Salvation for all nations ministries

This is the official face book page of salvation for all nations. Ministry of Evangelist Ruth Dawit

12/06/2024

ሳልቬሽን ፎር ኦል ኔሽንስ ሚንስትሪስ የሚሳተፍበት
የምሁራን ነፍስ ለኢየሱስ በሚል ርዕስ ሰኔ 8
በአዲስ አበባ ጎዳናዎች የተዘጋጀ የወንጌል ስርጭት

ተልዕኮ ለትውልድ ቤተክርስቲያን ከኢትዮጵያ ወንጌል ማኅበረተኞች ጋር በመተባበር የተዘጋጀ

11/06/2024

SFAN BOOK REVIEW!!!!

በ አፖስትል ማልዶናዶ የተፃፈው GLORY OF GOD መፅሀፍ የዚህ ሳምንት ጥናታችን ይሆናል ሙሉውን መፅሀፍ በ pdf ማግኘት የምትፈልጉ የቴሌግራም ቻናላችን ሊንክ በመጫን ይቀላቀሉ 👇👇👇👇👇👇

https://t.me/+ATd__GavTilmMTA0

10/06/2024

ታላቅ የወንጌል ስርጭት በ ጎሮ, ኮዬ ፈቼ እንዲሁም በሳፋሪ ሰሚት ለተከታታይ አራት ሳምንታት

ሳልቬሽን ፎር ኦል ኔሽንስ ሚኒስትሪስ ከ ዱናሚስ የወንጌል ህብረት ጋር በመተባበር

ዘወትር ማክስኞ እና አርብ ከ10.00 ጀምሮ

“በውድ ልጁም፥ እንደ ጸጋው ባለ ጠግነት መጠን፥ በደሙ የተደረገ ቤዛነታችንን አገኘን እርሱም የበደላችን ስርየት።”
— ኤፌሶን 1፥7

10/06/2024

ሁሉም ነፍስ ለሙሽራው ኢየሱስ
የወንጌል አጋራችን በሆነው የኢትዮጵያ ወንጌል ማህበረተኞች የተዘጋጀ የወንጌል ስርጭት ሰኔ 9 በአዳማ/ናዝሬት/ አደባባዮች ይካሄዳል!!!!

ማቴዎስ 25⁶ እኩል ሌሊትም ሲሆን፦ እነሆ፥ ሙሽራው ይመጣል፥ ትቀበሉት ዘንድ ውጡ የሚል ውካታ ሆነ።
⁷ በዚያን ጊዜ እነዚያ ቆነጃጅት ሁሉ ተነሡና መብራታቸውን አዘጋጁ።
#ወንጌል #ህብረት

09/06/2024

አንድ ነገርን ልምከራችሁ

ትናንትናችሁ ፍፁም የተበላሸ ሊሆን ይችላል የወደቃችሁበት ነገርም ብዙ ይሆናል ማንም የማይጠብቅባችሁን መንገድ ተራምዳችሁ ይሆናል ሰው ሁሉ ትቷችሁ ነገር ሁሉ እናንተን ተስፋ ለማስቆረጥ ይሰራ ይሆናል የትናንትናውን ጩከታችሁን እና ረሀባችሁን ቀጥ አድርጎ የሚገታ መንፈሳዊ መውረድ ውስጥ ገብታችሁ ሊሆን ይችላል

🙄ነገር ግን
ዛሬ ወስኑ አጥብቃችሁ ለመጸለይ
ዛሬ ወስኑ ቅድስናን የህይወት ዘይቤ ለማድረግ

ከትናንት መውረዳችሁ ያልጀመረ ነገር ግን ከዛሬ ቆራጥነታችሁ መሰመር የሚጀምር አዲስ ነገር በእርግጥ ሲሆን ትመለከታላችሁ::

ከሚልየኖች ጋር ትውልዳችሁ ተጣብቋልና ካላችሁበት ሰንሰለት ተፈትታችሁ የተላካችሁበትን አላማ ወደመፈጸም አድርሱ ከዚህ ትውልድ ተለይታችሁ አትቅሩ እግዚአብሔር የገባውን ቃል ፈፅሞ አያጥፍም ነገር ግን ለመቀበልና በታማኝነት ለማስፈጸም ትጉ::

እወዳችኋለው
ሪቫይቫል ይሆናል

09/06/2024

#ወንጌል #ህብረት

09/06/2024

የፀሀይን ብርሀን በጊዜው ላይ የሚሰለጥነው ለሊት ይወስድባታል እንዲሁም ደግሞ የጨረቃ ብርሀን ህያውነት በፀሀይ ብርሀን ምንጭ ላይ የተመሰረተ ነው!!!!!

ኢየሱስ የአለም የብርሀኗ ምንጭ ነው::

የሰው ልጆች የህይወት ብርሀን ምንጭ ነው ሀጥያት የሆነው ጨለማ እንኳን በእርሱ ላይ ስልጣን ከቶ የለውም!!!!!!

“ብርሃንም በጨለማ ይበራል፥ ጨለማም አላሸነፈውም።”
— ዮሐንስ 1፥5

Photos from Salvation for all nations ministries's post 09/06/2024

የ ሳልቬሽን ፎር ኦል ኔሽንስ ሚኒስትሪስ ተሳታፊ የሆነበት የ ጎዳና ላይ የወንጌል ስርጭት በ አብ ልብ ቤተክርስቲያን አዘጋጅነት በኮዬ ፈቼ አደባባዮች ላይ ተካሂዷል!!!

" እርሱንም በእግዚአብሔር በተወሰነው አሳቡና በቀደመው እውቀቱ ተሰጥቶ በዓመፀኞች እጅ ሰቅላችሁ ገደላችሁት። እግዚአብሔር ግን የሞትን ጣር አጥፍቶ አስነሣው፥ ሞት ይይዘው ዘንድ አልቻለምና።" ሐዋርያት 2:23-24

31/05/2024

ወንጌል በጦር ሀይሎች አደባባይ

“የእውነትን ቃል በቅንነት የሚናገር የማያሳፍርም ሠራተኛ ሆነህ፥ የተፈተነውን ራስህን ለእግዚአብሔር ልታቀርብ ትጋ።”
— 2ኛ ጢሞቴዎስ 2፥15

30/05/2024

ኢየሱስ!!!

29/05/2024

አማኑኤል:-ያህዌ ከእኛ ጋር

24/05/2024

የ ሳልቬሽን ፎር ኦል ኔሽንስ ሚኒስትሪስ ተሳታፊ የሚሆንበት የ ጎዳና ላይ የወንጌል ስርጭት በ አብ ልብ ቤተክርስቲያን ተዘጋጅቷል

" እርሱንም በእግዚአብሔር በተወሰነው አሳቡና በቀደመው እውቀቱ ተሰጥቶ በዓመፀኞች እጅ ሰቅላችሁ ገደላችሁት። እግዚአብሔር ግን የሞትን ጣር አጥፍቶ አስነሣው፥ ሞት ይይዘው ዘንድ አልቻለምና።" ሐዋርያት 2:23-24

ነፃ የ ህዝብ ትራንስፖርት ተዘጋጅቷል!!!

"ሁላችሁም ተጋብዛችኋል"

24/05/2024

የህይወታችሁ መርከብ

አንድ መርከብ ወይም ታንኳ በባህር ላይ ለመጓዝ ሲነሱ ዝም ብሎ ለመሄድ ሳይሆን የታለመ ወይንም የታሰበ አንድን አላማ ለመምታት ነው ፡፡ለምሳሌ
በ ዮሃንስ 21፡1-6 ታንኳዋ ለአሳ ማጥመጃነት እንደተጠቀሟት ታያላችሁ፡፡

አብዛኛውን ጊዜ ኢየሱስ ሰውን ለማጥመድ ተጠርታቸህኋል ካላቸው በኋላ እና የመከተል ምላሽን ከሰጡት በኋላ ታንኳዎቻቸው አሳ ከማጥመድ ባለፈ ለመንፈሳዊ አገልግሎት ውለዋል ኢየሱስ በታንኳቸው ላይ ተቀምጦ ያስተምር ነበር

በ ማቲዎስ 8፡23 ላይ ግን ደቀመዛሙርቱ ታንኳዋን ጌርጌስዮን ወደሚባል ቦታ የ ነጻ ማውጣት አገልግሎትን ለማካሔድ ተጠቅመውባታል

ልክ ህይወታችሁን እንደዚች ታንኳ አስቧት ጌታ ኢየሱስ ተከተሉኝ የሚል ጥሪን ከሰጣችሁ በኋላ እናንተነታችሁ ምድራዊን ነገር ከማጥመድ ባለፈ እና በተለየ መልኩ የእግዚአብሔርን የሆነውን ነገር ለማጥመድ እና ለመስራት ይዘጋጃል በዚህ ሁሉ መሃል ግን አንድ ነገር ይከሰታል እርሱም መናወጥ ይባላል፡፡

መናወጥ እንዴት ይከሰታል

1.እግዚአብሔር የሰጣችሁን ጥሪ በ ህይወታችሁ ውስጥ ብትሰሙም ባለመታዘዝ የምትሸሹባቸው የህይወት ክፍሎቻችሁ ከራሱ ከእግዚአብሔር መናወጥን ያስነሳባችኋል፡፡
የዮናስን ህይወት እንመልከት ፡-ዮናስ እንደሌሎቹ የእግዚአብሔር ሰዎች ቃል የመጣለት ፣የነነዌ ሰዎች ሀጥያት በመብዛቱ ምክንያት እንዲሰብካቸው እና ከክፉ መንገዳቸው እንዲመለሱ እንዲነግራቸው ሲነገረው ተነስቶ መኮብለልን መረጠ ፡፡ዮናስም ተነስቶ ወደ ተርሴስ በምትሄድ መርከብ ውስጥ ተሳፈረ ልክ እንደ ዮናስ በመንፈሳዊ ጥሪያችሁ ውስጥ በእግዚአብሔር እንደተጠራችሁ እያወቃችሁ ፣ያንን መፈጸም ግዴታችሁ እንደሆነ እያወቃችሁ ነገር ግን የትውልድን መልእክት እና ማዳን ይዛችሁ ለመሰወር እና ለመኮብለል እርምጃን ስትጀምሩ እግዚአብሔር በመንገዳችሁ ላይ መናወጥን ያመጣል፡፡ እናንተ ብቻ ሳትሆኑ ለመኮብለል የተሳፈራችሁበት መርከብ ሁሉ መናወጥ ይጀምራል ፡፡ በዚያን ግዜ ልክ በመርከቡ ላይ የተሳፈሩት ምክንያቱን ፈልገው እንዳገኙት እናንተም መርከባችሁን የሚያናውጠው ነገር በትክክል እግዚአብሔርን አለመታዘዛችሁ መሆኑን ፈልጋችሁ ባወቃችሁት ግዜ ያላችሁ አማራጭ ያንን አልታዘዝ ያላችሁበትን አካል አውጥታችሁ መጣል ነው አብረዋችሁ በመርከባችሁ የተሳፈሩት የእናንተ ማንነቶች ሁሉ የእናንተን የሸሻችሁበትን መንገድ ማዳን በመፈለግ ወደ ማትረፍ ቢነዷችሁም ጥበባችሁ እና ማስተዋላችሁ እንዲሁም ምክራችሁ በ እግዚአብሔር ላይ አይሆንምና መናወጡ ይቀጥላል፡፡

2.መንፈሳችሁን ባለማዳመጣችሁ እንዲሁም በምድራዊው ማንነታችሁ ብርታት እና ውሳኔ አሳላፊነት በመንቀሳቀሳቸሁ መርከባችሁ ከመናወጥ አልፎ ወደ መሰባበር ይደርሳል ቢሆንም በመናወጥ ውስጥ መንፈሳችሁን ማዳመጥ እና ሰማይ እንድታከናውኑት የሰጣችሁን ስራ ካወቃችሁ መዳን ይሆንላችኋል ፡፡

3.የአጋንንት ሀይላት
በ ማቲዎስ 8፡23 ጌርጋሴኖን ከመድረሳቸው በፊት ከባድ አውሎ ንፋስ አንደተነሳ እና መርከቢቱን ሊያሰምጣት እነደደረሰ እናያለን፡፡ ይህ አይነት መናወጥ በጭራሽ ፍረሀት እና ጭንቀት ሊያደርስባችሁ አይገባም ልክ እንደ ደቀመዛሙርቱ መርከብ ህይወታችሁ ከአቅማችሁ በላይ በብዙ ምልክቶች በታጀበ መናወጥ ይናወጥ ይሆናል ነገር ግን ሁሌም በዚህ መናወጥ ግዜ ማሰብ ያለባችሁ የናዝሬቱ ኢየሱስ በታንኳችሁ ውስጥ መሆኑን ነው፡፡ ወዳጃችን ኢየሱስ ዛሬም በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት በውስጣችን ይኖራል ይህም ደግሞ እርሱ ህይወታችንን እንዲቆጣጠር እድልን ከሰጠነው ማእበሉን ገስጾ ጸጥ የማሰኘት ሀይል አለው፡፡

21/05/2024

ohhhh God of Thy Azusa street

የ ዊሊያም ጄ ሲሞር አምላክ ሆይ ወደ የት ነህህህ????🔥🔥🔥🔥🔥😭😭😭😭😭

!!
ከሐዋሪያት ዘመን በኃላ በታሪክ ውስጥ ለአለም አቀፍ ደረጃ መንፈስ ወረደ የሚባለው በአዙሳ መንገድ በ 1906 በዊልያም ጄ ሲይሞር አገልግሎት ነው። ከዚያ ጀምሮ እስከ አሁን ወደ 600,000,000 (ስድስት መቶ ሚሊዮን) ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተሞልተዋል ተብሎ ይነገራል።

16/05/2024

upcoming Event
Sunday starts from 3.00Lt
@ Bole Arabsa

15/05/2024


🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
" ብዙ ወገኖችና ኃይለኞች አሕዛብ በኢየሩሳሌም የሠራዊትን ጌታ እግዚአብሔርን ይፈልጉ ዘንድ፥ እግዚአብሔርንም ይለምኑ ዘንድ ይመጣሉ።"
(ዘካ 8: 22)
በሪቫይቫል ጊዜ ሰዎች አይደሉም ቤተክርስቲያንን የሚሞሉት እግዚአብሔር እርሱ የሰውን ልብ በራሱ መሙላት ይጀምራል።
አዳራሾች ሳይሆኑ ራሱ እግዚአብሄር በሰው ልቦና ውስጥ ስፍራ ይኖረዋል።
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
ሪቫይቫል ክስተት አልያም ድንገተኛ ሁኔታ አይደለም። ነገር ግን አለም ሳይፈጠር በእግዚአብሄር አለም ላይ የነበረ የመለኮት አጀንዳ በምድር ላይ በሚኖሩ የእግዚአብሄርን ክብር ናፋቂዮች ሳቢያ የሚከሰት የመለኮት እቅድ ነው።
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
ሪቫይቫል ማስታወቂያ የማይፈልግበት ምክንያት ተፈጥሮአዊውና የመንፈስ ቅዱስ እሳት በባህርዩ ራሱን ከበቂ በላይ የማስተዋወቅ የታመቀ ብቃት በውስጥ ስላለው ነው። እሳት የሰዎችን እይታ እንደ ማግኔት ወደ ራሱ የመሳብ ጉልበት አለው።
★የእግዚአብሔር እሳት ማስታወቂያ አይፈልግም!!!★
★The 🔥Fire of God Doesn't need an Advertisment!!★
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
ቀዝቃዛነት ለቤተክርስቲያን አማራጭ አይደለም። የግዴታ ልትቀጣጠል ያስፈልጋል!!! እርሷ ሙሽሪት እንጂ ድርጅት አይደለችም!!!

Photos from Salvation for all nations ministries's post 14/05/2024

ስለ ኢየሱስ ለመናገር ደፋር ሁኑ!
Be bold to talk about Jesus!ꜱᴀʟɪᴠᴀᴛɪᴏɴ ꜰᴏʀ ᴀʟʟ ɴᴀᴛɪᴏɴꜱ

“እግዚአብሔር ለቍጣ አልመረጠንምና፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መዳንን ለማግኘት ነው እንጂ።”
— 1ኛ ተሰሎንቄ 5፥9

13/05/2024

ዛሬ ማታ 2.00 ላይ "መለየት " በሚል ርዕስ የ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ጊዜ ይኖረናል!!!!

ለምን እንለይ ???
ከማን እንለይ???
እንዴት እንለይ?? የሚለውን አብረን እናያለን

ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇

https://t.me/+XZYO7_jXxnZkM2U0

ተባረኩ!!!!!

11/05/2024

የደስታ መግለጫ
ዜና ሹመት!!

የኢትዮጵያ ወንጌል ማህበርተኞች ባካሄደው የሹመት ሂደት ውስጥ የ Salvation for all nations ministries vice president የሆነችው ወንጌላዊት ሩት ዳዊት የኢትዮጵያ ወንጌል ማኀበርተኞች ጠቅላይ ፀሀፊ በመሆን መሾሟን ከ ማኀበሩ የኘሬዘዳንት ቢሮ የደረሰን መረጃ ያመላክታል!!

ለአብሮ ተመራጭ የአገልግሎት አጋሮችሽ እንኳን ደስ አላችሁ እያልን መልካም የስራ ዘመንን እንመኝላችኋለን
" እጅ ለእጅ ተያይዘን የእግዚአብሔርን መንግስት በምድር እንደምናሰፋ ምሉእ እምነት አለን!!!"
ሳልቬሽን ፎር ኦል ኔሽንስ ሚኒስትሪስ!!!

10/05/2024

ታላቅ የወንጌል ስርጭት ስልጠና ከሳልቬሽን ፎር ኦል ኔሽንስ ሚኒስትሪ ጋር

ግንቦት 11 ከጠዋቱ ሶስት ሰአት ጀምሮ በ የክርስቶስ ወንጌል አለምአቀፍ ቤተክርስቲያን ቦሌ አራብሳ አጥቢያ

“ወጥተውም ንስሐ እንዲገቡ ሰበኩ፥ ብዙ አጋንንትንም አወጡ፥”
— ማርቆስ 6፥12
Healing Evangelist Ruth Dawit

02/05/2024

ወንጌል በ22 አደባባዮች

02/05/2024

የወንጌል ስርጭት
በኢትዮጵያ ወንጌል ማኅበረተኞች የተዘጋጀ
በአዲስአበባ ጎዳናዎች
“እንደ ተናገረ ተነሥቶአልና በዚህ የለም፤ የተኛበትን ስፍራ ኑና እዩ።” ማቴዎስ 28፥6

Photos from Salvation for all nations ministries's post 02/05/2024

ወንጌል በ 22 አከባቢ

19 ሰዎች ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ግል አዳኛቸው አድርገው ተቀብለዋል!!!!

“እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።”
— ኢሳይያስ 53፥5

30/04/2024

ታላቅ የወንጌል ስርጭት በ 22 እና ቦሌ አከባቢ
ረቡእ ከ8.00 ጀምሮ!!!!

“እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።”
— ኢሳይያስ 53፥5

Photos from Salvation for all nations ministries's post 28/04/2024

እግዚአብሔር በአደራ ያስቀመጠብሽን መለኮታዊ ጥሪ በጥበብ በእውቀት እየመራሽ ለእግዚአብሔር መንግስት ግንባታ አስተዋጾሽን እንደምትወጪ ተስፋ እያደረግን እግዚአብሔር በሰጠሽ እድል ተጠቀመሽ ያገኘሽውን
ጥበብ እግዚአብሔርን በመፍራት እና በማክበር ለሌሎች እንድታካፍይና እንድታገለግይ እንመኝልሻለን።
እንኳን ደስ አለሽ!

ሳልቬሽን ፎር ኦል ኔሽንስ ሚኒስትሪስ

Photos from Salvation for all nations ministries's post 26/04/2024

SFAN BOOK REVIEW
ተጨማሪ መፅሀፍት
በወንጌላዊው ሬሀይናርድ ቦንኬ የህይወት ዘመን አገልግሎት ከ 90 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎችን ኢየሱስ ክርስቶስን የህይወታቸው ጌታና አዳኝ አድርገው ተቀብለዋል ይህ ወንጌላዊ ከፃፋቸው መፅሀፍቶች ውስጥ

1.Daily fire devotional
2. Evangelism by fire
3.Taking Action
4.time is running out
5. Holy spirit
6. Faith
እነዚህ ይገኙበታል ሙሉውን መፅሀፍ በ pdf ማግኘት የምትፈልጉ የቴሌግራም ቻናላችን ሊንክ በመጫን ይቀላቀሉ 👇👇👇👇👇👇

https://t.me/+ATd__GavTilmMTA0

Photos from Salvation for all nations ministries's post 24/04/2024

SFAN BOOK REVIEW

" የእግዚአብሔር ሰው ስሚዝ ዊግልስ ወርዝና የእግዚአብሔር ሀይል,ፀሎት እንዲሁም ተአምራት " በሚል ርዕስ በ ሮበርትስ ሊያርደን የተፃፈው መፅሀፍ የዚህ ሳምንት ጥናታችን ይሆናል ሙሉውን መፅሀፍ በ pdf ማግኘት የምትፈልጉ የቴሌግራም ቻናላችን ሊንክ በመጫን ይቀላቀሉ 👇👇👇👇👇👇

https://t.me/+ATd__GavTilmMTA0

23/04/2024

መዳናችን በመወደዳችን ላይ የተመሰረተ ነው

በዮሀንስ ራዕይ ላይ ለወደደን ከሀጥያታችንም በደሙ ላጠበን ለእርሱ ከዘልአለም እስከ ዘልአለም ክብር ይሁን ተብሎ የተፃፈው እግዚአብሔር አብ ስለወደደን ብቻ ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ምድር ልኮታል የሚገባን ሆኖ ሳይሆን በመወደዳችን ብቻ የአለም መድሀኒት ለእኛ ተወልዶልናል!!!!!

ከሀጥያትና ከበደል ሊያድነን ለሀጥያታችንም ስርየት እንዲሆንልን ስጋን ለብሶ ወደ ምድር መጥቷል ለዚህም ነው የእግዚአብሔር ቃል ሲናገር እንሆ ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅንም ትወልዳለች ስሙንም ኢየሱስ ትለዋለች እርሱም ህዝቡን ከሀጥያት ያድናቸዋል የተባለለት

አሁን መልካምን እየሰራን ነው!!!
በባህሪም ትሁቶች ነን!!!!!
ታዲያ ከየትኛው በደልና ሀጥያት ነው ኢየሱስ ሊያድነን ነፃ ሊያወጣንም የተወለደው ስንል ወደ በዘፍጥረት ላይ ወዳለው የእግዚአብሔር ቃል እንመለሳለን አዳምና ሄዋን የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ በመተላለፍ በዲያቢሎስ ሽንገላና ሀሰት እግዚአብሔርን አልታዘዙም ነበር የእግዚአብሔር ቃል ሲናገር ሰውን ከተፈጠረበት አላማ ሀጥያት እንደለየው መልካምና በእግዚአብሔር ከተሰጠው የህወይወት መስመር ፈቀቅ እንዳደረገው ቃሉ ይናገራል

መንፈሳዊ ፍሬዎችን ማፍራት ሲገባው አይኖቹ ወደ ስጋ ስራ ተከፈቱ ቅዱስ መሆን ሲገባው በገባበት የሀጥያት ስር ምክንያት የረከሰ ሆነ በገላቲያ መፅሀፍ ላይ ሲናገር የስጋ ስራዎች የተገለጡ ናቸው ከዛ ውስጥ ጣኦትን ማምለክ አንዱ ነው ከእግዚአብሔር ዘወር ማለት የሰው ልጆችን ከእግዚአብሔር ከተለዩ በኋላ ያገኛቸው የሀጥያት ውጤት ነው!!!!

ቃየን በአቤል ላይ ተሰነስቶ የመግደል አቅምን ያገኘው ሀጥያት በከፈተለት በር ነው ሀጥያት በሰጠው ጉልበትና አቅም ነው
አዳም ከኤደን ገነት ከተባረረበት ሰአት ጀምሮ በዘመናት ሁሉ መካከል እግዚአብሔር አምላክ ሰውን እንደጠፋ በግ ከመፈለግ ወደኋላ አላለም ሰው ባይፈልገውም እግዚአብሔር በዘመናት መካከል ሰውን ፈልጓል ለዛም ነው በብሉይ ኪዳን ዘመን ህግን ካህናትን የሀጥያት መሸፈኛ የሚሆን መስእዋትን ህዝቤ ነው ባለው ሁሉ ፊት ያቀረበው ሰውን ወደ እርሱ ለማቅረብ ነገር ግን ይህ ድርጊት ዘመናትን ስላልሻገረ ስለ ሀጥያትም ዘላለማዊ እልባትን ለማምጣት ክርስቶስ ኢየሱስ ስጋን ለብሶ ወደምድር መጥቷል!!!!

Photos from Salvation for all nations ministries's post 18/04/2024

SFAN BOOK REVIEW

"የእግዚአብሔር ጀነራሎች"በሚል ርዕስ በሚል ርዕስ በ ሮበርትስ ሊያርዶን የተፃፈው እና አራት ክፍል ያለውን መፅሀፍ የዚህ ሳምንት ጥናታችን ይሆናል ሙሉውን መፅሀፍ በ pdf ማግኘት የምትፈልጉ የቴሌግራም ቻናላችን ሊንክ በመጫን ይቀላቀሉ 👇👇👇👇👇👇

God's Generals 1 - Why They Succeeded and Why Some Failed
God's Generals 2 - The Roaring Reformers
God's Generals 3 - The Revivalists
God's Generals 4 - The Healing Evangelists

https://t.me/+ATd__GavTilmMTA0

" የጎዳና ላይ የወንጌል ስርጭት " ፤ ክፍል አንድ 17/04/2024

https://youtu.be/rgD3K56JJhg?si=uHeT5HNaIuzzVQTt

" የጎዳና ላይ የወንጌል ስርጭት " ፤ ክፍል አንድ " የጎዳና ላይ የወንጌል ስርጭት " ፤ ክፍል አንድ ፤ አገልጋይ ወንደሰን ዘመድኩን ፣ አገልጋይ ሩት ዳዊት ፣ ወንጌላዊ ነጋ አበበ ፣ፓስተር አቢ ተካ ፤ የወጣቶች ፕሮግራምSubscribe: https://ww...

Want your place of worship to be the top-listed Place Of Worship in Kosti?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Videos (show all)

#ወንጌል #morningdevotion #TheGospel #decadeofdoubleharvest #የኢየሱስ_ምስክር #ህብረት
ወንጌል በጦር ሀይሎች አደባባይ“የእውነትን ቃል በቅንነት የሚናገር የማያሳፍርም ሠራተኛ ሆነህ፥ የተፈተነውን ራስህን ለእግዚአብሔር ልታቀርብ ትጋ።”  — 2ኛ ጢሞቴዎስ 2፥15
ኢየሱስ!!!
አማኑኤል:-ያህዌ ከእኛ ጋር
ወንጌል በ22 አደባባዮች
የታራሚዎች_ነፍስ_ለኢየሱስ በአዳማ /ናዝሬት/ማረሚያ ቤቶች በኢትዮጵያ ወንጌል ማኅበረተኞች የተዘጋጀኢሳይያስ 61¹ የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘን...
#የታራሚዎች ነፍስ ለኢየሱስ #ሚያዚያ 05 እና 06 #በአዳማ /ናዝሬት/#በኢትዮጵያ የወንጌል ማህበረተኞች የተዘጋጀለታራሚዎች የንፅህና መጠበቂያዎች አልባሳትንየትምህርት መርጃ መሳሪያዎች መፅሀ...
ኢየሱስ
ነገ ምሽት ከ 4.00 ጀምሮ ይተላለፋል ሊንኩን በመጫን ይከታተሉ!!!!የትምህርት ርዕስ:-የእግዚአብሔር ክብር
ከዚህም በኋላ ኢየሱስ ራሱ ለዘላለም ድኅነት የሆነውን የማይለወጠውን ቅዱስ ወንጌል ከፀሐይ መውጫ እስከ መጥለቂያው ድረስ በእጃቸው ላከው።”  — ማርቆስ 16፥8
“ሰውም እንደሌለ አየ፥ ወደ እርሱ የሚማልድ እንደሌለ ተረዳ ተደነቀም፤ ስለዚህ የገዛ ክንዱ መድኃኒት አመጣለት፥ ጽድቁም አገዘው።”  — ኢሳይያስ 59፥16

Telephone

Address


Kosti

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 17:00
Other Kosti places of worship (show all)
Bible Quotes Bible Quotes
英国,伦敦
Kosti, EC2

Life Is Not Easy But God Is Good

Fiat Lux Fiat Lux
Kosti

"Let there be light" is an English translation of the Hebrew יְהִי אוֹר‎ (yehi 'or) found in Genesis 1:3 of the Torah, the first part of the Hebrew Bible.

Unleashed Acts Unleashed Acts
Earth
Kosti

Seeking to live like the Acts Church today: empowered by Holy Spirit to creatively share the love of Jesus & create loving communities.

Bible Study Bible Study
伦敦
Kosti

CASA United Kingdom CASA United Kingdom
London
Kosti

� In Christ we United

God's word is light God's word is light
London
Kosti

God is good forever God is good forever
Kosti

But whosoever drinketh of the water that I shall give him shall never thirst; but the water that I shall give him shall be in him a well of water springing up into everlasting life...

الدعوة إلى الإسلام " Invitation To Islam " الدعوة إلى الإسلام " Invitation To Islam "
Kosti

Invitation To Islam as The Truth Religion