DireTube

DireTube.com is the #1 Ethiopian Video Sharing Site. DireTube is an Ethiopian media and entertainment website founded on October 26, 2008.

06/02/2024

በትናንትናው ስንፋጅ ነገን እያጣን ስለሆነ አሰባሳቢ የጋራ ትርክት ያስፈልገናል - ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)

ኢትዮጵያ ውስጥ በትናንትናው ስንፋጅ ነገን እያጣን ስለሆነ ልክ እንደ ዓድዋ አሰባሳቢ የጋራ ትርክት ያስፈልገናል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ በትናንትናው ስንፋጅ ነገን እያጣን በመሆኑ የጋራ ትርክት እጅግ አስፈላጊና መሠረታዊ ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡

ሰው ከትናንት ተምሮ፤ ዛሬ ሠርቶ፤ ነገን ማነጽ እንጂ ዛሬ ላይ ሆኖ በትናንትና እየተፋጀ ነገን ማጣት አይገባውም ሲሉም በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

ለዚህ ደግሞ ልክ እንደ ዓድዋ አሰባሳቢ የጋራ ትርክት እንደሚያስፈልግም አስገንዝበዋል፡፡

ዓድዋ መደመርን በተግባር ያሳየ፤ የጋራ ትርክትን በአንድ ቦታ ያሳየ ፕሮጀክት መሆኑን ጠቅሰው፤ ልክ እንደዚህ ንግግሮቻችንም ሰብሳቢ ቢሆኑ ይመረጣል፤ የሚያዋጣውም ይሄው ነው ብለዋል፡፡

የጋራ ትርክትን በተደራጀ አግባብ ተቋማዊ ማድረግ እንደሚገባም ነው ያመላከቱት፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ከተፈጠረው የባሰ አደጋ አጋጥሟቸው የነበሩት ደቡብ አፍሪካ፣ ጀርመን፣ ካናዳ እና ሩዋንዳ ችግራቸውን ጥለው የጋራ ትርክት በመገንባታቸው ብልጽግናን ተጎናጽፈው በሰላም እየኖሩ ነው ብለዋል፡፡

የጋራ ትርክት ከግላዊ አጨቃጫቂ ችግሮች መውጫ የመፍትሔ መንገድ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

(ኤፍ ቢ ሲ)

06/02/2024

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር ሲሸጥ በነበረበት ዋጋ የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።

በዚህም መሰረት ከጥር 28/05/2016 ዓ.ም ጀምሮ የሁሉም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በስራ ላይ በነበረበት ዋጋ እንዲቀጥል ተወስኗል።

(ኢ.ፕ.ድ)

06/02/2024

ድርቅን በተመለከተ የጠ/ሚ ዐብይ ማብራሪያ!...

"ድርቅ በተለያዩ አከባቢዎች ተከስቷል፡፡ ድርቁ የሰው ሕይወት እንዳይቀጥፍ ተባብረን መስራት አለብን፡፡ ነገር ግን ድርቁን ለፖለቲካ ፍጆታ ለማዋል የሚደረገው ጥረት ግን ተገቢነት የለውም፡፡ ድርቁን ለመከላከል በሚደረገው ስራ ውስጥ ትልቁን ድርሻ የሚይዘው መንግስት ነው፡፡ መንግስት ድርቁን ለመከላከል ከ14 ቢሊዮን ብር በላይ በማውጣት ሰብዓዊ ድጋፍ ተደራሽ እንዲሆን አድርጓል፡፡ መንግስት በቀጣይም ፕሮጀክቶችን በማጠፈም ጭምር ድርቁ በዜጎች ህይወት ላይ ጉዳት እንዳያደርስ የሚሰራ ይሆናል፡፡"

06/02/2024

"ከግጭት፣ ከጸብ፣ ከስድብ የምናተርፈው ነገር የለም፤ በአማራ ክልል፣ በትግራይ ክልል በነበረው ግጭት ምንም አላተረፍንም..."
ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ

06/02/2024

የካርል ሐውልት ጉዳይ ትዝብት ውስጥ የሚጥለን ብቻ ሳይሆን ሌላ ካርል እንዳይኖረን የሚያደርግም ነው፡፡
***
(ስናፍቅሽ አዲስ - ለድሬ ቲዩብ)

ሰሞኑን ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የታላቁ የበጎ አድራጎት የሚስተር ካርል ሐውልት ፈርሶ መሬት ወድቆ ስመለከተው እያደር ማነስ ባህላችን እየሆነ መጣ እንዴ አስብሎኛል፡፡

የአዲስ አበባ መንገድ መጨናነቅና የትራፊክ ፍሰት ስቃይ ይቀንስ ዘንድ በከተማዋ የነበሩ አደባባዮችን ወደ መብራት የመቀየሩ ስራ የተሻለ መፍትሔ ለመፈለግ ስለሆነ ልማቱ ላይ ቅሬታ የለኝም፡፡ ይሁን እንጂ በልማት ስም የሞራል ጥፋት ደግሞ ትናንትን ማውደም ብቻ ሳይሆን ነገ እንዳይኖረን ማድረግ ነው፡፡

ከዚህ ቀደም አሌክሳንደር ፑሽኪን የተባለን የሩሲያ ገጣሚ በአያቱ ሀበሻ ነው ብለን በአዲስ አበባ ጎዳና ሳር ቤት አካባቢ ሐውልት አቆምንለት፤ ያ ሐውልት በመንገድ ልማት ሲነሳ አነሳሱም የደረሰበትም ግልጽ ሳይሆን ስም ብቻ ሆኖ ቀረ፡፡

አሁን ደግሞ ሳር ቤት ቀድሞ ካርል አደባባይ ይባል በነበረው ስፍራ ቆሞ የነበረው እና የሰዎች ለሰዎች መስራችና የኢትዮጵያን ባለውለታ ይዘክር ዘንድ የቆመው የካርል በም ሐውልት አደባባዮን ወደ መብራት ለመቀየር በሚሰራ ስራ እንዲፈርስ ተደርጓል፡፡

ሐውልቱን ማፍረሱ ሳይሆን ጥፋቱ የሐውልቱ አፈራረስ ሥርዓትና ክብር ውለታ የማያውቁ ህዝቦች በሚያስብለን ደረጃ በነገ ካርሎቻችን ዘንድ ትዝብት ውስጥ የሚጥለን መሆኑ ነው፡፡

ካርል ሩቅ የምንለው በጎ ሰው ብቻ አይደለም፡፡ ከኢትዮጵያውያን ጋር ስለተጋራው ህመም መከራና ችግር ሁሉ ስናመሰግነው የምንኖር ባለውለታችን ሲሆን ለዚህም በኢትዮጵያ የክብር ዶክትሬት የተሰጠው ከዚያም ሲያልፍ በኦሮሞ ባህል በሞጋሳ ጎሳ አግኝቶ ኦሮሞነትን የተቀናጀ ነው፡፡

የዚህ ሰው ሐውልት ተሰርቶ ሲመረቅ እንደነበረው ደማቅ ስነ ስርዓት ሁሉ አሁን ደግሞ በቦታው የሚቆይበት ሁኔታ ከሌለ በተመሳሳይ መልኩ በክብር እና በድምቀት በማርሽ ባንድ ታጅቦ፣ የክብር እንግዶችና አድናቂዎቹ በተገኙበት ሊነሳ የሚገባበት ሁኔታ መፈጠር ሲገባው እንደ አሮጌ አጥር ባለውለታችን ያልነውን ታላቅ ሰው ሐውልት አፍርሶ መጣል አስገራሚ ነው፡፡

እንዲህ ስናደርግ ውለታ መብላት ብቻ ሳይሆን ነገ የሚውልልን ማጣትም ያመጣል ብዬ አምናለሁ፡፡ ብዙ ካርል ያስፈልጉናል እነሱ ደግሞ ነገም ከነገ ወዲያም የሚተካኩ ናቸው፡፡ በካርሎቿ የምታላግጥ ሀገር ከሆነች ስለ ኢትዮጵያ ለመድከም ማሰብ ሰብአዊነት እንኳን የማያሸንፈው ጭካኔን ይወልዳል፡፡
እንዲህ ያለ ባለውለታ ሐውልት በክብር አሰርቶ አስመርቆ ያቀመ ከተማ ድንገት በሆነ ቀን በጉልበት ሰራተኛ ነቅሎ አንዱ ጥግ መወርወር ካለፈው ካርል ይልቅ በሚመጡት ካርሎቻችን ላይ ቅሬታ የሚፈጥር፣ ይህቺስ ሀገር እንዲሉን የሚያደርግ እንደሆነ አስባለሁ፡፡

ዛሬ የሚከበሩ ሐውልቶች ነገ የሚገቡበት የማይታወቅባት ኢትዮጵያ ቀጣይ የሚባል ምልክቶችን በክብር ስለማኖር የሚያስብና የሚጨነቅ ማጣቷ ያሳዝናል፡፡

በካርል ሐውልት ውስጥ ደካማው ትናንትን የሚረሳ ያን መርሳት ደግሞ ነገ ሌላ ጠባሳ የሚያኖር እንደሆነ ለመረዳት አሁንም ዳተኞች እንደሆነንን ማሳያ ነው፡፡ ማን ያውቃል ዛሬ በማርሽ ባንድ የምናቆማቸው ሐውልቶች ነገ በተራቸው እንደ ትናንትናዎቹ የትም የሚወድቁ ይሆኑ ይሆናል?

06/02/2024

በኢትዮጵያ ውስጥ የፖለቲካ ፍላጎትን የማሳኪያ ስልት ልምምድ ሰላምን እየፈተነ ነው፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ባለፉት 50 እና 60 ዓመታት ሃሳብ ይዞ በሃሳብ አሸንፎ ስልጣን የመያዝ ልምምዱ ያልታየ በመሆኑ እንደባህልም እየተወሰደ ያለው የፖለቲካ ፍላጎትን በጠብመንጃ የማሳካት ፍላጎት አንዱ አደገኛ ስብራት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት የሰላም ችግር መሰረቱ የፖለቲካ ፍላጎት ማሳኪያ መንገድ ላይ ያለው ልምምድ መሆኑን ተናግረዋል።

የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት በሚደረጉ ጥረቶች ውስጥም ቢሆን እንደሀገር ያለን ልምምድ በውይይት ወይም በሽምግልና ለመፍታት ያለው ልምምድ አንስተኛ መሆኑን ጠቁመዋል።

በእነዚህ ችግሮች ውስጥም ተሁኖ የሰላም ጅማሮዎች ሲኖሩ ደግሞ ከግራም ከቀኝም በሰላም መንገድ ላይ ወጥመድ ማስቀመጥ መኖሩ የሰላም ልምምዱ ወደ ኋላ እንዲመለስ የማድረግ ልምምዱም ከፍተኛ ነው ብለዋል።

(EBC)

Photos from DireTube's post 06/02/2024

በተደጋጋሚ የመኪና ዕቃ ስርቆት ሲፈፅም የነበረ ተከሳሽ በእስራት ተቀጣ፡፡

ንጉሱ መኮንን የተባለው ተከሳሽ ወንጀሎቹን ሲፈፅም የነበረው በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ሰሚት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው።

የሰሚት አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ወንጀል መርማሪ ዋና ሳጅን ሰላማዊት አማረ እንደተናገሩት ተከሳሹ በለሊቱ ክፍለ ጊዜ የግቢ አጥር ላይ ዘሎ በመግባት ቆሞ ከሚያገኘው መኪና ላይ የግራና የቀኝ ስፖኪዮ በመንቀል ሰርቆ ሲሰወር ቆይቷል፡፡

እንደመርማሪዋ ገለፃ ፖሊስ የፈፃሚውን ማንነት ለማወቅ ጥናትና ክትትል ሲያደርግ ቆይቶ በቁጥጥር ስር ካዋለው በኋላ በተከናወነ ምርመራ የማስፋት ስራ የሶስት ተሽከርካሪዎችን የግራና የቀኝ ስፖኪዮ እንዲሁም የአንድ ተሽከርካሪን መስታወት በድንጋይ በመስበር በውስጡ ተቀምጦ የነበረ ላፕቶፕ ኮምፒውተር መስረቁን ማረጋገጥ ተችሏል፡፡

ንጉሱ መኮንን በፈፀማቸው ወንጀሎች አራት የክስ መዝገብ የተደራጀበት ሲሆን ጉዳዩን ሲመለከት የቆየው የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለሚ ኩራ ምድብ ችሎት በአንድ መዝገብ በ2 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ የወሰነበት መሆኑንና ቀሪዎቹ መዝገቦች ውሳኔ እየጠበቁ እንደሚገኙ ዋና ሳጅን ሰላማዊት ገልፀዋል።

(አዲስ አበባ ፖሊስ)

06/02/2024

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በምክር ቤት ለሚቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 14ኛ መደበኛ ስብሰባ ዛሬ ጥር 28 ቀን 2016 ዓ.ም ያካሂዳል ።

በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 55 (17) በተቀመጠውና በምክር ቤቱ የአሠራርና የአባላት ስነምግባር ደንብ ቁጥር 6/2008 መሠረት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በምክር ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች የሚሰጡትን መልስና ማብራሪያ የሚያዳምጥ ይሆናል።

በዚሁ መሠረት ምክር ቤቱ በነገው ዕለት በሚያካሂደው 14ኛው መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በምክር ቤት ለሚቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ የሚሰጡ እንደሚሆን ይጠበቃል።(ሕ/ተ/ም/ቤት)

Photos from DireTube's post 05/02/2024

ከትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚደንት ፅ/ቤት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የተሰጠ መግለጫ

Photos from DireTube's post 05/02/2024

2 ቢሊየን ብር ካፒታል ኢንቨስትመንት ያስመዘገበ ኩባንያ ወደ ስራ ሊገባ ነው

በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ላይ 7 ሺ ስኩዌር ሜትር የለማ መሬት ላይ 2 ቢሊየን ብር ኢንቨስት የተደረገበት ገሊላ የቆዳ ጫማና ሶል ማምረቻ ኩባንያ ወደ ስራ ሊገባ መሆኑ ተገልጿል።

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ የኩባንያውን ባለቤት አቶ በርሄን በፅ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ዋና ስራ አስፈፃሚው ኩባንያው ያለበትን የቅድመ ኦፕሬሽን ስራ አድንቀው ኩባንያው በሙሉ አቅሙ ስራ እስኪጀምር ድረስ የኮርፖሬሽኑ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። ገሊላ ማኑፋክቸሪንግ ኮርፖሬሽኑ ለሀገር በቀል ባለሀብቶችና ኩባንያዎች የሰጠውን ልዩ ትኩረት ማሳያ ነው ሲሉም ገልፀዋል።

ገሊላ ማኑፍክቸሪንግ በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ 7ሺ ስኩዌር ሜትር የለማ መሬት በመውሰድ የቆዳ ጫማዎችን እና ሶሎችን ለማምረት ማምረቻ ገንብቶ ያጠናቀቀ ሲሆን ማምረቻ ማሽኖችን የመገጣጠም እና የመጨረሻ ጥቃቅን ስራዎችን የማጠናቀቅ ስራ ብቻ ይቀረዋል።

ኩባንያው 2 ቢሊዮን ብር ያህል ኢንቨስት ያደረገ ሲሆን ከ2300 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል የሚፈጥር ይሆናል። ኩባንያው በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ ሲገባ ምርቶቹን ለጣሊያን ፤ ለተርኪዬ እና ለሌሎች የአውሮፓ ሀገራት ኤክስፖርት የሚያደርግ ይሆናል።

(የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን)

05/02/2024

👉በከተማችን አዲስ አበባ ቁልፍ ቦታዎችን አዘጋጅቶ ለግንባታ ዝግጁ አድርጓል ።

👉 በጎሮ ፣በላንቻ፣በጣሊያን ኤምባሲ ሳይቶች ህብረት ስራ ማህበራትን አደራጅቶ ግንባታ ጀምሯል።

👉 በመደበኛው ሞዴል ቀደም ሲል በነበረው ምዝገባ በቀሩት ጥቂት ቦታዎች በመመዝገብ በዕድሉ እንድትጠቀሙ ተጋብዘዋል ።

👉በሳራ አምፖል ሳይት በቀሩት ጥቂት ቦታዎች ፈጥነው ይመዝገቡ ።

https://youtu.be/L5bpW6rvXKE?si=eEIddfOV9xlvhkgb

ጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ
ቅድሚያ የመጣ ቅድሚያ ያገኛል።

Photos from DireTube's post 05/02/2024

የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤን ጨምሮ የምክር ቤቱ አባላት አዲሱን የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየምን ጎበኙ።

የኢፌዴሪ የሕዘብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎ የአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም፤ ሀገራዊ የጋራ ታሪካችንን በመዘከር አንድነታችንን የምናጠናክርበት እና የወደፊት ብልጽግናችንን የምናረጋግጥበት ነው ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተደደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ኘሮጀክትን በተመለከተ ለጎብኝዎቹ ገለፃ ያደረጉ ሲሆን፤ ከኘሮጀክቱ ጅማሪ እስከ ፍፃሚው ድረስ ለተሳተፉና አሻራቸውን ላስቀመጡ ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

በጉብኝቱ የምክር ቤቱን አፈ- ጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎን ጨምሮ ምክትል አፈ ጉባዔ፣ የመንግስት ተጠሪ እና ሌሎች የምክር ቤቱ አመራሮችና አባላት ተሣትፈዋል፡፡

የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የኢትዮጵያውያን የአብሮነት፣ የአንድነትና የአሸናፊነት ተምሳሌት የሆነው የዓድዋ ድል የታሪክ ስብራት የሚጠግን እና ለትውልድ የሚተላለፍ ህያው ታሪክ ሆኖ መገንባቱን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላቱ በጉብኝት ወቅት ገልፀውልናል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማኀበራዊ ገፃቸው አስፍረዋል።

Photos from DireTube's post 05/02/2024

አሐዱ ባንክ አ/ማ ከመገናኛ ብዙሐን ባለሙያዎች ጋር በቅርበት መሥራት የሚያስችለው ጉዳይ ላይ መከረ።

በማርዮት ኤክኪዩቲቭ አፓርትመንት ሆቴል ዛሬ ጥር 27/2016 ዓ.ም በተካኼደው መርሐግብር የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች የባንኩ ልዩ ደንበኛና ተጠቃሚ እንዲሆኑ እንዲሁም ባንኩ በሚያከናውናቸው የኮምኒኬሽን፣ የሚድያና የማኀበራዊ ኃላፊነት ተግባራት አጋር በሚሆኑበት ጉዳይ ላይ የውይይት መነሻ ኀሳብ ቀርቦ በዝርዝር ተወያይተዋል።

አንዳንድ የሚድያ ባለሙያዎች ስለመርሐግብሩ በሰጡት አስተያየት አሐዱ ባንክ በራሱ ተነሳሽነት የሚድያ ባለሙያዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የብድር ሥርዓት በማስተዋወቁ መደሰታቸውን ገልፀዋል።

አሐዱ ባንክ በተመሠረተ በአንድ ዓመት ተኩል ዕድሜው ካፒታሉን ወደ 5 ቢልየን ብር ከማሳደጉ በተጨማሪ ከ12 ሺ በላይ ባለአክስዮኖች፣ 3 ነጥብ 3 ቢልየን ተቀማጭ፣ ከ500ሺ በላይ ደንበኞችን፣ ከ4 ነጥብ 7 ቢልየን ብር በላይ ሐብት ማፍራቱ በመድረኩ ላይ በባንኩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገልጿል።(በድሬቲዩብ ሪፖርተር)

Photos from DireTube's post 05/02/2024

የአባይ ወንዝ ድልድይ መዳረሻ መንገድ ፕሮጀክት አስፓልት ንጣፍ ስራ ተጀመረ

በባሕር ዳር ከተማ ውስጥ በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘው ግዙፉ የአባይ ወንዝ ድልድይ መዳረሻ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት አስፓልት ንጣፍ ስራ ተጀመረ፡፡

ከሄኒ ጋርደን አደባባይ እስከ ዘንዘልማ መገንጠያ ድረስ የሚዘልቀው 4.7 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የባሕር ዳር አባይ ወንዝ ድልድይ መዳረሻ መንገድ የአፈር ቆረጣ እና ሙሌት እንዲሁም የመፋሰሻ ቱቦ ዋና ዋና ስራዎች በአብዛኛው ተጠናቀዋል፡፡ በተጨማሪም የሰብቤዝ ንጣፍ ፣ የቤስ ኮርስ ንጣፍ ፣ የቤዛዊት መንገድ መሿለኪያ እና መወጣጫዎች ሙሌት እንዲሁም የከርብስቶን ስራዎች በሰፊው ሲከናወን ቆይቶ ወደ አስፓልት ንጣፍ ስራ ተሸጋግሯል፡፡

የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቱ አሁን ላይ ያለበት የአፈፃፀም ደረጃ 38.2% ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት የአስፋልት እና የትራፊክ ምልክቶች ተከላ ፤ የቀለም ቅብ ስራዎች ፤ የመንገድ ላይ መብራቶች ተከላ እንዲሁም የእግረኛ መንገድ ንጣፍ በስፋት ለመጀመር ከፍተኛ ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል፡፡

የመንገዱን ግንባታ ለማከናወን የተመደበውን 825,659,857 ብር ሙሉ ለሙሉ የተሸፈነው በኢትዮጵያ መንግስት ነው።
መንገዱ የእግረኛ እና አካፋይን ጨምሮ መደበኛ ቦታዎች ላይ 51 ሜትር እንዲሁም የህዝብ ማጓጓዣ ማቆሚያ ቦታዎች ላይ 59 ሜትር ስፋት አለው፡፡

ከዚህም ባሻገር በአንድ ጊዜ በግራ እና በቀኝ 6 መኪናዎችን ማስተናገድ እንዲችል ተደርጎ በመገንባት ላይ የሚገኝ ሲሆን ፤ የመኪና ማቆሚያ ቦታንም ጭምር አካቶ በባህር ዳር ከተማ ፍኖተ ካርታ መሰረት የሚገነባ ሰፊ የመንገድ ፕሮጀክት ነው፡፡

ግንባታው ሃፍኮን ኮንስትራክሽን እና ክሮስ ላንድ ኮንስትራክሽን በተባሉ ሀገር በቀል የስራ ተቋራጮች በጥምረት በመካሄድ ላይ ነው፡፡ የማማከርና የቁጥጥር ስራውን ደግሞ ቦቴክ ቦስፈረስ የተባለ የውጭ ሀገር አማካሪ ድርጅት ከሀገር በቀሉ ስታዲያ ኢንጂነሪንግ ስራዎች ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ንዑስ አማካሪ መሃንዲስ ጋር በጋራ በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡

መንገዱ የኢትዮ ሱዳን ዋና መስመር የሆነው የአዲስ አበባ - ባህርዳር - ጎንደር-መተማ መንገድ አንዱ ክፍል ነው፡፡ ግንባታው ተጠናቆ ለትራፊክ አገልግሎት ክፍት ሲሆን ፤ በአገልግሎት ብዛት የተጎዳውን ነባር የባህር ዳር አባይ ወንዝ ድልድይ የትራፊክ ጫና ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ያስተነፍሳል ተብሎ እንደሚታመን በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የፕሮጀክቱ አስተዳዳሪ ኢንጅነር አዲስሕይወት ታደሰ ገልፀዋል፡፡

(ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር)

Photos from DireTube's post 05/02/2024

ቡና በህገ ወጥ መንገድ አከማችተው ለመሸጥ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ከ260 ኬሻ በላይ ቡና በህገ ወጥ መንገድ አከማችተው ለመሸጥ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

ተጠርጣሪዎቹ ቡና ለመሸጥ የሚያስችል ምንም አይነት ህጋዊ ፈቃድ የላቸውም፤ ነገር ግን በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ፉሪ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኝ አንድ መጋዘን ውስጥ ቡና ስለማከማቸታቸው መረጃ እና ጥቆማ የደረሰው ፖሊስ ክትትል ማድረግ ይጀምራል፡፡

ቡናውን የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3- A10225 ኢት በሆነ ተሽከርካሪ ጭነው ወደ ሌላ ቦታ ወስደው ለመሸጥ ሲንቀሳቀሱ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 አያት አካባቢ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ነው የተገለጸው።

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የልዩ ልዩ ወንጀል ምርመራ ክፍል ከፌደራል ቡና እና ሻይ ባለስልጣን ባገኘው መረጃ መሰረት ተጠርጣሪዎቹ ምንም አይነት ፍቃድ የሌላቸው ሲሆን በቁጥጥር ስር የዋለው 267 ኬሻ ቡና በፍርድ ቤት ትዕዛዝ መሰረት ለኢትዮጵያ ምርት ገበያ ገቢ እንዲሆን ተወስኗል፡፡ በተጠርጣሪዎቹ ላይም ምርመራ እየተጣራ እንደሚገኝ
ከአዲስ አበባ ፖሊስ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ህገ- ወጥ ንግድ በህጋዊ የንግድ ስርዓቱ ላይ አሉታዊ ጫና የሚያሳድር እና ጤናማ ገበያን የሚያቃውስ በመሆኑ መሰል ህገ ወጥ ተግባራትን ለመከላከል የህብረተሰቡ ተባባሪነት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳስቧል።(አዲስ ዋልታ)

Photos from DireTube's post 05/02/2024

በቦስተን የኒው ባላንስ የቤት ውስጥ ውድድር ጉዳፍ ፀጋይና ለሜቻ ግርማ አሸነፉ

በቦስተን የኒው ባላንስ የዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ውድድር ጉዳፍ ፀጋይ እና ለሜቻ ግርማ ውድድሩን በበላይነት አጠናቅቀዋል፡፡

በ1 ሺህ 500 ሜትር የተወዳደረችው ጉዳፍ ፀጋይ ርቀቱን በ3 ደቂቃ 58 ሰከንድ ከ11 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ቀዳሚ ሆናለች፡፡

በዚሁ ርቀት የ18 ዓመቷ አትሌት ብርቄ ሀየሎም 3 ደቂቃ 58 ሰከንድ ከ43 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት 2ኛ ደረጃን ይዛለች፡፡

ወጣቷ አትሌት ብርቄ ሀየሎም በርቀቱ ያስመዘገበችው ሰዓት ከ20 ዓመት በታች የዓለም ፈጣኑ ሰዓት ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

በተመሳሳይ አትሌት ለሜቻ ግርማ የ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ውድድርን በ7 ደቂቃ 29 ሰከንድ ከ08 ማይክሮ ሰከንድ በማጠናቀቅ ማሸነፉን የቦስተን ማራቶን መረጃ ያመላክታል፡፡

(ኤፍ ቢ ሲ)

05/02/2024

"በአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ አስገራሚ የጨዋታ ድራማዎች የሽርፍራፊ ሰከንድ ተዓምሮች አየተዝናኑ ፣ የአፍሪካ ዋንጫው ኦፊሺያል ስፖንሰር የሆነው ቴክኖ ሞባይል አዲሱን ‘Spark 20 pro+’ ስልክ የእርሶ እንዲያደረጉ ሲጋብዝዎ ታላቅ ደስታ ይሰማዋል ።

05/02/2024

በዲጂታል የነዳጅ ግብይት ሥርዓት ከ155 ቢሊየን ብር በላይ ግብይት ተፈጸመ

በዲጂታል የነዳጅ ግብይት ሥርዓት ከ155 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ ግብይት መከናወኑን የነዳጅና ኢነርጂባለስልጣን አስታወቀ፡፡

የነዳጅ ግብይት በዲጂታል ሥርዓት መካሄድ ከጀመረበት ሚያዝያ 2015 ጀምሮ እስካሁን ከ155 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ ግብይት መፈጸሙን የባለስልጣኑ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር በቀለች ኩማ ተናግረዋል፡፡

ግብይቱ በዲጅታል መሆኑ በዘርፉ ያለውን ኮንትሮባንድ በመቆጣጠር፣ የነዳጅ ብክነትን በማስቀረት እና ግብይቱን በማቀላጠፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱንም ጠቅሰዋል፡፡

ይሁን እንጂ አሁንም በግብይት ሂደቱ ላይ ክፍተቶች መኖራቸውን ነው ያመላከቱት፡፡

ግብይታቸውን በዲጅታል የማይፈጽሙ ማደያዎችን በመከታተልና ኦዲት በማድረግ ከነዳጅ ትስስሩ እንዲወጡ አቅጣጫ ተቀምጧል ብለዋል፡፡

በሀገሪቱ ከሚገኙ 1 ሺህ 589 ማደያዎች መካከልም 1 ሺህ 469 ያህሉ ግብይታቸውን በቴሌ ብር እየፈጸሙ መሆናቸውንም ነው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የተናገሩት፡፡

(ኤፍ ቢ ሲ)

05/02/2024

የ11 ዓመት ህፃን የደፈረው ግለሰብ በፅኑ እስራት ተቀጣ

ተከሳሽ የሱፍ ሙህዬ ነሐሴ 12 ቀን 2014 ዓ.ም በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ደመካ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በግምት ከቀኑ 8፡30 ሲሆን በ1996 ዓ.ም በወጣው የወንጀል ህግ አንቀፅ 627/1/ ስር የተመለከተውን በመተላለፍ እድሜዋ 11 አመት ከ8 ወር የሆነችን ህፃን አስገድዶ በመድፈር ወንጀል ፍ/ቤት ቀርቧል፡፡

የክስ ዝርዝሩ እንደሚያስረዳው የህፃኗ እናት በተከሳሽ ቤት በተመላላሽ ሰራተኝነት የምትሰራ ሲሆን ህፃኗን ይዛት የምትሄድ ከመሆኑም በተጨማሪ እናቷ በሌለችበትም ጊዜም በግለሰቡ ቤት ትላላካለች በእለቱም በተከሳሽ ቤት ውስጥ TV እያየች በተኛችበት በግምት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት አካባቢ የግብረስጋ ግንኑነት የፈጸመባት እና ክብረ ንጽህናዋ እንዲገረሰስ ያደረገ በመሆኑ ዐቃቤ ህግ በ1996 የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀፅ 627/1/ ስር የተመለከተውን በመተላለፍ ህፃናት ልጆች ላይ የሚፈጸም የግብረ-ስጋ ድፍረት በደል ወንጀል ክስ መስርቶበታል፡፡

ተከሳሽም ፍ/ቤት ቀርቦ አቃቤ ህግ የተከሳሽን ጥፋተኛነት ያስረዳሉ ያላቸውን የሰውና የሰነድ ማስረጃናዎች በማቅረብ የተከራከረ ሲሆን ተከሳሽ እንዲከራከር ብይን ቢሰጠውም ጥፋቱን ማስተባበል ባለመቻሉ ፍ/ቤቱም ጥፋተኛ ብሎታል፡፡

በመጨረሻም የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የካ ምድብ 7ኛ ወንጀል ችሎት የቅጣት ማክበጃ እና ማቅለያ ሁኔታዎችን በማየት ተከሳሹ በ14 ዓመት ከ4 ወር ፅኑ እስርት እንዲቀጣ ሲል ወስኖበታል፡፡

(ፍትህ ሚኒስቴር)

05/02/2024

ጎበዝ ሹፌር ጠንቃቃ ነው!!

04/02/2024

የቅሚያ ወንጀል ፈፅሞ ችሎት ሳይቀርብ የእስር ቅጣት የተላለፈበት ግለሰብ ከ4 ዓመት በኋላ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡
***
አላውዲ ደሊል የተባለው ግለሰብ ከሌሎች ግብራበሮቹ ጋር በመሆን ወንጀሉን የፈፀመው ሰኔ 5 ቀን 2010 ዓ/ም ከምሽቱ 2 ሠዓት ተኩል ገደማ በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው ባልቻ ሆስፒታል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው።

እየሩሳሌም በላይ የተባለችው የግል ተበዳይ በወቅቱ ከስራ ወደ ቤቷ እየሔደች በነበረችበት አጋጣሚ ተከሳሹ በእጇ የያዘችውን ቦርሳ እና ሞባይል ስልኳን ቀምቶ ለማምለጥ ሲሞክር ባሰማችው የድረሱልኝ ጥሪ በአካባቢው በነበሩ የህብረተሰብ ክፍሎች እና በፖሊስ ትብብር ከነ ግብራበሮቹ በቁጥጥር ስር ሊውል መቻሉን በክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ ከባልቻ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የተገኘው መረጃ አመልክቷል፡፡

ተከሳሽ አላውዲ ደሊል እና ሶስት ግብራበሮቹ በፈፀሙት ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸው ፍርድ ቤት ከቀረቡ በኋላ የዋስትና መብት ተፈቅዶላቸው ጉዳያቸውን በውጪ ሆነው እንዲከታተሉ ቢደረግም በተደጋጋሚ ጊዜ በነበረው የችሎት ቀጠሮ ሳይቀርቡ በመቅረት ተሰውረው ቆይተዋል፡፡

ጉዳዩን ሲመለከት የቆየው ፍርድ ቤትም የቀረበለትን ማስረጃ መርምሮ ጥፋተኝነታቸውን በማረጋገጥ ጥቅምት 26 ቀን 2012 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሌሉበት እያንዳንዳቸው በአምስት አመት ከስድስት ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጡ እና ፖሊስም ተከታትሎ በመያዝ ፍርደኞቹን ለማረሚያ ቤት እንዲያስረክብ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

ፖሊስ የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ ለማስፈፀም ትኩረት ሰጥቶ ሲሰራ የቆየ ሲሆን አላውዲ ደሊል የተባለው ፍርደኛ ከአራት ዓመት ከወራት በኋላ ከተሰወረበት ብቅ ሲል ጥር 21 ቀን 2016 ዓ/ም በቁጥጥር ስር አውሎ ለማረሚያ ቤት አስረክቧል፡፡

ውሳኔ የተላለፈባቸው ግብራበሮቹን ለመያዝ ክትትሉ የቀጠለ ሲሆን ማንም ሰው ወንጀል ፈፅሞ ለጊዜው ሊሰወር ቢችል እንጂ ከህግ ተጠያቂነት የማያመልጥ በመሆኑ ህብረተሰቡ ወንጀል ፈፃሚዎችን አጋልጦ በመስጠት እደረገ ያለውን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል ፖሊስ ጥሪውን አቅርቧል፡፡
(አ/አ ፖሊስ)

Photos from DireTube's post 04/02/2024

ከንቲባዋ ከጎንደር ሕዝብ ጋር ፍሬያማ ውይይት አድርገናል አሉ
***
በታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ ተገኝተን "ዘላቂ ሰላም በማስፈን ለጋራ ሀገራዊ ችግሮች መፍትሔ ማስቀመጥ እና የህዝብን አንድነት መፍጠር" በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ከጎንደር እና አካባቢዋ ነዋሪዎች ጋር ፍሬያማ ውይይት አድርገናል::

ከውይይቱ በኃላም በጎንደር ከተማ በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ ነዋሪዎች የሚያገለግል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባለ ሃብቶችን በማስተባበር ለሚገነባው የመጀመሪያው የተስፋ ብርሃን ምገባ ማዕከል ከሲዳማ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ክቡር አቶ ደስታ ሊዳሞ ጋር በመሆን የመሰረተ ድንጋይ አስቀምጠናል::
የህዝባችንን ህይወት ለመቀየር በቀጣይም በጋራ እና በትብብር መስራታችንን የምንቀጥል ይሆናል::

አዳነች አቤቤ
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ

Photos from DireTube's post 04/02/2024

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት 3ኛ የስራ ዘመን 3ኛ አመት 7ኛ መደበኛ ጉባኤውን የተለያዩ አዋጆችን እና ሹመቶችን በማጽደቅ ተጠናቋል።

በትላንትናው እለት የተጀመረው ጉባኤ በዛሬው እለትም የቀጠለ ሲሆን የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር የአስፈፃሚው እና የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የግማሽ በጀት ዓመት ባቀረቡት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ የምክር ቤቱ አባላት አስተያየት እና ጥያቄዎች ቀርበው ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቶባቸው ሪፖርቱን በሙሉ ድምፅ አጽድቋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ፍርድ ቤቶች የዳኞች አስተዳደር ጉባኤን እንደገና ለማቋቋም የወጣ ረቂቅ አዋጅ ፤የድሬዳዋ አስተዳደር ፍርድ ቤቶች ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ እንዲሁም የድሬዳዋ አስተዳደር የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤትን እንደገና ለማቋቋም የወጣ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።

በመጨረሻም ምክር ቤቱ በአስተዳደሩ ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሀር የቀረበለትን የተለያዩ አስፈፃሚ አካላትና ልዩ ልዩ ሹመቶችን አጽድቋል።

በዚህም መሰረት ዶ/ር ጽጌረዳ ክፍሌ የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ሀላፊ ሆነው ተሹመዋል።

በመቀጠልም የተከበሩ ከንቲባ ለይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ዳኝነት አቶ ሌሊሴ አሊይ፣ አቶ ጀማል ዩኒስ፣ አቶ አዋሌ ኢልሚ፣አቶ ፋህሚ አብዶንና አቶ አባይነህ ሙላቱን በእጩነት ቀርበው በሙሉ ድምጽ ጸድቋል።

የምክር ቤቱ ም/አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ከሪማ አሊ ለምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ አባልነት አቶ አደም አሊ፣ አቶ ጀማል አብዲ፣ ወ/ሮ ኡመልኸይር ሙሴንና አቶ አብዲ ሀሰንን በእጩነት አቅርበው ሹመታቸው በሙሉ ድምፅ በማጽደቅ ጉባኤው ተጠናቋል።
(ድሬደዋ ኮምኒኬሽን)

Photos from DireTube's post 04/02/2024

"በአማራ ህዝብ ጥያቄዎች ሽፋን በህዝቡ ላይ ያልተገባ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጫና ለመፍጠር የሚደረገዉ ሙከራ ፍፁም ተቀባይነት የለዉም"

ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል
የብልጽግና ፓርቲ የስራ አስፈፃሚ አባልና የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር፣

የፌዴራል ልዑካን ቡድን ከደሴ ከተማና ከደቡብ ወሎ ዞን ከተወጣጡ ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ዙሪያ የምክክር መድረክ አደረገ።

በምክክር መድረኩ ላይ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል የብልጽግና ፓርቲ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የፌዴራል የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር፣ ፍፁም አሰፋ (ዶ.ር) የብልጽግና ፓርቲ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር፣ አቶ ሳዳት ነሻ የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ አባልና የብልጽግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ፣ አቶ ፍስሃ ደሳለኝ በአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊና የደሴና የደቡብ ወሎ ዞን አመራሮች ተገኝተዋል።

መድረኩን በእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት የከፈቱት የደሴ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ እንኳን ወደ አብሮነት፣ መቻቻልና የፍቅር ከተማ ወደ ሆነችዉ ደሴ ከተማ በሰላም መጣችሁ ደሴ እንግዳ ተቀባይ፣ ሁሉም ኃይማኖቶች ተቻችለው የሚኖሩባትና የአስተዋይ ህዝብ ባለቤት ናት ብለዋል።እንደ ከተማችንም በርካታ አንገብጋቢ የሆኑ የልማት ጥያቄዎችን በቻልነዉ ልክ እየሰራን እንገኛለን በቀጣይም አጠናክረን እንደምንሰራ ቃል እየገባሁ በድጋሚ ወደ ውቢቷ ደሴ ከተማ በድጋሚ እንኳን በደህና መጣችሁ በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል።

ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ባስተላለፉት መልዕክት "በአማራ ህዝብ ጥያቄዎች ሽፋን በአማራ ህዝብ ላይ ያልተገባ ጫና ለመፍጠር የሚደረገዉ ሙከራ ፍፁም ተቀባይነት የለዉም ብለዋል። የአማራ ህዝብ ሀገር በመገንባትና ኢትዮጵያን በማፅናት ሂደት ላይ የራሱን አበርክቶ በማድረግ ደማቅ አሻራ አሳርፏል፤ ይሄም በደማቅ ታሪክ ላይ ሰፍሮ ይገኛል ሲሉም ገልፀዋል።የሀገራችን የሰላም እጦት በርካታ ምክንያቶች አሉት በተለይም ያልተፈታና የከረመ ችግር፣ አዳዲስ የተፈጠሩ ፍላጎቶችና አለም የደረሰበት ደረጃ መድረስ አለመቻላችን ለሀገራችን የሰላም እጦት ዋነኛ ችግሮች ናቸዉ በማለት ገልፀዋል።

አቶ ሳዳት ነሻ በበኩላቸው እንደገለፁት የወሎ ህዝብ በሰላም ላይ ያለዉ እሴት እጅግ በጣም ጠንካራ ነው፣ በተለይም ህዝቡ ከአመራሩ ጋር እጅ ለእጅ ተያይዞ ሰላሙንና ልማቱን ማረጋገጥ በመቻሉ የሚያስመሰግነው ነው ሲሉ ገልፀዋል።የሀገራችን የፖለቲካ ስርዓት ባለፉት ዓመታት በኋላቀር የእርስ በእርስ የመጠፋፋት ፖለቲካ ላይ ያተኮረ ስለነበረ ሀገራችን በርካታ አላስፈላጊ ዋጋዎችን ከፍላለች ስለሆነም የዴሞክራሲና የፖለቲካ ግንባታ ባህላችንን በማስተካከል ወደ ቀደመዉ ክብራችን መመለስ አለብን ብሎ ፓርቲያችን ብልጽግና አቋም የያዘ ሲሆን በተደጋጋሚ ጊዜም ከነፍጥ ትግል ወደ ሀሳብ ትግል እንምጣ በሚል ተደጋጋሚ ጥሪ አቅርቧል ሲሉ አብራርተዋል።

የአማራን ህዝብ ጥያቄዎች ፓርቲያችን ብልጽግና አምኖና ቆጥሮ ይዟል በከፍተኛ ሁኔታም እንዲፈቱ እየሰራ ይገኛል፤ ጥያቄዎች የሚፈቱበት ማዕቀፍ ከሌሎች ኢትዮጵያዊን ጋር በወንድማማችነትና በህትማማችነት የትብብር መንፈስ ነዉ ለብቻ ተሁኖ የሚፈታ ጥያቄም ችግርም የለም ብለዋል። ተፈናቃዮችን ለመመለስ አበረታች ስራ እየተሰራ ነዉ በቅርቡም በፍጥነት ወደ መኖሪያ ቀያቸው የሚመለሱ ይሆናል፤ በርካታ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ ነው ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው በመመለስ የፖለቲካ መነገጃና መጠቀሚያ እንዳይሆኑ በጋራ ልንሰራ ይገባል። እናንተም ከመንግስት ጎን በመቆም ልታግዙ ይገባችኋል በማለት ገልፀዋል።

ፍፁም አሰፋ (ዶ.ር) እንደተናገሩት አሁን የገጠመንና ፈተና የሆነብን የኑሮ ዉድነት ትልቁ መንስኤ የምርትና የምርታማነት ችግር ነዉ፣ ሌላዉ ለኑሮ ዉድነቱ መንስኤ የሆነው የሰላም እጦትና የተቋማት መዳከም በመሆኑ መንግስት ችግሩን ለመቅረፍ በረጂም ጊዜ ሊፈታ በሚችል ሁኔታ አማራጮችን ተጠቅሞ እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡ከስራ አጥነት አኳያ መንግስት ስራ ፈጣሪ አይደለም ስራን በዋናነት የሚፈጥረው የግሉ ሴክተሩ ነው የመንግስት ሚና ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠርና ተቋማትን ማጠናከር ነው ሲሉ አመላክተዋል።

04/02/2024

ጎጆ ብሪጅ...
👉በከተማችን አዲስ አበባ ቁልፍ ቦታዎችን አዘጋጅቶ ለግንባታ ዝግጁ አድርጓል ።

👉 በጎሮ ፣በላንቻ፣በጣሊያን ኤምባሲ ሳይቶች ህብረት ስራ ማህበራትን አደራጅቶ ግንባታ ጀምሯል።

👉 በመደበኛው ሞዴል ቀደም ሲል በነበረው ምዝገባ በቀሩት ጥቂት ቦታዎች በመመዝገብ በዕድሉ እንድትጠቀሙ ተጋብዘዋል ።

👉በሳራ አምፖል ሳይት በቀሩት ጥቂት ቦታዎች ፈጥነው ይመዝገቡ ።

https://youtu.be/L5bpW6rvXKE?si=eEIddfOV9xlvhkgb

ጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ
ቅድሚያ የመጣ ቅድሚያ ያገኛል።

04/02/2024

ዛሬ Feb 4(ጥር 26) ፡- የዓለም የካንሰር ቀን!!...
💞💕የእንክብካቤ ክፍተቱን ዝጋ?!..

👩 ⚕️👨 ⚕️ ስለ ካንሰር ቁልፍ እውነታዎች!..

🚨ካንሰር በአለም አቀፍ ደረጃ ለሞት የሚዳርግ ሁለተኛዉ ሕመም ነው፣

🚨በየዓመቱ 10 ሚሊየን ሰዎች በካንሰር ይሞታሉ፣

🚨ከ40 በመቶ በላይ የሚሆኑት በካንሰር ምክንያት የሚሞቱት ሞት ሊስተካከል ከሚችሉት እንደ ማጨስ፣ አልኮል መጠጣት፣ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አለማድረግ ጋር የተያያዙ ናቸው፣

🚨ከካንሰር ጋር በተያያዘ ከሚሞቱት መካከል ቢያንስ አንድ ሶስተኛው የሚሆነው አስቀድሞ በሚከናወን መደበኛ ምርመራ እና የቅድመ ምርመራ ህክምና መከላከል የሚቻል ነው፣

🚨70 በመቶ የካንሰር ሞት የሚከሰተው ከዝቅተኛ እስከ መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት ነው፣

🚨የመከላከያ ፣የቅድመ ምርመራ እና ህክምና ስልቶችን በመተግበር በየዓመቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ህይወትን ማዳን ይቻላል፣

🚨አጠቃላይ የካንሰር ዓመታዊ ኢኮኖሚያዊ ወጪ 1 ነጥብ 16 ትሪሊዮን ዶላር ይገመታል።

📣ስለ ካንሰር ግንዛቤን ለማሳደግ በጋራ እንስራ?!
(ዶ/ር ቤቴል ደረጀ/We Care)

Photos from DireTube's post 03/02/2024

ዳዎኤ ቡሹ/Dayoe Bushshu

በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት “ባህል ለልማትና ለአብሮነት ” በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ የነበረው የባህል ፌስቲቫል ተጠናቋል።

በክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ደስታ ሌዳሞ ጥር 21/2016 ዓ.ም የተከፈተው የባህል ፌስቲቫል ለተከታታይ 5 ቀናት ለህዝብ ክፍት በመሆን በርካታ ጎብኚዎችን ያስተናገደ ሲሆን የባህል ፌስቲቫሉ የሚፈለገውን ያህል ግንዛቤ ፈጥሯል ተብሏል።

“ዳዎኤ ቡሹ” የሲዳማ ብሄር የሰላምታ አሰጣጥ ዕሴት የሆነው ድንቅ ባህል ከአፍሪካ ድንቃ ድንቆች መዝገብ ድርጅት ጋር በመተባበር ዳዎኤ ቡሹ የሲዳማን ህዝብ ዕሴት ለአፍሪካ ለማስተዋወቅ እቅድ ተይዞ እየተሰራ ይገኛል።

“ዳዎኤ ቡሹ/Dayoe Bushshu” የሲዳማ ሕዝብ የሰላምታ አሰጣጥ ባህል ሲሆን ይህም ሕዝቦች እስር በርስ የመኖር አብሮነታቸውንን ከማጠናከር ባለፈ የሲዳማ ህዝብ ለእንግዶች በአክብሮት የሚሰጠው የሰላምታ ባህል ዕሴት ሲሆን ይህም የሕዝብ ለሕዝብ የመኖር መስተጋብሮች የሚጠናክር ከመሆኑ ባለፈ መከባበርን የሚገለፅበት መንገድ ነው።

የሲዳማ ሕዝብ “ለዳዎኤ ቡሹ” አንደ ማህበራዊ መስተጋብር እና ተግባቦት ትልቅ ዋጋ የሚሰጥ ሲሆን የመከባበር ፣ የእንግዳ ተቀባይነት በመሆኑም ማህበረሰቡ “ዳዎኤ ቡሹ” ባህል እሴት ነጸብራቅ ተደርጎ ይወሰዳል።

ይህም ዕሴት እንዲጎላ የሲዳማ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ከአፍሪካ ድንቃ ድንቆች መዝገብ ድርጅት ጋር በመሆን "የዳዎኤ ቡሹ" ፌስቲቫል ያካሄደ ሲሆን "ዳዮኤ ቡሹ" ለወደፊት ትልቅ ፌስቲቫል በሚሆንበት ደረጃ ለማሳደግ በጋራ ለመስራት ከስምምነት ተደርሷል::

የባህል ዐውደ ርዕይ፦ በፌስቲቫሉ የሲዳማ ህዝብ ባህላዊ ጥበባት፣እደ ጥበብ፣ አልባሳት እና ታሪካዊና ባሕላዊ ቅርሶች የሚያሳዩ በርካታ ቁሳዊ ታሪኮች ለመመልከት ተችሏል።

ባሕላዊ ትዕይንቶች፦ ሉዋ:ጉማታ: የግርዘት ሥርዓት: የግጭት አፈታት መርሆች መሰል ባህላዊ ኩነቶች በፌስቲቫሉ ላይ መመልከት ተችሏል።

በአውደ-ርዕይ፦የሲዳማ የተለያዩ ባህላዊ የምግብ ዓይነቶች እና መጠጦች መመገቢያቸው እና መጠጫ ቁሶች በፌስቲቫሉ ላይ ለጉብኝት ቀርበዋል።

የዕደ ጥበብ ውጤቶች፦ የቀርካሃ ውጤት ሥራዎች የሸክላ ውጤት ሥራዎች የስንደዶ የዘንባባ የሥራ ውጤቶች እና ወዘተ ለዕይታ የቀረቡ ሲሆን ፌስቲቫሉ በዕደ ጥበብ ዙሪያ ለተሠማሩ ማህበራት ምርቶቻቸው የገበያ ትሥሥር እንዲያገኝ ዕድል የፈጠረ እንደ ነበረ ለማወቅ ተችሏል::

ከባሕል ፈስቲቫሉ ጎን ለጎን የውይይት መድረኮች የተካሄዱ ሲሆን በዚህም በርካታ ስራዎች በቀጣይነት እንዲሰሩ በውይይት ላይ ተገልፇል።

የባህል ፌስቲቫሉ በሲዳማ ክልል ቱሪዝምን ለማስተዋወቅ ለማነቃቃት ጥሩ መድረክ ሆኖ ያገለገለ ሲሆን የክልሉን የተፈጥሮ ውበት፣ ታሪካዊ ስፍራዎች እና የባህል መስህቦች በፌስቲቫሉ ላይ ለማሳየት ጥረት ተደርጓል።

03/02/2024

!!

👉በከተማችን አዲስ አበባ ቁልፍ ቦታዎችን አዘጋጅቶ ለግንባታ ዝግጁ አድርጓል ።

👉 በጎሮ ፣በላንቻ፣በጣሊያን ኤምባሲ ሳይቶች ህብረት ስራ ማህበራትን አደራጅቶ ግንባታ ጀምሯል።

👉 በመደበኛው ሞዴል ቀደም ሲል በነበረው ምዝገባ በቀሩት ጥቂት ቦታዎች በመመዝገብ በዕድሉ እንድትጠቀሙ ተጋብዘዋል ።

👉በሳራ አምፖል ሳይት በቀሩት ጥቂት ቦታዎች ፈጥነው ይመዝገቡ ።

https://youtu.be/L5bpW6rvXKE?si=eEIddfOV9xlvhkgb

ጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ
ቅድሚያ የመጣ ቅድሚያ ያገኛል።

Photos from DireTube's post 03/02/2024

የብርሃን ዘኢትዮጵያ እቴጌ ጣይቱ ሀውልት በደብረታቦር ከተማ!
***
የሀገር ባለውለታ ለኾኑት እቴጌ ጣይቱ በደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር ሐውልት ቆመላቸው።
*******
የዓድዋ ጀግናዋ ንግሥት እቴጌ ጣይቱ በደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር ሐውልት ቆሞላቸዋል።

የሐውልት አሠሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ ቄስ መልካሙ ላቀው ስመ ጥር የኾኑ ጀግኖችን መዘከር፣ ለተተኪው ትውልድ ታሪክን ለማስተማር ይረዳል ነው ያሉት።

ለእቴጌ ጣይቱ ሐውልት ማቆም ትውልድን ማስተማር፣ ታሪክን ማክበር ነው ብለዋል።

ገድላቸውን መዘከር ስላስፈለገ ከተማዋን የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ እና በእቴጌ ታሪክ ትውልድን ለማስተማር መኾኑን አንስተዋል።

የካቲት 23/2015 ዓ.ም የመሠረተ ድንጋዩ የተቀመጠለት ሐውልቱ ጥር 25 /2016 ዓ.ም ተመርቋል።

ሐውልቱን በልደታቸው ነሐሴ 12 ቀን ለማስመረቅ ታስቦ እንደነበር እና በጸጥታ ችግር ምክንያት መቆየቱም ተመላክቷል።

ሐውልቱ በከተማዋ ነዋሪዎች እና በመንግሥት በጋራ የተሠራ ነው መኾኑም ተገልጿል።

የደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ደሴ መኮንን የእቴጌ ሐውልት የጥንታዊነት እና የታሪካዊነት እውነተኛ ማሳያ መኾኗንም ገልጸዋል።

ደብረ ታቦር የመጀመሪያው ኢንዱስትሪ የተሠራባት እና አያሌ ታሪኮች ያሏት ከተማ መኾኗን አመላክተዋል።

የዓድዋ ጀግናዋን ንግሥት ሐውልት ማቆም ታሪክ አክባሪነትን እንደሚያሳይም ገልፀዋል።

ሁላችንም ለታሪክና ባሕላችን መጠበቅ ርብርብ ማድረግ ይገባናል ብለዋል ሲል የዘገበው አሚኮ ነው።

Photos from DireTube's post 03/02/2024

የሴላቪ በርገር 15ኛ ዓመት የምስረታ በአሉን አከበረ

የሴላቪ በርገር 15ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በዛሬው እለት ቦሌ ብራስ በሚገኘው በዋናው ሴላቪ በርገር አክብሯል።

ሴላቪ በርገር 15ኛ አመት የምስረታ በዓሉን ምክንያት በማድረግ ከፊታችን ከዛሬ ጀምሮ እስከ የካቲት 9 ቀን 2016 ድረስ ለተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ በሚያዘጋጃቸው የተለያይ መጠን ያላቸው በርገሮች ዋጋ ላይ የ50 በመቶ ቅናሽ 'የተለያዩ ሽልማት የሚያሰጡ አዝናኝ ጨዋታዎች 1 በሴት ስራ ፈጣሪዎች ዙሪያ የተለያዩ ዝግጅቶችና በመጨረሻውም ቀን የ15ኛ አመት ምስረታ የመዝጊያ ቀነ ላይ በርገሮችን በ15 ብር ብቻ ለደንበኞች በማቅረብ ምስጋና እንደሚያቀርብ ተገልጿል።

ሴላቪ ቺክን ኤንድ በርገር ሴላቪ በርገር በሚል የንግድ ስም ላለፉት 15 አመታት በዋናውና በተለያዩ ቅርንጫፍ ሱቆቹ ለደንበኞቹ የተለያየ መጠን ያላቸው በርገሮችን ሲያዘጋጅ የቆየ ድርጅት ነው፡፡

በዚህ 15ኛ ዓመት ምስረታ በዓል ምክንያት በተካሄደው በደንበኞችን የእናመስግናለን የመክፈቻ ፕሮግራም ላይ እንደተገለፀው ሴላቪ በርገር በ3 ሰራተኛ ተጀምሮ አሁን ላይ ከ 200 በላይ ለሆኑ ሰራተኞች የስራ እድል ፈጥሯል።

በአሁን ሰአት ሴላቪ በርገር 3 ብራንቾች አሉት።
(በድሬቲዩብ ሪፖርተር)

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Our Story

DireTube is the Largest Ethiopian News & Video Platform. It has particularly proven its value when it comes to keeping the worldwide Ethiopian Diaspora connected to their home country.

In many parts of the world Ethiopians do not have direct access to Ethiopian news and entertainment, therefore, DireTube becomes their primary source for these. For this reason DireTube is now one of the most popular Ethiopian websites on the internet.

Videos (show all)

ጎበዝ ሹፌር ጠንቃቃ ነው!!
አንዘንጋ!...ፍጥነት ከባድ ዋጋ ያስከፍላል!!
ፍጥነት ይገድላል!!...
አንዘንጋ!...ፍጥነት ይገድላል!!
አንርሳ!...#ፍጥነት የአሪፍነት መገለጫ አይደለም!!
በደቡብ አፍሪካ የከምባታ ዞን ተወላጆች ልማት ማህበር
አሽከርክር ረጋ ብለህረጋ ብለህ!...
መንፈሳዊ አውደ ርዕይ -  በዓለም ገናየዓለም ገና ደብረ ሃሌ ሉያ ቅዱስ አማኑኤል ሕንፃ ቤተክርስቲያን እያነፁ ነው ! ሕንፃ አሠሪ ኮሚቴዎችም የቀን እረፍት የሌት እንቅልፍ የላቸውም።ምዕመኑን...
ፍጥነት ይገድላል!በዝግታ እናሽከርክር!!
መንፈሳዊ አውደ ርዕይ -  በዓለም ገናየዓለም ገና ደብረ ሃሌ ሉያ ቅዱስ አማኑኤል ሕንፃ ቤተክርስቲያን እያነፁ ነው ! ሕንፃ አሠሪ ኮሚቴዎችም የቀን እረፍት የሌት እንቅልፍ የላቸውም።ምዕመኑን...
#ፍጥነት ይገድላል!በዝግታ እናሽከርክር!!...

Address


Addis Ababa
Other Media/News Companies in Addis Ababa (show all)
Capital Capital
Bole Behind Rwanda Embassy
Addis Ababa, P.O.BOX95CODE1110

Capital is the longest-established private English newspaper in Ethiopia

Nile Brotherhood Nile Brotherhood
Addis Ababa

Nile Brotherhood is a non-Governmental non-Religious media outlate striving to bring round sided Reg

Pioneer Media Pioneer Media
Addis Ababa

Pioneer Media is the source of Entertainment, News Analysis, Battle of Debate, Home of Diversity and Agenda creator. It is your Midea and Enjoy it.

Jirra Oromia Jirra Oromia
Addis Ababa

Odeeffannoo waqtaawadhaaf JIRRA_OROMIA hordofaa!

Asash Media Asash Media
Adama Express Way
Addis Ababa

Oolanchitii Post Oolanchitii Post
Addis Ababa

Menen press Menen press
Haile Melekot Street
Addis Ababa

ይህ ፔጅ የመረጃና የዜና ምንጭ ነው

Gado daily quotes Gado daily quotes
Bole
Addis Ababa, 4549

provides latest quotes for changing life

Etho Media Etho Media
Addis Ababa

Wollo Times Wollo Times
Bole
Addis Ababa, 242624

Voice of Wollo

ሙዚቃ ህይወቴ ሙዚቃ ህይወቴ
Addis Ababa

በዚህ ፔጅ በኢትዮጵያ ውስጥ የተሰሩ ማንኛውም አይነት የጥበብ

Gurmad TV Gurmad TV
Addis Ababa

Ku soo dhawoow page-keena Gurmad TV, fadlan Follow na soo dheh kana mid Noqo Saxiibada Nagu xidhan.