Kidist Mariam Ethiopian Orthodox Tewahdo Church Los Angeles

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Kidist Mariam Ethiopian Orthodox Tewahdo Church Los Angeles, Religious Center, 5707 Shenandoah Avenue, Los Angeles, CA.

09/11/2019

እንኻን ለአዲሱ አመት በሰላም አደረሳችሁ።አመቱን የሰላም የፍቅር ያድርግልን።በዚ አጋጣሚ በዚ ፔጅ ከዚ ቀደም በተለጠፋት አንዳንድ አላስፈላጊ ነገሮች ይቅርታ እንጠይቃለን በተለይም መምህር ተከስተን።

09/19/2018

ታላቅ የምስራች ሰበር ዜና

እንኳን ደስ አለን ሰይጣን አፈረ!!!
ለሰይጣን የሚደግፉትም አፈሩ !!!

መልአከ መንክራት መምህር ግርማ ወንድሙ ለ ሶስት አመት የትም እንዳያገለግሉ ታግደውበት የነበረው ደብዳቤ ተነስቶላቸው በዛሬው እለት መስከረም 9 / 2011 ዓ.ም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያሪክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቃነ ጳጳሳት ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት መልካም ፍቃድ አሁን በተፈጠረው ችግሮች መምህር ግርማ ያስፈልጉናል በማለት የህዝቡን ችግር በመረዳት በመላው አለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋህዶ ሁሉ በቆመችበት እየዞሩ እንዲያገለግሉ ፍቃድ ተሰጥቷቸዋል።

አገልግሎቱ መቼ እደሚጀምር እና የት ቤተክርስቲያን እንደሚጀምሩ በቅርቡ እናሳውቃችዋለን

> ኦሪት ዘፍጥረት 50 ፤ 20

07/20/2018

የተደረገልንን እናስተውላለን ግን?!
«ዘውድአለም ታደሠ»

ኢየሱስ ክርስቶስ አንድ ቀን የደቀመዛሙርቱን እግር ዝቅ ብሎ አጥቦ ሲጨርስ «ያደረግሁላችሁን ታስተውላላችሁን?» ብሎ ጠየቃቸው!!
ሰው ከተደረገለት ይልቅ የተደረገበት ላይ ትኩረት ያደርጋል። ውለታ ፈጥኖ ይረሳል ቂምና በቀልን ልቡ ላይ ያትማል። የሰጡትን ይቀበላል። ነገር ግን አንዳንዴ ምን እንደተሰጠው እንኳ አያውቅም!! ለዚህ ይመስለኛል ኢየሱስ የተደረገላችሁን ታስተውላላችሁን? ብሎ የጠየቀው!!

ስለዶክተር አብይና የትግል ጓዶቹ ሳስብ እውነት ግን እኛ የተደረገልን ምን እንደሆነ ገብቶናል? ብዬ አስባለሁ!! ...እኔ ስለዶክተር አብይና አብረውት ለለውጥ ስለቆሙ ጓዶቹ ሳስብ የሚሰማኝ ይሄ ነው .....

ኢትዮጵያ መፈራረሷን አምነን ለቅሶ ተቀምጠን በነበረ ሰአት ፣ ዘረኝነት አየሩን በክሎት ከዳር እስከዳር ሐገር በግጭት ስትናጥ፣ ኢትዮጵያ ብሎ መጥራት አሳፋሪ የሆነበት ዘመን መጥቶ ሐገር ስትጨነቅ፣ ኢትዮጵያ የሚለውን ስም ከወደቀበት አንስተው በኩራት የሚጠሩ ወጣት መሪዎች ከኦህዴድ ውስጥ ብቅ አሉ!! በእንቦጭ ስበብ የኦሮሞ ወጣቶችን ወደባህርዳር አዝምተው ጉዟቸውን በፍቅር ጀመሩ!! አየሩን ሁሉ በኢትዮጵያ ስም እንደጢስ ሞሉት ... ልባችን በፍቅር ነደደች!! ደነገጥን!! የምናየው ህልም ይሁን ፊልም ግራ ገባን!! እነለማ፣ እነአብይ፣ እነአዲሱ፣ እነገዱ ከህዝብ ጎን ሲቆሙ የዘመናችን ጎልያዶች በፍርሃት ራዱ!! ህዝቡ ተስፋ በቆረጠባት ኢትዮጵያ ዳግም ተስፋ ያደርግ ጀመር!! ጠብመንጃና ባለጠብመንጃ በዚያ እነዶክተር አብይና ህዝብ በዚህ ረድፍ ሆነው ግጥሚያ ጀመሩ .... በመጨረሻም ከህዝብ ጎን የቆሙት አሸነፉ!

ዶክተሩ በመጀመሪያ የፓርላማ ንግግሩ ከሰላሳ ግዜ በላይ ኢትዮጵያን በመጥራት የኢትዮጵያኒዝም ጉዞውን ቀደሰው!! ህዝብ ግራ ተጋባ!! ተቃዋሚዎች እየጠረጠሩ ተገረሙ!! ብዙዎች «እውነት ዶክተር አብይ ይከዳን ይሆን?» ብለው ሲተክዙ፣ ብዙዎች «የወያኔ ሎሌ ነው። ምንም የማድረግ አቅም የለውም» ብለው ተስፋችንን ሊያከስሙ ሲፍጨረጨሩ፣ ዶክተር አብይ ግን በመጀመሪያው ቀን የገባውን ቃልኪዳን ስጋ እያለበሰ ለህዝቡ ማሳየት ጀመረ .....

የፖለቲካ እስረኞችን ጠራርጎ ፈታ!! ኢህአዴግን ለመጣል ጠብመንጃ ያነሳው አንዳርጋቸው ፅጌን ሳይቀር በመፍታት ቤተመንግስት ውስጥ በክብር ተቀበለው!! የዋልድባ መነኮሳት ፣ የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊዎች ፣ ጋዜጠኞች፣ ምሁራን፣ ዶክተሮች ፣ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች .... በሙሉ ተጠራርገው ተፈቱ!!!!!

ለፓርቲያቸው ባላቸው ታማኝነት ብቻ ዙፋን ላይ የተወዘቱ ኤክስፓይርድ ዴታቸው ያለፉ ባለስልጣኖችን በማንሳት አቅምና ችሎታ ባላቸው ምሁራን ተተኩ!!

ውጭ በስደት ያሉ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችና ተቃዋሚዎች በይፋ ወደሐገራቸው እንዲገቡ ጥሪ ቀረበላቸው። የውጭ ሚዲያዎች ወደሐገር ውስጥ እንዲገቡ ጥሪ ተደረገ፣ በግፍ የተፈረደባቸው እነብርሃኑ ነጋና ጃዋር አህመድን የመሳሰሉ ፖለቲከኞች ክሳቸው ሙሉ ለሙሉ እንዲነሳ ተወሰነ!

ሚዲያዎች ነፃ ሆኑ!! በኢሳትና በኢቲቪ መሃከል ያለው ልዩነት ጠበበ፣ በየማረሚያ ቤቱ በመንግስት ሲከወኑ የቆዩ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በግልፅ ህዝቡ ጋር እንዲደርሱ ተደረገ!!

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በይፋ መንግስት አሸባሪ እንደነበር አመኑ!! (ምናልባት በአለም የመጀመሪያው መሪ ናቸው የሚመሩትን መንግስት አሸባሪ ያሉ!)

ከግማሽ ምእተአመት በላይ የፈጀ ከመቶ ሺ በላይ ሰዎች የሞቱበት ፣ መቶ ሺዎች የተፈናቀሉበት፣ በመጎዳዳት ፖለቲካ ላይ የተመሰረተውን የኢትዮ ኤርትራ ታሪክ በመቶ ቀን ብቻ ሙሉ ለሙሉ ለወጡት!!! በመቶ ቀን ብቻ!! ይሄን በታሪክ ተመዝግቦ ዘልአለም የሚያስወድሳቸው ተግባር ፈፀሙ!! በመቶ ቀን ብቻ ኢትዮጵያ የኤርትራን አየር መንግድ ሃያ ፐርሰንት ገዛች። ቦርደሩ ለህዝብ ክፍት ሆነ። ለአመታት የተነፋፈቁ ወንድማማች ህዝቦች ለመጀመሪያ ግዜ ተገናኙ!! ለዘመናት ሲጠየቅ የነበረው የአሰብ ጉዳይ ምላሽ አገኘ!! ይህ ሁሉ በመቶ ቀን ብቻ!!!

ከሱዳን ፣ ከግብፅ፣ ከጅቡቲ፣ ከሶማሊያ፣ ጋር ያለን ግንኙት የበለጠ ጠነከረ!! ዘልአለም የአለም መሳቂያ እንዳልሆንን ፣ ዛሬ አለም ስለኢትዮጵያ መልካም ማውራት ጀምሯል። የአለም ሚዲያዎች ሁሉ ስለኢትዮጵያ በጎ መፃኢ እድል ተነበዩ!!

ህዝብ በታሪኩ ለመጀመሪያ ግዜ ለመሪው አደባባይ በመውጣት ድጋፉን ገለፀ!! ለመጀመሪያ ግዜ ህዝብ የማይፈራቸውን ግን የሚያፈቅራቸውን መሪ አገኘ!! በአይዲዮሎጂ የማይገናኙ የተለያየ አቋምና አመለካከት ያላቸው ሰዎች ለመጀመሪያ ግዜ በአንድ ድምፅ ይናገሩ ጀመር!!

እነዚህና እነዚህን መሰል ቆጥረን የማንጨረሳቸው ክስተቶች የተፈፀሙት አራት ወር ባልሞላ ግዜ ውስጥ ነው!! በመቶ ቀን ብቻ!!!!!!

አንተ ህዝብ!! የተሰጠህን አመስግን!! ይህን ያሳዩህን መሪዎች አክብር!! ትናንትህን ዞር ብለህ ተመልከት!! ከሶስት ወር በፊት እየተገረፍክ፣ እየተሰደብክ፣ እየተረገጥክ፣ እየተገደልክ፣ በሃሰት እየተከሰስክ፣ ትኖር ነበር!! ለሃያሰባት አመት ያልተመለሰልህ ጥያቄ በሶስት ወር ተመልሶልሃል!! ዝቅ ብለህ አመስግን! በሆነው ባልሆነው አታለቃቅስ!! የእግዚሀርን አይን አትውጋ!! ምስጋና ቢስ፣ ውለታ ቢስ፣ አትሁን!! ክብረቢስ አትሁን!! የተደረገልህን በረከት ቁጠር!! ሰው አይሳሳትም አልልህም ግን ከተደረገልህ አንፃር የተደረገብህ ኢምንት ነው!! ሐገር መምራት በግ መጠበቅ አይደለም። መሪዎች ይሳሳታሉ ፣ስህተታቸውን ያርማሉ፣ ሁኔታህኮ ሰባሰባት ቢሊዮን ብርና ኮንዶሚኒየም ጠፋ ሲሉህ ጭጭ ብለህ የኖርክ አትመስልም!!

ህሊና ይኑርህ!! አ ት ጨ ማ ለ ቅ!!

አንዲት ተዋህዶ ኦርቶዶክስ ናት (andit tewahdo orthodox nat) 02/11/2018

*ትምህርተ_ፆም_በሊቃውንት*

በዚህ ጽሑፍ ፆምን አስመልክቶ የቅዱሳን አባቶችን አስተምህሮ እንመለከታለን

አንድ የገዳም አበምኔት አንድ ወቅት አባ ጳይመን የሚባሉትን አባት
“እግዚአብሔርን መፍራት እንዴት ገንዘቤ ማድረግ ይቻለኛል” ብለው
ይጠይቋቸዋል፡፡ እሳቸውም ሲመልሱ “እንዴት ሰው በላመና በጣፈጠ
መብልና መጠጥ ሆዱን እየሞላ እግዚአብሔርን መፍራት ገንዘቡ
ሊያደርግ ይችላል? ስለዚህም ጦም እግዚአብሔርን ወደመፍራት
ይመራል፡፡ የጦም የመጨረሻ ግቡ እግዚአብሔርን ወደመፍራት
ማምጣት ነው” ብለው ይመልሱላቸዋል፡፡
አንድ ወቅት አንድ ጠዋሚ በጦም ወቅት ማልዶ ይርበዋል፡፡ እናም
ከሦስት ሰዓት በፊት ላለመመገብ ከፍላጎቱ ጋር ይሟገታል፡፡ ሦስት
ሰዓትም ሲሆን እንደምንም ብሎ እስከ ስድስት ሰዓት ሊቆይ ይወስናል፡፡
ስድስት ሰዓት ደርሶ ሊመገብ ማዕዱን በቆረሰ ጊዜ እንደገና ለራሱ እስከ
ዘጠኝ ሰዓት ልቆይ ብሎ በመናገር ምግቡን ከመመገብ ይከለከላል፡፡
ዘጠኝ ሰዓት ላይ ጸሎቱን አድርሶ ሊመገብ ሲል ሰይጣን ልክ እንደጭስ
ከሰውነቱ ሲወጣ ታየው ወዲያው ረሃቡ ጠፋ፡፡
+
ጾም መድኃኒት ናት ። አወሳሰድዋን በትክክል ላላወቁ ግን ጥቅም
የላትም ። ይህችን መድኃኒት የሚወስድ ሰው በየስንት ሰዓቱ
እንደምትወሰድ በምን ያህል መጠን እንደምትዋጥ ፣ ለምን ዓይነት በሽታ
እንደምትጠቅም ፥ በየተኛው ወራትና በየተኛው የአየር ኹናቴ
እንደምትወሰድ ፥ ከእርሷ ጋር የሚዱደና የማይሔዱ ምግቦችን
እንዲሁም ሌሎች ከእርሷ ጋር የማይስማሙ ነገሮችን ለይቶ ማወቅ
አለበት ።
እነዚህን ግምት ውስጥ አስገብተን የማንወስዳት ከኾነ ግን ከጥቅሟ
ይልቅ ጉዳቷ ያመዝናል ።አንድ በሐኪም የታዘዘልንን የደዌ ዘሥጋ
መድኃኒት በትክክል ከወሰድነው ከሕመማችን እንፈወሳለን ፤ የነፍሳችንን
ደዌ ለመፈወስ ብለን በምንወስደው መድኃኒት ደግሞ ከዚህ የበለጠ
መጠንቀቅ ይኖርብናል ።
ጾም ኹለመናችንን የምንለውጥባት መሣርያ ናት ። ምክንያቱም የጾም
መሥዋዕት ማለት ከምግብ ብቻ መከልከል አይደለምና ፤ ከኃጢአት ሁሉ
መከልከል እንጂ ። ስለዚህ እየጾምኩ ነው እያለ ራሱን ከምግብ ብቻ
የሚከለክል ሰው ቢኖር እርሱ ጾምን እያቃለለና እያጥላላ ነው ።
እየጾማችሁ ነውን ? እንግዲያውስ መጾማችሁን በተግባር አሳዩኝ ። "
እንዴት አድርገን እናሳይህ? " ትሉኝ ይሆናል ። እኔም እንዲህ ብዬ
እመልስላችኋለሁ ፦ ድኻው እርዳታችሁን ፈልጎ እንደ ሆነ ቸርነትን
አደረጉለት ። የጠላችሁትን ሰው ካያችሁት ፈጥናችሁ ታረቁ ።
ባልጀራችሁ ተሳክቶለት ስታዩት በእርሱ ላይ ቅናት አትያዙ ። ቆንጃጅትን
ስታዩ በዝሙት ዐይን አትመኙ ።እንዲህ እንዲህ እያደረጋችሁ በትክክል
መጾማችሁን አሳዩኝ ። ...
ይቆየን ፥ ከቅዱሱ አባታችን በረከት ይክፈለን ።
" ጾም " ( በ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ሰማዕትነት አያምልጣችሁ " በ ገብረ እግዚአብሔር ኪደ)
+
እየጦምክ ነውን? ለተራበ አብላ ፣ለተጠማም አጠጣ፣ ሕመምተኞችን
ጎብኝ፣ የታሰሩትን ጠይቅ፣ በመከራ ላሉት እራራላቸው፣ በጭንቀት
ወድቀው የሚያለቅሱትን አጽናናቸው፣ ርኅሩኅ፣ ትሑት፣የዋህ፣ ሰላማዊ፣
አዛኝ፣ይቅር ባይ፣ እውነተኛ እና ታማኝ ሁን፡፡ እንዲህ ከሆንክ
እግዚአብሔር ጦምህን ይቀበልልሃል፡፡ ስለንስሐም ብዙ የንስሐ ፍሬን
ይሰጥሃል፡፡ ጦም ለነፍስ ምግብ ነው፡፡
ቁጣ መቼም ቢሆን የሚመከር አይደለም፤በተለይ በጦም ሰዓት ከቁጣ
መራቅ ተገቢ ነው፡፡ ትሕትናንና ፣የዋሃትን ገንዘብህ አድርግ፤ክፉ
ፈቃዶችንና አሳቦችን ተቃወማቸው፤ ራስህን መርምር በየእለቱ ወይም
በሳምንት ውስጥ ምን መልካም እንደሠራህ አእምሮህን ጠይቀው፡፡
እንዲሁም ምን ስሕተትን ፈጽመህ እንደነበርና ስሕተትሕን ደግመህ
እንዳትፈጽም የመፍትሔህ እርምጃዎች ምን ሊሆኑ እንዲገባቸው
አሰላስል፡፡ ጦምህ እንዲህ ሊሆን ይገባዋልና፡፡
+
ምግብ ሰውነትን እንደሚያሰባ እንዲሁ ጦም ነፍስን ከሥጋ አስተሳሰብ
ተላቃ ወደ ላይ በመነጠቅ ሰማያዊ ነገሮችን ለመመርመርና ከምድራዊ
ደስታ ይልቅ እጅግ ግሩም የሆነ ደስታን ለማግኘት ጥንካሬን ይሰጣታል፡፡
አርባ ቀን ሙሉ ከምግብ ተከልክዬ ጦምኩ አትበለኝ፡፡ ይህንና ያንን
አልበላሁም ወይንም ከአፌ አልገባም አትበለኝ፡፡ እኔ ይህንን ካንተ
አልሻም፣ ነገር ግን ከቁጣ ርቀህ ታጋሽ መሆንህን አሳየኝ፤ ከጭካኔህ
ተመልሰህ አዛኝ ወደመሆን እንደመጣህ አሳየኝ፡፡ ነገር ግን ቁጣ
የሞላብህ ከሆነ ስለምን ሥጋህን በጦም በከንቱ ትጎስማታለህ ?
ሰዎችን ሁሉ የምትጠላና ስስታም ከሆንክ ለአንተ ከምግብ ተከልክለህ
ውሃ ብቻ መጠጣትህ ምን ትርፍ ያመጣልሃል?
ጦም እጅግ ግሩም የሆነ ነገር ነው፡፡ ኃጢአታችንን እንደማይጠቅም
አረም ከውስጣችን ይነቅለዋል፡፡ እውነተኛው የጽድቅ ተክልም
በውስጣችን ልክ እንደ አበባ እንዲያብብ ይረዳዋል፡፡ (ቅዱስ ባሲልዮስ)
ጸሎት፣ ጦም ፣ትጋህ ሌሊት እና ሌሎችም አንድ ክርስቲያን
የሚተገብራቸው ክርስቲያናዊ ተግባራት ምንም መልካሞች ቢሆኑ
የክርስቲያናዊ ሕይወት ግቦች ግን አይደሉም፡፡ ነገር ግን ወደ
ትክክለኛው ክርስቲያናዊ ሕይወት ለመድረስ የሚያገለግሉን መንፈሳዊ
ትጥቆች ናቸው፡፡ትክክለኛው የክርስቲያን ግብ መንፈስ ቅዱስ በእርሱ
ሰውነት ውስጥ ሥራ እንዲሠራ በመፍቀድ የመንፈስ ቅዱስ ፍሬዎችን
አፍርቶ መገኘት ነው፡፡በዚህ ምድር የመንፈስ ቅዱስ ፍሬዎች ማፍራት
እስካልቻልን ድረስ የእግዚአብሔርን መንግሥት መውረስ አይቻለንም፡፡
(ቅዱስ ሱራፊ)
+
የአዋጅ ጦም ሲገባ መንፈሳዊ የበጋ ወራቱ እንደገባ ልብ እንበል፡፡
ስለዚህም የጦር መሳሪያችንን እንወለውለው ከእርሻቸው አዝመራውን
የሚሰበሰቡትም ገበሬዎች ማጭዳቸውን ይሳሉ፤ ነጋዴዎችም በከንቱ
ገንዘባቸውን ከማባከን ይከልከሉ፣ መንገደኞችም ወደ እግዚአብሔር
መንግሥት ለመግባት መንገዳቸውን ያቅኑ፡፡ ወደ እግዚአብሔር
መንግሥት የምትወስደው ጎዳና ቀጭንና ጠባብ ናትና በጥንቃቄ
እያስተዋላችሁ ተጓዙ፡፡
እንዲያው በልማድ ሰዎች እንደሚፈጽሙት ዓይነት ጦም ትጦሙ ዘንድ
አልመክራችሁም፡፡ ነገር ግን ከምግብ ስለምንከለከልባት ጦም ብቻ
ሳይሆን ከኃጢአት ስለምንከለከልባት እውነተኛይቱ ስለሆነችው ጦም
እጽፍላችኋለሁ፡፡ ጦም በባሕርይዋ በሕግ ካልተመራች ለሚተገበሩዋት
ሰዎች ዋጋን አታሰጥም፡፡ ስለዚህም ጦምን ለመጦም ስንዘጋጅ የጦም
ዘውድ የሆነውን ነገር መዘንጋት የለብንም፡፡ ስለዚህ ስለምን ያ
በእግዚአብሔር ቤተመቅደስ ደጅ ሆኖ ጸሎቱን ያደረሰው ፈሪሳዊ
ከእግዚአብሔር ዘንድ ስለጦሙ አንዳች ዋጋ ሳያገኝ በባዶው እጁ
እንደተመለሰ መረዳት ተቀዳሚ ተግባራችን ሊሆን ይገባዋል (ሉቃ.
፲፰፥፱-፲፬(18፡9-14))፡፡ ቀራጩ አልጦመም ነገር ግን ጸሎቱ
ተሰምቶለታል፡፡ ጦም ሌሎች አባሪ የሚሆኑ መልካም ሥራዎች
ካልታከሉበት በቀር ልክ እንደዚኛው ፈሪሳዊ ዋጋ አያሰጠንም፡፡
+
ጦም ማለት መድኃኒት ማለት ናት፡፡ እንደ ሌሎቹ መድኃኒቶች ሁሉ
ጦምን እንዴት እንደሚጠቀምበት የሚያውቅ ሰው ዋጋ ያገኝበታል፡፡
በጥበብ ላልተጠቀመበት ሰው ግን የማይረባና የማይጠቅም
ይሆንበታል፡፡ ከጦም የሚገኘው ክብር ከምግብ በመከልከላችን
ምክንያት የምናገኘው ብቻ አይደለም፡፡ ከኃጢአት ሥራዎችም ፈጽመን
በመከልከላችን ምክንያት የምናገኘው ክብር ጭምር ነው ፡፡ ጦም
ሰይጣን ወደ እኛ እንዳይቀርብ እንደጋሻ የሚያገልግለን መሣሪያ ነው፡፡
ነገር ግን በጦም ሰዓት ኃጢአትን ፈቅደን የምንሠራት ከሆነ ሰይጣን
አጥሩን ጥሶ እንዲገባና በእኛ ላይ እንዲሠለጥን ምክንያት እየሆንነው
ነው፡፡ ጦማችን ከምግብ በመከልከል ብቻ የተወሰነ ከሆነ ጦምን
እናስነቅፋታለን፡፡
እየጦምክ ነውን ? መጦምህን በሥራህ ገልጠህ አሳየኝ፡፡ ድሃው
እርዳታህን ፈልጎ እንደሆነ ቸርነትን አድርግለት፡፡ ጠላት ያደረግኸውን
ካየኸው ከእርሱ ጋር ፈጥነህ ታረቅ፡፡ ጓደኛህ ተሳክቶለት ካየኸው
በእርሱ ላይ ቅናት አይደርብህ፡፡ አፍህ ብቻ አይጡም ዐይንህም
ጆሮህም እግርህም እጅህም የሰውነትህ ሕዋሳቶች ሁሉ ክፉ ከማድረግ
ይጡሙ፡፡
+
እጆችህ ከዝርፊያና ከሕግ ውጪ ለመክበር ሲባል ትርፍን ከማጋበስ
ይጡሙ፡፡ እግሮችህ የኃጢአት ሥራን ለመፈፀም ከመፋጠን ይጡሙ፡፡
ዐይኖችህም ውጫዊ በሆነ ውበት ምክንያት ከመቅበዝበዝ ይጡሙ፡፡
የሚታዩ ነገሮች ለዐይን ምግቦች ናቸው፡፡ ነገር ግን ከእግዚአብሔር ሕግ
ጋር የሚጣረሱ ምልከታዎች ጦምን ያፈርሳሉ፡፡ነፍስንም እንድትነዋወጥ
ያደርጉአታል፡፡ የምናያቸውን ነገሮች ከእግዚአብሔር ሕግ ጋር
የሚስማሙ ከሆኑ ጦማችንን ያስጌጡዋታል፡፡ በጦም ምክንያት በጦም
ሰዓት መመገብ የተከለከሉትን ምግቦች መመገብ የሚያስነቅፍ ከሆነ ፤
እንዴት ታዲያ በዐይናችን እንድንመለከተው በሕግ የተከለከልነውን ነገር
መመልከታችን ይበልጥ አያስነቅፈን ? ምግብን ከመብላት
ተከልክለሃልን? እንዲሁ ለሰውነትህ ጎጂ የሆኑ ነገሮችን በዐይንህም
በጆሮህም ከመመገብ ተከልከል፡፡ ጆሮ የምትጦመው ለኃጢአት
ከሚጋብዙ ክፉ ወሬዎችና ሐሜትን ከመስማት ነው፡፡ “ሐሰተኛ ወሬን
አትቀበል ሐሰተኛ ምስክርም ትሆን ዘንድ ከኃጢአተኛ ጋር እጅህን
አታንሣ፡፡”እንዲል(ዘጸአ.፳፫፥፩(23፡1))
አፍህም ከከንቱ ንግግር ይጡም ፡፡ ከአሣና በጦም ሰዓት መመገብ
ከተከለከልናቸው የፍስክ ምግቦች ተከልክለን ወንድሞቻችንንና
እኅቶቻችንን በክፉ ቃላችን ሕሊናቸውን የምናቆስልና በሐሜት ሥጋቸውን
የምንበላ ከሆነ ከጦማችን ምን ዋጋን እናገኛለን? ክፉ ተናጋሪ
የወንድሙን አካል ያቆስላል ሥጋውንም ይበላል፡፡ ስለዚህም ቅዱስ
ጳውሎስ ይህን አስመልክቶ እጅግ የሚያስደነግጥ ንግግርን ተናገረ
“ሕግ ሁሉ በአንድ ቃል ይፈጸማልና እርሱም፡- ባልንጀራህም እንደ ራስህ
ውደድ የሚል ነው፡፡ ነገር ግን እርስ በእርሳችሁ ብትነካከሱና ብትበላሉ
እርስ በእርሳችሁ እንዳትጠፋፉ ተጠንቀቁ፡፡(ገላ.፭፥፲፭(5፡15))ብሎ
አስጠነቀቀን፡፡
+
ስለታሙ የሐሜት ጥርስህ የሚያርፈው በወንድምህ ሥጋ ላይ ሳይሆን
ነፍስ ላይ ነው፡፡ በዚህም ጥርስህ ወንድምህን በእጅጉ ትጎዳዋለህ፡፡
እንዲህ በማድረግህ አንተም እርሱንም ሌሎችንም ብዙ ሺህ ጊዜ
ትጎዳቸዋለህ፡፡ በሐሜትህ አንተን የሚሰማህ ባልንጀራህ የሐሜት
ተባባሪ ይሆናል፡፡ በዚህም ምክንያት እርሱንም በደለኛ ታደርገዋለህ፡፡
እርሱም በእርሱ ላይ ከነገሠበት ኃጢአት የተነሣ ለሌላ ለወዳጁ ምን
መርጦ ማውራት እንዳለበት ሳያውቅ ከሐሜተኞች ጎራ ይቀላቀላል፡፡
እንዲህ ዓይነት ሰው ጻድቅ ልንለው እንችላለንን? እንዲህ ዓይነት ሰው
በመጦሙ ትልቅ የጽድቅ ሥራን እንደፈጸመ ቆጥሮ ይኩራራል፡፡ ሰዎችን
ወደ ኃጢአት እየመራ ትልቅ ሥራን እንደሠራ ሰው ራሱን በከንቱ
ያስኮፍሳል፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን ሊታይ የሚገባው ትልቁ ቁም ነገር
ስለቤተክርስቲያን ጥቅም ሲባል የእንዲህ ዓይነቱን ሰው ንግግር
ከመስማት መከልከል እንደሚገባ ነው፡፡ ምክንያቱም የዚህ ሐሜተኛ
ወሬ እርሱን ብቻ ኃጢአተኛ የሚያሰኝ ጉዳይ ሳይሆን ቤተክርስቲያንንም
ጭምር የሚያሰድብ ነውና፡፡
ስለዚህ በጦም ሰዓታችሁ ጊዜም ይሁን አይሁን ሦስት ነገሮችን
በሕሊናችሁ ትይዙ ዘንድ እመክራችኋለሁ፡፡ እነርሱም ክፉ ከመናገር
መከልከልን፣ ማንንም ሰው እንደጠላት ከማየት መቆጠብንና እንደልምድ
አድርጋችሁ ከያዛችሁት መሐላ ትርቁ ዘንድ እመክራቸኋለሁ፡፡
በአጨዳ ላይ ያለ ገበሬ እህሉን ከእርሻው ላይ በአንዴ እንዳይሰበስብ
ነገር ግን ጥቂት በጥቂት እንዲሰበስብ እኛም እነዚህን ምክሮች
ተግባራዊ በማድረግ በዚህ የጦም ወቅት ልንለማመዳቸው እና
መልካም ልምዶቻችን ልናደርጋቸው ይገባናል፡፡ እንዲህም በማድረጋችን
በቀላሉ መንፈሳዊ ጥበብን ገንዘባችን ማድረግ ይቻለናል፡፡ በዚህም
ዓለም ሳለን መልካም ተስፋ ያለውን አዝመራ እናፈራለን፡፡በሚመጣውም
ዓለም በክርስቶስ ፊት ያለፍርሃት በደስታ ተሞልተን እንድንቆም
ይረዱናል፡፡
+
ጦም የጤንነት እናት፣ የፍቅር እኅት፣ የትሕትና ወዳጅ ናት፡፡ ሕመሞች
አብዛኛውን ጊዜ ያለቅጥ ከመመገብ የሚመነጩ ናቸው፡፡ (ቅዱስ
ዮሐንስ አፈወርቅ)
ከምግባራት ሁሉ ታላቁ ጸሎት ነው ነገር ግን የእርሱ መሠረቱ ጦም
ነው፡፡የምንጦምበት ምክንያት ርኩስ የሆነውን የሰይጣንን መንፈስ
በነፍሳችን ውስጥ እንዳያድር ለመጠበቅ ነው፡፡ ሥጋችንን ለጦም
ባስገዛነው ጊዜ ነፍሳችን ነፃነትን፤ ጥንካሬን ሰላምን ፣ንጽሕናን
እንዲሁም እውቀትን ለመለየት እንድትበቃ ትሆናለች፡፡ (ጻድቁ ዮሐንስ
ዘክሮስታንድ)
እውነተኛ ጦዋሚ ራሱን ከክፉ ምግባራት የከለከለ፤ ከንቱ የሆኑ
ንግግሮችን ከመናገር የተቆጠበ፣ ሐሰትን የማይናገር፣ ሐሜተኛ ያልሆነ፣
በማንም ላይ የማይፈርድ፣ሽንገላን የማይወድና እኒህንም ከመሰሉ
ነገሮች ራሱን የተጠበቀ ፣የማይቆጣ፣ የማይበሳጭ ፣ተንኮለኛ ያልሆነ ፣
ቂመኛ ያልሆነና፣ እነዚህን ከመሳሰሉ ክፋቶች ሁሉ የራቀ ሰው ነው፡፡
ሕሊናህ ኃጢአትን ከማሰብ ይጡም፡ አእምሮህም ኃጢአትን
ከማስታወስ ይከልከል፡፡ ክፉን ከመመኘት ሁሉ ጡም፡፡ ዐይኖችህ ከንቱ
የሆኑ ነገሮችን ከመመልከት፣ ጆሮህም ከንቱ ከሆኑ ዘፈኖችና
ከሐሜተኞች ሹክሹክታዎች ጠብቅ፡፡ አንደበትህ ከሐሜት፣ በሌላው ላይ
ከመፍረድ ፣ከስድብ፣ ከውሸት ፣ከማታለል፣ከሽንገላ ንግግሮች እንዲሁም
ከማይጠቅሙና አጸያፊ ከሆኑ ቃላት ይጡሙ፡፡ እጆችህም ሰውን
ከመግደልና የሌላውን ንብረት ከመዝረፍ ይጡሙ፡፡ እግሮችህም
ኃጢአትን ለመፈጸም ከመሄድ ይጡሙ፡፡ ከክፉ ተመለስ መልካምንም
ፈጽም፡፡ (ቅዱስ ኤፍሬም)
+
ጦም ምን እንደሚያደርግ ትመለከታለህን? ሕመምን ይፈውሳል
፣አጋንንትን ያስወጣል፣ ክፉ አሳቦችን ከአእምሮ ያስወግዳቸዋል፣
ልብንም ንጹሕ ያደርጋታል፡፡ አንድ ሰው በክፉ መንፈስ የተያዘ ቢሆን
እንዲህ ዐይነት መንፈስ በጦምና በጸሎት እንደሚወጣ ያስተውል፡፡
ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ይህ ዓይነት ግን ከጸሎትና
ከጦም በቀር አይወጣም” እንዳለው (ማቴ. ፲፯፥፳፩(17፡21)) (ቅዱስ
ቲክሆን)
የአርባ ቀን ጦም የሥጋ ፍትወታትን ይገድላቸዋል፣ቁጣንና ብስጭትን
ከሰውነታችን ያስወግዳቸዋል፣ ከሆዳምነት ከሚመነጩ የትኞቹም
ነገሮች ሁሉ ነፃ ያወጣናል፡፡ በበጋ ወራት ፀሐይ ከነሙሉ ኃይሉዋ
እንድትወጣና ምድርንም በሙቀቱዋ እንደምታግል በላዩዋም የበቀሉ
አትክልቶችን እንደምታደርቅ፤ ከሰሜን የሚነፍሰውም ነፋስ የደረቁትን
ሳሮች እንደሚጠርጋቸው፤ እንዲሁ በጦም ወቅትም አብዝቶ በመመገብ
የበቀሉትን የሥጋ ፍትወታት ይወገዳሉ፡፡ (ቅዱስ አትናቴዎስ)
ቅዱሳን ጠዋሚዎች ጽኑ ወደሆነው የጦም ሥርዓት የገቡት ወዲያው
አይደለም፡፡ በጥቂት ምግብ ወደ መጥገብ የመጡት ቀስ በቀስ ነው፡፡
እነዚህ ቅዱሳን ኃጢአትን ፈጽመው አያውቋትም፡፡ ሁልጊዜ ለመልካም
ሥራ እንደተፋጠኑ ነው፡፡ በእነርሱ ዘንድ ሕመም አይታወቅም
እድሜአቸውም ከሰው ሁሉ በተለየ የረዘመ ነው፡፡ (ቅዱስ አግናጢዎስ)
ጦም የሰውን እድሜ አያሳጥርም ፣ ቅዱስ ቄርሎስ ዘአንኮራይት በ108
እድሜው አረፈ፡፡ ቅዱስ እንጦስም 105 ዓመት ሙሉ ኖሮአል፡፡ ቅዱስ
መቃርስ ዘእስክንድሪያ የኖረበት እድሜ 100 ዓመት ነበር ፡፡ (ቅዱስ
አውግስጢኖስ)
አርባውን ቀን መጦምን ቸል አትበሉ፡፡ ምክንያቱም ክርስቶስን
የምንመስልበት ሕይወት ከዚህ ጦም እናገኛለንና፡፡ (ቅዱስ እንጦስ)
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ለዘበቅዱሳኒሁ ይሴባሕ ይእዜኒ ወዘልፈኒ
ወለዓለም ዓለም አሜን፡፡ ወአሜን ለይኩን ለይኩን፡፡
ምንጭ: አንዲት ተዋህዶ ኦርቶዶክስ ናት
http://zemiad.blogspot.co.ke/2013/?m=1
፠፠፠፠
ቀደምት ሊቃውንት ሁለት ዓይን የተሰጠን በአንዱ የራሳችን በሌላው
የሌላውን ለማየት ነው፡፡ ሁለት ጆሮ የተሰጠን በአንዱ የራሳችንን
በሌላው የሌላውን ለመስማት ነው፡፡ ሁለት እጅ የተሰጠን በአንዱ
ለመስጠት በሌላው ለመቀበል ነው፡፡ ሁለት እግር የተሰጠን በአንዱ
ወደራሳችን በሌላው ወደ ሌላው ለመሄድ ነው ይሉ ነበር፡፡
፳፩ ፳፩ ፳፩ ፳፩ ፳፩
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የሲኦል ደጆች አይችሏትም
ቤተክርስቲያን አትታደስም!
የሐዋርያት ጉባኤ ስለሆነች ስለአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላም
እንማልዳለን!
(መጽሐፈ ሚስጢር)
የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን
መላእክት ተራዳኢነት፣ የጻድቃን፣ የሰማዕታት፣ የቅዱሳን ሐዋርያት፣
የቅዱሳን አበው መነኮሳት፣ የቅዱሳት አንስት፣ የደናግላንና የቅዱሳን ሁሉ
ምልጃና ቃል-ኪዳናቸው ባለንበት ከሁላችን ጋር ይሁን!!!
†† † † ††
ለአባ ሕርያቆስ ፤
ለቅዱስ ኤፍሬም ፤
ለቅዱስ ያሬድ ፤
ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
ለአባ ይስሀቅ
የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤
ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ፤ አሜን!!!

†† † † ††
ከዋክብት የሚያመሰግኑት
በስማቸውም የሚጠራቸው:
የፀጋው ብዛት የማይታወቅ
ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ለሐዋሪያት
እንዲሁም ለቀደሙ አባቶቻችን ምሥጢሩን እንደገለጽክላቸው ለእኛም
ግለጽልን።

አሜን አሜን አሜን!!!
†† † † ††
ወ ስ ብ ሐ ት ለ እ ግ ዚ አ ብ ሔ ር
ወ ለ ወ ላ ዲ ቱ ድ ን ግ ል
ወ ለ መ ስ ቀ ሉ ክቡር

አንዲት ተዋህዶ ኦርቶዶክስ ናት (andit tewahdo orthodox nat)

02/10/2018
02/07/2018

ከአባታችን ከመላአከ መንክራት ግርማ ወንድሙ በአሁን ሰአት በእርሳቸው ላይ ለተነሱት ተኩላወች የተላለፈ ወቅታዊ መልእክት! ሼር አድርጉት! https://youtu.be/jidCN5w7IbA

02/01/2018
01/31/2018

?

" #ጉድጓድ ተቆፍሮ ብሸኝም ወደ አፈር፣
አብቅቶ መኖሬ ብሞትም ብቀበር።
ዳግም ላለመለስ ድንጋዩም ቢጫነኝ ፣
በሙት ምናብ መንፈስ፦ ለገደሉኝ ሰዎች አንድ ጥያቄ አለኝ ።

#ግን ምን አረኳችሁ ?
#ጥምቀትን ላከብር ፦
የመስቀል ምልክት ግንባሬ ላይ ስዬ፣
እናትና አባቴን እመጣለው ብዬ።
ቁርስ እንኳን ለመብላት ትግስቱን አጥቼ፣
እየተጣደፍኩኝ ከቤቴ ወጥቼ።
በመዝሙር በወረብ በሀይማኖት ትምርት፣
ደስ ብሎኝ ብውልም በታቦቱ ሽኝት፣
እንደወጣው ቀረሁ እኔም ተሸኝቼ በፌዴራል ጥይት

#ግን ምን አረኳችሁ?
ሲያደርጉ አይቼ እንኳን የጥንቱን ባንዲራ ግንባሬ ላይ ባስር ፣
ሲሉ ሰምቼ እንኳን አብሬ ብሳደብ ድንጋይ ብወረውር
ሆኜ ብገኝ እንኳን እኔም አንዱ አጥፊ፣
ለኔ አይበቃም ነበር አንድ የእናት ልጅ ኩርኩም አንድ የወንድም ጥፊ ?
ይኸው እናንተ ግን ቅንጣት ሳታዝኑልኝ፣
ገና በዚህ እድሜዬ የሚገድል ጥይት ተኮሳችሁብኝ !!!

ግን ምን #አረኳችሁ?

01/27/2018

በቅድስት ማርያም በመናፋቁ ተከስተ ግብዣ በየዋሁ የቅ° ማርያም ምእመን ላይ ምንፋቅና ትዘራ የነበረችው ዘርፌ

01/26/2018

ቅ•ማርያም ቤ•ክ ይቺን ነበር እየጋበዘ ምንፋቅናን የሚያስፋፋው::

10/10/2017

Would you agree with this?
Should we keep our good deeds to ourselves or should we share them with the rest of the world in order to inspire others?

08/25/2017
08/22/2017

ዐረገች በስብሐት ዐረገች በዕልልታ
በስብሐት በዕልልታ ዐረገች/2/ በዕልልታ/2
ከሙታን ተነስታ ዐረገች በዕልልታ/2
ዐረገች/2/ በዕልልታ/2

††† "ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የዐጽብ ለኲሉ"፤ ሞት ለማናቸውም ሰው ሁሉ የተገባ ነው፡፡ የማርያም ሞት ግን ሁሉን ያስደንቃል ፡፡ ቅዱስ ያሬድ

††† ‹‹ወትቀውም ንግሥት በየማንከ በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኁብርት፤ በወርቅ ልብስ ተጎናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች››(መዝ 44(45)፥9)

††† «ወደጄ ሆይ ተነሺ፣ ውበቴ ሆይ ነይ፡፡ እነሆ ክረምት አለፈ ÷ ዝናቡም አልፎ ሄደ ፤ አበቦች በምድር ላይ ተገለጡ፣ የዜማም ጊዜ ደረሰ ÷ የቁርዬውም ቃል በምድራችን ተሰማ፡፡ በለሱ ጎመራ ወይኖችም አበቡ መዐዛቸውንም ሰጡ ወዳጄ ሆይ ተነሺ፤ ውበቴ ሆይ ነይ፡፡» (መኃ.2 ፥10-14)፡፡


✙ እንኳን ለእመቤታችን በዓለ ትንሳኤና በዓለ ዕርገት በሰላም በጤና አደረሰን:: ጾማችን ፥ሱባዔያችንና ጸሎታችንን በሰላም አስጀምሮ በሰላም ላስፈጸመን ለልዑል እግዚአብሄር ምስጋና ይግባው:: የእመቤታችን ቸርነትና አማላጅነት ለዘለዓለሙ ከኛ ጋር ይሁን:: መልካም አወደዓመት! ✙❤❤❤✙

Timeline photos 08/14/2017

የስኞ መልዕክቴ ነው።

07/30/2017

selam le Ethiopia

Timeline photos 07/28/2017

እውነቱ ይህ ነበር፦ (ሰቆቃው)

ከደዌዎች መንደር - ከሚሸተው ሥፍራ፤
ብርሃን ከሌላቸው - ከጨለማው ጎራ፤
ሕይወት ሰጥቷቸው - ክርስቶስ አበራ፤
እውነቱም ይህ ነበር - የአገልጋዮች ሥራ፤

እንደ ጌታው ኾኖ - ክፉውን ሳይፈራ፤
ችግር የሚካፈል - የሕዝቡን መከራ፤
ባዝነው የጠፉትን - ፈልጎ የሚመራ፤
እውነቱ ይህ ነበር - የአገልጋዮቹ ሥራ፤

ጊዜ ከጎዳቸው - ኑሮ ከጣላቸው፤
የሰይጣን ደዌ - ህመም ካጠቃቸው፤
መቼ ነው የምትቆመው? - ኾነህ ከጎናቸው፤
ዛሬ ዝቅ ቢሉም - እንዳ'ንተ ሠው ናቸው። (፪)

©ሰቆቃው ዘ መምህረ ግርማ ወንድሙ [ሬድዮ አቢሲኒያ ክፍል 55ለ፤ 58ኛው ደቂቃ ላይ]

Timeline photos 07/26/2017

ምንጭ ክእናተው ወድ እናተው
👉👉🏾 ይህን ፅሁፍ ማንበብ 100 መፅሐፍት የማንበብ ያህል ነው ፡፡
ምክር ለወዳጅ
:
👉👉🏾 በወጣትነት ሁሉም ነገር ትክክል ነው ከሚል መመሪያ ውጣ ፤ ሁሉንም ካላየሁ አላምንም አትበል ። ሰምቶ ማመን ፣ ከተጎዱት መማር አስተዋይነት መሆኑን አትርሳ ። የሰማንያ ዓመት ዕውቀትን ለመገብየት ግድ ሰማንያ ዓመት መኖር የለብህም ። ሰማንያ ዓመት ከኖሩት በትሕትና መጠየቅ ይገባሃል ።
:
👉🏾👉🏾 ምክርን ብትሰማ በነጻ ትማራለህ ። ምክርን አልሰማ ብትል ግን በዋጋ እንደምትማር እወቀው ። በዋጋ መማር ግን አድካሚ ደግሞም የሚያስመርር ነው ። ብልህ ከሆንህ በሰው ከደረሰው ትማራለህ ፣ ሞኝ ከሆንህ ግን በራስህ ሲደርስ ትማራለህ ።
:
👉🏾👉🏾 የታየህን አሳይ ፣ ያልታየህን አጥራው ። በደንብ ያልተረዳኸውን አታስተምረው። ያልቀመስከውን ለሰው አትጋብዝ ። የሰማኸውን ሁሉ አትመን ። ያየኸውን ሁሉ ስጡኝ ፣ የተናገርከውን ሁሉ ፈፅሙ አትበል ። የሰጠኽውን እርሳ እንጂ አታውራ። ፍፃሜውን ሳታይ ምስጋና አታብዛ ። ቀኑ ሳይመሽ ቀኑ ጥሩ ነው አትበል ።
:
👉🏾👉🏾 ዓይንህ የፊቱን ቢያይ ልብህ የኋላውን ያስብ ። ነገ ላይ እንድትደርስ የትናንቱን አትርሳ ። የምትሄድበት እናዳይጠፋህ የመጣህበትን አትዘንጋ ።
:
👉🏾👉🏾 የአባቶችህን መልካም ሥራ አብነት አድርግ ። ካሳለፉት ሕይወት ተማር እንጂ አወዳሽና ወቃሽ አትሁን ። ሌሎች መሆን ያለባቸውን ስታውቅ አንተ መሆን ያለብህ እንዳይጠፋህ ተጠንቀቅ ። ደግሞም አንተም በታሪክ ፊት መሆንህን እወቀው ።
:
👉🏾👉🏾 ክፋት አይሙቅህ ፣ መልካም ነገርም ብርድ ብርድ አይበልህ ። ለክፋት አቅም ካለህ ለበጎ ነገርም አቅም አለህና ተግባርህ የምርጫ ውጤት ነውና አስብበት ።
:
👉🏾👉🏾 ገንዘብ የሚመልሰው የገንዘብን ጥያቄ ብቻ ነውና ሁሉንም ነገር ገንዘብ ያስገኝልኛል ብለህ አታስብ ። ላለው አትሩጥ ፣ ምጽዋትህና ተግባርህ በአቅምህ መጠን ይሁን እንጂ ከአቅምህ አትነስ ። ድሃም ሆነህ ተበድረህ ስጦታ አትስጥ ። በጣም ካልቸገረህ ለቅንጦት አትበደር ። ያንተን ድርሻ ከጨረስህ ያልተጨረሰ የሌሎችን ድርሻ ፈፅምላቸው ።
:
👉🏾👉🏾 ለሀብታም አትሳቅ ፣ የደሀ ጉልበት አይለፍብህ ፣ ያለ ሰው ሰው አልሆንክምና ሰው አትጥላ ፣ የወጣህበትን መሰላል አትገፍትር ፣ ለመውረድም ያስፈልግሃልና ፣ ያየኽውን ሴት ሁሉ የመውደድ ጠባይህ ካለቀቀህ ትዳር አትያዝ ፣ ካልጋበዙህ በቀር አማካሪ አትሁን ፣ ባልጠሩህ ሥፍራ አቤት አትበል ፣ ካልሾሙህ መሪ አትሁን ፣ ጉድለት በሌለበት ቦታ ጊዜህን አታባክን ፣ የሰው ፊት ጥገኛ ሁነህ ሲስቁልህ የምትስቅ ሲቆጡህ የምታለቅስ አትሁን ፣ ነገርህን በልክ ፣ ቃልህን በጣዕም ፣ ድምፅህን በዝግታ ፈፅመው ።
:
👉🏾👉🏾 እውር እንዳይሉህ ያልታየኽን አያለሁ አትበል ። ጨካኝ እንዳይሉህ ያልተሰማህን ጩኸት እሰማለሁ አትበል ። ንፉግ እንዳይሉህ ያለ አቅምህ እረዳለሁ አትበል ። ነገር አይገባውም እንዳይሉህ ያልገባህን እንደገባህ አድርገህ አትለፍ ። አንድ በጎ ዕውቀት ሳትጨብጥ የዋልክበትን ቀን እንደ ኖርክበት አትቁጠረው ፣ ስለዚህ መፅሐፍትን አንብብ ፣ አዋቂዎችን ጠይቅ ፣ ሁሉን ሳትንቅ ስማ ።
:
👉🏾👉🏾 ሥልጣን ሲሰጥህ መሪ እንጂ አለቃ አትሁን ፤ ከፊት እየቀደምህ አስከትል እንጂ ከኋላ ሆነህ አትቅደም ።
:
👉🏾👉🏾 በዓላማ ኑር ፤ እንቅፋቶች የሚያጸኑህ እንጂ ተግባርህን የሚያስተውህ አይሁኑ ። ሕይወት ትምህርት ቤት መሆኑና ባለማወቅ ብዙ ትህምርቶች እንዳያመልጡህ ተጠንቀቅ ።
:
👉🏾👉🏾 የመከራ ቀን ወዳጆችህን አትርሳ ፤ የዛሬ ሰው ብቻ አትሁን ፤ የትላንቱንም አስብ ፤ አንገት የተፈጠረው ዞሮ ለማየት ነውና ።
:
👉🏾👉🏾 ዓለም ዋዣቂ ናት ። ከፍና ዝቅ ስትል አትደናገጥ ፤ ፀሐይ ዝናብን ተከትላ ትፈነጥቃለች ። ከመከፋትም በኋላ ትልቅ መፅናናት ይሆናል ። ከሌሊት በኋላም ሌሊት አይመጣም ። ከሀዘን በኋላ ደስታ ይሆናልና በርታ!
:
👉🏾👉🏾 መነቀፍን አትፍራ ፤ ነቀፋህን ግን አጥራው ፤ ስለ ሀሰት ሳይሆን ስለ እውነት ተገፋ ፤ ሌሎችን ውደድ ፍቅር ስጦታ እንጂ ብድር አይደለምና አልወደዱኝም ብለህ በአበዳሪዎች አንቀጽ አትካሰስ ፤ የገባህን አድርግ የዚህ ዓለም ሰው ሲወድህም ሲጠላህም ባለማወቅ ነው ። ብዙዎች ስለወደዱህ ይወድሃል ፤ ብዙዎች ስለጠሉህ ይጠላሃል ።
:
👉🏾👉🏾 ሁልጊዜ የበላዮችህን አትመልከት ፤ የበታቾችህንም ተመልከት ። ለድምፅ አልባዎች ጩህላቸው ፣ ለተጠቁት ተሟገትላቸው ። እውነት እውነት በማለትህ የምታጣው ሀሰተኛ ወዳጅህን ብቻ ነው ። እውነት እውነት በማለትህ የምታተርፈው ግን እውነተኛ ወዳጅን ነው ።
:
👉🏾👉🏾 ደጋፊዎች ተከታዮች አይደሉም ። ሰዎች ስለደገፉህም የያዝኩት እውነት ነው ብለህ መንቻካ አትሁን ፤ ምናልባት ዛሬ የሚጮሁልህ ዛሬን ሊረሱብህ ሊሆን ይችላልና ። ሲያለቅሱልህም ቃልህ ማርኳቸው ሳይሆን የሞተ ዘመዳቸው ትዝ ብሏቸው ሊሆን ይችላልና አለቀሱ ብለህ ንግግርህን ድንበር አታሳጣው ። እውነትንም በደጋፊ ብዛት እንዳትመዝናት ተጠንቀቅ ።
:
👉🏾👉🏾 ለእውነታ እንጂ ለይሉኝታ አትኑር ፤ ያን ስልህ የምትኖርበት ሕዝብና ባሕል ከእውነት ጋር እስካልተጋጨ መጋፋት የለብህም። ሠዎች የሚቀበሉህ ባሕላቸውን ስታውቅና ስታከብርላቸው ነው ።
:
👉🏾👉🏾 ልጅነት የለሰለሰ መሬት ፣ ወጣትነት የአዝመራ ዘመን ፣ ሽምግልና ደግሞ የአጨዳ ዘመን መሆኑን አስተውል ። በሽምግልናህ የምታጭደው የወጣትነትህን አዝመራ ነውና ዛሬ ለምትዘራው ተጠንቀቅ ።
:
👉🏾👉🏾 የሰዎችን ያለማወቅ አግዝ ፤ ዕውቀትህ ባላወቁት ላይ እንድትኮራና እንድትፈርድ አያድርግህ የአዋቂ ኩሩ ቁጥሩ ካላዋቂዎች ነውና ማወቅ ባለዕዳነት እንዳይሆን አላዋቂዎችን እርዳቸው ።
:
👉🏾👉🏾 ዛሬ የመዝራት ዘመንህ ነገ መከርህ ነውና በእምነት እውነትን ዝራ ፤ በምታውቀው ቦታ ላይ አገልጋይ በማታውቀው መልካም ተግባር ላይ ደጀን ሁን ፤ በቦታህ መምህር ያለቦታህ ተማሪ ሁን ፤ ክብሩ እንዳይቀንስብህ ከዕቃ ትምክህት ፣ ከዕውቀት ሙግት ራቅ ።
:
👉🏾👉🏾 ሁሉን ወሬ ላውራ አትበል ፣ የደበቁህን ምስጢር አታውጣጣ ፣ የሰማኽውን ወሬና የተገለጠልህን ምስጢር ምን መፍትሔ ሰጠኸውና ? ያየህውን ሥራ ሁሉ እሰራለሁ የሰማኸውን ትምህርት ሁሉ እማራለሁ አትበል ። ይህ የተሰወረው የቅንዓት ጠባይ ነውና ሁሉን ልያዝ ማለትም ዝንጉ አድረጎ እንዳያስቀርህ ሁሉም ውስጥ ልኑር አትበል ።
:
👉🏾👉🏾 ቆንጆዎች ቁንጅናቸው ሁሉን የሚተካ እየመሰላቸው ከዕውቀትና ከትሕትና ይርቃሉ ። ሁሉንም ሰው በመልካቸው የሚማርኩት ስለሚመስላቸው ኩሩና ተንኮለኞች ይሆናሉ ። አንተ ግን ቆንጆ ወዳጅን እንጂ ቆንጆ ቁመናን አትሻ ፤ ቆንጆ ትዳርን እንጂ ቆንጆ ሴትን አትመኝ ፤ የላይ ነገር ከንቱና ኀላፊ ነውና በሚፈርስ አካል ፣ ኑሮ በሚለውጠው መልክ አትደለል ።
:
👉🏾👉🏾 እወድሃለሁ ብለህ የምትናገረውን ቃል ውለታ አታድርገው ፣ መውደድህን የምትናገረው እንወድሃለን እንዲሉህ አይሁን ፣ ሠላም ያለው አፍቃሪ የራሱን ፍቅር ያለ ምክንያት መፈፀም የሚችል ብቻ እንደሆነ እወቅ ። መወደድህን ለመስማት አትጠብቅ ።
:
👉🏾👉🏾 የሰዎችን ያለማወቅ አግዝ ፤ ዕውቀትህ ባላወቁት ላይ እንድትኮራና እንድትፈርድ አያድርግህ የአዋቂ ኩሩ ቁጥሩ ካላዋቂዎች ነውና ማወቅ ባለዕዳነት እንዳይሆን አላዋቂዎችን እርዳቸው ።
:
👉🏾👉🏾 ዛሬ የመዝራት ዘመንህ ነገ መከርህ ነውና በእምነት እውነትን ዝራ ፤ በምታውቀው ቦታ ላይ አገልጋይ በማታውቀው መልካም ተግባር ላይ ደጀን ሁን ፤ በቦታህ መምህር ያለቦታህ ተማሪ
ሁን ፤ ክብሩ እንዳይቀንስብህ ከዕቃ ትምክህት ፣ ከዕውቀት ሙግት ራቅ ።
:
👉🏾👉🏾 ሁሉን ወሬ ላውራ አትበል ፣ የደበቁህን ምስጢር አታውጣጣ ፣ የሰማኽውን ወሬና የተገለጠልህን ምስጢር ምን መፍትሔ ሰጠኸውና ? ያየህውን ሥራ ሁሉ እሰራለሁ የሰማኸውን ትምህርት ሁሉ እማራለሁ አትበል ። ይህ የተሰወረው የቅንዓት ጠባይ ነውና ። ሁሉን ልያዝ ማለትም ዝንጉ አድረጎ እንዳያስቀርህ ሁሉም ውስጥ ልኑር አትበል ።
:
👉🏾👉🏾 ቆንጆዎች ቁንጅናቸው ሁሉን የሚተካ እየመሰላቸው ከዕውቀትና ከትሕትና ይርቃሉ ። ሁሉንም ሰው በመልካቸው የሚማርኩት ስለሚመስላቸው ኩሩና ተንኮለኞች ይሆናሉ ። አንተ ግን ቆንጆ
ወዳጅን እንጂ ቆንጆ ቁመናን አትሻ ፤ ቆንጆ ትዳርን እንጂ ቆንጆ ሴትን አትመኝ ፤ የላይ ነገር ከንቱና ኀላፊ ነውና በሚፈርስ አካል ፣ ኑሮ በሚለውጠው መልክ አትደለል ።
:
👉🏾👉🏾 እወድሃለሁ ብለህ የምትናገረውን ቃል ውለታ አታድርገው ፣ መውደድህን የምትናገረው እንወድሃለን እንዲሉህ አይሁን ፣ ሠላም ያለው አፍቃሪ የራሱን ፍቅር ያለ ምክንያት መፈፀም የሚችል ብቻ እንደሆነ እወቅ ። መወደድህን ለመስማት አትጠብቅ ።
:
👉🏾👉🏾 ቂም አፍን የሚያመር ፣ ልብን የሚያነቅዝ ፣ ተግባርን የሚያልፈሰፍስ ነውና ለበደለህ ሰው ቅያሜህን ግለጥለት ፤ ቂመኝነት በክፉ መሸነፍ እንጂ ጀግንነት አይምሰልህ ።
:
👉🏾👉🏾 ከህሊናህና ከመንፈሳዊ አማካሪህ ሳትመክር ምንም ነገር አትወስን ፤ አጥርተህ ሳትሰማ ቃል አትግባ ። መከራ ካልደረሰ በቀር ባል በሌለበት ቤት ውስጥ ከሚስቲቱ ጋር ብቻህን አትቀመጥ ።
:
👉🏾👉🏾 የሚበልጥህ ልኩራብህ እንዳይልህ ፣ ያነሰህ ልድረስብህ ብሎ እንዳያጠፋህ የሀብትህን ልክ እንዳታወራ ፤ በገዛ አፍህ ባንዱ ትከብራለህ ባንዱ ትቀላለህና ።
:
👉🏾👉🏾 በጣም በማክበርህ እንዳታመልከው ፤ በጣም በመናቅህ እንዳታዋርደው ሠው እንዳንተ መሆኑን እወቀው ።
:
👉🏾👉🏾 የእኔ መናገር ምን ይለውጣል? ብለህም ስህተትን አትለፍ ፤ የእኔ አስተዋፅኦ ምን ይጠቅማል ? ብለህም ስጦታህን አትጠፍ ።
:
👉🏾👉🏾 መልካም ቃል ከስጦታ ይበልጣልና መልካም ቃል ተናገር ፤ ማንኛውም ስጦታ ከልመና ወንበር አያስነሣም ። የተስፋ ቃል ግን እንደሚያስነሣ አውቀህ ለሰዎች የተስፋ ቃል ስጣቸው ።
:
👉🏾👉🏾 ትምህርት ለዕውቀት ያዘጋጃል እንጂ ዕውቀትን አይጨርስም ። ዕውቀትህን የምትይዝበትን ሥነ-ሥርዓት ግን ያሳይሃል ። አእምሮህን ለማረቅ ትምህርት ፣ ሰውነትህን ለመግዛት ትዕግስት ፣ ከማንም ጋር ለመኖር ሥነ-ሥርዓት ያስፈልግሃል ። ለህሊናህ እረፍት ግን እምነት ያሻሃል ። ተከታይ ለማበጀት ደግሞ ግልጽ መሆንና ታማኝነት ግድ ይልሃል ።
:
👉🏾👉🏾 አንተው እውነትን ጠልተሃት ዘመኑ እውነትን ጠልቷል አትበል ። ዘመን እኔና አንተ ነን ፤ በራሱ ክፉና ደግ የሆነ ዘመን የለም ።
:
👉🏾👉🏾 መልካም ምክር ብትሰማ ሕይወት ቀላል ይሆንልሃል ። ትክክለኛም ውሳኔ ከመልካም ምክር ነውና..!!

Timeline photos 07/24/2017

【እኔስ ሰው አማረኝ】
እስኪ ቀስቅሷቸው አበው ይናገሩ
የምንኩስና ግብር ምን ነበር ምሥጢሩ
የክርስትና ሕይወት ምን ነበር ተግባሩ
መቃብሩን ክፈቱና አበው ይመስክሩ፡፡
እኔስ ሰው አማረኝ የሃይማኖት ጀግና
ወልድ ዋሕድ ብሎ በእምነቱ የፀና
ጀግና ሰው አማረኝ ጠላት አሳፋሪ
ንጽህት ድንግል ብሎ እምነቱን መስካሪ፡፡
ነብያት በመጋዝ የተሰነጠቁት
ሐዋርያት ቁልቁል የተዘቀዘቁት
ሰማዕታት በእሳት የተለበለቡት
ቅዱሳን በገዳም ደርቀው የተገኙት
ምሥጢሩ ምን ነበር? አበው ይናገሩት፡፡
ይናገር ዝቋላ ግሸን ላሊበላ
የቅዱሳንን ዐፅም ለምን እንዳልበላ፡፡
ዋልድባ ይናገር ዜጋመልም ሳይቀር
እንባቸው መፍሰሱ ለምን እንደነበር፡፡
ነበር ወይ ፈልገው ሹመት ሽልማት?
ወይስ ሀብት ንብረት የተሟላ ቤት?
ወይስ አምሯቸው ነው ፈልገው መሞት?
እናንተ ገዳማት ምሥጢሩን አውሩት፡፡
ጐበዝ ሰው አማረኝ በእምነቱ የፀና
ምግባር ሃይማኖቱ በእጅጉ የቀና፡፡
እንጦንስ የወለደው በምግባር በእምነት
ተምሮ ያደገ ከተክለሃይማኖት፡፡
የጊዮርጊስ ወገን የት ነው የማገኘው?
በመሀል ከተማ በአራዳ ውስጥ ነው?
ወይስ በዝቋላ በደብረ ሊባኖስ በደብረ ዳሞ
ነው?
ወገን ሰው ናፈቀኝ ዐይኔን ሰው አማረው
የሃይማኖት ጀግና የትነው የማገኘው?
ልግባ ወይ ዋልድባ ጫካ ካለበት
ማኅበረ ሥላሴ ከቅዱሳን ቤት?
አክሱም ግሸን ማርያም ከቃል ኪዳን ቦታ
ይገኛል ወይ ጀግና ጠላት የሚረታ?
ፈሪሐ እግዚአብሔር በልቡ ያደረ
ቤተ ክርስቲያንን ያልተደፋፈረ፡፡
የት ነው የማገኘው ለሃይማኖቱ ሟች
ለተዋሕዶ እምነት ጠበቃ ተሟጋች፡፡
የወገን መመኪያ የከሀዲ መቅሰፍት
ማነው እሱ ጀግና ተኝቶ እንደሆነ ይነሣ
ቀስቅሱት፡፡
እስኪ ቀስቅሷቸው አበው ይናገሩ
የምንኩስና ግብ ምን ነበር ምሥጢሩ?
የክርስቲያን ሕይወት ምን ነበር ተግባሩ?
መቃብሩን ክፈቱት አበው ይመስክሩ፡፡
ወገን ሰው ናፈቀኝ ዐይኔን ጀግና አማረው
በእምነቱ የፀና የትነው የማገኘው?
ብቅ ይበል እንየው እሱ ማነው ጀግና?
በጐችን ከተኩላ ነቅቶ የሚጠብቅ
መከራ ቢከበው ከቶ የማይሰቀቅ
የሃይማኖት ጀግና ቆራጥ ሰው ገበሬ
እንደዚያ እንደ ጥንቱ ይገኛል ወይ ዛሬ?
የወገን የዘመድ ጥቅም ያላወረው
የመናፍቆች እጅ ኪሱን ያልዳበሰው
የዓለም አሸክላ ልቡን ያልማረከው
የክርስቶስ ወዳጅ እሱ ጀግና ማነው?
ምሥጢርን ከምሥጢሩ አንድ አድርጐ ቀምሮ
ወልድ ዋሕድ ብሎ ሃይማኖት መስክሮ
እንጦንስን መቃርስን በልቡ ያኖረ
ከአትናቴዎስ ከቄርሎስ ጥበብ የተማረ፡፡
ድንግል እመቤቴ ብሎ የሚመሰክር
መሆኗን የሚያምን ማኅደረ እግዚአብሔር
ቋቅ እንትፍ ብሎ የጠላ ክህደትን
ትንታግ ምላስም ጭንግፍግፉን
ልሳነ ጤዛ መናፍቅን
ወልደ አርዮስ ዲቃላውን፡፡
በሰይፈ ሥላሴ የሚቀላ
ጀግና ማነው ዝቅ ይበላ፡፡
ነበር ወይ ያን ጊዜ ለሹመት መጓጓት
እስኪ ጎርጎርዮሰ ይምጣና ጠይቁት
ፍቅርንም ይጠየቅ አባ ሕርያቆስ
ምሥጢርን ጠባቂ ወይም አባ መቃርስ፡፡
የክርስቶስ ባርያ የአጋንንት መቅሰፍት
ወንጌል አስተማሪ የሃይማኖት አባት
ይህንን ጉድ እንዲያይ ይምጣ ተክለሃይማኖት
የጸሎት ገበሬ ገብረ መንፈስ ቅዱስንም ይነሣ
ቀስቅሱት
ይነሣ ጊዮርጊስ ይመስክር ምሥጢር
የሃይማኖት ፍቅር ምን እንደነበር፡፡
ከእናቶቻችንም አሉ ለፍጥረት ያዘኑ
ዲያብሎስ እንዲማር ጌታን የለመኑ፡፡
ስንቱን ልዘርዝረው የአባቶችን ሙያ
መር ብለው የወጡት ከሥጋ ገበያ
ጾም ጸሎት ነበረ የሃይማኖት ጋሻ
መልከስከስ ምንድነው እንደ አበደ ውሻ፡፡
እንደ መስኖ ውሃ ከነዱት መነዳት
ዓላማው ምንድነው የዘመኑ ወጣት፡፡
እኔስ ሰው አማረኝ የሃይማኖት ጀግና
ወልድ ዋሕድ ብሎ በእምነቱ የፀና
ዐይኔን ሰው አማረው ጀግና ሰው ገበሬ
ሃይማኖት መስካሪ እንደ ጥንቱ ዛሬ፡፡

Timeline photos 07/21/2017

"We want to be strong. But let God be the source of our strength; let Him be the One who strengthens us, such that we do not depend on our personal strength but on His. We stand before Him weak so that we may take strength from Him"

+ Pope Shenouda +

07/02/2017

«ከዓመፃም ብዛት የተነሣ የብዙ ሰዎች ፍቅር ትቀዘቅዛለች።»
(ማቴ 24፥12)

Want your place of worship to be the top-listed Place Of Worship in Los Angeles?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Videos (show all)

Telephone

Address


5707 Shenandoah Avenue
Los Angeles, CA
90056
Other Los Angeles places of worship (show all)
JFF (Journey of Faith Fellowship) JFF (Journey of Faith Fellowship)
711 S Plymouth Street (Ritter Chapel)
Los Angeles, 90005

Come as you are. Be changed by the Journey

Mount Hollywood United Church of Christ Mount Hollywood United Church of Christ
1733 N. New Hampshire Avenue
Los Angeles, 90027

Sunday Celebration at 10:30am Office Hours by Appointment 1733 N New Hampshire Ave, Los Angeles, California 90027

LA Office of Religious Education LA Office of Religious Education
3424 Wilshire Boulevard
Los Angeles, 90010

The Office of Religious Education in the Archdiocese of Los Angeles is engaged in continuing the mission of Jesus Christ through evangelization and catechesis.

Newsong LA Newsong LA
5875 Green Valley Cir, Fl 2nd
Los Angeles, 90230

Newsong LA is a third culture church with a multicultural worship service, relevant message and a com

Cathedral of Our Lady of the Angels Cathedral of Our Lady of the Angels
555 W Temple Street
Los Angeles, 90012

A House of Prayer for ALL peoples! The Cathedral is rich in cultural diversity in a city which Sunday mass is celebrated in 42 different languages. We are transmitting Masses dai...

Hamakomla Hamakomla
6025 Valley Circle Boulevard
Los Angeles, 91367

A Vibrant Jewish Congregation in the west San Fernando Valley. Check back often for updates on eve

Community Christian Alliance Church Community Christian Alliance Church
15950 Chatsworth Street
Los Angeles, 91344

We've moved to a new location! As of December 8, 2019, CCAC's new location is: 15950 Chatsworth Street, Granada Hills, CA 91344. Our previous address: 18827 Roscoe Blvd, Northridg...

Actors of Salvation Actors of Salvation
18419 Sherman Way
Los Angeles, 91335

Ministerio de Artes de Iglesia de Restauracion Reseda (IREST) Visítenos en www.actorsofsalvation.com

The Urban Ministry Institute of Los Angeles The Urban Ministry Institute of Los Angeles
1977 S. Vermont Avenue
Los Angeles, 90007

Equipping men and women for Christian ministry!

Mt. Tabor MBC C & Y Ministry Mt. Tabor MBC C & Y Ministry
6614 S Western Avenue
Los Angeles, 90047

The Youth of Mt. Tabor welcome an opportunity to fellowship with you!

Faith Tabernacle Church Los Angeles Faith Tabernacle Church Los Angeles
2147 Purdue Avenue
Los Angeles, 90025

We are a multi-ethnic Christian church located in West LA, corner of Olympic Blvd and Purdue Ave

Valley Lighthouse Valley Lighthouse
6150 Tyrone Avenue
Los Angeles, 91401

A church to call home!