Hagere media

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Hagere media, Tai Chi Studio, Mombasa.

Photos from Hagere media's post 01/01/2023

የ16 ዓመት ታዳጊ አስገድዶ የደፈረው ግለሰብ በ8 አመት ከ5 ወር እስራት ተቀጣ።

በደሴ ከተማ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀመዉ አባወራ በእስራት መቀጣቱ ተሰምቷል።

ተከሳሹ ሳሙኤል ሹሙ ይባላል በደሴ ከተማ ቧንቧ ዉሃ ክፍለ ከተማ በመገናኛ ቀበሌ ነዋሪ ሲሆን ባለትዳርና የአንድ ልጅ አባት ነዉ፡፡

የ28 አመቱ ተከሳሽ አባወራ በቤቱ ዉስጥ በሠራተኝነት የቀጠራትን የ16 አመት ታዳጊ ህፃንን በማስፈራራት አስገድዶ መድፈሩን በደሴ ከተማ የ4ኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ ገልጿል።

ተከሳሹ ድርጊቱን የፈፀመዉ ባለቤቱ ወደስራ የምትሄድበትን ሠአት እና እቤት ዉስጥ ሠዉ የማይኖርበትን አጋጣሚ በመጠቀም ታዳጊዋን በማስፈራራትና አፍና አፍንጫዋን በማፈን በተለያየ ግዜ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ሲፈፅምባት መቆየቱ ተገልጿል።

ታዳጊዋ ህፃን ከደፋሪዋ ቤት ከወጣች በሗላ የደረሰባትን ጥቃት ለቤተሠቦቹዋ በመናገሯ ለፖሊስ ጥቆማ በማድረጋቸዉ አስገድዶ ደፋሪዉ አባወራ በቁጥጥር ስር ዉሎ ምርመራ ሲጣራበት ቆይቷል።

ፖሊስ በሠዉና ሀኪም ማስረጃ መዝገቡን በማጠናከር ወደሚመለከተዉ የፍትህ አካል ልኳል፡፡

መዝገቡን የተመለከተዉ የደሴ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት በቅርቡ በዋለዉ ችሎት ጥፋተኝነቱን በማረጋገጡ ተከሳሽ ሳሙኤል ሹሙ በ8 አመት ከ5 ወር እስራት እንዲቀጣ የወሠነበት መሆኑን በደሴ ከተማ የ4ኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ ህዝብ ግንኙነት ክፍል ዘግቧል፡፡

ሀገሬ ሚድያ

Photos from Hagere media's post 25/12/2022

በሰላም ተጠናቋል🙏
በታሪካዊቷ በመናገሻዋ ጎንደር "ለቅዱስ ሩፋኤል እሮጣለሁ: የህንፃ ቤተክርስቲያኑን አስፈጽማለሁ" በሚል የተዘጋጀው ታላቅ መንፈሳዊ የገቢ ማሰባሰቢያ የጎዳና ላይ ሩጫ በሰላም ተጀምሮ በሰላም ተጠናቋል ።

የከተማችን ማህበረሰብ የሩጫው ፕሮግራም በድምቀትና በሰላም ተጀምሮ በሰላም እንዲጠናቀቅ ላሳያችሁት ስነምግባርና ሀይማኖታዊ ሀላፊነት ምሰጋናየ ላቅ ያለ ነው።

ጥምቀትን በአፄዎቹ መናገሻ ጎንደር በጌምድር ያክብሩ።

ሀገሬ ሚድያ

25/12/2022

ኢትዮጵያን ጨምሮ 8 የአፍሪካ ሀገራት የ2027 የአፍሪካ ዋንጫን በጋራ ለማዘጋጀት ሀሳብ እንዳላቸው ተሰምቷል።

የኬንያ የንግድ ቢሮ ሀላፊ ሞሰስ ኩሪያ ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ዩጋንዳ፣ ታንዛንያ፣ ርዋንዳ፣ ቡሩንዲ፣ ዴሞክራቲክ ኮንጎ እና ደቡብ ሱዳን ጨዋታውን በአንድነት ለማዘጋጀት ውድድር ውስጥ እንደሚገቡ እንደተናገሩ የኬንያው ሲቲዝን ቲቪ ዛሬ ዘግቧል።
ግን አንድ ውድድር ለማዘጋጀት ስምንት ሀገር?

ሀገሬ ሚድያ

25/12/2022

⬆️
#ድንቃድንቅ ፖሊስ ተከሳሹን ፈልጎ እንዳጣ ቢናገርም ተከሳሹ ግን በድብቅ ችሎት እየገባ ክሱን አዳምጦ ይወጣ ነበር።

አቢሲኒያ ባንክን የ6.1ሚሊዮን ብር አሳጥተዋል ተብለው በከባድ ሙስና ወንጀል ከተከሰሱ ከ 5 ተከሳሾች መካከል አንደኛ ተከሳሽ አይተንፍሱ እንዳሻው ይባላል።

ይህ ተከሳሽ ክስ ከቀረበበት ጊዜ ጀምሮ በተደጋጋሚ ፖሊስ አፈላልጎ እንዲያቀርበው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ትዕዛዝ ተሰጥቶ ነበር።

በመጨረሻም ፖሊስ ተከሳሹን በመኖሪያ አድራሻው አፈላልጎ ማግኘት እንዳልቻለ ገልጾ መልስ መስጠቱን ተከትሎ ተከሳሹ በጋዜጣ ጥሪ እንዲደረግለት ተደርጓል። ከጋዜጣ ጥሪው በኋላ ተከሳሹ በችሎት አለመቅረቡን ተከትሎ በሌለበት መዝገቡ እንዲቀጥል ብይን ተሰጥቶ ነበር።

ይሁንና ግን ተከሳሹ ክስ ከቀረበበት ጊዜ ጀምሮ የችሎቱ ዳኞች በአካል ስለማይለዩት ተደብቆ ችሎት እየገባ ምን እንደተባለ አዳምጦ ሾልኮ ይወጣ ነበር። በዚህ መልኩ ተከሳሹ ተደብቆ ሲገባ አንደኛዋ ተከሳሽ ለፍርድ ቤት ለሚገኙ ፖሊሶች በቁጥጥር ስር እንዲያውሉት ብትጠቁማቸውም በቁጥጥር ስር ሳያውሉት ቀርተዋል። ተከሳሹም ሳይያዝ ከችሎት ወጥቶ ይሄዳል። ይህንን ሁኔታ ተከሳሿ ለችሎቱ ዳኞች ጥቆማ ሰጥታለች።

የችሎቱ ዳኞች አርብ ዕለት በነበረ ቀጠሮ ጉዳዩን ለማጣራት የተከሳሹ የአክስት ልጅ የሆነ በዚሁ መዝገብ ለቀረበ ግለሰብ ተከሳሹን በሚመለከት ጥያቄ አቅርበዋል።

''በቁጥጥር ስር ያልዋለውን አይተንፍሱ የሚባለው ተከሳሽ እዚህ ሲመጣ አይተኸዋል ወይ?'' ተብሎ የቀረበለት ግለሰብም በበኩሉ ''አዎ አይቼዋለሁ፣ እኔ እንደሚፈለግ አላቅም እንጂ ፍርድ ቤት እየመጣ ተከታትሎ ሲሄድ አይቻለው'' ሲል መልስ ሰጥቷል።

ተከሳሹን ፖሊስ በአድራሻው ማግኘት አልቻልኩም ብሎ መልስ መስጠቱን ተከትሎ በሌለበት ጉዳዩ እንዲታይ ተብሎ ብይን ከተሰጠ በኋላ በዚህ ደረጃ ፍርድ ቤት ተደብቆ እየገባ ምን እንደተባለ አዳምጦ ሾልኮ ሲሄድ በቁጥጥር ስር የሚያውለው የፖሊስ አካል አለመኖሩ የችሎቱ ዳኞችን አበሳጭቷል።

ፖሊስ ለቆመለት አላማን መተግበር ሲገባው በቸልተኝነት ተከሳሹን ተከታትሎ በቁጥጥር ስር ባለመዋሉ የተፈጠረ ችግር መሆኑን የችሎቱ ዳኞች ገልጸዋል።

''የዳኝነት ስራ ግልፅ ነው፣ የሚደበቅ ነገር የለም" ሲሉ ያብራሩት ሰብሳቢ ዳኛው የታሰረ ሰው ጥቆማ እየሰጠ ተከሳሹ ፍርድ ቤቱ ውስጥ ተደብቆ ገብቶ እየተንቀሳቀሰ ሌላው ማረሚያ ቤት ወርዶ የሚታይበት ሂደት በፍትህ ስርዓቱ ላይ መጥፎ አሻራ ጥሎ የሚያልፍ መሆኑን ገልጸዋል።

የወንጀል ፍትህ አስተዳደር ፍርድ ቤት ብቻ አደለም ያሉት ሰብሳቢ ዳኛው ፖሊስ ተከሳሾችን በቁጥጥር ስር በማዋል ረገድ እንደተቋም በተገቢ በጥረት ሊሰራ እንደሚገባም አፅንኦት ሰጥተዋል።

እንደ አጠቃላይ ይህ መዝገብ በሚመለከት ችሎቱ ለታህሳስ 25 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቶበታል።

ምንጭ: ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ

Photos from Hagere media's post 25/12/2022

"አርሂቡ" ኮምቦልቻ የፍቅር ሩጫ

| አርሂቡ ኮምቦልቻ የፍቅር ሩጫ በኮምቦልቻ ከተማ እየተካሄደ ነው።

የሩጫው ዓላማ ከተማዋ ባለፈው ዓመት በጦርነት የደረሰባትን ጉዳት ለመካስ የሚያስችሉ ስራዎችን ለመሥራትና እንዲሁም በከተማዋ የደረሰውን ሥነ ልቦናዊ ቀውስ በመርሳትና ዜጎችን ለፍቅር፣ ሠላምና አንድነት ለማነሳሳት በማሰብ ነው።

የሩጫ መርሐ ግብሩ የአዋቂዎች አምስት ኪሎ ሜትር እንዲሁም የህጻናት የሁለት ኪሎ ሜትር ያካተተ ሲሆን የከተማ አስተዳደሩ፣ የዞንና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ኮምቦልቻ ከተማ እና በከተማ ውስጥ የሚገኙ በመቶዎች የሚቆጠሩ ፋብሪካዎች ጉዳት የደረሰባቸው ቢሆንም በርካታዎች ወደ ቀድሞ ሥራቸው እየተመለሱ መሆኑ ይታወቃል።

ሀገሬ ሚድያ

Photos from Hagere media's post 25/12/2022

253 ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞችን በቀይ ባህር ከሞት አደጋ መታደግ ተቻለ

የጅቡቲ የባህር ዳርቻ ጥበቃ ሀይል በጅቡቲ በጋህሬ የባህር ዳርቻ አካባቢ 253 ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞችን ጭና ወደ የመን የምትጓዝ ህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪ ጀልባ በቁጥጥር ስር በማዋል ፍልሰተኞቹን ከሞት አደጋ ማትረፉ ተነግሯል፡፡

ከፍልሰተኞቹ መካከል 98ቱ ሴቶች ናቸው፤ ጀልባዋ በቁጥጥር ስር ባትውል ኖሮ ከአቅም በላይ በመጫኗ የመስጠሟና የፍልሰተኞች ህይወት የማለፉ እድል ከፍተኛ ነበር የተባለ ሲሆን ለፍልሰተኞቹ አስፈላጊው ድጋፍ ተደርጎላቸው ወደ ሀገራቸው እንዲገቡ ተደርጓል፡፡

ኃይሉ የአሁኑን ከስተት ጨምሮ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ ህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪ ጀልባዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ከ1000 በላይ ኢትዮጵያዊያን ህይወት መታደግ ችሏል፡፡

አራት የውጭ ዜጎች በህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪነት ተጠርጥረው ለፍርድ መቅረባቸውን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤንባሲ አሳውቋል።

ሀገሬ ሚድያ

Photos from Hagere media's post 25/12/2022

ፎቶ ፦ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎችን መቀበል ጀምረዋል።

አንዳንድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከቀናት በኃላ መሰጠት የሚጀምረውን 12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የሚፈተኑ ተማሪዎችን ዛሬ መቀበል ጀምረዋል።

ተቋማቱ ከወዲሁ ፤ ተፈታኝ ተማሪዎች ከገቡ በኃላ ፈተናው እስኪጠናቀቅ ድረስ ከተፈቀደላቸው የተቋሙ ሰራተኞች እና ፈተና አስፈፃሚዎች በስተቀር ተፈታኞች ባሉባቸው ቦታዎች ማንኛውም አካላት እንዳይንቀሳቀሱ ጥብቅ መመሪያ እየሰጡ ይገኛሉ።

በተለያዩ ምክንያቶች በመጀመሪያው ዙር ፈተና መውሰድ ያልቻሉ ተማሪዎች ከታህሳስ 18 እስከ 21 ድረስ ባሉት ቀናት ፈተናቸውን ይወስዳሉ።

የመጀመሪያ ዙር ተማሪዎች ፈተና ውጤት እስካሁን ይፋ ያልተደረገ እና ይፋ የሚደረግበት ትክክለኛ ቀን ያልታወቀ ሲሆን ትምህርት ሚኒስቴር ከዚህ በፊት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ፤ አጠቃላይ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ውጤት ፈተና በኋላ የሚገለጽ መሆኑን አሳውቆ ነበር።

Photo Credit : ቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Mombasa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address

Mombasa
Other Mombasa gyms & sports facilities (show all)
Shepherds RFC Shepherds RFC
Mombasa, 90450

The love of the game brought us together to shepherd the game

Mkunguni Youngstars FC Mkunguni Youngstars FC
Ziwa La Ngombe Ward
Mombasa, 80100

Talented Soccer youths development

Triathlon Kenya Triathlon Kenya
Mombasa

Kenya Triathlon Federation is the Official Sport Governing body for the sport of Triathlon in Kenya.

TAIFA STARS FC TAIFA STARS FC
Vok
Mombasa, KBC

We grow talents

ifitifyfitness ifitifyfitness
Old Msa Malindi Road
Mombasa

We are Personal and Group fitness trainers specialized in Bodyweight exercises & Minimal use of work

Mombasa Run Mombasa Run
Mombasa

Tukutane Mombasa on the 5th & 6th February. Let's celebrate the White & Blue City. Follow us to stay tuned for more details. 💬 +254758283803 for inquiries. Organised by Action Mark...

Kefootball_ Kefootball_
Mombasa

All Kenyan football news

Jumz Mse Wa Man Utd Jumz Mse Wa Man Utd
Mombasa, MOMBASA80100

GGMU FOR LIFE #KIBURI FC

Jux & Dosh Jux & Dosh
58776
Mombasa

Mombasa All Stars Football Club Mombasa All Stars Football Club
Mombasa

Mombasa All Stars Football Club aims at nurturing and exposing talents

Carlos thee pluto junior Carlos thee pluto junior
Mombasa

content creator you tube kicheche empire ig.kasweety carol ❤️ 🇰🇪best of all nipitie#nikupitie.

Shaffy Thee Og Skoolpheez Shaffy Thee Og Skoolpheez
Shkadabu
Mombasa

Football