from Addis Ababa Youth Federation's post 26/11/2020

መልካም የስራ ዘመን ይሁንልክ ወጣት
ጥበብ በቀለ የአዲስ አበባ ወጣቶችና
በጎ ፈቃድ ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊና የአዲስ
አበባ ወጣቶች ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት።

Photos from Addis Ababa Youth Federation's post 24/10/2020

የአዲስ አበባ ወጣቶች ፌዴሬሽን የታላቁን የኢትዮጵያን ህዳሴ ግድብ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ።

Photos from Addis Ababa Youth Federation's post 09/08/2020

የአርንጓዴ አሻራ ቀን በከተማችን ወጣቶች

17/06/2020

የአዲስ አበባ ወጣቶች ፌዴሬሽን ዜና
የአዲስ አበባ ወጣቶች ፌዴሬሽን በዘንድሮ የክረምት በጎ ፈቃድ ፕሮግራም የተለያዩ ተግባራት እንደሚከናወንና ገልጿል

Photos from Addis Ababa Youth Federation's post 10/06/2020

ምግባችን ከጓሮአችን

30/05/2020

መዘናጋት ይቁም እራሶን ከወረሽኑ ከተከላከሉ ሌላውን ማዳን ይቻላል።

Photos from Addis Ababa Youth Federation's post 30/04/2020

ዛሬም ልገሳው ቀጥሏል

ዛሬም የስፖርት ማህበረሰብ የደም ልገሳ መርሃ ግብር በስፖርት ኮሚሽን ቅጥር ግቢ ወስጥ እያካሄዱ ይገኛሉ፡፡
የስፖርት ማህበረሰቡ ደም በመለገስ የማይተካውን የሰው ህይወት እንታደግ በማለት የተደራጀ ተሳትፎ በማድረግ ላይ ናቸው ፡፡
ዜና ፌዴሬሽን

Photos from Addis Ababa Youth Federation's post 29/04/2020

የደም ልገሳ ዛሬም ቀጥሎ ውሎል
የመንግስት ሰራተኞች የደም ልገሳ መርሀ ግብር ዛሬም ቀጥሎ ውሎል፡፡ የበጋ በጎ ፍቃድ ከ15000 በላይ ደም ለመሰብሰብ በዕቅድ እየተሰራ ይገኛል፡፡ ነገ ደግሞ የስፖርት ማህበረሰብ ቀን በደማቅ ሁኔታ ከ5000 በላይ የደም ልገሳውን ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ሁላችንም በጎነት በተግባርም እናሳይ የዛሬው መልክታችን ነው፡፡
ዜና ፌዴሬሽን

29/04/2020

በጃን ሜዳ አካባቢ ተፈጥሮ በነበረው ግርግር በስድስት ሰዎች ላይ ቀላል እንዲሁም በአንድ ግለሰብ ላይ መካከለኛ ጉዳት መድረሱንና ጉዳቱ የተከሰተው በመገፋፋት እንደሆነ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ በዕለቱ ግብይቱ በመደበኛ ሁኔታ መካሄዱን ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡
***
በሀገራችን የተከሰተውን የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ ለመከላከል እንዲረዳ ታስቦ ፒያሳ አትክልት ተራ የነበረው የአትክልት እና የፍራፍሬ ግብይት ወደ ጃን-ሜዳ እንዲዛወር መደረጉ ይታወሳል፡፡

በጃን ሜዳ የሚደረገው ግብይት ለኮሮና ቫይረስ ስርጭት አጋላጭ እንዳይሆን ልዩ ልዩ ተግባራት የተከናወኑ ሲሆን በተለይ የንግዱ ስርዓት ህጋዊ መንገዱን ተከትሎ እንዲከናወን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፤ ከደንብ ማስከበር አገልግሎት እና ከሌሎች ተቋማት ጋር በጋራ እየሰራ ይገኛል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳ ለሚያዚያ 21 ቀን 2012 ዓ/ም ጠዋት ግብይቱ በመከናወን ላይ እንዳለ ከጠዋቱ 2፡ 30 አንዳንድ ግለሰቦች ባስነሱት ሁከት በተፈጠረ መገፋፋት ስድስት ሰዎች ላይ ቀላል እንዲሁም በአንድ ግለሰብ ላይ መካከለኛ ጉዳት ማጋጠሙን በየካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የፈረንሳይ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ሰለሞን ገ/ማርያም ገልፀዋል፡፡ ከተጎጂዎቹ መካካል ስድስቱ ህክምና አግኝተው ከሆስፒታሉ መውጣታቸውንና አንደኛው ተጎጂ ህክምናውን እየተከታተለ እንደሚገኝ ከኃላፊው ገለፃ መረዳት ተችሏል፡፡
በአካባቢው በተፈጠረው ግርግር ሁለት ሰዎች ሞተዋል ተብሎ በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን የተሰራጨው መረጃ ሐሰት መሆኑን ምክትል ኮማንደሩ ተናግረው ፖሊስ አጋጥሞ የነበረውን እረብሻ በቀላሉ ተቆጣጥሮ ግብይቱ እንዲቀጥል ማድረጉን ጨምረው ገልፀዋል፡፡
ዘገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ

Photos from Addis Ababa Youth Federation's post 28/04/2020

ዜና ወጣቶች
የደም ልገሳ ፕሮግራም

በጉለሌ ክፍለ ከተማ አመራሮች የደም ልገሳ አደረጉ
በደም ልገሳ መርሃ ግብሩ የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚን ጨምሮ "እኔም ለወገኔ" በሚል የፓርቲ ጽ/ቤት አመራሮች ደም የለገሱ ሲሆን በደም ልገሳ መርሃ ግብሩ እስከ ታችኛው መዋቅር የሚቀጥልና ከ10 ሺህ በላይ የማህበረሰብ አባላት ይሳተፋሉ ተብሌ ይገመታል።

26/04/2020

በኢትዮጵያ ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 41 ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 18፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገ 957 የላቦራቶሪ ምርመራ አንድ ሰው የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘበት የኢፌዴሪ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለፁ።

ሚኒስትሯ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 123 መድረሱን በፌስቡክ ገፀቸው ላይ አስታውቀዋል።

ቫይረሱ የተገኘበት ግለሰብ ከፑንትላንድ የተመለሰና በአስገዳጅ የለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበረ 30 ዓመት የጅግጅጋ ነዋሪ ነው።

በትናንትናው እለት 12 ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ማገገማቸውንም ነው ያመለከቱት።

ይህንንም ተከትሎ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 41 ደርሷል።

Photos from Addis Ababa Youth Federation's post 26/04/2020

የሸገር ዳቦ ፋብሪካ ያለበትን ደረጃ ከካቢኔ አባላት ጋር ተመልክተናል፡፡ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ከውጪ የሚገቡ እቃዎች ጋር በታሰበው ወቅት ለማስመጣት ፈታኝ ሁኔታዎች ቢገጥሙንም የማሽን ተከላው በሚያስገርም ፍጥነት እየተጠናቀቀ መሆኑን ታዝቤአለው፡፡

ለምርት የሚሆን የግብዓት ዝግጅት የተጠናቀቀ ሲሆን የተወሰኑ ማሽኖች ወደሀገር ውስጥ ከገቡ በኋላ ፋብሪካው ወደስራ የሚገባ ይሆናል፡፡

ስራውን የሚያስጀምሩና ለሀገር ውስጥ ባለሙያዎች ስልጠና የሚሰጡ ባለሙያዎች ወደሀገር ውስጥ መምጣት ባይችሉም "በኦን ላይን " ስልጠና በመስጠት ብቁ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎችን ማፍራት ተችሏል፡፡

በኢትዮጵያ የመገንባት አቅም 3 አመታት ይወስድ የነበረ ፋብሪካ በወራት ውስጥ ለማጠናቀቅ ጫፍ ላይ በመድረሳችንና በሂደቱም ብቁ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎችን በማፍራታችን ኩራት ተሰምቶኛል!

22/04/2020

“የእንቅስቃሴን ገደብ ማንሳቱ ቀስ በቀስ መሆን አለበት” - የዓለም ጤና ድርጅት

በርካታ አገራት የእንቅስቃሴ ገደባቸውን በግማሽ አሊያም ሙሉ ለሙሉ ማንሳታቸውን ተከትሎ የዓለም ጤና ድርጅት እንዲህ ያሉ ውሳኔዎች ቀስ በቀስ መሆን እንደሚገባቸው አሳሰበ፡፡

ድርጅቱ የአገራት ውሳኔ ወደ ሁለተኛ ዙር የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ ሊያመራ ይችላል ብሏል፡፡

የምዕራብ ፓስፊክ ሪጅናል ዳይሬክተር ታከሺ ካሳይ “ቢያንስ ክትባት አሊያም ውጤታማ የሆነ ህክምና እስከሚገኝ ድረስ እየተከተልነው ያለውን ሂደት አዲሱ የተለመደ ተግባራችን መሆን ይገባዋል” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

አክለውም የተጣሉ ገደቦችን ለማለዘብ አሊያም ለማንሳት የሚያስብ ማንኛውም መንግሥት ቀጣይነት ባለው ቁጥጥር እና ደረጃ በደረጃ ማድረግ ይገባቸዋል ብለዋል፡፡

ግለሰብም ሆነ ማህበረሰብ ለአዲሱ የኑሮ ዘይቤም ዝግጁ መሆን አለባቸው ሲሉ ዳይሬክተሩ አሳስበዋል፡፡

እንደ ጃፓንና ሲንጋፖር ያሉ አገራት ወረርሽኙን ተቆጣጠርነው ካሉ በኋላ አዳዲስ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎችን እያገኙ በመሆኑ በሁለተኛ ዙር የኮቪድ- 19 ወረርሽኝ እንዳይጠቁ ስጋት ፈጥሯል፡፡

ምንጭ፡-BBC

Photos from Addis Ababa Youth Federation's post 22/04/2020

የጠቅላይ ሚኒስቴር የደም መለገስ ጥሪ

ተምሳሌት መሆን እንደዚህ ነው።

Photos from Addis Ababa Youth Federation's post 21/04/2020

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ለአዲስ አበባ ወጣቶች ፌዴሬሽን 6የሙቀት መለኪያ እና የተለያዩ ፈሳሽ ሳሙና አልኮን አበረከቱ።
ይህ የሆነው ወጣቶች በጃንሜዳ የግብይት ቦታ አካላዊ መራራቅን ከማስተማራቸው በዘለለ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የሙቀት መለኪያን የታገዘ
ምርመራ በበጎ ፈቃደኛ ወጣት ባለሙያዎች ስራ
እንዲያግዝ የታለመ ሲሆን እንዲ አይነት ድጋፍ
ከባለድርሻ አካላት ሊቀጥል ይገባል።

ዜና ወጣቶች ፌዴሬሽን

Photos from Addis Ababa Youth Federation's post 19/04/2020

#ኮቪድ19 ለተገኘባቸው የሕክምና ማዕከል እንዲሆን፣ የሚሊኒየም አዳራሽ በብቁ የሀገራችን ጤና ባለሞያዎች አማካኝነት ተዘጋጅቷል። ዛሬ ጠዋት በነበረኝ ጉብኝት፣ ሥፍራውን በፍጥነት ወደ ማከሚያ ሆስፒታልነት ለመለወጥ መቻላቸውን ተመልክቼ ተደንቄያለሁ። የመጨረሻው አስከፊ ሁኔታ ቢደርስብን ለመቋቋም እንዲቻለን፣ ሰፋፊ ሥፍራዎችን በተመሳሳይ መልኩ ማዘጋጀት እንቀጥላለን።

Galmi Barkumee ogeessota fayyaa biyya keenyaa gahuumsa qabaniin namoota COVID-19 n qabamaniif giddugala wal'ansaa akka ta'uttu qophaa'eera. Daawwannaan har'a ganama godheen bakkicha ariitiidhaan gara bakka wal'aansaa hospitaalaatti jijjiiruu danda'uu isaanii argee dinqisiiffadheera. Haalli badaa iini dhumaa yoo nu mudate dandamachuu akka dandeenyu bakkeewwan babal'aa walfakkaatu qopheessu itti fufna.

This morning I visited the treatment center recently setup within Millenium Hall by our very able and capable medical professionals. I am pleased at how quickly the site was transformed to a hospital setup. The preparedness for any extreme eventualities in similar large spaces will continue.
PM DR Abiy Ahmed Ali

Photos from Addis Ababa Youth Federation's post 19/04/2020

የመዲናችን ወጣት #ባለሀብቶች እና የከተማችን ወጣት በጐ ፍቃደኞች እናመሰግናችሃለን
#በናተ ቅን አሳቢነትና #ድጋፍ በዛሬው እለት በክርስትና እምነት ተከታዬች ዘንድ በደማቅ ሁኔታ የሚከበረውን የትንሳኤ በአል ከ1700 በላይ የሚሆኑ አቅመ ደካሞች፤አረጋውያን እና ወላጅ አልባ ህጻናት የተለያዩ በአሉን በደማቅ ሁኔታ እንዲያከብሩ የሚረዳቸውን ለበዓል መዋያ በከተማ አስተዳደሩ አማካኝነት የተሰበሰብትን ከ40 በላይ የሚሆኑ በሬዎች በበጐ ፍቃደኛ ባለሀብቶች አማካኝነት ለሁሉም ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች በየመንደሩ በመዘዋወር ቁሳቁሶችን #ስጋ፣ #ዶሮ፤ #ጤፍ፤ #ሽንኩርት፤ #ገንዘብ እና #ዘይት ድጋፍ የተደረገ ሲሆን ፡፡
ድጋፉን ካደረጉ ወጣት ባለሀብቶች መካከል
**1ኛ የጊዬን ባስ ባለቤት አቶ ንዋይ
**2ተኛ ለምለም ተስፉ አስመጪ እና ላኪ
**3ተኛ ሄርሞን ሀጐስ
**4ተኛ ኤርሚያስ ማስታውቂያ
**5ተኛ ቢኒያም ማስታወቂያ ሲሆኑ በድጋፍ ወቅትም እንደገለጹት ወላጅ አልባ እና አቅመደ ካሞችን ለመርዳት ሁልጊዜ ከጐናችን መሆናቸውንም አረጋግጠዋል ለቀና ድጋፍችሁም ከልብ እናመሰግናለን ፡፡

Photos from Addis Ababa Youth Federation's post 13/04/2020

በአዲስ አበባ ከተማ ለ400 ሺህ ነዋሪዎች የምግብ ፍጆታ ስርጭት ሊጀመር ነው ስርጭቱ የሚከናወነው የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር በሚወሰደው እርምጃ ዜጎች ለጉዳት እንዳይዳረጉ ነው ተብሏል።የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር Takele Uma Banti ዛሬ በቂርቆስና በልደታ ክፍለ ከተሞች የምግብ ባንኮች ለስርጭቱ እያደረጉት ያለውን ዝግጅት ጎብኝተዋል። በባንኮቹ የተከማቸው የምግብ ፍጆታም እስካሁን ለተለዩት ከ400 ሺህ በላይ ነዋሪዎች ከመጪው ሐሙስ ጀምሮ ይሰራጫል ተብሏል።

ምንጭ: ኢዜአ

12/04/2020

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በአዋጅ ቁጥር 3/2012 አንቀፅ 4/1/ መሰረት የሚከተለውን ማስፈጸሚያ ደንብ አውጥቷል::

1. አጭር ርእስ

ይህ ደንብ ‘‘ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 3/2012 ማስፈፀሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ
ቁጥር-----/2012’’ ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል::

2. ትርጓሜ

ለዚህ ደንብ አላማ፡-

1. ‘‘አዋጅ’’ ማለት የኮቪድ-19 ሥርጭትን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠር እና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ የወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 3/2012 ነው፤
2. ‘‘የሚኒስትሮች ኮሚቴ’’ ማለት በዚህ ደንብ አንቀፅ 5 የተቋቋመው ኮሚቴ ማለት ሲሆን እንደአስፈላጊነቱ፣ በኮሚቴው የሚቋቋሙና ውክልና የሚሰጣቸው በፌዴራል፣ በክልሎች፣ በከተማና በወረዳ ደረጃ ያሉ ንዑሳን ኮሚቴዎችንም ያካትታል፤
3. ‘‘ስብሰባ’’ ማለት ማንኛውንም ተግባር ለመፈጸም፣ ለመነጋገር፣ ለመወያየት ወይም መሰል ተግባራትን ለማከናወን የአንድ ቤተሰብ አባላት ከሆኑ ውጪ አራትና ከዚያ በላይ ሆኖ በአንድ ቦታ በአካል መገኘት ነው፤
4. "ኳራንታይን" ማለት በኮቪድ-19 ተይዘዋል ተብለው የሚጠረጠሩ ሰዎችን በቫይረሱ መያዝ አለመያዛቸው እስኪረጋገጥ ድረስ በተለየ ቦታ እንዲቆዩ ማድረግ ነው፤
5. "ለይቶ ማቆየት" ማለት በኮቪድ-19 መያዙ የተረጋገጠ ሰው ቫይረሱን ወደ ሌሎች ሰዎች እንዳያስተላልፍ ከቫይረስ ነፃ እስኪሆን ድረስ ለብቻው ለይቶ እንዲቆይ ማድረግ ነው፤
6. "ሀገር አቀፍ የህዝብ ትራንስፖርት" ማለት ከአንድ ክልል ከተማ ወደሌላ ክልል ከተማ የሚደረግ ማንኛውም የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሲሆን በአንድ ክልል ውስጥ ከአንድ ከተማ ወደ ሌላ ከተማ የሚደረግ የህዝብ ትራንስፖርትንም ያጠቃልላል፤
7. "የከተማ ውስጥ የህዝብ ትራንስፖርት" ማለት በከተማ ውስጥ ትራንሰፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ታክሲዎችን፤ አውቶብሶችና የፐብሊክ ሰርቪስ ሰራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት አውቶብሶችን ያጠቃልላል፤
8. "መጠጥ ቤት" ማለት በግልፅ የሆቴልነት ስያሜ ከተሰጠው ቤት ውጪ ያለ ማናቸውም አይነት የአልኮል መጠጥ የሚሸጥበት ቤት ነው፤
9. "ለማህበራዊ አላማ" ማለት ሰርግ፣ለቅሶ፣ ክርስትና፣ ልደት፣ እድር እና ለመሳሰሉት አላማ ማለት ነው
10. "ፍትህ አካላት" ማለት፣ የክልልና ፌደራል ፖሊስና አቃቤ ህግ ተቋማትና ፍርድ ቤቶች ማለት ነው፣
11. በአዋጁ ላይ የተሰጡ ሌሎች ትርጓሜዎች ለዚህ ደንብም ተፈፃሚ ይሆናሉ::

3. የተከለከሉ ተግባራት

1. ለሀይማኖታዊ ወይም ማህበራዊ አላማ፣ ለመንግስታዊ ወይም ፖለቲካዊ ስራ ወይም ሌላ መሰል አላማ አምልኮ በሚደረግባቸው ቦታዎች፣ በመንግስት ተቋማት፣ በሆቴሎች፣ በማናቸውም የመሰብሰቢያ አዳራሾችና በማናቸውም ቦታ አራትና ከዚያ በላይ ሆኖ በአንድ ቦታ ላይ መገኘት የተከለከለ ነው፤
2. በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 1 የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ አስገዳጅ ሁኔታዎች በሚያጋጥሙበት ጊዜ የሚኒስትሮች ኮሚቴ ወይም በኮሚቴው የሚቋቋሙና ውክልና የሚሰጣቸው በክልሎች፣ በከተማና በወረዳ ደረጃ ባሉ ንዑሳን ኮሚቴዎች ስብሰባ እንዲደረግ ሊፈቅድ ይችላል፡፡
3. ማንኛውም ሰው ለሰላምታና ሌላ ማንኛውም አላማ በእጅ መጨባበጥ ክልክል ነው፣
4. ማንኛውም ሀገር-አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ ሰው በማንኛውም ጊዜ ከተሸከርካሪው ወንበር ብዛት 50% በላይ ሰዎችን ጭኖ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው፤
5. ማናቸውም የከተማ ውስጥ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ ታክሲ፣ አውቶቡስ፣ የፐብሊክ ሰርቪስ ሰራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት አውቶቡስ ከተሸከርካሪው የወንበር ቁጥር 50% በላይ ሰዎችን ጭኖ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው፤
6. ማንኛውም የግል ተሸከርካሪ ሾፌሩን ሳይጨምር ከተሸከርካሪው የወንበር ቁጥር 50% በላይ ሰዎችን ጭኖ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው፤
7. የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ከዚህ በፊት ሲጭን ከነበረው አቅሙ 25% በላይ ሰዎችን ጭኖ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው፤
8. የኢትዮ-ጂቡቲ የምድር ባቡር ከወንበር ቁጥሩ 50% በላይ ሰዎችን ጭኖ መንቀሳቀስ ተከለከለ ነው፤
9. ማንኛውንም ታራሚን ወይም ተጠርጣሪን በአካል በመገኘት በማረሚያ ቤት ወይም ፖሊስ ጣቢያ መጠየቅ ክልክል ነው፤ ሆኖም ይህ ድንጋጌ በፖሊስ ጣቢያ ለሚገኝ ተጠርጣሪ፣ ከተጠርጣሪው ጋር በአካል ሳይገናኙ ስንቅ ማድረስን አይከለክልም፤
10. በጭፈራ ቤቶችና በመጠጥ ቤቶች ማናቸውንም የመጠጥና መዝናኛ አገልግሎት መስጠት የተከለከለ ነው፤
11. በማናቸውም ቦታ የሺሻ ማስጨስና ጫት ማስቃም አገልግሎት መስጠት የተከለከለ ነው፤
12. የሲኒማ፣ ቲያትርና በአንድ ቦታ ብዙ ሰዎችን የሚያሰባስቡ መሰል የመዝናኛ አገልግሎቶችን መስጠት ክልክል ነው፣
13. ሆቴሎች፣ ካፌዎች ወይም ምግብ ቤቶች አገልግሎት በሚሰጡበት ጊዜ በአንድ ጠረጴዛ ላይ ከሶስት ሰው በላይ እንዲቀመጥ ማድረግ የተከለከለ ሲሆን ተገልጋዮች በሚቀመጡባቸው ጠረጴዛዎቹ መካከል ያለው ርቀትም ሁለት የአዋቂ እርምጃ መሆን አለበት፤ ሆኖም ተገልጋዮች የሚገለገሉት በጠረጴዛ ላይ ካልሆነ በመካከላቸው የሚኖረው ርቀት ሁለት የአዋቂ እርምጃ መሆን አለበት፤ በድንበር አካባቢዎች በሚገኙ ኬላዎች በኩል ወደ ሀገር ውስጥ መግባትም ሆነ ወደ ውጪ መውጣት የተከለከለ ነው፣
14. በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 11 የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ በውጪ ሀገር የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በኬላዎች በኩል ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ የሚኒስትሮች ኮሚቴ ፈቃድ ሊሰጥ ይችላል፤
15. ለዚሁ አላማ ከተቋቋመው ኮሚቴ ወይም በተመሳሳይ መልኩ በክልሎች ደረጃ በሚቋቋሙ
ንዑስ ኮሚቴዎች ወይም ተመሳሳይ አደረጃጀቶች አማካኝነት ፈቃድ ከተሰጠው ሰው ውጪ በማንኛውም የክልልም ሆነ የፌዴራል መንግስት ባለስልጣን ወይም ባለሙያ ኮቪድ-19ኝን በተመለከተ የፌዴራል ወይም የክልል መንግስትን ወክሎ መግለጫ መስጠት የተከለከለ ነው፣
16. በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 11 የተመለከተው ክልከላ ቫይረሱን አስመልክቶ የወጡ ህጎችን በተመለከተ የሚደረግ የሙያ ትንተናን ወይም በህክምና ባለሙያዎች የሚደረጉ ማብራሪያዎችን ወይም በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በየእለቱ የሚሰጡ መረጃዎችን አይመለከትም፤
17. ማንኛውም የመኖሪያም ሆነ የንግድ ድርጅት ቤት አከራዮች በተከራዩ ስምምነት ካልሆነ በስተቀር ቤቱን እንዲለቅ ማድረግ ወይም የቤት ኪራይ ዋጋ ጭማሪ ማድረግ የተከለከለ ነው፤
18. ማናቸውም በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 መሰረት የሚተዳደሩ ሰራተኞችን የሚያስተዳደሩ የግል ድርጅቶች በስራቸው ያሉ ሰራተኞችን የስራ ውል ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሚያስቀምጠው ስርአት ውጪ ማቋረጥ የተከለከለ ነው፣
19. ማንኛውም የመንግስትም ሆነ የግል ትምህርት ተቋም በትምህርት ቤት ወይም በሌላ ማናቸውም ቦታ አስተማሪና ተማሪዎች በአካል ተገናኝተው መማር ማስተማር ስራ እንዲሰራ ማድረግ ወይም ማስተማር የተከለከለ ነው፤
20. ማንኛውም ሁለትና ከዚያ በላይ ሰው በመሆን የሚጫወቱባቸውን ጨዋታዎች፣ ማጫወትም ሆነ መጫወት የተከለከለ ነው፤
21. ማናቸውንም የስፖርት ውድድሮች ወይም የቡድን ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ የተከለከለ ነው፤
22. የህፃናት ማጫዎቻ ቦታዎች አገልግሎት መስጠት የተከለከለ ነው፣
23. ማንኛውም ሰው የባንክ አገልግሎት በሚሰጥባቸው አካባቢዎች፣ በገበያዎች፣ በትራንስፖርት መሳፈሪያ ቦታዎች፣ በሱቆች፣ በመድሀኒት መሸጫ አካባቢዎች፣ ህዝባዊ አገልግሎት በሚሰጥባቸው ቦታዎችና ሌሎች ህዝብ በሚበዛባቸው መሰል አካባቢዎች ከሁለት የአዋቂ እርምጃዎ በታች በሆነ ርቀት መቆምም ሆነ መቀመጥ የተከለከለ ነው፡፡
24. መሰረታዊ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት እንደ መብራት ሀይል፣ ከውሃ አቅርቦት ጋር ግንኙነት ያለው ስራ የሚሰሩ ተቋማት ፣ ኢትዮ ቴሌኮም፣ የህክምና ተቋማት፣ ባንኮች፣ ከምግብ አቅርቦት ጋር ግንኙት ያለው ስራ የሚሰሩ ተቋማት፣ የጽዳት ስራዋችን የሚሰሩ ተቋማትና ባለሙያዎች፣ ከድንገተኛ ና የእሳት አደጋ መከላከል ጋር የተያያዙ ስራዎችን የሚሰሩ ተቋማት፣ ከጥበቃና ደህንነት ጋር የተያያዙ ድርጅቶች እና ተቋማት በማንኛውም መልኩ ስራን አለመስራተ ማቋረጥ ማስተጓጎል እና መሰል ተግባራትን መፈጸም የተከለከለ ነው፤
25. የደረቅና የፈሳሽ ጭነት አገልግሎትን፣ የምርት ስራን፣ የእርሻ ስራን ወይም የግንባታ ስራን ማቋረጥ፣ ማሰተጓጎል ወይም አለመስራት የተከለከለ ነው፣
26. ኮቪድ-19ኝና ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ ማህበረሰቡ እንዳይረጋጋ የሚያደርግና በማህበረሰቡ ላይ ስነ-ልቦናዊ ጫና የሚፈጥር ማናቸውንም መረጃ ማሰራጨት የተከለከለ ነው።

4. የተጣሉ ግዴታዎች

1. ማንኛውም ኮቪድ-19 እንዳለበት የተጠረጠረ ሰው ወይም ወደ ሀገር የሚገባ አለማቀፍ መንገደኛ
ኳራንታይን የመደረግና የኮቪድ-19 ምርመራ የማድረግ ግዴታ አለበት፤
2. ወደ ሀገር የገባ አለማቀፍ መንገደኛ ኳራንታይን በሚደረግበት ጊዜ የራሱን ወጪ የመሸፈን ሀላፊነት ያለበት ሲሆን፣ መንገደኛው የመክፈል አቅም የሌለው ከሆነ መንግስት ለዚሁ አላማ ባዘጋጀው ቦታ እንዲቆይ ይደረጋል፣
3. በኮቪድ-19 መያዙ የተረጋገጠ ማንኛውም ሰው መንግስት በሚያዘጋጀው ለይቶ ማቆያ ክፍል የመቆየት ግዴታ አለበት፤
4. በጉዞ ወቅት ኮቪድ-19 አለበት ተብሎ የሚጠረጠር መንገደኛ ሲኖር የማጓጓዣ አንቀሳቃሹ በአቅራቢያው ላለው ወይም ለሚያርፍበት የመግቢያና መውጫ ኬላ ሀላፊ ወይም የኮቪድ- 19 ምርመራ ለሚያደርግ ቡድን የማሳወቅ ሀላፊነት አለበት፤
5. የኮቪድ-19 ያለበት ወይም አለበት ተብሎ የሚጠረጠር ሰው ሰለመኖሩ የሚያውቅ ማንኛውም ሰው ለጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ወይም ለፖሊስ የማሳወቅ ግዴታ አለበት፣
6. የባንክ አገልግሎት በሚሰጥባቸው አካባቢዎች፣ በገበያዎች፣ በትራንስፖርት መሳፈሪያ ቦታዎች፣ በትራንስፖርት ውስጥ፣ በሱቆች፣ በመድሀኒት መሸጫ አካባቢዎች፣ ህዝባዊ አገልግሎት በሚሰጥባቸው ቦታዎችና ሌሎች ህዝብ በሚበዛባቸው መሰል አካባቢዎች የሚገኝ ማንኛውም ሰው አፍና አፍንጫው ላይ መሸፈኛ የማድረግ ግዴታ አለበት፤
7. በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 6 የተመለከተው የአፍና አፍንጫ መሸፈን ግዴታ ለዚሁ አላማ ተብሎ በፋብሪካ በተሰራ፣ በቤት ውስጥ ከተለያዩ ጨርቃጨርቆች በተዘጋጀ ወይም በማናቸውም አይነት ልብሶች ሊፈጸም ይችላል፡፡
8. ማንኛውም አገልግሎት የመንግስትም ሆነ የግል አገልግሎት ሰጪ ተቋም አገልግሎቱን ለማግኘት ወደ ተቋሙ ለሚመጡ ተገልጋዮች ቫይረሱን ለመከላከል የሚያስችሉ የንፅህና መጠበቂያ ቁሶችን ማዘጋጀትና ተገልጋዮች አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረጋቸውን የማረጋገጥ ሀላፊነት አለበት
9. ማናቸውም አገልግሎት የሚሰጡ የመንግስትም ሆነ የግል ተቋማት አገልግሎት ለማግኘት ወደ ተቋማቱ የሚሄዱ ተገልጋዮች ሁለት የአዋቂ እርምጃ ተራርቀው የሚቆሙበትን ቦታ ምልክት የማድረግ ሀላፊነት አለባቸው፤
10. የመንግስት የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎችና የግል የሚዲያ ተቋማት ኮቪድ-19ኝና ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ የሚያስተላልፏቸው መረጃዎች፣ የዜና ትንተናዎች ወይም ፕሮግራሞች ሳይጋነኑ ወይም ሳይቃለሉ ተገቢው መረጃ ወደ ሕዝቡ የማድረስ እና አላግባብ የሆነ ድንጋጤና ሽብርን የማይፈጥሩ መሆን አለባቸው::
11. ማንኛውም በፌዴራልም ሆነ በክልል የሚገኙ የመንግሥትም ሆነ የግል ተቋማት በተቋሙ ስር ለሚገኙ ሰራተኞች ስለቫይረሱ አስፈላጊውን መረጃ የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም የማድረስ፣ በመግቢያና መውጫ በሮችና ሌሎች አስፈላጊ ቦታዎች ላይ ቢያንስ
እጅ ለመታጠብ የሚያስችል ውሃና ሳሙና ማዘጋጀት ፣ በተቻለ መጠን ሌሎች የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የሚረዱ የጥንቃቄ ቁሳቁሶችን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
12. ማንኛውም በፌዴራልም ሆነ በክልል የሚገኙ የመንግሥትም ሆነ የግል ተቋማት በተቋሙ ስር የሚገኙ ሰራተኞች በአንድ ክፍል ውስጥ፣ በአንድ መስሪያ ቦታ ወይም በአንድ ትራንስፖርት ውስጥ ተጨናንቀውና አካላዊ ርቀትን ለመጠበቅ በማያስችል መልኩ እንዳይሰሩ ለማድረግ አስፈላጊውን ፈረቃ ማመቻቸት፤ ሰራተኞቹ ቤታቸው ሆነው የሚሰሩበትን ሁኔታ ወይም እረፍት በመውሰድ ስራ ቦታ እንዳይመጡ የማመቻቸት ሀላፊነት አለበት፤
13. ማንኘውም የፌዴራልም ሆነ የክልል የመንግስት ተቋምና በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 መሰረት የሚተዳደሩ ሰራተኞችን የሚስተዳድር የግል ድርጅት ሰራተኞቹ ወደ ስራ ቦታ ለመሄድ ትራንስፖርት መጠቀም አስፈላጊ ከሆነ በስራ ላይ ለሚገኙ ሰራተኞች የትራንስፖርት አገልግሎት የማመቻቸት ሀላፊነት አለበት፤
14. ፖሊስ ኮሚሽን ወይም ማረሚያ ቤት ተጠርጣሪዎች ከጠበቆቻቸው ጋር የሚገናኙበትን ሁኔታ የማመቻቸት ሀላፊነት አለበት፤
15. ማንኛውም የቤት፣ የሆቴል፣ የአፓርታማ፣ የተሽከርካሪ፣ የአዳራሽ ወይም የማንኛውም ንብረት ባለቤት መንግስት የኮቪድ-19 ሥርጭትን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠር እና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ ለሚያደርገው ጥረት አስፈላጊ የሆነ ንብረቱን ለዚህ አላማ አገልግሎት ላይ እንዲውል በሚኒስትሮች ኮሚቴ ወይም ኮሚቴው ውክልና በሰጠው የመንግስት አካል ሲወሰንና ሲጠየቅ ንብረቱን ለእለት ከእለት ፍጆታው የሚጠቀምበት ካልሆነ በሰተቀር ውሳኔውን ተግባራዊ የማድረግ ግዴታ አለበት፤
16. ማንኛውም አምራች ወይም አገልግሎት ሰጪ ድርጅት፣ የኮቪድ-19 ሥርጭትን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠር እና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ ለሚያደርገው ጥረት አስፈላጊ የሆነ አግለግሎት እንዲሰጥ፣ አገልግሎቱን እንዲያሰፋ፣ ምርት እንዲያመርት፣ የሚያመርተውን ምርት መጠን እንዲጨምር፣ አዲስ ምርት አይነት እንዲያመርት ወይም ምርቱን መንግስት በሚወስነው ተመጣጣኝ ዋጋ ለመንግስት፣ ለሾማቾች ወይም ለህብረት ስራ ማህበራት እንዲሸጥ በሚኒስትሮች ኮሚቴ ወይም ኮሚቴው ውክልና በሰጠው የመንግስት አካል የሚሰጠውን ትዕዛዝ ተግባራዊ ማድረግ አለበት።
17. ሆቴሎች ለደንበኞቻቸው አገልግሎት በሚሰጡበት ጊዜ የእጅ መታጠቢያ ውሀና ሳሙና የማቅረብ ሀላፊነት ያለባቸው ሲሆን፣ የሆቴሉ ተጠቃሚዎችም እጃቸውን
መታጠባቸውንና አስፈላጊውን ንፅህና አጠባበቅ ስርአት ተግባራዊ ማድረጋቸውን የማረጋገጥ እንዲሁም ደንበኞች ከተጠቀሙ በኋላ የተገለገሉባቸውን ጠረጴዛዎች፣ ወንበሮችና ሌሎች እቃዎች የማከም ግዴታ አለባቸው
18. ማንኛውም በስራ ላይ ያለ፣ ጡረታ የወጣ ወይም በትምህርት ላይ ያለ የጤና ወይም የሌላ ሙያ ባለቤት ወይም ማንኛውም ዜጋ የኮቪድ-19 ሥርጭትን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠር እና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ በሚደረገው ጥረት አስተዋፅዖ እንዲያደርግ በመንግስት ጥሪ ሲደረግለት የመተባበር ግዴታ አለበት፡፡

5. የሚኒስትሮች ኮሚቴ ስለመቋቋምና ስልጣና ተግባር

1. የሚኒስትሮች ኮሚቴ ከዚህ በኋላ "ኮሚቴ" እየተባለ የሚጠራ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሰብሳቢነት የሚመራ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሆነ ኮሚቴ በዚህ ደንብ ተቋቁሟል፤
2. የኮሚቴው አባላት ስብጥር እና ብዛት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ይወሰናል፤
3. ኮሚቴው የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፣
ሀ. የኮቪድ-19 ሥርጭትን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠር እና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ የሚሰራውን ስራ በበላይነት ይመራል ፣ ያስተባብራል፤
ለ. የቫይረሱን ስርጭት በተመለከተ አስፈላጊውን መረጃና ማስረጃ ይሰበስባል፣ ይተነትናል፤ በትንተናው ላይ ተመስርቶ አስፈላጊውን አቅጣጫ ይሰጣል፤
ሐ. በስሩ የተለያዩ ንዑሳን ኮሚቴዎችን በፌዴራል፣ በክልል፣ በከተማና ወረዳ ደረጃ ያቋቁማል፣ አስፈላጊውን መረጃ፣ ማስረጃና የስራ ስምሪት ይሰጣል፣ ሪፖርታቸውን ይገመግማል አቅጣጫ ያስቀምጣል፤
መ. በዚህ ደንብ ላይ የተደረጉ ክልከላዎችና የተጣሉ ግዴታዎች ቀሪ የሚሆኑበትን አግባብ እየገመገመና ችግሩ እየቀነሰ ከሄደ ክልከላዎቹና የተጣሉ ገደቦች ቀሪ እንዲሆኑ ይወስናል፣ በሚመለከተው ንዑሳን ኮሚቴ በኩል ለማህበረሰቡ እንዲደርስ ያደርጋል፤
ሠ. የቫይረሱ ስርጭት እየሰፋ እና እየጨመረ በመሄዱ ምክንያት ተጨማሪ ክልከላዎቸንና የሚጣሉ ግዴታዎችን በደንብ መደንገግ አስፈላጊ መሆኑን ባመነበት ጊዜ አስፈላጊው ደንብ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት እንዲቀርብ ትእዛዝ ይሰጣል፤
4. የኮሚቴውን ስብሰባ እና ዝርዝር የአሰራር ስነ-ስርዐት በሚያወጣው መመሪያ ይወስናል፤
5. ኮሚቴው ለክልሎችና ለከተማ መስተዳደሮች ለተመሳሳይ አደረጃጀቶች ስራቸውን በተመለከተ መመሪያና ውክልና ሊሰጥ ይችላል፡፡

6. ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች

1. በወንጀለኛ መቅጫ ስነ-ስርአት ህጉና ሌሎች ስነ-ስርአታዊ ጉዳዮችን በሚደነግጉ የወንጀል ህጎች ላይ የተመለከቱ ድንጋጌዎችን እንደተጠበቁ ሆነው፣ የአስቸካይ ጊዜ አዋጁ ጸንቶ በሚቆይበት ጊዜ የፍትህ አካላት የጊዜ ቀጠሮና ፍርድ ቤት መቅረቢያ ጊዜን የሚመለከቱ ድንጋጌዎችን የማክበር ግዴታ ለባቸውም፣
2. የክልልና ፌዴራል ፍርድ ቤቶች ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጋር ተያይዞ የሚመጡ ጉዳዮችንና ከምርት መደበቅና ዋጋ መጨመር ጋር የተያያዙ የወንጀል ደርጊቶችን በተመለከተ በአፋጣኝ ውሳኔ የሚሰጡ ችሎቶችን የማዘጋጀት ሀላፊነት አለባቸው፤
3. በፌደራል እና በክልል ጠቅላይ ፍርድቤቶች ውሳኔ መሰረት የክልል እና የፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍትሃ ብሄር ጉዳዮችን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ ማስተናገድ ሊያቆሙ ይችላሉ።
4. በኮቪዲ-19 ምክንያት ህይወቱ ያለፈ ማንኛውም ሰው የቀብር ስርአቱ የሚፈጸመው በመንግስት አማካኝነት ለዚሁ አላማ በተለዩ ቦታዎች ሲሆን በቀብሩ ላይ የሚገኘውን የሰው ብዛትና የቀብሩ ዝርዝር አፈፃፀሙ በመመሪያ ይወሰናል፣
5. በዚህ አዋጅ አንቀፅ 3 ንዑስ አንቀፅ 4፣ 5 እና 6 ከተመለከቱት ተሸከርካሪዎች ውጪ ያሉትን በተመለከተ በሚወጣ መመሪያ ይወሰናል፣
6. በዚህ ደንብ የተከለከሉ ተግባራትን የፈፀመ ወይም የተጣሉ ግዴታዎችን የተላለፈ ማንኛውም ሰው በአዋጁ ላይ የተመለከተው ቅጣት ተፈፃሚ ይሆንበታል፡፡

7. መመሪያ የማውጣት ስልጣን

የሚኒስትሮች ኮሚቴ አዋጁን እና አዋጁን ተከትሎ የወጣውን ይህን ደንብ ለማስፈፀም ዝርዝር የአፈፃፀም መመሪያ ያወጣል::

8. ደንቡ የሚፀናበት ጊዜ

ይህ ደንብ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ከፀደቀበት ጊዜ ጀምሮ አዋጁ በስራ ላይ ባለበት ጊዜ ተፈፃሚ ይሆናል::

አዲስ አበባ መጋቢት ---ቀን 2012 ዓ/ም

አብይ አህመድ/ዶ.ር/
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ
ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር

Photos from Addis Ababa Youth Federation's post 12/04/2020

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወጣቶችና በጎ
ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ ለወጣቶች በበጎ ፈቃድ ላይ ለተሰማሩት የሳንታይዘርና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ።
ድጋፉን ያደረጉት በዛሬው እለት ሲሆን የወጣቶችና
በጎ ፈቃድ ቢሮ ሀላፊ አቶ አብርሀም እንዳሉት ድጋፉ
በቂ ነው ብለን ባናምንም ግን በጅምር ደረጃ
ማስኬዳችን ወደ ታችኛው እርከን በእንደዚህ አይነት ትብብርና ድጋፍ እንዲቀጥል ለማብሰር ነው።
በርክክቡ ወቅት የክፍለ ከተሞች በጎ ፈቃድ ፅ/ቤት አስተባባሪና በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች የሚያስተባብሩ ወጣቶችም ተሳትፈዋል።
በመጨረሻም የአዲስ አበባ ወጣቶች ፌዴሬሽን
አመራሮች ለወጣቶች የሚያስፈልጓቸውን ግብአቶች እንዲሟላ የምናደርገውጥ ጥረቶች አንዱ አካል
በመሆኑ በከተማችን በበጎ ፈቃደኝነት የተሳተፉ ወጣቶች ቁጥር ሲታይ ድጋፉ ቢያንስም ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት እንደዚ አይነት ድጋፎቾ በማድረግ አኳያ ቢሮ የመጀመሪያ መሆኑ ሊመሰጉን ይገባል ቡለዋል።
ዜና ወጣቶች ፌዴሬሽን

Photos from Addis Ababa Youth Federation's post 12/04/2020

ዜና ወጣቶች ፌዴሬሽን
የኢ.ፌ. ዲ. ሪ የሴቶች ፣ህፃናትናወጣቶች ሚኒስቴር ሚኒስቴር እናየአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር ወጣቶች የበጎ ፈቃድ ማስተባበርያ ቢሮ ሀላፊው እንዲሁም የአዲስ አበባ ወጣቶች ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ አመራሮት በተገኑበት አካላዊ መራራቅን በጉሉሌ ክፍለ ከተማ
አዲሱ ገበያ አከባቢ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ ተሰራ።
በዚህ ወቅት ሚኒስቴራ እንዳለችው ሀገራችን አሁን
ብዙ በጎነት ስራዎች የሚሰሩላትን በጎ ፈቃደኞችን
ትፈልጋለች በዚህም የአዲስ አበባ ወጣቶች ምላሻቹ እንደ
ወጣት የምትሰሩትን መልካም ተግባራት እያመሰገንኩኝ
በአሁኑ ሰአት በአለም፣በሀገራችን የተከሰተውን ኮሮና ቫይረስ
ቅድመ ከመከላከል አንፃር ለህዝባችን ከአካላዊ መራራቅን ፤የጤና ባለሙያዎት ምክር፣የአቅም የሌላቸውድ ድጋፍ እና መንግስት የሚያወጣው አዋጆች ለማህበረሰባቹ ለማስጨበጥ የምትፋለሙ በጎ ፈቃደኛ ሰራዊቶች
ናችሁና በርቱ ሚኒስቴር መስሪያ ከጎናቹ ነው በማለት ወጣቶችን አሳስበዋል።
በመጨረሻም በመኪና ህዝብ የሚበዛባቸው አከባቢዎቾ ማህበራዊ(አካላዊ መራራቅን ጠብቀው እንዲንቀሳቀሱ አስተምረዋል።
ዜና ወጣቶች ፌዴሬሽን

Photos from Addis Ababa Youth Federation's post 12/04/2020

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸዉ የምግብ አቅርቦቶችን ለአዲስ አበባ መስተዳድር ዛሬ ለግሰዋል።

ባለፈው ሳምንት እያንዳንዱ ቤተሰብ ከሌላቸው ጋር “ማዕድ እንዲጋራ” ባቀረቡት ጥሪ መሠረት፣ በራሳቸው በኩል ለመስተዳድር የምግብ አቅርቦቶችን አስረክበዋል፡፡

ያስረከቡት የደረቅ ምግብ ዓይነት የከተማ መስተዳድሩ ‘እጅግ ተጋላጭ እና ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው የከተማይቱ ነዋሪዎች’ ብሎ ለለያቸው፣ ብዙ የቤተሰብ አባል ላሏቸው አንድ ሺህ ቤተሰቦች የሚበቃ ነው፡፡

ዜና ወጣቶች ፌዴሬሽን

Photos from Addis Ababa Youth Federation's post 09/04/2020

የአዲስ አበባ የታክሲ ተራ አስከባሪዎች በአስሩም ክፍለ ከተማ ባሉ የታክሲ ተርሚናሎች(መነሃሪያዎች)ላይ በመዘዋወር ለታክሲ ተጠቃሚው፣ለታክሲ ሹፌሩው፣እዲሁም ለአባሎቻችን የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ግንዛቤ መስጠትና የትራንስፖርት ቢሮ ኮሮናን ለመከላከል ያወጣውን መመሪያ እዲተገበር ሁለት ቀን ግንዛቤ ሲሰጡ ውለዋል፡፡

Photos from Addis Ababa Youth Federation's post 09/04/2020

ዜና ወጣቶች ፌዴሬሽን
የንግድ ቦታዎት አሁንም አካላዊ መራራቅን ስራ እንደሚጠይቅ የአዲስ አበባ ወጣቶች ፌዴሬሽን የኮሮና ቫይረስ ግንዛቤ አስጨባጭ ኮሚቴ አስታውቋል።
ይህነን ያለው ዛሬ በተለያዩ የግብይት ቦታዎች ወጣቶችን የአካላዊ መራራቅን የሚያስተምሩ ወጣቶች ቁጥራቸው ከማህበረሰብ እንቅስቃሴዎች ጋር መጨመር እንዳለበት ባስታወቁበት ጊዜ ነው።

Photos from Addis Ababa Youth Federation's post 08/04/2020

ዜና ወጣቶች ፌዴሬሽን

የዛሬው የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማወጣቶች አስተባባሪነት ከአስሩም ወረዳ የተወጣጡ በጎ ፍቃደኞች ወጣቶች የአካላዊ መራራቅን ለማህበረሰባቸው ግንዛቤ የሚሰጡ ወጣቶቾ ዛሬ ኦሬንትሽን እና ስልጠና ተሰጠ።

Photos from Addis Ababa Youth Federation's post 06/04/2020

ዜና ወጣቶች ፌዴሬሽን
የአዲስ አበባ ወጣቶች ፌዴሬሽን የአዲስ ክፍለ ከተማ ወጣቶች ብርቱ ጥረት ስራዎችን የከተማዋ
ከፍተኛ አመራሮች ምስጋና እና የቀጣይ
ስራዎች በተመለከተመከተል ያለብን
የመንግስት ጥብቅ ዲስፕልን የማህበረሰቡ ማስተማር እንዳለባቸው የአዲስ አበባ ከተማ የከንቲባው ህዝብ ግንኙነት ዋና አማካሪ አቶ ተስፍዬ በልጅጌ ገለፁ።
ምንጭ :-አዲስ አበባ ወጣቶች ፌዴሬሽን

06/04/2020

በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 44 ደረሰ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 28 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 164 ሰዎች ውስጥ አንድ ግለሰብ በኮሮና ቫይረስ መያዙ ተረጋገጠ።

በ24 ሰዓታት ውስጥ ምርመራ ከተደረገላቸው ሰዎች መካካል 26ቱ በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ መሆናቸውን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታውቀዋል።

ዛሬ በቫይረሱ የተያዙት ግለሰብ የ65 ዓመት ሴት ኢትዮጵያዊት ሲሆኑ የዱከም ከተማ ነዋሪና የውጭ ሃገር የጉዞ ታሪክ የሌላቸው መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ግለሰቧ ተጓዳኝ ለሆነ በሽታ ወደ ህክምና ተቋም ከሄዱ በኋላ የቫይረሱን ምልክት በማሳየታቸው ነው ምርመራ የተደረገላቸው።

በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ ግለሰቦች ቁጥር 44 የደረሰ ሲሆን ከእነዚህ መካከል አንድ ግለሰብ በጽኑ ህሙማን ማቆያ ይገኛሉ።

Photos from Addis Ababa Youth Federation's post 06/04/2020

ዜና ወጣቶች ፌዴሬሽን

የአዲስ አበባ ወጣቶች ፌዴሬሽን የየካና አራዳ እንዲሁም ጉለሌ በጎ ፈቃደኞች ወጣቶች የአትክልት ተራ ወደ ጃንሜዳ በመዘዋወሩ ምክንያት የግብይቱ የንግዱ ስራ ከኮሮና ቫይረስ ከመከላከል አኳያ ማህበራው መራራቅን የማያስተምሩ ወጣቶች የስምሪት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ ማስተባበርያ ቢሮ ሀላፊ ተግኝተው መልእክት ያስተላለፉ መሆኑን እየገለፅን ለወጣቶች መልካም የበጎ ፈቃድ ስራ።

Photos from Addis Ababa Youth Federation's post 06/04/2020

የአዲስ አበባ ወጣቶች ፌዴሬሽን የየካ እና የአራዳ እንዲሁም የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወጣቶች የኮሮና ቫይረስ ከመከላከል አንፃር በገበያ አካባቢዎች የሚከሰተውን ማህበራው መራራቅን ግንዛቤ ለመፍጠር የሚያስችል ስራየሚሰሩ ወጣቶች የስራ መመርያ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና በጎ ፈቃድ ማስተባበርያ ቢሮ ሀላፊ አቶ አብርሀም በኩል ኦሬንቴሽን ተሰጥቷል።
መልካም የበጎ ፈቃድ ስራ ሲምሪት።

05/04/2020

ቱኒዚያ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በሰዎች ዝውውር ላይ ቅኝት የሚያደርግ ሮቦት አሰማራች

*********************

የፖሊስን ተግባር የሚያከናውነው ሮቦት ቅኝት የሚያደርገው በቱኒዚያ ዋና ከተማ ቱኒዝ ሲሆን የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ዜጎች ከቤታቸው እንዲቆዩ የተጣለውን ገደብ ተግባራዊ ለማድረግ ነው ተብሏል፡፡

ሮቦቱ በርካታ ሰዎች መንገድ ላይ ተሰብስበው ሲመለከት ወደ ሰዎቹ በመጠጋት ለምን ከቤት እንደወጡ ይጠይቃቸዋል፡፡

በተጠየቁት መሰረት ለሮቦት ካሜራው ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ ማሳየት ይጠበቅባቸዋል፤ ምክንያቱም ሮቦቱ ስራውን በትክክል ሰለመከወኑ የሚቆጣጠር ባለሙያ በአቅራቢያው ስለሚኖር ነው፡፡

ቱኒዚያ የኮሮና ቫይረስን ለመቆጣጠር መድሃኒት እና አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁስን ለመግዛት ከሚወጡ በቀር ሁሉም ሰው በየቤቱ እንዲቆይ በሀገር አቀፍ ደረጃ ካወጀች 2 ሳምታት ተቆጥረዋል፡፡

በሀገሪቱ እስካሁን 436 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን 14 ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

ፒገርድ የሚል ስያሜ የተሰጠው ሮቦቱ ወደ ስራ መሰማራቱን የቱኒዚያ የሀገር ውስጥ ሚኒስትር ገልጸዋል፡፡

በ‘ሪሞት ኮንትሮሊንግ’ ተግባሩን የሚከውነው ሮቦት በካሜራው ፎቶ በማንሳት ተልዕኮውን ይወጣል ተብሏል፡፡

4 እግር ያለው ፒገርድ ሮቦት ሲጋራ ለመግዛት ከቤቱ የወጣን አንድ ግለሰብ አስቁሞ እያናገረ የሚያሳየውን ምስል በርካቶች በማህበራዊ ሚዲያ እየተቀባበሉት መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ሮቦቱ ለግለሰቡ "ሲጋራህን ይዘህ በፍጥነት ወደ ቤትህ ተመለስ" የሚል መመሪያ እንደሰጠው ዘገባው ጠቅሷል፡፡

በቻይና የአርቲፊሻል ኢንቴሊጀንስ ቴክኖሎጂ ኮሮና ቫይረስ ይኖርባቸዋል ተብለው የሚታሰቡ አካባቢዎችን ለማጽዳት አልፎ አልፎ ስራ ላይ ሲውል እንደነበር ዘገባው አስታውሷል፡፡

05/04/2020

ሁለተኛው ኢትዮጵያዊ አረፈ 😪

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በጽኑ ህሙማን ክፍል ህክምና ሲደረግላቸው የነበሩት ሁለተኛው ኢትዮጵያዊ ህይወታቸው አለፈ። ይህም በኢትዮጵያ በቫይረሱ የሞቱ ሰዎችን ቁጥር ሁለት አድርሶታል።

የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ዛሬ ማምሻውን ለኢዜአ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት ህይወታቸው ያለፈው ሁለተኛው ግለሰብ የ56 ዓመት ወንድና የአዲስ አበባ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያዊ ሲሆኑ ቀደም ሲል የውጭ አገር የጉዞ ታሪክ አልነበራቸውም።

ግለሰቡ ከመጋቢት 24 ቀን 2012 ዓም ጀምሮ በየካ ኮተቤ ሆስፒታል በጽኑ ህሙማን ክፍል በመተንፈሻ መርጃ መሳሪያ የታገዘ ህክምና ሲደረግላቸው ቆይቶ ዛሬ ከምሽቱ 12 ሰዓት ህይወታቸው እንዳለፈ ዶክተር ሊያ ገልጸዋል።

ከግለሰቡ ጋር የቅርብ ንክኪ የነበራቸው 47 ሰዎች ተለይተው ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኝም አመልክተዋል።

የተፈጠረው ክስተት አስደንጋጭ ቢሆንም ተረጋግተን መመሪያዎችን በመከተል ችግሩን ልንከላከለው ይገባል ብለዋል።

Want your organization to be the top-listed Non Profit Organization in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


Janmeda
Addis Ababa