የወላይታ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት- Wolaita Prosperity Party office

we are in the community!

Photos from የወላይታ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት- Wolaita Prosperity Party office's post 26/12/2023

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ በሳውላ ከተማ ከጎፋ ዞን ማህበረሰብ ጋር ውይይት እያካሄዱ ይገኛሉ።

በውይይት መድረኩ የክልሉ መንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ አለማየሁ ባውዲን ጨምሮ ለሎች የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

Photos from የወላይታ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት- Wolaita Prosperity Party office's post 26/12/2023

የዘንድሮ የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም "የዘመኑ ከተሞች ለኢትዮጵያ ብልፅግና" በሚል መሪ በወላይታ ሶዶ ከተማ እንደሚካሄድ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር አስታውቀ

ወላይታ ሶዶ፣ ታኅሣስ 16፣ 2016 የከተሞች ፎረም ከተሞች ወደሚፈለገዉ የብልፅግና መንገድ እንዲደርሱ የማድረግ ዓላማ አለው ሲሉ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ ገለጹ።

የዘንድሮ የከተሞች ፎረም "የዘመኑ ከተሞች ለኢትዮጵያ ብልፅግና" በሚል መሪ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ሶዶ ከተማ ከየካቲት 9 እስከ የካቲት 15 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚካሄድ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ፎረሙን አስመልክቶ ሚኒስትሯ ጫልቱ ሳኒ በሰጡት መግለጫ፤ ፎረሙ የተዘጋጀው በሚኒስቴሩና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትብብር መሆኑን ገልጸዋል።

በፎረሙ ከ150 በላይ ከተሞች፣ ከ20 በላይ ድርጅቶች እንዲሁም ከ20 ሺህ በላይ የሕብረተሰብ ክፍሎች ይሳተፋሉ ተብሏል።

ፎረሙ በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ዘርፍ የከተሞች ፈጣን ዕድገት ቅኝት የሚደረግበት ነዉ ብለዋል ሚኒስትሯ፡፡

ዘርፉን ከፍ የሚያደርጉና ከተማ ልማት ላይ ሚና ያላቸዉን አካላት በማስተባበር ከተሞችን ወደሚፈለገዉ የብልፅግና መንገድ እንዲደርሱ የማድረግ ዓላማ እንዳለዉም ነው የገለጹት።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ ብርሃኑ ዘዉዴ በበኩላቸዉ÷ ከክልል ጀምሮ እስከዞን ድረስ የተዋቀረ ኮሚቴ የተለያዩ ቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

ለፎረሙም 25 ነጥብ 55 ሄክታር መሬት ተዘጋጅቶ የተለያዩ መሠረተ ልማት ዝርጋታዎች በመከናወን ላይ እንደሚገኙም ተናግረዋል፡፡

ፎረሙ በሚካሄድበት ወላይታ ሶዶ ከተማ እንግዶች በሠላም ቆይተው በሰላም እንዲመለሱ ለጸጥታ ሥራዎች ልዩ ትኩረት መሰጠቱም ተመልክቷል በማለት ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

Photos from የወላይታ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት- Wolaita Prosperity Party office's post 26/12/2023

የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስርዓት ለሕጋዊ፣ ለአስተዳደራዊ እና ለስታቲክሳዊ ጉዳዮች የመረጃ ምንጭ መሆኑን የወላይታ ዞን ፍትህ መምሪያ አስታወቀ

ወላይታ ሶዶ፤ ታህሳስ 16/2016 የወላይታ ዞን ፍትህ መምሪያ የወሳኝ ኩኔት ምዝገባ ወደ መምሪያው በመዛወሩ ምክንያት ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የግንዛቤ ማስጨበጫና ምክክር መድረክ አካሂዷል።

የወላይታ ዞን ፍትህ መምሪያ ኃላፊ አቶ እንዳሻው አባተ በምክክር መድረኩ ላይ እንዳብራሩ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስርዓት ለሕጋዊ፣ ለአስተዳደራዊ እና ለስታቲክሳዊ ጉዳዮች የመረጃ ምንጭ መሆኑን ገልጸዋል።

የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ አገልግሎት ከዚህ በፊት በሠላምና ጸጥታ መዋቅር ይሰጥ የነበረውን ወደ ፍትህ ተቋም መዛወሩን መምሪያው ጠቁመዋል።

አቶ እንዳሻው የመዋቅራዊ ሽግግር ዙሪያ የሰጡት አስተያየት የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ አገልግሎት ከዚህ በፊት በሠላምና ጸጥታ መዋቅር ይሰጥ የነበረውን ዳግም ወደ ፍትህ ተቋም መዛወሩን አስረድተዋል ።

የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ አገልግሎት ክፊያ ተመኑ የወጣው መሰረታዊ ባህሪያትና የህብረተሰቡን የመክፈል አቅም ባገናዘቤ መልኩ አነስተኛ እንዲሆን ታስቦ በየኩነት ዓይነቶች ተሰልተው በወጣው መመሪያ መሠረት ክፍያው እንዲፈጸም አቶ እንዳሻው አሳስበዋል።

ወሳኝ ኩነቶችን ማስመዝገብ ከግለሰባዊ ጠቀሜታው ባሻገር የዜግነት ግዴታ መሆኑና የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስርዓት ለሕጋዊ ለአስተዳደራዊ እና ለስታቲክሳዊ ጉዳዮች የመረጃ ምንጭ ነው ብለዋል።

ተቋሙ የኩኔቶች የምስክር ወረቀቶችን የማረጋገጥና የማመሳከር ሥራ የሚያከናውን በመሆኑ በዞኑ በተለያዩ ምክንያት ሰነዶች እንዲረጋገጡ የማድረግ ሥራ እየተሰራ መቆየቱ ተገልጿል ።

የወላይታ ዞን ሠላምና ጸጥታ መምሪያ አቶ ጳውሎስ ጬማኣ በርክብክብ ወቅት እንደተናገሩት ከዚህ በፊት በተቋማቸው ስሰጥ የነበረው የወሳኝ ኩነት አገልግሎት ወደ ፍትህ መዛወሩ የበለጠ የተቀላጠፈ አገልግሎት ለማግኘት ይረዳል ብለዋል ።

ልደት፣ ጋብቻ፣ ፊቺ፣ ሞት በወሳኝ ኩነቶች በማስመዝገብ ኃላፊነት እንዲወጡና ወሳኝ ኩነቶችን መረጃ በአገባቡ መመዝገብና ማደራጀት ግምታዊ አሰራርን እንደሚያስቀር አስተያየት ሰጪዎች ጠቁመዋል ።

እስከታችኛው መዋቅር ድረስ ያሉ ቅንጅታዊ አሠራርን በማጠናከር በቀጣይነት አገልግሎት አሰጣጥን ለማሳለጥ እንደሚሰራ ተጠቁመዋል።

በወላይታ ዞን ፍትህ መምሪያ የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ዋና ሥራ ሂደት ከሐምሌ 30/2008 ዓም ጀምሮ መንግሥት የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ የሚያመነጨው ወቅታዊ መረጃዎችን ለሕግ፣ ለፍትሕ ለአስተዳደርና ለስታቲስክስ የሚሰጠው ከፍተኛ ፋይዳ በመገንዘብ በአዋጅ ለጥር 760/2004 እና በተሻሻለው 1049/2009 መሠረት ባለፉት 8 ዓመታት ኤጀንሲው ይህ ሥራ ለሕብረተሰቡ የሚሰጠውን ፋይዳ በመገንዘብ በርካታ ቁሳዊና ሞራላዊ አገልግሎት ስሰጥ እንደቆየ ተጠቅሷል።

Photos from የወላይታ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት- Wolaita Prosperity Party office's post 26/12/2023

ፓርቲው በሁሉም መስክ ጠንካራ እንዲሆን የሰው ኃይሉንና የፋይናንስ አቅሙን ለማጎልበት በልዩ ትኩረት እየተሰራ ይገኛል፦ አቶ ዘካሪያስ ታደሰ

ወላይታ ሶዶ፤ ታህሳስ 16/2016 የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀብት ልማት ዘርፍ የእስካሁን የዕቅድ አፈጻጸምና ቀጣይ አቅጣጫዎችም ላይ ተወያይተዋል፡፡

የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀብት ልማት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዘካሪያስ ታደሰ ፓርቲው በሁሉም መስክ ጠንካራ እንዲሆን የሰው ኃይሉንና የፋይናንስ አቅሙን ለማጠናከር በልዩ ትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ለፓርቲው የፋይናንስ ምንጭ የጀርባ አጥንት እንደመሆኑ መጠን የአባላት መዋጮ የሁሉንም ማህበራዊ መሰረቶች አሟጥጦ በመጠቀም ገቢን ማሰባሰብና ማሳደግ እንዳለበትም አመላክተዋል።

የዘርፉ አመራሮች የዘርፉን ስራ ተቋማዊ አሠራርና መመሪያዎችን ተከትሎ እንድፈጽም ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መምራት እንደሚገባም አሳስበዋል።

ከሁሉም ማህበራዊ መሠረት በዝግጅት ምዕራፍ ላይ 50% ተጨምሮ ተሸንሽኖ በተሰጠው ዕቅድ መሠረት ፓርቲውን ወደፊት ሊወስዱ የሚችሉ የአዳዲስ አባላትን የማፍራት ሥራ ተጠናከሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡

ብልጽግና ፓርቲ መተዳደሪያውና ገቢው ከአባሉና ደጋፊዎቹ የሚሰበስብ መዋጮ መሆኑን የገለጹት አቶ ዘካሪያስ ጥራት ያለውን አባል መገንባትና ግልጸኝነት ያለው የፋይናንስ አሰራር የማጠናከር ስራ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባም አሳስበዋል።

ዘርፋ ለፓርቲው አቅም ለማጎልበት ያለው ፋይዳ ከፍተኛ ነው ያሉት አቶ ዘካሪያስ ለዘርፉ ተገቢው ትኩረት መስጠት እንደሚገባም አመላክተዋል።

በቀሪው ወራት ዓመታዊ ዕቅዱ እንድሳካ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ለመስራት ዝግጅት ማድረጉንም ገልጸዋል።

በአፈጻጸም ግምገማ መድረክ የሁሉም ወረዳና ከተማ አስተዳዳር የሀበት ልማት ዘርፍ አመራሮችና የሚመለከታቸው ዘርፍ ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

Photos from የወላይታ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት- Wolaita Prosperity Party office's post 26/12/2023

የዐሥር ዓመቱ የልማት ዕቅድ ለፍራፍሬ ምርት እና ሌሎች ዓይነተኛ የዘርፉ ምርቶችን የሚያካትተውን የሆርቲካልቸር ልማት ሥራን ለማስፋፋት ያለመ ነው፡፡ በመስኖ የተደገፈ እና ምርቱ የላቀ የሆርቲካልቸር ሥራ ለማከናወን የተደረገው ጥረት አስደናቂ ውጤቶችን በማሳየት ላይ ይገኛል፡፡ የዚህ ውጤት ዋና ማሳያ በፓፓያ ምርት ላይ የታየው ምርታማነት ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ

Photos from የወላይታ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት- Wolaita Prosperity Party office's post 26/12/2023

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ጎፋ ዞን ዛላ ወረዳ ገቡ

ርዕሰ መስተዳድሩ ጎፋ ዞን ዛላ ወረዳ ስገቡ ከሜላ ከተማ ጀምሮ የዞኑ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ህብረተሰቡ ደማቅ አቀባበል አድርገዋቸዋል ።

ርዕሰ መስተዳድሩ በቆይታቸው በዞኑ ዛላ ወረዳ የተገነቡ የተለያዩ ተቋማት ግንባታዎችን እንደሚያስመርቁ ፣የልማት ሥራዎችን እንደሚጎበኙ እንዲሁም ከስድስቱ የክልል ማዕከል የህግ አስፈጻሚና ተርጓሚ ማዕከል በሆነችው ሳውላ ከተማ ከህብረተሰቡ ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል ።

በጉብኝቱ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለማየሁ ባውዲን ጨምሮ ከፍተኛ የክልሉ ቢሮ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።

Photos from የወላይታ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት- Wolaita Prosperity Party office's post 25/12/2023

በወላይታ ዞን በሁሉም ወረዳና ከተማ አስተዳደር ለቀበሌ አመራር እና አባላት ሲሰጥ የነበረ የአቅም ግንባታ ሥልጠና የተለያዩ በጎ ተግባራት በመከናወን ተጠናቀቀ

ወላይታ ሶዶ፣ ታህሳስ 16/2016 በወላይታ ዞን በሁሉም ወረዳና ከተማ አስተዳደር ''ከዕዳ ወደ ምንዳ'' በሚል ርዕስ ለቀበሌ አመራር እና አባላት ለአራት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የነበረ የአቅም ግንባታ ሥልጠና ግቡን በማሳካት ተጠናቋል።

ስልጠናው በወረዳና ከተማ አስተዳደር ማዕከላት በየማህበራዊ መሠረት የተሰጠ ሲሆን ስልጠናው የአመራሩና አባሉ አቅምን ከመገንባት አንጻር ያበረከተው አስተዋጽኦ የጎላ መሆኑን ተገልጿል።

አቅም ግንባታ ስልጠናው በመንግስትና ፓርቲ የታቀዱ ዕቅዶች ለማሳለጥ ለአመራሩና አባሉ አቅም የሚፈጥር መሆኑንም ተመላክቷል።

ሰልጣኞቹ ከስልጠናው ጎን ለጎን የተለያዩ በጎ አገልግሎት ተግባራትን ያከናወኑ ሲሆን በየአካባቢው የተሰሩ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።

መጥፎ ትርክቶችን በማስወገድ የጋራ መግባባትን ለመፍጠር መንገድ ያሳዬ ስልጠና እንደሆነ የገለጹት ሰልጣኞቹ ችግሮችን ብቻ ትኩረት አድርገን ከምናይ ይልቅ ለችግሮቹ መፍተሄ እንዲናበጅ አመለካከታችንንና ዕይታችንን የቀየረ ስልጠና ነው ብለዋል።

ስልጠናው ከዚህ በፍት ከተሰጡት የተለየና የበለጸገች ኢትዮጵያን እውን ለማደረግ አቅማችንን ያሳደገ ስልጠና እንደነበረም ገልጸዋል፡፡

Photos from የወላይታ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት- Wolaita Prosperity Party office's post 25/12/2023

አመራሩና አባሉ በስልጠናው የቀሰመውን ዕውቀት ወደ ተግባር በማሸጋገር የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሌት ቀን መትጋት ያስፈልጋል፦ አቶ ሳሙኤል ፎላ

ወላይታ ሶዶ፣ ታህሳስ 15/2016 በወላይታ ዞን "ከዕዳ ወደ ምንዳ" በሚል ሀሳብ ለብልጽግና ፓርቲ አመራርና አባላት ለአራት ተከታታይ ቀናት ሲስጥ የቆየው አቅም ግንባታ ስልጠና ውጤታማነቱ ተገምግሟል።

የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ፎላ እንደገለፁት ስልጠናው ለአመራሩና አባሉ የአስተሳሰብ፣ የአመለካከትና የተግባር አንድነት የፈጠረ ነው ብለዋል።

ስልጠናው የተቀመጡ ግቦችን አሳክቷል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ሀገርን ወደ ተሻለ ምእራፍ ለማሸጋገር ለአመራሩና አባሉ አቅም የገነባ ስልጠና መሆኑንም ገልጸዋል።

አመራሩና አባሉ በስልጠናው ያገኘውን ዕውቀት በተጨባጭ ወደ ተግባር በመቀየር የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ መትጋት እንደሚገባም አሳስበዋል።

ሁልጊዜ ችግሮችን ብቻ ከማጉላት ይልቅ አዳዲስ የመፍትሄ ሀሳቦችን በማመንጨት ማህበረሰቡን የሚጠቅም ስራ በመስራት ላይ ማተኮር እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

ለአመራሩና አባሉ የተሰጠው ስልጠና የስኬቶችን እና የፈተናዎችን ምክንያትና ውጤት ተረድቶ ለአዳዲስ ስኬቶች የሚዘጋጅ እንዲሁም አዳዲስ ፈተናዎችንም በጽናት የሚመክት አመራርና አባል ለመፍጠር ያለመ መሆኑን አስምረውበታል፡፡

የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሳምነው አይዛ በበኩላቸው ሥልጠናው በሀገሪቱ የተጀመረውን የለውጥ፣ የዕድገትና የብልፅግና ጉዞ ለማሳካት አቅም የሚሆን አመራርና አባል እንዲፈጠር ዕገዛው የጎላ እንደነበረ ገልጸዋል።

አሁን ያለው ዓለም አቀፋዊና ሀገራዊ ነባራዊ ዐውዶችን አመራሩና አባሉ በተገቢው በመረዳት ምልዓተ ህዝብን በማሳተፍ ብልፅግና ፓርቲ አቅዶ የተነሳውን ራዕይን ወደ ግብ ለማድረስ ስልጠናው አቅም የፈጠረ መሆኑን አክለዋል።

በተለያዩ ሀሰተኛ ሚዲያዎች የሚሰራጩ ከፋፋይ አጀንዳዎችን በማረም በህዝቦች መሐል እንድነትን በሚፈጥርና ገዥ ትርክቶችን በመገንባት ሀገራችን አሁን ካለችበት መጠነ ሰፊ ችግር እንዲትወጣ አባሉ ከስልጠናው የጠራ ግንዛቤ እንዲይዝ ማስቻሉንም ጠቁመዋል።

በየአካባቢው ያሉ እምቅ ሀብቶችን በአግባቡ በመጠቀም፣ ሀብት በመፍጠርና በማስተዳደር የስራ አጥነትና የኑሮ ውድነት ችግሮቹን ለመቅረፍ አመራሩና አባሉ ሌት ቀን መትጋት እንደሚገባም ተመላክቷል።

ህዝቡ የሚፈልጋቸውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ አመራሩና አባሉ ውስጣዊ አንድነቱን በማጠናከር ለቀጣይ ሀገራዊ ተልእኮ በታላቅ ተነሳሽነት ለመውጣት አቅም የፈጠረ ስልጠና መሆኑ ከተሳታፊዎች ተነስቷል።

የብልጽግና ፓርቲ በምርጫ ወቅት የህዝብን ጥያቄ ለመመለስ ቃል በገባው መሠረት ብቁ አመራርና አባል በመገንባት በአመለካከትና በተግባር የጠራ እሳቤ ይዞ እንዲወጣ የሥልጠና ጽንሰ ሃሳብ በተግባር በየቦታ የተደረገው መስክ ምልከታ እጅግ ተስፋ ሰጪ እንደሆነና ለቀጣይ ቁጭት የፈጠረበት ሁኔታ መኖሩ በጥንካሬ ተነስቷል።

በመጨረሻ በየመድረኮች ለፓርቲው ግብአት የሚሆኑ ፣ መጥራት እና መስተካከል ያለባቸው፣የአመለካከት ዝንፈቶች እና ውጤታማነት ችግሮችን አመራሩ ገባ ብሎ በተገቢው በመገንዝብ ፈጣን ምላሽ እየሰጠ በተገቢው የመምራት ኃላፊነት መወጣት እንዳለበት አቅጣጫ ተቀምጧል።

በመድረኩ የዞኑ ፊት አመራሮችን ጨምሮ አጠቃላይ የዞን አመራሮች ተሳትፈዋል።

Photos from የወላይታ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት- Wolaita Prosperity Party office's post 25/12/2023

በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ቤንዚል በቁጥጥር ስር ማዋሉን የወላይታ ሶዶ ከተማ ፖሊስ አስታወቀ

ወላይታ ሶዶ፤ ታህሳስ 15/2016 በወላይታ ሶዶ ከተማ በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ቤንዚል በቁጥጥር ስር ማዋሉን የከተማው ፖሊስ አስታውቋል።

የከተማው ፓሊስ አዛዥ የሆኑት ዋና ኢንስፔክተር ተስፋዬ ምስጋናው እንደገለፁት መነሻውን ሀላባ አድርጎ ወደ ዳውሮ አካባቢ በመሄድ ላይ የነበረ 200 ሌትር እና 40 ሮቶ በመባል የሚታወቀው ነው የተያዘው።

ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ እና ፖሊስ ባደረገው ክትትል ከቀናት በፊት ከምሽቱ 9:00 ላይ ምንም አይነት ህጋዊ ማስረጃዎች የሌላውን እንዲሁም ተቀጣጣይ እና ለአደጋ በሚያጋልጥ መልኩ ሲንቀሳቀስ ቤንዚል መያዙን ዋና ኢንስፔክተር አስታውቀዋል።

የከተማው ፖሊስ አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ተስፋዬ ፖሊስ ያለማቋረጥ እና ያለመታከት ህግ ያስከብራል ሲሉ ተናግረዋል ቤንዚሉ ከተያዘ በኋላም የወንጀሉን ዳካ የማሳደዱ ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን አብራርተዋል።

ማህበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል ዘርፍ ሀላፊው ዋና ሳጅን አድማሱ ሱማኖ በበኩላቸው የታርጋ ቁጥር 03 አአ 23166 የሆነው ተሽከርካሪ እንዲቆም ቢጠየቅ ጥሶ በመሄዱ የወላይታ ሶዶ ከተማ ፓሊስ አባላት አሳደው እንደያዙት ገልፀዋል።

ዋና ሳጅን አድማሱ አክለውም ሁለት ተጠርጣሪዎች ተይዘው የምርመራ መዝገብ እየተጣራ መሆኑን ጠቁመዋል።

ፖሊስ እና ህብረተሰቡ በቋሚነት የሚሰሩ አጋሮች በመሆናቸው ለማንኛውም አጠራጣሪ ነገር በከተማ ፖሊስ የስልክ መስመር 0465510146 ጥቆማ መስጠት እንደሚቻል ጥሪ ቀርቧል በማለት የከተማው ህዝብ ግንኙነትና ማህበራዊ ሚዲያ ዘርፍ ዘግቧል።

25/12/2023

ለአመራሩና ለአባሉ የተሰጠው አቅም ግንባታ ስልጠና የተቀመጠውን ግቦች በማሳካት ተጠናቀቀ፦ አቶ አሳምነው አይዛ

ወላይታ ሶዶ፤ ታህሳስ 15/2016 በወላይታ ዞን ለብልፅግና ፓርቲ አባላትና አመራር እስከ ቀበሌ ድረስ ሲሰጥ የነበረ አቅም ግንባታ ስልጠና ግቡን በማሳካት መጠናቀቁን የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሳምነው አይዛ አስታወቁ።

በስልጠናው ከ633 ሺህ በላይ አባላት መሳተፋቸውን አቶ አሳምነው አስታውቀዋል።

"ከዕዳ ወደ ምንዳ" በሚል መሪ ሀሳብ የተሰጠው ስልጠና ፀጋዎችን በመጠቀም ለቀጣዩ ትውልድ ዕዳን ሳይሆን ምንዳን ለማስተላለፍ ለአመራሩና ለአባሉ አቅም የፈጠረ ነው ብለዋል።

የብልጽግና ዕሳቤን ከውስጥ ተቀብሎ የሚፈጽም ጠንካራ አመራርና አባልን ለመፍጠር ስልጠናው እጅግ አስፈላጊ እንደሆነም አስረድተዋል።

ፓርቲው ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋጥ በሚያደርገው ጥረት በተለይም የአባሉና አመራሩ የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት ወሳኝ መሆኑንም አስገንዝበዋል።

በየአካባቢው ያሉ እምቅ የተፈጥሮ ሀብት እና ሰፊ የመልማት አቅም በአግባቡ ስራ ላይ ማዋል አለብን ያሉት አቶ አሳምነው የተሻለች ኢትዮጵያን ለመፍጠር ሁሉም በተሰማራበት ሚናቸውን በብቃት ለመወጣት ዝግጁ መሆን እንደሚገባም አሳስበዋል።

የብልጽግና ፓርቲ ለህዝቡ የገባውን ቃል ለማስፈፀም የሚያስችል ለአመራርና አባሉ አቅም የመፍጠርና ዓላማን የሰነቀ ስልጠና መሆኑን ገልፀዋል።

መላው አመራርና አባል በተግባር የሚተገ፣ ውጤታማ፣ በአሉባልታዎች የማይናወጥ በጽኑ መሰረት እና በመርህ ላይ የቆመ ሊሆን እንደሚገባው አስገንዝበዋል።

ሁሉም አመራርና አባል በእውነት፣ በዕውቀትና በቅንነት ላይ የተመሰረተ ትግል በማድረግ ህብረብሔራዊ አንድነትና ብሔራዊነትን ማጽናት እንደሚገባም አመላክተዋል።

በአፍራሽ ሀሳቦች አማካኝነት የተፈጠሩ ብዥታዎችን ማጥራትና ከብልጽግና ጉዟችን ሳንደናቀፍ ፈተናዎችን በስኬት ለማለፍ የአመራሩና አባሉ አቅምን መገንባት ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ለሁለንተናዊ ብልጽግና እውን መሆን መሰረት በሆነው በሰላም ግንባታ ላይ መላው አመራርና አባል የየበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበርክት አቶ አሳምነው ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

በየአካባቢያችን ያሉ እምቅ ሃብቶችን በአግባቡ በመለየትና በመረዳት ጥቅም ላይ ማዋል ከቻልን የምንመኘውን ሁለንተናዊ ብልፅግናን እውን ማድረግ እንችላለን ብለዋል።

በስልጠናው ጎን ለጎን የስልጠና ተሳታፊዎች የተለያዩ በጎ ተግባራቸውን ማከናወናቸውን በማመስገን ስልጠናው በስኬት እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

አመራሩና አባሉ በስልጠናው የቀሰሙት ዕውቀትን ወደ ተግባር በመቀየር እና ከመስክ ምልከታው ያገኙትን ልምድ እና ተሞክሮ በማስፋት የህዝባችን ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ መትጋት እንዳለባቸው ጥሪ አቅርበዋል።

Photos from የወላይታ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት- Wolaita Prosperity Party office's post 25/12/2023

ሥልጠናው ያጠናቀቁ የዞን ማዕከል ብልጽግና ፓርቲ አባል መንግስት ሰራተኞች በዞኑ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጎበኙ

ወላይታ ሶዶ፤ ታህሳስ 15/2016 "ከዕዳ ወደ ምንዳ" በሚል ርዕስ ሥልጠናው ያጠናቀቁ የወላይታ ዞን ማዕከል ብልጽግና ፓርቲ አባል መንግስት ሰራተኞች በዞኑ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።

ጉብኝቱ ሰልጣኞቹ በንድፈ ሀሳብ ያገኙት ዕውቀት ጋር በማስተሳሰር ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየር ጥሩ ተሞክሮና ልምድ የሚቀስሙበት ነው።

አካባቢያችን ብሎም ሀገሪቱ ለወደፊት ምን ተስፋ አለው፤ በንግግር የሚገለጽ ተስፋ ነው ወይስ በተጨባጭ የሚታይ ነው የሚለውን በደምብ ማየት እንዲችሉ የመስክ ጉብኝቱ የስልጠና አንድ አካል መሆኑን ተገልጿል።

ሰልጣኞቹ ስልጠናው ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ገልጸው በጉብኝታቸውም እምቅ ሃብቶች መጠቀምና በአግባቡ የማስተዳደር ሂደቶችን መገንዘባቸውንም ገልጸዋል።

በዞኑ ለህዝባችን ተስፋ የሚጫሩ በርካታ የልማት መኖራቸውን መመልከታቸውን ጠቅሰው ሀብት መፍጠርና ብልፅግና ለማረጋገጥ አባሉን ጨምሮ የህዝቡ ትብብርና የጋራ ልማት ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።

"ከዕዳ ወደ ምንዳ" በሚል መሪ ሀሳብ የወሰድነው ስልጠና ፀጋዎችን በመጠቀም ለቀጣዩ ትውልድ ዕዳን ሳይሆን ምንዳን ለማስተላለፍ አመራሩና አባሉ ሌት ተቀን መስራት እንዳለበት የጋራ አቋም የወሰድንበት ነው ያሉት።

ሰልጣኞቹ በሶዶ ዙሪያ ወረዳ የሚገኝ ግቤ-3 ሀይል ማስተላለፊያ ማዕከል፣ የማር መንደር፣ በሶዶ ከተማ የሚገኝ የዳቦና ዱቄት ማቀነባበሪያ ፋብሪካ፣ በአርሶ አደሮች እየለማ የሚገኘውን የተለያዩ የግብርና ስራዎችን፣ በመንግስት እና በህዝብ ተሳትፎ የተሰሩና እየተሰሩ ያሉ መሠረተ-ልማቶች እና በግል ባለሀብቶች የለሙ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ተዘዋውረው ተመልክቶዋል።

በጉብኝቱ የዞን ማዕከል ከፍተኛ አመራሮች፣ የመምሪያውና ጽ/ቤት ብልጽግና ፓርቲ አባል የመንግስት ሰራተኞች ተሳትፈዋል።

Photos from የወላይታ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት- Wolaita Prosperity Party office's post 25/12/2023

9ኛዉ የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ሶዶ ከተማ ለማዘጋጀት ሥራው መጀመሩን ተገለጸ

ወላይታ ሶዶ፤ ታህሳስ 15/2016 9ኛው ሀገር አቀፍ የኢትዮጵያ የከተሞች ፎረም ከከተማና መሰረተ ልማት ሚንስቴር ጋር በጋራ በመሆን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በወላይታ ሶዶ ከተማ ለሚዘጋጀው የአዘጋጅ ኮሚቴ ሥራዎች የደረሱበትን ደረጃ የክልሉ ርዕሰ መስተደድርና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ባሉበት አብይ ኮሚቴው የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በጋራ ገምግመዋል።

የህብረተሰቡን ትጋትና የማልማት አቅምን ተጠቅመን ክልላችን ለማስተዋወቅ ጠንክረን እየሰራን እንገኛለን ሲሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ጥላሁን ከበደ ገልፀዋል።

የክልሉ ርዕሰ መስተደድር አቶ ጥላሁን ከበደ እንዳሉት ክልሉ አዲስ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የህብረተሰቡን የልማት ተነሳሽነትና ተሳታፊነት በመጠቀም ጠንካራ ስራ ሰርተን በ9ኛው የከተሞች ፎረም ክልላችንን ለማስተዋወቅ በተሻለ ሁኔታ እየሰራን እንገኛለን ብለዋል።

ይህ የከተሞች ፎረም የክልሉን አቅም ለማሳየትና የህዝባችን ጥንካሬ ለመግለጽ ትልቅ ዕድል ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ይህን የተሳካ ለማድረግ አቢይ ኮሚቴ ተቋቁሞ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ገልጸዉ ሥራው የደረሰበትን ደረጃ በጋራ ለመገምገም መድረኩ መዘጋጀቱን ጠቅሰዋል።

ክልሉ ሰፊ ባህልና ቱሪዝም ያለው በመሆኑ ይህን ዕምቅ ጸጋ ለማስተዋወቅና እንግዶችን ለመቀበል መዘጋጀት አለብን ብለዋል።

የክልሉ ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ በበኩላቸው 9ኛውን የከተሞች ፎረም ለማስተናገድ ኮሚቴ ተዘጋጅቶ ሰፊ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ጠቅሰው የመሰረተ ልማትና የጸጥታ ሥራዎች ለአብነት የሚጠቀሱ መሆኑን ገልጸዋል።

Photos from የወላይታ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት- Wolaita Prosperity Party office's post 25/12/2023

ለዞን ማዕከል ብልጽግና ፓርቲ አባል መንግስት ሰራተኞች ሲሰጥ የነበረው የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቀቀ

ወላይታ ሶዶ፣ ታህሳስ 15/2016 በወላይታ ዞን ለዞን ማዕከል "ከዕዳ ወደ ምንዳ" በሚል ሀሳብ ለብልጽግና ፓርቲ አባል የመንግስት ሰራተኞች ለአራት ተከታታይ ቀናት ሲስጥ የቆየው አቅም ግንባታ ስልጠና ግቡን በማሳካት ተጠናቀቀ።

ስልጠናው ትኩረት ያደረገባቸው ሀብትና ብልጽግናን መፍጠርና ማስተዳደር፣ገዥ ትርክትና ግንባታ፣ አገልጋይና ስልጡን ፐብልክ ሰርቪስ እና የሠላም ባህል ግንባታ ላይ ነው።

ስልጠናው ለአባል መንግስት ሠራተኞች የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት የፈጠረ ሲሆን ወንድማማችነት እና እህትማማችነት በማጎልበት ሀገራዊ ራዕይ ከግብ ለማድረስ ብቁ አባል መፍጠር ላይ ያተኮረ ነው።

አባሉ በስልጠናው ያገኘውን ዕውቀት በተጨባጭ ወደ ተግባር በመቀየር የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ መትጋት እንደሚያስፈልግም ተመላክቷል።

ስልጠናው በሀገሪቱ የተጀመረውን የለውጥ፣ የዕድገትና የብልፅግና ጉዞ ለማሳካት አቅም የሚሆን አባል እንዲፈጥር ዕገዛው የጎላ መሆኑ ተገልጿል።

አሁን ያለው ዓለም አቀፋዊና ሀገራዊ ነባራዊ ዐውዶችን አባሉ በተገቢው በመረዳት ምልዓተ ህዝብን በማሳተፍ ብልፅግና ፓርቲ አቅዶ የተነሳውን ራዕይን ወደ ግብ ለማድረስ ስልጠናው አስፈላጊ መሆኑ ተገልጿል።

በተለያዩ ሀሰተኛ ሚዲያዎች የሚሰራጩ ከፋፋይ አጀንዳዎችን በማረም በህዝቦች መሐል እንድነትን በሚፈጥርና ገዥ ትርክቶችን በመገንባት ሀገራችን አሁን ካለችበት መጠነ ሰፊ ችግር እንዲትወጣ አባሉ ከስልጠናው የጠራ ግንዛቤ እንዲይዝ ማስቻሉንም ተጠቁሟል።

በየአካባቢው ያሉ እምቅ ሀብቶችን በአግባቡ በመጠቀም፣ ሀብት በመፍጠርና በማስተዳደር የስራ አጥነትና የኑሮ ውድነት ችግር መቅረፍ እንደሚገባም ተመላክቷል።

ህዝቡ የሚፈልጋቸውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ አባሉ ውስጣዊ አንድነቱን በማጠናከር ለቀጣይ ሀገራዊ ተልእኮ በታላቅ ተነሳሽነት ለመውጣት አቅም የፈጠረ ስልጠና መሆኑም ተብራርቷል።

ፓርቲው በምርጫ ወቅት የህዝብን ጥያቄ ለመመለስ ቃል በገባው መሠረት ብቁ አባል ለመገንባትና አመራሩም በአመለካከትና በተግባር የጠራ እሳቤ ይዞ እንዲወጣ ተደርጓል።

Photos from የወላይታ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት- Wolaita Prosperity Party office's post 25/12/2023

በወላይታ ዞን ዳሞት ወይዴ ወረዳ በበዴሳ ከተማ " ሻሎቴ አጠቃላይ የንግድና ምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ የግንባታ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ተካሄደ

ወላይታ ሶዶ፣ ታህሳስ 15/2016 ዓ/ም በዳሞት ወይዴ ወረዳ በበዴሳ ከተማ " ሻሎቴ አጠቃላይ የንግድና ምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ " የግንባታ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር በዛሬው እለት ተካሂዷል።

ፋብሪካው ስጠናቀቅ "ከ200 በላይ ሥራ አጦች በቋሚና በጊዚያዊ ሥራ ዕድል እንደሚፈጥር ተገልጿል ።

በይፋ የግንባታ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ላይ የተገኙት የዳሞት ወይዴ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላላንዳ ዶዳ እንደገለጹት የሻሎቴ አጠቃላይ የንግድና ምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ባለቤት አቶ ታንቱ ሻንካ በዛሬው እለት የፋብሪካ ግንባታ ሥራ በማስጀመር ወደ ግንባታ በመግባቱ በማመስገን ይህ ኘሮጀክት በስኬት እስክጠናቀቅ ድርስ የወረዳው መንግስት አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልፀዋል ።

ዳሞት ወይዴ ወረዳ ለኢንቨስትመንት አመቺ ከመሆኑም አልፎ በጥራት ተወዳዳሪ የሌለውና ያለ ምንም ወጪ በስበት ኃይል የሚፈስ የንፁህ መጠጥ ውሃ ባለቤት በመሆኗ ወደ ወረዳዋ ባለሀብቶች በመምጣት በተለያዩ ሥራ ዘርፎች ኢንቨስት እንዲያደርጉ አቶ ላላንዳ ጥሪ አስተላልፏል ።

የሻሎቴ አጠቃላይ የንግድና ምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ባለቤት አቶ ታንቱ ሻንካ በበኩላቸው የፋብሪካው ግንባታ በ1 ዓመት ውስጥ ተገንብቶ በማለቅ በቋምነት 50 እና በጊዜያዊነት 150 ሥራ አጦችን በመቅጠር የሥራ እድል የሚፈጥር መሆኑን በመጠቆም ፈብረካው የዱቄት ፣ የሞኮሮኒ እና የፖስታ ምርቶችን በማምረት አገልግሎት የሚስጥ መሆኑንም ጭምር ገልፀዋል ።

ለፋብሪካው የሚያስፈልጉ አጠቃላይ መሠረት ልማት ለማሟላት የወረዳው መንግስት አሰፈላጊ ድጋፍ እንዲያደርግ አቶ ታንቱ በመጠየቅ ወረዳዋ ብዙ እምቅ ሀብትና ለኢንቨስትመንት ምቹ በመሆኗዋ ባለሀብቶች መጥተው ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ አስተላልፏል ።

የግንባታ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ላይ የዳሞት ወይዴ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላላንዳ ዶዳ ፣ የወረዳው የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ መብራቱ ሕዝቅኤልና የፊት አመራሮች ፣ የሻሎቴ አጠቃላይ የንግድና ምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ባለቤት አቶ ታንቱ ሻንካ ፣ የበዴሳ ማዘጋጃ ሥራ አስኪያጅ አቶ ኤፍሬም ተክሌ ፣ የሀይማኖት መሪዎች ፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ተጋባዥ እንግዶች መገኘታቸው የወረዳው ህዝብ ግንኙነትና ማህበራዊ ሚዲያ ዘርፍ ዘግቧል ።

25/12/2023

ብልጸግና አሰባሳቢ ትርክትን በመቅረፅ የበለጸገች ኢትዮጵያ ይገነባል!

ሀገራችን ኢትዮጵያ የአሁኑንና የመጪውን ትውልድ ጥቅምና ፍላጎት የሚያስከብር አስተማማኝ መሰረት ዛሬ ላይ ለመገንባት ሰላም፣ ዴሞክራሲ፣ ኅብረ ብሔራዊ አንድነት፣ የዜጎች ክብር፣ ፍትሕ እና የጋራ ብልጽግና የተረጋገጠባት ሀገር መሆን ይኖርባታል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ የጥንታዊ ስልጣኔና የቀደመ ሀገረ-መንግስት ባለቤት ብትሆንም አሰባሳቢ የሆነ ሀገራዊ ትርክት መገንባት ባለመቻሏ ትርክቶቿ በስርዓታት ፖለቲካ ፍላጎት ላይ ብቻ የተንጠለጠሉ ሆነው በመቆየታቸው ስርዓታት በወጡ እና በወረዱ ቁጥር የሚገለባበጡ ነጠላ ትርክቶች ገዥ እየሆኑባት የሀገረ-መንግስት ግንባታ ተግባሯን ያለ ተቃርኖ ለማስቀጠል አልታደለችም። በአንፃሩ የአሜሪካን፣ የቻይናን የፈረንሳይን ሀገራዊ ገዥ ትርክቶች የሚነግሩን ስርዓቶች ቢቀያየሩም ገዥ ሀገራዊ ትርክታቸው መሰረቱ ሀገረ-መንግስቱ ላይ በመገንባቱ በየወቅቱ የሚነሱ ፖለቲካዊ ፍላጎቶች አይለዋወጥም።

ሀገራት ህዝባቸውን ከየት እንደተነሱና ወዴት እንደሚደርሱ በአሰባሳቢ ገዥ ትርክት በመገንባት ከአስተዳደራዊ ወሰናቸው አልፈው በዓለም ላይ የበላይነታቸውን ቅቡልነት አረጋግጠዋል።

የዓለማችን ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች የሚዘውሩት የትርክት የበላይነት በያዙ ሀገራት እና ተቋማት ፍላጎት ነው። እነዚህ ሀገራትም ይሁኑ ተቋማት የትርክታቸውን የበላይነት ለማስጠበቅ ሁሉንም ዓይነት ሀይል የማስጠበቂያ አማራጮችን ይጠቀማሉ።

ትርክት ቻይናን ከወደቀችበት አንስቶ የዓለም ተፆዕኖ ፈጣሪ ሀገር አድርጎ ከፊት አስቀምጧታል። ትርክት ሶሪያ ከዓለም ቀደምት ሀገርነት ወደ ፍርስራሽነት ቀይሩታል። ትርክት ኢትዮጵያን ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲነገር የሚኖረውን በቅኝ-ገዥዎች ቅኝ ያለመገዛት ታሪክ እንዲትሰራ አስችሏታል።

ትርክት በህዝብ ውስጥ ለጋራ ዓላማና ራዕይ በአብሮነት በማነሳሳትን በአርበኝነት እንዲፈፅሙ የሚያንቀሳቅስ ታላቅ ሀይል መሆኑን በመረዳት ብልጽግና ፓርቲ በተራራቀ ዋልታ የሚገኙትን የሀገራችን ትርክቶች ወደ አሰባሳቢ ገዥ ትርክት ለማምጣት በህብረ-ብሄራዊ አንድነትና ወንድማማችነት ላይ የተመሰረት ብሄራዊ አርበኝነት የሀገራችን ገዥ ትርክት እንዲሆን እየሰራ ይገኛል።

ብልፅግና በህብረ-ብሄራዊ አንድነትና ወንድማማችነት ላይ የተመሰረተው ብሄራዊ አርበኝነት የሀገራችንን ያልፈውን የጉዞ ምዕራፍ ፣ የዛሬን ነባራዊ ሁኔታ እና የነገን መዳራሻ የምንመለከትበት የጋር አሰባሳቢ ሀገራዊ ፕሮጀክት ነው ብሎ ያምናል።

በህብረ-ብሄራዊ አንድነትና ወንድማማችነት ላይ የተመሰረተው ብሄራዊ አርበኝነት ገዥ ትርክት የትላንቱን ኢትዮጵያ ህዝቦች ታሪክ መሰረት አድርጎ የዛሬውን አስተሳስሮ ነገን ማመልከት የሚችል የህዝባችንን ዋና ዋና የጋራ እሴቶችን፣ ፍላጎቶችንና ግቦችን የሚያሳካና የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን ያደርጋል።

ፓርቲያችን ህዝባችን የጋራ ታሪክ ያለው፣ ብዙ ትላንቶችን በጋራ የተሻገረ አሁን ስንቅ ልናደርጋቸው የሚገቡ አያሌ ታሪኮችን እንዳሉት ያምናል።

በዚሁ አግባብ ብልፅግና በገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገር እና ገበታ ለትውልድ አማካይነት ነባር የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት፣ ታሪካዊ እሴቶችን አውጥቶ በማበልፅግ እና በማህበራዊ ካፒታላችንን በመጠቀምና በእነዚህ ላይ እሴቶችን በመጨመር ለነገ ብልጽግናችን በሚሆን መንገድ ማልማት በሰፊው ቀጥሏል።

ከትላንት የተሻለ ሀገራችንንና ህዝቡቿን የሚጠቅም ታሪክ እንድሰራ፣ የትውልዶችን ድካም በማረም ለትወልድ የበለፅገች ሀገር ለማስረከብ እንትጋ። ስለዚህ ትርክታችን ያለፈውን ብቻ ሳይሆን የዛሬን ዕድል እና የገነን ተስፋ ታሳቢ ያደረገ መሆን አለበት።

መልካም የስራ ሳምንት ይሁንልዎ!!

24/12/2023

የገበታ ለሀገር - የጨበራ የዝሆን ዳና ሎጅ

Photos from የወላይታ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት- Wolaita Prosperity Party office's post 24/12/2023

ዛሬ በወላይታ ዞን በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ በጢዮ ሄምቤቾ ቀበሌ በበጋ መስኖ እየለማ ያለውን የስንዴ ማሣ ጎብኝተናል:: በየአከባቢያችን ያለውን እምቅ ፀጋ ለይተንና አቅደን ከህዝባችን ጋር ተባብረን ከሠራን ተጨባጭ ውጤት ማምጣት እንደሚቻል በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ተመልክተናል። ከህዝባችን ጋር ተባብረንና በርትተን ከሰራን የምንመኘውን ብልፅግናን እውን እናደርጋለን።

የተከበሩ አቶ ሳሙኤል ፎላ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ

24/12/2023

ሚዲያን ለጥላቻ፣ ለብሽሽቅና ለከፋፋይ አጀንዳ ከመጠቀም ይልቅ ለህዝቦች አብሮነትና ወንድማማችነት እንድሁም ለጋራ ሰላምና ዕድገት ብንጠቀም ትርፉ ሰላም፣ ፍቅር፣ መቻቻልንና አብሮ መበልፀግን ይጨምርልናል እንጂ ክፋት የለውም።

አቶ አሳምነው አይዛ
የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ

Photos from የወላይታ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት- Wolaita Prosperity Party office's post 24/12/2023

የወላይታ ዞን ከፍተኛ አመራሮች በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ በበጋ መስኖ እየለማ ያለዉ ስንዴ መስክ ምልከታ አደረጉ

ወላይታ ሶዶ፤ ታህሳስ 14/2016 የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ፎላ የተመራ ልዑክ በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ በበጋ መስኖ እየለማ ያለው ስንዴ መስክ ምልከታ አድርገዋል።

የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ፎላ በመስክ ምልከታው እንደገለጹት በዓመት ሶስት ጊዜ ምርት የሚሰጡ ሰብሎችን ለማምረት በሚደረገው ሂደት ውስጥ የአርሶአደሩ ሚና የጎላ እንደሆነም ተናግረዋል።

በአካባቢያችን የሚገኙ የተፈጥሮ ሀብቶችን በተገቢው በመጠቀም የሰብል ምርቶች ለማስፋፋት እንተጋለን ሲሉም ዋና አስተዳዳሪው ተናግረዋል።

የበጋ መስኖ ስንዴ ለማምረት በሚደረገው ጥረት ውስጥ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በመቅረፍ ለላቀ ውጤት እንረባረባለን ብለዋል አቶ ሳሙኤል ።

የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሳምነው አይዛ በበኩላቸው የምንመኘውን ብልጽግናችን ለማረጋገጥ የበጋ መስኖ ስንዴ ምርት ከፍ ማድረግ ከዕቅዱ ዋና ተጠቃሽ እንደሆነ አብራርተዋል።

አያይዘውም ብልጽግና ከመናገር ባለፈ በተግባር የሚያረጋግጥ እንደሆነ የበጋ መስኖ ስንዴ ማሣያ ነው ብለዋል አቶ አሳምነዉ።

የአከባቢው አርሶአደሮች የበጋ መስኖ ስንዴ ለማምረት ያካሄዱት መነቃቃት ተስፋ ሰጪ መሆኑን የወላይታን ዞን የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ አቶ ተመዝገን አልማየሁ ተናግረዋል።

ከሌሎች ግብርና ምርቶች ይልቅ የበጋ መስኖ ስንዴ ማምረት ምግብ ዋስትናችንን ለማረጋገጥ ሁነኛ መፍትሄ እንደሆነ አቶ ተመዝገን አስረድተዋል።

የዞኑ ም/አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን ዳዊት በማህበር የተደራጁ ወጣቶች የበጋ መስኖ ስንዴ እያለሙ መሆኑ እጅግ እንዳስደሰታቸው ገልጸው ለሥራ ተግዳሮት የሚሆኑ ማንኛውም ችግር ለመፍታት የዞኑ መንግሥት ዝግጁ እንደሆነም ተናግረዋል።

በግብርናው ዘርፍ ትኩረት ተደርጎ ከተሰራ በቅርቡ ብልጽግናን ማረጋገጥ እንደሚቻል የጠቆሙት አቶ መስፍን ለስራ አጥ ወጣቶች የስራ ዕድል መፍጠሪያ እንደሆነም አስገንዝበዋል።

በወረዳ ደረጃ የበጋ መስኖ ስንዴ ምርት ለመሰብሰብ የተያዘው ዕቅድ ከግብ እንዲደርስ አመራሩ ፣የግብርናው ዘርፍ ባለሙያዎች እና አርሶአደሮች በቁርጠኝነት ልሰሩ ይገባል ብለዋል የቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ዋና አስተዳደር አቶ አያኑ ቢረጋ።

የዘገባው የቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የህዝብ ግኑኝነትና ማህበራዊ ሚዲያ ዘርፍ ነው

24/12/2023

ብልጽግና ፓርቲ የሀገሪቱን አቅሞች በመጠቀም ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ የጀመረውን ውጤታማ የአመራርነት ሚና አጠናክሮ ይቀጥላል - አቶ አደም ፋራህ

ብልጽግና ፓርቲ የሀገሪቱን አቅሞች በመጠቀም ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ የጀመረውን ውጤታማ የአመራርነት ሚና አጠናክሮ እንደሚቀጥል የፓርቲው ምክትል ፕሬዝዳንትና የዋና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የገበታ ለሀገር ኮይሻ ፕሮጀክት አካል የሆነውን የጨበራ የዝሆን ዳና ሎጅ ትላንተ መርቀው ከፍተዋል።

በምረቃ መርኃ ግብሩ ላይ የተገኙት የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንትና የዋና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ፤ ኢትዮጵያ ብዙ አቅም ቢኖራትም ወደ ልማት መለወጥ ላይ ውስንነቶች መኖራቸውን ተናግረዋል።

ለዚህም በየአከባቢው ያሉ አቅሞችን በአግባቡ አይቶ፣ አቅሞችን ወደ ተጨባጭ ኃብት በመቀየር የሕዝብን ተጠቃሚነት ከማረጋግጥ አኳያ የአመራር ውስንነት ዋነኛው ምክንያት መሆኑን አንስተዋል።

በተለይም የመሪዎች የኃሳብ አመንጪነት እንዲሁም የማስፈጸም አቅም አናሳ እንደነበር ጠቅሰዋል።

በሌላ በኩል በመሠረታዊ ጉዳዮች ላይ መግባባት አለመፈጠሩን ተከትሎ በሚነሱ ግጭቶች የሚመጣ የፖለቲካ አለመረጋጋት ጸጋዎችን ለመጠቀም አዳጋች እንደነበር አንስተዋል።

የብልጽግና ፓርቲም በሀገሪቱ በተለያዩ ሥፍራዎች ያሉ አቅሞችን አሟጦ ለመጠቀም አመራሩ ሚናውን እንዲወጣ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ውጤታማ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።

ከዚህ አንጻር በተለይም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኃሳብ አመንጪነት ትላንት የተመረቀው የጨበራ የዝሆን ዳና ሎጅ ጨምሮ ሌሎች የልማት ሥራዎች ተጠቃሽ መሆናቸውን ነው የገለጹት።

ጎን ለጎንም በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ለማምጣትና ሀገሪቱ ያሏትን እምቅ አቅሞች እንድትጠቀም በተለይም በሀገራዊ ምክክሩ አማካኝነት ልዩነቶች እንዲፈቱ ያላሰለሰ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።

በኢትዮጵያ እየተተገበሩ ያሉ ፕሮጀክቶች የኃሳብ ኃይል ምን ያክል ወሳኝ እንደሆነ ትምህርት የሚወሰድባቸው መሆናቸውን ገልጸዋል።

በተለይም የተፈጥሮ ጸጋዎችን ለሀገሪቱ የብልጽግና ጉዞ እንዴት መጠቀም እንደሚገባ ትልቅ ማሳያዎች መሆናቸውን ጠቁመዋል።

በሌላ በኩል ፕሮጀክቶችን በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ እንዲሁም በከፍተኛ የጥራት ደረጃ እንዴት ማጠናቀቅ እንደሚቻል የፕሮጀክት አመራር ጥበብን የተማርንባቸው ናቸው ሲሉም ተናግረዋል።

እነዚህ ፕሮጀክቶች በሕዝብ ተሳትፎ የተገነቡ መሆናቸውን ጠቅሰው በቀጣይም ሕዝቡን በሁሉም ደረጃ በማሳተፍ የሕዝቡን ተጠቃሚነትና የሀገሪቱን ብልጽግና ለማረጋገጥ የታያዙ ውጥኖች እውን እንዲሆኑ ይሰራል ብለዋል።

በመሆኑም በቀጣይም የብልጽግና ፓርቲ የአገሪቱን አቅሞች በመጠቀም ሀገሪቱን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ የጀመራቸውን ውጤታማ የአመራርነት ሚና አጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው ያረጋገጡት።(ኢዜአ)

Photos from የወላይታ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት- Wolaita Prosperity Party office's post 24/12/2023

ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች የኮይሻ የሃይል ማመንጫ ፕሮጀክትን ጎበኙ።

የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንትና የጽ/ቤቱ ኃለፊ አቶ አደም ፋራህ፣የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈጉባኤ ፣ የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈጉባኤ ፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች እና ሚኒስትሮች የኮይሻ የሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ግንባታ ሥራን ጎብኝተዋል።

በአፍሪካ ደረጃ በግዙፍነቱ ሶስተኛ ደረጃ የሆነዉን የኮይሻ ግድብ የንፁህ የኃይል ማመንጨት ስራችንን ያለበት ደረጃ አበረታች መሆኑን አመራሮቹ በምልከታቸዉ አይተዋል።

በጨበራ ጩርጩራ ብሔራዊ ፓርክ በቅርብ ርቀት የሚገኘዉ የኮይሻ ግድብ ለሀገራችን ተጨማሪ የኢኮኖሚ አቅምና የመልማት ዕድል የሚፈጥር ነዉ።

በግንባታ ሂደትም ለበርካቶች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል እየፈጠረ ይገኛል::

24/12/2023

ብልጽግና ሀገራችን አምቃ የያዘችውን ሀብት ለብልፅግናዋ ስኬት እንዲሆን አበክሮ እየሰራ ያለ ፓርቲ!

በኢኮኖሚው ረገድ ሀብት ያፈራች ሀገር መገንባት ካልቻልን ሀገራዊ ክብር ሊኖር አይችልም። ለስንዴ ልመና እጅ የሚዘረጋ ሀገር ሀገራዊ ክብሩን ማስጠበቅ ይሳነዋል። ኢኮኖሚ የሁሉ ነገር መሠረት ነው። የሀገር ክብርን ለማስጠበቅ የዳበረ ኢኮኖሚን እውን ማድረግ ያስፈልጋል።

ፓርቲያችን ብልፅግና የብዝሃ ዘርፍ ኢኮኖሚ ልማት ማዕከል አድርጎ፣ ለሀገራችን መልማት አስተዋፅኦ ያላቸውን ዘርፎች በሙሉ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት በርካታ ውጤት እያመጣ ነው። ኢኮኖሚው በብዝሃ ዘርፍ ብቻ ሳይሆን ብዝሃ ተዋንያንም ያስፈልገዋል። በሁሉም የልማት አቅሞች ተመጣጣኝ የኢኮኖሚ እድገት ሲመጣ የብዝሃ ተጠቃሚነትን እውን በማድረግ ህዝባችንን ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚቻል ማሳያ ውጤት እመጣ ይገኛል።

ኢትዮጵያ ሁሉም የመልማት አቅሞች ያሏት ሀገር መሆኗን ፓርቲያችን ብልፅግና በተግባር እያረጋገጠ ይገኛል። በአፋር፣ በሶማሌ ከአርብቶ አደርነት ወጣ ብሎ በማየት በመስኖ ስንዴ ምርት ውጤት ማምጣት እንደሚቻል በተግባር አረጋግጧል። ግብርናው ላይ በርካታ ያልተነኩ አቅሞች ቢኖሩም በጅምር ስራችን አመርቂ ውጤት መጥቷል። በጅማ የተጀመረው የሩዝ ምርት አይናችንን መግለጥ ስንችል ያለን አቅም ትልቅ መሆኑን እንረዳለን። ፓርቲያችን ይህንኑ ገለጥ አድርጎ የማየት ብቃት እያሳየ ውጤት እያመጣ ነው።

በማዕድን ዘርፉ ኢትዮጵያ በርካታ ያልተነኩ አቅሞች እንዳሏት በማሳየት ኢኮኖሚውን አንድ ደረጃ ወደ ፊት ማራመድ አስችሏል። ኢትዮጵያ ኤምራልድ፣ ኦፓል፣ ሩቢ፣ ሳፋየር፣ ፖታሽ፣ የድንጋይ ከሰል፣ ወርቅ፣ ታንታለም፣ ማርብል፣ ፕላትኔም፣ ነዳጅ እና ሌሎችንም ማዕድናት አምቃ ይዛለች። ፓርቲያችን ሀገራችን አምቃ የያዘችውን ሀብት ለብልፅግናዋ ስኬት እንዲሆን አበክሮ እየሰራበት ነው።

በቱሪዝም ዘርፍ አቅሙ እያለን ሳንጠቀም ለዘመናት ቆይተናል። ፓርቲያችን ብልፅግና ያሉንን ጥንታዊ ታሪካዊ የቱሪዝም መዳረሻ በመጠበቅ በማስተዋወቅና አገልግሎት አሰጣጡን በማዘመን የሚያስገኙት ገቢ ከፍ እንድል እየሰራ ነው። ፓርቲያችን ያሉንን የቱሪስት መዳረሻዎች ከመጠበቅ፣ ከመንከባከብ ባለፈ አዳዲስ ውብ መዳረሻዎችን በመገንባት ከውጭም ከውስጥም ያሉ ጎብኝዎችን አዲስ መዳረሻ እንዲኖራቸው እየሰራ ነው። በገበታ ለሸገር የተገነቡት ውብ መዳረሻዎች ወንድማማችነት፣ አንድነት፣ ሸገር፣ እንጦጦ ፓርኮች ተጠቃሽ ናቸው። በገበታ ለሀገር ወንጪ፣ ኮይሻ፣ ጎርጎራ ታይተው የማይጠገቡ መዳረሻ ሆነዋል። ሃላላ ኬላ የሁሉንም ቀልብ በመሳብ ኢትዮጵያ ከጥንት እስከዛሬ የሚታይ የሚነገር፣ የሚዳሰስ፣ ታይቶ የማይጠገብ የቱሪስት መስህብ እንዲትሆን እየሰራን መሆናችን ማሳያ ነው።

በአይሲቲው ዘርፍ በአዲስ እይታ የኢኮኖሚው ደጋፊ እንዲሆን በመስራት ውጤት ማምጣት አስችሏል። ይህ ተግባር ፓርቲያችን ብልፅግና ዛሬን ብቻ ሳይሆን ነገን ቀድሞ የሚያይ የነገው ትውልድ ፓርቲ መሆኑን የሚያሳይ ነው። የአካባቢ ጥበቃ እና ዘላቂ አረንጓዴ ልማት እውን በማድረግ ኢኮኖሚያዊ እድገታችን ለሰው ልጅ ብቻ ሳይሆን ለፍጡራን ሁሉ ከጎንዮሽ ጉዳት የፀዳ ተስማሚ አድርጎ የሚሰራ ፓርቲ ነው።

እነዚህ እና ሌሎች አቅሞችን በመጠቀም ሁላችንም የተሰጠንን ኃላፊነት በብቃት በመወጣት የበለፀገች፣ ክብሯ የተጠበቀ፣ የከፍታ ማማ ላይ ያለች ኢትዮጵያን እውን እናድርግ።

ሀገራዊ ክብርን ያስጠበቀ ኢትዮጵያን በአለም አደባባይ ከፍ የሚያደርግ ስራ መስራት የአሁኑ ትውልድ ኃላፊነት ነው።

23/12/2023

የማየት ብልጽግና ፣የመሥራት ብልጽግና ፣የመጠበቅ ብልጽግና በኮንታ ዞን።

Photos from የወላይታ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት- Wolaita Prosperity Party office's post 23/12/2023

በባይራ ኮይሻ ወረዳ ለትምህርት አመራሮችና አባላት የሚሰጥ የአቅም ግንባታ ስልጠና ቅድመ ዝግጅት ዙሪያ ውይይት ተደረገ

ወላይታ ሶዶ፣ ታህሳስ 13/2016 ዓ ም በወላይታ ዞን ባይራ ኮይሻ ወረዳ "ከዕዳ ወደ ምንዳ" በሚል ርዕስ ለትምህርት አመራሮችና አባላት የሚሰጥ የአቅም ግንባታ ስልጠና ቅድመ ዝግጅት ዙሪያ ከር/መምህራንና ሱፔርቫይዜሮች ጋር የውይይት መድረክ ተካሂዷል።

እንደ ሀገር ወጥ በሆነ መንገድ ለአመራሮችና ለአባላት እየተሰጠ የሚገኘው "ከዕዳ ወደ ምንዳ" የአቅም ግንባታ ስልጠና በመላው ዜጎች ዘንድ ተመሳሳይ አረዳድና ሀገራዊ መግባባትን ለመፍጠር የላቀ ሚና እንዳለው ይታወቃል።

ስልጠናው በዚህ ዙር ለትምህርት አመራሮችና አባላት የሚሰጥ ስሆን በትምህርት ዘርፍ ያጋጠመውን ስብራት ለመጠገን በእያንዳንዱ አባላት ዘንድ የነበረውን ሀላፊነትን በውጤት ያለማሳየት ዕዳን ለመክፈል የሚያስችል ግንዛቤ ይፈጥራል ተብሎ ይታመናል።

በዛሬው መድረክ በቀጣይ ዕለተ ዕሮብ 17/04/2016 ዓ ም የሚጀምረው የአቅም ግንባታ ስልጠና በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ በቅድመ ዝግጅት ምዕራፎች ዙሪያ ሰፋ ያለ ውይይት የተደረገ ስሆን በሎጅስትክና ሌሎች መሟላት ባለባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር ተደርጓል።

Photos from የወላይታ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት- Wolaita Prosperity Party office's post 23/12/2023

በባይራ ኮይሻ ወረዳ "ከዕዳ ወደ ምንዳ" በሚል ሀሳብ ለአመራርና አባል አቅም ለመገንባት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ

ወላይታ ሶዶ፣ ታህሳስ 12/2016 ዓ ም በወላይታ ዞን ባይራ ኮይሻ ወረዳ በሁሉም ቀበሌያት " " በሚል መሪ ሀሳብ ለብልፅግና ፓርቲ አመራሮችና አባላት ስሰጥ የቆየር የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቀቀ።

ስልጠናው ሀገራዊ አንድነትን ለመፍጠር በሚያስችል መልኩ የአመራሩንና የአባሉን አቅም በመገንባት ለብዙ አመታት በአሰራርና በአፈፃፀም እንዲሁም በግንዛቤ እጥረት ምክንያት የተከማቸውን ዕዳ ለመቀየር ሰፊ ግንዛቤ የፈጠረ እንደሆነ ተገልጿል።

ኢትዮጵያ ለብዙ ዘመናት በእርስ በርስ አለመግባባት ውስጥ በመሆን የለውጥና የእድገት ስራዎች እንዲሁም የዜጎች ኑሮ ደረጃ እንዳይሻሻል የተዛባ የፖለቲካ ምህዳርና አስተዳደራዊ በደሎች እንደ አንድና ዋነኛ ማነቆ ሆኖ የሀገሪቱን እድገት እንዲስተጓጎል ማድረጉ በስልጠና መድረኮች ላይ ተነስቷል።

ሀገራችን ለዘመናት ከተያዘችበት ከራብና ከድህነት አረንቋ የሚትላቀቀው በአከባቢያችን ያለውን በጎ ስጦታዎች በአግባቡ ተጠቅመን ወደ ውጤት ስንቀይር ነው ስሉ የስልጠና ተሳታፊዎች ገልጿል።

ከአስተሳሰብና ከአመለካከት ዕዳ፣ ከነጠላ ትርክት፣ የሰላም እጦት መንስኤ፣ ... ወዘተ የሆኑ ችግሮችን በጥልቀት የተረዳንበትና በቀጣይ በግልም ሆነ እንደሀገር የተሻለ ለውጥ ለማምጣት በጋራ ለመስራት የሚያነሳሳና የሚያበቃ እንዲሁም የጋራ ተግባቦትን የፈጠረ ስልጠና ነው ብሏል።

በሁሉም ቀበሌና በወረዳ ኢንተርፕራይዝ ግንባር ላለፉት ሶስት ቀናት ሀገራዊ ስልጠናን የተከታተሉ ሰልጣኞች በስልጠና ማገባደጃ ላይ በአካባቢያቸው ላይ ያለውን የልማት ስራዎች፣ ምርጥ ተሞክሮ ቦታዎችንና መስኖ ሳይቶች ላይ ጉብኝት አድርጓል።

በተጨማሪም የወረዳ ኢንተርፕራይዞች ግንባር ሰልጣኞች ለአቅመ ደካሞችና ለአረጋውያን በበጎ ፍቃዳቸው የገንዘብና የአልባሳት ድጋፍ አድርጓል።

Photos from የወላይታ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት- Wolaita Prosperity Party office's post 23/12/2023

በገሱባ ከተማ ለአመራርና አባል አቅም ለመገንባት ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ

ወላይታ ሶዶ፤ታህሳስ ፤ 13/2016 ዓ.ም 'ከዕዳ ወደ ምንዳ'' በሚል መሪ ሀሳብ ወላይታ ዞን በገሱባ ከተማ አስ/ር ለአራት (4) ቀናት ሲካሄድ የቆየው ፐብሊክ ሰርቫንት ፣ የከተማ ነዋሪዎች፣ የአርሶ አደር እና የኢንተርፕራይዞች ስልጠና ተጠናቅቋል።

ሁሉም የብልፅግና ፓርቲ አባል በተሰማራበት በሥራ መስክ ቁርጠኛ አገልጋይና ሃገር ጠቃሚ ትውልድ ሆነው ለመቀጠል የአዕምሮ ክህሎት እና የአስተሳሰብ ለውጥ ያመጣ ስልጠና መሆኑን ተሳታፊዎች አንስተዋል።

ስልጠናው ህብረ- ብሔራዊ አንድነትን ያጠናከረ፣ በሀገራችን ዘላቂና አዎንታዊ ሰለም ለማምጣት የእርስ በርስ ፍቅር የጨመረ ስልጠና መሆኑን ተሳታፊዎች ገልጿል።

የስልጠና ተሳታፊዎች ከስልጠናዉ ካገኙት መሠረታዊ ጽንሰ-ሀሳብና አዳዲስ እሳቤዎች ጎን ለጎን የባህልና የልምድ ልዉዉጥ ከማድረጋቸውም ባሻገር ህብረ-ብሔራዊ አንድነትን የሚያጠናክር ቆይታ እንደነበረ ተጠቁሟል።

በአካባቢያችን ያለው ጸጋዎችን በመፍጠርና በመፍጠን ቁርጠኛ ስብዕና በመላበስ አገልጋይነትን በማስፈንና አቅምን በማጠናከር እንዲሁም የሠለጠነውን በተግባር በማሳየት ለተጀመረው እድገት የበኩላችን አሻራ ማስቀመጥ እንደሚገባ ተቀምጧል።

ስልጠናው በቂ እውቀት፣ ክህሎት እና ልምድ የተገኘበት መሆኑን እና ሠልጠኞቹ ለስልጠና ያላቸው ፊላጎትና ዲሲፒሊን የሚደነቅ እና በጠበቀው መልክ በላይ የተጠናቀቀ እንደሆነ ተገልጿል።

በስልጠናው ጎን ለጎን የተለያዩ በጎ ተግባራትን በማከናውን እና በከተማው የተሰሩ እና እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎች ጎብኝተዋል።

በስልጠናው ማጠቃለያው ላይ ሁሉም የስልጠና ተሳታፊዎች ከዞን፣ከከተማ አስተዳደር ፊት አመራሮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር የተሰሩ የልማት ሥራዎች፣ የVEG BOX ፕሮጀክት፣ የለማት ትሩፋት ጉብኝት ካደረጉ በኃላ የደሃ ደሃ ቤት ጥገናና የቤት ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደርጓል።

የዘገበው የከተማው ህዝብ ግንኙነትና ማህበራዊ ሚዲያ ዘርፍ ነው

Photos from የወላይታ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት- Wolaita Prosperity Party office's post 23/12/2023

የህዝባችን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ በእጃችን ያሉ ዕድሎችን በአግባቡ መጠቀም አለብን"፦ አቶ ጀገና አይዛ

ወላይታ ሶዶ፤ታህሳስ 13/2016ዓ.ም የወላይታ ሶዶ ከተማ ከንቲባ አቶ ጀገና አይዛ በከተማ 5ኛ ዙር "ከዕዳ ወደ ምንዳ" የብልጽግና ፓርቲ አባላት አቅም ግንባታ ሥልጠና ለፐብሊክ ሰርቫንት ግንባር ሰልጣኞች ቀጠይ የሥራ ስምሪት ስጥተዋል።

ለአራት ተከታታይ ቀናት ስሰጥ የነበረው 5ኛ ዙር "ከዕዳ ወደ ምንዳ" የብልጽግና ፓርቲ አባላት አቅም ግንባታ ሥልጠና ለፐብሊክ ሰርቫንት ግንባር በዛሬው ዕለት መጠናቀቁን በማስመልከት አቶ ጀገና የማጠቃለያ መልዕክት እና ቀጣይ የሥራ ስምሪት ሰጥተዋል።

ያሉንን ምቹ ሁኔታዎችን እና ፈተናዎችን በተገቢው በመለየት ምቹ ሁኔታዎችን በመጠቀም የህዝባችን ፍላጎት ማርካት ይገባናል ብለዋል።

አቶ ጀገና አያይዘውም የሥራ ባህላችንን በማስተካከል ስልጡንና አገልጋይ ፐብሊክ ሰርቫንት ተምሳሌት በመሆን ህዝባችንን በተገቢው ልናገለግል ይገባል ብለዋል።

ብልሹ አሰራሮችን አምርሮ በመታገል ለሁለንተናዊ ለብልጽግና የበኩላችንን አስተዋጽኦ ልናበረክት እንደሚገባ አንስተዋል።

አክለውም በከተማችን አልፎ አልፎ የሚስተዋለውን ህገ ወጥ ንግድ በመከላከል እዳችንን ወደ ምንዳ መቀየር አለብን ብለዋል።

በገቢ አሰባሰብ ሁሉም ፐብሊክ ሰርቫንት አባላት በባለቤትነት ትግል በማድረግ የገቢ አቅማችንን በማሳደግ ህዝቡ የሚጠይቀውን የልማት እና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ ሁላችንም አርበኛ ልንሆን ይገባል ብለዋል።

የወላይታ ሶዶ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አበባየሁ ኡኩሞ በበኩላቸው ሀብት እና ብልጽግናን በማስተዳደር እና ከከፋፋይ ሃሳቦች ይልቅ ገዢ ትርክቶችን የጋራ በማድረግ አብሮን የኖረ ወንድማማችነት እና እህትማማቾነትን በማጎልበት ለሀገራችንን ብልጽግና ጉዞ የበኩላችንን ጉልህ ሚና ልወጣ ይገባል ብለዋል።

የወሰድነውን ስልጠና እና በእጃችን ያሉ ዕድሎችን ወደ ሀብት በመቀየር ብልጽግና ስኬት ፐብሊክ ሰርቫንት አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑ ገልጸዋል።

የወሰድነውን ስልጠና ወደ ተግባር በመቀየር ለህዝባችን ቀልጠፋ እና ፍትሃዊ አገልግሎት በመስጠት ዕዳ የሆኑ ጉዳዮችን ወደ ምንዳ ለመቀየር መዘጋጀታቸውን አሰልጣኞች ገልጸዋል።

በመጨረሻም ሰልጣኞች አንድ የአቅመ ደካማ ቤት ግንባታ ፣አንዲት እናት ቤት ጥገና እንዲሁም ለአንድ ቤተሰብ የተለያዩ የምግብና የቤት ቁሳቁስና ገንዘብ በመስጠት 5ኛ ዙር ስልጠናው ተጠናቋል።

**oProsperity

Photos from የወላይታ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት- Wolaita Prosperity Party office's post 23/12/2023

"ስልጡን ገለልተኛ እና አገልጋይ ፐብሊክ ሰርቫት ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ ከፍተኛውን ሚና ይወጣል!!" አቶ አበባየሁ ኡኩሞ

ወላይታ ሶዶ: ታህሳስ 13/2016 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ከተማ ለ4 ተከታታይ ቀናት በ10 መሠረታዊ ድርጅቶች ስሰጥ የነበረው "ከዕዳ ወደ ምንዳ" የፐብሊክ ሰርቫንት አባላት ስልጠና በድምቀት ተጠናቀቀ።

ስልጠናው የታለመለትን ግብ ያሳካ ነው ያሉት የወላይታ ሶዶ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አበባየሁ ኡኩሞ ስልጠናው ለአባላት የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት የፈጠረ ነው ብለዋል።

ስልጡን ገለልተኛ እና አገልጋይ ፐብሊክ ሰርቫት ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ ከፍተኛውን ሚና እንደሚወጣ ገልጸዋል።

አባላት አሁን ያለው ዓለም አቀፋዊና ሀገራዊ ነባራዊ ዐውዶችን በተገቢው በመረዳት በሙላት በመሳተፍ ብልፅግና ፓርቲ አቅዶ የተነሳውን ራዕይን ወደ ግብ ለማድረስ ልረባረቡ እንደሚገባም አሳስበዋል።

በየጊዜው የሚገጥሙን ጥቃቅን ጊዜያዊ ፈተናዎች ትልቁን እይታችንን እንዳይጋርዱ ነገሮችን አሻግረን ማየትና ለችግሮቹም መፍትሄም በጋራ ልንረባረብ ይገባናልም ብለዋል፡፡

በየአካባቢው ያሉ እምቅ ሀብቶችን በአግባቡ በመጠቀምና ሀብት በመፍጠር የስራ አጥነትና የኑሮ ውድነት ችግር መቅረፍ እንደሚያስፍልግም አንስተዋል።

ስልጠናው በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ፐብሊክ ሰርቫንት አባላት ላሳዩት ተሳትፎና ቁርጠኝነት አቶ አበባየሁ ምስጋና አቅርበዋል።

Photos from የወላይታ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት- Wolaita Prosperity Party office's post 23/12/2023

የጨበራ የዝሆን ዳና ሎጅ
Chebera Elephant Paw Lodge

Photos from የወላይታ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት- Wolaita Prosperity Party office's post 23/12/2023

በወላይታ ሶዶ ከተማ ገበያን ለማረጋጋት የተጀመረው ሰንበት ገበያ(Sunday market) ተጠናክሮ ቀጠለ

ወላይታ ሶዶ፤ታህሳስ 13/2016ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ከተማ ገበያን ለማረጋጋት የተጀመረው ሰንበት ገበያ(Sunday market) መሠረታዊ የፍጆታ ዕቃዎችን በማሟላት ተጠናክሮ ቀጥሏል።

ከአምራቹ በቀጥታ ለሸማቹ የሚቀርቡ መሠረታዊ የፍጆታ ዕቃዎችን በቅናሽ ዋጋ በማቅረብ ግብይቱ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

ሰንበት ገበያው የህብረተሰቡን ኑሮ ወድነትንና ገበያ ለማረጋጋት እፎይታ የሚሰጥ መሆኑን ተገልጿል።

Photos from የወላይታ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት- Wolaita Prosperity Party office's post 22/12/2023

ሥልጠናው ያጠናቀቁ የአራዳ ቀበሌ ሰላም መሠረታዊ ድርጅት አባላት የአንዲት አቅመ ደካማ እናት ቤት ግንባታ አስጀመሩ

ወላይታ ሶዶ: ታህሳስ 12/2016 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ከተማ 5ኛ ዙር "ከዕዳ ወደ ምንዳ" የብልጽግና ፓርቲ አመራርና አባላት አቅም ግንባታ ስልጠና የጨረሱት የአራዳ ቀበሌ ሰላም መሠረታዊ ድርጅት አባላት የአንዲት አቅመ ደካማ እናት ቤት ግንባታ አስጀመሩ።

የወላይታ ሶዶ ከተማ በቦታው ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክታቸው ብልጽግና የዜጎችን ጉስቁልና ለመከላከል ከያዛቸው ሰው ተኮር ፕሮግራም አካል የሆኑ በርካታ ድሃ ተኮር ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን በማስታወስ፤ ፓርቲው ይህን እንደ አንድ የፖለቲካ ፕሮግራም አካል አድርጎ ሲይዝ በአገራችን የቆየ የመረዳዳትና የመደጋገፍ ባህልን ለማስቀጠልም በማሰብ ስሆን ሰልጣኞች በራሳቸው ተነሳሽነት ያደረጉት የበጎ ተግባር ተጠናክሮ የሚያስመሰግን ነው ብለዋል፡፡

እንደ ሀገር የተያዘውን ሰው ተኮር ተልም እውን ለማድረግ መሰል ተግባራትን በየ አከባቢው በማስፋፋት የመረዳዳት ባህላችንን ቀጣይነት ባለው መልክ ልናሳድግ እንደሚገባም አሳስበዋል።

የወላይታ ሶዶ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አበባየሁ በየአካባቢያችን የሚኖሩ አቅመ ደካሞችን በመደገፍ ሀገራችን የያዘችውን ሁሉን የማበልጸግ አላማ ለማሳካት ትኩረት ሰጥተን መስራት አለብን ብለዋል።

የበጎ ሥራ የጀመርነውን ሰው ተኮር ሥራችን አካል ነው ያሉት አቶ አበባየሁ ዜጎችን ተጠቃሚ በማድረግ የመተሳሰብ ባህላችንን ልናሳድግ ይገባል ብለዋል።

Want your organization to be the top-listed Government Service in Sodo?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Videos (show all)

የገበታ ለሀገር - የጨበራ የዝሆን ዳና ሎጅ
የማየት ብልጽግና ፣የመሥራት ብልጽግና ፣የመጠበቅ ብልጽግና በኮንታ ዞን።
ከዕዳ ወደ ምንዳ
አጃራ መንትያ ፏፏቴ- ወላይታ
በየተቋማት የሚሰጡ የአገልግሎት አሰጣጥ ለተገልጋይ ህብረተሰብ እርካታ የሚሰጥ መሆን እንዳለበት የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ፎላ ተናገሩ።
ኢትዮጵዊነት አንድነትና ፍቅር ስለመሆኑ በቆይታችን አረጋግጠናል አሉ የ4ኛዉ ዙር በወላይታ ሶዶ ማዕከል ሀገር አቀፍ የመንግስት አመራር ስልጠና እየወሰዱ የሚገኙ ሰልጣኞች፡፡
ኦቦ ሽመልስ አብዲሳ ወላይታ ሶዶ ሲገቡ የተደረገላቸው አቀባበል
የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ይፋዊ ስራ ማስጀመሪያና ማብሠሪያ ፕሮግራም ላይ የተገኙት የፓርቲያችን ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፈራህ፥ የህዝቦችን የዓመታት ጥያቄ ሠላማዊ፣ ዲሞ...
ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሰላምና የብልጽግና ተምሳሌት
የወላይታ ምዕራቡ ክፍል ሲጎበኝ
የእንግዳ ተቀባይ ተምሳሌት
የወላይታ ሶዶ ከተማ በምታስተናግደው የደቡበ ኢትዮጵያ ክልል ይፋዊ ምስረታ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ላይ የከተማው ነዋሪ አሻራውን እንዲያሳርፍ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ፎላ ጥ...

Telephone

Address

S**o
026
Other Political Organizations in S**o (show all)
Dddd Dddd
S**o

Dddd is an unknown political organization

Wolaita Soddo City Prosperity Party Office Wolaita Soddo City Prosperity Party Office
S**o

ይህ በሶዶ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት መሪነት የተከናወኑ ተ?

S**o Town DiliBegerera Amba Kebele Prosperity S**o Town DiliBegerera Amba Kebele Prosperity
Woliata S**o
S**o

To promote socioeconomic development and political issues of the community.