Fit Corner sport Training & Consultancy P.L.C, Addis Ababa Videos

Videos by Fit Corner sport Training & Consultancy P.L.C in Addis Ababa. Fit Corner consultancy P.L. C. Is an organization working on Sport. Specially to solve the problem i

የኤርገንዶ ምርቶች የሆኑትን ምቹና ተመራጭ የሆኑ የተለያዩ ምንጣፎች (Mats) ይዘንላችሁ ቀርበናል።
1ኛ:- ምቹና አስተማማኝ የጅምናዚየም ወለል ምንጣፍ (Gym mats)
2ኛ:- የህፃናት ወለል ምንጣፍ (Child mats)
3ኛ :- የእንቅስቃሴ መስሪያ በተለያየ መጠን (Exercise mats)
4ኛ:- ምቹ የማሳጅ ምንጣፍ (Massage mat)
ከፊት ኮርነር ስፖርት አማካሪ በተመጣጣኝ ዋጋ ያገኛሉ።
ቅርንጫፎቻችን:-

√ አዲስ አበባ ፡- አራት ኪሎ፣ ቅዱስ ፕላዛ ህንፃ 2ኛ ፎቅ
√ ባህር ዳር፡- እንቁ የገበያ ማዕከል 1ኛ ፎቅ (141)
√ ሀዋሳ፡- ሰፈረ ሰላም፣ ትሩፋት፣ የትራፊክ መብራቱ አካባቢ (አድማስ ህንጻ ፊት ለፊት)
በ0910626879 ይደውሉልን፡፡

Other Fit Corner sport Training & Consultancy P.L.C videos

የኤርገንዶ ምርቶች የሆኑትን ምቹና ተመራጭ የሆኑ የተለያዩ ምንጣፎች (Mats) ይዘንላችሁ ቀርበናል። 1ኛ:- ምቹና አስተማማኝ የጅምናዚየም ወለል ምንጣፍ (Gym mats) 2ኛ:- የህፃናት ወለል ምንጣፍ (Child mats) 3ኛ :- የእንቅስቃሴ መስሪያ በተለያየ መጠን (Exercise mats) 4ኛ:- ምቹ የማሳጅ ምንጣፍ (Massage mat) ከፊት ኮርነር ስፖርት አማካሪ በተመጣጣኝ ዋጋ ያገኛሉ። ቅርንጫፎቻችን:- √ አዲስ አበባ ፡- አራት ኪሎ፣ ቅዱስ ፕላዛ ህንፃ 2ኛ ፎቅ √ ባህር ዳር፡- እንቁ የገበያ ማዕከል 1ኛ ፎቅ (141) √ ሀዋሳ፡- ሰፈረ ሰላም፣ ትሩፋት፣ የትራፊክ መብራቱ አካባቢ (አድማስ ህንጻ ፊት ለፊት) በ0910626879 ይደውሉልን፡፡

ታህሳስ 24/ 2014 ዓ.ም #ቀጥታ_ከመስቀል_አደባባይ #መስቀል_አደባባይ በትውልደ ኢትዮጵያዊያን ፣ በኢትዮጵያ ወዳጆችና በከተማዋ ነዋሪዎቿ ከማለዳው 12:00 ሰዐት ጀምሮ #በማስ_ስፖርት ደምቃ አረፈደች ። #የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይ አህመድን #ኑ_ወደ_ኢትዮጽያ የሀገር ቤት መመለስ ጥሪን ተቀብለዉ ከተለያዩ አለም ሀገራት ወደ እናት ሀገራቸዉ #ኢትዮጵያ የሚመጡ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ( ዲያስፖራ ) እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በመዲናችን አዲስ አበባ በሚኖራቸዉ ቆይታ በተለያዩ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችና ሁነቶች ተሳትፎ እንደሚያደርጉ ይታወቃል አንዱና ዋነኛው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ዛሬ #ማስ_ስፖርት በይፋ ተጀምሯል ። በክብር እንግድነት የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራል አባይ በመዲናዋ ቆይታቸው በወጡ መርሀ ግብሮች በተለያዩ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች እና ሁነቶች ተሳትፎ በማድረግ ለአካላቸው ጤንነትን ፣ በግንኙነታቸው ይበልጥ ኢትዮጵያዊነትን ፣ አንድነትን ፣ መዋደድንና መረዳዳትን የሚያጠናክሩበት መድረኮችም እንዲሆኑ ተመኝተዋል ። መድረኩን #የፊት_ኮርነር_ስፖርት_አማካሪ ስራ አስኪያጅ ኢንስትራክተር ነፃነት ካሳ በብቃት መርቶታል ። #የፊት_ኮርነር_ስፖርት_አማካሪ #የአዲስ_አበባ_ወጣቶችና_ስፖርት_ቢሮ

Coming Soon on EBC News channel

ሚያዚያ 10 / 2013 ዓ.ም #ቀጥታ_አቃቂ_ቃሊቲ_ክፍለ_ከተማ #10ኛው_ከተማ_አቀፍ_የአካል_ብቃት እንቅስቃሴ የኮቪድ 19 ፕሮቶኮል መመሪያንና አሰራርን በጠበቀ መልኩ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን መሪነትና አዘጋጅነት #በአቃቂ_ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተናጋጅነት #በኮዬ_አደባባይ በድምቀት ተካሄደ #አጭር_ቪዲዮ ይመልከቱ ። በአመራሩ ቁርጠኝነትና መሪነት የተጀመረው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ #ማስ_ስፖርት እንደሚቀጥል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር በላይ ደጀን አስታወቀዋል ።

የዓለም የስፖርት ቀንን ስናከብር ሁላችንም በአቅማችን ልክ መደበኛ በሆነ መንገድ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንስራ።

መጋቢት 26 / 2013 ዓ.ም #ቀጥታ_አምቦ_ከተማ ። #አብሮነታችን_ለሀገራችን ! ለሰላማችን ፣ለአንድነታችንና ለወንድማማችነት በሚል መሪ ሀሳቦች #በአምቦ_ከተማ ከማለዳው 12:00 ሰዐት ጀምሮ ከነዋሪው ፣ ከከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ፣ ከአዲስ አበባ የስፖርት የሰላም አባላቶች ጋር #የአካል_ብቃት_እንቅስቃሴ ( ማስ ስፖርት ) ተካሄደ ። #አጭር_ቪዲዮ ይመልከቱ ። የአምቦ ከተማ አስተዳደርና ነዋሪዎች እንግዳ ተቀባይ፣ ሰላም ወዳዶችና ስፖርት አፍቃሪ መሆኑን በተለይ ወጣቱ በተግባር አሳይቷል ። #ፊት_ኮርነር_አማካሪ! #አዲስ_አበባ_ስፖርት_ኮሚሽን #ኦሮሚያ_ስፖርት_ኮሚሽን

የካቲት 28 / 2013 ዓ.ም #ቀጥታ_መስቀል_አደባባይ ##የሴቶች_ቀን #ማርች_8 የሴቶች ተሳትፎ ለሁለንተናዊ #ብልፅግና በሚል መሪ ሀሳብ በመስቀል አደባባይ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ #ክብርት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር በላይ ደጀን ፣ ከፍተኛ የመንግስት ሀላፊዎች ፣ የከተማው ነዋሪ ሴቶችበተገኙበት #በሴቶች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አሰልጣኞች አሰሪነት፤ በኢንስትራክተር ነፃነት ካሳ የመድረክ የበላይ አስተባባሪነት በደመቀ ሁኔታ ተጀምሮ በመጠናቀቁ እናመሰግናለን ። #የፊት_ኮርነር_አማካሪ ለመላው የሀገራችን ሴቶች እንኳን #ለማርች_8 አደረሳችሁ እያለ ! #የአካል_ብቃት እንቅስቃሴ መስራት የሁልግዜ ተግባራችሁ እንዲሆን ይመክራል ።

የካቲት 07 / 2013 ዓ.ም #ቀጥታ_አዲስ_ከተማ ። #6ኛው_ዙር_ከተማ_አቀፍ_የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በልዩ በድምቀት እና ልዩ ልዩ ዝግጅቶች ከማለዳው 12:00 ሰዐት ጀምሮ #መድሀኒዐለም መሠናዶ ትምህርት ቤት አደባባይ ተካሄደ ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር #ስፖርት_ኮሚሽን አመራርና አስተዳደሩ በታላቅ አክብሮት ላደረገው አስተዋፅኦና ዝግጅት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ በአቶ ይታያል ደጀኔ በራሳቸው ስምና በከተማው ነዋሪ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።

የካቲት 07 / 2013 ዓ.ም #ቀጥታ_አዲስ_ከተማ ። #6ኛው_ዙር_ከተማ_አቀፍ_የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በልዩ በድምቀት እና ልዩ ልዩ ዝግጅቶች ከማለዳው 12:00 ሰዐት ጀምሮ #መድሀኒዐለም መሠናዶ ትምህርት ቤት አደባባይ ።

የካቲት 06 / 2013 ዓ.ም #ቀጥታ_ደብረ_ብርሃን ከተማ #አብሮነታችን_ለሀገራችን በሚል መሪ ቃል ማህበረሰብ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ #ማስ_ስፖርት ለለሁሉም ዜጋ በሁሉም ቦታ ዛሬ ከማለዳው 12:00 ሰዐት ጀምሮ በደብረ ብርሀን ከተማ ተካሄደ ።#አጭር_ቪዲዮ በኢንስትራክተር ነፃነት ካሳ መድረኩን መሪነት እና በአካል ብቃት ባለሙያዎች አሰሪነት #ደብረ_ብርሀን ደምቃ አረፈደች ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን ከደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር የተዘጋጀ የአብሮነት ተምሳሌት #ማስ_ስፖርት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽነር በላይ ደጀን ፣ #የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ኤልያስ ሽኩር ፣ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕረዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ፣ ምክትል ኮሚሽነር ዱቤ ጅሎ እና ጥሪየተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል። #የፊት_ኮርነር_አማካሪ በጥረትና ባለብን ሀላፊነት እንደርሳለን!! ለነበረን ቆይታ፣ ፍቅርና አቀባበል እናመሠግናለን

ታህሳስ 18 / 2013 ዓ.ም #ቀጥታ_ለሚ_ኩራ ክፍለ ከተማ #ለሀገሬ_ሰላም_ዘብ_እቆማለሁ_ለመከላከያ_ሰራዊት ቅድሚያ እሰጣለሁ! በሚል መሪ ሀሳብ #ከተማ_አቀፍ የሰላም ንቅናቄ #የአካል_ብቃት እንቅስቃሴ ማስ ስፖርት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን አዘጋጅነት በኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር በድምቀት ተጠናቀቀ ። #መድረኩን_ በኢንስትራክተር ነፃነት ካሳ መሪነት በአካል_ብቃት እንቅስቃሴ ባለሙያዎች በመታገዝ ተሳታፊዎች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ባማረ መልኩ አድርገዋል ። #ስፖርት ለሰላም ፣ ለአንድነት ፣ ለፍቅር ፣ ለጤንነት ፣ ለመቻቻል ፣ ለአብሮነት ፣ ለልማትና ለትብብር ያለው ፋይድ ታላቅ መሆኑን ስፖርት ኮሚሽን በተግባር አሳይቷል ። በፕሮግራሙ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር በላይ ደጀን #የኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ኤልያስ ሽኩር የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ ፣ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ኤልያስ ፣ የቦሌ ፣ የየካ ስራአስፈፃሚዎች ፣ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው ነዋሪዎችና ተሳታፊዎች ታድመዋል ።

ታህሳስ 03 / 2013 ዓ.ም #የደመቀ_ዝግጅት ተጠናቀቀ በቲንሻ ሁለገብ ስታዲየም ከማለዳው 12:00 ሰዐት ጀምሮ #በፊት_ኮርነር_አማካሪ ስራ አስኪያጅ በኢንስትራክተር ነፃነት ካሳ መሪነት #የስፖርት_ሳይንስ_የመምህራን ሰልጣኞች #የአካል_ብቃት እንቅስቃሴ መዝጊያ ፕሮግራም ተካሄደ በአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን አዘጋጅነት በንድፈ ሀሳብና በተግባር በከፍተኛ የዘርፉ ባለሙያዎች ሲሰጥ የቆየው የስፖርት ሳይንስ #የመምህራን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ስልጠና ዛሬ እሁድ ታህሳስ 04/2013 ዓ.ም #ከማለዳው 12 :00 ሰዐት ጀምሮ #በቲንሿ_ሁለገብ ስታዲየም የከተማችን ምክትል ከንቲባ ክቡር አቶ ዣንጥራር አባይ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር በላይ ደጀን ፣የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዘላለም ሙላት ፣ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ፣ ሰልጣኞች ፣ ርዕሳነ መምህራኖች ሚዲያዎቾ በተገኙበት በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እና #በማስ_ስፖርት ተጠናቀቀ ። #የፊት_ኮርነር_አማካሪ_በሁሉ_ቦታ_ለሁሉም_ዜጋ እንደርሳለን!!

ህዳር 06 / 2013 ዓ.ም #አራዳ_ክፍለ_ከተማ ዛሬ ከማለዳው 12:ዐዐ ሰዐት ጀምሮ የአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ክብርት ዶክተር ሀና የሺንጉስ ፣ የስፖርት ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ዮሀንስና አመራሮች፣ ነዋሪዎች ፣ ታዳጊ ህፃናቶች በተገኙበት #ማስ_ስፖርት ተሰርቷል ። በ8ኛው የአራዳ ክፍለ ከተማ #የማስ_ስፖርት እንቅስቃሴ የክፍለ ከተማው ስፖርት ፅህፈት ቤት፣ የክፍለ ከተማው ማስ ስፖርት ኮሚቴ #ከፊት_ኮርነር_አማካሪ ጋር በመቀናጀት ያካሄደው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አዲሷ ተሿሚ ክብርት ዶክተር ሀና የሺንጉስ #ማስ_ስፖርት በክፍለ ከተማችን እስከ ታችኛው ወረዳና ማህበረሰብ ድረስ በተጠናከረ መልኩ ይቀጥላል ብለዋል ። #የፊት_ኮርነር_አማካሪ ለአራዳ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ለክብርት ዶክተር ሀና የሺንጉስ መልካም የስኬትና የስራ ዘመን እየተመኘ #በስፖርቱ_ሁለንተናዊ ለውጥ ከጎናቸው በመሆን እንደሚሰራ በዚህ አጋጣሚ ቃል ይገባል

ነሀሴ 24/ 2012 ዓ.ም #አራዳ_ክፍለ_ከተማ_በቀጥታ ። #በአራዳ_ክፍለ_ከተማ__ከሁሉወረዳ የተውጣጡ ነዋሪዎች ጤናቸውን ለመጠበቅና ከድብርት ለመላቀቅ #ርቀታችንን_እንጠብቃለን_ወረርሽኙን_እንከላከላለን ይበልጥም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንሰራረን በሚል መሪ ሀሳብ የጀመሩት ተግባር ዛሬም ከማለዳ 12:00 ሰዐት ጀምሮ በክፍለ ከተማው ቅጥር ግቢ ውስጥ #የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ሰርተዋል ። ከአካል ብቃት እንቅስቃሴ ጎን ለጎን #ተላላፊ_ያልሆኑ በሽታዎች ምርማራ ለስፖርቱ ማህበረሰብ ተደርጓል ። #አካል_ብቃት_እንቅስቃሴ ( #ማስ_ስፖርት ) በማድረግ ጤናችንን እንጠብቅ #ከኮቪድ_19 ወረርሽኝ እንከላከል በሚል መሪ ሀሳብ የአራዳ ክፍለከተማ ስፖርት ፅህፈት ቤት #ከፊት_ኮርነር_አማካሪ ከአካል ብቃት ባለሙያዎች ጋር በመቀናጀት በክፍለ ከተማው ካሉ የተውጣጡ ነዋሪዎች #አካላዊ_ርቀታቸውን በመጠበቅ በክፍለ ከተማው አስተዳደር ግቢ ውስጥ አካላዊ እንቅስቃሴ እንዲሰሩ ተደርጓል ። በአስደማሚ እና አንቃቂ ሁኔታ ተጠናቋል ። የኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ ወዲህ ነዋሪዎች በተለይ ህፃናትና ወጣቶች እራሳቸውን ለመጠበቅ በቤታቸው የሚገኙ ሲሆን ካላስፈላጊ ድብርት ፣ ጭንቀት ፣ ውፍረትና ተላላፊ ካልሆኑ በሽታዎች ለመከላከል #የአካል_ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ እንደሚኖርባቸው ከአለም የጤና ድርጅትና ከኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር የሚወጡ መረጃዎች ያመ

መስከረም 10 / 2012 ዓ.ም #አራዳ_ክፍለ_ከተማ ። #ሁሌ_ከእኛ_ጋር በመሆናችሁ #ለጤናችሁ እንጨነቃለን አብረን ሁሌ እንሰራለን ።#ፊት_ኮርነር_አማካሪ ። #በአራዳ_ክፍለ_ከተማ__ከሁሉወረዳ የተውጣጡ ነዋሪዎች ጤናቸውን ለመጠበቅና ከድብርት ለመላቀቅ #ርቀታችንን_እንጠብቃለን_ወረርሽኙን_እንከላከላለን ይበልጥም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንሰራረን በሚል መሪ ሀሳብ የጀመሩት ተግባር ዛሬም ከማለዳ 12:00 ሰዐት ጀምሮ በክፍለ ከተማው ቅጥር ግቢ ውስጥ #የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ሰርተዋል ። ከአካል ብቃቱ ጎን ለጎን #የስፖርት_ቤተሰቦች እና ነዋሪዎች ተላላፊ ካልሆኑ ህመሞች ስኳር ፣ ደም ግፊት እና የመሳሰሉት ለመከላከል ከጤና ባለሙያዎች የቅድመ ምርመራ ተደርጎላቸዋል ። #አካል_ብቃት_እንቅስቃሴ ( #ማስ_ስፖርት ) በማድረግ ጤናችንን እንጠብቅ #ከኮቪድ_19 ወረርሽኝ እንከላከል በሚል መሪ ሀሳብ የአራዳ ክፍለከተማ ስፖርት ፅህፈት ቤት #ከፊት_ኮርነር_አማካሪ የአካል ብቃት ባለሙያዎች ጋር በመቀናጀት በክፍለ ከተማው ካሉ የተውጣጡ ነዋሪዎች #አካላዊ_ርቀታቸውን በመጠበቅ በክፍለ ከተማው አስተዳደር ግቢ ውስጥ አካላዊ እንቅስቃሴ ዛሬም እንደወትሮው እንዲሰሩ ተደርጓል ። የአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሚደቅሳ ከበደ #የአካል_ብቃት እንቅስቃሴ በክፍለ ከተማችን እስከ ታችኛው ወረዳና የጋራ መኖሪያ ቤቶ