Health info and vaccancy news

HIVN media adresses health related news, vacancies and health educational topics

17/06/2024

አሰደሳች ዜና

የዓይን ሞራ ግርዶሽ ላለባቸው ወገኖቻችን በሙሉ❗
የደብረ ብርሃን አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከሲስተር ሀቱና ፋዉንዴሽን ጋር በመተባበር ከሰኔ 17-20/2016 ዓ.ም የዓይን ሞራ ግረዶሽ የመግፈፍ ህክምና በነፃ ስለሚሰጥ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

አይነ-ስዉራንን መቀነስ ድህነትን መቀነስ ነው
ሲ/ር ሀቱና ፋውንዴሽን
ለበለጠ መረጃ:-0911948265 ይደውሉ
ምንጭ:ከሆስፒታሉ

16/06/2024

የስራ ቅጥር | አደራ የህክምና ማዕከል ያወጣው የስራ ቅጥር
ተፈላጊ መደቦች: 97 ጤና ባለሙያዎች

Photos from Health info and vaccancy news's post 16/06/2024

?
Source: via Ethiopian Reporter

16/06/2024

ኑሮ የከበዳቸው የመንግሥት ሠራተኞች የምሳ ሰዓትን በቤተ እምነቶች እያሳለፉ መሆኑ ተነገረ‼️
👉የቤት ኪራይ መክፈል ያልቻሉ ተደብቀው ቢሮ ውስጥ ያድራሉ ተብሏል።

መንግሥት የሚከፍላቸው ወርኃዊ ደመወዝ አልበቃ ያላቸው የመንግሥት ሠራተኞች የምሳ ሰዓታቸውን ወደ ቤት እምነቶች በመሄድ፣ እንዲሁም ቤት ተከራይተው መኖር የማይችሉት ደግሞ ቢሮ ውስጥ ተደብቀው እንደሚያድሩ ተገለጸ፡፡

በ2010 ዓም ተሻሽሎ ወደ ሥራ ገበቶ የነበረው ባለ 106 አንቀጽ የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ፣ ከስድስት ዓመታት አገልግሎት በኋላ፣ በ160 አንቀጾች ተዋቅሮ በረቂቅ አዋጁ ላይ ውይይት እየተደረገበት ነው፡፡

ለመንግሥት መሥሪያ ቤት ኃላፊዎች የበዛ ሥልጣን የሚሰጥ፣ ለሠራተኞች ችግር ደግሞ መፍትሔ የማያመጣና ተቋማዊ አሠራርና አደረጃጀት ላይ ብቻ ያተኮረ ነው የሚል ትችት በረቂቅ አዋጁ ላይ ቀርቧል፡፡ የመንግሥት ሠራተኛውን ሕይወት የሚቀይር ሥራ እንጂ አዋጅ ማውጣት ብቻ አገርን አይቀይርም የሚሉ ድምፆችም ተሰምተዋል፡፡

ለመንግሥት ሠራተኞች የሚከፈለው ደመወዝ አነስተኛና ሊያኖር የማይችል ከመሆኑም በላይ፣ በበርካታ የኢትዮጵያ ክልሎች የሚገኙ የመንግሥት ተቋማት ደመወዝ መክፈል ተስኗቸው ሠራተኞች ለወራት ደመወዝ ሳይከፈላቸው መቆየታቸውን፣ እንዲሁም በአንዳንድ ክልሎች ደግሞ ከሚቀጥሉት ዓመታት በጀት ተበድረው ደመወዝ እየከፈሉ መሆናቸው በተደጋጋሚ ሲነገር ይደመጣል፡፡

በረቂቅ አዋጁ ላይ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪና ሰው ሀብት ልማት ቢሮ የሰው ሀብት ሥራ አመራር ድጋፍና ክትትል ቡድን መሪ አቶ አብርሃም ደግፌ በሰጡት አስተያየት፣ በከተማ አስተዳደሩ 70 ያህል የመንግሥት ተቋማት ላይ ክትትል እንደሚያደርጉና ሥልጠና እንደሚሰጡ ጠቅሰው የሠራተኛው ሕይወት እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡

በከተማ አስተዳድሩ አንድ ከፍተኛ የሚባል ባለሙያ ያልተጣራ ደመወዙ 9,056 ብር መሆኑን ጠቅሰው፣ ‹‹ከዚህ ግብር ተከፍሎበት በእጁ የሚደርሰውን ገንዘብ አስልታችሁ ድረሱበት፤›› ሲሉ ተሳታፊዎችን ጠይቀዋል፡፡ በዚህ ደመወዝ የቤት ኪራይ የከተማዋ ጫፍ እንኳ ቢኬድ 10,000 ብር መድረሱን፣ ነገር ግን ይህ ከፍተኛ ባለሙያ ሙሉ ደመወዙን ለቤት ኪራይ ላድርግ ቢል ገንዘቡ እንደማይበቃው አስረድተዋል፡፡

በዚህ ሁኔታ ላይ ያለ አንድ ሠራተኛ የተሻለ አገልግሎት መስጠት ይቻላል ወይ? ተፈጥሯዊ ሁኔታውስ በራሱ ይፈቅድለታል ወይ? ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ ይህ ችግር ደመወዝ በመጨመርም ይፈታል ብለው እንደማያስቡ ገልጸው፣ በሌሎች አማራጮች እንዲጠቀም ቢደረግ ችግሩ ሊቀል ይችላል እንጂ 2,000 ብር ቢጨመር እንኳን ሕይወቱ ላይ ለውጥ እንደማያመጣ ተናግረዋል፡፡ ‹‹በዚህም የተነሳ ሠራተኞች አንዳንዴ ቢሮ መጥተው ያለቅሱብናል፣ ምሳ የምንበላበት የለም በማለት በግልጽ ይናገራሉ፤›› ብለዋል፡፡

ገንዘብ አልበቃቸው ያሉ የመንግሥት ሠራተኞች በምሳ ሰዓት ወደ ቤተ እምነቶች ሄደው እንደሚያሳልፉ አስረድተዋል፡፡ የመንግሥት ሠራተኛው ታማኝ ግብር ከፋይ ቢሆንም፣ ነገር ግን የሠራተኛውን ሕይወት የሚቀይር ነገር እስካልመጣ ድረስ በሚፈለገው ደረጃ አገልግሎት ሊሰጥ እንደማይችል ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

በተመሳሳይ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የሰው ሀብት አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ሰሎሞን ይልማ፣ ‹‹የረቂቅ አዋጁን መዘጋጀት የሰማ የመንግሥት ሠራተኛ የደመወዝ ጭማሪ አለ የሚል አዝማሚያ እየሰማን ነው፤›› ብለዋል፡፡ የመንግሥት ሠራተኛው የረቂቅ አዋጁን ዝርዝር የማየትና የመስማት ፍላጎት እንደሌለው ጠቅሰው፣ ‹‹አዋጁ ቶሎ ተዘጋጅቶ ሠራተኛው የሚጠቀምበት አሠራር ካልተዘረጋ በቀጣይ ከሠራተኛው ጋር የምንጋፈጠው እኛው ነን፤›› ብለዋል፡፡ የመንግሥት ሠራተኛው ተስፋ መቁረጡንና ችግር ውስጥ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ሰሎሞን፣ ‹‹አሁን ስለአዋጁ ወይም ዝርዝር እንድናወራለት ፍላጎት የለውም?›› ሲሉ አስረድተዋል፡፡

በአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ውስጥ የሚሠሩና ደንብ የሚቆጣጠሩ ከ6,500 በላይ ኦፊሰሮች በወር 3,934 ብር እየተከፈላቸው ለአሥር ዓመታት በተመሳሳይ ደመወዝ እያገለገሉ መሆኑን ኃላፊው ተናግረዋል፡፡ በዚህ የተነሳ መሄጃ እያጡ ቢሮ ምቹ ሁኔታ አለ በሚል እየተደበቁ የሚያድሩ አሉ ብለዋል፡፡ በመሆኑም የመንግሥት ሠራተኞች መነሻና መድረሻ ደመወዝ ሊስተካከል ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ዳይሬክተር አቶ ካሳየ አረጋ፣ ሠራተኞች በተደጋጋሚ እየለቀቁ ዓመቱን በሙሉ ቅጥር ሲፈጸሙ እንደሚውሉ ገልጸዋል፡፡ ‹‹ነገር ግን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አገልግሎት ለመስጠት የተሻለ አደረጃጀትና ባለሙያ፣ ቢቻልም የሥራ አስፈጻሚው የመንግሥት አካል ውስጥ ያለውን ባለሙያ ሊገዳደሩና ሊጠይቁ የሚችሉ፣ ለቋሚ ኮሚቴዎች የተሻለ ድጋፍና ሙያ ያላቸው ሠራተኞች ቀጥረን ልንሠራ ይገባል፤›› ብለዋል፡፡

‹‹አልቻልንም ባለሙያም የለም፣ ጉዳዩ በደንብ መታየት አለበት፤›› ያሉት ዳይሬክተሩ፣ አዋጅ በወጣ ቁጥር ሠራተኛው ተስፋ የሚያደርግበት ድንጋጌ እየገባ ነገር ግን ለዓመታት ሳይተገበር ቆይቶ እንደገና እንዲሻሻል መምጣቱ በቅጡ ሊጤን ይገባል ብለዋል፡፡

የቤት ሠራተኛ ወርኃዊ ደመወዝ ከ2,500 ብር ላይ ባለፈበት በዚህ ጊዜ አንድ መንግሥት የፅዳት ሠራተኛ በ1,300 ብር መቅጠር የሰብዓዊ መብት ጥሰት አይሆንም ወይ ሲሉ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ በመሆኑም አሁንም ወደፊት ታይቶ የሚባለው ነገር ቀርቶና ያለው ነባራዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ ገብቶ፣ ታች ያለው ሠራተኛ ዜጋ በመሆኑ ችግሩ ሊታይለት ይገባል ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

በፌዴሬሽን ምክር ቤት የሕገ መንግሥት ትርጉምና የሕጎች ሕገ መንግሥታዊነት ዳይሬክተር አቶ ሙለዬ ወለላው፣ የመንግሥት ሠራተኛው ሀቀኛና ታማኝ ግብር ከፋይ ሆኖ እያለ ለተለያዩ ዓይነቶች የታክስ ግዴታዎች ተገዥ መደረጉን፣ ለአብነትም ሠራተኛውን እንዲጠቅም ተብሎ ለትራንስፖርትና ለቤት ኪራይ የሚከፈል ገንዘብ ጭምር ግብር እየተከፈለበት እየተበዘበዘ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ የሰው ሀብት ክትትል ድጋፍና ኦዲት ዳይሬክተር አቶ መላኩ ተመስገን በሰጡት አስተያየት፣ አዋጆች እየወጡ ቁልፍ ጉዳዮች በመመርያ ይታያሉ እየተባሉ ነገር ግን መመርያ ሳይወጣና በውስጡ ያለው ድንጋጌ ሳይፈጸም ጊዜው ደርሶ እንደገና እንደሚሻሻል አስረድተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ተወዳዳሪ ባለመሆኑ ሠራተኞችን መሳብና ማቆየት እንደማይቻልና አንዳንዶችም ‹‹መሄጃ አጣን ብለው የተቀመጡ መሆናቸውን›› የተናገሩት አቶ መላኩ፣ እነዚህ ሠራተኞች እንዴት አገልግሎት ማሻሻል ይችላሉ? ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር) በሰጡት ምላሽ፣ በአዲስ አበባ ያለው ክፍያ የፌዴራል ተቋማት ከሚከፍሉት ይሻላል ብለዋል፡፡ ነገር ግን በሁለቱም የሚከፈለው ግን የኑሮ ሁኔታን ለመቋቋም የሚያስችል አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡

‹‹ብዙውን ጊዜ ትኩረት የሚሰጠው የመጨረሻ ውጤት ላይ እንጂ ደመወዝ እዚህ ደረጃ ድረስ እንዲወርድ ያደረገው ምንድነው የሚለው በሚገባ አይታይም፡፡ አሁን ኃላፊነት ላይ ያለን ሰዎች ነን ወይ በዚህ ጉዳይ ላይ መጠየቅ ያለብን?›› ሲሉ ተሳታፊዎችን ጠይቀዋል፡፡
=========================
ለተጨማሪ የስራ ቅጥር ÷ COC እና ጤና ነክ መረጃዎች ቻናሎችችንን ይቀላቀሉ 👇
https://t.me/addlist/IWOV6uABAi5lYTA0

15/06/2024

✳️የማህፀን ጫፍ ቅድመ ካንሰር ምርመራ ምንድነው ?

✅ቅድመ ምርመራ ማለት አንድ ህመም ምልክት ከማሳየቱ በፊት መመርመር ማለት ሲሆን ፣ የማህጸን ጫፍ ቅድመ ካንሰር ምርመራም ከነዚህ ምርመራዎች መካከል ይገኝበታል።

✳️ለምን ይጠቅማል ?

✅በ ማህፀን ጫፍ ላይ የሚታይ የቅድመ ካንሰር ለውጥ ወደ ካንሰር ለመቀየር ከ ሶስት እስከ ሰባት አመታትን ብቻ የሚፈጅ ስለሆነ በ ቅድመ ካንሰር ምርመራ የ ህመም ምልክት ሳይታይ ይደረስበታል ።

✳️መቼ መደረግ አለበት ?

ከ 21 አመት ጀምሮ በ የ ሶስት አመቱ ይደረጋል። ነገር ግን ከዚህ በታች የተዘረዘሩት አጋላጭ ሁኔታዎች ካሉ ከ ሶስት አመት ባነሰ ጊዜ ውስጥም ምርመራውን ማድረግ ያስፈልጋል፦

1) የ ሰውነት የመከላከል አቅም በተለያዩ ምክንያቶች የተዳከመ ከሆነ ለ ምሳሌ ኤች አይ ቪ ያለባቸው ህሙማን
2) በቅርብ ጊዜ የተሰራ ምርመራ ወይም ናሙና ቅድመ ካንሰር ጠቋሚ ከሆነ ።

✳️ምርመራውን መቼ ማቆም ይቻላል ?

✅ከ 65 አመት በኋላ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መስፈርቶች ከተሟሉ ምርመራውን ማቆም ይቻላል፦
1) ከዚህ በፊት ምንም አይነት የ ማህጸን ጫፍ ቅድመ ካንሰርም ሆነ የ ካንሰር ህመም ታሪክ ከሌለ።
2) ሶከማህጸን ጫፍ ነጻ የሆኑ ተከታታይ የቅድመ ካንሰር ምርመራ ውጤቶች በ አስር አመት ውስጥ የመጨረሻው ውጤት ሶስት አመት ያላለፈው ከሆነ።

✳️በ ሀገራችን ያለበት ሁኔታ ?

✅22 ሚሊዮን የሚገመት ቁጥር ያላቸው እድሜያቸው ከ 15 አስከ 49 የሆነ ሴቶች በየ አመቱ ይያዛሉ፣ ከነዚህ ዉስጥም 7095 ኬዞች 4732 የሚሆኑትን ለሞት ይዳረጋሉ ። በ ሀገሪቱ በ ገዳይነቱ እና ብዙ ህዝብ በማጥቃት ሁለተኛ ደረጃን ይዟል ። የ ማህፀን ጫፍ ቅድመ ካንሰር ምርመራ አንደኛው የ ማህፀን ጫፍ ካንሰርን መከላከያ መንገድ ቢሆንም ፤ ምርመራውን የሚያደርጉ ሴቶች ቁጥር እጅግ አናሳ ነው።

💹
ምርመራው በ ሆስፒታላችን 24 ሰዓት የሚሰራ ሲሆን ውጤቱም ከ ሁለት ቀን ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ይደርሳል። ምርመራው በ ሶስት ደቂቃዎች ውስጥ ይወሰዳል።

✳️ከምርመራ በፊት የሚደረጉ ቅድመ ዝግጅቶች ምንድናቸው ?

1)የ ወር አበባ ላይ ላለች ሴት ምርመራው አይሰራም። 2) ከ ምርመራው 24 ሰዓት አስቀድሞ ከ ግብረ ስጋ ግንኙነት ፣ ብልትን ከመታጠብ እንዲሁም በ ብልት ውስጥ ከሚደረጉ ማናቸውም አይነት መድሐኒቶች ወይም ክሬሞች መቆጠብ ያሻል።

✍️ ዶ/ር ያልፋል አስታጥቄ
የማህፀን እና ፅንስ ስፔሻሊስት ሃኪም

15/06/2024

ለመላው እስልምና እምነት ተከታይ ቤተሰቦች በሙሉ እንኳን ለ1445ኛው ዓመተ ሂጅራ የ ኢድ ዓል-አድሃ (አረፋ ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ::
ኢድ ሙባረክ!

15/06/2024

በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ለመከታተል ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ሐምሌ 22 እና 23/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ሪፖርት ማድረጊያ ቦታዎች፦

➧ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በፖሊ ካምፓስ
➧ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በግሽ ዓባይ ካምፓስ

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➧ የ12ኛ ክፍል ሰርቲፊኬት ዋናውና ኮፒው
➧ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ
➧ አራት ጉርድ ፎቶግራፍ

ባህር ዳር ዩንቨርስቲ Health info and vaccancy news

15/06/2024

EXAM

15/06/2024

ክፍት የስራ ማስታወቂያ | አፍሪኬር የቤት ለቤት ሕክምና አገልግሎት
1. የስራ መደቡ መጠሪያ:- የህክምና ዶክተር
2. ፃታ:- አይለይም
3. ተፈላጊ ቸሎታ:- ጀነራል ሜዲካል ፕራክትሽነር
4. አገልግሎት(ልምድ):- እስከ 2 አመት
5. ብዛት:- 1
6. የስራ ቦታ:- አ.አ እና በ አ.አ ዙሪያ, ቢሮ እና በተመደበበት/ችበት የታካሚ ቤት በመሄድ ለታካሚ ክትትል የማግረግ ስራን ለመስራት ፍቃደኛ የሆነ/ች
7.የቅጥር ሁኔታ:- በቁዋሚነት
8. ደሞዝ:- በስምምነት

ማሳሰቢያ፡- ከላይ ለተጠቀሰው የስራ መደብ የሚያመለክት ማንኛውም አመልካች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት 08/10/2016 ቀን ጀምሮ እስከ 20/10/2016 ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት ከታች የተዘረዘሩትን ህጋዊነታቸው የተረጋገጠ(Authenticated) የሆኑ ኦርጂናል የትምህርት ማስረጃዎች በአካል በማቅረብ እና በማመሳከር መመዝገብ አለበት/ባት፡፡ በ 22/10/2016 የፅሁፍ ፈተና ቀን ይሆናል፡፡

1. የትምህርት ማስረጃ (credentials) ኮፒ
2. ላይሰንስ (License) ኮፒ
3. ከ 2 ገፅ ያልበለጠ CV
4. የስራ ልምድ ማስረጃ

=> በ Telegram እና በ email የተመዘገበ በተቀመጡት ቀናት ውስጥ በአካል ዶክመንት ካላስገባ መፈተን አይችልም፡፡

14/06/2024

ለ ስፔሻሊቲ ትምህርት ፈላጊ ሐኪሞች | በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ሕክምና ትምህርት ቤት የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል

14/06/2024

ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአረጋዊያን መጠለያ እና መጦሪያ ሰንሻይን ፊላንትሮፊ ፋውንዴሽን ማዕከል ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ክፍት የስራ መደቦች ላይ ሰራተኞችን አወዳድሮ በቋሚነት መቅጠር ይፈልጋል

Photos from Health info and vaccancy news's post 14/06/2024

ነፃ ሕክምና

Photos from Health info and vaccancy news's post 14/06/2024

ማሳሰቢያ | ሐሰተኛ ማስታወቂያ ስለሆነ መልክቱ ይድረሳችሁ

14/06/2024

የቅጥር ጥሪ | ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ለተወዳደራችሁ
ጠቅላላ ሀኪም
ሚድዋይፍ
እንቫይሮመንታል ሄልዝ ባለሙያዎች ያለፋችሁ

14/06/2024

ስራ ቅጥር | ወረኢሉ ንግስት ዘውዲቱ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

14/06/2024

𝗩𝗮𝗰𝗮𝗻𝗰𝘆 | Care land General Hospital External Vacancy Announcement

Required positions
Position 1: – Pharmacist

Education: BSc in Pharmacy.

Experience: 2 years

Position 2: Supervisor and Ticket order

Qualification: Diploma in Hotel Management and Above

Requirements: 2 year and above
Person Needed: 1

Position 3: Junior Chef

Qualification: Level II in Hotel Management and above
Experiance : 0 year

Person Needed: 2

Position 4: IT Officer

Education: Bachelor's Degree

Required number: 3

Deadline: June 15, 2024

𝗙𝗼𝗿 𝗮𝗹𝗹 𝗣𝗼𝘀𝗶𝘁𝗶𝗼𝗻𝘀:
Language: Excellent in Afan Oromo, Amharic and English, oral and written.

Job type: Permanent

Salary: as per organization scale

How to Apply:
Interested and qualified applicants can send your CV within 05 consecutive days via this email address: [email protected] or you can submit your application in person. Please mention the position you are applying for at the subject part of your email. For more information please call to 0977868686

Addreess:-Sheger city (Furi Sub-city) Aba Geda Square Adjacent to GM Furniture

Health info and vaccancy news

14/06/2024

List of candidates Accepted to Join the NIEMI schools.

SPHMMC has submitted the final grades to the Ministry of Health. You have to Contact the Human Resources Directorate for further information.

If you have any APPEAL (compliant) on the Final Grades you may come to The HSEDC office and file your complaint after paying 400 birr on the following CBE account. 1000208431068.

The dates of filing complaints will be
Monday Sene 10, and Tuesday Sene 11, 2016 E. C. 9:00 am to 4:00 pm

List👇
https://t.me/healthinovation/37230

14/06/2024

🎉 Just completed level 3 and I'm so excited to continue growing as a creator on Facebook!

14/06/2024

የነፃ አገልግሎት ጥሪ | ለጤና ባለሙያዎች
ሚዛን ቴፒ

14/06/2024

Vacancy Announcement |
Organization: Medicins Sans Frontiers - Holland

Minimum Experience: 2 years

Positions:-

Position 1: Epidemiology Activity Manager

Education: BSc or MSc in Epidemiology or Public Health

Starting gross salary/month: 88,862.00 ETB

– Transportation allowance: 2,200.00 ETB

– Medical Coverage : as per organizational Policy

Deadline: 16th June 2024

Languages Essentiall: Mission language (English )

Desirable: Local language (Amharic ,Somali, Tigrigna, Nuer/ agnuak )

Knowledge Essential: Basic computer skills (e.g. excel, MS word, MS Power Point), R for Epi software,

Work place: Jigjiga

Position 2: NURSE

Education: Diploma/ BSc in Nursing or Midwifery
Required No: 2

Starting gross salary: ETB 28,861

Medical cover: as per the organization's policy

Place of work: Sreru project based in Jigiga

Deadline : 20 June 2024
How to Apply: apply on the link provided bellow for this position only. Link https://t.me/healthinovation/37225

14/06/2024

JOB VACANCY

Organization: J stripes Clinic 2

Position:

2. Diploma or Bsc Nurse with 1 year minimum valid experience from Hospital and Clinic

You are expected to attach your previous works experience .

- Location: Hadero Kenbata Zone

Salary: negotiation

How to apply: Submit your CV and Related Documents

Via Telegram 0939453800

14/06/2024

Urgent vaccancy announcement for medium clinic.

Required Positions
Position 1: Nurse
S*x: male/female
Required Quantity: 5
Salary: negation.
Experiance: 3 year and above phone number 0923130697 or 0977355968
place ; Adiss Abeba (Alemgena )

14/06/2024

𝗩𝗮𝗰𝗮𝗻𝗰𝘆 | KEBI healthcare services PLC

Required qualifications
1. General practitioner - 0 year Experience
2. Health officer - 5 year Experience
3. Nurse - 1 year Experience
4. Midwive - 1 year Experience
5. Lab technician - 1 year Experience
6. Radiology - 0 year Experience

Work place: Addis Ababa, Asco

How to Apply and more detail: atached

13/06/2024

𝗩𝗮𝗰𝗮𝗻𝗰𝘆 | Cadila Pharmaceutical Ethiopia

Position: Junior QA Pharmacist

Work place: Addis Ababa

Qualification: BSc Degree in Pharmacy or in a related field of study

Quanitity Required: 3

Experience: 0 years

Deadline: June 22, 2024

How To Apply: Submit your Cvs via email : [email protected] or via mail: P.O. Box 571 Code 1250, Cadila Pharmaceuticals (Ethiopia) PLC, Addis Ababa, Ethiopia

13/06/2024

ክፍት የስራ ማስታወቂያ

ድርጅት፡ ሪስቶር ሜዲካል

የስራ መደቡ፡ የቆዳ ህክምና ባለሙያ

ቦታ፡ አዲስ አበባ

ሥራ፡ ውል፣ የሙሉ ጊዜ

ማለቂያ ሰአት፡ ክፍት (ተስማሚ እጩ እስኪገኝ ድረስ)

የሥራ መስፈርቶች
ትምህርት፡ የህክምና ዶክተር በልዩ የቆዳ ህክምና ከትክክለኛ ፕሮፌሽናል ፈቃድ ጋር

የስራ ልምድ፡ 2 አመት እና ከዚያ በላይ የስራ ልምድ
የሕክምና ምርመራ ማድረግ ግዴታ ነው
ለ EFDA እውቅና ፈቃድ ለመጠቀም ፈቃደኛ መሆን

ማመልከት
ፍላጎት እና መስፈርት የምታሟሉ አመልካቾች በቴሌግራም አካውንት +251976980006 መመዝገብ ትችላላችሁ።

13/06/2024

የጥሪ ማስታወቂያ #ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ

13/06/2024

Immediate Vacancy-
We are looking to hire a data collector for a short-term period
Required Qualifications:
•At least first degree in health-related field.
•Having practical experiences in electronic data collection including use of mobile/tablet applications
•Experience in anthropometric measurement
•Experience in field blood sample collection
Work place: Addis Ababa
Duration - One month
Payment: as per the organization’s scale
•Interested applicants can send CV by email to: [email protected] or submit in person.
• Deadline for application is 22 June 2024

13/06/2024

ነጻ የአይን ህክምና በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል።

HCP የተሰኘ መንግስታዊ ያልሆነ ግብረሰናይ ድርጅት ከቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የአይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ከሐምሌ 8/2016 ጀምሮ ለተከታታይ 5 ቀናት ይሰጣል።

በመሆኑም የቅድመ ምርመራ (screening) በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ስለተጀመረ ማንኛውም ችግሩ ያለበት ዜጋ የእድሉ ተጠቃሚ እንዲሆን በአክብሮት እናሳውቃለን።

13/06/2024

የስራ ቅጥር | 3ዲ ዲያግኖስቲክ ኢሜጂንግ ማዕከል

ተፈላጊ መደቦች
#2 ነርስ
#2 እንግዳ ተቀባይ
#1 ጉልበት ሰራተኛ

Want your practice to be the top-listed Clinic in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Videos (show all)

መጥፎ የአፍ ጠረን የአለማችንን 25% የሚሆን ማህበረሰብን ያጠቃል። ለችግሩ ብዙ መነሻ ምክንያቶች ቢኖሩም አብዛኛውን ግዜ መነሻው ከአፋችን ነው። ስለ መጥፎ የአፎ ጠረን (ሐሊቶሲስ/ halit...
የደም አይነት እና አመጋገብ #Ethiopia #habeshastyle #oromobeauty #Amhara #ሀበሻ #foryoupageシ #reelsfacebook
የፈተና ጥሪየደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ በተለያዩ የህክምና ሙያ ባለሙያዎች አወዳድሮ ለመቅጠር ላወጣው የቅጥር ማስታወቂያ ለተመዘገባችሁና ለተመረጣችሁ አመልካ...
Eat healthy #health #nutrition #healthydiet
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የተለያዩ አምስት ፕሮጀክቶችን በዛሬዉ እለት በደማቅ ሥነ - ስርዓት እያስመረቀ ይገኛል፡፡
በስራ እጦት ምክንያት ወደ ግብርና ሙያ የተሰማራው ሀኪም #Ethiopia
እስከ መጨረሻ አዳምጡ✋ | By Hussen Zahab Golina
ይህን መልእክት እስከ መጨረሻ አዳምጡ ✋በተለይ ደግሞ ከጤና ሙያ ውጭ ላለው ምህበረሰብ ማጋራት አለብን | By Hussen Zahab Golina
አንዳንድ የግል ክሊኒኮች ያሉበት ወቅታዊ ሁኔታ አንድ ታካሚ ሲመጣ ባላስፈላጊ ምርመራ እና መርፌ በግድ ኪሱን አጥበው የሚልኩበት ሁኔታ ነው ያለው:: #ኢትዮጵያ #ሕክምና
ኑሮ ውድነት በ 1997 ዓ ም
ናቲ በግል ሕክምና
ናቲ በግል ሕክምና ተቋም

Category

Telephone

Website

https://bit.ly/3UUq6al

Address


Addis Ababa
Addis Ababa
0000
Other Medical & Health in Addis Ababa (show all)
Janmeda Health Center Janmeda Health Center
Addis Ababa

Janmeda primary Health Care Unit

DXN_addis Amanuel DXN_addis Amanuel
Addis Ababa

Holistic Medicine and Supplementary Products Selling Platform.....All Herbal&Organic Products

DR Mitiku Medium Clinic DR Mitiku Medium Clinic
Amfo Square
Addis Ababa

our patients are our family

South Sudanese future pharmacists South Sudanese future pharmacists
Addis
Addis Ababa, 2023

Our major aim is to brightening the future of upcoming generations.

Tesfa  home care nursing Tesfa home care nursing
Bole
Addis Ababa, 1000

Our company provides ultimately medical care with mobility and with senior nursing abilities from minor to severe cases with a reasonable price.

Shalom Medical Consultancy Shalom Medical Consultancy
Swazeeland Street
Addis Ababa, 1271

This page is created to promote helath realted issues and provide medical consultation for pateints

Ethiopian anesthetists voice Ethiopian anesthetists voice
Addis Ababa

Here we are for better Health care

Xarunta dhireedka Yemen Xarunta dhireedka Yemen
بولي ميكائيل . فندق ومسجد جعفر
Addis Ababa

Ethio medical Ethio medical
Bole
Addis Ababa, 1056

Duko medicine Duko medicine
Addis Abeba
Addis Ababa

Do right health worker Do right health worker
Shashemene
Addis Ababa