ፀዳል /ዶ/ር ፈቃደ ጌታቸው/ ልዩ የእናቶች እና ሕፃናት ህክምና ክሊኒክ Tsedal MCH clinic
በ ዶ/ር ፈቃደ ጌታቸው የተቋቋመ
ለመላው የክርስትና ና እስልምና እምነት ተከታዮች መልካም የፆም ወቅት እንመኛለን!
ሽህ መንደፈር!
ፀዳል ልዩ የእናቶች ና ህፃናት ህክምና ክሊኒክ(Tsedal Maternal and Child health specific alty clinic):
እንኳን ለብርሀነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ!
የጥር ወር የጤናማ እናትነት ወር እንዲሁም የማህፀን በር ካንሰር ግንዛቤ ማስጨበጫ ወር ነው።
በመሆኑም ከእርግዝና በፊት የጤና ሁኔታን በማወቅና የእርግዝና ክትትልን ሶስት ወር ሳይሞላ በመጀመር፣ በጤና ተቋማት በመውለድ የእርግዝና ወሊድና ድህረ ወሊድ ጤናማ ጊዜን እናሳልፍ!
አንዲት ሴት በተለይ ከ30 አመት እድሜ በላይ ከሆነች በየ አምስት አመቱ የማህፀን በር ቅድመ ካንሰር ምርመራ በማድረግ እራስን ካስከፊው የማህፀን በር ካንሰር እራሳችን እንከላከል።
ኑ በፀዳል የማህፀን ፅንስና ህፃናት ህክምና ክሊኒክ የቅድመ ካንሰር ምርመራ በካንሰር ህክምና ድህረ ስፔሻሊስት ባለሙያወች በጥራት በርህራሄና በንፅህና ያግኙ።
መልካም በዓል!
ይህ የቴሌግራም ቻናል ለ ብዙሀኑ እንዲደርስ ለወዳጆቻችሁ invite በማድረግ ተባበሩን!
https://t.me/tsedalclinic
መልካም የጥምቀት በዓል እያልን የጥር ወር የማህፀን በር ካንሰር ግንዛቤ ማስጨበጫ ወር እንደመሆኑ ክሊኒካችን ፀዳል የማህፀን ፅንስና ህፃናት ህክምና ክሊኒክ ለየት ባለ መንገድ እህቶቻችን እና እናቶች በቀጥታ ከራሳቸው ገንዘብ ሳይከፍሉ ( በነፃ) በ "ፓፕ ስሚር" ( Pap smear) በሚባለው የማህፀን በር ቅድመ ካንሰር ምርመራ ዘዴ ምርመራ ማድረግ የሚችሉበትን መንገድ አመቻችተናል።
ይሄውም እንዴት ነው :- አቅሙ ያላቸው እና እናቶችን ከዚህ አስከፊ ነገር ግን ሙሉ በሙሉ መከላከል የሚቻል ካንሰር እንዲጠበቁ የማድረግ ፍላጎት ያላቸው በጎ አድራጊ ኢትዮጵያውያን ክፍያውን በሚችሉት መጠን እንዲሸፍኑ እድል ኣመቻችተናል።
ሀምሳ ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክም ነው ለሀምሳ ግን ጌጥ ነው።ስለዚህ ይህን ፀዳል ክሊኒክ ያመቻቸችውን እድል በመጠቀም በትንሽ ወጭ የእናቶችን ህይወት እንታደግ! ለአንድ እናት የማህፀን በር ቅድመ ካንሰር ምርመራ ለማድረግ የሚያስፈልገው ወጭ 2000 ብር ብቻ ነው።
ክሊኒካችን ይህን ምርመራ በጥራት ለመስጠት ልምድ ያላቸው የማህፀን ካንሰር ሀኪሞች፣ የስነ ደዌ ሀኪሞች፣ የላቦራቶሪ ባለሙያወች ዝግጁ አድርጓል።
ጥራቱ የተጠበቀ የምርምራ ውጤት እንዲኖርም ውጤቱ ቢያንስ በሁለት የፓቶሎጅ ስፔሻሊስቶች ተረጋግጦ ነው ወጭ የሚደረገው።
በራስ አቅም የማህፀን በር ቅድመ ካንሰር ምርመራን ለሁሉም ሴቶች እናዳርስ!
ወጭውን ለመሸፈን ፍላጎት ያላችሁ በጎ አድራጊወች
1000149693096- CBE መጠቀም የምትችሉ ሲሆን በቴሌ ብር ወይም CBE ብር ለመጠቀም የምትፈልጉ
0910105042 መጠቀም ይቻላል!
ፀዳል ለ ቤተሰብ ጤና!
ባህር ዳር ቀበሌ 07
ከፓፒረስ ሆቴል ወደ ስላሴ በሚወስደው መንገድ ሀን ጤና ጣቢያ ፊት ለፊት እንገኛለን!
ዒድ ሙባረክ!
መልካም የእናቶች ቀን!
በፈጣሪም በፍጡራንም ትልቅ እምነት የሚጣልባት እናት ናት!
እናቶች ስናገለግላችሁ በትልቅ ደስታ ነው!
ፀዳል የእናቶችና ህፃናት ህክምና ክሊኒክ
ባህር ዳር ቀበሌ 7 ፓፒረስ ሆቴል አካባቢ ሀን ጤና ጣቢያ ፊትለፊት።
ኢድ ሙባረክ!
ፍቅር ያሸንፋል!
ፀዳል የእናቶችና ህፃናት ህክምና ክሊኒክ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች መልካም የትንሳኤ በዓል ትመኛለች!
ፀዳል ለቤተሰብ ጤና!
እንኳን ለታላቁ ረመዳን ወር አደረሰን!
መልካም የከተራ ና የ ጥምቀት በዓል!
እንደምን ሰነበታችሁ!
ዛሬ የ ካንሰር ህመም ታክሞ መዳን እንደሚችል የሚያሳይ ታሪክ ልናካፍላችሁ ወደድን!
በነገራችን ላይ በካንሰር ህክምና ትልቁ ችግር የታማሚወችና ቤተሰብ ተስፋ መቁረጥ እና ህክምና እቋርጦ ወደ ቤተ እምነትና የባህል ህክምና ብቻ በመሄድ ካንሰር የሚሰራጭበት እድል እንዲያገኝ እና ከተዳከሙ በሗላ እንደገና ወደ ዘመናዊው ህክምና ሲመጣ ብዙ መርዳት የማይቻልበት ደረጃ ላይ መገኘት ነው።
ዘመናዊ የካንሰር ህክምና ከፀበል ጋር ወይም ከፀሎት ጎን ለጎን ሳይቋረጥ መከናወን ይገባል!ይህን ማድረግ ከእምነት ጋር ተቃርኖ ስለሌለው !
የካንሰር ህክምና አላማወች
1. ከካንሰር ሙሉ በሙሉ መፈወስ
2. ካንሰር ህክምና በመስጠት እድሜን ያለ ስቃይ ማራዘም
3. የካንሰር ህመምና ስቃይ መቀነስ
እና ሌሎችም ናቸው።
ህክምና ህመም እንደታወቀ መጀመር ከካንሰር ሙሉ በሙሉ የመፈወስ እድልን ይጨምራል!
በሉ እስኪ ወደ ታሪኩ ( ከ "እናቶች ወግ ስለ ልጆች አመጋገብና አስተዳደግ " ገፅ ላይ የተገኘ ነው!)
ይኼን ታሪክ የማካፍላችሁ ትንሽም ቢሆን በምንችለው cancer ህሙማንን እንድንረዳ ብዬ ነው።የዛሬ ሁለት አመት ነበር እናቴ የጡት ካንሰር እንዳለባት ያወቅነው በጣም ከባድ ነበር:ካንሰር እንደማይድንና የተገኘበት ሰው ወዲያው የሚሞት ነበር የሚመስለኝ የነበረው ግን በጊዜው የተነገረን ነገር ቢከብደንም ወዲያው ሰርጀሪ ተሰርታ chemotherapy ጀመረች በጣም ከባድ ነው ስቃዩ እንደዚህ ነው ተብሎ የሚወራ አልነበረም🥺እንኳን ለታማሚው አስታማሚ ራሱ ይታመማል እና መልካቸው ይቀየራል የፀጉር መርገፍ ከላይ ልናያቸው የምንችላቸው ለውጦች ነበሩ በጣም ብዙ እናቶች በዚህ በሽታ ይሰቃያሉ።የቀጠሮ ቀናችን ተመሳሳይ ስለነበር አስታማሚዎች ማለቴ የካንሰር ታማሚ ልጆች ቤተሰብ ሆነናል እንደዋወላለን ስለአመጋገብ ስለለውጣቸው እናወራለን ምን ማድረግ እንዳለብም ምክንያቱም የባህሪይ ለውጥም ተስፋ መቁረጥም ስለሚኖር 🥺ከህክምናው ቀጥሎ ከባድ ነገር እሱ ነበር :አንዳንዴ ነርሶች ካርዳችሁ የለም ፈልጋችሁ አምጡ ስለሚሏቸው ብዙ እናቶች ብቻቸውን የሚመጡ ነበሩ ከሩቅ አገር ወደ አዲስ አበባ አንዳንዴ ካርዳቸውን በመፈለግ አግዛቸውም ነበር ይመርቁኛል🥺ከሩቅም የመጡ አሉ ለምን ብቻችሁ ትመጣላችሁ? ስላቸው በብዛት የሚመልሱልን መልስ ተመሳሳይ ነበር ሴት ልጅ የለኝም🥺(ለካ ሴት ልጅ ለእናቷ ብዙ ነገር ናት) በተለይ የማህፀን ካንሰር ታማሚ የነበረች እናት ያጫውቱኝን ልንገራችሁ የሳቸው ካንሰር ያለህክምና ቆይተው ስለነበር ተሰራጭቷል። ለምን እንደዚህ እስከሚሆኑ ሀኪም ጋር አልታዩም ብዬ ጠየኳቸው ልጄ አራት ልጆች አሉኝ ትልልቅ ግን እንዴት ብዬ ላውራቸው ወንዶች ናቸው ሴት ልጅ ብትኖረኝ እናቴ የቱ ጋር ነው የሚያምሽ? ምን ሆንሽ?እያለችኝ ትረዳኝ ነበር🥺ደም ይፈሰኛል ብዬ ለወንድ ልጆቼ እንዴት ልንገራቸው?ሴት ልጅ ብትኖረኝ እንዲህም ሳልሆን በጊዜ ህክምና አገኝ ነበር አሉኝ አንዳንድ እናቶች ወንዶች ልጆቻቸውን ላለማስጨነቅም ሆነ ህመሙን አይረዱም ብለው ስለሚያስቡ አያወሩም።ሴት ልጅ ይስጥሽ እግዚአብሔር ብለውም መረቁኝ(ከዚህ የተረዳሁት እናቶችን አስጨንቃችሁም ቢሆን ህመም ስሜት ሲኖር እንዲያወሯችሁ አድርጓቸው) ወደ ታሪኬ ስገባ በጣም ብዙ አሳዛኝ ክስተቶች ነበሩ።በቀጠሮ ቀን በየ21ቀን ስንሄድ የሚጎሉ ሰዎችም ነበሩ እንትናስ ስንል ሞተችኮ ነበር የምንባለው በጣም ከባድ ነው ቤተሰብ ያጣው ያህል ነበር የሚሰማኝ የነበረው ከነዚህ ሁሉ አንድ የማልረሳትን እድሜዋ 37የሆነች ፀይም ቆንጂዬ ልጅ ሁሌ አወራት ነበር breast cancer stage 4 ነው የሷ ሳንባዋን ነክቶታል ብቻ ተሰራጭቷል መድሃኒት ልገዛ ከግቢ ውጭ ወጥቼ ስመለስ መንገድ ላይ አገኘኋት መድሃኒት ሲወስዱ ቀን ሙሉ ነው በግሉኮስ የሚወስዱት እና ለምን ወጣሽ መድሀኒት ከሆነ እኔን አትልኪኚም ነበር?ብዬ ጠየኳት በፈገግታ ነበር ያዋራችን በዛ በሚያምር ፊቷ መድሃኒቱንኮ አስቆሙኝ አለቺኝ ደንግጬ ለምን ስላት ለመሞት 28ቀን ነው የቀረሽ ተባልኩኝ አለቺኝ😭😭አቀፍኳት እምባዬን መቆጣጠር አቃተኝ እግዚአብሔር ምን ይሳነዋል? እግዚአብሔር ይቀይራል ምንም አትሆኚም ምንም ነገር አይሳነውም እያልኩኝ ውስጤን አመመኝ💔 እሷ ግን የኔ ቆንጆ በሚቀጥለው ወር ካልመጣው ሞቼ ነው እሺ🥺አለቺኝ በፈገግታና በእምባ😭 እኔም ሆድ ባሰኝ ትልቁ ወንድሟ አጠገቧ ቆሟል እምባ ዝም ብሎ ነበር ከአይኑ የሚፈሰው ተቃቅፈን የነበርነውን አላቆን ሂጂ በቃ መድሀኒቱን አድርሺላት አለኝ እንዴት ልለያት የእውነት ድጋሚ የማላያት መሰለኝ💔 ድጋሚ የቀጠሮ ቀን ሲደርስ ቀድሜ እሷን ነበር የጠየኩት እንዳረፈች ሰማሁ😭😭
እናቴም ህክምናዋን ስትጨርስ እግዚአብሔር ረድቶን ከካንሰር ነፃ ሆነች እኛም ደስ አለን እግዚአብሔርም አመሰገንን🥺 ሲስተር መዓዛ ከካንሰር ነፃ ሆና ወደ ስራ ገበታዋ ተመልሳለች ነርስ ነች በአንድ ሆስፒታል ውስጥ እግዚአብሔር ረድኤት ሆነን እና cancerበጊዜ ከታከመ የሚድን በሽታም ነው። አመሰግናለሁ እናቶችዬ🙏🙏🙏
🖍 ለእርግዝና በመዘጋጀት ላይ ኖት?
🧬💊ለማርገዝ እያሰቡ ከሆነ፣ የተወሰኑ እርምጃዎችን መውሰድ በእርስዎ እና በልጅዎ ላይ የሚደርሱ ጉዳቶችን ለመቀነስ ይረዳል። ለማርገዝ ከመወሰንዎ በፊት በጥሩ ጤንነት ላይ መሆን በእርግዝና ወቅት ጤናማ አካልን የመጠበቅን ያህል አስፈላጊ ነው።
💊የመጀመሪያዎቹ ሳምንታት ለልጁ እድገት አስፈላጊ ናቸው። ነገር ግን ብዙ ሴቶች ከፀነሱ ከጥቂት ሳምንታት በኋላ እርጉዝ መሆናቸውን አይገነዘቡም።
♦️ከመፀነስዎ በፊት እራስዎን መንከባከብ ለእርስዎ እና ለልጅዎ ማድረግ የሚችሉት ምርጥ ነገር ነው።
🧬ለጤናማ እርግዝና ለመዘጋጀት በጣም አስፈላጊ ከሆኑ እርምጃዎች አንዱ የቅድመ-ወሊድ ምርመራ ማድረግ ነው። ምርመራው ከመፀነስዎ በፊት አቅራቢዎ ባለ የህክምና ባለሟያ ይከናወናል።
በዚያ ጉብኝት ወቅት
♦️ አጠቃላይ የጤና ምርመራ ይደረግሎታል።
♦️እርግዝናን አስቸጋሪ ሊያደርጉ ስለሚችሉ
ማናቸውም የአደጋ መንስኤዎች (potential
risk) ያሳውቁዎታል።
♦️እንዲሁም በእርግዝና ምክንያት ሊለወጡ
ለሚችሉ የጤና ችግሮች (እንደ የስኳር በሽታ
ወይም የልብ ሕመም ያሉ) ምክር እና ህክምና
ማግኘት ይችላሉ ።
🔴👩⚕👀⛑ የቅድመ ፅንስ ምርመራ የሚከተሉትን ሊያካትት ይችላል-
📌 የቤተሰብ ጤና ታሪክ፦ የጤና ታሪክዎ ማንኛውም የቤተሰብ አባል እንደ የደም ግፊት፣ የስኳር በሽታ፣ ወይም የእድገት እክል ያሉ የጤና እክሎች አጋጥሞት እንደሆነ ለማወቅ ይረዳል።
📌 የጄኔቲክ ቴስቲንግ፦ ብዙዎቹ በቤተሰብ ውስጥ ሊተላለፉ ስለሚችሉ ማናቸውንም የጄኔቲክ ችግሮች ግምገማ መደረግ አለበት።
📌 የጤና ታሪክዎ፦ የሚከተሉትን ለማወቅ ሃኪሞዎ የእርስዎን የግል የጤና ታሪክ ይገመግማል:
♦️በእርግዝና ወቅት ልዩ እንክብካቤ
የሚያስፈልጋቸው የጤና ችግሮች፣ ለምሳሌ
የሚጥል በሽታ፣ የስኳር በሽታ፣ የደም
ግፊት፣ የደም ማነስ ወይም አለርጂ
♦️የቀድሞ ቀዶ ጥገናዎች
♦️ያለፈው እርግዝና ታሪክ፣ ቁጥሩን፣የእርግዝና
ጊዜን፣ የቀድሞ እርግዝና ችግሮች ወይም
የእርግዝና መጥፋትን (pregnancy
losses) ጨምሮ
📌 ክትባቶች፦ በአግባቡ መከተቦን እና ወቅተታዊ የሆኑ ክትባቶችን መውሰዶን ያረጋግጡ።
📌የኢንፌክሽን ምርመራ፦ ይህ የሚደረገው እርስዎ እና የወደፊቱን ህጻን ሊጎዱ የሚችሉ ማንኛውም አይነት ኢንፌክሽን እንዳለዎ ለማወቅ ነው።
⛑💊🧬 ለችግር ተጋላጭነትዎን ይቀንሱ
👨⚕የችግሮች ስጋትዎን ለመቀነስ የሚረዱ እርምጃዎችን መውሰድ ይችላሉ። እነዚህ እርምጃዎች ለጤናማ እርግዝና እና ወሊድ ለመዘጋጀት ይረዳሉ።
🖊እነሱም የሚከተሉትን ያካትታሉ፦
♦️ጤናማ አመጋገብ ይኑሮት፡ ከእርግዝና
በፊት እና በእርግዝና ወቅት የተመጣጠነ
ምግብ መመገብ ለአጠቃላይ ጤናዎ
ጠቃሚ ነው።
♦️ጤናማ ክብደት ይኑሮ፣ የአካል ብቃት
እንቅስቃሴ ያድርጉ፡ ከመጠን በላይ
ወፍራም ከሆኑ እንደ የደም ግፊት ወይም
የስኳር በሽታ ያሉ የጤና ችግሮች
ሊያጋጥምዎት ይችላል። ከክብደት በታች
መሆን ልጅዎ ዝቅተኛ ክብደት እንዲኖረው
ሊያደርግ ይችላል።
♦️የጤና ችግሮችዎን በአግባቡ ይታከሙ፡እንደ የስኳር በሽታ ወይም የደም ግፊት ያሉ ወቅታዊ የጤና ችግሮችዎን ይቆጣጠሩ።
♦️ፀንሱ ላይ ሊከሰት የሚችል የአፈጣጠር እንከን (ችግር) መከላከል፡ በየቀኑ 400 mcg ፎሊክ አሲድ ይውሰዱ (እርገዘና ከመፈጠሩ 2 ወር አስቀድሞ)
♦️አልኮል አይጠጡ፡ በእርግዝና ወቅት አልኮሆል መጠጣት የፅንስ መጨንገፍ፣ የፅንስ መምት እና የእድገት መዘግየት ሊያስከትል ይችላል።
♦️ማጨስን ማቆም፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ሲጋራ በሚያጨሱ እናቶች የሚወለዱ ሕፃናት ቶሎ ግዜያቸው ሳይደርስ ይወለዳሉ ወይም ዝቅተኛ የወሊድ ክብደት ይኖራቸዋል። እንዲሁም ለሲጋራ ጭስ መጋለጥ ዝቅተኛ ክብደት ያለው ልጅ የመውለድ ዕድሉ ከፍተኛ ያደርገዋል።
♦️ የሚወስዱትን ማንኛውንም መድሃኒት ለሃኪሞ ሪፖርት ያድርጉ፡
♦️ ከጎጂ ኬሚካሎች ይራቁ፡
♦️ በየቀኑ ቫይታሚኖችን ይውሰዱ፡ ይህም ሰውነትዎ ጤናማ ልጅን ለመመገብ የሚያስፈልጉትን ንጥረ ነገሮች እና ቫይታሚኖች ማግኘቱን ለማረጋገጥ ይረዳል።
♦️ ኢንፌክሽንን መከላከል፡
♦️ለቤት ውስጥ ብጥብጥ (Domestic violence) እርዳታ ያግኙ፡ ከእርግዝና በፊት በደል ከደረሰብዎ በእርግዝና ወቅት ለተጨማሪ ጥቃት አደጋ ሊጋለጡ ይችላሉ።
ዶ/ር አንዱአለም ዘገዬ (Obstetrician and Gynecologist)
ሰላም ጤና ይስጥልኝ‼️🙏
የጡት ካንሰር ግንዛቤን መፍጠሪያ ወር (October month) አስመልክቶ የተከተበ ፅሁፍ፦
1) የጡት ካንሰር ምንድነው?
የጡት ካንሰር ማለት መነሻውን ከጡት ህዋሶች ያደረገ በተለይም የጡት ወተትን ወደ ጡት ጫፍ ከሚወስዱት ቀጫጭን ቱቦዎች እና የጡት ወተትን አመንጪ በሆኑት ዕጢዎች ላይ የሚከሰት የበሽታ አይነት ነው።
የጡት ህዋሳቶች ከሰውነታችን ቁጥጥር ውጪ በሆነ መንገድ በቁጥር መብዛት ወይንም በመጠን መጨመር ለበሽታው እንደ መንኤነት ተቀምጧል።
የጡት ካንሰር በብዛት ሴቶች ላይ ቢታይም አንድ ፕርሰንት ያክሉ ግን በወንዶች ላይ ይከሰታል።
2) ስንት አይነት የጡት ካንሰር አለ?
የጡት ካንሰር በጠቅላላው ለሁለት ሲከፈል እነኚህም፦ የህዋሶችን መሸፈኛ የገረሰሰ (Invasive Cancer) እና በህዋሶች መሸፈሻ ታቅፎ የተያዘ (Non Invasive) በመባል ይከፈላል። እነዚህ ትልልቅ ክፍልፋዮች በውስጣቸው ሌሎች ትንንሽ ክፍፍሎችን ይዘዋል።
I) በህዋሶች መሸፈኛ ታቅፎ የተያዘው አይነት ክፍል ሁለት አይነቶች ይኖሩታል። እነሱም፦
📌ከእናት ወተት ማመላለሻ ቱቦዎች የሚነሳ ዕጢ (Ductal Cancer insitu) - ይሄ ገና ለካንሰርነት ያልበቃ ነገር ግን ወደ ካንሰርነት ለመለወጥ ሰፊ ዕድል ያለው የበሽታው አይነት ነው።
📌ከእናት ወተት ማመንጫ ዕጢዎች የሚነሳ የተዛባ ዕድገት ያለው ዕጢ (Lobular Neoplasm)
ይሄ አይነት በሽታ በእናት ወተት ማምረቻ ዕጢዎች ውስጥ ባሉት ህዋሶች ላይ የሚታይ የተዛባ የህዋሶች ውቅር ሲሆን፡ ወደ ካንሰር የመለወጥ ዕድሉም ሰፊ ነው።
II) ከጡት ህዋሶች መሸፈኛ አፈትልኮ የወጣ (መሸፈኛውን የገረሰሰ) ካንሰር - Invasive Breast Cancer
ይህ አይነቱ ካንሰር የእናት ጡት ወተት ቱቦዎችን ብሎም ወተት አምራች ዕጢዎቹን አልፎ ያመለጠ ካንሰር ሲሆን በስነ ደዌ ሐኪሞች በብዙ አይነቶች ይከፋፈላል። ለምሳሌ፦ ቱቡላር፣ ሙሲነስ፣ ሜዱላሪ፣ ፓፒላሪ...... ወዘተ
🎯የጡት ካንሰር ከላይ ከተገለፀው ክፍፍል በተጨማሪ በደረጃ መጠንም ለሶስት ይከፈላል።
ሀ) በጡት ህዋሶች ውስጥ ብቻ የሚገኝ ካንሰር(Early Breast Cancer -> Stage 0 - IIA)
ይሄ አይነት የካንሰር ደረጃ ያላት ታካሚ በጥሩ ደረጃ ላይ በመገኘቷ ምክንያት ካንሰሩን ሙሉ በሙሉ ለማዳን ይቻላል። የዚህ ደረጃ መገለጫዎች የሆኑት አነስተኛ የጡት ዕብጠት እና አነስተኛ ቁጥር ያላቸው የብብት ንፍፊቶች በአግባቡ በቀዶ ጥገና መታከም ይችላሉ።
ለ) ከጡት ህዋሶች ያለፈ እና በጡት ዙሪያ ባሉት የሰውነት ክፍሎች እና ንፍፊቶች ላይ የተዛመተ ካንሰር (Locally Advanced Breast Cancer -> Stage IIB - III)
ይህ አይነት ደረጃ ላይ የመጣች ታካሚ በቀዶ ጥገና ሙሉ በሙሉ የመዳን ዕድሏ የቀነሰ ቢሆንም የበሽታው ስርጭት ግን የተገታ ስለሆነ በሌሎች ህክምና መንገዶች ታግዞ የመዳን ዕድሉን መጨመር ይቻላል።
ሐ) በመላ ሰውነት ውስጥ የተሰራጨ የጡት ካንሰር (Metastatic Breast Cancer)
ከጡት ህዋሶች ተነስቶ በደምስር፣ በንፍፊቶች ዕገዛ እና ዙሪያውን ባሉ ህዋሶች ታግዞ የተሰራጨ ካንሰር ሲሆን ለህክምናም አዳጋች የሚባል አይነት ነው። በተለምዶ በብዛት ወደ አጥንት፣ ጉበት ወይም ሳንባ የመዛመት ዕድሉ ከፍተኛ ነው።
🎯 ሶስተኛው አይነት የጡት ካንሰር በሽታ ክፍፍል በጡት ህዋሶች የሆርሞን ግብረ መልስ ላይ ይመሰረታል። (በተለይም ኢስትሮጅን እና ፕሮጄስትሮን ለሚባሉት ሆርሞኖች‼️) እነዚህ ሆርሞኖች በካንሰር በተጠቁት የጡት ህዋሶች ላይ የሚገኙ ተቀባይ (Receptors) ካላቸው፡ የጡት ካንሰሩ መልካም የሚባል እና ለሆርሞን ህክምናም ያለው ቅቡልነት በጣም ጥሩ ነው። እነዚህ የህዋሶቹ ሆርሞን ተቀባይ ክፍሎች፦ ኢስትሮጅን ሪሴፕተር፣ ፕሮጄስትሮን ሪሴፕተር እንዲሁም ኅርቱ ሪሴፕተር በመባል ይታወቃሉ።
3) የጡት ካንሰር ምልክቶች ምን ምንድናቸው?
☑️የጡት ዕባጭ
☑️የጡት ቅርፅ እና መጠን መለወጥ (በተለይ ሁለቱንም ጡቶች ማወዳደር ሲቻል)
☑️የጡት ቆዳ መሰርጎድ እንዲሁም የጡት ቆዳ መወፈር
☑️የጡት ጫፍ ወደ ውስጥ መግባት (መሰርጎድ)
☑️በጡት ቆዳ ላይ የሚታይ ሽፍሽፍታ
☑️በጡት ጫፍ የሚወጣ ለየት ያለ ፈሳሽ ወይም ደም
☑️በብብት ስር የሚወጣ ዕባጭ/የንፍፊት መጠን መጨመር
☑️ጡት ላይ የሚከሰት ለብዙ ጊዜ የሚቆይ ህመም
☑️የጡት ቆዳ መቅላት ወይም የቆዳ ቀለም መቀየር
☑️ጡት ውስጥ በዳሰሳ የሚገኝ የጡት ህዋሶች መወፈር
🎯እነዚህን ከላይ የተጠቀሱትን ምልክቶች ያየች ዕንስት ወይም ያየ ወንድ በአቅራቢያ በሚገኝ የጤና ተቋም አስፈላጊውን ምርመራ እንድታደርግ/እንዲያደርግ ይመከራል።
4) የጡት ካንሰር ስርጭት ምን ይመስላል?
የጡት ካንሰር በስፋት የሚታይ ካንሰር ሲሆን በዓመት እስከ 1.7 ሚሊየን ሰዎችን የሚያጠቃ የበሽታ ዓይነት ነው። እ.ኤ.አ በ2013 ብቻ በጡት ካንሰር በሽታ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከግማሽ ሚሊየን በላይ ሆኖ ተመዝግቦ ነበር‼️
በአደጉት ሀገራት ከስምንት ሴቶች አንዷ በህይወት ዘመኗ የጡት ካንሰር በሽታ ያጋጥማታል። በአውሮጳ ብቻ በየሁለት ደቂቃው አንድ ሰው በጡት ካንሰር በሽታ ይያዛል፤ በየስድስት ደቂቃው ደግሞ በጡት ካንሰር ምክንያት ይሞታል። እነዚህ ቁጥራዊ መረጃዎች የበሽታውን አያሌ ስርጭት ያሳያሉ‼️ በሀገራችን ደግሞ ከሁሉም ካንሰሮች በግምባር ቀደምተኝነት ላይ ይገኛል። በአዲስ አበባ ካንሰር ሪጅስትሪ በተጠናው ጥናት መሰረት የጡት ካንሰር በሽታ በ32% የመጀመሪያውን ቦታ ይይዛል። እንዲሁ እኔ በምሰራበት በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ሕይወት ፋና ካንሰር ክፍል በተደረገው የታካሚዎች መረጃ ስብሰባ የበሽታው ምጣኔ እስከ 40% ይገመታል‼️🎯
5) የጡት ካንሰር መንስዔዎች ምንድናቸው?
የበሽታውን መንስዔዎች ሙሉ በሙሉ እነዚህ ናቸው ለማለት ባያስደፍርም ጥናቶቹ ግን አጋላጭ ናቸው ያሏቸውን ምክንያቶች ጠቁመዋል።
i) በፆታ ሴት መሆን በራሱ
ii) በዕድሜ ጎልማሳ መሆን - በተለይ ከ50 ዓመት በላይ በሆኑ ዕንስቶች ላይ
iii) በቤተሰብ የሚተላለፍ የጡት ካንሰር(የመራሔ ለውጥን ሸሽጎ የያዘ የጡት ካንሰር)
iv) የተዛባ የኢስትሮጅን ሆርሞን ዑደት ወይም የኢስትሮጅን ሆርሞን ከቁጥጥር ውጪ መጨመር
v) ደረታቸው ላይ የጨረር ህክምናን የወሰዱ ግለሰቦች
vi) ልጅ ያልወለዱ ዕንስቶች ወይም ልጅን ዘግይተው (ከ30 ዓመት ዕድሜያቸው በላይ) የወለዱ እናቶች
vii) ከመጠን በላይ ያለፈ ክብደት - Obesity
viii) የአልኮል መጠጥ አዘውትረው የሚጠጡ ዕንስቶች
ከላይ ከተገለፁት አጋላጭ ሁኔታዎች ትልቁን የመጋለጥ ዕድል የሠዘው የቤተሰብ ታሪክ ነው። በተለይም የአንድ ዕንስት እናት፣ እህት ወይም አክስት ተይዘው ከነበረ የመተላለፍ ዕድሉ ሁለት ዕጥፍ ይጨምራል። የተጠቃችው የቅርብ ዘመድ ደግሞ ከ50 ዓመት በታች ከሆነች በበሽታው የመያዝ ዕድሉ በሶስት ዕጥፍ ይጨምራል‼️
6) የጡት ካንሰር እንዳለብን እንዴት ይታወቃል?
የጡት ካንሰር የሚታወቀው በጠቅላላ የሰውነት ምርመራ፣ በምስል ምልከታ እና የናሙና ምርመራ ነው። ከዚህ በተጨማሪ አስፈላጊ የሚባሉትን የህክምና ታሪክ መረጃዎች ለሚያክመው ሐኪም በአግባቡ መሰጠት ይኖርባቸዋል።
ምርመራው በቀዶ ጥገና ስፔሻሊስት ሐኪም ወይም በካንሰር ሐኪም መደረግ ሲኖርበት ሐኪሙም ደረጃ በደረጃ ከጠቅላላ ምርመራ አንስቶ የጡት እና የብብት ምርመራዎችን በአይን ምልከታ እና በዳሰሳ ያደርጋል።
የሚያጠራጥር ሁናቴ የሚኖር ከሆነ ደግሞ የጡት ራጅ (ማሞግራፊ)፣ የጡት አልትራሳውንድ፣ የጡት MRI እንዲሁም የጡት ናሙና ምረመራ ይደረጋል። የናሙና ምርመራው በመርፌ ወይም በቀዶ ጥገና ከተወሰደው የጡት ህዋስ ላይ በስነ ደዌ ሐኪም ይደረጋል።
7) የጡት ካንሰር ህክምና ምን ይመስላል?
🎯 ህክምናው በጡት ካንሰር አይነቶቹ፣ በጡት ከንሰሩ ደረጃ እና የጡት ካንሰሩ የሆርሞን መዋቅር ላይ ተመርኩዞ ይደረጋል። ህክምናው ቀዶ ጥገናን፣ የጨረር ህክምናን፣ በደምስር የሚሰጥ ህክምናን (ኬሞቴራፒ) እንዲሁም የተዛባውን የሆርሞን መጠን የማከም ህክምና ይደረጋል። አሁን ላይ ደግሞ የዘመነው የህክምና ስርዓት ታርጌትድ የሚባለውን ዓይነት የካንሰር ህዋሶችን ብቻ አድኖ የሚገለውን ህክምና እንካቹ ብሏል። ደረጃቸው የጨመረ እና ለህክምና አዳጋች በሆነ ደረጃ ላይ የሚገኙ ግለሰቦችን ደግሞ በህይወት የማቆየት እንዲሁም ምቾትን የመስጠት ህክምና ይደረግላቸዋል። (Palliative Care)
8) የጡት ካንሰር ከታከመ በኋላ ክትትሉ ምን ይመስላል?
እንደሁሉም የካንሰር በሽታ ታካሚ ቢያንስ ለአምስት ተከታታይ ዓመታት በካንሰር ህክምናው ጠበብቶች የቅርብ ክትትል መደረግ አለበት። ጥናቶቹ የሚመክሩት ክትትሉ ለመጀመሪዎቹ ሁለት ዓመታት በየሶስት ወሩ እንዲደረግ ሲሆን ለቀሪዎቹ ሶስት ዓመታት ደግሞ በስድስት ወራቶች እንዲሆን ነው።
9) የጡት ካንሰር ታካሚዎች የዕገዛ ማህበራት አስፈላጊነት? (The need for Breast Cancer Support Group)
በጡት ካንሰር የተጠቁ ዕንስቶች በማህበር ታቅፈው አስፈላጊውን የስነ አዕምሮና እና የስነ ልቦናዊ ተግዳሮቶችን የሚፈቱባቸው መድረኮች መዘጋጀት ይኖርባቸዋል። የእነዚህ ማህበራት አስፈላጊነት እና ጥቅም የእትየለሌ ነው‼️ ማህበራዊው ተሳትፎው ታካሚዎቹን ከመርዳት ባለፈ ስለጡት ካንሰር ግንዛቤን ለመፍጠር ሁነኛ መፍትሔም ነው። ለዚህም ነው ጥናቶቹ የእነዚህን ማህበራት መዋቅራዊ ማዕቀፍ አለምአቀፋዊ እንዲሆን የሚመክሩት።
10) የጡት ካንሰር ቅድመ ምርመራ እና ጥቅሞቹ?!
🎯በአደጉት ሐገራት በወር አንዴ ዕድሜያቸው ከ20 ያለፉ ዕንስቶች እራሳቸውን በእራሳቸው ጡቶቻቸውን እንዲፈትሹ ይመከራል‼️ (Self Breast Examination)
🎯 ዕድሜያቸው ከ40 ያለፉ ሴቶች ደግሞ በዓመት አንዴ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ በካንሰር ህክምና ጠቢባኑ ጡቶቻቸውን እንዲያስፈትሹ ይመከራል‼️ ከምርመራው ባለፈ የጡት ራጅም እንዲነሱ ምክር አዘል ትዕዛዛቸውን ያስቀምጣሉ።
🎯 ስለዚህ ዕንስቶች ይሄን ተረድተው በየዓመቱ በሚደረገው የጥቅምት ወር የጡት ግንዛቤ መፍጠሪያ ዝግጅቶች ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ ይመከራል‼️‼️‼️ (ሳይቃጠል በቅጠል እንዲሉ አበው)
ዶ/ር ሚካኤል ሻውል ለማ ፤ በካንሰር ህክምና ረዳት ፕሮፌሰር ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ፥ ህይወት ፋና ካንሰር ሴንተር
🤰🤰 ነፍሰጡር ነሽን? እንግዲያውስ እነኝህን ከታች የተዘረዘሩትን ነጥቦች አስተውይ!!🤰🤰
በዶ/ር ዳዊት መስፍን፤ የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት
1. እራስ ምታት፣ አይን ብዥ ማለት ወይም መጨለም፣ ከእምብርት በላይ እና በሆድሽ በላይኛው ቀኝ ክፍል ህመም ካለ
⚠️ አስተውይ! :- በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት የግፊት ምልክት ስለሆነ በቶሎ ወደ ጤና ተቋም ሂጂ።
2. ከ 7 ወር በኋላ ከማህፀን የሚወጣ ደም አለን?
⚠️ አስተውይ! :- የእንግዴ ልጁ ቀድሞ ከሆነ፣ ከእንግዴ ልጁ ጀርባ ደም እየፈሰሰ ከሆነ፣ የማህፀን ኢንፌክሽ ካለ እናም ሌሎች ከባድ የሆኑ የጤና እክሎች ምክንያት ስለሚሆን በቶሎ ወደ ጤና ተቋም ሂጂ::
3. በመጀመሪያዎቹ 7 ወራት ደም እና ስጋ የመሰለ ነጭ ነገር ከማህፀን መፍሰስ ፣ ከእምብርት በታች ሆድ መቁረጥ፣ የጀርባ መቁረጥ፣ ውሀ የመሰለ ፈሳሽ መፍሰስ ካለ
⚠️አስተውይ! :- የውርጃ ምልክት ሊሆን ስለሚችል የጤና ተቆምን መጎብኘት ግድ ያስፈልግሻል
4. ጆሮ መጮህ ፣ ማዞር ፣ ከፍተኛ ድካም ፣ እራስ ምታት፣ ልብ ሲመታ መታወቅ ካለ
⚠️ አስተውይ! : - እነኝህ የ ደም ማነስ ምልክቶች ስለሆኑ በቶሎ ወደ ጤና ተቆም ሂጂ
5. በመጀመሪያዎቹ 4 ወራት ከፍተኛ የሆነ ማስታወክ እና ማቅለሽለሽ ፣ ከ5% በላይ ከእርግዝና በፊት ካለሽ ኪሎ መቀነስ
⚠️ አስተውይ! :- ይህ (ማቅለሽለሽና ማስታወክ) በአብዛኞቹ እናቶች ላይ ሊታይ የሚችል ችግር ቢሆንም ነገር ግን በጣም ከፍተኛ ሲሆን እና ኪሎ መቀነስ ሲኖር የህክምና እርዳታ ስለሚያስፈልግሽ ወደ ጤና ተቋም ሂጂ
6. የልጅሽ እንቅስቃሴ ከወትሮው ቀንሶብሻልን?
⚠️ አስተውይ! :- ከ5 ወር በውሀላ አብዛኞቹ እናቶች የልጃቸውን እንቅስቃሴ ማስተዋል ይጀምራሉ ይሁንና የልጅን እንቅስቃሴ የሚቀንሱ ነገሮች ብዙ ቢሆኑም የልጅሽ እንቅስቃሴ ከወትሮው በጣም ከቀነሰብሽ ምክንያት የሚሆኑ ነገሮች:- ውሀው መቀንስ ወይም ደሞ በጣም መጨመር ሲኖር ፣ ከማህፀን ደም ሲፈስ ፣ ፅንሱ ከአእንግዴ ልጁ ታች ሲሆን ፣ ወይም የአንቺ ክብደት እና የስራ ሁኔታ እንዳይሰማሽ ካደረገ አልያም ደግሞ ልጅሽ እንቅልፍ ላይ ሲሆን ሊሆን ይችላል።… ለሁሉም ግን ሀኪምሽን ማማከሩ እና ምርመራ ማድረጉ ተገቢ ነው።
7. ከ 9 ወር በፊት ድንገት በተኛሽበት ፣ ቁጭ ባልሽበት ወይም ስራ ላይ ሆነሽ ውሀ የመሰለ ወይም ሽንት የመሰለ ነገር ‘ፏ ‘ ብሎ ከመሀፀንሽ ከፈሰሰ
⚠️አስተውይ!:- ይህ የእንሽርት ውሀ ሰለሆነ ቶሎ ብለሽ ወደጤና ተቋም ሂጂ አለበለዚያ ለተለያዩ አደጋዎች ልትጋለጭ ትችያለሽ ለምሳሌ የህፃኑ እትብት ሊወጣና እና መታፈን ፣ ለመሀፀን ኢንፌክሽን መጋለጥ እና ለደም መፍሰስ ልትጋለጪ ትችያለሽ::
ዶ/ር ዳዊት መስፍን፤ የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት
መልካም አዲስ አመት! ዘመን እኛን ትመስላለች ስንከፋ ትከፋለች መልካም ስንሆን መልካም ትሆናለች!
ክፋት ከኢትዮጵያ ልጆች ልብ ሁሉ ጠፍታ ዘመናችን መልካም ትሆንልን ዘንድ ፈጣሪ ልብ ይስጠን!
መልካም የትንሳኤ በዓል !
በክሊኒካችን ፀዳል አገልግሎት የሚሰጡት የማህፀን ና ፅንስ ህክምና ስፔሻሊስትና በማህፀን ካንሰር ህክምና ልዩ ስልጠና ያላቸው ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት ዶር እያያ ምስጋን ስለማህፀን በር ካንሰር ማብራሪያ ለ በኩር ጋዜጣ ሰጥተዋል ሙሉውን እንደሚከተለው ጋበዝናችሁ!
የከፋው የማህፀን ችግር የቱ ነው?
ስማቸው አጥናፍ
ካንሰር የሚለው ቃል ሊያስጨንቀን እና ሊያስፈራን ይችላል። አብዛኛውን ጊዜም ሰዎች ስለሞት እንዲያስቡ ሊያደርጋቸው ይችላል። ነገር ግን አብዛኞቹ የካንሰር ዓይነቶች በጊዜ ታውቀው ተገቢው ክትትል ከተደረገላቸው ታክመው ሊድኑ እንደሚችሉ የዘርፉ ባለሙያዎች አረጋግጠዋል፡፡
እኛም በጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የማህፀን እና ፅንስ ሕክምና ስፔሻሊስት (ተባባሪ ፕሮፌሰር) እንዲሁም የማህፀን ካንሰር ሃኪምና ተመራማሪ ዶ/ር እያያ ምስጋን ጋር በማህፀን ጫፍ ካንሰር ዙሪያ ቆይታ አድርገናል፡፡
ዶ/ር እያያ እንደሚሉት የማህፀን ጫፍ ካንሰር ተጠቂዎች ወደ ሕክምና የሚመጡት ህመሙ በከፍተኛ ደረጃ ከተሰራጨ በኋላ ነው። በተለይም የማህፀን ጫፍ ካንሰር አብዛኛዎቹ ተጠቂዎች የሚመጡት በቀዶ ሕክምና ማዳን ከሚቻልበት አልፈው ጨረር በሚያስፈልግበት ደረጃ ደርሰው ነው።
እንደ ሀገር የጨረር ሕክምና የሚሰጥባቸው ሆስፒታሎች የሚገኙት ከክልሉ ውጭ ጥቁር አንበሳ፣ ጅማ እና የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ሕይወት ፋና መሆናቸው ደግሞ ከመጓጓዣ እስከ ሕክምና እጅግ ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ በመሆኑ አንዳንዶች ሕክምናውን ሳያገኙ ለሞት መዳረጋቸውንም ነግረውናል።
ለመሆኑ የማህፀን ጫፍ ካንሰር ምንድን ነው?
የማህፀን ጫፍ ማህፀን ካሉት ብዙ ክፍሎች መካከል አንዱ ነው፡፡ ማህፀን እንደ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች በተለያዩ አይነት በሽታዎች ይጠቃል፡፡ የማህፀን ጫፍ ካንሰር ደግሞ ትልቁ የማህፀን የጤና ችግር ነው፡፡
አጋላጭ ምክንያቶችስ?
የማህፀን ካንሰር ሃኪምና ተመራማሪዉ እንደገለጹት ለማህፀን ጫፍ ካንሰር መከሰት በርካታ ምክንያቶች ቢኖሩም በዋናነት የሚጠቀሰው ግን ከ100 በላይ የቫይረስ ዝርያ ያለው ሂውማን ፓፒሎማ ቫይረስ (HPV) ነው። የሂውማን ፓፒሎማ ቫይረስ የማህፀን ካንሰር እንዲፈጠር ምክንያት የሚሆነው ቫይረሱ በቀላሉ ወደ ታማሚው የሚገባበትን የተመቻቸ መንገድ በመጠበቅ ነው። በዚህም የአባላዘር በሽታ በተለይም በተደጋጋሚ የሚመላለስ የማህፀን ፈሳሽ ለቫይረሱ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል፡፡
የወሊድ መቆጣጠሪያ ክኒኖችን/ታብሌቶችን/ ለረጅም ጊዜ መጠቀምም በማህፀን ጫፍ ካንሰር የመያዝ አጋጣሚን ይጨምራል። ይህ ማለት ግን የወሊድ መቆጣጠሪያዉ በራሱ ካንሰር የሚያመጣ ሆኖ ሳይሆን የማህፀን ጫፍ ላይ የሚያመጣው አካላዊ ለውጥ ቫይረሱ አካባቢውን በቀላሉ እንዲያጠቃ ስለሚያግዘው መሆኑን ተመራማሪዉ ገልጸዋል።
ሲጋራ ማጨስም የማህፀን ጫፍ እንዲጠቁር እና እንዲላላጥ በማድረግ የማህፀን ጫፍ በሂውማን ፓፒሎማ ቫይረስ አማካኝነት በሚመጣው የማህፀን ጫፍ ካንሰር እንዲጠቃ ሌላው አጋላጭ ምክንያት እንደሆነ አስገንዝበዋል። ዕድሜያቸው 18 ዓመት ሳይደርስ ጾታዊ ግንኙነት የሚጀምሩ ልጃገረዶችም በልዩነት ለማህፀን ጫፍ ካንሰር የመጋለጥ አጋጣሚያቸው ሰፊ መሆኑን ተናግረዋል።
የችግሩ ስፋትስ እንዴት ይገለጻል?
ሴቶችን ከሚያጠቁ የካንሰር ዝርያዎች መካከል አንዱ የማህፀን ጫፍ ካንሰር ነው፡፡ በኢትዮጵያ ከጡት ካንሰር ቀጥሎ ከፍተኛ ስጋትን ደቅኗል። በዓለም በየዓመቱ ከ500 ሺህ በላይ አዳዲስ ሴቶች የማህፀን ጫፍ ካንሰር ተጋላጭ ናቸው። በኢትዮጵያም የተጣራ መረጃ ባይኖርም እስከ ስድስት ሺህ 200 ሴቶች በየዓመቱ በአዲስ ይያዛሉ፡፡ አምስት ሺህ ሴቶች ደግሞ በማህፀን ጫፍ ካንሰር ለህልፈት እንደሚዳረጉ ተባባሪ ፕሮፌሰሩ ጠቁመዋል፡፡
የማህፀን ጫፍ ካንሰር ለምን መካከለኛ እና ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት ላይ በስፋት ይከሰታል?
የዓለም ሕዝብ ከፍተኛ ስጋት የሆነው ካንሰር ሁሉንም የአካል ክፍል የሚያጠቃ እና በአይነቱም በርካታ ነው። ይሁን እንጂ ከበርካታ የካንሰር አይነቶች መካከል በክትባት መከላከል የሚቻለው የማህፀን ጫፍ ካንሰርን እና የጉበት ካንሰርን ብቻ መሆኑን ዶ/ር እያያ ጠቁመዋል። እነዚህን የካንሰር አይነቶች በክትባት በመከላከል የችግሩን ስፋት መቀነስ እንደሚቻል ቢታመንም መልካም ውጤቱ ግን በምጣኔ ሐብት ካደጉት ሀገራት ውጭ እውን አልሆነም። በእርግጥ እነዚህ የካንሰር አይነቶች ባደጉት ሀገራትም ከፍተኛ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫናን አሳድረው ነበር፤ ቢሆንም ሀገራቱ የክትባት ሽፋናቸውን ከ70 በመቶ በላይ ማድረሳቸው ከአሳሳቢው መዛመት መዳን እንደቻሉ ነው ያስታወቁት።
በአንጻሩ ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት የማህፀን ጫፍ ካንሰር ስርጭትና የሞት ምጣኔ እየጨመረ ይገኛል። ይህም ሆኖ የክትባት ሽፋኑ ዝቅተኛ መሆኑን ጠቁመዋል። ለዚህም የማኅበረሰቡ ስለ በሽታውና ስለ ክትባቱ ያለው ግንዛቤ ዝቅተኛ መሆን፣ የጤና ተቋማት ዝግጁነት በስጋቱ ልክ አለመሆን እና እንደ ሀገር ያለው ቁርጠኝነት ዝቅተኛ መሆን ዐቢይ ምክንያቶች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
የማህፀን ጫፍ ካንሰር ምን አይነት ምልክቶችን ያሳያል?
የማህፀን ጫፍ ካንሰር እንደ ሌሎች በሽታዎች ሁሉ ፈጣንና ቅጽበታዊ ምልክቶችን አያሳይም። የሚያሳያቸውም ምልክቶች በጊዜ ሂደት የተወሰኑ እንዳልሆኑ፣ እንደ ታማሚዉ በሽታ የመከላከል አቅም የሚወሰኑም ስለመሆናቸው ስፔሻሊስት ሃኪሙ ገልጸዋል። ለአብነት በሽታ የመከላከል አቅማቸው ደካማ በሆኑ ሰዎች ላይ ምልክቶቹ በአጭር ጊዜ ሊታዩ ይችላሉ።
ሂውማን ፓፒሎማ ቫይረስ የማህፀን ጫፍ ካንሰር ከማምጣቱ በፊት በጣም ረጅም የቅድመ ካንሰር ደረጃ አለው። በዚያ ጊዜ ውስጥ የቅድመ ካንሰር ምርመራ የሚያደርጉ እናቶች ህመሙን ሙሉ በሙሉ በሕክምና ማዳን እንደሚቻል ጠቁመዋል። ካንሰር በቅድመ ካንሰርና በካንሰር ደረጃ የተለየዩ ምልክቶች አሉት። በቅድመ ካንሰር ደረጃ ሊስተዋል የሚችለውን ጠቋሚ ምልክት ማወቅ የሚቻለው በአብዛኛው በላብራቶሪ እና በሕክምና ባለሙያው በዕይታ ምርመራ ነው።
የማህፀን ጫፍ ካንሰር ከቅድመ ካንሰር ደረጃ ሲያልፍ ከሚያሳያቸው ምልክቶች መካከል በግንኙነት እና ብልትን በሚታጠቡበት ጊዜ መድማት፣ የጀርባ እና የወገብ ህመም እንዲሁም መጥፎ ጠረን ያለው የማህፀን ፈሳሽ መሆናቸው ሊዘነጋ አይገባም ብለዋል።
ህመሙ ከፍተኛ ደረጃ መድረሱን ከሚነግሩ ምልክቶች መካከልም የዘንጋዳ ውኃ የመሰለ ሽታ ያለው ፈሳሽ፣ የማያቋርጥ ደም መፍሰስ፣ ሽንት መቆጣጠር አለመቻል፣ በፊኛ እና በፊንጢጣ በኩል ከሽንትና ከሰገራ ጋር ተቀላቅሎ ደም መፍሰስ ዋና ዋናዎቹ መሆናቸውን የሕክምና ተባባሪ ፕሮፌሰሩ ተናግረዋል።
እንዴት እንከላከለው?
የማህፀን ጫፍ ካንሰር ፍቱን የመፍትሄ መንገድ ሕክምናው ሳይሆን መከላከል ላይ መሥራት ነው። በአሁኑ ወቅት የትኛውም ጤና ተቋም የቅድመ ካንሰር ምርመራና የቅድመ ካንሰር ደረጃዎችን ማከም የሚያስችሉ መሳሪዎች የተሟሉላቸው በመሆናቸው አገልግሎቱን በቀላሉ ማግኘት እንደሚቻል ሃኪሙ ጠቁመዋል።
የማህፀን ጫፍ ካንሰር መከላከያ ዘዴዎችን ዶ/ር እያያ በሦስት ከፍለው አብራርተውልናል። የመጀመሪያ ደረጃ የመከላከያ መንገዶች በዋናነት የሚያገለግሉት ዕድሜያቸው ከ14 ዓመት በታች ለሆኑ ልጃገረዶች ነው። ለዚህም ዕድሜያቸው ከዘጠኝ እስከ 14 ዓመት ለሆኑ ልጃገረዶች የሂውማን ፓፒሎማ ቫይረስ መከላከያ ክትባት ይሰጣል። የማህፀን ጫፍ ካንሰርን ለመከላከል ሦስት አይነት ክትባቶች ቢኖሩም በአሁኑ ወቅት አራት የሂውማን ፓፒሎማ ቫይረስ ዝርያዎችን መከላከል የሚያስችለው ጋርዳፊን የተሰኘው መድሀኒት በኢትዮጵያ እየተሰጠ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
የጤና መረጃዎችን ማዳረስ፣ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች (ያለ ዕድሜ ጋብቻ፣ ከጋብቻ በፊት ጾታዊ ግንኙነት ማድረግ፣ ሲጋራ ማጨስ) እንዲወገዱ ማስተማር፣ አደገኛ ምልክቶችን ማሳወቅ ከበሽታው አሳሳቢነት ለመራቅ የሚያግዙ የመጀመሪያ ደረጃ የመከላከያ መንገዶች መሆናቸውን ጠቁመዋል።
ሁለተኛው የማህፀን ጫፍ ካንሰር የመከላከያ መንገድ ከ15 እስከ 30 ዓመት ዕድሜ ላይ በሚገኙ ሴቶች ላይ የሚተገበር ነው። በዚህ ዕድሜ መካከል ጾታዊ ግንኙነት በከፍተኛ ደረጃ ይጀመራል። ይህም በአንጻራዊነትም ቢሆን ለሂውማን ፓፒሎማ ቫይረስ ተጋላጭነት ከፍ የሚልበት ነው። ስለሆነም የቅድመ ካንሰር ምርመራ በማድረግ እና የቅድመ ካንሰር ደረጃዎችን በመለየት ከሚደርሰው ዘርፈ ብዙ ችግር መታደግ እንደሚቻል የማህፀን ካንሰር ተመራማሪዉ አስገንዝበዋል። ከዚህ ውጭ ኮንዶምን በአግባቡና በትክክለኛው መንገድ መጠቀም ከበሽታው ራስን ለመሰወር አንዱ የመከላከያ መንገድ ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል።
ዕድሜያቸው ከ30 በላይ በሆኑ ሴቶች ላይ በአብዛኛ የማህፀን ጫፍ ካንሰር ይከሰታል። ይህም የሚሆነው የቅድመ ካንሰር ጊዜው በማለፉ ምክንያት ሲሆን መከላከል የሚቻለውም እንደ ህመሙ ደረጃ በመድሃኒት፣ በቀዶ ጥገና እና በጨረር ተገቢውን ሕክምና በመስጠት መሆኑን ዶ/ር እያያ ገልጸዋል።
የክትባቱን ፋይዳ በሕዝብ ዘንድ እንዴት እናስርጽ?
የማህፀን ካንሰር ተመራማሪዉና ተባባሪ ፕሮፌሰሩ ዶ/ር እያያ እንዳሉት ሕዝቡ ስለ ማህፀን ጫፍ ካንሰር ምንነት፣ ስለሚከሰትበት መንገድ እና በቅድመ ካንሰር ምርመራም መከላከል እንደሚቻል በተደጋጋሚ የተለያዩ የግንኙነት ሰንሰለቶችን በመጠቀም ግንዛቤን ማሳደግ በሽታው እያደረሰ ካለው ሰብዓዊና ምጣኔ ሐብታዊ ኪሳራ መውጣት ይቻላል። ጤናማ ዜጋን ለመፍጠር የጤና ትምሕርት በትምሕርት ቤት ደረጃ ለተማሪዎች በመስጠት ለማኅበረሰቡ ተደራሽ እንዲያደርጉ ማስቻል የመጀመሪያው የችግሩ ስፋት የመቀነሻ የመፍትሄ መንገድ መሆኑን ጠቁመዋል። በሌላ በኩል ደግሞ የሀገር ሽማግሌዎችን፣ የሃይማኖት አባቶችን እና ታዋቂ ግለሰቦችን በመጠቀም እና መድረኮችን በመፍጠር ማኅበረሰቡን ማስተማር እንደሚገባም ጠቁመዋል።
መገናኛ ብዙኀንም የሕዝብ የጤና ስጋት የሆኑትን ግን ደግሞ በሕዝብ ዘንድ ትኩረት ተነፍጓቸው ከፍተኛ ኪሳራ እያስከፈሉ የሚገኙትን በሽታዎች በመለየት ተደጋጋሚ ሥራዎችን በመሥራት ለሕዝብ ተደራሽ ማድረግ ሌላው የስርጸት መንገድ እንደሆነ አስገንዝበዋል።
የገጠርና የከተማ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች በበኩላቸው በሥራቸው ለሚገኙት አባላት በቂ ትምሕርት በመስጠት ዕድሜያቸው ለክትባት የደረሱ ልጃገረዶች ክትባቱን እንዲወስዱ በማድረግ፤ በቅድመ ካንሰር ምርመራ ዕድሜ ክልል ላይ የሚገኙትም ወደ ጤና ተቋም በመሄድ ራሳቸውን አውቀው ተገቢውን ሕክምና እንዲያደርጉ የማድረግ ኀላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ጠይቀዋል።
ከሰሞኑ የ ማህፀን በር ካንሰር አምጭ ባይረስ መከላከያ ክትባት (Gardasil) በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች መሰጠት ጀምሯል።ይህ ክትባት በበርካታ የአለማችን ክፍል የሚሰጥና በኢትዮጵያም ከ ተወሰኑ አመታት በፊት በአንዳንድ የግል ተቋማት ሲሰጥ የነበረ ነው። በአሁኑ ወቅትም በመላ ኢትዮጵያ በአማራ ክልል ጨምሮ በትምህርት ቤት ለሚገኙ የ 14 ዓመት ሴት ተማሪወች እየተሰጠ ይገኛል።
ክትባቱ የሚሰጠው በአለማቀፍ ደረጃ ሁሉም ክትባቶች ለሰው ልጆች ሁሉ እንዲዳረሱ ጥረት በሚያደርገው GAVI በተሰኘ ተቋም ድጋፍ ሲሆን ክትባቱን በዩኒሴፍ በኩል Merck እና gsk ከተባሉ ሁለት አምራቾች ተገዝቶ የሚቀርብ እንደሆነ መረጃወች ያሳያሉ።እነዚህ አምራቾቺ በአለም አቀፍ ደረጃ ጥራት ያለው ክትባት በማምረት ይታወቃሉ። የነዚህ ኩባንያ ምርቶች የአሜሪካን ደረጃ አሟልተው የብቃት ማረጋገጫ አግኝተዋል።ክትባቱ ከ ቫይረሱ በበቂ ሁኔታ እንደሚከላከል የሚያሳዮ ጥናቶች ቢኖሩም ከሁሉም የቫይረሱ አይነቶች የማይከላከል በመሆኑ ምክንያት ጥያቄ ይነሳበታል።
ወደ 16 የሚደርሱ የቫይረሱ ዝርያወች የማህፀን በር ካንሰር ሊያመጡ የሚችሉ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ ሁለቱ 70% ለሚሆነው የማህፀን በር ካንሰር ምክንያት ናቸው።በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የሚሰጠው ክትባት እነዚህን ሁለቱን የ ቫይረሱን አይነቶች የሚከላከል ሲሆን በተጨማሪም ሌሎች ሁለት ቫይረሶችን ይከላከላል። ባጠቃላይ 6,11,16,18 የተባሉትን የቫይረሱን ዝርያወች ይከላከላል።በመሆኑም ይህን ክትባት በመውሰድ ብቻ ቫይረሱን ሙሉ በሙሉ መከላከል ስለማይቻል የማህፀን በር ቅድመ ካንሰር ምርመራን አጠናክሮ መቀጠል ተገቢ ነው። የቫይረሱን መከላከያ ክትባት ከ ማህፀን በር ቅድመ ካንሰር ምርመራ ጋር አጠናክሮ በመስጠት በርካታ እናቶችን ከ ማህፀን በር ካንሰር መከላከል ይቻላል ተብሎ ይታመናል ።
ክትባቱ የራሱ የጎን ጉዳቶች ያሉት ሲሆን አብዛኞቹ አሳሳቢ አይደሉም። አልፎ አልፎ ግን አሳሳቢ የጎን ጉዳቶች ሊከሰቱ ይችላሉ ከነዚህም መካከል ለተወሰነ ጊዜ ራስን መሳት እንዲሁም ከባድ አለርጅ ሊከሰት የሚችልበት እድል አለ። እነዚህ የጎን ጉዳቶች ሌሎች የክትባት አይነቶች ሲወሰዱም ሊመጡ የሚችሉ ናቸው። ከዚህም በተጨማሪ ጉንፋንም ሆነ ሌሎች ቀላል የቫይረስ ኢንፌክሽኖችን ተከትሎ ሊመጣ የሚችል GBS የተባለ ጊዚያዊ የሰውነት ጡንቻወችን የሚያልፈሰፍስ ህመም ሊያስከትል ይችላል የሚሉ ወገኖች ቢኖሩም በተለይ አምራቾቹ ይህን የሚያሳይ ጥናት የለም ይላሉ።
ባጠቃላይ ይህ ክትባት አሜሪካን ጨምሮ በአለማችን ከ 120 ሀገራት በላይ ይሰጣል።
ፀዳል ክሊኒክና ባለሞያወቹ ለሁሉም ወላጆች ልጆቻቸው ክትባቱን እንዲያገኙ እንዲያደርጉ አበክረው ይመክራሉ።
መልካም የገና በዓል!ሰላም ለኢትዮጵያ!
ጤና ይስጥልን!
አንዷና ውድ ሀገራችን ኢትዮጵያ ሰላም እንድትሆን እየተመኘን የእናቶች እና ህፃናት ጤናን በተመለከተ ጥያቄወቻችሁንና አስተያየታችሁን እንድታቀርቡልንና የጤና መረጃ እንድታገኙ ተከታዩን የቴሌግራም ቻናላችን ተቀላቀሉ!
https://t.me/tsedalclinic
ፀዳል ልዩ የእናቶች ና ህፃናት ህክምና ክሊኒክ You can view and join right away.
እንደምን ሰነበታቹህ ውድ ተከታታዮቻችን?
ሠላም ለኢትዮጵያችን እየተመኘን የሚከተለውን ፁሁፍ ጋበዝናችሁ!
የህጻናት አጥንት መለስለስ - Rickets👶🦴
[ወላጆች ሊያነቡት የሚገባ]
ሪኬትስ በቫይታሚን ዲ እጥረት ምክንያት የህጻናት አጥንትን ጥንካሬ የሚቀንስ በሽታ ነው። ቫይታሚን ዲ ከጸሃይ ብርሃን እና ከምግብ የሚገኝ ሲሆን ለህጻናት የአጥንት ጥንካሬ እና እድገት ትልቅ ድርሻ አለው።
ሪኬትስ በምን ምክንያት ይመጣል❓
1. በቂ የጸሃይ ብርሃን አለማግኘት እና ልጆችን በተገቢው ሁኔታ እና በትክክል ጸሃይ አለማሞቅ 🔆
2. ቫይታሚን ዲ እና ካልሺየም ያላቸውን ምግቦች በበቂ ሁኔታ አለመመገብ🍲
3. የአንጀት ፣ የጉበት እና የኩላሊት ህመሞች
ምልክቶቹ ምንድን ናቸው?
🔹የጉልበት መጣመም(ብራኬት ፣ የጉልበት መነካካት)
🔹የእድገት መቀንጨር
🔹የአጥንት ህመም
🔹የግንባር አጥንት መተለቅ
🔹ጥርስ ለመውጣት መዘግየት🦷
🔹ለመዳህ እና ቆሞ ለመሄድ መዘግየት
🔹ድካም
🔹የአጥንት መሰበር እንዲሁም የጀርባ አጥንት መጣመም ሊከሰት ይችላል።
ህጻናት ሪኬትስ (የህጻናት አጥንት መለስለስ) እንዳላቸው እንዴት ማወቅ ይቻላል?🔎
🔸ሃኪሙ የህጻኑ አጥንት ላይ በሚያድርገው ምርመራ
🔸የደም ምርመራ💉
🔸የአጥንት ራጅ ምርመራ
ህክምናው እንዴት ነው?👩⚕️
👉በሃኪም የሚታዘዙ መድሃኒቶች 💊በህጻኑ አጥንት ውስጥ እጥረት ያላቸውን እንደ ካልሺየም እና ቫይታሚን ዲ ያሉ ንጥረ ነገሮች በሂደት እንዲስተካከል ያደርጋል። በዚህም የአጥንቱ ጥንካሬ እየጨመረ ይሄዳል።
👉የከፋ የአጥንት ምጣመም እና መሰበር ከተከሰተ የቀዶ ህክምና ሊያስፈልግ ይችላል።
የሪኬትስ በሽታን መከላከል ይቻላል?
✔️ህጻናት ጤናማ አጥንት ኖሯቸው እንዲያድጉ
ጸሃይ ማሞቅ ( ምንም ቅባት ሳይቀቡ ፣ ከ 4 እስከ 7 ሰአት ፣ ከ20 – 30 ደቂቃ ያህል እርቃናቸውን መሞቅ አለባቸው)🌞
✔️ልጆች በክረምት ከሆነ የተወለዱት እና የእናት ጡት ብቻ እሚጠቡ ከሆነ ተጨማሪ ቫይታሚን ዲ ያስፈልጋቸዋል🌧
✔️በቂ ቫይታሚን ዲ እና ካልሺየም ያላቸውን ምግቦች እንደ ወተት🥛 እና የወተት ተዋፅኦ ፣ አሳ ፣ የአሳ ዘይት ፣እንቁላል🥚 እና የመሳሰሉትን መመገብ ያስፈልጋል
ለሁሉም ወላጆች 👨👩👧👦 ይህ 👁️🗨️ መረጃ ይደርስ ዘንድ share ያድርጉት
አዘጋጅ ፦ዶ/ር ናርዶስ ወርቁ : የህጻናት አጥንት ቀዶ ህክምና ሰብ-ስፔሻሊስት
ውዶች እንኳን ለብርሀነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ! ሀገራችን እናቶች እልል የሚሉባት ህፃናት የሚቦርቁባት ሰላም የተመላች ያድርግልን! ሰላም!ሰላም! ሰላም ለፍጡራን ሁሉ!
ውድ ደምበኞቻችን እንኳን ለ 2014 ዓም አደረሳችሁ።
አዲሱ አመት የሰላም ፣የጤና እና የስኬት አመት እንዲሆንላችሁ እንመኛለን!
ፀዳል ክሊኒካችን ከዚህ ቀደም የምንሰጠውን የማህፀንና ፅንስ ህክምና በማሳደግና ሙሉ የህፃናት ህክምናን በመጨመር አድራሻችን ወደ ፓፒረስ ሆቴል አካባቢ - ከፓፒረስ ሆቴል ወደ አዲሱ መናኸሪያ በሚወስደው መንገድ ሀን ጤና ጣቢያ ፊት ለፊት ያዛወርን መሆኑን በደስታ እንገልፃለን!
መልካም አዲስ አመት!
እንደምን ሰነበታቹህ ?
ዛሬ አጭር መረጃ ስለ ማህፀን በር ቅድመ ካንሰር ምርመራና ህክምና እንሰጣቹሀለን
1.አገልግሎቱ የት ይገኛል ?
በአማራ ክልል እና አዲስ አበባ ከመጀመሪያ ጀረጃ ሆስፒታል (primary hospital )ጀምሮ በሁሉም የመንግስት ሆስፒታሎች ና በተመረጡ ጤና ጣቢያወች ይገኛል
2.አገልግሎቱ ለማን ይሰጣል?
እድሜያቸው ከ 30-49 ለሆኑ ሴቶች በየአምስት አመቱ
እድሜያቸዉ ከ15-49 ለሆኑ በኤች.አይ.ቪ (HIV) ተጠቂ ሴቶች በየሁለት አመቱ
ይሄንን መልክት ለሁሉም ሴቶች በማድረስ ቤተቦቻችን ካስከፊውና ገዳዩ የማህፀን በር ካንሰር እንከላከል !
ሁሉንም የማህፀንና ተያያዥ ካንሰሮች በክሊኒካችን ልዩ የማህፀን ካንሰር ህክምና ስልጠና ባላቸው ባለሙያዎች እንሰጣለን።
ባህር ዳር ቀበሌ 13 ሀይሌ ት/ቤት አካባቢ እንገኛለን!
ውድ ደምበኞቻችና ተከታታዮቻችን እንደምን ሰነበታችሁ ?
ሰላምና ጤንነት እንመኝላችሗለን!
ክሊኒካችን ይብለጥ በመደራጀትና ተጨማሪ ባለሙያወችንም በመያዝ አገልግሎቱን ቀጥሏል!
በተለይ በዚህ ወቅት የተከሰተውን አለምአቀፍ የኮሮና ወረርሽኝ ለደምበኞቻችን ስጋት እንዳይሆን በአንድ ጊዜ አራት ተገልጋዮችን ብቻ ርቀታቸውን ጠብቀው እንዲስተናገዱ እያደረግን እንገኛለን።
በተጨማሪም ለቤተሰብ ምጣኔ ተገልጋዮች ሁሉንም አማራጮች ማለትም
- በማህፀን የሚቀበር ሉፕ
- በክንድ የሚቀበር ኢምፕላንት
- በመርፌ የሚሰጥ ዴፖ
- በየቀኑ የሚወሰድ ፒልስ
- ለአጥቢወች ተስማሚ ፒልስ
- በ72 ሰአት ውስጥ የሚወሰድ ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ - ፖስት ፒል
- ኮንዶም
በክሊኒካችን ያለ ምንም ስጋትና መጉላላት ያገኛሉ።
ሌሎች የስነ ተዋልዶ አገልግሎቶችንም በስፔሻሊስት ሀኪሞች እየሰጠን ነው።
ላቦራቶሪያችን ይበልጥ ዘምኖ የኤች አይ ቪ ና የጉበት ባይረስ ምርመራን ጨምሮ ለስኴርና የደም ግፊት ተጋላጭ የሚያደርጉ የሰውነት ስብ ክምችትንም መለካት ጀምረናል አስፈላጊውን የቅድመ ጥንቃቄ ምክርም እንሰጣለን!
የመካነት ምርመራ ለሴቶችም ለወንዶችም እንሰጣለን ውጤቱንም ሆነ ህክምናውን በአንድ ቀን ጨርሰው ወደ ቤት እንዲመለሱ እንሰራለን።በርካታ ጥንዶች በመካነት ምርመራና ህክምናችን ልጅ ወልደው ለመሳም በቅተዋል። ዛሬ ነገ እያሉ ጊዜወትን አያጥፉ መጥተው ያማክሩን አብዛኛዎቹ የመካነት ችግሮች በቀላሉ የሚቀረፉ ናቸው።
የማህፀን እጢ እና የማህፀን በር ቅድመ ካንሰር ምርመራ ና ህክምና ያለ ቀጠሮ በመጡበት ሰአት ጨርሰው እንዲሄዱ እያደረግን ነው።
የአባለዘር በሽታ ምርመራና ህክምና እንዲሁም በተደጋጋሚ የፅንስ መቋረጥ ( ውርጃ) ለሚያስቸግራቸው እናቶች ህክምና እንሰጣለን!
የሾተላይ ምርመራና ህክምና እንሰጣለን!የአልትራሳውንድ አገልግሎታችንም በሁልጊዜም ጥራቱ እንደቀጠለ ነው።
የወንዶች ግርዛት በተለይ ለህፃናት በቀለበት ከተወለዱ ከ ሰባተኛው ቀን ጀምሮ በህፃናት ቀዶ ህክምና ልዩ ስልጠና ባላቸው ባለሙያ እየሰጠን እንገኛለን!
ውብና ፀዱ በሆነው ክሊኒካችን በተመጣጣኝ ዋጋ ና በፍፁም አክብሮት ያለስጋት አገልግሎታችን ያገኛሉ!
ባህርዳር ቀበሌ 13 የቀድሞው አልካን ወደ ሀይሌ(ሽምብጥ) ት/ቤት በሚወስደው መንገድ ላይ እንገኛለን!
ቀጠሮ ለማስያዝም ሆነ ለበለጠ መረጃ
በ 0583208555 ወይም 0910105042 ይደውሉ!
የህክምና ባለሙያዎችን እና የጤና ሚንስትር ምክሮችን በመተግበር እእንዲሁም የ ኮሮና መከላከያ ክትባት በመውሰድ ከኮሮና ወረርሽኝ ቤተሰባችንና ማህበረሰባችን እንከላከል!!
ፀዳል ለቤተሰብ ጤና!!
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Bahir Dar