Elias Girma Pastor

Elias Girma Pastor

You may also like

SALEM MEDEA
SALEM MEDEA

Pastor

11/09/2024

እንኳን ለ2017 ዓ.ም. በሰላም አደረሰን 🌼🌼🌼

መልካም አዲስ ዓመት 🌻

08/09/2024
02 Yahweh | ያህዌ | Meskerem Getu 31/08/2024

02 Yahweh | ያህዌ | Meskerem Getu Music Arrangement - Elias KassahunChoir Arrangement- Ermiaas MollaBackground Vocal - Hildana Shibabaw, Naod Shibabaw , Ermias Molla Recording - Mesfin DensaM...

Photos from Elias Girma Pastor's post 21/08/2024

👉…ኢየሱስ ያድናል!!!

👉…ወንጌል ለሁሉም ሁሉም ለወንጌል!!!

"…ስለ ወንጌል ሁሉን አደርጋለሁ" 1ቆሮ9:23

28/07/2024

"በፖለቲካ አቋም፤ በኢኮኖሚ ቁመና እና ዘር ላይ የተመሰረተ ክርስትና ክርስትና አይደለም።"

19/07/2024

“… ትዕግስቱን ሁሉ ያሳይ ዘንድ፥ ምህረትን አገኘሁ።”
1ጢሞ(1፥16)

05/07/2024

ቆይ ተረጋጋ! ድንጋዩን አስቀምጠው፣ ሰይፍህን ወደ ሰገባው መልስ።
ብዙ ጊዜ ለራስህ የሰጠኸውን የይቅርታ ዕድል ጥቂቱን እንኳን ለሌላው አትንፈገው።

ዛሬ ይቅርታ መስጠትህ ግን ነገ ላለመበደልህ (ላለመጎዳትህ) ዋስትና ይሰጥሃል ማለት አይደለም።

እውነት ነው የበደሉን ክብደትና ተደጋጋሚነት ያስከተለውም ጉዳት ዛሬ ድረስ ያልሻረ ሊሆን ይችላል።

ይቅር ከማለት ውጪ የተሻለ አማራጭ የለም።

ይቅርታ ስነ ልቦናዊ፣ አካላዊ፣ ማሕበረሰባዊ ፋይዳ ቢኖረውም
ለአማኝ ግን የላቀ ብዙ ትርጉም ያለው ክርስቲያናዊ እሴት ነው።

የይቅርታ ባለሃብቶች ያድርገን🙏

18/06/2024

የሕይወት መንፈስ

ከአሮጌው ሰው ፍሬ፣ ከአሮጌው ኪዳን መፍትሄ መጠበቅ ዓሣን እንደ ንስር እንዲበር ወይም ንስር እንደ ዓሣ እንዲዋኝ መጠበቅ አይመስላችሁም? አንድን ነገር ከተፈጥሮው ውጪ ውለድ ዓይነት ሙግት ተስፋ መቁረጥን ከማስከተል ውጪ ይሄ ነው የሚባል ውጤት አይኖረውም።

ለበርካታ ክፋት የመፈልፈያ ምክንያት የሆነውን በጉያችን ይዘን የምንዞረውን ባላንጣ አዳማዊ ባህርይ (አሮጌው ሰው) አስተምረንና አሰልጥነን ጥሩ ሰው ወይም ቅዱስ ለማድረግ ማሰብ "ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ" እንደማለት ነው።

እንዲሁም በአሮጌው ኪዳን መንፈሳዊ ሆኖ ለመኖር ያለ ትግል የተፈለገውን ያህል ውጤት አያስገኝም። ሕጉንም ከተሰጠበት ዓላማ ውጪ በመጠምዘዝ ውለድ የማለት ግብግብ ነው።
ለሥጋ ሥራ መፍትሔው፣ ለመንፈስ ፍሬ ምንጩ በመንፈስ መሞላትና በመንፈስ መኖር ነው። ቀላል የሚመስል ግን ዘላቂ መፍትሔ። ከሥጋ (ከአሮጌው ሰው) ጋር ትንቅንቅ ላይ ላሉ ለገላቲያ አማኞች ጳውሎስ መፍትሔ አድርጎ የሰጣቸው ለእርሱ የደረሰለትንና ነጻ ያወጣውን የሕይወት መንፈስ ነው (ሮሜ8:2 ገላ 5:16-26)።

አማኝም በዚህ የሕይወት መንፈስ ካልተመላለሰ አሮጌው ሰው የኃጢአት ተገዢ ያደርገዋል። ከፍ ብሎ ለመብረር በመንፈስ መመላለስ አማራጭ ሳይሆን የግድ ነው።

እስቲ አስቡት መስመሩ የተቋረጠ የውሃ ቧንቧ ወይም ኃይል የማያስተላልፍ የኤሌክትሪክ ሽቦ ምን ፋይዳ አለው?
ውሃ የሌለው ቧንቧ በቤታችን ሁለት ሶስት አለን ብለን ብንፎክር፣ ኃይል የማያስተላልፍ የኤሌክትሪክ ገመድ ዙሪያችንና ሰፈራችንን ቢሞላው ምን ትርጉም ይኖረዋል?

ደግሜ እላለሁ ያለ መንፈስ ቅዱስ የሆነ ሕይወትም እንዲሁ ነው። ማለት ማሳ ያላገኘ ዘር፣ ከውሃ የወጣ አሳ፣ ከግንዱ የተለየ ቅርንጫፍ፣ ከአፈሩ የተለየ አበባ እጣቸው ምን ሊሆን እንደሚችል ለማወቅ ሊቅ መሆን አይጠይቅም።

Photos from Elias Girma Pastor's post 16/06/2024

በቶያንዶ ኬብሮን ቤተ ክርስቲያን ሦስት አስደናቂ ቀናትን እግዚአብሔር ሰጠን። ስሙ የተባረከ ይሁን።

07/06/2024

እህቴ አሁንም እግዚአብሔር ያጽናናሽ

30/05/2024

ይገርማል🤭
ቃየል ወደ መስክ እንውጣ ሲለው በልቡ ሸምቋል ብሎ አቤል እንዴት ሊያስብ ይችላል? ድንጋይ ሲያነሳ እንኳን ቢያየው ሊገድልልኝ እንጂ ሊገድለኝ ነው ብሎ በምን አግባብ ይገምታል? የእናት የአባቱ ልጅ ታላቅ ወንድሙ🤦‍♂️ (በድንጋይ ስለመገደሉ እርግጠኛ ባንሆንም)

#ተሳስቼ_ነበር ‼️...በአፍንጫዬ ይውጣ ‼️#Pastor_Dan_Sileshi "የ 48 አመት ክርስትና እና አገልግሎት ምስክርነት"NShow -Tigist Ejigu 26/05/2024

#ተሳስቼ_ነበር ‼️...በአፍንጫዬ ይውጣ ‼️#Pastor_Dan_Sileshi "የ 48 አመት ክርስትና እና አገልግሎት ምስክርነት"NShow -Tigist Ejigu የተወደዳችሁ የኒቆዲሞስ ሾው ቤተሰቦች፡ ከታች ያለውን link ላይክ በማድረግ facebook ገፃችንን እንድትቀላቀሉ በታላቅ አክብሮት እጋብዛለሁ፡፡ 👇👇https://www.facebook.com/nikodimosshow/ፕሮግራማችንን እ...

Photos from New Life Church አዲስ ሕይወት  ቤተክርስቲያን  ጆሃንስበርግ's post 05/05/2024
05/05/2024

ኢየሱስ ተነሥቶአል!!

02/05/2024

አንተ የሕማም ሰው ፦ ጀርባህን ለገራፊዎች ጉንጭህንም ለጠጉር ነጪዎች ሰጠህ፤

የክብር ዘውድ የሚገባውን ራስህን የእሾህ አክሊል ደፉበት፣ ሊሹት የሚገባውን ፊትህን ተፉበት፣ ተለተሉህ፣ በደም ተጠመቅህ፣ ተጠማህ፣ የቁስልህን ጥዝጣዜ የነፍስህን ስቃይ ችለህ የገላህ ሰንበር ሳይደርቅ ለገዳዮችህ ምህረትን ለመንህ…ራስህን አዘንብለህ ነፍስህን ሰጠህ…
ኧረ ምን አይነት ፍቅር ነው!

ከዓለት በተፈለፈለ መቃብር ውስጥ ቀበሩህ፣ በድንጋይም ዘጉት፣ በማህተብ አሸጉት። ጠባቂ አኖሩበት።
አስወገድነው የሚለው የቤተ መቅደስ እና የቤተ መንግሥት ድለቃም ቀላል አልነበረም።
ይሁን እንጂ መግነዝ ፍቱልኝ፣ መቃብር ክፈቱልኝ፣ ድንጋይ አንሱልኝ ሳትል እንደ ተናገርከው ሞትን አሸንፈህ ተነሥተሃል።

ይህ ሥርና መሠረት ያለው ታሪካዊ ክስተት ከመሆን ባሻገር በሕይወታችን ያጣጣምነው ሕያው ሁነት። ኢየሱስ ተነሥቶአል!!! (ኤልያስ ግርማ)

26/04/2024

ፋሲካችን…

ወቅቱ ከአባቶቻቸው በትውፊት የወረሱትን የፋሲካን በዓል ለማክበር ሽር ጉድ የሚሉበት ነው።
እንደ ልማዳቸው የሕጉን ትእዛዝ ለመፈጸም አይሁዳውያን ከየአቅጣጫው ወደ ኢየሩሳሌም ለክብረ በዓሉ በጥድፊያ ላይ ናቸው።
የዛሬውን በዓል ግን ለየት የሚያደርገው እውነተኛው ፋሲካ ክርስቶስ ታዳሚ መሆኑ ነው። የሚገርመው ግን ለበዓሉ ከመጡት ግምት የሰጠው ሰው ያለ አይመስልም፤ ከተወሰኑት ቀናት በኋላ በማስተዋሉና በመልሱ ከመገረም ውጪ (ሉቃ2፡41-47)።
በዓል በራሱ ክፉ አይደለም። ነገር ግን ለበዓሉ ጌታ ጀርባን ሰጥቶ የበዓል አፍቃሪ መሆን ዘላለማዊ ፋይዳው አይታየኝም። ፋሲካን ስናከብር ከመብላትና ከመጠጣት ባሻገር ቆም ብለን ልናነሳው የሚገባ ጥያቄ አለ፡፡

ለምን ተጨነቀ? በአፉ ተንኮል ሳይገኝ፣ ምንም ወንጀል ሳይሠራ፣ ከአመጸኞች ጋር ለምን ተቆጠረ? የፖለቲካ፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ ከሕዝቡም አብላጫው በግድያው ለምን ተስማሙ? የታመሙትን በፈወሰ? በአጋንንት የተያዙትን ነጻ ባወጣ? በሺህ የሚቆጠሩትን በመገበ? ይህ ያሸልመው እንደሆነ እንጂ እንደ ወንጀለኛ የሚያስቆጥረው አይደለም ።
ይባስ ብለው ኪስ አውላቂውን፣ ቤት ሰርሳሪውን፣ የማሕበረሰቡ ጠንቅ የሆነውን በርባንን ፍታልን፣ ኢየሱስ የተባለውን ንጹህ የእግዚአብሔር ልጅ ስቀለው፣ ስቀለው፣ ብለው በአንድ ድምጽ አስተጋቡ መልካም ካደረገላቸው ከኢየሱስ ይልቅ ዘራፊው በርባን ተሻላቸው።
የሚገርመው ግን ዛሬም ከታሪክ አለመማራችን ነው። ስንቱ ይሆን ከሞተለት ይልቅ የገዳዩ አቀንቃኝ? ኧረ ለመሆኑ ፋሲካችን ክርስቶስ ለምን ታረደ?

👉… ከእግዚአብሔርን ቁጣ ሊያድነን

"አጥፊው የበኩሮችን ልጆች እንዳይነካ ፋሲካንና ደምን መርጨትን በእምነት አደረገ" (ዕብ 11፡28)

ለእስራኤል ልጆች ፋሲካ የያህዌን ማዳን የሚያስታውበት ነጻ የመውጣትና የማለፍ በዓል ነው። በግብጻውያን እየወረደ የነበረው መቅሰፍት የእነርሱን ቤት እንዳይነካ የተገደደው በጉበኑ ላይ ከተረጨው ከበጉ ደም እንደሆነ ሁሉ

ሰውም በኃጢያቱ ምክንያት ከእግዚአብሔር ቁጣ በታች ሳለ በፋንታው ሊሞትለት ምትክ ያስፈልገው ነበርና ክርስቶስ በደላችንን ተሸክሞ ስለ እኛ ኃጢያታችን የተግሳጹ በትር ወረደበት ስለዚህ ስርየት አገኘን። የእግዚአብሔር ቁጣ ለዘላለም አልፎን ሄደ።

👉…በአዲስ ሕይወት እንድንኖር

"ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዷልና ስለዚህ በቅንነትና በእውነት . . . በዓልን እናድርግ" (1ቆሮ 5፡7)

ፋሲካ፦ የአሮጌው ሕይወት ግባተ-መሬት፣ የአዲሱ ሕይወት ብስራት፣ እግዚአብሔር ለኃጢአት ያለውን ጥላቻ፣ ለሰው ያለውን ፍቅር ያሳየበት ነው።

የክርስቶስ ሞት ከኃጢአት ፍርድ ማዳን ብቻ ሳይሆን ከኃጢአትም ድነን በአዲሱ ሕይወት እንድንኖር ነው።
ፋሲካ በጩኸት እንዲህ ይላል፦ የግፍ፣ የክፋት፣ የትምክህት እርሾ በቃ ይልቁንም በእውነትና በቅንነት በዓልን እናድርግ።

መንፈሳዊውን ዓለም በአምልኮ ቅኔ የሞላ፣ አለቆችንና ሥልጣናትን ማዕረጋቸውን ገፎ ትጥቃቸውን ያስፈታ፣ የትውልድን ዕዳ የከፈለ እንቢልታ ሊነፋለት፣ ነጋሪት ሊጎሰምለት፣ በገና ሊደረደርለት የሚገባው "የታረደው በግ ኃይልና ባለጠግነት ጥበብም ብርታትም ክብርም ምስጋናም በረከትም ሊቀበል ይገባዋል" ራዕይ 5፡12🙏🙏👑👑👑

“ይሔ በወንጌል ላይ መሳለቅ ነው!” ዘንዶዎቹ እየወጡ ነው! የወንድም ንጉሴ ቡልቻ አስደናቂ ምስክርነትና ወቅታዊ መልዕክት Nikodimos Show 21/04/2024

ጋሽ ንጉሤ ረጅም እድሜ ከጤና ጋር ይስጥልን። አድምጡት ትጠቀማላችሁ።

“ይሔ በወንጌል ላይ መሳለቅ ነው!” ዘንዶዎቹ እየወጡ ነው! የወንድም ንጉሴ ቡልቻ አስደናቂ ምስክርነትና ወቅታዊ መልዕክት Nikodimos Show የተወደዳችሁ የኒቆዲሞስ ሾው ቤተሰቦች፡ ከታች ያለውን link ላይክ በማድረግ facebook ገፃችንን እንድትቀላቀሉ በታላቅ አክብሮት እጋብዛለሁ፡፡ 👇👇https://www.facebook.com/nikodimosshow/ፕሮግራማችንን እ...

18/04/2024

ዘወትር እሁድ ማለዳ ከ4:30
ዕሮብ ከምሽቱ 1:00 ጀምሮ
አድራሻ፡173 Queen.St
Kensington Johannesburg 2094

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Johannesburg?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Videos (show all)

እንኳን ለ2017 ዓ.ም. በሰላም አደረሰን 🌼🌼🌼መልካም አዲስ ዓመት 🌻
"በፖለቲካ አቋም፤ በኢኮኖሚ ቁመና እና ዘር ላይ የተመሰረተ ክርስትና ክርስትና አይደለም።"
እህቴ አሁንም እግዚአብሔር ያጽናናሽ
ኢየሱስ ተነሥቶአል!!
ፋሲካችን…ወቅቱ ከአባቶቻቸው በትውፊት የወረሱትን የፋሲካን በዓል ለማክበር ሽር ጉድ የሚሉበት ነው።እንደ ልማዳቸው የሕጉን ትእዛዝ ለመፈጸም አይሁዳውያን ከየአቅጣጫው ወደ ኢየሩሳሌም ለክብረ በ...
ዘወትር  እሁድ ማለዳ ከ4:30          ዕሮብ ከምሽቱ 1:00 ጀምሮ አድራሻ፡173 Queen.StKensington Johannesburg 2094

Category

Telephone

Website

Address


Webber Road
Johannesburg
Other Public Figures in Johannesburg (show all)
Leigh-Ann Mol Leigh-Ann Mol
Johannesburg

Social Media Manager & Content Specialist at Prime Pixels UK | CliffCentral Podcast Creator

The Klassikist The Klassikist
Johannesburg

Retro and rock'n'roll DJ

SPHEctacula & DJ Naves SPHEctacula & DJ Naves
Suite 106, 108 Elizabeth Avenue, Parkmore
Johannesburg, 2091

This is the official page for the South African DJ SuperDuo, MetroFM Radio Hosts, and Eventing Gurus

The Jumper The Jumper
Johannesburg

URBAN REIGN URBAN REIGN
107 Lesley Drive, Douglasdale Fourways
Johannesburg, 2021

DJ disco DJ disco
45 Van Lill Str
Johannesburg, 1724

Mfundo Shabangu Mfundo Shabangu
Goldreefsands 92 Data Crescent Ormonde
Johannesburg

Marketing Agent and Talent Manager at @Brand-I and @Shoutout4PR @Vitazone_SA

CODE RED - Youth & Children's Ministry Department Southern Africa CODE RED - Youth & Children's Ministry Department Southern Africa
121 Rissik Street
Johannesburg, 2001

The Salvation Army Southern Africa Youth Department Page

SHOWLOVE SHOWLOVE
Johannesburg

The Creators of Cool

Verna van Schaik - Lessons from a World Record Verna van Schaik - Lessons from a World Record
Johannesburg, 2000

Being the Deepest Woman taught Verna about fear, dreams, choices and creating - anything! What would

Norman Callan Norman Callan
117A Algernon Road, Norwood
Johannesburg, 2192

Ladies Couture and Bespoke Fashion

Nonhle Thema Nonhle Thema
Johannesburg

Founder @talent coaching academy👩🏽‍🎓 TV Host,Actress🎬Speaker [email protected]💜