Elias Girma Pastor, Johannesburg Videos

Videos by Elias Girma Pastor in Johannesburg. Pastor

እንኳን ለ2017 ዓ.ም. በሰላም አደረሰን 🌼🌼🌼

መልካም አዲስ ዓመት 🌻

Other Elias Girma Pastor videos

እንኳን ለ2017 ዓ.ም. በሰላም አደረሰን 🌼🌼🌼 መልካም አዲስ ዓመት 🌻

"በፖለቲካ አቋም፤ በኢኮኖሚ ቁመና እና ዘር ላይ የተመሰረተ ክርስትና ክርስትና አይደለም።"

እህቴ አሁንም እግዚአብሔር ያጽናናሽ

ኢየሱስ ተነሥቶአል!!

ፋሲካችን… ወቅቱ ከአባቶቻቸው በትውፊት የወረሱትን የፋሲካን በዓል ለማክበር ሽር ጉድ የሚሉበት ነው። እንደ ልማዳቸው የሕጉን ትእዛዝ ለመፈጸም አይሁዳውያን ከየአቅጣጫው ወደ ኢየሩሳሌም ለክብረ በዓሉ በጥድፊያ ላይ ናቸው። የዛሬውን በዓል ግን ለየት የሚያደርገው እውነተኛው ፋሲካ ክርስቶስ ታዳሚ መሆኑ ነው። የሚገርመው ግን ለበዓሉ ከመጡት ግምት የሰጠው ሰው ያለ አይመስልም፤ ከተወሰኑት ቀናት በኋላ በማስተዋሉና በመልሱ ከመገረም ውጪ (ሉቃ2፡41-47)። በዓል በራሱ ክፉ አይደለም። ነገር ግን ለበዓሉ ጌታ ጀርባን ሰጥቶ የበዓል አፍቃሪ መሆን ዘላለማዊ ፋይዳው አይታየኝም። ፋሲካን ስናከብር ከመብላትና ከመጠጣት ባሻገር ቆም ብለን ልናነሳው የሚገባ ጥያቄ አለ፡፡ ለምን ተጨነቀ? በአፉ ተንኮል ሳይገኝ፣ ምንም ወንጀል ሳይሠራ፣ ከአመጸኞች ጋር ለምን ተቆጠረ? የፖለቲካ፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ ከሕዝቡም አብላጫው በግድያው ለምን ተስማሙ? የታመሙትን በፈወሰ? በአጋንንት የተያዙትን ነጻ ባወጣ? በሺህ የሚቆጠሩትን በመገበ? ይህ ያሸልመው እንደሆነ እንጂ እንደ ወንጀለኛ የሚያስቆጥረው አይደለም ። ይባስ ብለው ኪስ አውላቂውን፣ ቤት ሰርሳሪውን፣ የማሕበረሰቡ ጠንቅ የሆነውን በርባንን ፍታልን፣ ኢየሱስ የተባለውን ንጹህ የእግዚአብሔር ልጅ ስቀለው፣ ስቀለው፣ ብለው በአንድ ድምጽ አስተጋቡ መልካም ካደረገላቸው ከኢየሱስ ይልቅ ዘራፊው

ዘወትር እሁድ ማለዳ ከ4:30 ዕሮብ ከምሽቱ 1:00 ጀምሮ አድራሻ፡173 Queen.St Kensington Johannesburg 2094

"ዓለም ተስፋ ቁረጭ አልተገናኘንም"

ዛሬ ምሽት ከ1:00 ሰዓት ጀምሮ አድራሻ፡173 Queen.St Kensington Johannesburg 2094

ዘወትር እሁድ ማለዳ ከ4:30 ዕሮብ ከምሽቱ 1:00 አድራሻ፡173 Queen.St Kensington Johannesburg 2094

ግሩም መልዕክት ነው አድምጡት ብልጫ ያለው የጌታ ማህበር one of my best friends ኤርሚ ጌታ ኢየሱስ ይባርክህ።

በዚህ መዝሙር የተጽናናችሁ፣ ያለፋችሁ እንደ እኔ ትኖሩ ይሆን? የሆነ ዘመን ያስታውሰኛል፡ ወግ ያለው ክርስትና። ወንጌል በገባኝ የመጀመሪያዎቹ ጊዜ አካባቢ በሕይወቴ ተጽዕኖ ካደረጉ የኳየር ዝማሬዎች የጌጃ ቃለ ሕይወት፣ የደብረዘይት ምስጋና ቤ/ን፣ የናዝሬት ሙሉ ወንጌል፣ የወላይታ ሙሉ ወንጌል፣ የአዲስ አበባ ሙሉ ወንጌል…ካስታወስኳቸው። አሁን ድረስ አቅም ያላቸው። እግዚአብሔር ይባርካችሁ።