Natanim photo studio

Natanim photo studio
Photos from Natanim photo studio's post 23/12/2023

ማቲዬ አመሰግናለሁ 🙏

23/12/2023

አንዳንድ ወዳጆች አሉ ጓደኛ መስለው ገብተው 🙄 ታላቅ ወንድም የሆኑ በችግር በደስታ ሁሉ ካጠገብህ የሚቆሙ ላንተ ትልቅ ቦታ መድረስ ላንተ ስኬት የሚመኙ ስትደክም የሚያበረቱ ጊዜና ገንዘብ ጉልበታቸውን ላንተ ሳይሰስቱ የሚሰጡ በኩራት የምትመሰክርላቸው 🙏
ወንድም እንደሽ ሁሌም አመሰግናለው ቅንነትህ ቁምነገረኛነትህ ሁሌም ይገርመኛል ብዙ ደስታ ብዙ ስኬት ብዙ ፍቅር ላንተና ለቤተሰብ እመኛለው 🙏

23/12/2023

212k view
#ስለወደዳችሁት #እናመሰግናለን 🙏
አሪፍ አሪፍ የተመረጡ የቤተሰብ ታሪኮችን ወደእናተ እናደርሳለን ላይክ ሼር ሰብሰክራይብ እያደረጋችሁ ETOP TV ዩቲዩብ ቻናል https://youtu.be/1jo65Y7tBvU

23/12/2023

📷 ፈገግ ስትሉ ዋሉ

22/12/2023

አሪፍ ፊልም እንጠብቃለን

22/12/2023

ጀግናው ወንድሜ እዮባ እንደተለመደው አስገራሚ ድምፁ ምርጥ ሙዚቃ ከጀግና ባለሙያዎች ጋር ያሰናዳውን አሪፍ ስራ ይዞ ተከስቷል ተጋበዙልኝ 🙏

Photos from Natanim photo studio's post 20/12/2023

ከፈጣሪ ለሚሰጥህ ውድ ስጦታ ምስጋና ለማቅረብ ታስብና ከስጦታው ታላቅነት የተነሳ ምስጋህን የሚገልፅልህ ቃላት ታጣለህ ❤
የደስታ ዕንባ ከልብ የሆነ ምስጋና ሁሌም በረከቱ ረድኤቱ ለማይለየን ቅዱስ ጊዮርጊስ 🙏

19/12/2023

ከስር ባለው ሊንክ እየገባችሁ ሙሉ ቪዲዮ ተለቋል ደሞ ቤተሰብ እየሆናችሁ
https://youtu.be/aDLq-vBq-RU

19/12/2023

ተመስገን 🙏

14/12/2023

አሪፍ ቢዝነስ ሃሳብ ያለው 100.000 እንደሚሸለም ለምን አልነገራችሁኝም ካለቀ ቡኋላ ምን ይሰራልኛል አስበላችሁኝ ለማንኛውም በቀጣይ ሲጀመር አስታውሱኝ ሲቭል ሆኖ ተደረጃቶ በዘመናዊ መንገድ የከተማውን ሌባ ተጋግዞ መያዝ ማስተማር ከዚህ ክፉ ተግባር እንዲለወጡ ማድረግ ነበር የስራ ፈጠራው 💪 አናምንም ጊዜ ተበላሽቷል የፈጠራ ብሩን ብንሰጥህም ይበሉሃል በጣም ዘምነዋል ለምትሉ እውነት ስለሆነ አልከራከርም 🙏

13/12/2023

ለዚህች አጭር ህይወት መልካም መስራት ቢያቅተን!ቢያንስ ለሰዎች የእንባቸው መንስኤ አንሁን😔

13/12/2023

ወደ ሜክሲኮ ሰዎች! ክፉና ደግ!

በተሳፋሪ በኩል ያለው መስተዋቱን ቀስ ብዬ ዝቅ እንዲል በጣቴ ስጫን አይኖቼ አንድ በ60ዎቹ መጨረሻ የዕድሜ ክልል የሚሆኑ አባት ፊት ላይ አረፈ። ከሁለቱም አይኖቻቸው እንባ ዱብ ዱብ እያለ ይረግፋል። ኪሶቻቸውን ይዳብሳሉ ይፈትሻሉ። እንባቸው ይብሱን ዠቅ ዠቅ አለ ደነገጥሁ እውነት ሳላስበው እንባዬ በአይኔ ሲሞላ ታወቀኝ እና

"አባት አባት ብዬ ጠራኋቸው" ሰምተውኛል አዩኝ አሁንም አይኖቻቸው እንባ እያፈለቁ ነው።

"ምን ሆነው ነው ምን ገጠመዎት?" አልኳቸው መኪና ዳር አሲይዤ እየቆምኩ

"ዘረፉኝ ልጄ ዝርፍ አደረጉኝ የልጆቼን የዕለት ጉርስ መግዣ ዘረፉኝ ለአውቶብስ እንኳን ሳያስቀሩ ወሰዱት ይይይ እመብረሃን ምን አደረኩሽ"

እንባቸው ተንዠቀዠቀ የምር እኔ ሰው ሲያለቅስ አልችልም እንባዬ በፊቴ ላይ ሲወርድ ሞቀኝ
"አይዞን ምን አባቱ አባ እኔ ልሸኞት ወደ ቤትዎ የት ነው ሰፈርዎ?"
"ኧረ ሩቅ ነኝ ልጄ ወደ ኮተቤ ነኝ ካራ"
"ውይ የሰፈሬ ሰው ኖታ ኑ ግቡ በቃ አደርሶታለሁ "

እንባቸውን እየጠራረጉ ገቡ። ትራፊኩ ፊሽካ ነፋ ቆምኩ። እዚህ ጋር መቆም አይቻልም መንጃ ፍቃድ አለኝ የሆነውን ነገርኩት ወደ አባ ዞር ብሎ ሰረቆት ብዙ ብር ነው አላቸው። በእንባ የጨቀዩ አይኖቻቸውን ከኪሳቸው አውጥተው በማህረብ እየጠረጉ

"አይ ልጄ አምስት ሺ ብር እኮ ነው ልጄ ለፍታ የላከችውን ለወሮበላ ያስበላሁት" አሉና ድጋሜ ስቅስቅ ብለው ሲያለቅሱ ትራፊኩ እንደ እኔ እንባው ቀደመው ኮፍያውን ውልቅ አድርጎ ግራ በተጋባ ስሜት ኪሱ ገባ

"ሜክሲኮማ በቃ የሌባ መናህሪያ ሆነ አይዞት በቃ አባቴ አንድ ሺ ብር ነው ያዙት ብሎ አስቀምጦ "ውጣ በቃ " ብሎኝ እንባ ያቀረሩ አይኑን እየጠረገ ሄደ።

ሰውዬው ለቅሷቸው አልቆመም። ስለህይወታቸው እያወሩኝ እምባዬ በአይኔ እየሞላ መገናኛ ልንደርስ ስንል የምሰራበት ቢሮ ደንበኛ የሆነ አንድ ወዳጄን መንገድ ላይ ቆሞ አገኘሁት። አጋጣሚ መኪናው ተበላሽቶ ገራዥ አቁሞ ወደ ቤቱ ሊሄድ እራይድ ሊጠራ ነበር። እሱንም ጭኜው እኝህ ምስኪን አባት የገጠማቸውን ሲያወሩት አለቀሰ። በቤተሰብ ችግር ምክንያት ከኖሩበት ተገፍተው ንብረታቸውን አጥተው እዚህ ጥበቃ ሆነው እንደሚሰሩ ወዘተ ሲያጫውቱን እሱም እንባ ከአይኑ ቀደመው። የሰራቋቸውን ተራገመ ተሳደበ። ሊወርድ ሲል ኪሱ ገባ ብር ቆጠረ፣ ሰባት ሺህ ብር ቆጥሮ ሰውዬው እንቢ ቢሉም አስቀምጦላቸው ወረደ።

ውስጤ በደስታ ተሞላ አንዳች የተቀደሰ ነገር ያደረገ መሰለኝ። አንተ የተባረክ ልጅ ነህ ክፉ አይንካህ ዘርህ ይባረክ አቤት ምርቃት ከእንባቸው ጋር አጅበው መረቁኝ እጄን ሳሙኝ። ስምህ ማነው ልጄ አሉኝ አቤል አልኳቸው ስልክህን ፃፍና ስጠኝ አሉኝ ሰጠኋቸው። የእውነት በድጋሜ እንባዬ ዱብ ዱብ አለ። ተከራይተው ከሚኖሩበት ሰፈር አድርሻቸው ተመለስኩ።

ኧረ ሌቦች ግን የሚሰርቅ ሰው እንኳን ምረጡ። ሜክሲኮ መገናኛ ኧረ ቢያንስ አቅመ ዳካሞችን ምስኪኖችን አትስረቁ። እውነት እንባም ይጥላል እንቅፋትም ያስመታል።

መልካም ያደረጋችሁ ልበ ቀና ደጎቹ ትራፊኩና ወዳጄ ዞላዬ ግን ውለታው ከፈጣሪ ነው እግዚአብሄር ያክብርልኝ !!

ቸር ዋሉልኝ !!
አቤል ወርቁ ዘ-ኮተቤ

12/12/2023

እዚህ ሀገር ስንት የሚያስቅ ህግ ወጣ 😂
ሰው የሚገሉ ሰው የሚዘርፉ ዳግም ወደዛ ወንጀል እንዳይገቡ ትልቅ ህግ እንደማውጣት ሻይ አዞ ወደቀኝ ያማሳለ ይቀጣል ምናምን ቅብርጥሴ አረ ወዲያ ምናለ የሚቀድመውን ብታስቀድሙ እንደው 🙏 በተለይ እየተባባሰ የመጣው የመኪና ስርቋት የሞባይል ስርቆት በቅርቡ ebs ላይ ምናምን ስፖንሰር ሁሉ አድርገው የሚተዋወቅ ነው የሚመስለኝ 😂 ሰው ዳግም ወደዛ ወንጀል እንዳይገባ እንደ ሀገር ቶሎ ጥሩ ህግ አውጡና ስሩልን 🙏??
#ከመቶ ትንሽ ፐርሰንትም ቢሆን ያው ተከታትላችሁለምትይዙት አክብሮት አለኝ 🙏

12/12/2023

Photos from Natanim photo studio's post 12/12/2023

🙏🙏🙏❤️❤️❤️

ቤዛ

ከ 1 ቢሊዮን የኢትዮጵያ ብር በላይ ወጪ በማድረግ የአርባምንጭ " ዝጊቲ ቤተክርስቲያን " እያሰራች ያለች ድንቅ ሴት::

እረጅም እድሜ ከጤና ጋር ይስጥልን

🙏🙏🙏❤️❤️❤️

ጉርሻ ✍️
🌴🌴🌴

12/12/2023

ለአንዱ ፈታሽ ፖሊስ ስልኬ ላይ ያለው የቦብ ማርሌ ፎቶ እንጂ ሸኔ እንዳልሆነ ሳስረዳ ያመሸሁበት ሁኔታ ነው ያለው😂😥

12/12/2023

ታርዬ

አንድ አመት 😭

ስለነበረን ጓደኝነት
ደግ ስለነበርክ
ስለሰጠከን ስራዎች
ስለተማርኩብህ

ሁሌም በልቤ ትኖራለህ ❗️
CChernet fikadu - ቸርነት ፍቃዱ✍️

Photos from Natanim photo studio's post 11/12/2023

#ስለ #አንድ #ብዙ #ያልተነገረለት #ጀግና ትንሽ ልበል 🙏

የማቀው በዝና ነው ብዙዎች ጀግናው አሰልጣኝ ይሉታል የተዋወኩት እኛ አካባቢ በከፈተው ዘመናዊ ጂም ነው የሚገርመው ቢኒ አሰልጣኝ ብቻ አደለም ለትንሹም ለትልቁም የሁሉም ሰው ወንድም ጎደኛም ነው ። በተለይ ሰዎች ባለው ነገር ማገዝ መተባበር ተፈጥሮ ነው ። ሁሌም ሀቀኛ ቅን ሰው ትገርመኛለህ ሁሌም ደስታው የሚያሰልጥናቸው ልጆቹ ትልቅ ቦታ ደርሰው ማየት ፈጣሪም አላሳፈረውም በርካታ ቢኒ ያሰለጠናቸው ልጆች በተለያዩ ዓለማት ድንቅ ብቃታቸውን እያሳዩም ነው 🙏 ሰሞኑን እንኳን ሁለት ቡድን ለረጀም ጊዜ ሾ ለማቅረብ ግማሹ እንግሊዝ ግማሾቹ አሜሪካ ሲሄዱ አስታውሳለው ለዚህም ስለበቁልህ ሁሌ እንኳን ደስ አለህ ማለት እፈልጋለው 🙏 አንዳንዴ ባገኘውት አጋጣሚ ሁሉ ሁሌም ሃሳቡ ልጆቼ የተሻለ ደረጃ ደርሰው ቤተሰባቸውን እንዲያግዙ በዲስፕሊን የታነፁ እንዲሆኑ ነው እንዲህ ያለ ጀግና በቁጥር ትንሽ ነው ። ወደ ግል ብቃቱ ስመጣ ያልተሸለመው ነገር ያለ አይመስለኝም ስለሚገባ አክባሪህ ነኝ ። ለሰዎች ደግ ማሰብ ቅንነት ሰዎችን ሁሌ ደራሽ በአካባቢው ተወዳጅ ሰው ጥቀስ ብባል ግንባር ቀደም አንተ ነህ ቢኒ ጀግናችን ሁሌም ያሰብከው ይሳካ 🙏
ቢኒን የምታቁት የምትጨምሩት አክብሮት ካለ ኮመንት ላይ አስቀምጡ 🙏

Photos from Natanim photo studio's post 10/12/2023

ሮዚ በእነዚህ ምርጫዎች መሀከል ናት

🎯 የቱን ትምረጥ?!

ይህችን ወጣት ኬንያዊት ብዙዎቻችሁ ታውቋታላችሁ ።

ኑሮን ማሸነፍ ባለመቻሏ ፡ ሦስት ልጆቿን ትታ ወደሊባኖስ የተሰደደችው ሮዚ ለአመታት በቆየችበት የሊባኖሳውያኑ ቤተሰብ ውስጥ ከሞግዚትም አልፎ እንደ አንድ የቤተሰባቸው አባል ስላደረጓት ፡ ሰሞኑን ወደ ኬንያ ተጉዛ ልጆቿን ለማየት በወሰነችበት ወቅት ፡ ሊባኖሳውያኑ ወላጆችና ፡ ሮዚ ያሳደገቻቸው ልጆች ያላንቺ አይሆንልንምና ተመልሰሽ እንደምትመጭ ቃል ግቢልን ሲሏት ታይቷል ።.......
የአመቱ ምርጥ ሞግዚት የሚል ስያሜ የተሰጣት ኬንያዊቷ ሮዚም ፡ተመልሳ እንደምትመጣ ቃል ገብታ ፡ ለአመታት አብራቸው ከኖረችው ቤተሰቦች ጋር ተላቅሳ ወደ ሀገሯ ኬንያ ከገባች ቀናት ተቆጥረዋል ።....
እናም ይህ ቪዲዮ በቲክቶክ ተለቆ ከ134 ሚሊየን ሰወች በላይ ከተመለከቱትና በመላው አለም ቫይራል መሆኑን ተከትሎ ለሮዚ የተለያየ አድናቆት እና የምስጋና ቃል ከማቅረብም ባለፈ ፡ አንድ የጉዞ ድርጅት ፡ ለሮዚ ያላሰበችውን እድል አቅርቦላታል ።

Vintmark Travel Agency የተባለው የዚህ ድርጅት ዳይሬክተር የሆነችው Catherine Joe እንዳስታወቀችው ፡ የሮዚን መልካምነት ካየች በኋላ ፡ ለዚች ምስጉን ሞግዚት ፡ በካናዳ መማር እና መስራት የምትችልበት ቪዛ እና ይህ ፕሮሰስ እስኪያልቅም በወር 30 ሺህ የኬንያ ሽልንግ ደሞዝተኛ የምትሆንበትን ጊዜያዊ የስራ እድል እንዳመቻቸችላት ተናግራለች ።.......
ይህ የሮዚ መልካምነት ያመጣው እድል ፡ በቀላሉ የማይገመት ትልቅ ነገር ነው ። ሆኖም ሮዚ ፡ የቱን እንደምትመርጥ ጨንቋታል ።

ከእቅፏ አንላቀቅም ብለው በእንባ የሸኟት ሊባኖሳውያን ቤተሰቦቿን ፡ ተመልሳ እንደምትመጣ ቃል ገብታላቸዋለች ።

አሁን ደግሞ ፡ የነጻ የትምህርትና ፡ የስራ እድል እንስጥሽ የሚሉ መልካም ሰዎች ሀሳባቸውን ነግረዋታል ። ይህ ከተሰማና ፡ ሮዚ ባልታሰበ መልኩ ዝነኛ ከሆነች በኋላም ፡ ሊባኖሳውያኑ ቤተሰቦች ፡ በርግጥ እሷን ማጣት ከባድ ቢሆንም ከልጆቿ ጎን ሆና ለማሳደግ የሚያስችል ፡ የተሻለ እድል ካጋጠማት ቃሏን ጠብቃ ባለመምጣቷ እንደማይከፉ ነግረዋታል ።

ሮዚ አሁን በዚህ መሀል ናት ። ....
አየህ ፡ ቅን እና ጥሩ ሰው ስትሆን ፡ በብዙ መልካም ነገሮች ትከበባለህ ።

Wasihun Tesfaye

10/12/2023

#ሸንኮራ #የምትወዱ #እያዘዛችሁ 🙏

የኔ ጀግና አቤት ትህትና አቤት ምርቃት አቤት ብርታት 🙏
ብርትት ብሎ ፈጣሪን እያመሰገነ የሚሰራ ሰው ሳከብር 🙏
በጦርነቱ ምክንያት መንገድ ስለተዘጋ ነገሮች ሰላም ሆነው ወደቀያቸው እስኪመለሱ እንደው ቁጭ ከምል ልስራ ብዬ ነው ልጆች ባለቤቴም ከገጠር ናቸው አሁን ሸንኮራ ከ ሩቅ እያመጡ በየመንገዱ እያዞሩ ይሸጣሉ ማማረር የለ በፈገግታ በምርቃት ፈጣሪ ይመስገን ሰዎች በቃ ጠርተው አባቴ ሸንኮራ እያሉ ይገዙኛል ደሞ ምርቃታቸውስ አቤት እንዴት ደስ እንዳሉኝ ሀሙስ ይመጣሉ ሸንኮራ እንደኔ ምትወዱ ለማበረታታት አገዙም 🙏 ደሞ ለማበረታታት ለአባታችን ጫማና ከተገኘም ልብስ የሚገዛልኝ ሰው እፈልጋለው ሰርፕራይዝ ባደርጋቸው ሸንኮራ ከፈለጋችሁ በፈለጋችሁት ብር ግዙ ዴሊቨሪ እናደርጋለን 🙏
በሰላም ዋሉ ሁሌም እንዲህ ጀግና ብርቱ ስታገኙ ለማበረታት ግዙ ከተቻለም ቲፕ እየሰጣችሁ 🙏

09/12/2023

ጁመአ ሙባረክ
ብራዘር 🙏

09/12/2023

ሙሉ ቪዲዬ ከስር ባለው ሊንክ ይመልከቱ እናመሰግናለን
https://youtu.be/ZOgU2ku4yx4

Photos from Natanim photo studio's post 08/12/2023

#የኔ #ጀግና #አባት 🙏

ዛሬ በጣም የምወደው አባቴ ለ 15 ዓመት በታማኝነት ከሰራበት የኢትዮጵያ መድን ድርጅት
በክብር ተሸኝቷል :: አባቴን አክብራችሁ በክብር እና በፍቅር ስለሸኛችሁት የስራ ባልደረቦቹ ከልብ እናመሰግናለን 🙏 አባቴ በጣም እወድሃለው አባቴ የቤታችን ድምቀት በጣም እንወድሃለን አንተ ብዙ የሚገባህ ጀግና አባት ነህ 🙏አንተ የኛም የሁሉም አባት ነህ 🙏 በስራ ባልደረቦች በዚህ ደረጃ በአክብሮት መሸኘትህ እድሜ ጤና ስጥቶ ለዚህ ስላበቃህ ደስ ብሎናል 🙏 በድጋሜ አባቴን ስላከበራችሉልን ስላስደሰታችሁልን ሙሉ ቤተሰቡ ምስጋናውን ያቀርባል 🙏🙏🙏

Photos from Natanim photo studio's post 07/12/2023

#ሀበሻ ቢራ #ለኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ በስጦታ የሰጠው አዲሱ ዘመናይ ባስ ?Natanim photo studioooo📷

05/12/2023

የኔ ወንድም የኔ ሰው አክባሪ እንኳን ተወለድክ ቀሪ ዘመንህ ከምትወዳቸው ጋር ነፍ ዓመት በደስታ ያኑርህ 🙏
Millikidu Berhane🙏

04/12/2023

ክፍያውን በሰማይ ሊያደርጉለት ነው - ነቃፊዎቹ።
ደስ ይበለው!
እሸቱ መለሰ
እግዚአብሔር አገልግሎቱን ይባርክ!!
ያሬድ ሹመቴ ✍️

04/12/2023

ከፊልም ስራዎች የጠፋው ተወዳጁ የፊልም ተዋናይ አለምሰገድ በአዲስ ፊልም ስራ ተከስቷል

04/12/2023

ሰላም ዋሉ 🙏

Photos from Natanim photo studio's post 03/12/2023

ሂዊ ከቀናት በፊት ማታ ላይ ስትደውልልኝ አላነሳሁም ነበር!እንዳየሁት መልሼ ስደውልላት "አንድ ጉዳይ አስጨንቆኝ ነበር ሳታነሳ ስትቀር በራሴ ለመፍታት እየሞከርኩ ነው" አለችኝ!! "ምን ነበር ምንድነው?" ብዬ ስጠይቃት "አንድ ልጅ ራሱን ሊያጠፋ ፎቅ ላይ ሆኖ ደወለልኝ ስራ እንዲያገኝ እየሞካከርኩለት ነው ተስፋ የሰጡኝ ስላሉ የከበደኝ ነገር ካለ አሳውቅሀለው"አለችኝ!!

ይኸው ከቀናት በኋላ ስለራሷ ጉዳይ እንባ እየተናነቃት "አድኑኝ"ብላ ስትማፀን ሰማኋት!!

እናንተ ልበደጎች ለብዙዎች ሳቅ ምክንያት የሆነችው እህታችን አብሯት ለረጅም ጊዜ የቆየ vein fistula የሚባል የእጅ ህመም ታማ "አስቸኳይ የውጭ ህክምና ያስፈልግሻል" ተብላለች! የምንችለውን እናግዛት #ሼር በማድረግ እንድረስላት🙏
#አካውንት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000181181129-ህይወት መስፍን
"ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም"

Heni ✍️

Photos from Natanim photo studio's post 02/12/2023

🇪🇷 አሥመራ

| የአማናዊት ጽዮን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እና የታቦተ ጽዮን ክብረ በዓል 🙏
አንድ ቀን ሀገርም ዓለምም ሰላም ሆና በየቦታው የኦርቶዶክስ የሆኑ ቦታዎች ላይ መሄድ እንዲህ ያሉ ቀኖችን ማየት 🙏

Photos from Natanim photo studio's post 01/12/2023

የቤት ስም እየወጣላት ድምፅ ስጡ
#ልዕልት
#ኒሻን
#ፍቅር
#በፀሎት
#ወርቄ
#ዲና
ጥሩ ስም ካለ ተቀባይነት ያገኛል ድምፅ ስጡ
Natanim photo studioo📷

01/12/2023

የኔ ዓለሞች ❤
በነገራችን ላይ በማማ ብዙ ነገር አይቻለው በተለይ ስለ እናት እናቶች ጀግኖች ናችሁ ማርያምን የማትሰለቹ የማትደክሙ የልጃችሁ ነገር እያንዳንዶ ነገር የሚሰማችሁ ብቻ ለሁሉም እናቶች ፈጣሪ ብርታት ሰላም ጤና ፍቅር ይስጣችሁ 🙏

01/12/2023

https://youtu.be/1jo65Y7tBvU
ሙሉ ቪዲዬ ከላይ ባለው ሊንክ ዩቲዩብ ላይ ያገኙታል

01/12/2023

ለማርያም 🙏
በማለዳ እዚህ ስፍራ ላይ መገኘት ያለው ሰላም 🙏

Photos from Natanim photo studio's post 23/11/2023

ሆሆ
እውነት አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የየት ሀገር ሰው አረከኝ 😀😀
ለማንኛው ለቀጣይ ፊልም ስራ ዝግጅት ሲባል አንድ ሳምንት ከፌስቡክ ጡረታ ወጥተናል 🙏 ይቺን ነገር ግን እናተም ተለማመዶት ለጥሞና ይረዳል በተለይ የሚተርፋችሁ ጊዜ 💪

23/11/2023

ከነገ ጀምሮ የፈለጋችሁበት የዓለም ሀገር ማንነታችሁን በሚገልፅ መታወቂያ ብቻ ሂዱ ቢባል እስኪ መሄድ የምትፈልጉ ?

23/11/2023

አንዱን ጓደኛችን አሜሪካ ሊሄድ ቦሌ ልሸኘው ሄደን እኛን ስያየን ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ ተው አይለቀስም እንለዋለን ለእናንተ እኮ ነው የማለቅሰው እዚህ ለምትኖሩት አላለም
make

23/11/2023

ከአርብ ህዳር 14 ጀምሮ በዓለም ሲኒማ ፣ በአዶት ሲኒማ ፣ በፖወር ሲኒማ እና በመንግስት (አምፒር ፣ኢትዮጵያ ፣አምባሳደር ) ሲኒማ ቤቶች ብቻ ይታያል

Spacial thanks





.7

ሼር ስለምታደርጉት አመሰግናለሁ

Chernet fikadu - ቸርነት ፍቃዱ💪

fikadu - ቸርነት ፍቃዱ

22/11/2023

በጣም የምወደው 📷 ነው ።
ሁሌም የምቆጭበት ነገር ቢኖር አድዋ የእግር ጉዞ ባለመሳተፌ ወደፊት ሁሉ ሰላም ሲሆን የዚህ ታሪክ አካል ብሆን ምኞቴ ❤

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in St John?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Videos (show all)

ከስር ባለው ሊንክ እየገባችሁ ሙሉ ቪዲዮ ተለቋል ደሞ ቤተሰብ እየሆናችሁ https://youtu.be/aDLq-vBq-RU
ሙሉ ቪዲዬ ከስር ባለው ሊንክ ይመልከቱ እናመሰግናለንhttps://youtu.be/ZOgU2ku4yx4
https://youtu.be/1jo65Y7tBvU ሙሉ ቪዲዬ ከላይ ባለው ሊንክ ዩቲዩብ ላይ ያገኙታል
#በችግሬ #ደረሳችሁልኝ ባለፈው አንድ  ፍላት ቲቪ ለአንድ እናት  ግዙልን  ብለን  ፖስት አድርገን  ነበር 🙏  እድሜ ለእናተ ደጋጎች በርካቶች ሼር አድርገውት  ወዲያው አንድ ቀን ውስጥ 4 ...
ቃልዬ እንኳን ተወለድሽ  🎉 በቃ ሁሌም ፎቶቹ ላይ እንዳለሁ ከልብ የእውነት እየሳቅሽ እንድትኖሪ ነው ምኞቴ ❤️ እንደ ጨረቃ አምረሽ፣ እንደ ከዋክብት ደምቀሽ፣ በእግዚአብሔር በረከቶች ተከበሽ...
🙏
https://youtu.be/znyqQ0NcQJIሙሉ ቪዲዬ ከላይ ባለው ዩቲዩብ ሊንክ  ተለቃለች ደሞ ሞክሯት ስጦታ ለሚስቶች መስጠት ያሰባችሁ 🤙
❤️🙏
ዛሬ ምሽት እንገናኝየከተማችን ምርጡ ቦታthe wave club and lounge presents
አብሮነታችን ይልቃል የተጋራነው ይበልጣል
አብሮነታችን ይልቃል የተጋራነው ይበልጣል
የልቡን ለነገርሽ 🙏

Category

Telephone

Website

Address


St John