Miracle Medium clinic O.P.D by experienced Doctors
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Miracle Medium clinic O.P.D by experienced Doctors, Medical and health, Topeka, KS.
04602873252263864/starclick.com
ሜታ ቨርስ
አስቡት በጠዋት ትነሳላቹ ከሰዓት ቢሮ ትሄዳላቹ ከዛ በእኩል ሌሊት በጣም የምቶዱትን አርቲስት ኮንሰርት ትገባላቹ; ይሄ ሁሉ ከቤታቹ ሳትወጡ ነው የሚሆነው የ ጠፈር( space) ስፋቱ ምንም አያሳስበንም ምክንያቱም በ metaverse ዓለም ውስጥ ነው ያላቹት.
ሁለት ነገሮች አሉ የሰው ልጅ ሁሌም ሊያሸንፋቸው የሚፈልጋቸው በምድር ውስጥ ና ከምድር ውጪ ያለ ቦታ(space) ና ጊዜ(time)ናቸው.ግን እስከ አሁን የፈለግንበት ቦታ ያለገደብ መሄድ አልቻልንም.በ ጊዜም ውስጥ በ ፈለግነው አቅጣጫ ማለትም ወደ ኃላም ወደ ፊትም መንቀሳቀስ አልቻልንም.
ከ ግመል ወደ ፈረስ.ከፈረስ ወደ ጋሪ.ከጋሪ ወደ መኪና, አሮኘላን, ና ሮኬት እያልን ኖረናል.እኛ እየሞከርን ያለነው ቦታን(space) ለማጠፍ ነው እየሞከርን ያለነው.ማለትም ዓለምን ካላት እውነተኛ ስፋት ለማጥበብ ነው እየሞከርን ያለነው.ደብዳቤ ከመፃፍ እስከ ስልክ መደዋወል ና ኢ-ሜል መላላክ አሁን ደሞ በ virtual reality. እኛ ሁሌም በብዙ በጣም በተራራቁ ቦታዎች ላይ በአካልም ባይሆን በመገኘት መልክት መለዋወጥ ስራዎችን ማስኬድ እና ማህበራዊ ሂወትን መኖር እንሞክራለን.የተለያዮ ፈጠራዎቻችንን ብናይ ምንም በአካል ብንራራቅም እርስ በእርስ በቀላሉ መልክት እንድንለዋወጥ የሚረዱን ናቸው ምክንያቱም የሰው ልጅ በተፈጥሮ ማህበራዊ ነው.
አሁን teleportation የተባለውን የ ሳይንስ ልብ ወለድ ሀሳብ ብናይ; physical teleportation (በ አካል ከአንድ ቦታ በቅፅበት ወደ ሌላ ሩቅ ቦታ መሄድ) ባለው ተጨባጭ ሁኔታ መቼም የሚሆን አይመስልም.ምክንያቱም የዚህን ሀሳብ ፊዚክስ ብናይ የሰውነታችን አተሞች ተበታትነው ሌላ እሩቅ ቦታ ላይ ተገጣጥመው ሰው ይሆናሉ ማለት የማይመስል መፈላሰፍ ይሆናል.ግን ምንድን ነው ችግሩ ይሄን ነገር በ ኢንተርኔት ብናደርገው?በጥልቁ ውቂያኖስ ውስጥ ገብተን ማየት መስማት ከፈለግን ይቻላል; ከማርስ ሆነን ምድርን ማየት ብንፈልግ ይቻላል; የአደጋ አጋጣሚዎች ሳያሳስቡን ኮንሰርት መታደም ብንፈልግ ይቻላል.
በጊዜ ውስጥ እንደፈለግን የመንቀሳቀስ ሀሳብ (time travel) እስከ አሁን አልተቻለም.ግን በሜታቨርስ ዓለም ይሄም ይቻላል.የ ቱ ፓክን ኮንሰርት መታደም ብንፈልግ; በ18ኛው ክፍለ ዘመን የንግስት ቪክቶሪያን አኗኗር ማጥናት ብንፈልግ ይቻላል.
ይሄ "Metaverse" የተባለ ነገር መሳሪያ እንደመሆኑ ሰዎች ለ መጥፎ አላማ ሊጠቀምበት ይችላሉ.ይሄን ቴክኖሎጂ በዋነኝነት እየሰራበት ያለው ድርጅት Facebook ለብዙ የወንጀል የዘር ማጥፋት ጨምሮ ስራ ማስፈፀሚያነት እንደዋለ ማየት ይሄን ለመረዳት በቂ ነው.እነዚህ social media platforms በቀላሉ መልክት ቢያለዋውጡንም እርስ በእርስ የሚያራርቁንም እነሱ ናቸው.በዘመናችን ተሰብስቦ እያወሩ ጥሩ ጊዜ ማሳለፍ እየቀረ ነው በ social media ምክኒያት.ሜታቨርስ ደሞ ያለውን የ social media አሉታዊ ተፅኖ በብዙ እጥፍ ሊጨምር ይችላል ተብሎ ይፈራል.
ይሄን ዝግጅት ያቀረብኩላቹ ዶ/ር ቢኒ ነበርኩ መልካም ቀን ይሁንላቹ!!!
ስቶይሲዝም(stoicism)
እ.ኤ.አ. ከክርስቶስ ልደት በፊት በ 300 ዓመተ ዓለም በ ሳይኘረስ ከተማ ውስጥ የሚኖር ባለፀጋ ነጋዴ ነበረ ስሙም ዚኖ ይባል ነበረ.ከ ፎኔሺያ ወደ ፒሩስ በመርከብ እየተጓዘ መርከቧ በድንገት ትሰምጥ እና ሀብቱን ሙሉ ለሙሉ አጥቶ በአንድ ጊዜ ደሀ ይሆናል.እናንተ በዜኖ ቦታ ብትሆኑ ምን ታደርጉ ነበር?አብዛኞቻችን እናዝናለን,እንናደዳለን...ይሄ የተለመደው የአፀፋ ምላሽ ነው.ዜኖ ግን እንደሱ አላደረገም የስቶይሲዝም ፍልስፍና አባት.
የስቶይሲዝም ማከላዊ ሀሳቡ "መቀበል እና ተመሳሳይነት" ተብሎ ሊቀመጥ ይችላል.ዜኖ ከሶቅራተስ ስር የተማረ ና ስለ"ስቶይሲዝም" ያስተማረ ነው.እሱም ሲያስተምር እንዲህ ይላል"ሕይወታችን ላይ የሚከሰቱ ነገሮች ላይ ስልጣን ባይኖረንም እነሱ እንዴት ህይወታችንን እንደሚነኩት ና እንደሚቀይሩት ላይ ግን ስልጣን አለን.ይሄን ስልጣን የደረሰውን ክስተት የሚያመጣውን ጉዳት ለመቀነስ እናውል የሚል ነው."የዜኖ ትምህርት ሰዎች ምንም ቢገጥማቸው የተረጋጉ ና ስሜታዊ ያልሆኑ የመሆን ጥበብን ያስተምራል.ስቶይሲዝም ጥሩ ያልሆኑ አጋጣሚዎችን ጥሩ ካልሆኑ ልምዶች እንድንረዳ ያግዘናል.እናም አለምን የምናይበትን ልዮ የሆነ መንገድ ይፈጥርልናል.
ይሄ ትምህርት በጊዜው ገናና የነበረ ና ለሺህ አመታት የዘለቀ ነው.ማንም ሰው ስቶይሲዝምን ተምሮ ስቶይክ መሆን ይችላል.እነ ኤፒክቲተስ(epictitus)-በባርነት ያገለግል የነበረ ነው;ሴኒካ-የታወቀ መሪ ነበር; ማርከስ ኦሪሊየስ-የሮማ ንጉስ ነበር.
አንድ ነገር የሚያሳዝነን ነገሩ ጥሩ ስላልሆነ ሳይሆን ነገሩ ያልጠበቅነው ስለሆነ ነው.ለምሳሌ ዝናብ ለተክሎች ውሀ ያጠናል,የከብቶችን ጥም ይቆርጣል, አየሩን ያቀዘቅዛል.ነገር ግን ዣንጥላ ሳንይዝ ዝናብ መንገድ ላይ ከያዘን ጥሩ ያልሆነ አጋጣሚ ይሆናል.ግን የአየር ጸባይ መቆጣጠር እስካልቻልን ዝናብ በመንገዶች ላይ ሊዘን እንደሚችል መጠበቅ አለብን.ስቶይሲዝም እንደሚለው ሁሌም የአንድን ነገር በጣም የከፋውን ውጤት ማሰብ እና መዘጋጀት አለብን.አንዱ የስቶይሲዝም መለማመጃ "voluntary discomfort "ይባላል...ለምሳሌ ስፖርት መስራት, አልጋ ላይ ከመተኛት ይልቅ የኩሽናችን ወለል ላይ መተኛት, በሙሉ ውሀ እንታጠብ ከነበረ በቀዝቃዛ ውሀ መታጠብ, ድንች ብቻ ለተወሰኑ ቀናት መብላት...ወዘተ.እነዚህን ማድረግ ለክፋ ቀን ዝግጁ ያደርገናል.
ስቶይሲዝም እንደሚለው እራሳችንን ለራሳችን ስንል ብቻ እናሻሽል.ነገሮችን የምናደርገው በማሀበረሰቡ ፊት የተሻለ መስሎ ለማየት ከሆነ በመጨረሻ ሀዘን ላይ ይጥለናል.ለምሳሌ የውስጣችንን ባዶነት ለመሸፈን ስንል ገንዘባችንን በውድ መኪና ,ቤት ላይ ልናጠፋ እንችላለን;ቤተሰብ ልንመሠርት እንችላለን.እነዚህ ነገሮች ውጫዊ ዋጋ ያላቸው ናቸው.እንደ ስቶይሲዝም አስተምሮ ሕይወትን በዚህ መንገድ የምንኖር ከሆነ ደስታችንን ልንቆጣጠረው የማንችለው ውጫዊ ሀይል እጅ ላይ ይወድቃል.እነዚህ ሀይሎች ደሞ ሁሌም የውድቀት ምንጭ ናቸው.ግን በሕይወት ውስጥ በነፃ የሚገኙ ነገሮች እራሱ ያለንን የተዝናና የሕይወት አካባቢ ተቀናሽ አድርገውብን ነው የሚመጡት. ሴኒካ እንዳለው "ሰው በዙሪያው ያሉትን ነገሮች በደንብ መቀነስ ቢችል በሕይወቱ ውስጥ በጣም አስፈላጊ ለሆኑት ነገሮች በቂ ቦታ ያገኛል."ዋጋ የምንሰጣቸው ነገሮች ለራሳችን ጥቅም ያላቸው ና ለመታየት ብቻ ያልሆኑ እንዲሆኑ ማድረግ ና የተረጋጋ አእምሮ ባለቤት መሆንን መምረጥ አለብን.
በሕወታችን ውስጥ ያሉትን ነገሮች በሁለት ይከፈላሉ "መቆጣጠር የምንችላቸው ና መቆጣጠር የማንችላቸው ነገሮች" እንደስቶይሲዝም አስተምህሮ ዋጋ ያላቸውን ነገሮቻችንን መቆጣጠር የምንችላቸው በማድረግ ደስተኛ መሆን እንችላለን.
አብሪያቹ የቆየበት ዶ/ር ቢኒ ነበርኩ መልካም ቀን.ባመሞት ጊዜ ሁሉ የ online clinic"miracle medium clinic O.P.D" በፌስ ቡክ ፔጁ ይጠብቃቿል.
TR-3B Black manta
ሰላም ጤና ይስጥልኝ የፔጃችን ቤተሰቦች ዛሬ በጉጉት ስለምጠብቁት ነገር እናወራለን.ከላይ የምናየው የስለላ አውሮፕላን ብዙ ታላላቅ ተቋማት ማለትም የአሜሪካ አየር ሀይል, ለሊቱን ሙሉ ኮከብ ላይ አፍጠው የሚያድሩ የከዋክብት አጥኚዎች, የታሪክ ተመራማሪዎች ና የአቬሽን ኢንዱስትሪ ባለሙያዎች አይተው ምስክርነት የሰጡለት ግን በሚስጥር የሚገኝ አውሮፕላን ነው.ይሄ የስለላ አውሮፕላን የሶስት መዓዘን ቅርፅ ያለው ሲሆን ዲዛይኑ የሳይንስ ፊክሽን እንጂ እውነት ያለ አይመስልም.በዚህ ላይ ጂ-ተርን(G-turn) ከሀይለኛ ከፍታ ላይ መስራት ይችላል,በራዳር አይታይም.ተሰራ ተብሎ የሚታመነውም ከነዓዚ የጀርመን መንግስት የድብቅ ምርምሮች ላይ ተሰርቆ ነው.የዚህ አውሮፕላን ሞተር ፀረ-የመሬት ስበት ምትሀት ብለው የዘርፉ ባለሙያዎች ይገልፁታል ስሙም TR-3B Black manta ይባላል.የአሜሪካ አየር ሀይል የተወሰኑ አውሮኘላኖችን ለምሳሌ "አሮራ" የምትባለውን አውሮፕላን የሉም ብሎ ምላሽ በመስጠት ይታወቃል.ከነዚህ መካከል ደሞ Black-manta አንዷ ነች.በእርግጠኛነት የሁላቹም የመጀመሪያ ጥያቄ የሚሆነው "አውሮኘላኑ ፀረ-የመሬት ስበት ይጠቀማል ማለት ምን ማለት ነው?"ነው. ይሄ ማለት አውሮፕላኑ በከፍተኛ ግፊት ስር ያለ ሜርኩሪን በኒኩለር ሀይል የሽክርክሪት ፍጥነቱን የሚጨምር ይሆናል.ከዛ ኘላዝማ ይፈጠራል. ይሄም ፀረ-የመሬት ስበትን በአውሮኘላኑ ዙሪያ ይፈጥራል.በአውሮኘላኑ የመሀለኛ ክፍል ውስጥ የኤሌክትሪክ ጥምጣም አለ እሱም የኤሌክትሮ-ማግኔቲክ ድራይቭ ይፈጥራል.እሱም ከ ኺግስ-ቦሶን ፊልድ(higgs-boson field) ጋር በኳንተም ደረጃ መስተጋብር ይፈጥራል ማለት ነው.ይሄ አይነት አውሮፕላን የተራ አውሮኘላን ሞተር ወይም የሮኬት ሞተር አይጠቀምም...ይልቁኑስ ከፍተኛ ሀይል የሚጠቀም ኘላዝማ የማስፈንጠሪያ መንገድ ነው የሚጠቀመው.ይህ የፀረ-የመሬት ስበት ቴክኖሎጂ ከ2ኛው የአለም ጦርነት በኃላ በኘሮጀክት "ፔፐር ክሊኘ" ስም ምርምር ሲደረግበት 70ዓመታትን ቆይቷል.አሮኘላኑ አፍንጫው አካባቢ የተራ አውሮኘላን ሞተር አለው.ይህም አቅጣጫውን ለመቀያየር ና ፍጥነቱን ለመጨመር ይጠቅመዋል.ብዙ ምሁራን የዚህ አውሮኘላን ዲዛይን ከ ዮ.ኤፍ.ኦ. ቴክኖሎጂ የተኮረጀ ነውም ይላሉ.አንዳንድ መፅሄቶችም በተለያየ ጊዜ ታዮ የሚባሉት 3መዓዘን በራሪ የ U.F.O መገለጦች በዚህ የስለላ አውሮኘላን የተፈጠሩ ሳይሆኑ አይቀሩም ብለው ዘግበዋል.
አብሪያቹ የነበርኩት ዶ/ር ቢኒ ነበርኩ መልካም ቀን.ህመም ከተሰማዎት በ online ክሊኒካችን እንጠብቆታለን "miracle medium clinic O.P.D " በ whatsapp button ኑ በኩል ይምጡ.
የካርዳሼቭ ስኬል(The KARDASHEV scale)
እ.ኤ.አ. በ1964 ዓ.ም የሶቭየት ህብረት ሳይንቲስቱ ኒኮላይ ካርዳሼቭ በጣም ያደገ ስልጣኔ አይነቶችን አሳይቷል.የ ስልጣኔዎቹ ደረጃ የሚለካው መጠቀም ና ማስቀመጥ በሚችሉት የሀይል መጠን ነዉ.ይህ ስኬል ሎጋርዝሚክ(logarithmic) ነው ማለት ቀዳሚው ከተከታዮ ስልጣኔ በጣም ያንሳል ማለት ነው.
በጣም ያደገ ስልጣኔ-1...ይሄ ስልጣኔ planetary civilization በመባል ይታወቃል.ይሄ ስልጣኔ በአንድ ኘላኔት ውስጥ ያለ ሀይልን በሙሉ መጠቀም ያስችላል.ከፀሀይ የሚገኘውን ጨምሮ ምድራችን 7×10^17 ዋት ያላት ሲሆን መጠቀም የቻልነው ግን 17.35 ቴራ ዋት ብቻ ነው.የአሜሪካው አስትሮኖመር ካርል ሳጋን(Carl Sagan) የስልጣኔዎችን መጠን የምንለካበት ቀመር አሳይቷል ማለትም K=log10 P-6/10... k=የስልጣኔ ደረጃ; P= ስልጣኔው መጠቀም የቻለው ሀይል በዋት ማለት ነው.ስለዚህ የአሁኑ የሰው ልጅ ስልጣኔ k=0.72 ነው.ቀሽሞቹ የሰው ልጆች አንደኛው ዓይነት ስልጣኔ ላይ እንኳን አልደረስንም.የኛ ስልጣኔ ዓይነት-0 ነው የሚባለው.ቲዮረቲካል ፊዚዚስቱ ሚቺዮ ካኩ(michio kaku) የሰው ልጅ የስልጣኔ ዓይነት-1 ላይ ከ100-200 ዓመት በኃላ; ዓይነት-2ን ከ ጥቂት ሺህ ዓመታት በኃላ;ዓይነት-3ን ከ100,000-1000,000ዓመታት በኃላ ይደርስበታል.ሰው የስልጣኔ ዓይነት-1 ላይ ሲደርስ የኘላኒቱን የአየር ንብረት ይቆጣጠራል በመሬት ላይ ና ውስጥ ያሉ ነገሮችን ሁሉ መጠቀም ይችላል.
በጣም ያደገ ስልጣኔ-2(advancedcivilization type-2)...ይሄ ስልጣኔ በአንድ የኮከብ ስርዓት ውስጥ ያለውን ሀይል በሙሉ መጠቀም የሚያስችል ነው.ይሄን ማድረግ የሚያስችሉን አሁንም በጥናት ላይ ያሉ መንገዶች አሉ.የመጀመሪያው የዳይሰን ስትራክቸርን(Dyson structure) መጠቀም ነው.ይሄ ነገር በአንድ የ ኮከብ ስርዓት ውስጥ ያለን ኮከብ ሀይል ሙሉ በሙሉ በመውሰድ ለስርዓቱ አባላት በሙሉ በበቂ ሁኔታ ማድረስ የሚያስችል ሲስተም ነው.ሲስተሙን ያስተዋወቀን ሰው ፍሪ ማን ዳይሰን ይባላል.ሁለተኛው መንገድ ደሞ ልክ ቻርጅ የስልጣን ባትሪ ውስጥ እንደምናስቀምጠው በአንድ የ ኮከብ ስርዓት ውስጥ ያለን ኮከብ ብላክ ሆል(black hole) ውስጥ በማስቀመጥ ሀይልን በአስፈላጊው የስርዓቱ ቦታ መጠቀም ነው.
በጣም ያደገ ስልጣኔ-3(advanced civilization type-3)...ይሄ ስልጣኔ Galactic civilization በመባል ይታወቃል.ይሄ ዓይነት ስልጣኔ ለማሰብ እራሱ የሚያስፈራ ነው.የሰው ልጅ ይሄ ስልጣኔ ላይ ከደረሰ በቢሊዮን የሚቆጠሩትን በአንድ ጋላክሲ ውስጥ የሚገኙ ኮከቦችን ሀይል ሙሉ በሙሉ ለፈለገው ነገር ሁሉ መጠቀም ይችላል ማለት ነው.ጋላክቲክ ሪል ስቴት(Galactic real estate) ማለትም ሰዎች በ ጋላክሲያቸው ውስጥ የመረጡት ቦታ ላይ ቤት ሰርተው መኖር መቻላቸው እውን ይሆናል.ጋላክሲ እንደ አንድ መንደር ይሆናል ማለት ነው በአጭሩ.
እስከ አሁን አብሪያቹ የነበርኩት ዶ/ር ቢኒ ነበርኩ መልካም ቀን. .በ አመማቹ ጊዜ ሁሉ የ online ክሊኒካችን "miracle medium clinic O.P.D" በፌስ ቡክ ፔጁ በኩል በቀን ለ24 ሰዓት ማንኛውንም ዓይነት የተመላላሽ ህክምና በ25 ብር ብቻ በቤቶ ይሰጣል!!!
ኢምፖስተር ሲንድረም(imposter syndrome)
ሀይ ወዳጄ ስንፈልግህ ነበር.አዎ አንተን.ስላንተ ሁሉንም ነገር እናውቃለን.የማታውቀውን እደምታውቅ ሆነህ ትታያለህ.አመታት የፈጀውን የትምህርት ቤት ቆይታህን በመተኛት እዳሳለፍከው, የማይገባኽን ሽልማት እንደተቀበልክ, በኺወትህ አንድ እንኳን ተገብቶህ ያገኘኸው ነገር እንደሌለ እናውቃለን.እኛ ፍቅረኛህ ፊት ግርማ ሞገስ እንዳለህ ልታሳያት እንደምትጥር እናውቃለን.ባይገርምህ ግን እሷን አትመጥናትም.ለጔደኞችህ የነገርካቸው ያ ቀልድ ስለሚያስቅ ሳይሆን እንዳይከፋህ ነው የሳቁልህ.ይሄን ሁሉ እናውቃለን አንተም ታውቀዋለህ አይደል?በማጭበርበር የተሞላህ ነህ.እድለኛ ባትሆን ኺወትህ የውድቀት ነው.በዚህ ጊዜ ግን እድለኛነት አያድንህም.ሰዓትህ አልቋል.አንድ ሰው የደረስክበት ስኬት እንደማይገባህ ቢያውቅ ሌሎቹን ሰዎች እንዴት ማሳመን ትችላለህ?
አንድ ስራ በከፍተኛ ብቃት ለመስራት በጣም ትለማመዳለህ ከዛ የሆነ ደረጃ ትደርሳለህ ግን እራስህን ከሌሎች ተመሳሳይ ሞያ ካላቸው ሰዎች ጋር ስታነፃፅረው አሁን የደረስክበት ደረጃ ያንተ ብቃት አጥጋቢ ሆኖ ሳይሆን በማስመሰል ና አጋጣሚዎችን በመጠቀም ያገኘኸው እንደሆነ ታስባለህ.ሰዎች ደሞ የማይገባህን አድናቆት ይሰጡሀል.አንተም አድናቆታቸው እንደማይገባህ ብታውቅም ቢያንስ ጥሩ ሰራ መባል ጥሩ ነው ትላለህ.
imposter syndrome የተሸናፊነት ስሜት እንዲሰማን የሚያደርግበት አንዱ ምክንያት ነገሩ እኛ ብቻ የሚሰማን ስለሚመስለን ነው.ይሄ ግን ከእውነት የራቀ ነው. ጥናቶች እንደሚያሳዮት 70%ቱ የአለማችን ሰዎች በ imposter syndrome ይጠቃሉ.እኔ ግን ቁጥሩ ከዛ በላይ እንደሚሆን አስባለሁ.በ አንድ ወቅት በተደረገላቸው ቃለ-መጠይቅ እነ jeniferlopez, Tom hank, Emma Watson "የሚቀረን ነገር አለ" ብለው መልስ ሰጥተው ነበር ስለዚህ ነገሩ እኛንም ቢያጠቃን ሊገርመን አይገባም.
እኛ የምንሰራውን ስራ እንደሆነ ለመስራት ምን ያህል ሰው ታድሏል?ምን ያህል ሰው የ youtube ቻናል ከፍቶ እንደኛ ሀሳቡን ለመግለፅ ሞክሯል?ብለን ብናስብ ትክክለኛውን ዋጋችንን መገመት እንችል ይሆናል.በ አንድ ቀን አንድ የአሜሪካ የባህር ሀይል ፓይለት በሀገሩ ሳይንቲስቶች ተጋብዞ ንግግር ሲያደርግ "እኔ እዚህ መቆም እንደማይገባኝ እየተሰማኝ ነው. እኔ ማን ሆኜ ነው እናንተን ለሚያካክል ሳይንቲስቶች መድረክ ላይ ቆሜ ንግግር የማደርገው?" ሲላቸው...አንዱ ሳይንቲስት ቀበል አድርጐ " ኒል አርም ስትሮንግ ጨረቃ ላይ የወጣኸው ብቸኛ ሰው አንተ ነህ ለዛ ነው" ብሎ መልሶለት ነበር.ይህን ማድረግ ብቻውን ከሰው ሁሉ የበለጥን ሊያስመስለን ይችላል.
በአጠቃላይ imposter syndrome ማለት እኛ ስለኛ በምናስበው እና ሰዎች ስለኛ በሚያስቡት መሀል ያለው ልዮነት ነው.የ imposter syndrome ተፅኖ ለአንዳንዶች የተሻለ ደረጃ የሚያደርስ ሲሆን ለአንዳንዶች ግን ተስፋ አስቆራጭ ይሆናል.
Imposter syndrome እንዴት ነው የሚመጣው?ከየት ነው የሚመጣው የሚለው ግን አይታወቅም.ምናልባት ልጅነታችን ;ምናልባት ቤተሰቦቻችን የፈጠሩብን ወይም ምንም ማለት ይሆናል.
አብሬአቹ የነበርኩት ዶ/ር ቢኒ ነበርኩ በክሊኒካችን " miracle medium clinic O.P.D" ማንኛውንም የተመላላሽ ህክምና በ online በቤቶ ሆነው በ 25 ብር ብቻ መታከም ይችላሉ. ለበለጠ መረጃ ፔቻችንን ይጐብኙ.
እርጅናን የምናዘገይባቸው በሳይንስ የተረጋገጡ መንገዶች
1.ሰን እስክሪን ለፀሀይ ተጋላጭ የሆነውን የሰውነት ክፍል የቀኑን የአየር ጠባይ ማሰብ ሳያስፈልገን በቀን አንዴ መቀባት
2.የቆዳ ድርቀትን የሚከላከሉ ሞይስቸራይዘሮችን በየ አራት ሰዓቱ ያለማቋረጥ መቀባት
3.በ እሲያ ሀገራት ታዋቂ ከሆነው ስር "ጂንሰንግ" የሚሰራውን የጂንሰንግ ሴረም/የጂንሰንግ ማስክ ፊታችን ላይ ማድረግ በ መጨረሻም በቀዘቀዘ ውሀ መታጠብ
4.ፊታችንን ማሳጅ ማድረግ(በተጨበጠ እጅ ከጉንጭ ወደ ኋላኛው መንጋጋ ከዛ ወደ ላይኛው አንገት በማድረግ ለ10 ደቂቃ ማሳጅ ማድረግ; ከዛ መሀል ጣትን በአይኖቻችን መሀል ማድረግ እና ጠቋሚ ጣትን በአይናችን እና በጆሯችን መሀል በማድረግ ወደታች ማሳጅ ማድረግ ለ10 ደቂቃ; ከዛ ወጣቶችን የጀርባ ጫፎች ከግንባር ወደ ከጉንጭ በላይ ወዳለው ቦታ በመሄድ አንድ ጊዜ በክብ ቅርፅ ማሳጅ ማድረግ ለ 10 ደቂቃ)
5.በቀን ከምግብ የምንወስደውን ካሎሪ መቀነስ. ይሄን ለማድረግ ብዙ ጊዜ የምንወስዳቸው ምግቦች ፍራፍሬ ና ቅጠላቅጠል(አቮካዶ, ብርቱካን, ሎሚ, ቃሪያ, ጥቁር ቸኮሌት, የጂንሰንግ ስር, ጥቅል ጐመን, ብሉ ቤሪ)ቢሆኑ ይመከራል.
6.መፀሀፍ ማንበብ
7.መደነስ
8.ስድስት እና ከዛ በላይ ጐደኛ ያለው ሰው መሆን
9.በቀን ቢያንስ ለ 8 ሰዓት መተኛት
10.ሻይ በቀን ከ 3-4 ጊዜ መጠጣት
ዝግጅቱን ያቀረብኩላቹ ዶ/ር ቢኒ ነኝ. ለማንኛውም ህመሞ በህክምናው ብዙ ልምድ ካላቸው ሀኪሞች ጋር በመሆን በ online ክሊኒካችን(miracle medium clinic)ላይ እንጠብቃችኃለን መልካም ቀን. ለበለጠ መረጃ ፔጃችንን ይጐብኙ!!!
We are here for you folks. Up on your request American specialist Doctors will wait to be consulted in our online clinic for only 500 ETB (10$). It is coming out of generosity in Good world citizens' heart....be wise and use the opportunity right now!!!
Note this We give service for only adults. For payment use mobile internet or telebirr and enjoy righteous quality O.P.D Medical service right at your home and save your thousands of birr to be spent on unnecessary expensive tests done by Greedy health institutions!!!
About 70% of illness faced by world community can be treated at O.P.D with outpatient treatment which can be done thru internet cheaply and with great convenience and privacy. That is what inspired us to avail this page to you folks. Welcome to the new era of technology and medicine.
Welcome to our medium clinic O.P.D. Anyone who seeks a fast medical outpatient department service our experienced Doctors can serve you for only 25 ETB(0.5$).
First you pay thru our account then you can get the treatment real quick on WHATSAPP.
Click here to claim your Sponsored Listing.
Videos (show all)
Category
Contact the practice
Website
Address
Topeka, KS
66603
5200 SW Huntoon Street
Topeka, 66604
Founded in 1871. This is the official page of the Kansas Dental Association. Please contact the KDA for advertising/marketing opportunities. Spam and unapproved marketing will ...
2727 SW Wanamaker Road
Topeka, 66614
Hello, My name is Nicole. I have been a massage therapists for over 9+ years. Are you in pain? Stubborn knots? I specialize in Deep Tissue. I am passionate about making my clients ...
1111 SW Gage Boulevard Ste 100
Topeka, 66604
🏆 BEST OF TOPEKA Weight Loss Center 2023 & 2024 🏆 BEST OF TOPEKA Women's Health Services 2024 | Medical 🩺 | Lifestyle 😀 | Injections 💉 ♥️A life-changing medical weight loss experie...
4646 NW Fielding Road, Suite C
Topeka, 66618
Medical alert buttons, medication reminders and medication dispensers.
631 SW Horne Street Suite 340
Topeka, 66606
Dr. Camille H**b • Dr. Audrey Roberts • Kathy Seim-Snyder NP 🔹Accepting patients 0-21. Dr. Stephanie Lind coming August 5th!
6001 SW 6th Avenue #110B
Topeka, 66615
We strive to provide the highest quality patient care and customer service with kindness & enthusiasm
1170 SW Mission Suite D
Topeka, 66604
First Responder. Studied Biology in College and Massage School. Managed medical office . Female.
623 SW 10th Street
Topeka, 66612
KHC is a nonprofit 501(c)3 organization dedicated to transforming health care in Kansas.
5865 SW 29th Street
Topeka, 66614
Weight Loss (Medically Managed), Testosterone Therapy, Affordable Lab Panels, and more…