Anami Tibeb አናሚ ጥበብ

Ethiopia has been & remains to be Great
ታላቅ ነበር በታላቅነታችን እንቀጥላለን

03/04/2024

የሞጆ ደረቅ ወደብ የግንባታ 60 በመቶ መደረሱ ተገለፀ

መጋቢት 24፣ 2024 (ኢማባ) - የሞጆ ደረቅ ወደብ የግንባታ ሂደት 60 በመቶ መድረሱን የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ኢንጂነር ደሳለኝ ጌታሁን ገለፁ፡፡

አስተባባሪው ፕሮጀክቱን ለጎበኙት የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን ሃላፊዎችና ሰራተኞች በግንባታው ሂደት ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

አስተባባሪው እንደገለጹት ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ የተርሚናሉን አቅም በእጥፍ ያሳድገዋል፡፡
የሞጆን ደረቅ ወደብ ወደ ማዕከልነት የማሳደግ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም አስተባባሪው ጨምረው ተናግረዋል፡፡

03/04/2024

የሰዎችን ቀልብ በእጅጉ ከሚስቡ ጉዳዮች መካከል ባህር እና ባህር ነክ ጉዳዮች ቀዳሚዎቹ ናቸው፡፡ ስለዚህ እናንተ የምትሰሩበት መስሪያ ቤት በፌስቡክም ሆነ በሌሎች ማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች የማያቋርጡ መረጃዎን ለተከታዮቻችሁ መስጠት የሚያስችላችሁ ነው፡፡ ራሳችሁን እንደ እድለኛ የኮሙኒኬሽን ባለሙያ ቆጥራቸሁ በትጋት መስራት ይኖርባችኋል ማለት ነው፡፡

Photos from Anami Tibeb አናሚ ጥበብ's post 08/08/2023

ለመጪው የኢትዮጵያ አዲስ አመት ድምቅ የሚሉባቸውን ውብ የሃገር ባህል አልባሳት እንሰራለን። ይዘዙን በቀናት ውስት ባሉበት እናደርሳለን።




Anami Tibeb አናሚ ጥበብ

08/08/2023

ውብ ሽፎኖችን እና የባህል አልባሳትን በምርጫዎ መሰረት በቀናት እናደርሳለን ይዘዙን Anami Tibeb አናሚ ጥበብ
Ethiopian Community of Charlotte

08/08/2023

Anami Tibeb አናሚ ጥበብ
ባሉበት ሆነው ይዘዙን

23/03/2023

ድምቅ ድምቅምቅ በራስ ቀለም

02/03/2023

ቁንፁል ዕውቀት አደገኛ ነው!
ያ የሀገሩን ታሪክ በውል የማያውቀው ትውልድ የኢትዮጵያ ብሔርተኝነት "ፌክ" ነው ብሎ አወጀ፤ ብሔር ምንድነው? ብለህ ብትጠይቀው ግን ምላሽ የለውም፤ ስለ ብሔርተኝነት አስረዳኝ ብትለው ግን ወገቤን ይላል።
ብሔርተኝነት ግን ዓይነተ ብዙ ነው፤ አንዳንዶች የሲቪክ፣ የዘውግ የባህል ብሔርተኝነት ወዘተ እያሉ ዝርዝሩን እስከ 10 ያደርሱታል።
ኢትዮጵያን በመላ ዓለም ከፊት ተርታ ያሰለፋት አንድ የብሔርተኝነት ዓይነት አለ፤ ይህም የፀረ-ቅኝ አገዛዝ ብሔርተኝነት ተብሎ ይጠራል፤ በእንግሊዝኛው "Anticolonial Nationalism" ወይም "Anti-imperial nationalism" ይሰኛል። አንዳንዶችም የዚህን ብሔርተኝነት ፅንሰ ሐሳብ በማስፋት "Internationalist Nationalism" የሚለውን ስያሜ እስከመስጠት ደርሰዋል...እነ ማርክስ የነደፉት ዓለም አቀፋዊ የናሽናዝም ዓይነት ማለታቸው ነው።
ታዲያ ብዙዎች የናሽናሊዝም አጥኚዎች ስለዚህኛው ዓይነት ብሔርተኝነት በስፋት ከትበዋል፤ ከነዚህም ውስጥ Robbie Shilliam, John Bruelli ,Julian Go, Jake Watson, John M.Lonsdale, EREZ MANELA, Chacko Priya ይገኙበታል። ዝርዝሩ ለሌላ ጊዜ ይቆይና እነዚህ አጥኚዎች በየጥናቶቸው ውስጥ ስለ ኢትዮጵያ ፀረ ቅኝ አገዛዝ ብሔርተኝነት በአያሌው ጠቅሰዋል።
እናም ዋለልኝ መኮንን "የኢትዮጵያ ናሽናሊዝም ፌክ ነው" ያለው ከብዙ የብሔርተኝነት ዓይነቶች አንዱን ሰበዝ ብቻ መዝዞ ነው፤ መለስ ብለን በ1960ዎቹ መግቢያ ያነበበውን ፅሁፉን የተመለከትን እንደሆነ እሱ "ፌክ" ነው ያለው "Cultural Nationalism"ን ነበር...ቋንቋ፣ ልብስ ሙዚቃ፣ ባህል ወዘተ። ከዚህ በመለስ ዋለልኝ መኮንን "Anticolonial Nationalism" የሚባል ፅንሰ ሐሳብ ይኑር አይኑር ያወቀው አይመስልም።
የኢትዮጵያ "Anticolonial nationalism" ግን ፌክ አይደለም። በአጥንትና ደም የተዋቀረ ገሃዳዊ ናሽናሊዝም ነው፤ ድንበር ተሻግሮ የአፍሪካን፣ የእስያን፣ የካሪቢያን እና የአሜሪካ ጥቁሮችን ጭምር ካንቀለፉበት ቀስቅሶአቸውና አንድ አድርጎአቸው ለነፃነት ትግል አልፎ ተርፎም ለድል ያበቃቸው የናሽናሊዝም ዓይነት ነው። የማህተመ ጋንዲ የነፃነት ትግል አጋርና ከነፃነት በኋላ የሕንድ የመጀመሪያ ጠ/ሚኒስትር የነበረው "Jawaharlal Nehru" ስለ ኢትዮጵያ "Anticolonial Nationalism" ሲያነሳ...የሕንድ ነፃነት የሚመሠረተው ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት ላለመገዛት በምታደርገው ትግልና ትንቅንቅ ላይ ነው" ስለማለቱ ስንቶቻችን አንብበነው ይሆን?
ወዳጄ እንደ ቁንፁል ዕውቀት አደገኛ ነገር የለም! አንድ ሰበዝ ብቻ እያስመዘዘ ኢትዮጵያ የምትባል ትልቅ ሀገርን ዛሬ ለመፍጠር እስከመዳፈር ያደርሳል፤ አድርሷልም። እንደዚህ ዓይነቱን ዓይን ያወጣ ቁንፁልና ነጠላ ትንታኔን የማህበረሰብ ሳይንስ ፕሮፈሰሩ ሲንሳ ማሌሴቪክ " The fallacy of single factor analysis" በማለት ይጠረዋል።
የፀረ ቅኝ-አገዛዝ ብሔርተኝነት ባለፈ ታሪክ ላይ ስለተመሠረተ ዛሬ ያለው ፋይዳው ወይም ሌገሲው ምንድነው? የሚል አይጠፋም፤ ሌገሲውማ የትየለሌ ነው፤ አንዱና ዋናኛው የዛሬው የኢትዮጵያ ሉዓላዊ መልክዓ ምድር...Political Map..ነው። አያት ቅድመ አያቶቻን በዚህኛው ብሔርተኝነት ሥር ተጠልለው ቅኝ ገዥዎችን በመጡበት ባይመልሷቸው ኖሮ ዛሬ ላይ አማራ ክልል 10 ቦታ ኦሮሚያ 30 ቦታ፣ደቡብ ደግሞ 20 ቦታ ወዘተ ተከፋፍለው የቅኝ ገዥዎች ሲሳይ ከመሆን አይዘሉም ነበር፤ ዛሬ በቁንፁል ዕውቀቱ ኢትዮጵያ ላይ አፉን የሚከፍተው አፍቃሪ-ዘውጌ ጎሰኛ ሁሉ "ክልሌ" ምናምን እያለ የሚደነፋለትን ጂዖግራፊያዊ አካባቢውን ጠብቆ ያስረከበው የእነ አፄ ምኒልክና የአጋር አርበኞች መስዋዕትነት ስለመሆኑ ቆም ብሎ ለማስተዋል የታደለ አይመስልም።
ለማንኛውም በመጪው እሑድ የካቲት 26 2015 ዓ.ም. በኤፍ ኤም 107.8 ከጧቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በ"የልጆቻችን ኢትዮጵያ" መርሃግብር ላይ በፀረ ቅኝ አገዛዝ ብሔርተኝነት ላይ ተመስርተን ከጋዜጠኛ ቢንያም ፍርድአወቀ ጋር በሰፊው እንወያያለን። የዛሬው ለቅምሻ ያህል በበዓሉ ዕለት የተለቀቀ የውይይቱ ናሙና መሆኑ ነው፤ ከዚህም አልፎ ተርፎ በዕለቱ በምኒልክ የአድዋ የክተት ጥሪ አዋጅ ላይ ሰፋ ያለ ትንታኔን ይዘን እንቀርባለን!
ክብር...የዛሬውን የኢትዮጵያ መልክዓምድራዊ አቀማመጥን ላስረከቡን የፀረ ቅኝ አገዛዝ ብሔርተኝነት አርበኞች ይሁን!
መልካም የአድዋ በዓል
Getahun Heramo
Great Ethiopia ታላቋ ኢትዮጵያ

27/02/2023

ቦረና
በሎሬት ጸጋዬ ገብረመድኅን
------
ደምበል! ገላልቻ ሌሮ!
ኢማጂ ዲና! አባ ገናሌ!
ደምበል! እንዲያው በስመ ደምበል
የክረምቱን ጎርፍ አይደለም።
የዘንካቶቹን እንጂ
የአሬሮን ምንጭ ቅጅ!
የነ ገላልቻን ቅጅ!
የዲናው መቅሰፍት እለት
ዱታው የነጉዮ አባት
ደምደል! ድምፅ አባሮሮ
እንደ ምንሽር አምሮ
ሸንቃጣው ግዳይ-ጣሌ
ሮሮዬም እንደ ቃሌ
ደምበል! አባ ገናሌ!
መልሼ መላልሼ
ደጋግሜ አሰልሼ
ደጋግሞ ገዳይ ሾጤ
መላልሶ ጣይ ሰተቴ
ብላ ወልዳኝ እናቴ
ደምበል ገደል-ከሣቴ!
እንደ አይጥ ፈፋ ምሳ
እንዳይሞት ትቢያ ልሶ
ቢቀር በጉዲፈቻ
ነበር ያረኩት አቻ።
ደምበል! የሚያውቅ ይወቀኝ
ወትሮም የቦረን እሳት።
እሚሰኘው እኔ ነኝ!
የሚያውቀኝ ወትሮም ያውቃል፡
ዱታው የነዲና ጣር!
የማያውቀኝ ያው ልማር
ያውሬን ጭለማ ጠለል
የደኑን ዋሻ ገደል
መንጥሮ-ገበን ደምበል!
ባንዲት መካን ሴት ኩራት
አልሰማ ብዬ ጥቃት
የቆንጨሮ ፍም እሳት
ሌሊት ጀምበር ሳትወጣ
ገበሁት በጨበጣ!
ጨረር ስትቀላ በደን
በዋርሲቱ ልጆች ቀን
የሰባት ጓድ ሁለት ረድፍ
ጭለማ ለብሶ ሲከንፍ
እኔ የመቅሰፍቱ እጁ
የነ ጎልማሳ ልጁ
ተግ ሊል እንዳየሁት
በገዛ ደሙ አጠብኩት!
ስመለስ ቀን ሰይነጋ
ጥንድ አውራሪስ አድፍጦ
ቢጋፈጠኝ አፍጥጦ
በከረዩ ሴት ኩራት
አልኖር ብዬ በጥቃት
ቤቴን በረቴን ትቼ
ሎጋ ጦሬን አንግቼ
በደምበል ስም እንደማልኩ
ኮርማ አውራሪስ ተንተራስኩ።
ሸንቃጣው ግዳይ-ጣሌ
ደምበል! አባ ገናሌ!
ደምበል! ሮሮምሳ ሳጲራ!
ደምባል! ጋላልቻ ሬሮ!
ኢማጂ ዲና! አባ ጋናሌ!
*****
📝ፀጋዬ ገብረመድኅን (1965)፣ እሳት ወይ አበባ፣ 1966፣ ገጽ- 53-55


Yared Shumete - ያሬድ ሹመቴ

24/01/2023

ባይደረጉ:-
--
(1) ወደ ኮፕቶች ማንጋጠጥ ቢቀር። በሢመት ጉዳይ አዎንታዊ ሚና የመጫወት የተአማኒነት ታሪካቸው ደካማ ነው።
(2) በሢመቱ የተገኙ ሦስቱ ጳጳሳትን ግላዊ ሁኔታዎች በማኅበራዊም ሆነ በብሮድካስት ሚዲያ መዘርዘሩ የሚያንጽ ሆኖ አልታየኝም። ስም አጠራራቸውም ሲኖዶስ ውሳኔ እስኪሰጥ በነበረበት ሊቀጥል ይገባል። አውርዶ አንተ ማለት፣ ወይም በመዓርጋቸው ላይ የሚጨመሩ ቅጽሎችን በትእምርተ ጥቅስ ውስጥ መክተት ሥልጣናችን አይደለም። ፎቶ ሾፕ ጸያፍ ነው።
(3) በብሶትና በእልህ ጉዳዩን የነጥብ ማስቆጠሪያ ያደረጉ ቤተሰቦች አሉን። በእምነቱ ሳይኖሩበት አጀንዳውን በልዩ ልዩ ምክንያት የገዙ ከቅን ልቡና የራቁ (ከሁለት ጥፋት አንድ እውነት ለማውጣት የሚጥሩ) ሰዎች አሉ። ከእነርሱ ቴክኖሎጂው በፈጠረልን ዕድል ለጊዜው ታቅቦ መቆየት "አርምሞ ተዐቅብ ሃይማኖተ" የሚጠቀስበት ተግባር ነው።
--
ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንተ ላዕለ ኲሉ ጉባኤ ዘሐዋርያት።
በአማን ነጸረ

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Address


Addis Ababa
1000
Other Social Media Agencies in Addis Ababa (show all)
ONE KOO OROMO ONE KOO OROMO
Addis Abeba
Addis Ababa

Menelik Stock Menelik Stock
Addis Ababa

Menelikstock is an African-based provider of stock photography, stock footage, and stock music. It provides an opportunity both for professional artists and non-artists to contribu...

Dubakko Dubakko
Addis Ababa

welcome to our official page. In this page you will learn more about content marketing and advertisi

Tesloach Riek Jikany Tesloach Riek Jikany
Addis Ababa, 1000

https://youtube.com/channel/UCwI5ou16JhT7-ew--eaB0Pw

Dagisak & Evan Dagisak & Evan
Bole
Addis Ababa, 1000

dagisak & evan official page

Jossy Man Jossy Man
Addis Ababa

Speak the Truth

Ethio Boost Marketing Ethio Boost Marketing
Addis Ababa
Addis Ababa, 1000

A leading digital marketing agency in Ethiopia, dedicated to helping small businesses and individuals

EwketJobs EwketJobs
Addis Ababa

Pluto Agency Pluto Agency
Addis Ababa

Social Media Marketing Agency -Facebook,IG Ads -Youtube,tiktok ads -Social media automation -web devt

FinFine Times FinFine Times
Adama
Addis Ababa

አልጀዚራ.  Ethiopia አልጀዚራ. Ethiopia
Swaziland Street
Addis Ababa, 21900

Oduu lolaa dhugaa fii haaraa isiniin geenya./ትኩስ የጦረነት ዜና እንድ ደርሳቹ