Adona Cosmetics

Adona Cosmetics is a Beauty & Fragrance Store which involved in retailing cosmetics, perfumes, toile

05/06/2024

ከሰሞኑ አዶና ስፓ የነበረ ጨዋታ ነው፡፡

እሱ - ስቲም ሳውና ፈልጌ ነበር። እሁድ ሙሽራ ነኝ
ስፓ ኮኦርድኔተሯ - እንኳን ደስ አለህ። ለስንት ሰው ነው?
እሱ- ከነሚዜዎቼ ሰባት ነን። ሰባት ሰው የሚይዝ ስቲም ሳውና አላችሁ?
ስፓ ኮኦርዲኔተሯ - 10 ሰው ድረስ ትችላላችሁ። 10 ሰው ከመጣ ለሁለቱ የ50% ቅናሽ አገልግሎት እንሰጣችኋለን። ለአንተ ደግሞ ሙሽራ ስለሆንክ በሰርግህ ቀን ደምቀህ እንድትታይ ፌሻል (Facial) በነጻ ።
እሱ (ግራ በመጋባት እየሳቀ) - ኧረ እኔ ፌሻል አልፈልግም። ፌሻል ለወንድ ይሆናል እንዴ? እሱን ለሚስቴ ስጡልኝ።

እውን ፌሻል (Facial) ለሴት ብቻ ነው?
እስቲ በጣም መሠረታዊ ጠቀሜታውን አይተን እንፍረድ

1- በደንብ ማጽዳት (Deep Cleansing) - ፌሻል ሲሠራ ባለሙያው የፊትን ቆዳ በደንብ ያጸዳል። በዚህም በፊት ላይ ያለን ቆሻሻና ዘይት ሙልጭ አድርጎ በማጽዳት በፊት ቆዳ ላይ ያሉትን ቀዳዳዎች በደንብ እንዲከፈቱ ያደርጋል። የነዚህ ቀዳዳዎች መከፈት የፊት ቆዳ በቀላሉ አየር እንዲያገኝ ይረዳዋል።
2- የሞቱ የቆዳ ቅንጣቶችን ማስወገድ (Exfoliation ):- ፌሻል በሚሠራበት ወቅት ባለሙያው ቆዳዉን በጥንቃቄ በማፅዳት በፊት ቆዳ ላይ ያሉ የሞቱ የቆዳ ቅንጣቶችን በማስወገድ ፤ አዳዲስና ጤነኛ የቆዳ ቅንጣቶች እንዲወጡ በማድረግ፣ ውብ፣ ለስላሳና ጤነኛ ቆዳ እንዲኖር ያደርጋል።
3 - ድርቀትን ማስወገድ (Hydration) - ፌሻል የቆዳ ድርቀትን በማስወገድ ቆዳ ሞይስቸራይዝድ እንዲሆን ያደርጋል። ይህም የቆዳን መለጠጥ (elasticity) በመጨመር ሊፈጠር የሚችል የቆዳ መሸብሸብን (wrinkles) ይከላከላል።
4- እርጅናን መከላከል (Anti-Aging) :- ፌሻል የቆዳን ቴክስቸርና እና ቶን በመጨመር እንዲሁም የኮላዥገንን (Collagen) ምርት መጠን በከፍተኛ ሁኔታ እንዲጨምር በማድረግ በቆዳ ላይ የሚፈጠር እርጅናን፣ መሸብሸብን እና በዚያ ምክንያት የሚመጡ ጉዳቶችን ይከላከላል።
5- ጭንቀትን ያስወግዳል :- ፌሻል በሚሠሩበት ወቅት ሰውነት እረፍት ስለሚያደርግ በተለይም የፊት ማስክ ካደረጉ በኋላ ለጥቂት ደቂቃዎች መቆየት ስለሚያስፈልግና በዚያን ወቅት ላይ መተኛት ስለሚቻል (ብዙ ሰው እንቅልፍ ይወስደዋል) በድካም የዛለ ሰዉነት እረፍት እንዲያገኝ ያስችላል።ጥሩ እንቅልፍ እና እረፍት ማድረግ ደግሞ በጭንቀት ምክንያት ከሚመጣ የቆዳ በሽታ ለመከላከል ጠቃሚ ነው። ጭንቀት የቆዳ ችግርን ከሚያባብሱ ነገሮች አንዱ ነው።

ፌሻል እነዚህና የመሳሰሉት ጠቀሜታዎች ሲኖሩት ጠቀሜታውም ጾታን የማይለይ ነው።

ሙሽራውም በስፓ ኮኦርድኔተሯ ይህና የመሳሰሉት ጠቀሜታዎች ሲነገሩት... "እኔ ሞክሬ አላውቅም። ሽልማት ከሆነ ልሞክርበታ" ብሎ ገብቶ ውጤቱን ካየ በኋላ እጅግ በመደሰቱ በሚቀጥለው ወር ድጋሚ ለመምጣት ቀጠሮ ይዞ ሔዷል። .......
እኛም መልካም ጋብቻ ብለን ሸኝተነዋል።

በነገራችን ላይ
ተጠቅሞ ሲወጣ መጀመሪያ "ለሚስቴ ስጡልኝ" ያለውን ረስቶት ነበር።

ወደ ስፓ መሔድ ቅንጦት አይደለም።

01/06/2024

አዶና ስፓ ውስጥ አንድ ደንበኛችን ፔዲኪዩር እየተሠራ የመጣ ጓደኛው ደንገጥ ብሎ
"እንደሴት ....ኧረ በጣም ይደብራል" አለው .....
እውን ፔዲኪዪር መሠራት ለሴት ብቻ ነው?
እስቲ ጠቀሜታውን እንይ።
ከዚያ እንፈርዳለን

1- የጤናና የንጽህና (hygiene) ጠቀሜታ አለው። በየጊዜው እግር መንከባከብ (ፔዲኪዩር) በእግር ጥፍር ላይ ሊከሰት የሚችልን በሽታን እና የጥፍር መበላሸትን ይከላከላል። እግርንም ንጹህና ጤነኛ አድርጎ ለመጠበቅ ይጠቅማል።
2- የደም ዝውውር :- ፔዲኪዩር ውስጥ ያለው ማሳጅ በእግር ላይ ያለን የደም ዝውውር በማቀላጠፍ በእግር በመተጣጠፊያና ጡንቻ በቂ ኦክሲጅንና ምግብ እንዲደርስ በማድረግ የእግርን ጤና ለመጠበቅ ያስችላል።
3- የሞተ ቆዳን ማፅዳት (exfoliation):- ፔዲኪዩር በእግራችን ላይ ያሉትን የሞቱ የቆዳ ቅንጣቶችን ለማጽዳት እና እግራችን ጤነኛ እና ንጹህ ቆዳ እንዲኖረው ያደርጋል።
4- ጭንቀትን ያስወግዳል ፡- ፔዲኪዩር በሚሠራበት ወቅት ያለው መዝናናትና እረፍት ጭንቀትን ውልቅ አድርጎ ለመጣል ያስችላል።
5- ጤነኛና ቆንጆ እግር :- ንጹህና ጤነኛ እግር ሲኖር በራስ መተማመን ይጨምራል። "ጫማ የሚወለቅበት" ስንደርስ ለማውለቅ ማንም አይቀድመን። 😂

እንጠይቃለን........

እና ፔዲኪዩር ለሴቶች ብቻ ነው ያለው ማነው?
ይህ ማለት እኮ ወንዶች እግር የላቸውም ማለት ነው።

#ፔዲኪዩር እግር ላለው ሁሉ ነው።

ወደስፓ መሔድ ቅንጦት አይደለም።

24/05/2024

Ayalew በጠየቀን መሠረት የሳውናን ጥቅም በመጠኑ
ሳውናን መጠቀም በርካታ ትሩፋቶች አሉት።
እስቲ በጥቂቱ እንመልከታቸው
1- የካርዲዮቫስኩላር ጤና :- በየጊዜው ሳውናን መጠቀም የደም ዝውውርን ቀልጣፋ ስለሚያደርገውና የልብ ምትን ስለሚጨምር የካርዲዮቫስኩላር ጤንነትን ለመጠበቅ ይረዳል። ይህም በልብ ላይ ሊከሰት የሚችልን ችግር ይቀንሳል።
2- ዲቶክሲፊኬሽን :- ሳውናን መጠቀም በሰውነት ውስጥ ያሉ መርዛማ ንጥረ ነገሮችን በላብ መልክ እንዲወጡ ይረዳል። ይህም በእንግሊዘኛው ዲቶክስ (detox) ይባላል።
3 - የጡንቻና የመገጣጠሚያ ጤንነት :- ሳውና መጠቀም በመገጣጠሚያ ላይ ያሉትን ፈሳሾች (lymph) በቀላሉ እንዲንቀሳቀሱ በማድረግ ድርቀትን ስለሚያስወግድ በመገጣጠሚያ ላይ የሚከሰት ሕመምን ይቀንሳል።
4- ጭንቀትን ለማስወገድ :- ሳውናን መጠቀም የኢንዶርፊንን መጠን በመጨመር ጭንቀትን ለማስወገድና ጥሩ ሙድን ለመፍጠር ይረዳል።
5- የቆዳ ጤንነት :- ሳውናን መጠቀም የደም ዝውውርን ስለሚጨምር ይህም በቂ የሆነ ኦክሲጂንና ንጥረ ነገሮችን ወደ ቆዳ በፍጥነት ስለሚያደርስ የቆዳ ድርቀትና ቡግርን የመሳሰሉትን በማስወገድ የቆዳ ጤንነትን ለመጠበቅ ይረዳል።
6- የመተንፈሻ አካላት ጤንነት :- ሞቃት አየርን ወደውስጥ መሳብ በመተንፈሻ አካል ውስጥ ያለ መዘጋትን ስለሚከፍት በቀላሉ እንድንተነፍስ ይረዳናል። ይህም የመተንፈሻ አካላትን ጤንነት ለመጠበቅ ፍቱን መፍትሔ ነው።
7- በቂ እንቅልፍ ማግኘት:- ሳውናን መጠቀም ጭንቀትን በመቀነስ ተዝናኖትን ከፍ ስለሚያደርግ ሰውነት በቂ እንቅልፍና እረፍትን እንዲያገኝ ይረዳዋል።
8:- የበሽታ መከላከል አቅም መጨመር :- ሳውናን መጠቀም የነጭ የደም ሴሎችን ቁጥር ስለሚጨምር ሰውነት በሽታን የመከላከል አቅሙ ይጨምራል።
9:- ካሎሪን ለማቃጠል :- በሳውና ውስጥ ያለው ሙቀት የልብ ምትን በመጨመርና በማላብ ሰውነት የተወሰነ ካሎሪ እንዲያቃጥል ይረዳዋል።
10- የአእምሮ ጥራት :- ሳውና መጠቀም የሚፈጥረው ተዝናኖት እረፍት አእምሮ በጥራት እንዲያስብ፣ አትኩሮት እንዲሰጥና በሚገባ እንዲያስብ ስለሚያደርገው የአእምሮ ጤንነት የተጠበቀ ይሆናል።
ሳውናን በአግባቡ ከተጠቀምን እነዚህንና ሌሎች ጠቀሜታዎችን ልናገኝ እንችላለን።
ለዛሬው በዚህ ይብቃን

Pic: Antonio Fiorente
Adona Spa Lodge PLC

23/05/2024

ሳውና እንግባ!
****************
ወቅቱ የሠርግ ነው። ሙሽሮችና ሚዜዎች ሽክ ድምቅ ብለው ለመታየት የሚሞክሩበት ወቅት ነው።
ሽክ ለማለቱ ቆንጆ ቆንጆ ልብሶች ይገዛሉ።
ወይ ይሰፋሉ ካልሆነም ይከራያሉ።
ድምቅ፤ ፍክት ብሎ ለመታየትና ዓይን ውስጥ ለመግባት ደግሞ " ኧረ ሳውና እንግባ እንጂ" ይባላል።
ሠርግ..... የቀጣዩ ሠርግ መሰረት የሚጣልበት ነው ይባል የለ።
************

ለመሆኑ ሳውና ምንድነው?
******************
ሳውና ፊኒሾች (ፊኒላንዳዊያን) ለዓለም ያበረከቱት ምርጥ ስጦታ ነው። Nokia ሞባይልን የተጠቀመ መቼም ፊንላንድን አላውቃትም አይልም።
ፊንላንድ በሰሜን ንፍቀ ክበብ የምትገኝ በክረምቷ የቅዝቃዜ መጠኑ ከ -30 ዲ.ሴ በታች የሚመዘገብባት እጅግ ቀዝቃዛ አገር ናት።
ታዲያ ፊኒሾች ዝም ብለው አልተቀመጡም።
ልቀመጥ ቢሉስ ቅዝቃዜው መች ያስቀምጥና።
መፍትሔ ፈለጉ።
ዘዴ ዘየዱ፡፡
ይህንን ቅዝቃዜ ለመቋቋም በየቤታቸው ከሸክላ ምድጃዎችን እየሠሩ ቤታቸውን ማሞቅ። እነዚህን ምድጃዎች ነው እንግዲህ "ሳውና" የሚሏቸው።
የዛሬ እንዳይመስላችሁ ደግሞ። ከ2ሺ ዓመት በላይ ሆኖታል ታሪኩ።
ታዲያ ሳውና ለፊኒሾች ራሳቸውንና ቤታቸውን ከማሞቅም በላይ ነው። ሰብሰብ ብለው የሆድ የሆዳቸውን የሚጫወቱበት ቦታም ጭምር እንጂ። የምድጃ ዳር ጨዋታ እንበለው ይሆን?
ይኼ ነው እንግዲህ የሳውና መነሻ።
ዘመን ሲሰለጥን፣ ዕውቀት ሲዳብር "ሳውና" ከምድጃ ዳር ወጥቶ ዛሬ የምናያቸውን ዓይነቶችን ሆኖ መጥቷል።
Dry Sauna, Infrared Sauna, Smoke Sauna, Bio Sauna, Portable Sauna ወዘተ እየተባሉ በተለያየ ሁኔታና መልክ እየተገነቡ በዓለም ሁሉ ይሠራጫሉ።
እንደ መውጫ
አንዳንድ ሰዎች ወደ አዶና ስፓ ይመጡና "ሳሙና" አለ? ይላሉ።
አዶና ስፓ ምርጥ "ሳውና" ነው ያለው።

ሙሽራ ነዎት ወይስ ሚዜ?
አጃቢም ከሆኑ በሳውና ድምቅ ይበሉ።

ሳውናን መጠቀም ቅንጦት አይደለም!
ፎቶግራፍ - አዳነ ፍርዴ
ቦታዉ - አዶና ስፓ

20/05/2024

በቅዳሜ ልጥፋችን "ስፓ" ምንድነው? የሚለውን ለማየት ሞክረናል። ከታሪካዊና ቋንቋዊ ዳራው የስፓን ትርጉም ለማብራራት ጥረት አድርገናል።
ዛሬ ደግሞ የተወሰኑ የስፓ ዓይነቶችን ለማየት እንሞክራ።
ተከተሉን...
በነገራችን ላይ :-የአማርኛ ገላጭ ትርጉም እስከምናገኝላቸው ድረስ ስማቸውን በቀጥታ ከእንግሊዘኛው ነው የተዋስነው።
*************************************

**ዴይ ስፓ** ከስሙ እንደምንረዳው ዴይ ስፓ በቀን ብቻ አገልግሎት የሚሰጥ የስፓ ዓይነት ነው። የምሽት የስፓ አገልግሎት የሚፈልግ ሰው ወደዚህ ስፓ እንዲሄድ አይመከርም። በእነዚህ ስፓዎች ውስጥ ማሳጅ፣ ሞሮኪያን ባዝ፣ ፌሻል፣ ፔዲኪዩር፣ ማኒኪዩር ፣ ዋክስ ወዘተ አገልግሎቶችን ማግኘት ይቻላል። በከተማችን ውስጥ ካሉ ዴይ ስፓዎች መካከል አዶና ስፓና ቦስተን ዴይ ስፓ ይጠቀሳሉ።

**ዴስቲኔሽን ስፓ** ይህ የስፓ ዓይነት ለጥቂት ቀናት ከከተማ ወጣ ብለን (ከተማ ውስጥም ሊሆን ይችላል) በስፓ ውስጥ እንድንቆይ የሚያደርግ የስፓ ዓይነት ነው። በዚህ ስፓ ውስጥ አጠቃላይ የዌልነስ አገልግሎት ማለትም የአካል ብቃት (fitness)፣ አመጋገብ (nutrition) የስፓ ትሪትመንቶች እና የኑሮ ዘይቤ (life style) ወርክሾፖች የሚሰጡበት ነው። ዋናው ዓላማው ከተለመደው የሕይወት አዙሪት ወጣ ብሎ ለራስ ጤናና ውበት አትኩሮትን እንዲሰጡ ማስቻል ነው።

**ሪዞርት ስፓ** ይህ የስፓ ዓይነት ከተለመደው የስፓ አገልግሎት በተጨማሪ በሪዞርቶች ውስጥ የምናገኛቸው አገልግሎቶች ማለትም ጎልፍ ፣ ቴኒስ፣ ዋና፣ የእግር ጉዞ ወዘተ አካቶ የያዘ ነው። አብዛኛውን ጊዜ በሆቴሎችና ሪዞርቶች ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ተዝናኖትን (relaxation) ከቅንጦት ጋር አዋህዶ የሚሰጥ ነው።

**ሜዲካል ስፓ** ይህ የስፓ ዓይነት የውበትና የጤናቸውን ሁኔታ ለማሻሻል ለሚፈልጉ ሰዎች የሜዲካል ትሪትመንት የሚሰጥበት ነው። በዚህ ስፓ ውስጥ ቦቶክስ (botox)፣ የሌዘር ትሪትመንት እና የመሳሰሉት የኮስሜትክ ፕሮሲጀሮች የሚሰጡ ሲሆን ዋና ዓላማውም ሰዎች በሐኪም ክትትል በሚያደርጉት የተለያዩ ሕክምናዎች ጤናቸውንና ውበታቸውን እንዲጠብቁ ማድረግ ነው።
አስተውሉ :-ይህን ዓይነት ስፓ ለመጠቀም ከፍተኛ ጥንቃቄና ምርጫ ማድረግ ያስፈልጋል።

**ተርማል** ስፓ ከስሙ እንደምንረዳው ይህ የስፓ ዓይነት በፍልውሃዎች አከባቢ የሚገኝ ነው። በዚህ ሰፓ ከተለመደው የስፓ አገልግሎት በተጨማሪ በማዕድናት በበለጸገ የፍልውሃ መታጠብን ያካትታል። ከውሃው የምናገኘው ንጥረ ነገር ከጤና ጠቀሜታው በተጨማሪ ውበትን ከፍ የሚያደርግ ነው። አገራችን በስምጥ ሸለቆ ውስጥ መገኘቷ እጅግ ብዙ እንደዚህ ዓይነት ፍልውሃዎች እንዲኖሯት ቢያደርግም በተገቢው ሁኔታ ግን እየተጠቀምንባቸው አለመሆኑ የሚያሳዝን ነው። የአዲስ አበባው ፍልውሃ የዚህ ስፓ ዓይነት ማሳያ ነው።

**ክለብ ስፓ** ይህ የስፓ ዓይነት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ (fitness) እና ተለምዷዊው የስፓ አገልግሎት በጥምረት የሚሰጥበት ነው።

**አዩርቬዲክ ስፓ** ይህ የስፓ ዓይነት ባሕላዊው የሕንድ የአዩርቬዳ አገልግሎት የሚሰጥበት ነው። አዩርቬዳ ከ3ሺ ዓመታት በላይ ያስቆጠረ የሕንድ የሕክምና ጥበብ ሲሆን አዪርቬዳ የሚለው የሳንስክሪት ቃል ከሁለት ቃላት የተመሰረተ ሲሆን አዪር (ሕይወት) ማለት ሲሆን ቬዳ (ሳይንስ፤ ዕውቀት) ማለት ነው።ስለዚህ አዩርቬዳ በግርድፉ ስለሕይወት ማወቅ ይሆናል። በዚህ ስፓ ውስጥ ባሕላዊ የዕጽ (herbal) ትሪትመንት፣ ማሳጅና የዮጋ አገልግሎት ይሰጣል። ዓላማውም ባሕላዊውን የሕንድ የሕክምና ጥበብ ተጠቅሞ ጤናንና ውበትን መጠበቅ መቻል ነው።

ከእነዚህ በተጨማሪ "ሚኔራል ስፕሪንግ ስፓ"፣ "ክሩዝ ሺፕ ስፓ"፣ "ኢኮ ስፓ" ወዘተ የሚባሉ እንደሚሰጡት አገልግሎትና እንደሚገኙበት ቦታ የተወሰኑ የስፓ ዓይነቶች አሉ።
በተጨማሪም ኢንደስትሪው በፍጥነት እያደገ ያለ ስለሆነ ወደፊትም የተለያዩ የስፓ ዓይነቶች መፈጠራቸው አሌ የማይባል ነው።
ለዛሬ በዚህ ይብቃን።
መልካም የሥራ ሳምንት

ወደስፓ መሔድ ቅንጦት አይደለም!!

Photo : Adane Firede (https://www.instagram.com/adane.firde)
Adona Spa Lodge PLC

18/05/2024

ዛሬ ቀኑ ቅዳሜም አይደል። እስቲ ስለ "ስፓ" እንጨዋወት።
"ስፓ" ማለት ምን ማለት ነው?
"ስፓ" የሚለው ቃል ታሪካዊም ቋንቋዊም (linguistic) ዳራ ያለው ቃል ነው።

ታሪካዊ ዳራው ፡- በቤልጅየም የምትገኘውና በፍልውሃዎቿ የታወቀችው "ስፓ" የተሰኘችው ከተማ አሁን ላለው ስፓ ለተሰኘው ቃል መነሻ ነች ተብሎ ይታመናል። በጥንት ጊዜ ዓለምን በመዳፋቸው ሥር አድርገው ያስተዳድሩ የነበሩት ሮማዊያን (የቄሳሮች አገር) ከተማዋን ከአውሮጳ አጥንት የሚሰብር ቅዝቃዜ ዞር ለማለትና በፍልውሀዎቿ ለመፈወስ ይጠቀሙባት ነበር። "Aquae Spadanae" ይሏታል ከተማዋን በቋንቋቸው። ባለፍልውሃዋ የስፓ ከተማ እንደማለት ነው በግርድፉ።
በነገራችን ላይ አዲስ አበባስ የተመሰረተችው በፍልውሃ ምክንያት አይደል?

ቋንቋዊ ዳራ :- ስፓ (SPA) የሚለው ቃል ምንጩ ላቲን ሲሆን Sanus Per Aquam የሚለው አጠር ተደርጎ ሲነበብ ነው የሚሉም አሉ።"ጤናን በውሃ ማግኘት" ብለው ይተረጉሙታል። የሐሳቡ ምንጭ ደግሞ በውሃ በሚሰጥ ቴራፒ ጤናን መጠበቅ የሚለው ነው። በውሃ በመታጠብ፣ በመጠመቅ፣ በመታጠን ወዘተ ጤናችንን መጠበቅ እንችላለን ነው። የዘመናዊ ስፓ አገልግሎት ዋና መሠረቱ ይህ ነው እንግዲህ። Sanus Per Aquam.

ዘመነኛ እሳቤው :- በግርድፉ ስፓ የሚባሉት ሰዎች ውሃን ተጠቅመው ጤናቸውን የሚጠብቁባቸው ቦታዎች ማለት ነው። በዘመነኛ እሳቤ ግን ስፓ ማለት ከውሃ በተጨማሪ ሰዎች የተለያዩ ትሪትመንቶች እያገኙ (ለምሳሌ ማሳጅ፣ ሞሮኪያን ባዝ ፣ ፌሻል ፣ማኒኪዩርና ፔዲኪዩር....) ወዘተ እያገኙ ጤናቸውንም ውበታቸውን የሚጠብቁባቸው ማዕከላት ማለት ነው።
ልክ እንደ አዶና ስፓ!
ስፓዎች እንደሚሰጡት አገልግሎት እየታዩ ዴይ ስፓ፣ ዴስቲኔሽን ስፓ፣ ሪዞርት ስፓ፣ ክለብ ስፓ ወዘተ እየተባሉ ይመደባሉ።
ለዛሬ ይብቃን!
መልካም የሳምንት መጨረሻ

ስፓን መጎብኘት ቅንጦት አይደለም!

13/05/2024

ጥያቄ :- ማሳጅ በየስንት ጊዜ ላድርግ?
ማሳጅ የሚያደርጉበትን ጊዜ ለመወሰን የተለያዩ ሁኔታዎችን ግምት ውስጥ ማስገባት ያስፈልጋል።
- የጤንነት ሁኔታ
- የተለየ ፍላጎት ካለ
- ለማሳካት የሚፈልጉት ግብ ካለ ወዘተ
ማሳጅን ለአጠቃላይ ዌልነስና መዝናናት የሚፈልጉ ሰዎች ቢያንስ በወር አንድ ጊዜ ማሳጅ እንዲያደርጉ ይመከራል። ነገር ግን የተለየ ፍላጎት ያላቸው ማለትም የጤና ሁኔታ፣ ውጥረት ያለው ሥራ፣ ወይም ደግሞ በሌላ አስገዳጅ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ሰዎች ግን ከዚያ በፈጠነ ሁኔታ ማሳጅ ቢያደርጉ ይመከራል። ለምሳሌ በሳምንት አንድ ጊዜ ግፋ ካለም በሁለት ሳምንት አንድ ጊዜ ማሳጅ ቢያደርጉ ጠቀሜታው የጎላ ነው። በተጨማሪ ሰውነትን ማዳመጥና የማሳጅ ቴራፒስቶችን ማማከር ትክክለኛው ማሳጅ የማድረጊያ ጊዜን ለመወሰን ይረዳል።
ወደ ስፓ መሔድ ቅንጦት አይደለም !!
መልካም የሥራ ሳምንት

10/05/2024

ማሳጅ ማድረግ የደም ግፊትን ይቀንሳል?
**
ማሳጅ ማድረግ በሰውነታችን ውስጥ ያለውን ወጥረትና ጭንቀት በማስወገድና ሰውነታችን ዘና፤ ፈታ በማድረግ ለጊዜውም ቢሆን የደም ግፊትን ለመቀነስ ይችላል። ነገር ግን የደም ግፊት በሽታን ሊያድን አይችልም።
የደም ግፊትን ለመቆጣጠር የኑሮ ዘይቤን (lifestyle) መቀየር ፤ በሐኪም የታዘዘ መድኃኒትን መውሰድና በትኩረት ራስን መንከባከብ ያስፈልጋል።

ወደ ስፓ መሔድ ቅንጦት አይደለም።

መልካም የሳምንት መጨረሻ!

Photo : Adnae Firde
Adona Spa Lodge PLC

09/05/2024

አጭር መረጃ
*****
ጥያቄ:- ሳውና ባዝ መጠቀም ክብደት ለመቀነስ ይረዳል?
መልስ:- አዎ
ጥያቄ:- እንዴት
መልስ:- ሳውና ባዝ በተዘዋዋሪ መንገድ ለአጭር ጊዜ ክብደትን ለመቀነስ ይረዳል። ወደ ሳውና ባዝ ስንገባ በሳውናው ውስጥ ያለው ሙቀት የልብ ምትንና የደም ዝውውርን በመጨመር በሰውነታችን ውስጥ ያለው ፈሳሽ በላብ መልክ እንዲወጣ ስለሚያደርግ መጠነኛ የክብደት መቀነስ ሊያጋጥመን ይችላል። በዚህም የተወሰነ ካሎሪ እናቃጥላለን። ነገር ግን ሳውና በሰውነት ውስጥ ያለን የስብ መጠን አይቀንስም። የሰውነት ክብደት ለመቀነስ የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ ጤናማ የሆነ አመጋገብን ከአካል እንቅስቃሴና ከሳውና ባዝ ጋር አዋህዶ ቢጠቀም የሚፈለገውን ግብ ሊያገኝ ይችላል።
******
አስተውሉ :-
ክብደት ለመቀነስ ከፈለጉ በቅድሚያ የህክምና ባለሙያዎችን እንዲያማክሩ እጅግ በጣም ይመከራል።
******ወደ ስፓ መሔድ ቅንጦት አይደለም።

Photo : Adane Firde
Adona Spa Lodge PLC

07/05/2024

ወደ ስፓ ስንሔድ ምን እናድርግ?
****************************
በዓለም ላይ ያሉ ስፓዎች የሚጠቀሙበት የታወቀ የስፓ ሥነምግባር (Etiquette ) አላቸው።
እነዚህም
1- የሌሎችን መብት መጠበቅ :- ወደ ስፓ ስንሔድ የሌሎች የስፓ ተጠቃሚዎችን ላለመረበሽና ግለሰባዊ መብታቸውን (Privacy) መጠበቅ ያስፈልጋል።
2- ጸጥታ :- የስፓ ተጠቃሚዎች ወደ ስፓ የሚመጡበት አንዱና ትልቁ ምክንያት እረፍት ለማግኘት ነው። ስለዚህም ወደ ስፓ ስንሔድ የስፓውን ጸጥታ የሚረብሽ ነገር ከማድረግ መቆጠብ ያስፈልጋል
3- የቀጠሮ ሰዓትን ማክበር :- ወደ ስፓ ስንሔድ በቂ ጊዜ ለራሳችን መስጠት ያስፈልገናል። ስለዚህም በተገቢው ሁኔታ አገልግሎቱን ለማግኘት በቀጠሮው ሰዓት በቦታው መገኘት በጣም አስፈላጊ ነው።
4- ስለምንፈልገው አገልግሎት በደንብ ማወቅ :- ወደ ስፓ ስንሔድ ምን ዓይነት አገልግሎት ለመጠቀም እንደምንፈልግ ማወቅ አለብን። ይህንንም ለእንግዳ ተቀባዮቹ እና አገልግሎቱን ለሚሰጡን ቴራፒስቶች በደንብ ማስረዳት ያስፈልጋል። እርዳታ ከፈለግንም ቴራፒስቶቹን ስለአገልግሎቱ ማብራሪያ መጠየቅ ያስፈልጋል።
5- በስፓ ውስጥ ያሉ ደንቦችና ሕጎችን ማክበር :- ስፓዎች የተለያዩ አገልግሎቶችን ስንጠቀም መከተል ስላለብን የሚጠቁም መመሪያና ደንብ በየቦታው ያስቀምጣሉ። ይህንን ደንብና መመሪያ መከተል መልካም የሆነ ግንኙነት ለመፍጠርም ሆነ አገልግሎቱን በደንብ ለማግኘት ስለሚረዳ እነዚህን ደንብና መመሪያዎች መከተል ይገባል።
6- ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ ወደ ማረፊያ ክፍል አለማስገባት :- ስልክና የመሳሰሉትን የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች በልብስ መቀየሪያ ሎከሮች ውስጥ ማስቀመጥተ ወደ አገልግሎት መስጪያ ክፍሎች ይዞ መግባት የሚፈለገውን ውጤት እንዳያገኙ ያደርጋል። ሌሎች ተጠቃሚዎችንም ይረብሻል።
7- መታጠብ :- የትኛውንም የስፓ አገልግሎት ከመጀመር በፊት ሻወር መውሰድ ያስፈልጋል። በተለይም ስቲም፣ ሳውና ወይም ማሳጅ ከመጠቀም በፊት ገላን መታጠብ በጣም ጥሩ ነው።
በአጠቃለይ ወደ ስፓ የምንሔደው ራሳችንን ዘና እና ፈታ ለማድረግ በመሆኑ ይህንን ሁኔታ ሊያበላሽ ከሚችሉ ነገሮች በመራቅ በስፓ ውስጥ እጅግ በጣም ጥሩ ጊዜን ለማሳለፍ መሞከር በጣም ጥሩ ነው።
ወደ ስፓ መሔድ ቅንጦት አይደለም!!

25/04/2024

አንዳንድ ጥያቄዎች ስለ ማሳጅ
********
1- ማሳጅ መች ላድርግ? ጠዋት ወይስ ማታ?
ማሳጅ ለማድረግ አሪፉ ጊዜን የሚወስነው ማሳጅ ለማድረግ ያለን ፍላጎትና ሰዓት ነው። አንዳንድ ሰዎች በጠዋት ማሳጅ ማድረግ ንቁ እና ብሩህ የሆነ ቀን ለማሳለፍ ይጠቅመናል ስለሚሉ በጠዋት ማሰጅ ያደርጋሉ። ሌሎቹ ደግሞ ቀን በሥራ ሲደክም የዋለን ሰውነት ዘና ለማድረግና ጥሩ እንቅልፍ ለማግኘት ይረዳናል ብለው በማታ ማድረግን ይመርጣሉ። የምርጫ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ሁለቱም ትክክል ናቸው።

2- ምግብ ከበላሁ በኋላ ወይስ ከመብላቴ በፊት ማሳጅ ላድርግ?
ማሳጅ ለማድረግ ሲያስቡ ከበድ ያለ ምግብ አለመብላት ይመከራል። ከበሉም ቢያንስ ለአንድ ሰዓት መቆየት አስፈላጊ ነው። ያለበለዚያ እጅግ ቀለል ያሉ ምግቦችን መመገብ (ለምሳሌ የፍራፍሬ ጭማቂ፣ ኩኪስ ወዘተ)

3- ማሳጅ ከማድረጌ በፊት ውሃ ብጠጣስ?
ማሳጅ ከማድረግ በፊትም ሆነ በኋላ በቂ ውሃ መጠጣት ሰውነት በቂ የውሃ መጠን እንዲኖረው (Hydrate) እንዲያደርግ ይረዳል። ይህም ማሳጅ በሚደረጉበት ወቅት ከሰውነት ላይ የሚወጡ መርዛማ ነገሮች (toxins) በቀላሉ እንዲወገዱ ይረዳል። በመሆኑም ውሃ መጠጣት በጣም ይመከራል

4- ከአልኮል መጠጥ በኋላ ማሳጅ ባደርግስ
አልኮል ከጠጡ በኋላ ማሳጅ ማድረግ የሚመከር ነገር አይደለም። አልኮል ሲጠጡ የሚመጣው ስካር አንድም ማሳጁን በደንብ እንዳንዝናናበት ሊያደርገን ይችላል። ሲቀጥልም አልኮል መጠጣት የደምን ዝውውር በመጨመር የልብ ምትን ስለሚያፈጥን ማሳጅ በሚደረግበት ሰዓት አደጋ ሊያመጣ ይችላል። በዚህም ምክንያት ማሳጅ ከማድረግ በፊትም ሆነ ማሳጅ እንዳደረጉ ወዲያውኑ አልኮል መጠጣት አይገባም።

5- ከስቲም ባዝ በኋላ ማሳጅ ባደርግስ?
ከስቲም ባዝ በኋላ ማሳጅ ማድረግ እጅግ ድንቅ ነገር ነው። ስቲሙ የሰውነት ጡንቻ ዘና እንዲል፣ በቆዳ ላይ ያሉት ቀዳዳዎች እንዲከፈቱ ሰውነት ማሳጅ ለመደረግ ዝግጁ እንዲሆን ስለሚያደርግ ከማሳጅ በፊት ስቲም ባዝ መጠቀም በጣም ይመከራል።

መልካም ምሽት!

Photo: Adane Firde
Adona Spa Lodge PLC

23/04/2024

ሞሮኪያን ባዝ
******
ሞሮኪያን ባዝ በአገራችን በተለምዶ "ሞሮኮ" እየተባለ ይጠራል። ሞሮኪያን ባዝ ሌላኛው ስሙ ሐማም ሲባል ምርጩ ሰሜናዊቷ አገር ሞሮኮ ናት ይባላል። አንዳንዶች ግን በዚህ ሳይስማሙ ምንጩ የኦቶማኖችና ወይም የሮማዊያን በገንዳ መታጠብ (Bath) ባሕል ነው። ከዚያ ነው ሞሮኳዊያን ወስደው ለራሳቸው ያደረጉት ይላሉ።
ታሪክ እንደሚነግረን ከሆነ የሞሮኪያን ባዝ በጣም አስፈላጊ የሆነ የማህበረሰብ ባሕል አካል ሲሆን ሰዎች ንጽህናቸውን ከመጠበቅም በላይ ሰብሰብ ብለው እየተዝናኑና እየተጫወቱ እርስ በርስ ሶሻላይዝ የሚያደርጉበት ኹነት ነው። የሞሮኪያን ባዝ ባሕል ከሞሮኮ ወደ ሰሜን አፍሪካና መካከለኛው ምሥራቅ አገራት በመስፋፋትና በየአገሩ ያሉ አንዳንድ ተጨማሪ ባሕሎችን በመቀላቀል ዛሬ የምናየውን መልክ ሊይዝ ችሏል።
ይህ ባሕል ከዓመታት በፊት ድንበር ተሻግሮ አገራችን የገባ ሲሆን አንደ አንድ የስፓ አገልግሎት በየቦታው እየተሰጠ ይገኛል። ስለሙያው የሚያሰለጥኑ ት/ቤቶች ባይኖሩም ድርጅቶች የየራሳቸውን ሠራተኞች እያሠለጠኑና የራሳቸውን ሲግኔቸር ትሪትመንቶች እያዘጋጁ አገልግሎቱን ለመስጠት ሲሞክሩ ይታያል።
******
ሞሮኪያን ባዝ አገልግሎት የተለያዩ ደረጃዎችን ያልፋል
1- ስቲም ማድረግ :- አገልግሎት ተጠቃሚው ስቲም ሲያደርግ በቆዳው ላይ ያሉ ጥቃቅን ቀዳዳዎች እንዲከፈቱ ሲያደርግ ቆዳውም ለሚቀጥለው ደረጃ ዝግጁ ይሆናል።
2- ኤክስፎሌሽን :- እዚህኛው ደረጃ ላይ ተጠቃሚው ከወይራ ዘይት በተሠራ ልዩ ሳሙና መላው አካሉ ይቀባል። በማስከተልም ለዚሁ በተዘጋጀው ጓንት ከሰውነቱ ላይ የሞቱ የቆዳ ቅንጣቶችና ሌሎች አላስፈላጊ ነገሮች (Dead skin & impurities) እንዲወጣ ይታሻል።
3- ማለቅለቅ :- የሞቱ የቆዳ ቅንጣቶችና ቆሻሻው እንዲወጣ ከተደረገ በኋላ በንጹህ ውሃ መላው ሰውነት ይታጠባል። በዚህም በሰውነት ላይ ያለ ሳሙናና ቆሻሻ ይወገዳል።
4- ተጨማሪ ትሪትመንት:- እንደየሞሮኪያን ባዙ የተለያየ ቆዳን የሚያሳምሩና ጤንነቱን የሚጠብቁ ትሪትመንቶች ይቀባል። ለምሳሌ ማስክ፣ ከተለያየ የእህልና ዓይነትና ወተት የተዘጋጀ ትሪትመንት፣ ጥቁር አዝሙድ ወዘተ ሊሆን ይችላል
5- ማጠቃለል:- እንደ ትርትመንቱ ዓይነት ተጠቃሚው የተወሰነ ሰዓት ቆዳው ላይ እንዲቆይ ከተደረገ በኋላ በማጠብ የሞሮኪያን ባዙን አገልግሎት ይጠቃለላል።

*****
ምን ይጠቅማል?
- የቆዳ ጤንነት :- ከተጠቃሚው ቆዳ ላይ የሞቱ የቆዳ ቅንጣቶቹና ሌሎች አላስፈላጊ ነገሮች ሲነሱ ቆዳ ለስላሳ፣ ንፁህና ጤናማ ይሆናል።
- በደንብ መጽዳት - ስቲምና የሞተ የቆዳ ቅንጣት ለማውጣት የሚደረገው ስክራብ ቆዳ ላይ ያለ ቀዳዳዎች እንዲከፈቱና ቆሻሻ ነገሮች እንዲወገዱ በጣም ይረዳል።
- የደም ዝውውርን ማቀላጠፍ ፦ ስቲምና ማሳጅ ማድረጉ የደም ዝውውርን በማቀላጠፍ የቆዳን ጤንነት ይጠብቃል
- ጭንቀትን ማስወገድና ማዝናናት ፦ ሞቃት የሆነው ክፍሉና አጠቃላይ የሞሮኪያን ባዝ ቆይታው በሰውነት ላይ ተዝናኖትን በማምጣት ጭንቀት እና ውጥረት እንዲወገድ ያደርጋል።

በአጠቃላይ ሞሮኪያን ባዝ ለአእምሮና ለአካል የጤና ጠቀሜታን ከመስጠት ባሻገር ተጠቃሚው ታድሶ፣ ተደስቶ፣ ተዝናንቶና እጅግ ጸድቶ እንዲውል ያደርገዋል።
*******
አስተውሉ:- ሞሮኪያን ባዝ ወይም ሐማም እንጂ ሞሮኮ አይባልም። ሞሮኮ የአገር ስም ነው!

Photo : Adane Firde
Adona Spa Lodge PLC

20/04/2024

በአገራችን አሁን አሁን ለማሳጅ ቴራፒ ከሚሰጠው "አላስፈላጊ" ትርጉም በተቃራኒ ማሳጅ ለተለያየ የሕክምና አገልግሎት ይውል ነበር። አሁንም የተሰበረን ማሸት፣ የወለቀን መመለስ፣ የደከመን ማንቃት በተለያዩ ባሕላዊ ሐኪሞች የሚሰጥ መፍትሔ ነው። በአንድ ወቅት በየጥጋጥጉ የተከፈቱ "ማሳጅ ቤቶች" አገልግሎቱ ከሚያበረክተው ትልቅ መፍትሔ በተቃራኒ በማኅበረሰቡ ዘንድ አሉታዊ ምስል እንዲፈጠር ሆነ።
ለመሆኑ ማሳጅ ቴራፒ ምንድነው? ከታሪካዊ ዳራው እንጀምር
*********************
የማሳጅ ቴራፒ መች ተጀመረ?
የማሳጅ ቴራፒ ታሪክ የሚጀምረው ከሺ ዓመታት በፊት ነው። የተለያዪ ባህሎች ማሳጅን ለተለያየ አገልግሎት ይጠቀሙበት ነበር። በጥንታዊቷ ቻይና ማሳጅ ቴራፒን ከአኩፓንቸርና ባህላዊ መድሃኒቶች ጋር አብሮ ለሕክምና ይሰጥ ነበር። በተመሳሳይ በጥንታዊቷ ሕንድ ውስጥ የአዩርቬዲክ (Ayurvedic) ባለሙያዎች ለአንድ በደዌ ለተመታ በሽተኛቸው ከመንፈሳዊው ፕራክቲስ ጋር በማጣመር የማሳጅ ቴራፒን እንደ አንድ የሕክምና መንገድ ይጠቀሙበት ነበር። የግሪክና የሮማዊያን አዋቂዎች ማሳጅን ከተለያዪ የሕክምና መንገዶች ላይ በማጣመር እንደ እጅግ አስፈላጊ የጤና መንከባከቢያ መንገድ ይጠቀሙበት ነበር። በተለይም በስፖርት እንቅስቃሴ ላይ ለሚሳተፉ አትሌቶቻቸው ማሳጅን እንደ ዋና የሕክምና መንገድ የይጠቀሙ ነበር።
ከጊዜያት በኋላ የማሳጅ ቴራፒ በመላው ዓለም ከመሰራጨቱም በላይ ከጊዜ ጊዜ እየተሻሻለ፣ ተጨማሪ ቴክኒኮች እየተጨመሩለት፣ ከዘመናዊው የሕክምና ዕድገት ጋር በተጓዳኝ እንዲያድግ እየተደረገ ዛሬ የደረሰበት ደረጃ ሊደርስ ችሏል።
በአሁኑ ወቅት የማሳጅ ቴራፒ ጥበብ በጣም አድጎ ለተለያዩ ሕመሞች እንደ ፍቱን መፍትሔ እየተሰጠ ከመሆኑም በተጨማሪ ከበሽታ ቀድሞ ለመከላከልም እንደ አንድ አማራጭ እየታየ ያለ ጥበብ ነው።...
በነገራችን ላይ
አዩርቬዳ በሕንድ ከ3ሺ ዓመታት በፊት የተጀመረ የሕክምና ጥበብ ሲሆን በሳንስክሪት "አዩር" ማለት ሕይወት ማለት ሲሆን "ቬዳ" ደግሞ "ሳይንስ ወይም ዕውቀት" ማለት ነው። አዩርቬዳ ማለት "ስለሕይወት ማወቅ" የሚል ትርጉም ይሰጣል። .....

ይቀጥላል........

ማሳጅ ያድርጉ ፤ ጤናዎን ይጠብቁ

19/04/2024

ባለን የረጅም ጊዜ የስራ ልምድ አብዛኛዎቹ ደንበኞቻችን የስቲምና የሳዉና ባዝ አጠቃቀማቸዉ ያልተስተካከለ እንደሆነ እንታዘባለን፡፡ በዚህም ምክንያት ደንበኞቻችን ስቲምና ሳዉናን እንዴት መጠቀም እንዳለባቸዉ ሙያዊ ምክር እንሰጣለን፡፤
እንዴት እንጠቀም
1- **ራስን ማዘጋጀት**፡- ወደ ስፓዉ እንደገቡ ቀጥታ ወደ ስቲምና ሳዉና ባዝ መግባት አይመከርም፡፡ለተወሰኑ ደቂቃዎች አረፍ ብሎ ራስን ማረጋጋት ያስፈልጋል፡፡ ከዚያ ሞቅ ባለ ዉሃ ሻወር መውሰድ፡፡ሻወር ስንወስድ በሰዉነታችን ላይ ያለዉን ቅባትም ሆነ ሎሽን ለማስወገድ ይረዳል፡፡ ሻወር አድርገን ከጨረስን በኋላ ዉሃ መጠጣት ጥሩ ነዉ፡፡
2- **ወደ ስቲም /ሳዉና ክፍል መግባት** ፡- ስቲም / ሳዉና ክፍል ዉስጥ ከገቡ በኋላ በሩን መዝጋት እንዳይረሱ፡፡
3- **የሙቀቱን ሁኔታ ማስተካከል**፡- አብዛኘዉን ጊዜ ስቲም ክፍሎችን ሙቀትና እፍጋት (humidity) ማስተካከል ስለማይቻል በዚህ አይጨነቁ፡፡ ካለም መልካም፡፡ የሳዉና ክፍሎች ግን ማስተካከያ ስላላቸዉ ለሰዉነታችን ተመጣጣኝ ወደ ሆነ ሙቀት ክፍሉን ማስተካከል ያስፈልጋል፡፡
4- **ዘና ማለት** - አንዴ ክፍሉ ወስጥ ከገቡና የክፍሉን ሙቀት በሚመች መንገድ ካስተካከሉ በኋላ ተቀምጠዉ ወይም ጋደም ብለዉ ሰዉነትዎን ዘና ያድርጉ፡፡
5- **ዉሃ መጠጣት**፤- ዉሃ በደንብ ይጠጡ፡፡ በተለይም በጣም የሚያልብዎ ከሆነ በርከት ያለ ዉሃ በመጠጣት ከሰዉነትዎ የሚወጣዉን ፈሳሽ ይተኩ፡፡
6- **የጊዜ ገደብ ይስጡ**፤- በመጀመሪያዉ ክፍለ ጊዜ ከ15-20 ደቂቃ ብቻ ይቆዩ፡፡ ከዚያ በፊት ሰዉነትዎ ምቾት ካልተሰማዉ ግን ቀደም ብለዉ ይዉጡ፡፡
7- **ሰዉነትን ማረጋጋት** ፤- የመጀመሪዉን ክፍለ ጊዜ (ከ15-20 ደቂቃ) ከተጠቀሙ በኋላ ለብ ባለ ዉሃ ሻወር በማድረግ ሰዉነትዎን ያረጋጉ፡፡ በስቲምና ሳዉና ባዝ ዉስጥ እያሉ በከፍተኛ ደረጃ ጨምሮ የነበረዉ የሰዉነትዎ ሙቀት ለብ ባለ ዉሃ ሻወር በሚወስዱበት ጊዜ ቀስ እያለ ወደ ቦታዉ ይመለሳል፡፡
8- **እረፍት ማድረግ** ፤- ሻወር ከወሰዱ በኋላ ወደ ማረፊያ ሔደዉ ጋደም ይበሉና እረፍት ያድርጉ፡፡
9- **መድገም**፡- ጥቂት እረፍት ካደረጉ በኋላ ሁለተኛዉን ክፍለጊዜ መቀጠል ይችላሉ፡፡ በዚህ መንገድ ቢያንስ ሶስት ክፍለ ጊዜዎችን ቢጠቀሙ ጥሩ ነዉ

**አስተዉሉ**፡- ስቲምና ሳዉናን መጠቀም እጅግ ብዙ ጠቀሜታዎች አሉት፡፡ እነዚህን ጠቀሜታዎች ልናገኝ የምንችለዉ ከላይ የተጠቀሱትን መመሪያዎች በመከተል በአግባቡ መጠቀም ስንችል ብቻ ነዉ፡፡ በተጨማሪም ስቲምና ሳዉና መጠቀም በጤና ምክንያት የማይፈቀድላችዉ ሐኪማቸዉን ቀድመዉ ማማከር በጣም አስፈላጊ ነዉ፡፡

መልካም የሳምንት መጨረሻ!!

12/04/2024

ስለ ሳውና እንጨዋወት
የሳውና አጀማመር እስከ ሁለት ሺህ ዓመት ወደ ኋላ ይወስደናል፡፡ ጅማሬውንም ያደረገዉ በፊንላንድ ነዉ ይላሉ ታሪኩን ያጠኑ፡፡ መዛግብት እንደሚያሳዩት ከሆነ ከ1112 ዓመታት በፊት ፊኒላንዳዊን (ፊኒሾች) ሳዉናን የሚሰሩት መሬትን በመቆፈርና እንደምድጃ በማድረግ ነበር፡፡ በኋላ ላይ ግን ከምድር በላይ የሳውና ቤትን በድንጋይ መገንባት ቻሉ፡፡ ለጭስ ማስወጫ የሚሆን እንደመስኮት ያለች ቀዳዳ በመስራት ክፍሉ ሙቀት እንዲኖረው ያደርጉ እንደነበር በነዚሁ መዛግብት ላይ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡
ከፊኒሾቹ በተጨማሪ የቀድሞ ሥልጡን ሕዝቦች የነበሩት ማያዎችም ከሳውና ጋር ተመሳሳይነት የነበረዉ ክፍልን ከዛሬ 3000 (ሦስት ሺ) ዓመት በፊት ይሰሩ እንደነበር ታሪክ ይነግረናል፡ ማያዎች ይህንን ክፍል ለተጠቃሚው በላቦት (ላብ) መልክ ሕክምናን ለመስጠትና ለመንፈሳዊ አገልግሎት ይጠቀሙበት ነበር ይላሉ፡፡ አጃኢብ ነው!
ከዚህ ባሻገር ሳውና በተለያዩ አገሮችና ባህሎች ውስጥ በተለያየ ስምና ሁኔታ ተግልጾ ይገኛል፡፡ታዲያ ስሙ ይለያይ እንጂ ሁሉም የሚጠቀሙበት ለተመሳሳይ ጉዳዮች ማለትም ለተዝናኖት፤ ለቴራፒ ፤ ለጤንነት ጥበቃ፤ እንዲሁም ለተለያዩ መንፈሳዊና ባሕላዊ ክንውኖች ነው፡፡ በአገራችንም እንደ ወይባ ጢስ ያሉ ከሳዉና ጋር ተመሳሳይ ባሕሎች እንዳሉን እናውቃለን፡፡ በአጤ ፋሲል ዘመንም መሳፍንቱና መኳንንቱ ድንጋይ እያጋሉና በላዩ ላይ ውሃ እያፈሰሱ የሳዉና ስሜት ይፈጥሩ እንደነበር ተመዝግቦ ተቀምጧል፡፡
ስለ ታሪኩ ይህቺን ታህል ከተጨዋወትን ስለ ሳውና ዓይነቶች ደግሞ ጠቀስ ጠቀስ እናድርግ
በመሠረታዊነት ሦስት ዓይነት ሳውናዎች አሉ፡፡ ባሕላዊ የፊኒሾች ሳዉና ፤ ደረቅ ሳዉና እና ኢንፍራሬድ ሳውና ይባላሉ፡፡

1. ባሕላዊ የፊኒሾች ሳውና (Traditional Finnish Sauna)
ይህ ዓይነት ሳውና የሚሰራዉ ከሚገጣጠሙ ጣውላዎች ሲሆን በአገራችን በሁሉም የሳውና አግለግሎት በሚሰጡ ድርጅቶች ውስጥ የሚገኝ ነው፡፡ በመሠረታዊነት በውስጡ በኤሌክትሪክ የሚሠራ ምድጃ ፤ ምድጃዉ ላይ እንዲግል የሚደረግ ድንጋይ፤ አነስተኛ ባልዲ እና ጭልፋ፤ እንዲሁም የሙቀትና እፍጋት (humidity) መቆጣጠሪ እንዲሁም በየ 15 ደቀቃዎች የተከፋፈለ የአሸዋ ሰዓት ይገኛል፡፡ ተጠቃሚዉ ወደ ሳዉናዉ ከገባ በኋላ በባልዲዉ ውስጥ ከተቀመጠዉ ውሃ (አብዛኛዉን ጊዜ የባህር ዛፍ ሽታ ያለው) እየጨለፈ በጋለዉ ድንጋይ ላይ በማፍሰስ የክፍሉን ሙቀትና እፍጋት እንደሚፈልገው ይቆጣጠረዋል፡፡ አብዛኛዉን ጊዜ ከ 20% እስከ 40% ባለዉ. ውስጥ ከፍና ዝቅ ይላል፡፡ በሳዉና ውስጥ ያለዉ ሙቀት ሲጨምር እፍጋት (humidity) ይቀንሳል፡፡
2. ደረቅ ሳውና (Dry sauna)
ደረቅ ሳዉና የሚባለው ከባሕላዊ የፊኒሾች ሳውና ጋር አሰራሩ አንድ ዓይነት ሆኖ ልዩነቱ እዚህኛዉ ላይ የሚጨመር ውሃ ስለሌለ ሳዉናው እፍጋት (humidity) አይኖረውም፡፡ በዚህም ምክንያት ሳውናዉ እርጥበት ስለማይኖረው ደረቅ ሳዉና ይባላል፡፡ በነገራችን ላይ ደረቅ ሳዉናን ውሃ ብቻ በመጨመር ወደ ባሕላዊ የፊኒሾች ሳውና በቀላሉ መለወጥ ይቻላል፡፡
3. ኢንፍራሬድ ሳዉና ፡-(Infrared Sauna)
ኢንፍራሬድ ሳዉና ከሌሎቹ የሳዉና ዓይነቶች የተለየ የሚያደርገዉ ምንም ዓይነት እፍጋት (humidity) ስለሌለዉ ነዉ፡፡ ይህ የሳዉና ዓይነት ሙቀትን የሚሰጠዉ ከተገጠሙለት መብራቶች (ኢንፍራሬድ) ላይ ከሚወጣ ሙቀት ነዉ፡፡
በሚቀጥለዉ የሳዉና ባዝን ጠቀሜታና አጠቃቀምን በተመለከተ እንጫወታለን፡፡
ቸር ያሰንብተን፡፡

10/04/2024
27/02/2024

Book Now!
+251-116-180578
+251-912-506480
[email protected]
around 22, Next to Addis Hiwot Hospital

24/02/2024

Book Now
+251-116-180578
+251-912-506480
[email protected]
around 22 next to Addis Hiwot Hospital
Addis Ababa

TikTok · NapiOfficial27 17/02/2024

https://vm.tiktok.com/ZM6EWfAEX/

TikTok · NapiOfficial27 9267 likes, 100 comments. “ pranked in addis ababa ethiopia”

17/02/2024

Our Beauty Salon is ready!
Book Now!

TikTok · adonaspa 12/02/2024

Book Now

TikTok · adonaspa Check out adonaspa's video.

29/12/2023

Around 22, Next to Addis Hiwot Hospital
Addis Ababa

22/12/2023

Book Now
+251-116-180578
+251-912-506480
around 22, next to Addis Hiwot Hospital
[email protected]
adonaspa.com

15/12/2023

Book Now
+251-116-180578
+251-912-506480
Around 22 Next to Addis Hwot Hospial
adonaspa.com

Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Address

Around 22, Next To Addis Hiwot General Hospital
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:00 - 20:00
Tuesday 08:00 - 20:00
Friday 08:00 - 20:00
Saturday 08:00 - 21:00
Sunday 08:00 - 21:00
Other Addis Ababa beauty salons (show all)
Dagi's Day Spa Dagi's Day Spa
1/Atlas Branch, Yoly Hotel 3rd Floor, 2/Imperial Branch , Alfoz Plaza 1st Floor
Addis Ababa

No 1 Day Spa in Addis Ababa. Located @Yoly Hotel 3rd Floor around Bole Atlas and 2nd branch is located at Alfoz Plaza 1st floor. Dagi's is open 24/7

Ethio Nuru Massage Ethio Nuru Massage
ATLAST Int. HOTEL
Addis Ababa

BEST BODY TO BODY MASSAGE CENTER.. IN ADDIS ABABA, ETHIOPIA OUTDOOR SERVICE *HOTEL *ROOM *HOME *OFFICE

QAROO HIREE QAROO HIREE
Finfinnee
Addis Ababa, 147532

Aadaa fi duudhaa hawaasa kiyyaa addunyaatti daran muldhisuuf kutadhee ka'eera. Isinis Gama keessanii

Marti cosmo. Marti cosmo.
Djibouti Street
Addis Ababa

Marta cosmo. we provide original brand products with affordable price from USA and Europe.Contact us: 0911934958/0911409940 telegram:https://t.me/hm_cosmo22

Urjii Kiyya Urjii Kiyya
Addis Ababa

Hailu Barber Hailu Barber
Jamo 1
Addis Ababa

Hailu Barber

Qàpîir źhàækã Qàpîir źhàækã
Itoobiya
Addis Ababa, AFDHEER

XIGMAAWI BOY�

Ayub Mohammed Ayub Mohammed
Addis Ababa

Sebina fashion and gift store Sebina fashion and gift store
Addis Ababa

This page is for selling both Men and women accessories

Bottled Royalty Bottled Royalty
Addis Ababa

If simply wearing a perfume can make you fabulous then why bother with other complications.

Belay Belay
Awassa
Addis Ababa, 12902188

Glamour Glamour
1. Gerji, Alfoz Plaza, 2. Bole, Morningstar Mall , 3. Sumit, Fiyelbet, 4. Bisrate Gebriel, Tsemex Apartment
Addis Ababa

Nail and Eyelash extension