ሳይኮሎጂ-Inner Motivation Videos

Videos by ሳይኮሎጂ-Inner Motivation. ራስን ለማወቅ የሚረዱ ጥያቄዎች, ኮመንቶች እና ማብራሪያዎች የሚገኙበት የሳይኮሎጂ ገፅ ነው::

ራስን, አካባቢን, አለምን መቀበል መቻል...... Accpetance

Other ሳይኮሎጂ-Inner Motivation videos

ራስን, አካባቢን, አለምን መቀበል መቻል...... Accpetance

ለካ ምላሴን አልወደውም ነበር 🤔😄

መቀበል እረፍት ይሰጣል! https://youtu.be/2X2SAvcgxRQ?si=jCmOGeGHp5PzvVB2

Communicate with your emotions.

ነፃነትን ማግኘት የሚቻለው በኃላፊነት ውስጥ ነው

ስንፍህን አምነህ መቀበል እንጂ ማብራራት ምን ያደርጋል! ስንፍና በማድረግና ባለማድረግ መካከል ልዩነት እንዳናይ ይሸፍንብናል!

የምንኖርበትን አካባቢ መቋቋም ሲያቅተን እናፍራለን!

16,000 ተከታይ ደርሰናል እናመሰግናለን!

ስሜት ምንድን ነው? ስሜት ሰውነት ምላሽ የሚሰጥበት መንገድ ነው። አሁን ሰውነቴ ውስጥ እየተካሄደ ያለውን የማውቀዉ በሚሰማኝ ስሜት ነው። ብዙዎቻችን እንደምንለው ስሜት እንዲሁ የሚነዳን ወይም ጠላታችን አይደለም። አሉታዊ ስሜቶች ልክ ያልሆነ ነገር እንዳለ የሚጠቁሙንና ማድረግ የሚገባን ነገር እንዳለ አመላካች ናቸው። አዎንታዊ ስሜቶች ላደረግነው ትክክለኛ ድርጊት ማረጋጫ ናቸወ። ለምሳሌ ረጅም ሰዓት ስራ ላይ የቆዬ ሰው የድካም ስሜት ይሰማዋል። ይህም ሰውነቱ እረፍት እንደሚፈልግ መልእክት ነው። ሰውነትም በቂ እረፍት ሲያገኝ የመነቃቃትና ዘና የማለት ስሜትን ይናገራል። ነገር ግን ያለ በቂ እረፍት ስራችንን ብንቀጥል ሰውነት የድካም ስሜትን መንገር እየቀነሰ ይሄዳል በሇላም ዝም ይላል። ታዲያ በዚህ ግዜ አንዳንድ ሰዎች ምንም ያህል ብሰራ የድካም ስሜት አይሰማኝም፤ ሰርቼ አልጠግብም ይላሉ። ያልተረዱት ነገር ሰውነት መልስ መስጠት ሲያቆም እየደከመና እየሞተ መሆኑን ነው። ህመሞችን እያከማቸ መሆኑን አናውቅም። የሰውነታችንን መልእክት ግዜ ሰጥተን ብናደምጠው ሰውነታችን በጣም ጤናማና ረጅም ግዜ የሚያገለግለን መሆን ይችላል። ስሜትን ባለማድመጥና በመካድ ጤናማ መሆን አይቻልም። ስለዚህ ስሜት ጠቃሚና ቦታ ሰጥተን ልናደምጠው የሚገባን ነገር ነው!

የትኛውም በእኔ ህይወት ላይ ጉዳይ በሙሉ መኖር የሚችለው ቅድሚያ እኔ ስኖር ነው፡፡ የኔ ህይወት ማዕከል እኔ ነኝ!