Cyberigna

Cyberigna

ይህ ገጽ ዜጎች ራሳቸዉንና ሃገራቸዉን ከማንኛዉም የሳይበር ጥቃት ሊከላከሉ እንዲችሉ የሚያስችል መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነዉ፡፡

07/10/2022

አለም አቀፍ የሳይበር ወር እና ታሪካዊ ዳራዉ
አለም አቀፍ የሳይበር ወር በወርሃ ጥቅምት በአለምአቀፍ ደረጃ ስለ ሳይበር ደህንነት ግንዛቤን ከፍ ለማድረግ ታስቦ የሚካሄድ የሳይበር ደህንነት ግንዛቤ ማስጨበጫ የንቅናቄ መርሃ ግብር ነዉ፡፡
የሳይበር ደህንነት ወር ለመጀመሪያ ጊዜ በዩናይትድ ስቴትስ በ2004 እ.ኤ.አ የዜጎችን የሳይበር እዉቀት ለመጨመርና ንቃተ ህሊናቸዉን ከፍ በማድረግ ደህንነቱ የተጠበቀ የሳይበር አጠቃቀምን እንዲተገብሩ ታስቦ መከበር ጀመረ፡፡
ቀስ በቀስ በአዉሮፓ እና ሌሎች የአለም ሀገራት ተቀባይነቱ እየጨመረ መጥቶ፤ ከዩናይትድ ስቴትስ ቀጥሎ በአዉሮፓ ሀገራት ከ2012 እ.ኤ.አ. ጀምሮ መከበር ጀምሯል፡፡
የተለያዩ ሀገራት ይህን ፕሮግራም ሙሉ ወሩን አልያም ከወሩ ሳምንትን መርጠዉ እንደሚያከብሩት መረጃዎች ያስረዳሉ፡፡
አዉስትራሊያን ጨምሮ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ለምሳሌ ጋና፣ሳዉዝ አፍሪካ፣ ሞሪሽየስ፣ ኢስዋቲኒ፣ጋምቢያና ሩዋንዳን ጨምሮ ሙሉ ወሩን ባይሆንም ከጥቅምት ወር አንዱን ሳምንት መርጠዉ እንደሚያከብሩት መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
ሀገራችን ኢትዮጵያ በ2012 ዓ/ም የመጀመሪያዉን ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር በሳምንት ደረጃ በጥቅምት ወር የመጨረሻው ሳምንት “ትኩረት ለሳይበር ደህንነት” በሚል መሪ ቃል የተለያዩ የሳይበር ደህንነት ንቃተ ህሊና መርሃ ግብሮችን በማካሄድ ማክበር ጀምራለች፡፡
በ2014 ዓ.ም ደግሞ “የሳይበር ደህንነት የጋራ ሃላፊነት፤ እንወቅ፤ እንጠንቀቅ” በሚል መሪ ቃል 2ኛዉን የሳይበር ደህንነት ንቅናቄ በወር ደረጃ ከ ጥቅምት 1 ቀን እስከ 30 በተሳካ ሁኔታ ለአንድ ወር ያክል በኮንፈረንስ፣ በስልጠና ብሎም በተለያዩ የሚዲያ አውታረ መረቦች ንቅናቄዎች ተካሂደዉ ነበር፡፡
3ተኛዉ የሳይበር ወርም እንዲሁ በጥቅምት 2015 አ.ም በተሳካ ሁኔታ ይከበራል፤ የወሩ አላማወች እና ዝርዝር አላማዎችም የሚከተሉት ናቸዉ
የወሩ ግብ
የሳይበር ማህበረሰቡንና የተቋማትን የሳይበር ደህንነት ንቃተ-ህሊና ለማጎልበት የሚያስችል ንቅናቄን በማካሄድ የሃገራችንን የብሄራዊ ጥቅሞችን የማስጠበቅ ተልዕኮን ማገዝ ነዉ፡፡
የወሩ ዝርዝር አላማዎች
• የተቋማትን የሳይበር ደህንነት ጥቃት ተጋላጭነት ለማሻሻል
• የግሉ ዘርፍ የሳይበር ደህንነትን በማስጠበቅ የሚኖረዉን አስተዋዕፆ ማሳደግ
• የሳይበር ደህንነትን ማስጠበቅ የሚያስችል የሰዉ ሃብት ልማት ላይ ንቅናቄ መፍጠር ነዉ፡፡
• የማህበረሰቡን የሳይበር ደህንነት ግንዛቤ የሚያሳድግ ንቅናቄ መፍጠር

22/09/2022

የበዓል ሰሞን የሚደርሱ ማጭበርበሮች ወይም ስጋቶች ምን ምን ሊሆኑ ይችላሉ
የገንዘብ ስርቆት፣ የማንነት ስርቆት እና የማጭበርበር ተግባራት
ማህበራዊ ምህንድስና እና ክፍያ ማጭበርበር
የስጦታ ካርድ ማጭበርበሮች/Gift Card Scams
የውሸት ማህበራዊ ሚዲያ ማስተዋወቂያዎች/Fake Social Media Promotions
የውሸት በጎ አድራጎት ድርጅቶች/የበጎ አድራጎት ማጭበርበሮች/Charity Scams
የጥቅል ማቅረቢያ ማጭበርበሮች/Package Delivery Scams
Vishing scams
ሊደረጉ የሚገቡ የጥንቃቄ እርምጃዎች
 ማንኛዉንም አይነት ሊንክ ከመክፈቶ በፊት ያስቡ/ከማይታወቁ ላኪዎች በኢሜይሎች ውስጥ አገናኞችን ወይም ዓባሪዎችን አይክፈቱ አታድርጉ።ብዙ አጭበርባሪዎች በመስመር ላይ ተደብቀው በመኖራቸው፣ በዚህ የበዓል ሰሞን የግል መረጃ ከሳይበር ወንጀለኞች ለመጠበቅ የደህንነት ግንዛቤ ቁልፍ ነው። አጥቂዎች የግል መረጃን ለመስረቅ እና ለማታለል ብዙ ጊዜ የኤስኤምኤስ መልዕክቶችን ከአስጋሪ ድህረ ገፆች ጋር ይልካሉ። አንድ ሰው የኤስኤምኤስ መልእክት በውስጡ አገናኝ ከላከለት አይክፈቱት
 ደህንነቱ የተጠበቀ አውታረ መረቦችን ይጠቀሙ
 ወደ መልዕክት መቀበያ ሳጥኖዎት የሚላክሎትን አጠራጣሪ አገናኞች ፣ አባሪዎች እና ሌሎች መልእክቶችን ከመክፈትዎ በፊት በጥንቃቄ ያጢኑ፡፡
 በበዓላት ወቅት የመረጃ ጠላፊዎች ኣጥፊ ተልእኮ ያላቸዉ ሰነዶችን፣ ደረሰኝ፣ ስጦታ፣ ዝመና ወይም የትዕዛዝ መረጋገጫ በማስመሰል ሊልክልዎት ይችላሉ፡ከቻሉ ሁል ጊዜ በክሬዲት ወይም በዴቢት ካርድ ይክፈሉ፣ እንደ ሸማች ተጨማሪ ጥበቃ ይሰጥዎታል።
 በኢ-ሜይል ለሚላክልዎት ቅጽ ወይም አገናኝ የይለፍ-ቃልዎን ወይም የፋይናንስ መረጃዎን አያስገቡ፡፡
 ስጦታ ሲቀበሉም ሆነ ሲሰጡ ጥንቃቄ ያድርጉ ፤ በዚህ በዓል ቴክኖሎጂ ነክ ስጦታ እየተቀበሉ ወይም እየሰጡ ከሆነ የሚጠቀሙበት ቁስ የዘመነና የቅርብ ጊዜ ሶፍትዌር ያለው መሆኑን ያረጋግጡ
 ጊዜያቸው ያለፈባቸው ሶፍትዌሮች ተጋላጭነቶችን የያዙ ሊሆኑ ይችላሉ ፤ ያዘምኑ።
 ያገለገለ ቁስ እየተቀበሉ ወይም እየሰጡ ከሆነ ከመስጠትዎ ወይም መጠቀም ከመጀመርዎ በፊት መሳሪያውን ወደ መጀመሪያ የፋብሪካ ምርት ሥርዓት መመለስዎን ያረጋግጡ፡፡
 የበይነ መረብ ጋር የተቆራኙ ቁሶችን ደህንነት ለመጠበቅ የሳይበር ደህንነት ማስጠበቂያ እርምጃዎችን ይውሰዱ፡፡
 ከበይነ-መረብ ጋር የተቆራኙ ቁሶች ደካማ የሚባል የደህንነት ጥበቃ ሪከርድ ያላቸው በመሆኑ የቁሶችን ደህንነት በአግባቡ አለማስጠበቅ ለአጥፊዎች ይበልጥ ሥራቸውን ቀላል እያደረጉላቸው መሆኑን አይዘንጉ።

22/07/2022

ባለብዙ ደረጃ ማረጋገጫ (multifactor Authentication)
 ባለብዙ ደረጃ ማረጋገጫ ማለት ምን ማለት ነው?
 ባለብዙ ደረጃ ማረጋገጫ ማለት እንደ አፕሊኬሽን፣ የመስመር ላይ መለያ ወይም ቪፒኤን የመሳሰሉ መገልገያዎችን ለማግኘት ተጠቃሚው ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የማረጋገጫ ሁኔታዎችን እንዲያቀርብ የሚፈልግ የማረጋገጫ ዘዴ ነው።
 ባለብዙ-ደረጃ ማረጋገጫ የጠንካራ የማንነት እና ተደራሽነት አስተዳደር ፖሊሲ ዋና አካል ነው። የመጠቀሚያ ስም እና የይለፍ ቃል ብቻ ከመጠየቅ ይልቅ ባለብዙ ደረጃ ማረጋገጥ አንድ ወይም ተጨማሪ የማረጋገጫ ሁኔታዎችን ይፈልጋል፣ ይህም የተሳካ የሳይበር ጥቃት እድልን ይቀንሳል።
 ባለብዙ ደረጃ ማረጋገጫ አንድ መለያ ወይም ስርዓት ለመድረስ ከአንድ በላይ መታወቂያ የሚፈልግ የደህንነት መለኪያ ነው ተጠቃሚው መዳረሻ ከመሰጠቱ በፊት ማን ነው የሚሉትን ለማረጋገጥ ከአንድ በላይ ማስረጃዎችን የሚፈልግ ተጨማሪ የደህንነት ሽፋን ነው። የባለብዙ ደረጃ ማረጋገጫን ማከል መለያዎችን ከጠላፊዎች ለመጠበቅ ይረዳል።
 የባለብዙ ደረጃ ማረጋገጫ ዋና ዋና ጥቅሞች
የባለብዙ ደረጃ ማረጋገጫ ከሁለት-ደረጃ ማረጋገጫ የበለጠ የደህንነት ንብርብሮችን ይሰጣል።
የተጠቃሚዎችን ማንነት ይበልጥ ያረጋግጣል።
የቁጥጥር ደንቦችን በተሻለ ያሟላል።
ከቀላል አተገባበር ጋር ይመጣል።
ነጠላ መግቢያ (Single sign-on) መፍትሄዎችን ያሟላል።
በርቀትም ቢሆን የሚቀጥለውን ደረጃ ደህንነትን ይጨምራል።
ውጤታማ የሳይበር ደህንነት መፍትሄ ነው።
 የባለብዙ ደረጃ ማረጋገጫን ለመተግበር ሊጠቀሙባቸው የሚችሏቸው የማረጋገጫን ዓይነቶች በርካታ ሊሆኑ ይችላሉ ለምሳሌ፦
 የኤስኤምኤስ ማረጋገጫ መልክት
 የኢሜል ማረጋገጫ መልክት
 የሶፍትዌር ማረጋገጫ መልክት
 የሃርድዌር ማረጋገጫ መልክት
 የስልክ ጥሪ ማረጋገጫ
 የባዮሜትሪክ ማረጋገጫ
 የደህንነት ጥያቄዎች ማረጋገጫ
በዋናነት ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡

23/06/2022

የትሮጃን ጥቃት
ክፍል 2
o ላለመጠቃት ምን ማድረግ ይገባል
የትሮጃኖች ጥቃት ሰለባ ላለመሆን
• ካልታወቀ ላኪ የሚመጣ ማንኛውንም ከመልዕክቱ ጋር የተያያዘ ፋይል ከመክፈት መቆጠብ
• የማያስፈልጉ ፖርቶችን መዝጋት
• በፈጣን መልዕክት መላላኪያ የሚላኩ መተግበሪያዎችን ከመቀበል መቆጠብ
• ነባሪና የተለመዱ የመተግበሪያዎችን አወቃቀር ማስተካከል፣ ማረምና ደህንነታቸውን ማጠንከር
• በውስጥ ኔትዎርክ ውስጥ የሚኖር ማንኛውንም ግንኙነት በጠንካራ የምስጠራ ዘዴዎች በመጠቀም ማጣንከር እና ትራፊኩን ማመስጠር
• ታማኝ ካልሆኑ የሶፍትዌር ማከማቻ ምንጮች(በተለይ እንደ ቶረንት) አለማወረድና አለመጫን
• ለመተግበሪያዎቹና ለኦፐሬትንግ ሲስተሙ የደህንነት ዝመናዎችንና እድሳቶችን መጫን
• የዳታ ማስቀመጫና መላላክያ ቁሶችን (ለምሳሌ እንደ ፍላሽ) በጸረ ቫይረስ ሶፍትዌር ማስፈተሽ
• የኦፐሬትንግ ሲስተሙን ሙሉ ፈቃድ መገደብ በተለይም ተንኮል አዘል መተግበሪያዎች እንዳይጫኑ
• ኦፐሬትንግ ሲስተሙን መሰረት ያደረገ ጸረ ቫይረስ፣ ፋየርዎልና የጥቃት መለያ መፍትሄዎችን ተግባራዊ ማድረግ
o ከተጠቃን ምን ማድረግ አለብን
በተለያየ መንገድ ተጠቃሚዎች በትሮጃን ተንኮል አዘል መተግበሪያዎች ሊጠቁ ይችላሉ። በጥቃት ወቅትም ፋይል ወይም ዳታ ሳይጠፋ ወይም ሳይበላሽ መመለs የሚቻልባቸው ዘዴዎች ውስጥ/
• የዘመነ አንቲ ቫይረስ ወይም ጸረ ተንኮል አዘል መተግበሪያን በመጫን ሙሉ ኦፐሬቲንግ ሲስተሙን ማሰስና ትሮጃኖችን ማጽዳት
• ሲስተሙን ለጊዜው ከኢንተርኔት ጋር ያለውን ግንኙነት ማቋረጥ
• ለየት ያሉና የማይታወቅ መተግበሪያዎችን ማስወገድ
• ከአቅም በላይ ከሆነ ደግሞ ወደ ኮምፒውተር የደህንነት ባለሙያዎች መውሰድ

21/06/2022

የትሮጃን ጥቃት
ክፍል 1
ትሮጃን ምንድነዉ
ትሮጃኖች በኤሚይል ወይም በሌሎች ዘዴዎች ማለትም በማህበራዊ የትስስር ገጾች ወይም ታማኝ ካልሆኑ የመተግበሪያ ክምችቶች በተጠቃሚዎች የጥንቃቄ ጉድለትና የእውቀት ክፍተት ምክንያት የሚወርዱና የሚጫኑ ሶፍትዌሮች ናቸው። ትሮጃኖች ትክክለኛ ወይም ህጋዊ ሶፍትዌር የሚመስሉ ግን ሌላ ተንኮል አዘል ስራዎችን ወይም ሌላ መተግበሪያዎችን መጫን የሚያስችል አሰራር ያላቸው ማልዌሮች ናቸው።
አጥቂዎች ተጠቃሚውን አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎችን ተፈጻሚ እንዲያደርግ በመሸወድ እንዲጭን የሚያደርጉ አሰራሮችንም በውስጣቸው ያካተቱ ሲሆን፤ አንድ ጊዜ ከተጫኑ እና ስራ ላይ ከዋሉ በኋላ በውስጣቸው ያለው ተንኮል አዘል ኮድ ራሳቸውን እንዲያነቁ እና ሌሎች ተንኮል አዘል መተግበሪያዎችን በማውረድ መጠነ ሰፊ ጥቃቶችን ወይም ጉዳቶችን ማድረስ እንዲችሉ ያደርጋል። ይህም ገደብ የለሽ የተጠቃሚ ፈቃድን ማግኘት የሚያስችላቸውን ዘዴዎች በመጠቀም ዳታን መቀየር፣ ማጥፋት፣ መስረቅ እንዲሁም የሩቅ መር አሰራርን (ሪሞት ኮንትሮሊንግን) በመፍጠር አጥቂዎች ለስለላና ለመሳሰሉ አይነት የመቆጣጠሪያና የጥቃት ዘዴዎች እንዲጠቀሙባቸው የሚያስችሉ ናቸው።
o ከተጠቃን ምን ሊደርስ ይችላል?
እንደየ ትሮጃን አይነቱ ስራቸውና አላማቸው የተለያየ ሲሆን ብዙውን ጊዜ ግን የሚከተሉትን ምልክቶች ያሳያሉ፤
• የኮምፒውተር ስክሪን ከለር መቀያየርና በትክክል አለመስራት ለምሳሌ ብልጭ ድርግም ማለት፣ መገለባበጥ
• የስክሪን የጀርባ ምስል ወይም የምስል ውቀሮችን መቀያየር
• ኮምፒውተሩ ያለትእዛዝ ዶክመንቶችን ፕሪንት ለማድረግ መሞከር
• ያለተጠቃሚው ትዕዛዝ የድር ጣቢያዎች መከፈት
• የድምጽ መጠን በድንገት መለዋወጥ
• የጸረቫይረስ ፕሮግራሞች ወይም መተግበሪያዎች ማቆም እና የዳታ መቀየር፣ መጥፋት ወይም መበላሸት
• የኮምፒውተሩ የሰዓት እና ቀን መለወጥ
• የማውስ ከርሰር (ወይም ጠቋሚ) በራሱ መንቀሳቀስና የቀኝና የግራ ጠቋሚ አሰራርና ተግባር መለዋወጥ
• የዊንዶውስ የስታርት ቁልፍ(ወይም በተን) መጥፋት
• ፖፕ አፖች (ወይም ብቅ ብቅ የሚሉ የመተግበሪያ ክፍሎች) ግልጽ ካልሆነ መልዕክት ጋር መምጣትና ተጠቃሚውን መረበሽ
• የኬይቦርድና የማውስ ስራ ማቆም
• ተጠቃሚው ግንኙነት ከሌለው አካል የኢሜይል መልዕክት መምጣት
• እንግዳ የሆኑ የጥያቄና የማስጠንቀቂያ የመልዕክት ሳጥኖች ከአዎንታዊና አሉታዊ አማራጮች (በሁሉም አማራጮች ተጠቃሚውን ለሌላ ጥቃት በር መክፈቻነት ሰለባ የሚያደርጉ) ጋር መምጣት
• ባልተለመደ መንገድ የኮምፒውተር የእንደገና መነሳት(ሪስታርቲንግ)
• የታስክ ማናጀር ስራ ማቆም ይህም ለአጥቂው ወይም ለትሮጃኑ ተጠቃሚው ምን ምን ፕሮሰሶች ስራ እየሰሩ እንደሆነ እንዳያውቅ ለማደረግ እና በትሮጃኑ የተጫኑ ፕሮሰሶች ራሳቸውን እንዲደብቁ ለማድረግ
• የሲስተም ፍጥነት ወይም የስራ ሂደት አቅም መገደብ ወይም መቀነስ
• የትክክለኛ መተግበሪያዎች ስራ ማቆም ወይም በትክክል አለመስራት እና መረበሽ

14/04/2022

ሳይበር ሀይጅን
ሳይበርሃይጅንማለትማንኛዉምየኮምፒዉተርወይምመሰልመገልገያዎችተጠቃሚዎችየኮምፒዉተራቸዉንደህንነትአሊያምጤንነትለመጠበቅሲሉየሚያደርጓቸዉጥንቃቄዎችዎይምየሚወስዱዋቸዉእርምጃዎችናቸዉ፡፡በተጨማሪምማንኛዉንምየኢንፎርሜሽንቴክኖሎጂሲስተምእናመገልገያወችንምመጠበቅእንዲሁምየሳይበርደህንነትመልካምተሞክሮዎችንመተግበርመቻልጭምርነዉ፡፡
ምንምእንኳንበዲጂታልአለምዉስጥበርካታስጋቶችናተጋላጭነቶችቢኖሩምየሳይበርሃይጅንቁልፍልምዶችንተግባራዊማድረግየደህንነትስጋቶችንከመቀነስአንፃርእጅግጉልህአስተዋፅኦአለዉ፡፡
• የሳይበርሀይጅንፖሊሲንተግባራዊማድረግዎሳኝነዉይህየሳይበርሀይጅንየሚያካትታቸዉ
 የይለፍቃሎችንበየጊዜዉመቀየር ፡ ዉስብስብናሊገመቱየማይችሉየየለፍቃሎችንመጠቀምናበየጊዜዉምመቀያየርየመረጃደህንነትንለማረጋገጥጠቃሚነዉ፡፡
 ሶፍትዌሮችንማዘመን ፡ ሁልጊዜምየምንጠቀምባቸዉንሶፍትዌሮችማዘመንናየተሻሻሉትንቅጂዎችመጠቀምየሳይበርሀይጅንዋናተግባርነዉ፡፡
 ሃርድዌሮችንማዘመን ፡ ረጅምጊዜአገልግሎትላይየዋሉኮምፒዉተሮችናሌሎችመሰልመገልገያዎችንጭምርማዘመንእናመተካትመቻልየደህንነትስጋቶችንይቀንሳል፡፡
 አዲስኢንስቶልየሚደረጉመተግበሪያዎች ፡ ወደመገልገያዎቻችንኢንስቶልየምናደርጋቸዉአዳዲስመተግበሪያዎችበትክክልዶኪመንትሊደረጉናመዘመንመቻልይኖርባቸዋል፡፡
 የተጠቃሚዎችንቁጥርመገደብ ፡ በአንድኮምፒዉተርወይምመገልገያላይበጋራየሚጠቀሙተጠቃሚዎችንቁጥርማብዛትተጋላጭነትንከፍየሚያደርግበመሆኑይህእንዳይሆንማድረግተገቢነዉ፡፡
 ባክአፕዳታ(መጠባበቂያዳታ) መያዝ ፡ ሁሉንምወሳኝመረጃዎች (ዳታዎች) በሁለተኛአማራጭመጠባበቂያማኖርተገቢነዉይህምከኮምፒዉተራችንበተጨማሪመረጃንበሃርድድራይቮችወይምክላዉድስቶሬጅማከማቸትሊሆንይችላል፡፡
 እያንዳንዱንየኦንላይንአንቅስቃሴዎችበጥንቃቄመምራትመቻልተገቢነዉ፡፡

10/03/2022

የመተግበሪያ ደህንነትን እንዴት ማስጠበቅ ይቻላል?
የመተግበሪያ ደህንነት ተጠቃሚዎች፣ ደንበኞች፣ የንግድ አጋሮች እና ሰራተኞችን ጨምሮ በውስጥ እና በውጪ ባለድርሻ አካላት የሚጠቀሙባቸውን ሁሉንም አይነት አፕሊኬሽኖች (እንደ ሌጋሲ፣ ዴስክቶፕ፣ ድር፣ ሞባይል፣ ማይክሮ አገልግሎቶች ያሉ) ድርጅቶች እንዲጠብቁ ያግዛል። ይህም
• አንድ መተግበሪያ ከመመረቱ ጀምሮ በሚኖረው የንድፈ ሃሳብ ደረጃ እና በመመረት ላይ እያለም አስፈላጊውን የፍተሻ ሂደቶችን በመተግበር እና ክፍተቶቹን በመዝጋት፣
• የመተግበሪያውን የስራ ላይ ከባቢ ሁኔታ ደህንነት በመፈተሽ እንዲሁም አስፈላጊውን የደህንነት ግብዓቶችን በተገቢው መንገድ ማመቻቸት፣
• በስራ ላይ ባለበት ጊዜም ወቅታዊ የሆነ የደህንነት ፍተሻና ግምገማ በማካሄድ፣
• በየጊዜው የሚለቀቁትን የመተግበሪያው የደህንነት እድሳት አማራጮችን በተጠንቀቅ በመጠበቅ እና በማዘመን፣
• ምንጫቸው ያልታወቁ መተግበሪያዎችን ባለመጫን፣
• ታማኝ ካልሆኑ የመተግበሪያ ማከማቻ ድሮች መተግበሪያዎችን ባለማውረድ እና ባለመጫን እንዲሁም ታማኝ ያልሆኑ የድር ጣቢያዎችን ወይም ድር መተግበሪያዎችን ከማሰስ በመቆጠብ፣
• እንደ ተቋም ለተጠቃሚዎች ወይም ለሰራተኞች ተገቢውን የደህንነት አጠባበቅ ዘዴዎችን በማስተማር እና ስልጠናዎችን በመስጠት የመተግበሪያ ደህንነትን እንደ ተቋም፣ እንደ ግለሰብ ወይም እንደ ተጠቃሚ ማስጠበቅ እና ከጥቃት ራስን መጠበቅ ይቻላል።

03/03/2022

ወላጆች ልጆቻቸውን በኢንተርኔት አማካኝነት ከሚደርስ አደጋ ለመጠበቅ ምን ማድረግ
ይችላሉ?
  ኢንተርኔት ላይ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ለመከታተል የልጆቻችን ኮምፒውተር በቤት ውስጥ የሚታይ ቦታ (common Area ) ማስቀመጥ።
  የልጃችንን የመረጃ መቃኛ ታሪክ ( Browser History) ደጋግሞ መፈተሽ።
  የደህንነት ሶፍትዌር ወይም መሳሪያዎችን መጠቀም።
  የግላዊነት ገጽታዎችን(privacy features) የሚደግፉ በመተግበሪያዎ ወይም በኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢዎ አማካኝነት ያንቀሳቅሱ።
  ልጆችዎ የሚጠቀሙባቸውን ሌሎች ኮምፒውተሮችን ወይም መሣሪያዎችን ማወቅ።
  የልጆችን የይለፍ ቃል (password)ማወቅ።
  በኢንተርኔት አማካኝነት የሳይበር ጉልበተኝነት (cyber bullying) እንደተፈፀመ ወይም የሳይበር ጉልበተኝነት ጥቃት ከሚፈጽም ሰው ጋር ግንኙነት እንዳለው የሚጠቁሙ የልጆችዎ ባሕርይ ለውጦች ካሉ ማስተዋል
 ለልጆቻችሁ ጠንካራ የይለፍ ቃላትን እንዴት ማዘጋጀት እንደሚቻል ፣ እንዲሁም አፕሊኬሽኖችን ማውረድ የሚችሉትና የማይችሉት እነማን ናቸው የሚልቱን ነገሮች ማስተማር ተገቢ ነው
 ልጆች የኢንተርኔት ጉልበተኛም ሆነ ማንኛውም ሰው ቢያስቸግሯቸው ሁልጊዜ ወደ እናንተ መምጣት እንደሚችሉ መንገርና መገኘት በጣም አስፈላጊ ነው።
 ታዳጊዎች በኢንተርኔት አማካኝነት የሚያገኝዋቸውን እንግዳ ሰዎች እንዳያነጋገሩ አበረታቷቸው።
 በተጨማሪም በኢንተርኔት አማካኝነት ያገኟቸውን ሰዎች ማግኘት በጣም አስፈሪ የሆነ አደጋ
ሊያስከትል እንደሚችል ንገሯቸው፤ቢቻል በአካል ከሚያቇቸው ጓደኞቻቸውና ዘመዶቻቸው ጋር ብቻ እንዲነጋገሩ አበረታቷቸው።

23/02/2022

ታዳጊዎች የኦንላየን ቴክኖሎጂን በሚጠቀሙበት ጊዜ ሊያጋጥማቸው የሚችሉ ስጋቶች ምንድናቸዉ
1. ተገቢ ያልሆነ ይዘቶች (Inappropriate content)፡ ይህም ሲባል፡-
  የወሲባዊ ይዘት ያላቸው (የህፃናት\አዋቂዎች ፖርኖግራፊ፣ ከፊል እርቃን እና \ወይም እርቃን ምስሎች እና ተንቀሳቃሽ ምስሎችን መመልከት
  የዓመፅና የስቃይ ምስሎች እና ተንቀሳቃሽ ምስሎች
  የጥላቻ ቡድኖችን የሚደግፍ የሚያበረታታ ይዘት ያላቸዉ መረጃዎች
  ህገ ወጥ ተግባር የሚያሳዩ ማስታወቂያዎች
  ጽንፈኛ ድረገፆች፤ የሽብርተኛ ድርጅቶችን፣ ቦምብ የሚሰሩ ቦታዎችን ወዘተ መረጃዎች
  አደገኛ ፀባይን የሚያበረታቱ ድረ ገጾች
  ጸያፍ ንግግሮችንና ጸያፍ ድርጊቶችን የሚጠቀሙ ይዘቶችን ያካትታል
2. የቻት ሩም "ጓደኞች" (Chat room “Friends”)
 አንዳንድ አዳኞች(predators) ወደ ቻት ሩም ወይም በማኅበራዊ ድረ ገጾች ተጠቅመው ትንንሽ ልጆችን ማግኘት ይችላሉ። በእነሱ ዕድሜ ላይ የሚገኙ መስለው በመቅረብ ጓደኛ ይሆኗቸዋል። አብዛኛውን ጊዜ ደግሞ እንደዚህ አይነት ሰዎች በአንድ ወቅት በአካል ለማግኘት ይሞክራሉ ብሎም በታዳጊዎች ላይ ተገቢ ያልሆነ ብዝበዛ ሊፈፅሙ ይችላሉ
3. የሳይበር ጉልበተኝነት (Cyber Bullying)
በማህበራዊ ሚዲያ ድረገፆች አማካኝነት የሚደርስ የሳይበር ጉልበትኝነት (cyber bullying):- ህጻናት በማንነታቸዉ ምክንያት የሚደርስባቸዉ ዘለፋ እና ስድብ ነክ ትችት በስነልቦናቸዉ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ከማድረስ አልፎ ራስን የመጥላት ብሎም ራስን የማጥፋት ስሜት ዉስጥ ሊያስገባቸዉ ይችላል
4. 4. የኦንላይን (መስመር ላይ) ማጭበርበሪያዎች (Online Scams)
ብዙውን ጊዜ በኢንተርኔት ለሚሰነዘሩ ማጭበርበሪያዎች ዋነኛ ዒላማ የሚሆኑት አዋቂ ሰዎች እንደሆኑ ተደርገው ቢቆጠርም ልጆችም ለነዚህ አይነት ማጭበርበሪያዎች በጣም የተጋለጡ ናቸው። ታዳጊዎችን በሚፈልጉት እና ሊያገኙት በሚፈልጉት ነገር ጋር በማያያዝ በሀሰት ሊጭበረበሩና ለከፋ ጉዳ ሊደረጉ ይችላሉ፡፡

28/12/2021

የቴሌግራም አፕ እና የደህንነት ጥንቃቄዎች
የቴሌግራም መተግበሪያ ለአንድሮይድ እና አይኦኤስ ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች በተንቀሳቃሽ ስልኮችና እንዲሁም ለዴስክቶፕ በእ.ኤ.አ 2013 ተግባር ላይ የዋለ እና መልዕክቶችን ለመላላክ፣የድምፅ እና የተንቀሳቃሽ ምስል ጥሪዎችን ለማድረግ ብሎም ፋይሎችን ለመጋራት እና ሌሎች ተግባራትን ለማከናዎን ጥቅም ላይ የዋለ መተግበሪያ ነዉ፡፡
ይህ መተግበሪያ በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነት እና ተወዳጅነትን ያተረፈ መተግበሪያ ሲሆን በርካታ ሰዎችም እየተጠቀሙበት ይገኛሉ በሀገራችንም ተወዳጅ ከሆኑ የመተግበሪያዎች ዝርዝር መሀል አንዱ እንደሆነ ይታመናል፤ ታዲያ ይህ መተግበሪያ እንደማንነኛዉም ሌላ መተግበሪያዎች ሁሉ የሳይበር ጥቃት ሊያስተናግድ ይችላል ባለፈዉ በሰኔ ወር እንኳን በርካታ ቴሌግራም ላይ የተመሰረቱ ጥቃቶች እንደተሰነዘሩ ዘ ሀከርኒዉስ ዘግቧል፡፡
የቴሌግራም መተግበሪያ እንዴት ሊጠቃ ይችላል
o የሶሻል ኢንጅነሪንግ ፡ ይህ ማለት በኢምፐርሶኔሽን ዘዴ ተመሳስልው በሚሰሩ መልእክቶች ሰዎች በቴሌግራም የሚላክላቸውን መልእክት በማመን የሚላኩ ሊንኮችን ሊጫኑ አባሪዎችን ሊከፍቱ እና ለጥቃት ሊጋለጡ ይችላሉ
o ፊሺንግ፡ ይህም ፊሺንጎች ተመሳስለዉ በሚሰሩ የማታለያ መንግዶች የሚትገበሩ ሲሆኑ የቴሌግራም ፊሺንጎችም ህጋዊ እና እዉነተኛ ከሚመስሉ አካዉንቶች የተላኩ በሚመስሉ ሃሰተኛ መልዕክቶች የማጭበርበር እና በመተግበሪያዉ ላይ እና በሌሎችም የመተግበሪያዉ ሲስተሞች ላይ ጭምር ጥቃት ማድረስ ነዉ
o ደህንነታቸዉ ያልተጠበቀ ሌሎች አፕሊኬሽኖከች፡ በመተግበሪያችን ላይ ኢንስቶል የምናደረጋቸዉ መተግበሪያዎች ከታወቁ ምንጮች የተገኙ እና ደህንነታቸዉ የተረጋገጠ መሆናቸዉን ካላረጋገጥን የቴሌግራም አካዉንቶችን ወይም ሌሎችን መተግበሪያዎችን ጭምር የሚሰልሉ ሊሆኑ ይችላሉ
o የምንጠቀምበትን መገልገያ በራሱ አለመዘመን
o የመገልገያ አካላዊ መሰረቅ አሊያም መጥፋት
የቴሌግራምመተግበሪያንስንጠቀምማድረግየሚገባንየደህንነትጥንቃቄወችንእንመልከት፡
o የቴሌግራም መተግበሪያን እንደየሚጠቀሙበት ኦፕሬቲንግ ሲስተም ከ ተገቢዉ የ መተግበሪያ ቋት ማዉረድ ተገቢ ነዉ
o በየጊዜዉ ለሚደረጉ ዝመናዎች ትኩረት መስጠት እና ተከታትሎ ማዘመን ተገቢ ነዉ
o አንቲ ቫይረስ እና አንቲ ማልዌር መጠቀም
o የቴሌግራም ቦቶችን መጠንቀቅ ማለትም ማሊሺየስ የሆኑ አለመሆናቸዉን ማረጋገጥ
o በመተግበሪያዉ የተካተቱ መለያዎች(features) በመጠቀም የደህንነት መለያዎችን መተግበር ለምሳሌ የ2 ፋክተር አዉተንቲኬሽንን መተግበር እንዲሁም የ ቴልገራም ፓስኮድ መለያ መተግበር
o በተቻለ መጠን የቴሌግራምንም ይሁን ሌሎች መተግበሪያዎችን ደህንነቱ በተረጋገጠ የአፕሊኬሽን ሎከር መቆለፍ
o በቴሌግራም የሚላኩ ሊንኮች(አስፈንጣሪዎች) እና አታችመንቶች(አባሪዎች) እንደሌሎች የኦንላይን ተግባራት ሁሉ የ ፊሺንግ መንገዶች ስሚሆኑ ጥንቃቄ ማድረግ
o የምንጠቀምበትን መገልገያ አካላዊ ደህንነት መጠበቅ
o ሌሎች የደህንነት ጥንቃቄዎችን ተግባራዊ ማድረግ እንዲሁም ቴሌግራማችን የተጠቃ መስሎ ከተሰማን ሌሎች ሴሽኖችን በሙሉ መቋረጥ ብሎም እስከወዲያኛዉ ማጥፋት ተገቢ ነዉ

21/12/2021

ስለ ማልዌር
ክፍል 3
የማልዌር ጥቃት ቢደርስ ሊወሰዱ የሚገባቸዉ ርምጃዎች ምንድናቸዉ
የማልዌር ጥቃት ተጠቂ እንደሆንን ከተረጋገጠ ሊወሰዱ የሚገባቸዉ ርምጃዎችን ለመመልከት ያህል፡-
 የኦፍላይን አንቲቫይረስ ስካን ማድረግ
 ፈፅሞ ግላዊ ወደሆኑ ሌሎች አካዉንቶችም ይሁን ገንዘብ ነክ የሆኑ አካዉንቶች ሎግ ኢን ከማድረግ መቆጠብ
 ያሉትን ፀረቫይረሶች ማዘመን እና ከሌሉም በፍጥነት በማግኘት ስካን ማድረግ
 አጠራጣሪ መስለዉ የሚታዩ አፕሊኬሽኖች/ፕሮግራሞችን ማጥፋት
 የኦንላይን እርዳታዎችን መጠየቅ አይመከርም
 የፀረ ቫይረስን በሴፍ ሞድ ጥቅም ላይ ማዋል ይሄም ቫይረሶች ራሳቸዉን እንዳይደብቁ በማድረግ የፀረ ቫይረሱን ጥቅም የበለጠ ዉጤታማ ያደርጋል
 ለሁሉም ግልጋሎቶች ጥቅም ላይ ያሉ የይለፍ ቃሎችን መቀየር
 የመገልገያዉን ኢንተርኔት ግንኙነት ሙሉ ለሙሉ ማቋረጥ
 አማራጮችን ሁሉ ጥቅም ላይ አዉሎ መፍተሄ ካልተገኘ መገልገያዉን ሙሉ ለሙሉ ቡት/ ሪስቶር ማድረግ
 መገልገያዉን እንደ አዲስ ጥቅም ላይ ሲዉል ሁሉንም የጥንቃቄ ርምጃዎች መከተል

20/12/2021

ስለ ማልዌር
ክፍል 2
የማልዌር ጥቃት ቢደርስብን እንዴት ማወቅ እንችላለን
የማልዌር ጥቃት ሰለባ የሆነ መገልገያ የሚያሳያቸዉ ልዩ ባህሪትን ከተመለከትን የማልዌር ጥቃት ተጠቂ መሆናችንን ማወቅ የሚቻል ሲሆን ከባህሪያቱ አንዱን ጥቂቶቹን አሊያም አብዛኞቹን ባህሪ ሊያሳይ የሚችል ሲሆን ሊታዩ የሚችሉት ባህሪያት የሚከተሉት ናቸዉ፡-
• በድንገት የኮምፒዉተሩ ስራ መንቀርፈፍ፣ትእዛዙ መዘጋት አሊያም ሙሉ ለሙሉ መዘጋት ወይም የትእዛዝ ስህተትነትን የሚገልፅ መልዕክት መመልከት
• ኮምፒዉተሩን ለመዝጋት ወይም እንደገና ለማስጀመር አለመቻል ወይም አለመታዘዝ
• ሶፍትዌርን ለመዝጋት ወይም ለማጥፋት አለመቻል
• ድንገታዊ ያልተጠበቁ ፖፕአፖች ወይም ማስታዎቂያዎች በሌላ ፔጅ ኮንተንት ላይ ብቅ ማለት እና ጣልቃ መግባት
• ትክክለኛ በሆኑ ድረገፆች ላይ ያልተለመዱ እና ወጣ ያለ ይዘት ያላቸዉ ማስታዎቂያዎችን መመልከት
• ያልተለመዱ ቱልባሮች እና አይከኖች በመገልገያዉ ወይም በአሳሾች (ብሮዉዘሮች) ላይ መታየት
• ተጠቃሚዉ ያልፈቀደዉ ዲፎልት አሳሽ ጥቅም ላይ ሲዉል መመልከት ወይም ያልተከፈቱ አሳሶችና ታቦች ተከፍተዉ መመልከት
• ከተለመደዉ ፍጥነት በላይ የባትሪ መጠን መቀነስ እና ማለቅ ወይም መገልገያዉ ሳይታሰብ የመብራትና መጥፋት ሁኔታ መታየት

17/12/2021

ስለ ማልዌር
ክፍል 1
ማልዌር ማሊሽየስ ሶፍትዌር ከሚለዉ የሀረጋት ጥምረት የተገኘ ቃል ሲሆን ብዙ የኮምፒዉተሮችና መገልገያዎችን በማጥቃት ጉዳት የሚያደርስ ፕሮግራም ሲሆን ቫይረሶችን፣ትሮጃኖችን እና ሌሎች በካይ ፕሮግራሞችን የሚይይዝ ነዉ፡፡ ማልዌር በተለያዩ መስፈርቶች ሊከፋፈል እና አይነቶችም ሊኖሩት ይችላሉ
የመጀመሪያዉ አጥፊ ፕሮግራሙ እንዴት ሊዛመት እና ጥቃት ሊያደርስ ይችላል የሚለዉን መሰረት አድርጎ ቫይረስ፣ወርም እና ትሮጃን በሚል ሊለይ ይችላል፡፡ ሌላዉ ማልዌሮችን የመከፋፋያ ወይም የመመደቢያ መሰረት ማልዌሩ የተጠቂዉን መገልገያ ካጠቃ በኋላ ምን ያደርጋል ወይም አላማዉ ምንደነዉ የሚለዉ ሲሆን ብዙ አይነቶችን መጥቀስ ይቻላል ከነዚህም የተለመዱትን ስፓይዌር፣ራንሰምዌር፣ አድዌር፣ሩትኪት እና ክሪፕቶጃኪንግ የመሳሰሉትን ማንሳት ይቻላል፡፡
የማልዌር ጥቃቶች ተጠቂ ላለመሆን ምን መደረግ አለበት
የማልዌር ተጠቂ ላለመሆን ሚደረጉ የጥንቃቄ ርምጃዎች ምንጊዜም ከተጠቁ በኋላ ከሚደረግ ተግባር ቀላልና ተመራጩ ነዉ እናም ግለሶችም ይሁኑ ተቋማት ማልዌርን ለመከላከል የሚደረጉ ተግባራትን አፅንኦት ሊሰጡት የሚገባ ተግባር ነዉ፤ ታዲያ ራስን ከማልዌር ጥቃት ለመከላከል ስለሚደረጉ የጥንቃቄ እርምጃዎች መመልከት ተገቢ ነዉ፡-
 ፀረ ቫይረስ፣ስፓይዌር እና አድዌር በአጠቃላይ ፀረ ማልዌር መጠቀም እንዲሁም በየጊዜዉ ማዘመን
 ሆስት ቤዝድ የሆኑ ፀረ ቫይረሶች፣ፋየርወሎች እና ኢንትሩዥን ዲቴክሽን ሲስተሞችን ለኮምፒዉተሮች መጠቀም
 ካልታወቁ እና ካልታመኑ ላኪዎች የሚመጡ የኢሜይል አባሪዎችን ከመክፈት መቆጠብ
 የምንጎበኛቸዉ ድህረገጾችን አስተማማኝ እና ደህንነታቸዉ የተጠበቀ መሆኑን በማጤን መጠቀም
 ለመገልገያዎች ኦፕሬቲንግ ሲስተም እና መተግበሪያዎች ፓቾች(የክፍተት ሙሌት) እና አፕዴቶች (ዝመናዎች) ትኩረት ሰጥቶ ማከናወን
 ኤክስተርናል ዩኤስቢድራይቮችና ዲቪዲዎችን ከመገልገያዎች ጋር በምናገናኝበት ወቅት በቅድሚያ ስካን ማድረግ
 የመገልገያዎችን ፍቃድ መገደብ(ፐርሚሽን ሪስትሪክት) ማድረግ ይህም አላስፈላጊ ፕሮግራሞችን ወደ ኮምፒዉተሮች ላለማዉርድ ስለሚያስችል
 መደበኛ የሆነ ለሁሉም ድራይቮች የሚደረግ ስካን ማዘጋጀት እና ስካን ማድረግ
 ሁሌም ቢሆን ቀሪ (ባክ አፕ) መያዝ
 የኔትዎርክ ሞኒተሪንግ ቱሎችን ጥቅም ላይ ማዋል
 ራስን ከዘመናዊ የማልዌር ትሬንዶች ጋር በማስተዋወቅ በቂ መረጃ እንዲኖረን ማድረግ ይህም ለመከላከል ይረዳል
 ተቋማት ደግሞ የሰራተኞቻቸዉን የሳይበር ደህንነት ንቃተ ህሊና ከፍ ማድረግ

10/12/2021

አፕሊኬሽኖችና ሶፍትዌሮች /መተግበሪያዎችን/ ከየት ማግኘት ተገቢ ነዉ?
አፕሊኬሽኖች ወይም ሶፍትዌሮች አንድ የተወሰነ አላማን ለመከወን የተዘጋጁ መተግበሪያዎች ሲሆኑ ለተለያዩ ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች ታቅደዉም ነዉ የሚሰሩት ማለትም ለማይክሮሶፍት ዊንዶ፣ለአፕል ማክኦኤስ፣ለሊኑክስ እና ሌሎች የኮምፒዉተር ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች እና እንዲሁም ለተንቃሳቃሽ ስልኮች ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች በተለይም ለአንድሮይድ እና አፕል አይኦኤስ ማለት ነዉ፡፡ ታዲያ እነዚህ መተግበሪያዎች እንደየኦፕሬቲንግ ሲስተሞቹ አይነት መተግበሪያዎቹ የሚገኙበት ታማኝ ቋቶችም አሉ፤እነዚህ አቅራቢዎች ታዲያ ስለጥራቱ እና አስተማማኝነቱ የተሻለ ማረጋገጫን ያቀርባሉ እነዚህም፡-
 ለአንሮይድ፡ ከጎግል ፕሌይ ስቶር አሊያም አማዞን አፕ ስቶር
 ለአይኦኤስ፡ ከአፕስቶር
 ለዊንዶስ፡ ከኦፊሻል ማይክሮሶፍት ሳይት ወይም ማይክሮሶፍት ስቶር
 ለማክ ኦኤስ፡ ከማክ አፕ ስቶር
ከታማኝ ምንጮች ዉጪ ከሆኑ ሳይቶች መተግበሪያዎችን ማዉረድ ምን ጉዳት ያስከትላል?
እነዚህ ከላይ ከተዘረዘሩት ታማኝ የመተግበሪያዎች ቋቶች ዉጭ ካሉ ህጋዊነታቸዉ ካልተረጋገጠ ሳይቶች መተግበሪያዎችን ማግኘት ለተለያዩ ጥቃቶች ሊዳርጉ እንደሚችሉ ይታመናል ይኸዉም በተለይ ከደህንነታቸዉ ጋር ተያይዞ ማሊሽየስ ከሆነ ሶፍትዌሮች ጋር ሊቀርቡ የሚችሉ መተግበሪያዎችን ተጠቃሚዎች የማግኘታቸዉ እድል ሰፊ ያደርገዋል፤ ለምሳሌ እንደ ባክዶር፣ራንሰምዌር፣ስፓይዌር፣ኪሎገር፣ወርም አሊያም ትሮጃኖች በዉስጣቸዉ የያዙ መተግበሪያዎችን ተጠቃሚዎች በመገልገያዎቻቸዉ ጥቅም ላይ ካዋሉ አጥቂዎች የተጠቃሚዎችን መገልገያዎች እንዲጠቀሙበት ወይም የተጠቃሚዎችን ግላዊ መረጃዎችን ለግል ጥቅም ላይ እስከማዋል እና ሌሎች አገልግሎቶችና መረጃዎችን እስከማጥፋት ድረስ ጥቃት እንዲፈጸም ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ
ከታማኝ ምንጮች የሚወርዱ አፕሊኬሽኖችና ሶፍትዌሮች አስተማማኝነት ምን ያህል ነዉ?
ከላይ እንደተጠቀሰዉ ታማኝ ካልሆኑ እና ተገቢዉ እዉቅና ካልተሰጣቸዉ ሳይቶች መተግበሪያዎችን ማግኘት ለጥቃት አጋላጭነቱ እጅግ ከፍ ያለ ሲሆን ከታማኝ ቋቶች ማግኘት ግን በጥራትና ደህንነት ዙሪያ የተሻለ አስተማማኝ መሆኑ ግልፅ ነዉ፤ነገር ግን ይህ ማለት ከታማኝ ምንጮች የተገኙ መተግበሪያዎች 100% አስተማማኝና ፍፁም ከስጋት ነጻ ናቸዉ ማለት ግን አይደለም፡፡ ምክንያቱም ጥራትና ደህንነታቸዉ ተፈትሾ ወደ ቋት በሚገቡ መተግበሪያዎች ጭምር የሚገኙ የደህንነት ስጋቶች እንደ “bugs/flaws” የመሳሰሉ ማልዌሮች ራሳቸዉን ደብቀዉ ሊገኙ ይችላሉ፤የሳይበር ጥቃት ፈጻሚዎች እጅግ በተራቀቀ መልኩ አስርገዉ ካስገባቸዉ እና አንዴ ወደ ቋቶቹ ፍቃድ አግኝተዉ ከገቡ በኋላ ብዙ ተጠቃሚዎች መተግበሪያወቹን ሊገለገሉባቸዉና ማልዌሮቹም ድብቅ ተግባራቸዉን ሊፈፅሙ ይችላሉ፤ለምሳሌ፡-
 በ2018 ፎርብስ ሪፖርት እንዳደረገዉ ግማሽ ሚሊየን የሚደርሱ የአንድሮይድ ተጠቃሚዎች ከጎግል ፕሌይ ባወረዱት የዉድድር ጌም መተግበሪያ ዉስጥ ቫይረስ እንደተገኘ ያሳያል
 በ2017 እንዲሁ ከዋትስአፕ መተግበሪያ ጋር ተመሳስሎ የተሰራና ለጎግል ፕሌይ ስቶር አዲስ የዋትስአፕ ቨርዥን መስሎ በመታየት ነገር ግን ተግባሩ ከተጠቃሚዎች ከአድቨርታይዝመንት ሂሳብን በመቀነስ ለአበልፃጊዎቹ የሚሰጥ መተግበሪያ ማሊሺየስ መሆኑ ሳይደረስበት በፊት በሚሊየን የሚቆጠሩ ተጠቃሚዎች አዉርደዉ ጥቅም ላይ ካዋሉት በኋላ ከጥቅም ዉጪ እንደሆነ ይታወሳል
 በ2019 እንዲሁ በርከት ያሉ አድዌሮች በጎግል ፕሌይ ዉስጥ መኖራቸዉ እንኳን ሳይታወቅ ከአንድ አመት በላይ ቆየተዉ እንደነበር መረጃዎች ያመለክታሉ
ተጠቃሚዎች መተግበሪያዎችን ወደ መገልገያዎቻቸዉ ሲያወርዱ ምን ነገሮችን ታሳቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል?
ተጠቃሚዎች ሁሌም ቢሆን ከደህንነት ጋር ተያይዞ መተግበሪያዎችን ከታማኝ ቋቶችም ቢሆን ሲያወርዱ የሚከተሉትን ተግባራት ታሳቢ እንዲያደርጉ ይመከራል
 የመተግበሪያዎቹ የ “privacy policy” ምን ይላል፣ “terms of agrements” ላይ የሚገኙ ስምምነቶችስ ምን ምን ያካትታሉ?
 የ ፕራይቬሲ ፖሊሲዎቹ በተለይም ከፐርሰናል ኢንፎርሜሽን ጋር በተያያዘ ምን ያህል ደህንነቱ የታመነ ነዉ?
 መተግበሪያዎቹን ጥቅም ላይ ያዋሉት ተጠቃሚዎች ቁጥር ምን ያህል ነዉ?፣ ምን ያህል ሬቲንግ አግኝቷል?፣ እንዲሁም ስለመተግበሪያዉ የተጠቃሚዎች አስተያየት እና ጥያቅና መለስንም መመልከት ተገቢ ነዉ፡፡

06/12/2021

የመረጃን እዉነተኛነት ማጣሪያ መንገዶች
መረጃዎች በተለያየ ጊዜ በተለያዩ የመረጃ ምንጮች ይለቀቃሉ ታዲያ ሀሰተኛ የሆኑ መረጃዎችም ሊሰራጩ ይችላሉ፤በተለይ የማህበራዊ ሚዲያዎች የመረጃ ሰጪዉን ሙሉ ነፃነት ስለሚያጎናፅፉ በማወቅም ይሁን ባለማዎቅ እዉነት ያልሆኑ መረጃዎች ይሰራጫሉ፡፡ የመረጃዎችን እዉነተኝነት ለማረጋገጥ ልንጠቀምባቸዉ ከሚገቡ ዘዴዎች የሚከተሉት ዋነኞች ናቸዉ፡-
• መረጃዉን ያስተላለፈዉ አካል ማነዉ የኋላ ታሪኩስ ምን ነበር ብሎ መጠየቅ፡ ይህ የመረጃ አስተላላፊዉን አቋም ከግምት ዉስጥ በማስገባት ሥለመረጃዉ ትክክለኛነት የግል አስተያየትና ተጨማሪ ማረጋጋጫ ለመፈለግ ያግዛል
• መረጃዉ የተለቀቀበት ትክክለኛ ቀን እና ሰዓት መች ነዉ የሚለዉን ማጣራት፡ አንዳንድ መረጃዎች ቀደም ብለዉ የተለቀቁ ሆነዉ እንደ አዲስ በድጋሜ የሚወጡ ከሆኑ በ እርግጥም መች እንደነበር ማረጋገጥ ተገቢ ነዉ
• ርዕሰ ዜናዉ/ርእሰ አንቀፁ እና በስሩ የሚገኙ ማብራሪያዎች ተመሳሳይነትን ማረጋገጥ፡ አንዳንድ ርእሶችና መረጃዎቹ የሚለያዩ ሊሆኑ ይችላሉ ርእሶች የመረጃ ተቀባዩን ትኩረት ለመሳብ ተብሎ ብቻ ከአባሪዉ መረጃ ጋር የተለያዩ ሊሆኑ ስለሚችሉ መሉ መረጃን ማንበብ ወይም ማድመጥ ተገቢ ነዉ
• በምንጭነት የተጠቀሰ ምንጭ ወይም አባሪ የጠቀሰ ከሆነ ማንነት እና ምንነቱን ማረጋገጥ፡ መረጃዎች እንደምንጭነት የጠቀሱትን አካልም ይሁን አባሪ በራሱ በድጋሜ እዉነተኛ መረጃ መሆኑን ማረጋገጥ
• በድጋሜ ማጣራትን ተግባራዊ ማድረግ፡ መረጃዉ በተደጋጋሚ እና በታማኝ ምንጮችም የተረጋገጠ መሆኑን ማረጋገጥ
• ጥያቄ የሚያስነሱ እና የሚያጠራጥሩ ፎቶዎች ወይም ጥቅሶችን መጠራጠር እና ስለ እዉነተኛነታቸዉ ተጨማሪ ማጣራት ማድረግ
• ወገንተኝነትን ማስወገድ፡ መረጃዎችን እኛ የምንፈልጋቸዉ አይነት ብቻ ስለሆኑ ማመን የማንፈልጋቸዉ ሲሆኑ ደግሞ አለማመንን ብቻ ከመምረጥ መቆጠብ
• የመረጃ ማጣሪያ ቱሎችን ጥቅም ላይ ማዋል፡ የተለያዩ የምስል ትክክለኛነትን የሚያጣሩ የ“ፋክት ቼክ” ቱሎችን ተጠቅሞ ከመረጃዉ ጋር የተያያዙ ምስሎች ትክክለኛነት ለማጣራት ለምሳሌ ፎቶዎቹ ፎቶ ሾፕድ የሆኑ ወይም በሌላ ቦታና ሁኔታ ጥቅም ላይ ዉሎ በድጋሜ ለሀሰተኛ ማስረጃነት ጥቅም ላይ የዋለ ከሆነ በ ሰርች ኢንጅን ለምሳሌ “የጎግል ሪቨርስ ኢሜጅ ሰርች”( Google Reverse Image Search)፣በዌብሳይት ለምሳሌ “ፎቶ ፎረንሲክ” (FotoForensics) ወይም “ቲን አይ”( TinEye) አሊያም በአፕሊኬሽን ለምሳሌ “ትሩ ፒክ”( Truepic) ወይም “findexif” የመሳሰሉ እና ሌሎች በርካታ ዘዴዎችን በመጠቀም ስለ ምስሉ ተገቢ መረጃን በመሰብስብ ስለ ተያያዥነቱ ማጣራት እንዲሁም ሀሰተኛ ተንቀሳቃሽ ምስሎች (ዲፕ ፌክ) የሆኑ መረጃዎችን በጥንቃቄ መመልከት እና ያልተለመዱ እና ተፈጥሯዊ ያልሆኑ እንቅስቃሴዎችን በመመልከት ሀሰተኛ መሆኑን እና አለመሆኑን ማረጋገጥ ተገቢ ነዉ
• መረጃዎችን ከተገቢ ምላሽ ሰጪ አካል፣ ከቦታዉ ካለ አካል ማጣራት እና የግል ሚዛናዊነት እጅግ ወሳኝ ሚና አላቸዉ፡፡

01/12/2021

የሳይበር ጥቃት እንደደረሰ የሚያመለክቱ ምልክቶች
የሳይበር ጥቃቶች በግለሰብም ይሁን በተቋማት አካዉንቶች ላይ እንደደረሱ ሊያመለክቱ የሚችሉ ምልክቶችን መገንዘብ ተገቢዉን እርምጃ ለመዉሰድ ወሳኝ በመሆኑ ሊታዩ የሚችሉ ምልክቶችን እንመልከት
• በተደጋጋሚ የሚፈጠሩ ያልተለመዱ የብሮዉዘር/ማሰሻ/ ፖፕአፕስ/ብቅ ባዮች/መደጋገም/
• ከተጠቃሚ እዉቅና ዉጪ የብሮዘር ቱልባሮች ተጭነዉ አሊያም ተከፍተዉ መገኘት
• በተጠቃሚዉ ያልታዘዙ ሶፍትዌሮች በመገልገያዎች ላይ ተጭነዉ መገኘት
• ወደ አልተፈለገ ዌብሳይት አዉቶ ሪዳይሬክት እንዲያደርግ ተጠቃሚዉ ከተገደደ
• ሀሰተኛ የሆኑ ተጠቃሚዎች ራሳቸዉን እንዲከላከሉ የሚጠይቁ ማስጠንቀቂያዎች/fake protection alerts/
• ፋይሎች ወይም ሙሉ የኮምፒዉተር ሲስተም መቆለፍ አሊያም ከጥቅም ዉጪ መሆን
• በሶሻል ሚዲያ አሊያም ኢሜይሎች ላይ ተጠቃሚዉ ያልተገበረዉ ተግባር ተተግብሮ መታየት ለምሳሌ ከባለቤቱ እዉቅና ዉጪ መልእክቶች ተልከዉ መገኘት
• የይለፍ ቃል/ፓስወርድ/ አለመስራት ወይም ተቀይሮ መገኘት
• የማዉዝ ፖይንተር ወይም ከርሰር ያልተፈለገ እንቅስቃሴ መፈጸም
• የታስክ አሳይ ታስክ ባር ለማየት መቸገር
• ፀረ ቫይረስ/ ፀረ ማልዌር/ እንዲሁም ፋየርወል እና ሌሎች የደህንነት ማስተካከያዎች ጠፍተዉ /disabled/ መገኘት
• አጠራጣሪ የሆኑ ካልተለመደ ወይም ተጠቃሚ ከማያዉቀዉ ብሮዘሮች ሎግኢኖች መኖር
የመሳሰሉት ምልክቶች ምናልባትም በግለሰብ ደረጃ ወይም በተቋም ደረጃ አካዉንቶች ተጠልፈዉ ወይም ሌላ የሳይበር ጥቃት ደርሶ ሊሆን እንደሚችል ተገንዝቦ አስፈላጊዉን እርምጃ መዉሰድ ያስፈልጋል

24/10/2021

የዚህ ሳምንት የ50 ብር የሞባይል ካርድ የሚያሸልም ጥያቄ:-

* አንድ የኢሜል አካዎንት እንዳይበረበር (ሃክ እንዳይደረግ) ለመከላከል የሚያስችሉ አምስት መንገዶችን ይጥቀሱ።
---------------
ትክክለኛ መላሹ ሃሙስ የሚገለጽ ይሆናል።
DON'T FORGET TO LIKE & SHARE

24/10/2021

3

የሳምንቱ 2ኛዉ የ50 ብር የሞባይል ካርድ አሸናፊ
- Muluwas Atissa Ercs-sob

* Inbox us your number

24/10/2021

የሳምንቱ የ25 ብር የሞባይል ካርድ አሸናፊ
- Henok Hailemariam

Inbox us your number

24/10/2021

የሳምንቱ የ50 ብር የሞባይል ካርድ አሸናፊ
- Achro Be

* Please Inbox us your number.

14/10/2021

የ50 ብር የሞባይል ካርድ የሚያሸልም ጥያቄ ቁጥር 2
………………………............................
ከሚከተሉት ዉሰጥ የኮምፒዉተራችንን/ስልካችንን ደህንነት ለማስጠበቅ ማድረግ የሚገባን የትኛዉን ነዉ?

A. ጠንካራ የይለፍ ቃላትን (Password) መጠቀም
B. ፈቃድ ያለዉ (Licenced) የሆነ የፀረ-ቫይረስ መከላከያ መጠቀም
C. የሚጠቀሙባቸዉን ሶፍትዌሮች/አፕሊኬሽኖች ማዘመን (updating)
D. A & B
-----------------------------------
ልብ ይበሉ በዉድድሩ ለመሸለም፡-
- ይህን የፌስቡክ ገጽ ላይክ (Like) ያድርጉ
- ይህን የፌስቡክ ገጽ ሼር (Share) ያድርጉ
- ለቀረበልዎ ጥያቄ መልስዎን ኮመንት ላይ ያስቀምጡ

13/10/2021

የ50 ብር የሞባይል ካርድ የሚያሸልም ጥያቄ
---------
ከሚከተሉት ውስጥ ደካማ የይለፍ ቃል (Password) የሆነዉ የቱ ነው?
A. 12345678
B. የስልክ ቁጥር መጠቀም
C. ስምን እና የትውልድ ቀንን አጣምሮ መጠቀም
D. በሚወዱት ሰዉ ስም (ለምሳሌ፡- በልጆች ስም) ማድረግ

----------------------------
በዉድድሩ አሸናፊ ለመሆን፡-
- ይህን የፌስቡክ ገጽ ላይክ (Like) ያድርጉ
- ይህን የፌስቡክ ገጽ ሼር (Share) ያድርጉ
- ለቀረበልዎ ጥያቄ መልስዎን ኮመንት ላይ ያስቀምጡ

12/10/2021

የ25 ብር የሞባይል ካርድ የሚያሸልም የመጀመሪያ ጥያቄ:-
በኢትዮጵያ እየተከበረ የሚገኘዉ "የሳይበር ደህንነት ወር" ለስንተኛ ጊዜ እና ምን በሚል መሪ ቃል ነዉ እየተከበረ የሚገኘዉ?

---------------------------
በዉድድሩ ለማሸነፍ:-
- ይሄን Post Like ያድርዱ
- Share ያድርጉ
- መልስዎን Comment ያድርጉ
(መልስዎን እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት ድረስ ያስቀምጡ። ይመልሱ፣ ይሸለሙ)

12/10/2021

ይመልሱ ይሸለሙ

2ኛዉን ሃገራቀፍ የሳይበር ደህንነት ወርን በማስመልከት በዚህ ፌስቡክ ገጽ በየቀኑ በሚደረግ የጥያቄና መልስ ዉድድር ይሳተፉ፤ በየቀኑ የ50 & 100 ብር የሞባይል ካርድ ተሸላሚ ይሁኑ፡፡
በዉድድሩ ለመሳተፍ
- ይህን የፌስቡክ ገጽ ላይክ (Like) ያድርጉ
- ይህን የፌስቡክ ገጽ ሼር (Share) ያድርጉ
- ለቀረበልዎ ጥያቄ መልስዎን ኮመንት ላይ ያስቀምጡ

30/09/2021

የሳይበር ጥቃት አሳሳቢነት በኢትዮጲያ
የሳይበር ቴክኖሎጅን ዕደገት በተመለከተ ከጊዜ ወደ ጊዜ ቴክኖሎጅው እያደገና ውስብስብነቱም በዛው ልክ እየጨመረ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲሁም በሀገራችን የቨርቹዋሉ ዓለም የሳይበር ደህንነት ስጋቶችና ጥቃቶች እየጨመሩ ይገኛሉ፡፡ በሀገራችን ኢትዮጵያም ከ2008 እስከ 2013ዓ.ም ባሉት ተከታታይ ስድስት (6) ዓመታት ጊዜ ውስጥ የሳይበር ጥቃቶች እጅጉን እየጨመሩ እንደሆነ የኢመደኤ መረጃ ያመላክታል፡፡
አሃዛዊ መረጃዉ እንደሚያሳየው በኢትዮጵያ የሳይበር ጥቃት ከዓመት ዓመት እየጨመረ መምጣቱንና በአንድ ዓመት ልዩነት በእጥፍ መጨመሩን ነው፡፡ የሳይበር ጥቃት ሙከራውም በድረ-ገፅ ላይ፣ በአጥፊ ሶፍትዌሮች (ማልዌር) አማካኝነት፣ በመሠረተ ልማት ቅኝቶች፣ ወዳልተፈቀደ ሲስተም ሰርጎ መግባት እና የሳይበር መሠረተ-ልማቶችን ሥራ የማቋረጥ የጥቃት ሙከራዎች እንደተካሄዱ የሚያሳይ ነው፡፡ ከእነዚህም ከተሰነዘሩ ጥቃቶች ውስጥ 75.25% ለሚሆኑ ጥቃቶች ምላሽ እንደተሰጣቸውና ለቀሪዎች ጥቃቶች ደግሞ ምላሽ እየተሰጠባቸው እንደሚገኝ ኤጀንሲው ይገልፃል ፡፡
ይህም ጥቃቶቹ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ከዕጥፍ በላይ እንደጨመሩ ያሳያል፤ ለዚህም እንደ ምክንያትነት ከተጠቀሱት ውስጥ በሀገራችን በዓባይ ግድብና በሌሎች ወሳኝ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የሚስተዋሉ ሀገራዊና ዓለምአቀፋዊ የፖለቲካ ጫናዎች፣ በበርካታ ተቋማት ዘንድ ያለው የሳይበር ደህንነት ንቃተ-ህሊና ክፍተት እንዲሁም ተቋማት ቀደም ሲል ይጠቀሙበት ከነበረው ተለምዷዊ የአሰራር ስርዓት ወደ ኦንላይን ስርዓት (System) መግባታቸው ሊጠቀሱ እንደሚችሉ መረጃው ያብራራል፡፡
በአጠቃላይ የሳይበር ጥቃቶችና ስጋቶችን ቀጣይ ዓለምአቀፋዊ ሁኔታን ስንመለከት በዓለም የኢኮኖሚክ ፎረም የ2020 ግሎባል ሪስክ ሪፖርት እንሚያመላክተው እኤአ በ2021 ከዓለምአቀፍ ሰው ሰራሽ አደጋዎች ውስጥ የሳይበር ጥቃት የመጀመሪያውን ደረጃ ሊይዝ እንደሚችልና ተያያዥ የሳይበር ወንጀሎችም በየደቂቃው ወደ 11ነጥብ 4 ሚሊዮን ዶላር ኪሳራ ሊያደርሱ እንደሚችሉ ይግልፃል፡፡

21/01/2021

3. ስንጥቅ (የክራክ) ሶፍትዌር እና የደህንነት ክፍተቶች (Gaps of Cracked Software)
ስንጥቅ (ክራክ) ሶፍትዌር ምን ማለት ነው?
ክራክ ሶፍትዌር ሲባል በነፃ የማይገኙ ሶፍትዌሮች የራሳቸው የፍቃድ ማረጋገጫ ዘዴ ስለማይኖራቸው፤በሶፍትዌሩ ውስጥ የሚገኝ ለዚህ አላማ የሚውል ኮድ በሳይበር መንታፊዎች ተቀይሮ ያለምንም ፍቃድ ማረጋገጫ አልፎ እንዲጫን የሚደረግበትን ሁኔታ የሚገልፅ ነው፤ ይህ ከሆነ በኋላ የሶፍትዌሩ ጥቅል/package አካል የሆኑ ጎጂ ፕሮግራሞች (ለምሳሌ ቫይረሶች) እንዲካተቱበት ይደረጋል።
ክራክ ሶፍትዌር የመጠቀም ዋነኛ ምክንያት በቀላሉ ስለሚገኙና ገንዘብ ወይም ወጪ ወይም በሌላ ምክንያት ሰዎች ሊጠቀሙ ይችላሉ፤ ይሁን እንጂ ድርጊቱ ለደህንነትና ለኮፒራይት ችግሮች ሊዳርግ እንደሚችል መታወቅ ይኖርበታል፤
የስንጥቅ (ክራክ) ሶፍትዌር የደህንነት ክፍተቶች
• ለማልዌር ጥቃት ያጋልጣል
ክራክ ሶፍትዌሮች ሲጫኑ ድብቅ አደገኛ ማልዌር አንድላይ በመጫን ለስስ መረጃዎች ወይም ለማንነት ስርቆት (ይለፍ ቃል፣ የሂሳብ ቁጥር፣ ....) ስርቆት ያጋልጣሉ፤ እንደ ኪሎገር፣ አድዌርና ስፓይ ዌር የመሳሰሉት ባልታወቀ መንገድ እንዲጫኑ በማድረግ ባልተፈቀደ አክሰስ ለመንታፊዎች ግላዊ መረጃ ስርቆት፣ አባሪዎች ማጥፋት፣ ፕሮግራሞች መዝጋት፣ ስፓም መልእክቶች መላክ የመሳሰሉት ጥቃቶች እንዲፈፀሙ መንገድ ይከፍትላቸዋል”
• ወደ አደገኛ ድረገፆች መምራት
ክራክ የሆኑ ሶፍትዌሮች አብዛኛውን ግዜ ከእውነተኛ ድረገፆች ስለማይጫኑ ለጥቃት አጋላጭ የሆኑ ፖፕአፕስ/Popups ወይም ሌሎች አላስፈላጊ መልእክቶች በማሳየት ወዳልተፈለገ አደገኛ ድረ-ገፅ ሊመሩን ይችላሉ። ስለሆነም ለአድዌርና ራንሰምዌር የመሳሰሉት ተጓዳኝ ጥቃቶች ሊያጋልጡን ይችላሉ፤
• በኔትዎርክ ውስጥ ለሚገኙ ሌሎች መሳርያዎች ጉዳት ማድረስ
ሶፍትዌሩ ያለበት መሳርያ ወደ ኤንተርኔት በሚገናኝበት ግዜ ይዞት የመጣ ማልዌር ወደ ሌሎች ኮምፒዩተሮች ወይም ሌሎች መሳርያዎች በቀላሉ ይሰራጫል፤
• ሶፍትዌሩ የተጫነበት መሳርያ እንዲበላሽ
በማልዌር ወይም በቫይረስ የተጠቃ መሳርያ ብቃቱ እንዲቀንስና እንዲበላሽ ያደርጋል፤
• በትክክል አለመስራት
ምንም አይነት ዋስትና ስለማይነረው ሊሰራም ላይሰራም ይችላል፤በስትክክል እንዲሰራ የሚያስችሉ አዳዲስ ገፅታዎች ወይም ስሪቶች (ዝማኔዎች፣ የደህንነት ሙሌቶች ወዘተ) አይለቀቁለትም በመሆኑም ለረጅም ግዜም አገልግሎት ላይሰጥ ይችላል፤
• የተወሰኑ የኦፕሬቲንግ ሲስተም ክፍሎች እንዳይሰሩ (disable) እንዲሆኑ ያደርጋል
ክራክ ሶፍትዌር በትክክል እንዲጫንና እንዲሰራ የተወሰኑ ክፍሎች እንዳይሰሩ (disable) እንዲሆኑ ሊያደርግ ይችላል።
• ለተጨማሪ ማልዌሮች መጫን ምክንያት
ይህም ሌሎች ተጨማሪ ማልዌሮች እንዲጫኑና አደጋው ወይም ጥቃቱ የከፋ እንዲሆንም መንገድ ይከፍታል፤ ክራክ ሶፍትዌር ለመጫን የደህንነት መከላከያ እንደ ፀረ-ቫይረስና የመሳሰሉት እንዳይኖሩ ወይም (disable) እንዲሆን ሊጠይቅ ስለሚችል ተጨማሪ ስጋት ይፈጥራል። ምንም አይነት ዝማኔዎች ስለማይደረግላቸው በቆዩ ስሪቶች/old versions መጠቀም የደህንነት ቀዳዳ ወይም ክፍተት ይኖራቸዋል፤
• እንደ ቫይረስ መሆን
በማንኛውም ፀረ-ቫይረስ ክራክ ሶፍትዌር እንደ ትክክለኛ ሶፍትዌር ሳይሆን እንደ ቫይረስ ሆኖ ነው የሚጫነው፤
• ለህጋዊነት ችግር ያጋልጣል
በህገወጥ መንገድ ክራክ የሆነ ሶፍትዌር መጠቀም በህግ አግባብ ሊያስጠይቅ ይችላል፤ ስለሆነም ለተወሰነ ግዜ ወይም እስከ መጨረሻ ላለመጠቀም ወይም ለዕግድ ሊያስከትል ይችላል።

21/01/2021

የሳይበር ጥቃቶች መጨመር
የሣይበር ጥቃት በአለምም ሆነ በአገራችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣና ወደፊትም ሊጨምር የሚችል ክስተት ነዉ፡፡ ይህም በተለያዩ ተቋማት ተመዝግቦ የሚገኝ ሲሆን በአገራችንም ያለዉ የጥቃት ሁኔታ ላለፉት አስር አመታት የመዘገበዉ የሚከተለዉን ይመስላል፡፡
 2008--------214
 2009--------479
 2010--------576
 2011--------791
 2012--------1087
የሳይበር ጥቃት በግለሰቦች የሚያደርሰዉ ጉዳት
 የፋይናንስ- በአብዛኛዉ የሳይበር ጥቃት የሚፈፀም በፋይናንስ ተቋማት ነዉ፡፡ ይህም ግለሰቦች ገንዘባቸዉን እንደባንክ እና ሌሎች የቁጠባ ተቋማት ላይ በመሆኑ በአንድም በሌላም መንገድ የጥቃቱ ሰለባ ያደርጋቸዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ጥቃቱ ዲቫይሶችን የሚያበላሽ መሆኑና ሰወችም ለነዚህ እቃዎች ግዥ የሚያወጡት ወጭ ከፍተኛ በመሆኑ ጥቃቱ ሲደርስ ኪሳራዉ ከፍተኛ ይሆናል፡፡

 የመረጃ ስርቆት- መረጃ የዘመናችን ዉድ ሃብት ነዉ፡፡ ይህንን የሳይበር ጥቃት ፈፃሚዎች ጠንቅቀዉ ያዉቃሉ፤ ለዚህም መረጃ ስርቆት ላይ ከፍተኛ ትኩረት ያደርጋሉ፡፡ የመረጃ ስርቆት ጥቃት መረጃዉን ወስዶ ከመጠቀም የሚያልፍበት አጋጣሚ ሰፊ ነዉ፡፡ ይህም መረጃን በማገት በምትኩ የገንዘብ ክፍያን ወይም ሌሎች ስነ-ልቦናዊ ጥቃቶችን ሊፈፅሙ የሚችሉበት እደል ሰፊ ነዉ፡፡

 የስራ መስተጓጎል- ይህ ጥቃት ሰዎች ስራቸዉን እንዳይሰሩ የማድረግ ጥቃት ሲሆን በአብዛኛዉ ተጠቂዎች አገልግሎት ለማግኘት የተጠየቁት ገንዘም መክፈል ግዴታ በመሆን የሚጠናቀቅ ነዉ፡፡

 የሥም ማጥፋት- ስም ማጥፋት የግለሰቦችን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ለማወክ የሚደረግ ነዉ፡፡ በዚህም ግለሰቦች ከኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች እንዲገደቡ የሚያደርግ ነዉ፡፡

መደረግ የሚገባቸዉ ጥንቃቄዎች
• መረጃንና መገልገያን መመስጠር፡- ሌሎች ሰዎች በቀላሉ ሊጠቀሙበት በማይችሉበትና እኛ በሚገባን መንገድ መመስጠር፡፡
• ጠንካራ የይለፍ-ቃል መጠቀም፡- በየጊዜዉ የሚቀየርና የተለያዩ ካራክተር የያዙ የይለፍ ቃሎችን መጠቀም፡፡
• ኦፕሬቲንግ ሲስተምን ማዘመን፡- አዳዲስ ኦፕሬቲንግ ሲስተም መጫንና ያሉትም ማደስ፡፡
• ትክክለኛ ፀረ-ቫይረስ መጠቀም፡- ምንጫጨዉ ከተረጋገጠ ገፆችና ተቋማት ፀረ-ቫይረሶችን መጠቀም፡፡
• ማስፈንጠሪያን መጠንቀቅ፡- በየጊዜዉ ከሚመጡልን ማስፈንጠሪያዎች መጠበቅ፡፡ ለሚጠይቁን መልስ ከመስጠት መቆጠብ፡፡

21/01/2021

1. የመተግበሪያዎቻችንን ደህንነት እንዴት ማስጠበቅ እንችላለን (Application security)
በተለያዩ ዲቫይሶቻችን ማለትም በስልኮቻችን፣ ታብሌት፣ ላፕቶፕና ዴስክቶፕ ኮምፒተሮቻችን ላይ የምንገለገልባቸውን መተግበሪያዎች ደህንነታቸውን ማስጠበቅ ይኖርብናል፤ ይህም በዕለት ከዕለት ማስሻነት (browsing) አገልግሎት የምንጠቀምባቸውን ቋሚ (default) መተግበሪያውችንና ሁሉንም አዳዲስ የሚፈጠሩ መተግበሪያዎችን ለመጠቀም ስንፈልግ ማድረግ የሚገቡን ጥንቃቄዎች ይኖራሉ፡- ከነዚህም ውስጥ፡-
የምንጠቀምባቸውን ዲቫይሶች አካላዊ (physical) ደህንነት ማስጠበቅ፤
ለምንጠቀምበት ዲቫይስ ጠንካራ የይለፍ ቃል መጠቀም፤
የዘመነ ጸረ-ቫይረስ መጠቀም፤
ለመተገበሪያዎቻቸን አዳዲስ ማዘመኛዎች መለቀቃችውን ማረጋገጥና ማዘመን፤
መተግበሪዎችን ከትክክለኛ ምንጭ ማውረድና መጠቀም፤
የምንጠቀምበትን ዲቫይስ አጠቃላይ የኦፕሬቲንግ ስርዓት ማዘመን፤
አፕሊኬሽኖችን ከሌሎች አለመውሰድ ይልቅ ከታማኝ የመተግበሪያ ቦታዎች (apps store) ማውረድና በቀላሉ መጠቀም መቻል፤
መተግበሪያዎችን በምናወርድበት ወቅት ከድርጀቱ የሚሰጡ ፖሊሲዎችንና ቅድመሁኔታዎችን (terms and policies to be seen) መመልከት፤
በተለያዩ መተግበሪያዎችና ሌሎች የሳይበር ደህንነት ጉዳዮች ላይ ፈጣን መረጃዎች እንድናገኝ የሳይበር ደህንነት መረጃ ሰጭ ድረ-ገጾችን በመከታተል የተለያዩ የሳይበር ደህንነት ማስጠበቂያ ስልቶችን መተግበር ያስፈልጋል፡፡

21/01/2021

2. ስለ ሳይበር ምህዳሩ የተሳሳቱ እሳቤዎች
የሳይበሩ አለም ከጊዜ ወደ ጊዜ ህይወታችንን በብዙ መልኩ እየተቆጣጠረ ሲሆን ብዙ መልካም አጋጣሚዎችን አቅርቦልናል፤ ነገር ግን የራሱ የሆነ ስጋትም አለዉ ይኸዉም በከፍተኛ ሁኔታ አሳሳቢ የሆነዉ የሳይበር ጥቃት ነዉ፡፡ ታዲያ ከሳይበር ጥቃት ለመጠበቅ እና ደህንነቱ የተጠበቀ እንቅስቃሴ ለማድረግ ስለ ጉዳዩ ትኩረት መስጠት እና የበለጠ መረዳት ተገቢ ነዉ፡፡ ቀጥለን ስለ ሳይበር ምህዳሩ የተሳሳቱ እሳቤወችን እንመለከታለን፡-
 የሳይበሩ አለም ሙሉ ለሙሉ ደህንነቱ የተጠበቀ ነዉ አሊያም ደግሞ የተጠቃሚዎች እርምጃዎች ምንም ዋጋ የላቸዉም ብሎ ማሰብ
የሳይበሩ አለም ሁሌም ቢሆን የስጋት ምንጭ ነዉ ይህ ሊታመን የሚገባዉ ጉዳይ ሲሆን የተጠቃሚዎች የደህንነት እርምጃም ግን እጅግ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት እና ለደህንነት ወሳኝ መሆኑን መረዳ ተገቢ ነዉ ስለዚህ ሁሌም ቢሆን ስጋት የለም ብሎ ከማሰብም ሆነ እኔ ተጠንቅቄ ምን ልፈይድ ከሚሉ ሀሳቦች መላቀቅ ወሳኝ ነዉ፤
 የሳይበር ጥቃት በእኔ ላይ አይደርስም ወይም እኔ የጥቃት ኢላማ አይደለሁም ብሎ ማመን
ማንኛዉም በምህዳሩ ዉስጥ ያለ አካል የጥቃት ተጋላጭ እና ኢላማም ሊሆን እንደሚችል መገንዘብ እና ቸል ከማለት መቆጠብ ተገቢ ነዉ፤
 የቴክኖሎጂዉ ዘርፍ ላይ ብቻ ኢንቨስት ማድረግ የሳይበር ጥቃትን ይከላከላል ብሎ ማሰብ
የሳይበሩን አለም ያዋቀሩት ዋና ዋና ዘዉጎች ማለትም ቴክኖሎጂ፣ የአሰራር ሂደት እና የሰዉ ልጆች ሁሉም ዘርፎች ወሳኝ ናቸዉ፡፡ ነገር ግን ለ ቴክኖሎጂዉ ዘርፍ ብቻ ትኩረት ማድረግ ሳይሆን የሰዉ ልጆችንም ስለ ሳይበር ደህንነት ተገቢዉ ንቃተ ህሊናና ባህል እንዲያዳብሩ ማድረግ እጅግ ወሳኝ ነዉ ምክንያቱም ከ 80 በመቶ በላይ የሚሆኑ የሳይበር ጥቃቶች የሚደርሱት በሰዉ ልጆች ስህተት በመሆኑ፤
 ስለ ሳይበር ጥቃቶች አላስፈላጊ በራስ መተማመን መኖር
ሰዎች የሳበር ጥቃት እንደማይደርስባቸዉ እና ከስጋት ነፃ እንደሆኑ ያምናሉ ይህ ከፍተኛ የሆነ ስለ ዘርፉ በጥልቅ እዉቀት ላይ ያልተመሰረተ መተማመን ተገቢ አለመሆኑን መገንዘብ ተገቢ ነዉ፤ ከነዚህ አስተሳሰቦች ለምሳሌ፡- ስልኬ አይፎን ስለሆነ ጥቃት አይደርስብኝም፣ መገልገያዬ (ኮምፒዉተሬ) ፀረ ቫየረስ ስላለዉ ስጋት የለብኝም የመሳሰሉትን መጥቀስ ይቻላል፤
 የሳይበር ደህንነት ጉዳይ እና ሀላፊነት የአይቲ ባለሙያዎች ወይም የሳይበር ደህንነት መስሪያ ቤቶች አሊያም የመንግስት ሃላፊነት ብቻ አድርጎ ማየት
የሳይበር ደህንነት የተወሰነ አካል ሃላፊነት ብቻ ሳይሆን የእያንዳንዱ የምህዳሩ ተጠቃሚዎች የጋራ ሀላፊነት ነዉ ምክንያቱም ምህዳሩ ሁሉንም አካላት እኩል ያስተሳሰረ ስለሆነ፤
 የደህንነት ጥንቃቄዎች እና መሰረታዊ የዘርፉ እዉቀቶችን ችላ ማለት
የሳይበር ደህንነት ጉዳይን ተገቢዉን ትኩረት አለመስጠት እና ስለጉዳዩ በቅርበት ያለመረዳት እንዲሁም አዉቆ ተግባራዊ ያለማድረግ በግለሰቦችም ይሁን በ ተቋማት ብሎም እንደ ሀገር ዋጋ ሊያስከፍል እንደሚችል መገንዘብ ተገቢ ነዉ፡፡

Want your business to be the top-listed Advertising & Marketing Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


South Africa Street
Addis Ababa
ETH
Other Social Media Agencies in Addis Ababa (show all)
Kida Digital Solutions Kida Digital Solutions
Addis Ababa, 1874

Kida Digital Solutions is a full-service digital marketing agency.

Dubakko Dubakko
Addis Ababa

welcome to our official page. In this page you will learn more about content marketing and advertisi

እፎይ Advertising Ethiopia እፎይ Advertising Ethiopia
Bole
Addis Ababa

ሽያጭዎን ለማሳደግ ከእኛ ጋር ይስሩ፡፡ ለመሸጥ የፈለጉትን እቃ ወይም አገልግልዎት እኛ ለትክክለኛ ደምበኛ በተመጣጣኝ ዋጋ እናስተዋዉቅልዎታለን ፡፡

WDO Kolfee/Kolfe OUA WDO Kolfee/Kolfe OUA
Ethiopia � Hachalu Street
Addis Ababa

Volunteers

Tesloach Riek Jikany Tesloach Riek Jikany
Addis Ababa, 1000

https://youtube.com/channel/UCwI5ou16JhT7-ew--eaB0Pw

Sololo Intercept Sololo Intercept
Addis Ababa

Social media is the ultimate equalizer. It gives a voice and a platform to anyone willing to engage. Amy Jo Martin Amy Jo Martin

Ethioline Ethioline
Bole Roads
Addis Ababa, 251

ኢትዮላይን

Jossy Man Jossy Man
Addis Ababa

Speak the Truth

Ethio Boost Marketing Ethio Boost Marketing
Addis Ababa
Addis Ababa, 1000

A leading digital marketing agency in Ethiopia, dedicated to helping small businesses and individuals

EwketJobs EwketJobs
Addis Ababa

Pluto Agency Pluto Agency
Addis Ababa

Social Media Marketing Agency -Facebook,IG Ads -Youtube,tiktok ads -Social media automation -web devt