Prosperity party yeka woreda 8 branch-ብልጽግና

Prosperity party yeka woreda 8 branch-ብልጽግና

ይህ ትክክለኛ የካ ክ/ከተማ ወረዳ 08 ብልጽግና ፓርቲ የፌስቡክ ገጽ ነው

10/09/2024

እንኳን ለአዲሱ ዓመት 2017 በሠላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን !!

አሮጌ ዓመት አልፎ፣ በአዲሱ ሲተካ፣ ሁላችንም በህይወታችን ዉስጥ አዲስ ነገር እንጠብቃለን፤ እንመኛለን። ብሩህ ተስፋ ተላብሰን ለአዳዲስ ዉጤቶችም እንነሳሳለን።

ባለፈው አመት በወረዳችን የተመዘገቡ ስኬቶቻቻችንን አቅም አድርገን፤ ጉድለቶቻችንን ደግሞ በጋራ ጥረታችን አርመን በአዲሱ ዓመት ተጨማሪ አዳዲስ ስኬቶችን አንደምናረጋግጥ ሙሉ እምነት አለኝ ፡፡

በአዲሱ አመት አንድነታችንን ወንድማማችነትን/እህትማማችነትን አጠናክረን በመረዳዳት በመደጋገፍ ስኬቶችን እንደምናስመዘግብ ትልቅ ተስፋ አደርጋለሁ ።

በአሉን ስናከብር የተቸገሩትን በመጠየቅ፤ አብሮነትን በመግለፅ አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የፍቅር፣ የጤና፣ የአንድነትና የብልፅግና ዘመን እንዲሆን እመኛለሁ ።

ለመላዉ የወረዳችን ህዝቦች ብሎም መላው ኢትዮጵያዊያን አዲሱ ዓመት የሠላም፣ የስኬትና የደስታ እንዲሆን የመልካም ምኞት ነው።

አቶ መሳይ ተካልኝ
የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ

10/09/2024

እንኳን ለ2017 አዲስ ዓመት የእንቁጣጣሽ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን!!

የተከበራችሁ የሃገራችን ህዝቦች፣ የተወደዳችሁ የወረዳችን ነዋሪዎች ፣ የተከበራችሁ የመንግስት ሰራተኞች እንዲሁም ለመላው ኢትዮጵያውያን በሙሉ ከሁሉ አስቀድሜ እንኳን ለአዲሱ አመት 2017 የዘመን መለወጫ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን ለማለት እወዳለሁ፡፡

ያሳለፍነው 2016 በጀት ዓመት እንደ ሃገር ሰፋፊ ድሎችን ያስመዘገብንበት የገጠሙንን ተግዳሮቶች ወደ ስኬት በመቀየር ዘርፈ ብዙ ውጤቶችን ያስመዘገብነበት እንዲሁም የወረዳችንን የነዋሪዎች ተጠቃሚነት ያረጋገጠው እና የከተማችን ገፅታ የቀየረው የኮሪደር ልማት በስኬት የተሰራበት ዓመት ነበር፡፡

በ2017 እንደ ወረዳችን የተጀመሩ ልማት ስራዎችን በታቀደላቸው ጊዜ ለመጨረስ ርብርብ የምናደረግበት የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች የሚፈቱበት ቀልጣፋና በቴክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎት ለመስጠት ከፍተኛ ስራ የሚሰራበት፣ የሰው ተኮር ተግባራት ተጠናክረው የሚቀጥሉበት እና የከተማ ግብርናና የሌማት ትሩፋትን በማጠናከር የወረዳችንን ነዋሪዎች ተጠቃሚነት የምናረጋግጥበት አመት ይሆናል።

በመጨረሻም ለሁሉም የወረዳችን ሰራተኞች ፣ነዋሪዎች እንኳን አደረሳችሁ እያልኩ በዓሉን ስናሳልፍም በመረዳዳት በመደጋገፍ አብሮነታችንን በማጠናከር እንድናሳልፍ በዚሁ አጋጣሚ መልእክቴን አስተላልፋለዉ፡፡

መልካም አዲስ አመት

አቶ ጥሩአለም ባሳዝነዉ
የየካ ክፍለ ከተማ የወረዳ 08 አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ

10/09/2024

እንኳን ለ2017 አዲስ አመት አደረሳችሁ

የተከበራችሁ የክፍለ ከተማችን የብልፅግና ፓርቲ አባላቶች፣ነዋሪዎች፣ አርሶ አደሮች፣ የመንግስት ሰራተኞች፣ ጤና ባለሙያዎች፣ መምህራን፣ ነጋዴዎች፣ ኮንትራክተሮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ወጣቶች፣ ባለ ሃብቶችና በተለያዩ የሙያ መስክ ተሰማርታችሁ የምትገኙ ግለሰቦች እንኳን ለ 2017 ዓ.ም አዲስ ዓመት የዘመን መለወጫ በዓል በሰላም አደረሳችሁ/አደረሰን

አቶ መገርሳ ገላና
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ጽ/ቤት

መልካም አዲስ ዓመት🌻
https://heylink.me/YEKAPROSPERITYPARTY/

Yekaprosperity.org.et

10/09/2024

እንኳን ለ2017 አዲስ አመት በሰላም አደረስዎ።አዲሱ አመት የሰላም ፣ የፍቅር እና የስኬት እንዲሆልንዎ በራሴና በክ/ከተማው አስተዳደር ስም ከልብ እመኛለሁ።

አቶ ብርሃኑ ረታ
የየካ ክ/ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ

https://heylink.me/YEKAPROSPERITYPARTY/

Yekaprosperity.org.et

10/09/2024
10/09/2024

የከንቲባ አዳነች አቤቤ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት...!

በሀገር ውስጥና በውጭ የምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ፤
እንኳን ለ2ዐ17 ዓ.ም በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን።

በሰላም ያደረሰን ፈጣሪ አምላክ የተባረከና የተመሰገነ ይሁን፡
መልካም አዲስ አመት !
አዲሱን አመት የሠላም፣ የፍቅር፣ የደስታና የስኬት ያድርግልን፡፡

ባሳለፍነው ዓመት እንደ ሀገር የተጋረጡብንን በርካታ ፈተናዎች በድል የተሻገርንበት፣ ሴኬታማ ስራዎችን በመስራት ውጤቶችን ያስመዘገብንብት፤ እና የሕዝባችንን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ ያደርግናቸው ጥረቶች ፍሬ ማፍራት የጀመሩበት ነው፡፡

የኢትዮጵያ መልክ የሆነችው፡ መዲናችን አዲስ አበባም በፍቅር የደመቀች እና በህብረ-ብሔዊነት ያጌጠች ከተማ መሆኗን በተግባር እያሳየች የአብሮነት፣ የመተባበርና የመከባበር እሴትን አጠናክራ ያሳየችበት አመት ነው፡፡
ባለፈ ያሳለፍነው አመት አብሮነታችንን በማጠናከርና የበጎ ተግባር ስራዎቻችንን በማስፋት፡ የበርካታ የከተማችንን አቅመ ደካማ የሀገር ባለውለታዎች እና ለችግር የተጋለጡ ወገኖችቻንን እንባ ያበስንብት፣ የትኩረትና ክብር ተነፍጓቸው የኖሩ ወገኖቻችንን ዝቅ ብለን በማገልገል ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን ያጎላንበት አመትም ነው፡፡

ልማታችን ማንንም ወደኋላ የተወ አይደለም፡፡

በመሆኑም ባሳለፍነው ዓመት እንደ ሀገር ያስመዘገብናቸው የተሻሉ ውጤቶችን በመዘከር በቀጣይ ትልሞቻችን ላይ የሰላምና የልማት ሀይሎችን በማስተባበር በርካታ ሀገር አሻጋሪ ተግባራትን ለማከናወን ተዘጋጅተናል፡፡

በአዲሱ አመት እስከ አሁን በሰራነው ሳንረካ ይልቁንም የዛሬውን ትውልድ ከነገው ትውልድ ጋር በማስተሳሰር የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በብዙ ጥረት፣ በብዙ ትጋትና እና በማያቋርጥ ልፋት እጅ ለእጅ ተያይዘን በመስራት ሕዝባችንን ዝቅ ብለን እናገለግላለን፡፡

አዲሱ ዓመት በአንድነት የምንነሳበት፤ ከማይረቡን አጀንዳዎች ርቀን፡ እጆቻችንን ለስራ በማትጋት የሀገራችንን የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት በማረጋገት ሰላማችንን ምናፀናበት ከውጭና ከውስጥ የሚተናኰሉንን ሀይሎች በመመከት የኢትዮጵያን ሉአላዊነት አስጠብቀን የምንቀጥልበት እንደዚሁም የነዋሪዎቻችንን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎች ለመመለስ ተግተን የምንሰራበት ፍሬያማ ዓመት እንዲሆንልን ከልብ እመኛለሁ ፡፡
አመሰግናለሁ
መልካም አዲስ ዓመት!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!!

Photos from Prosperity party yeka woreda 8 branch-ብልጽግና's post 10/09/2024

የዛሬ ትጋት ለነገ ትሩፋት

ፓርቲያችን ብልጽግና የሴቶችንና የወጣቶችን ተጠቃሚነት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ከሚሰራባቸው ተግባራት ዋነኛው ሲሆን ወደ ብልጽግና ጉዞ ትልቅ አቅም ይፈጥራል ብሎም ያምናል በዚህም መሠረት ።

የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 8 አስተዳደር የሴቶችንና የወጣቶችን የስራ እድል ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከስራ አጥ ልየታ ጀምሮ የተለያዩ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎችን በመስጠት እንዲሁም የስራ እድል በማመቻቸት ላይ ይገኛል ።

በዛሬው እለት ''የዛሬ ትጋት ለነገ ትሩፋት'' በሚል መሪ ቃል በሁሉም ብሎኮች ከስራ እድል ፈጠራ ጋር ተያይዞ ውይይት ተደርገዋል ።

10/09/2024

በአዲስ ምዕራፍና መሻት ወደ ላቀ ዓፈጻጸም ከፍ ባለ ትጋት!

ዜና ሹመት!

ፓርቲያችን ብልጽግና በብሔራዊነት ወንድማማችነትና እህትማማችነትን መርህ ባደረገ ዕሳቤ ሀገራዊ ልዕልናን ለመገንባት እየተጋ ይገኛል። በተለይም የአድስአበባን ብልጽግናዊ ተምሳሌትነት በማስቀጠል በወል ዕውነት የፀናች የወል ሀገር ትኖር ዘንድ በመታተር ተልኮና ስምሪትን በመስጠት ዕምርታን እያስመዘገበ ቀጥሏል። ቃልን በተግባር በዓዲስ ምዕራፍ በማጽናት የአስተሳሰብና የተግባር አንድነትን ያጣመረ ለላቀ አፈጻጸም የሚያተጋ የአመራርር ምደባና ስምሪት ተካሂዷል።

በዚህም የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህብረተሰቡን የበለጠ ለማገልገል የሚያስችል የፖለቲካ ጤንነት፣ አቅም ፣ የተግባር ዉጤታማነት መሰረት ያደረገ የክ/ከተማ አመራሮች መልሶ ማደራጀት ተችሏል።
በዚህም
የካቢኔ አባላት

1 አቶ ምርክነህ ያቆብ
:-ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ
2 ጫሊ ቤኛ
:-ፐብሊክ ሰርቪስ ኃላፊ
3:-መለሰ ከበደ
:- አረንጓዴ ልማትና ከተማ ውበት ጽ/ቤት ኃላፊ
4 ሃይሌ ንጉሴ
:- አርሶአደርና ከተማ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ
5 አበባው ደመቀ
:- ኘላን ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ
6 ፈይሳ ረጋሳ
:-ዲዛይናግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ኃላፊ
7 ማስተዋል ፋንታሁን
:-ፋይናንስ ጽ/ቤት ኃላፊ
8 ሱራፌል እሸቱ
:-ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት
9 እናቴነሽ አለማየሁ
:- ሴቶችና ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ
10 አለማየሁ ማሞ
:- ንግድ ጽ/ቤት ኃላፊ
11 ታመነ አበበ
:-ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ
12 አብይ ጌታቸው
:-የባህል ኪነ ጥበብ እና ቱሪዚም ጽ/ቤት ኃላፊ
13 አለሙ ኢምሮ
:-ህብረተሰብ ተሳትፎ እና በጎ ፈቃድ ጽ/ቤት ኃላፊ

14:-ዮሃንስ ስዮም
:-ወጣቶችና ስፓርት ጽ/ቤት ኃላፊ
15:-አበበ ታመነ
:-ግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር

ፓርቲ ኮሚቴ
1:-ደረጄ ቴሪቦ
:-የፓርቲ ፋይናንስና ሰውሀብት ዘርፍ
2:-ጎሳዬ ሃሰን
የፓ/ዘርፍ ም/ኃላፊ
3:-አባይነህ ይፍሩ
የአደረጃጀት ዘርፍ ም/ኃላፊ

አማካሪ
1:-መሰረት መካሻ
:-የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ
2:-ወንደሰን ሙላት
:-የመልካም አስተዳደር ዘርፍ አማካሪ
3:-ያረጋል በላቸው
:-ኢኮኖሚ ዘርፍ

ፑል
1:-ዳዊት አብዲሳ
:-የዋና ስራ አስፈፃሚ ፑል ሃላፊ
2:-ብርሃኑ ደርሎ
:-ፐብሊክ ፑል ሃላፊ

ነን ካቢኔ
1:-ታሪኩ ደሳለኝ
:-ዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት ኃላፊ
2:-ቢሻው ግርማ
:-ህብረት ስራ ጽ/ቤት ኃላፊ
3:-ደስታ ነዳሳ
ስራና ክህሎት ም/ኃላፊ

https://heylink.me/YEKAPROSPERITYPARTY/

Yekaprosperity.org.et

Photos from Prosperity party yeka woreda 8 branch-ብልጽግና's post 10/09/2024

እንኳን ለ2017 የዘመን መለወጫ በዓል ዕንቁጣጣሽ በዓል አደረሳችሁ

ዘመን ዕድል ነው፡፡ ዘመንን መጠቀም ግን የሥራ ውጤት ነው፡፡ ዘመንን ፈጣሪ ለሁላችንም በእኩልነት ሰጥቶናል፡፡ ልዩነት የሚፈጠረው በዘመን በመሥራትና ባለመሥራት ነው፡፡ በታሪካችን ውስጥ የምንኮራባቸው ምእራፎች አሉ፡፡ በሕይወታችን ውስጥም ደስ የሚያሰኙን ጊዜያት አሉ፡፡ እነዚያ ምእራፎችና ጊዜያት ሌላ ነገር አይደሉም፡፡ የተሰጠንን የዘመን ዕድል በሚገባ ተጠቅመን የሠራንባቸው ወቅቶች ናቸው፡፡

እኛ ብንፈልግም ባንፈልግም ዘመን ይለወጣል፡፡ ጊዜ ወደፊት ብቻ የሚሄድ ማሽን ነውና፡፡ ማንም አያስቆመውም፤ አቅጣጫም አያስቀይረውም፡፡ የሚቻለው በጊዜ መጠቀም ብቻ ነው፡፡ “ክረምት ለሰነፍ ገበሬ መዓት፤ ለጎበዝ ገበሬ ምሕረት ነው” ይባላል፡፡ ምሕረትና መዓቱ ከዝናቡ የሚመጣ ሳይሆን ከገበሬዎቹ ዝግጅትና ሥራ የሚገኝ ነው፡፡ በሰነፍ ገበሬ ላይ ዘመን ይለወጥበታል፤ ብርቱው ገበሬ ግን ዘመንን ራሱን ይለውጠዋል፡፡

በ2016 ለኢትዮጵያ ምን አሳክተናል? በ2017ስ ለኢትዮጵያ ምን ተዘጋጅተናል? የእነዚህ ጥያቄዎች መልስ የዘመን መለወጥን ትርጉም ይቀይረዋል፡፡ ዘመን እየተለወጠብን ነው ወይስ ዘመኑን እየለወጥነው ነው? የሚለውን ያመለክተናል፡፡ ኢትዮጵያን ዘመን እየለወጣት ብዙ ጊዜ ኖራለች፡፡ አልፎ አልፎ ደግሞ በብርታትና በትጋት ዘመኑን ለውጣው ታውቃለች፡፡ ዘመን ሲለውጠን፣ ከተራራ እንደተፈነቀለ ድንጋይ፣ ወዳሰብነው ሳይሆን ወደ ፈለገው ነው የሚወስደን፡፡

2017 የሚለውጠን ሳይሆን የምንለውጠው ዓመት እንዲሆን ነው ምኞቴ፡፡ ዕቅዶቻችንን ተግብረን፤ ፕሮጀክቶቻችንን በጊዜና በጥራት አጠናቅቀን፤ ግጭቶቻችንን በውይይትና በድርድር ፈትተን፤ የዘመናት ስብራቶቻችንን በምክክርና በሽግግር ፍትሕ ጠግነን፤ በብዙ ነገሮች ራሳችንን ችለን፤ ሪፎርሞቻችንን በብቃት አሳክተን፣ የምንለውጠው ዘመን እንዲሆን ነው ምኞቴ፡፡

2017ን በኢትዮጵያ ታሪክ የሚጠቀስ ዘመን ለማድረግ እንዘጋጅ፡፡ የዘመናት ዕዳዎቻችን የምናወራርድበት፤ የኖሩ ቁስሎቻችን የምናክምበት፤ የዘመናት ሕልሞቻችንን ሥር መሠረት የምናስይዝበት፤ የታሪክን መኪና መሪና ማርሽ የምንቆጣጠርበት ዘመን ለማድረግ እንነሣ፡፡

ወደፊት የሚመጡት ልጆቻችን “ይሄ ታሪክ የተሠራው፣ የዛሬ ስንት ዓመት በ2017 ነው” እንዲሉን እናድርገው፡፡

በወጀብና በዐውሎ ውስጥ አስገራሚ ሥራዎችን እንድንሠራ የፈቀደ ፈጣሪ ዛሬም ከእኛ ጋር ነው፡፡ ነገም ከእኛ ጋር ነው፡፡ መሥራት የእኛ ማከናወንም የእርሱ ነው፡፡ እኛ ከተነሣን ዘመኑን እንድንለውጠው እርሱ ይረዳናል፡፡

በድጋሚ እንኳን ለ2017 የዘመን መለወጫ በዓል ዕንቁጣጣሽ አደረሳችሁ

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ጳጉሜን 5፣ 2016 ዓ.ም

//

:- ጠ/ሚንስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ

Photos from Prosperity party yeka woreda 8 branch-ብልጽግና's post 10/09/2024

የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የ2ኛ ዙር የኮሪደር ልማት የወንዝ ዳር ፕሮጀክት የቅድመ ዝግጅት ስራን ከወረዳ ዋና ስራ አስፈፃሚዎች ጋር ገመገመ

አስተዳደሩ የ2ኛ ዙር የኮሪደር ልማት የወንዝ ዳር ፕሮጀክት የቅድመ ዝግጅት ስራ ፕሮጀክቱ ከሚሰራባቸው ወረዳ ዋና ስራ አስፈፃሚዎች ጋር ገምግሟል።

የግምገማ መድረኩን የመሩት የየካ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ እና የስራና ክህሎት ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ እንዳልካቸው አስራት እንደገለፁት የ2ኛ ዙር የኮሪደር ልማት የወንዝ ዳር ፕሮጀክት ለከተማዋ ተጨማሪ ውበት የሚያላብስ እና ለነዋሪዎቿ ምቹ አከባቢ የሚፈጥር መሆኑን አንስተው ስራውን በየጊዜው እየገመገሙ መሄድ ፕሮጀክቱ በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ የጎላ ሚና እንዳለው በመግለፅ ስራውን በጥንቃቄ እና በልዩ ትኩረት መምራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

በመርሀ ግብሩ የ2ኛ ዙር የኮሪደር ልማት የወንዝ ዳር ፕሮጀክት ቅድመ ዝግጅት ስራ ሪፖርት በየካ ክፍለ ከተማ የዋና ስራ አስፈፃሚ የመልካም አስተዳደር ዘርፍ አማካሪ በአቶ ዮሃንስ ስዩም ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።

10/09/2024

የዛሬ ትጋት ለነገ ትሩፋት
ጳጉሜ 5, 2016 ዓ.ም

Photos from Prosperity party yeka woreda 8 branch-ብልጽግና's post 09/09/2024

ጠንካራ አብሮነት ለጽኑ አንድነት

በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 አስተዳደር ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎፍቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ በኢኮኖሚ ዝቅተኛ ለሆኑ የህብረተሰብ ከፍሎች የአዲስ አመት በዓልን ምክንያት በማድረግ የዶሮ ስጦታ አበረከተ።

በፕሮግራሙ ላይም ተገኝተዉ ንግግር ያደረጉት የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 08 ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ መሳይ ተካልኝ ብዙ ልንደርስላቸው የሚገቡ የተቸገሩ ወገኖቻችን አሉ እነኝህን ወገኖቻችንን በመተጋገዝ እና በመደጋገፍ ልንረዳቸው ይገባል በማለት አዲስ ዓመት የመተሳሰብ የመደጋገፍ በዓል እንዲሆን እኛም በወረዳችን የሚገኙ አቅመ ደካማ ነዋሪዋች እንኳን አደረሳችሁ ብለን የዶሮ፣ዘይት፣ዱቄት ስጦታ ስናበረክት በታላቅ ደስታ ነው ብለዋል።

አቶ መሳይ ተካልኝ አያይዘዉም በዓልን ሳንጠብቅ ሰውን ለመደገፍ ጊዜና ወቅት አያስፈልገውም እና በየትኛውም ጊዜ ለመርዳት ለመደገፍ ዝግጁ መሆን አለብን ብለዋል።

Photos from Prosperity party yeka woreda 8 branch-ብልጽግና's post 09/09/2024

መረዳዳት መደጋገፍ የብልጽግና እሴት ነው

ፓርቲያችን ብልጽግና ሰው ተኮር ፓርቲ ሲሆን የአቅመ ደካሞችን ቤት በማደስ በማዕድ ማጋራት በተግባር አስመስክሯል ።

የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 08 ብልጽግና ፓርቲ ኢንስፔክሽንና ስነ-ሞግባር ቅ/ፅ/ቤት የኮሚሽን ቤተሰብ በማስተባበር ጷግሜ 4 ''የህብር ቀን''ን አስመልክቶ በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ አቅም የሌላቸውን ነዋሪዎች እና የኮሚሽን አባላት ድጋፍ ተደርጓል።

በማዕድ ማጋራት ወቅት የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሳይ ተካልኝ፣ የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ብልጽግና ፓርቲ ኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ይመናሹ ጌታቸው እና የኮሚሽን ኮሚቴዎች ተገኝተዋል ።

Photos from Prosperity party yeka woreda 8 branch-ብልጽግና's post 09/09/2024

ማዕድ ማጋራት የሀገር ወዳድነት ምልክት፤ የወዳጅነት ውብ ማስታወሻ ነው። ማዕድ ማጋራት አንጡራ ባህላችን ነው። ካለን ላይ እናጋራ፤ ደስታን እንጋራ፣ እርስ በርሳችን እንደጋገፍ፤ በዓሉን በኀብረት ካለችን ለሌለው እያካፈልን ልባችንን እና ነፍሳችንን የሚመግቡ ትውስታዎችን በመፍጠር እናሳልፍ።

:- ጠ/ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ

Photos from Prosperity party yeka woreda 8 branch-ብልጽግና's post 09/09/2024

ጠንካራ አብሮነት ለጽኑ አንድነት

ፓርቲያችን ብልጽግና አብሮነት የሚያጠናክሩ የመረዳዳት የመጋገፍ ባህላችንን የሚያጉሉ ተግባራትን እየሰራ ሲሆን ሰው ተኮር ተግባራትን አጠናክሮ ቀጥሏል።

ከእነዚህ ሰው ተኮር ተግባራት ውስጥ አንዱ ማዕድ ማጋራት ሲሆን መጪው አዲስ አመት 2017 አስመልከቶ የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 8 አስተዳደር አቅመ ደካሞቸን ማዕድ ማጋራት ተችሏል ።

በማዕድ ማጋራት ፕሮግራም ላይ የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 08 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጥሩዓለም ባሳዝነዉ፣የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 08 ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ እና የወረዳዉ ሥራና ክህሎት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ መስፍን ሞግሶ፣የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 08 ዋና አፈጉባኤ ወ/ሮ ሙሉነሽ ሽፈራዉ፣የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 08 ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ጌታሁን ተረፈ፣የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 08 የብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ ወ/ሪት ኤልዳና በየነ፣የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 08 ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎፍቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ጣሰዉ ሺመላሽ እንዲሁም የወረዳዉ አመራሮችና አቅመ ደካማ ነዋሪዎች ተገኝተዉበታል።

የመክፈቻ ንግግር እና የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ያስተላለፉት የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 08 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጥሩዓለም ባሳዝነዉ ችግራችሁ ችግራችን በመሆኑ ተጋግዘን አብረን ተደጋግፈን ይችን ጊዜ በማሳለፍ ያለው ለሌለው በማጋራት ሁለት ያለው አንድ በመስጠት የተቸገሩትን የመደገፍ የማገዝ ሃላፊነት ስላለብን የመረዳዳት ባዕላችንን ማጠናከር እና ማጎልበት አለብን ብለዋል፡፡አቶ ጥሩ አለም አያይዘዉም እንደ ወረዳ በርካታ የበጎ ፍቃድ ስራዎች በመሰራት ላይ መሆነቸዉን ገልጸዉ በቤት እድሳትም ሆነ በማዕድ ማጋርት እንዲሁም በተለያዩ በጎ ተግባራት አቅም ያላቸዉ ግለሰቦች ባለሀብቶች ነጋዴዎች በማሳተፍ እንደ ወረዳ የተጀመሩትን የልማት እና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን ትኩረት ሰጥተን እየሰራን እንገኛለን በቀጣይም አጠናክረን እናስቀጥላለን ብለዋል፡ ።

በመጨረሻም በወረዳዉ ለሚገኙ አቅመ ደካማ የወረዳ ነዋሪዎች ማዕድ አጋርተዋል።

Photos from Prosperity party yeka woreda 8 branch-ብልጽግና's post 09/09/2024

በኅብር እንቆማለን የነገ ትልሞችን እናሳካለን
ጳጉሜ 4, 2016 ዓ.ም

ከተማችን አዲስ አበባ የአፍሪካ መዲና የተለያዩ አለም አቀፍ ተቋማት መቀመጫ ስትሆን የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ ከፍተኛ ስራ እየተሰራ ይገኛል ።

በዛሬው እለትም ''በኅብር እንቆማለን የነገ ተልሞችን እናሳካለን'' በሚል ከመገናኛ እስከ አበቤ ሱቅ ኮሪደር ልማት ላይ የፅዳት ንቅናቄ ተከናወነ ።

በጽዳት ወቅት የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጥሩአለም ባሳዝነው፣ የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሳይ ተካልኝ፣ የወረዳው አጠቃላይ አመራሮች እንዲሁም የወረዳው ነዋሪዎች ተገኝተዋል ።

09/09/2024

ኅብር ለሰላማችን
ጳጉሜ 4, 2016 ዓ.ም

Photos from Prosperity party yeka woreda 8 branch-ብልጽግና's post 08/09/2024

የኅብር ቀን በአብሮነት

ፓርቲያችን ብልጽግና ሰው ተኮር ፓርቲ በመሆኑ የበጎ ፈቃድ ተግባራትን በማጠናከር በቤት እድሳት ማዕድ በማጋራት አቅደ ደካሞችን በመደገፍ በተግባር አስመስክሯል ።

በዚህም መሰረት የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 08 አስተዳደር ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በነገው ዕለት የ2017 አዲስ ዓመት በዓልን ምክንያት በማድረግ ማዕድ ማጋራት መርሃ-ግብር እንደምያከናወን መሆኑን በዛሬው ዕለት ገልጸዋል

የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 08 አስተዳደር ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጣሰው ሺመላሽ እንደተናገሩት የማዕድ ማጋራት ቅድመ-ዝግጅት ሥራዎች መጠናቀቁን ገልጸው በነገው ዕለት የ2017 አዲስ ዓመት በዓልን ምክንያት በማድረግ ከሁሉም ቀጠና ለተወጣጡ አቅመ ደካማ የወረዳው ነዋሪዎች ማዕድ እንደምያጋሩ መሆኑን ገልጸዋል

Photos from Prosperity party yeka woreda 8 branch-ብልጽግና's post 08/09/2024

ሉአላዊነታችንን በደማችን፤ ልማታችንንም በላባችን እናረጋግጣለን
:-ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ጳጉሜን 3 የሉአላዊነት ቀን በመስቀል አደባባይ በደማቅ ስነ ስርአት ተከብሯል፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ የአዲእ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል። በመልእክታቸውም ኢትዮጵያ ከጎረቤቶቿም ሆነ ከሌሎች አገሮች ጋር በሰላምና በፍቅር መኖር ትፈልጋለች ነገር ግን ሉአላዊነቷን ለሚዳፈሩ ሁሉ መስዕዋትነት የሚከፍሉ ጀግኖች አሏት ብለዋል፡፡

እኛ ምንግዜም ቢሆን ሰላም እንሻለን ለዚህ ሰላም ጥሪ ደግሞ ተገቢውን ምላሽ የማይሰጥ ካለ ለሀገር መስዕዋትነት የምንሰስተው ነገር የለንም ብለዋል፡፡
ከውጭ የሚተነኩሱን የምናቀርበውን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ለሰላም ቅድሚያ ሊሰጡ ይገባልም ብለዋል፡፡ ከዚህ በፊት በጀግኖች እና አገር ወዳዶች የተገኘውን ሉአላዊነት አስጠብቀን ሰላማችንን እና ልማታችንን እናጸናለንም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ሰላም እጅግ ወሳኝና መሰረታዊ ጉዳይ ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ከጸጥታ ኃይሎች ጋር በመሆን ለመዲናዋ ሰላም ለሰሩት ስራ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ከእንግዲህ ለአገራችን እና ለከተማችን ሰላም ተባብረን በጋራ ልንቆም ይገባልም ብለዋል፡፡
ከዚህ በኋላ ለትውልዱ ምንዳ እንጂ እዳ ማስተላለፍ የለብንም ያሉት ከንቲባ አዳነች እስካሁንም በሰራናቸው የተለያዩ የልማት ስራዎች ከፍተኛ ውጤት መመዝገቡንም አስታውሰዋል፡፡

ለዚህም የአዲስ አበባን ሁለንተናዊ ልማት በማሳያነት ያነሱት ከንቲባ አዳነች አዲስ አበባን የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ እና እነንደ ስሟ ውብ እና አበባ ለማድረግ በተሰሩ ስራዎች ውጤት መመዝገባቸውን ጠቁመዋል፡፡

በቀጣይ ለአገር እና ለከተማችን ልማት ያለ እረፍት በትጋት መስራት ይኖርብናል ብለዋል፡፡ ሉአላዊነታችን ደምና አጥንት ተከፍሎበታል ያሉት ከንቲባ አዳነች አገራችን ኢትዮጵያ በጀግኖች ልጆቿ መስዕዋትነት ታፍራ እና ተከብራ እዚህ ደርሳለችም ብለዋል፡፡
ይህን ህይወት የተገበረበት መስዕዋትነት እኛም ልናስቀጥለው ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ለዚህም ጀግኖችን አመስግነዋል፡፡

https://heylink.me/YEKAPROSPERITYPARTY/

Yekaprosperity.org.et

08/09/2024

ክብር በሁሉም መስክ መስዋዕት ለከፈላችሁና ለምትከፍሉ ጀግኖቻችን!! እንኳን ለሉዓላዊነት ቀን አደረሳችሁ !!

ሀገራችን ኢትዮጵያ ከዉጭና ከዉስጥ የሚገጥሙ ፈተናዎችን በጽናት እየተሻገረች ሉዓላዊነተን ጠብቃ የቆየች፤ ሉዓላዊነቷን በመዳፈር ነጻነቷን ለመግፈፍ የሚሞክሩ የዉጭ ጠላቶችን በጀግኖች ልጆቿ መስዋዕትነት እየቀለበሰች፤ የዉስጥ ባንዳዎችንም እኩይ ሴራና ተልዕኮ እያከሸፈች ሉዓላዊነትቷን አስከብራ ኖራለች፡፡

በሌላ በኩል በደም የተገኘን ነጻነት በላብ ማጽናት ተስኖን ለዘመናት የረሃብና ድህነት ምሳሌ ተደርገን ስንቆጠር ነበር!!
ይህን ሁኔታ ለመቀየር የአሁኑ ትውልድ ለዛሬና ለነገ አስቦ ላቡን በማፍሰስ ወደ ብልጽግና ማሻገር ብሎም ከትናንት የወረሰውን ሃገርን በመስዋዕትነት የማጽናት ወኔን ተላብሶ ጀግኖችን መዘከርና ራሱ የጀግንነት ታሪክ መስራት ይገባዋል።

በድጋሜ እንኳን አደረሳችሁ
ጳጉሜ 03/2016 ዓ.ም

:-አቶ ብርሃኒ ረታ
የየካ ክ/ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ

https://heylink.me/YEKAPROSPERITYPARTY/

Yekaprosperity.org.et

Photos from Prosperity party yeka woreda 8 branch-ብልጽግና's post 08/09/2024

ህብር ለሁለንተናዊ ሉዓላዊነት
ጳጉሜ 3, 2016 ዓ.ም

የየካ ክ/ከተማ ነዋሪዎች የሉዓላዊነት ቀንን ለማክበር በመስቀል አደባባይ

08/09/2024

ኅብር ለሁለንተናዊ ሉዓላዊነት
ጳጉሜ 3, 2016 ዓ.ም

Photos from Prosperity party yeka woreda 8 branch-ብልጽግና's post 08/09/2024

ህብር ለሁለንተናዊ ሉዓላዊነት
ጳጉሜ 3, 2016 ዓ.ም

የየካ ክ/ከተማ ነዋሪዎች የሉዓላዊነት ቀንን ለማክበር በመስቀል አደባባይ ተገኝተዋል ።

Photos from Prosperity party yeka woreda 8 branch-ብልጽግና's post 07/09/2024

በአዋሬ የተገነባው የመኖሪያ መንደር ብቻ ሳይሆን የሰውን ህይወት እና አኗኗር እንዲሁም አካባቢን እንደ አዲስ የመቀየረ ተግባር ሲሆን የአዋሬ የጋራ መኖሪያ መንደር 275 መኖሪያ ቤቶችን፣ 130 ሱቆችን፣ 3 ሰፋፊ እና አካፋይ መንገዶችን፣ የወንዝ ዳርቻ ልማትን፣ የአረንጓዴ ቦታዎች ልማትን፣ የህፃናት መጫወቻን እንዲሁም የመኪና ማቆሚያዎችን ያካተተ ነው።

ለአዋሬ ተነሺዎች ለተገነቡት አምስት ባለ 11 ወለል ህንፃዎች ግንባታ እና አርዓያነት ያለው የመሪነት ሚና ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶ/ር ዐቢይ አሕመድን በከተማችን ነዋሪዎች ስም ላመሰግናቸው እወዳለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Photos from Prosperity party yeka woreda 8 branch-ብልጽግና's post 07/09/2024

አዋሬን ለሰው ልጅ ክብር ምቹ አድርጎ ወደ ህያውነት የመለወጥ ትልማችን እና ጥረታችን እውን ሆኗል።

Our aspiration to transform Aware has become a reality, bringing dignified living to life.

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ

Photos from Prosperity party yeka woreda 8 branch-ብልጽግና's post 07/09/2024

መረዳዳት መደጋገፍ የብልጽግና እሴት

ፓርቲያችን ብልጽግና ሰው ተኮር ፓርቲ በመሆኑ አብሮነትን መደጋገፍ እሴቱ በማድረግ እየሰራ ይገኛል ።

በዛሬው እለትም የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ምክር ቤት በወረዳው ውስጥ ላሉ አቅመ ደካሞች ማዕድ ማዕድ ማጋራት ችሏል።

በማዕድ ማጋራት ላይ የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጥሩአለም ባሳዝነው፣ የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሳይ ተካልኝ፣ የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ሙሉነሽ ሽፈራው እና አጠቃላይ አመራሮች ተገኝተዋል ።

Photos from Prosperity party yeka woreda 8 branch-ብልጽግና's post 07/09/2024

ቀልጣፋ አገልግሎት የስልጡን ዜጋ መገለጫ ነው

የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 8 አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች '' የሪፎርም ቀን'' አስመልክቶ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ምልከታ አደረጉ ።

በምልከታው ወቅት የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጥሩአለም ባሳዝነው፣ የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሳይ ተካልኝ እና የአስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ተገኝተዋል ።

ቀልጣፋ ፣ ግልፅ፣ በቴክኖሎጂ የተደገፈ እንዲሁም ምቹ የስራ አከባቢን በመፍጠር አልግሎት አሰጣጥ በማዘመን ሁለንተናዊ ብልጽግናችንን ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ በምልከተው ወቅት ተገልጿል ።

በተቋማቱ ምልከታ ያደረጉት የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጥሩአለም ባሳዝነው፣ የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሳይ ተካልኝ እንዲሁም አስተባባሪዎች የእንኳን አደረሳችሁ ስጦታ ለባለሙያዎች እንዲሁም በ''አገልግሎት ቀን'' ለተገኙ የወረዳችን ነዋሪዎች አበርክተዋል ።

Photos from Prosperity party yeka woreda 8 branch-ብልጽግና's post 07/09/2024

የሪፎርም ቀን
ቀልጣፋ አገልግሎት የስልጡን ዜጋ መገለጫ ነው
ጳጉሜ 2,2016 ዓ.ም

Photos from Prosperity party yeka woreda 8 branch-ብልጽግና's post 07/09/2024

Want your organization to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Videos (show all)

የምትተክል ሀገር የሚያፀና ትውልድ የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 8 የአንድ ጀንበር አረንጓዴ አሻራ #600_ሚሊየን_ችግኝ #ነሐሴ_17_2016 #አረንጓዴ_አሻራ #aa_prosperity #prosperi...
የየካ ወረዳ 8 ነዋሪዎች ጉዞ ወደ አረንጓዴ አሻራ
የመገናኛ ሲኤምሲ መስመር!!፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ ----------ዘመንን የዋጀ ፤ ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የመደመር ትውልድ ታሪካዊ የብልፅግና ጉዞዋችን አሻራ:- የአዲስ አበባ ...
...ለሀገራችን ይህ አዲስ ነገር ነው!!"ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከኢ.ቢ.ኤስ ቴሌቪዥን እሁድን በEBS ፕሮግራም ጋር ካደረጉት ንግግር የተወሰደ!
ዘመንን የዋጀ ዘመን ተሻጋሪ የመደመር ትውልድ ደማቅ ታሪካዊ አሻራ! የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት!!ሰናይ ሰኞ!!#aa_prosperity
ተግዳሮት ያልበገረው የመደመር ትውልድ የለኮሰው ብልጽግናዊ ጉዞ ፦ የየካ የኮሪደር ልማት!https://heylink.me/YEKAPROSPERITYPARTY/#aa_prosperity #addisabab...
“የምትተክል ሀገር፣ የሚያፀና ትውልድ”
ውብ አዲስ አራዳ፣አዲስ ጽጌሬዳ::ግምቦች ጌጠኛ...ጎዳናው ጤነኛጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
የሚድያ ስርጭት ጥቆማ!!አዲስን እንደ አዲስ!!ክፍል ሁለት ዛሬ ምሽት:-በ👉AMN = 2:30👉 Walta = 4:30👉 Prime media = 2:30👉 NBC = 4:30👉 EBC = 3:30 ላይ ይ...

Telephone

Website

Address


Addis Ababa