Tirita Home-Healthcare and Ambulance Service P.L.C

We are a group of nurses and physicians with tremendous work experience striving to improve palliative and hospice care in Ethiopia.

Photos from Tirita Home-Healthcare and Ambulance Service P.L.C's post 04/05/2024

ለመላዉ የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ ። መልካም በአል እንዲሆንላችሁ ድርጅታችን ይመኛል።

Photos from Tirita Home-Healthcare and Ambulance Service P.L.C's post 09/04/2024

ትርታ የቤት ለቤት ጤና እንክብካቤ ተቋም እንኳን ለዒድ አል-ፊጥር በዓል በሰላም አደረሰዎት እያልን
በዓሉ የሠላም፣ የደስታ፣ የፍቅርና የመተሳሰብ እንዲሆንልዎ ከልብ እንመኛለን!

Photos from Tirita Home-Healthcare and Ambulance Service P.L.C's post 01/03/2024

እንኩዋን ለ 128ኛው የ አድዋ ድል በአል በሰላም አደረሳቹ። ክብር ለጀግኖች አባቶቻችን።

Photos from Tirita Home-Healthcare and Ambulance Service P.L.C's post 06/01/2024

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን ።

TikTok · Tirita home care 🫂 20/07/2023

የአባለዘር በሽታ

TikTok · Tirita home care 🫂 Check out Tirita home care 🫂's video.

Photos from Tirita Home-Healthcare and Ambulance Service P.L.C's post 27/06/2023

በፍቅር እና በደስታ የሚያሳልፉት ዒድ አል- አድሃ (አረፋ) በዓል እንዲሆንልዎ ከልብ እንመኛለን!

ዒድ ሙባረክ!

03/06/2023

Hemorrhoids

19/05/2023

ስለ እርግዝና መከላከያ ማወቅ ያሉብን ነገሮች

20/04/2023

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ቤተሰቦቻችን ኢድ ሙባረክ መልካም በአል ይሁንላችሁ ።🌙🌙🥰🥰🥰

Photos from Tirita Home-Healthcare and Ambulance Service P.L.C's post 15/04/2023

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኩዋን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዐል በሰላም አደረሳችሁ ።

30/03/2023

የአፍንጫ አስም/allergic rhinitis/

27/03/2023

HIV virus

23/03/2023

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች መልካም የረመዳን ጊዜ እንዲሆንላችሁ ትርታ ሆም ኬር ይመኛል።

Happy Ramadan 🌙🌙🌙

15/03/2023

የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን (Vulvovaginal yeast infection)
የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን ምንድን ነው?
የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን በሴት ብልት የውጨኛው ቆዳ ላይ የመቆጣት እና የማሳከክ ስሜት የሚያስከትል ኢንፌክሽን ነው።
ይህ ኢንፌክሽን የሚከሰተው ካንዲዳ(candida) በመባል በሚጠራው የፈንገስ ዝርያ ነው።
የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን ምልክቶችና የህመም ስሜቶች ምንድን ናቸዉ?
ምልክቶቹ የሚከተሉትን ያካትታሉ
● የሴት ብልት የውጨኛው ቆዳ ማሳከክ
● የሽንት ማቃጠል
● የሴት ብልት እና የሴት ብልት የውጨኛው ቆዳ ማቃጠል፣ መቅላት ወይም መቆጣት
● በወሲብ ወቅት ህመም
● የሴት ብልት ፈሳሽ
አንዳንድ የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን ያላቸው ሴቶች ከሴት ብልት ውስጥ ትንሽ ፈሳሽ ሊኖራቸው ይችላል። ይህ ፈሳሽ በአብዛኛው ነጭና እንደ አይብ የሚበጣጠስ ነው። ነገር ግን ቀጭን እና እንደ ውሃም ሊሆን ይችላል።
ምልክቶቼ በፈንገ ኢንፌክሽን ምክንያት መሆኑን እንዴት አውቃለሁ?
አብዛኛዎቹ ሴቶች የምልክታቸው መንስኤ የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን ይሁን ወይም ሌላ ነገር ይሁን ሊያውቁ አይችሉም ። የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን ምልክቶች ከሌሎች የሴት ብልት ኢንፌክሽን ምልክቶች ጋር ተመሳሳይ ናቸው ፤ ስለዚህ ምርመራ ሳያደርጉ በዚህ ምክንያት ነው ብሎ ለመናገር በጣም አስቸጋሪ ነው። እርግጠኛ ለመሆን ሃኪም ወይም ነርስጋ ቀርቦ መታየት እና ከማህጸን ፈሳሽ ናሙና ተወስዶ የላቦራቶሪ ምርመራ ማድረግ ያስፈልጋል።
የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን እንዴት ነው የሚከሰተው?
የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን የሚያመጣው ፈንገስ አብዛኛውን ጊዜ በአንጀት ውስጥ እና በሴት ብልት ውስጥ ይኖራል። ይሁንና የፈንገሱ ቁጥር አነስተኛ በመሆኑ አብዛኛውን ጊዜ የበሽታ ምልክቶች አይኖርም።
የተወሰኑ መድሃኒቶች (በተለይም አንቲባዮቲክስ) ፣ ጭንቀትና ሌሎች ምክንያቶች ፈንገሶቹ እንዲባዙ ሊያደርጉ ይችላሉ። ይህ በሚሆንበት ጊዜ የማህጸን የፈንገስ ኢንፌክሽን ምልክት መታየት ይጀምራ።
ከስር የተዘረዘሩት ለሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን
የሚያጋልጡ ሁኔታዎች ናቸዉ
●የአንቲባዮቲክስን መጠቀም
●የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብሎች መጠቀም
●የስኳር በሽታ
●እርግዝና
●የተዳከመ የሰውነት የበሽታ መከላከያ ስርዓት (የኬሞቴራፒ ሕክምና፣ኤች አይ ቪ)
የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን እንዴት ይታከማል?
ለሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን የሚሆኑ መድኃኒቶች ​​ሊወስዱ ይችላሉ። መድኃኒቶች የሚዋጡ ወይም በሴት ብልት ውስጥ የሚቀመጡ ሊሆኑ ይችላሉ። በሴት ብልት ውስጥ የሚቀመጡት መድሃኒቶች በክኒን ወይም በክሬም መልክ ሊመጡ ይችላሉ። ለሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን የሚወሰዱ ሁሉም መድሃኒቶች ኢንፌክሽኑን የሚያስከትሉ ፈንገሶችን በመግደል ይሰራሉ።
ጥሩ ስሜት የሚሰማኝ መቼ ነው?
ሕክምና እንደጀመሩ በጥቂት ቀናት ጊዜ ውስጥ ጥሩ ስሜት ሊሰማዎት ይችላል። ህክምናን ካጠናቀቁ በኋላ ካልተሻለዎት ​​ዶክተርዎን ወይም ነርስዎን እንደገና ማየት አለብዎት ፤ ተጨማሪ መድሃኒት መውሰድ ወይም ሌላ መድሃኒት መውሰድ ይኖርብዎት ይሆናል።
ባለቤቴስ ህክምና ማድረግ ይጠበቅበታል?
የሴት ብልት የፈንገስ ኢንፌክሽን በግብረ ስጋ ግንኙነት የሚተላለፍ አይደለም ። አልፎ አልፎ ከአንዱ ወደ አንዱ የመጋባት ሁኔታ ቢስተዋልም ፤ ባለሙያዎች የወሲብ ጓደኛ ህክምና እንዲያደርግ አይመክሩም።
ለበለጠ መረጃ Website: tiritahome.com
Telegram: https://t.me/tiritahome
Twitter:
Instagram: tiritahome
Phone No.: 0965500000/0902200002

Photos from Tirita Home-Healthcare and Ambulance Service P.L.C's post 10/03/2023

• #በአፍንጫ ደም መፍሰስ ወይም ነስር
በአንዱ ወይም በሁለቱ የአፍንጫ ቀዳዳ ቀላል ወይም ከባድ ደም መፍሰስ ሲሆን ከጥቂት ሰኮንዶች እስከ 15 ደቂቃ ወይም ከዚያ በላይ ሊቆይ የሚችል ደም መፍሰስ ነው።
• አፍንጫ የውጨኛው ዋና የመተንፈሻ አካል ክፍል ሲሆን የአፍንጫ የውስጠኛ ግድግዳ በብዙ ደቃቅ የደም ቱቦዎች የተለበደ ነው። እነዚህ የደም ቱቦዎች ደግሞ በቀላሉ መጎዳትና መድማት የሚችሉ ናቸው።
• አፍንጫ አየርን ለማስገባትና ለማስወጣት እንድሁም ለማሽተት ወሳኝ ክፍል ሲሆን የምናስገባውን አየር ማሞቅ፡ ማርጠብና ማጠራት ዋና ስራው ነው።
• አፍንጫ በዋናነት በሁለት ምክናየቶች ይደማል።
1. ደረቅና ቀዝቃዛ አየር በብዛትና ተደጋጋሚ ሲያልፍበት እና
2. አፍንጫን ሲጎረጎር ነው።
#ተጨማሪ ለአፍንጫ መድማት እንደምክናየት የሚቆጠሩት
• የሳይነስ ኢንፌክሽን
• አላርጅ
• መድሀኒቶች እንደ አስፕሪንና ደም ማቅጠኛዎች
• አፍጫን የሚቆጠቁጡ ኬሚካሎች እንደ አሞኒያ
• ኮኬን መጠቀም
• የአፍንጫ ኢንፌክሽን
• ጋዝ መድሀኒቶች
• የአፍንጫ ምት/ግጭት
• የደም ካንሰር
• የፕላቴሌት ማነስና ችግር
• አፍንጫ ውስጥ የተፈጠሩ እብጠቶች
• እርግዝና እርጅና
• የአፍንጫ ቀዶ ጥገና
• ህፃን መሆን
• የአየር ፀባይ መቀየር
• ከፍታማ ቦታ
#ማሳሰቢያ
• በአፍንጫ ደም መፍሰስ የከፍተኛ ደም ግፊት ምክናየት ወይም ምልክት አይደለም። ነገር ግን ከፍተኛ ደም ግፊት የአፍንጫ ደም መፍሰስን ያባብሳል። የአፍንጫ ደም መፍሰስ ብዙዎችን ቢያስፈራም የከባድ ችግር ምልክት ወይም ከባድ ችግር ግን አይደለም። ብዙዎችም እዛው በቤታቸው እራሳቸውን ያክማሉ።
#ነስርን ለማቆም የሚከተሉትን መንገዶች ይጠቀሙ።
ማሳሰቢያ፡ ነስርን ለማቆም ወደ ሗላ ማንጋጠጥና አንዳዶች ደግሞ ፈሶ ይውጣ የሚለው ተግባር ፈፅሞ ስህተት ነው።
• ሲያንጋጥጡ ደምዎት ወደውስጥ እየፈሰሰ ነው።
• ፈቅደው ሲያፈሱት ደግሞ ደምዎትን እያጡነውና አያድርጉት።
#ቅደም ተከተል
1. መጀመሪያ ሰውነተወን ዘና አድርገው ምቹ ቦታ ላይ ቁጭ ይበሉ።
2. አየአፍንጫዎትን ላስላሳ ክፍል ወደአፍንጫዎት አጥንት ክፍል ጠጋ ብለው በአውራጣትና ሌባ ጣተዎ ጠበቅ አድርገው በመያዝ ወደፊት አንገተዎትን ያንጋጡ(ያግጥጡ)። ከ10-15ደቂቃም እንደያዙት ይቆዩ። ወደሗላ ማንጋጠጥና ወደታች ማቀርቀር አይደለም። በዚህ ወቅት በአፈዎ ይተንፍሱ።
3. ከግንባር ትንሽ ወረድ ብሎ ባለ ቦታ ላይ በፎጣ የተጠቀለለ በረዶ ያስቀምጡ።
4. ይህን ቢያንስ ሁለት ዙር ይሞክሩ። ብዙ ጊዜ ቶሎ ይቆማል። ግን ከ10-15 ደቂቃ ለመያዝ ትዕግስት ይኑረዎት!
5. በዚህ ካልቆመ ተጨማሪ ህክምና ፈጠን ብለው ያግኙ። ለበለጠ መረጃ Website: tiritahome.com
Telegram: https://t.me/tiritahome
Twitter:
Instagram: tiritahome
Phone No.: 0965500000/0902200002

07/03/2023

1. በኦፕራሲዮን መውለድ ጥቅሞች
የእናት ጉዳት እና ሞትን ይቀንሳል
የሕፃን ጉዳት እና ሞትን ይቀንሳል
የመራቢያ አካላት መላላትና ወደ ዉጭ መዉጣትን ይከላከላል
🥷🥷🥷🥷🥷🥷🥷🥷🥷🥷🥷
2. ጉዳቶቹስ ምንድናቸው?
የማደንዘዣ አና ተያያዥ ችግሮች
ከፍተኛ ደም መፍሠስ
ኢንፌክሽን
ቁስሉ አካባቢ መደንዘዝ እና ሕመመም
በኦፕሬሽን ወቅት የሚከሰት የሆድ እቃ መጎዳት(internal organ injury )
የቁስል መፈታት( dehiscence )
የሆድ እቃ መጠባበቅ(Adhesions)
👌👌👌👌👌👌👌👌👌👌👌
3. መደረግ ያለባቸው ጥንቃቄዎች
3.1 እንቅስቃሴ- ከማደንዘዣ እነደወጣች መጠነኛ አንቅስቃሴ ይመከራል
6.2 ምግብ - ያልተወሳሰበ ኦፕራሲዮን ከሆነ 4-6 ሰዓት በኋላ መመገብ ደመከራል።
3.3 ሻወር-ከኦፕሬሽኑ ከ48-72 ሠዓታት በቤተሰብ የታገዘ ሻወር ይመከራል።
3.4- ግንኙነት 6-8 ሳምነታት በኋላ ይመከራል
🕒🕒🕒🕒🕒🕒🕒🕒🕒🕒🕒🕒
4. ስንት ጊዜ cs መሆን ይቻላል?
የበፊት አመመለካከቶቾ ከሶሥት CS በላይ የማይፈቅዱ ቢሆንም የቅርብ ጊዜ ጥናቶች ምንም አይነት ገደብ አያስቀምጡም። በሃኪም እና በታካሚዋ ምክክር ይወሰናል።
🤷‍♀🤷‍♀🤷‍♀🤷‍♀🤷‍♀🤷‍♀🤷‍♀🤷‍♀🤷‍♀🤷‍♀🤷‍♀
5. ወደፊት ምን ጉዳት ሊያስከትል ይችላል?
የአንግደ ልጅ አቀማመጥ መዛበት ና መጣበቅ
ተደጋጋሚ ኦፕራሲዮን ተጋላጭነት ይጨምራል
ቁሥሉ አካባቢና መራቢያ አካል የመደንዘዝ ስሜት ሊፈጥር ይችላል።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
6. ያለበቂ የሕክምና ምክነያት Cs ሊሠራ ይችላል?
ባደጉ አገራት በእናት ጥያቄ መሰረት ኦፕራሲዮን የሚፈቀድ ሲሆን በሀገራችን ኢትዮጵያ አስካሁን የተቀመጠ ሕግ የለም።በWHO እስካሁን ድረሥ ፈቃድ አላገኘም
💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪
7. በኦፕራሲዮን ወልዶ አምጦ መውለድ የቻላል?
አንድ ኦፕራሲዮን ያላት አናት በቀጣይ እር ግዝና ምጥ መሞከር(VIBAC) የምትችል ሲሆን የሕክምና በለሙያ ጥብቅ ክትትል ስር መሆን አስፈላጊ ነው።
🕒🕒🕒🕒🕒🕒🕒🕒🕒🕒🕒🕒
8. CS ስንት ሠዓት ይፈጃል?
በአማካይ 45 ደቂቃ ሲሆን በኦፕራሲዮን ወቅት ባሉ ሁኔታዎች ይወሰናል።
🧜‍♀🧜‍♀🧜‍♀🧜‍♀🧜‍♀🧜🧜🧜🧜🧜🧜🧜
9. ምን አይነት የሠመመን ዓይነት የተሻለ ነው?
በአሁን ወቅት ከወገብ በታች ማደንዘዣ(regional Anesthesia ) ተመራጭና የ95 በመቶ ድርሻ ሲይዝ በተለያዩ ምክንያት ጠቅላላ ማደንዘዣ (General anesthesia ) ልንጠቀም እንችላለን ።Website: tiritahome.com
Telegram: https://t.me/tiritahome
Twitter:
Instagram: tiritahome
Phone No.: 0965500000/0902200002

04/03/2023

ስለ የደም ማነስ መረዳት ያሉብን ነገሮች ።

01/03/2023

ሳል
• ሳል ብዙ ጊዜ አጣደፊ የሆነ የአጭር ጊዜ (ከሶስት ሳምንት ያነሰ) ወይም የረጅም ጊዜ (ከአራት ሳምንት) የዘለለ ሊሆን ይችላል።

• ጉንፋን
• ኢንፊሎወንዛ
• አለርጅ
• የብናኝና ኬሚካል መግባት
• የሳንባ ምች
• ትክትክ በሽታ
• ቲቢ
• አስም
• የብሮንከስ ኢንፌክሽን
• የጉሮሮ በሽታ
• የሳይነስ ኢንፌክሽን
• የፈሳሽና አየር ሳንባ ውስጥ መጠራቀም
• አንዳንድ መድሀኒቶች
• የሳንባ ካንሰር
• ከባድ የልብ ችግር
• ሌሎችም

1. ሻይ
2. የማር ሻይ
3. የሎሚ ሻይ
4. ዝንጅብል ሻይ
5. በቂ ፈሳሽ መውሰድ
6. ስቲም ወይም እንፋሎት መጠቀም
7. ጨው ባለው ውሀ ጉሮሮን መጉመጥመጥ ወይም ማኩረፍረፍ
8. ፍራፍሬ እንደ ብርቱካን አይነት መጠቀም
9. የአናናስ ጁስ መጠጣት እና ሌሎችም ለበለጠ መረጃ Website: tiritahome.com
Telegram: https://t.me/tiritahome
Twitter:
Instagram: tiritahome
Phone No.: 0965500000/0902200002

26/02/2023

አስም

23/02/2023

ሩማቶይድ አርተራይተስ / ቁርጥማት?

ሩማቶይድ አርተራይተስ በዋናነት መገጣጠሚያዎችን የሚያጠቃ የኢሚዩኒቲ መስተጋብር መፋለስ በሽታ ነው፡፡

በአለም ደረጃ 18 ሚሊዬን ሰዎች የዚህ በሽታ ተጠቂ ናቸው፡፡ በሀገራችን ያለው የበሽታ ስርጭት በውል አይታወቅም፡፡ ከግማሽ እስከ አንድ ሚሊዬን የሚደርሱ ተጠቂዎች ሊኖሩ እደሚችሉ ይታመናል፡፡ ዋና መነሻ ምክንያቱ በውል ባይታወቅም የዘር ተዋረድ፤ ሴት መሆን እና ሲጋራ ማጨስ አጋላጭ እንደሆኑ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ በሽታው በሁሉም እድሜ ክልል ያሉ ሰዎችን ያጠቃል፡፡ ሴቶች ከ ወንዶች ይልቅ ሶስት እጥፍ ተጠቂ ናቸው፡፡

ምልክቶቹ የሚከተሉት ናቸው

የመገጣጠሚያ ህመም ፤ እብጠት እና ተፈጥሮአዊ ቅርፅ መዛባት፡፡ ጠዋት ከእንቅልፍ ሲነሱ መላ ሰውነት መተሳስር፤ ልብስ ለመልበስ እና የግል ንፅህናን ለመጠበቅ መቸገር፤ ቀኑ ረፈድ እያለ ሲሄድ ሰውነትን ለቀቅ ማደረግ፡፡ ይኸ በዋናነት በእጅ እና እግር ጣቶች ላይ በርትቶ ቢስተዋልም ሁሉንም መገጣጠሚያዎች ያጠቃል፡፡

ከመገጣጠሚያ ውጪ ያሉ አካል ክፍልንም ያጠቃል፡፡ የድካም ስሜት፤ ማታ መታ ማላብ፤ የአይን መቅላት እና ህመም ፤ የቆዳ ላይ ቁስለት እና እብጠት (Rheumatoid nodule) ፤ ሳንባ በሚያጠቃበት ጊዜ ሳል እና የትንፋሽ ማጠር ምልክቶች ይታያሉ፡፡
በሽታው በደም ላይ የሚያሳያቸው ምልክቶች አሉት፡፡ የ ኢ ኤስ አር (ESR)እና ሲ ር ፒ(CRP) ከፍ ማለት /ቁጥር መጨመር፤ የ ሩማቶይድ ፋክተር (Rheumatoid factor) እና አንታይ ሲሲፒ(Anti CCP) ቁጥር መጨመር። እነዚህ ምልክቶች ሲታዩ ወደ ህክምና መሄድ እና በሽታው መታወቅ አለበት። ለበለጠ መረጃ Website: tiritahome.com
Telegram: https://t.me/tiritahome
Twitter:
Instagram: tiritahome
Phone No.: 0965500000/0902200002

14/02/2023

#መካንነትን እንደት መከላከል ይቻላል? በተለይ በሴቷ በኩል?

• ጤናማ የአኖኖር ዘይቤን መከተል
• ከፍተኛ የአካል እንቅስቃሴን መተው
• አነቃቂ መጠጦችን መቀነስ
• አልኮልን መተው ወይም መቀነስ
• አለማጤስ
• የተመጣጠነ ምግብ
• አትክልትና ፍራፍሬ መመገብ
• ክብደትን ማመጣጠን
• የተለያዩ በሽታዎች ካሉ መታከም
• ስኳር ህመም ካለ መታከም
• የታይሮድ መጠን አነስተኛ ወይም ከፍተኛ መሆነ ለማስተካከል መሞከር
• እራስን ከአባላዘር በሽታ መጠበቅ። ካለ ፈጥኖ መታከም
• ሳይዘገዩ ለማርገዝ መሞከር
• የጤና ምርመራ በየጊዜው ማድረግ ዋና ዋናዎቹ ናቸው። ለበለጠ መረጃ Website: tiritahome.com
Telegram: https://t.me/tiritahome
Twitter:
Instagram: tiritahome
Phone No.: 0965500000/0902200002

10/02/2023

#ውፍረት

አሁን ላይ ለብዙ ሀገራት አስጊ የሆነ ውስብስብ በሽታ ሲሆን መገለጫውም ከመጠን በላይ የሆነ የስብ መከማቸት ነው።


1. በቤተሰብ ወፋፍራም መሆን
2. ብዙ መብላት። አትክልትና ፍራፍሬ አለማዘውተር
3. እንቅስቃሴ አለማድረግና እረፍት ማብዛት
4. የእንስሳት ተዋፅኦን አፍቃሪ መሆን። የስጋ፡ እንቁላልና የወተት ተዋፅኦ ማዘውተር
5. አልኮል መጠጣት
6. መድሀኒቶች

# በጤና ላይ የሚያመጣው ችግር
• የልብ ችግር
• የስኳር ህመም
• ከፍተኛ የደም ግፊት
• ካንሰር
• መጨናነቅ
#ውፍረት መቀነሻ መንገዶች
በጣም አስቸጋሪ መሆኑ ይታወቃል። ይሁን እንጅ ውፍረትን መቀነስ ይቻላል። ዋናውና ብዙዎች የሚያጡት ቁርጠኝነቱን ነው። ውፍረት ለመቀነስ የሚከተሉትን ይጠቀሙ።
1. ቁርጠኛ ይሁኑ
2. ፍራፍሬና ቅጠላቅጠል ይመገቡ
3. እረጅም የአካል እንቅስቃሴ ያድርጉ
4. የእንስሳት ተዋፅኦ ይቀንሱ
5. እራስዎን በስራ ቢዚ ያድርጉ
6. አልኮል አይጠጡ ለበለጠ መረጃ Website: tiritahome.com
Telegram: https://t.me/tiritahome
Twitter:
Instagram: tiritahome
Phone No.: 0965500000/0902200002

06/02/2023

የ ምች በሽታ ምንድን ነው?

Photos from Tirita Home-Healthcare and Ambulance Service P.L.C's post 05/02/2023

ትኩረት የማጣት እና የመረጋጋት ችግር (Attention Deficit hyperactivity Disorder)-ADHD
~
> ADHD ልጆች ላይ ሊከሰት የሚችል የእድገት እክል ነው።
> አንዳንድ ወላጆች ልጆቻቸውን ከሌሎች በተለየ ትዕግስት የለሽ፣ ቀዥቃዣና አስቸጋሪ ሆነውባቸው መፍትሔ ሲፈልጉ ይታያሉ፡፡ እነዚህ ህፃናት የሚይዙት የሚጨብጡት የሚጠፋባቸው፣ አንድ ነገር ጀምረው አፍታም ሳይቆዩ ሌላ የሚያምራቸው፣ ለመናገርና ለመጠበቅ ትዕግስት የማይኖራቸውና ችኩል ናቸው፡፡
ይህ አይነት የስነባህሪና የስነአእምሮ ችግር ያለባቸው ህፃናት ትኩረት ያጡ፣ ትዕግስት የለሽ ቀዥቃዣነት (ADHD) ህመም ተጠቂዎች ናቸው፡፡

የእነዚህ ህፃናት መሰረታዊ መገለጫዎች
አንድ ነገር ጀምረው በቀላሉ ወደ ሌላ የሚሳቡና አንድን ነገር ጀምሮ
ለመጨረስ ትኩረት የሌላቸው
በትምህርት ቤት ግዴለሽነት የሚታይባቸውና ቀላል ስህተቶችን በፈተና ላይ በተደጋጋሚ የሚሰሩ
የማያዳምጡና የተባሉትን የማያደርጉ
የክፍልና የቤት ስራን ጀምሮ ለመጨረስ እንኳን ትዕግስት የሌላቸው
በተሰጣቸው ስራ ላይ ሀሳባቸውን መሰብሰብ የማይችሉ
ዝንጉነት በእጅጉ የሚታይባቸው
በየአቅጣጫው የሚሮጡና እረፍት የሌላቸው፣ ዛፍም ሆነ ደረጃ ላይ
ላይ ለመውጣት የሚታገሉ
እጅና እግራቸው የሚቅበጠበጥና አደብ የሌላቸው
ከጓደኞቻቸው ጋር እየተጫወቱ ተራቸው አስኪደርስ መጠበቅ ሞት
የሚመስላቸው
በቀላሉ የሚበሳጩና የሚናደዱ ናቸው፡፡

ስለዚህም ይህ ትኩረት የለሽነታቸውና ትዕግስት አልባነታቸው የትምህርት አቀባበልና አረዳዳቸውን በእጅጉ ይጎዳዋል ።

የADHD መምጫ ምክንያት

> ለዚህ ህመም እንዲህ ነው የሚባል ምክንያት ባይኖርም በእርግዝና ጊዜ አልኮልና ሲጋራ መጠቀም እንደ አጋላጭነት ይጠቀሳሉ፡፡ ዓለም አቀፍ ጥናት እንደሚያሳየው ከሆነ ለትምህርት ከደረሱ ህፃናት መካከል ከ5-10 በመቶ የሚሆኑት ህፃናት ይህ ችግር ሊታይባቸው ይችላል፡፡

ህክምናው
> አብዛኛው ትኩረት የለሽ ህፃናት በስነ ልቦና ህክምና፣ በአማራጭ ትምህርት(Special Education) እና በመድሀኒቶች በመታገዝ የሚስተካከሉና መሻሻል ሊያሳዩ ይችላሉ፡፡ ሆኖም አንዳንዶች የጎላ ችግር ያለባቸው ካደጉ በኋላም ራስን ዝቅ ማድረግና ከማህበራዊ ግንኙነቶች ማፈግፈግ ሊታይባቸው ይችላል፡፡
> ወላጆች እንዲህ አይነት ባህሪ ያላቸውን ህፃናት በአግባቡ በማሳከምና በቤት ውስጥ ድጋፍና አንክብካቤ በማድረግ ችግራቸውንና የትምህርት አቀባበላቸውን ቀስ በቀስ ማስተካከል ይችላሉ፡፡ ለበለጠ መረጃ Website: tiritahome.com
Telegram: https://t.me/tiritahome
Twitter:
Instagram: tiritahome
Phone No.: 0965500000/0902200002

02/02/2023

ስለ የደም ግፊት እንረዳ ።

Photos from Tirita Home-Healthcare and Ambulance Service P.L.C's post 31/01/2023

የምች በሽታ

የምች በሽታ ምንድን ነው?

ምች (cold sore) በተለምዶ ከሚከሰቱ የቆዳ ኢንፌክሽኖች መካከል ዋነኛው ሲሆን በተለይም የላይኛው ወይም የታችኛው የከንፈር ጠርዝ ከፊታችን ቆዳ ጋር በሚገናኝበት አካባቢ ላይ በሚወጡ ውሃ የቋጠሩ ጥቃቅን ቁስለቶች ይታወቃል።

☑️ ከምች በሽታ በሰተጀርባ ምን አለ?

በተለምዶ የምች በሽታ የምንለው (Cold sores) የሚከሰተው የኸርፒስ (Herpes) ቫይረስ 1 በሚባሉ በሽታ አምጭ ተዋህስያን ነው። የኸርፒስ (Herpes) ቫይረስ ቤተሰቦች በቫይሮሎጂ የትምህርት ዘርፍ በስፋት ከተጠኑ የቫይረስ ቤተሰቦች መካከል አንዱ ነው።

በውስጡም ከ100 በላይ የቫይረስ ዝርያዎች ሲኖሩ 8ቱ በሰዉ ልጅ ላይ በሽታ ያስከትላሉ። ከነዚህም መካከል የምች አምጪ ተህዋስያን ኤች.ኤስ.ቪ- 1 ይገኙበታል።

የኸርፒስ (Herpes) ቫይረስ ቤተሰቦች ቆዳን ጨምሮ በኣይን፣በመራብያ አካላት እንዲሁም የተለያዩ የሰዉነት ክፍሎች ኢንፌክሽኖች ያስከስታሉ። ግዙፉ የምርምር መረጃ ቋት ፕብ ሜድ በገጹ እንዳሰፈረዉ በአለም ላይ ከ90% በላይ በአዋቂ እድሜ ላይ ያሉ ጝለሰቦች በአንድ ወይም ከአንድ በላይ የኸርፒስ ቫይረስ ተለክፈዉ ይገኛሉ።

የምች አምጪ ተህዋስያን ኤች.ኤስ.ቪ- 1 (HSV-1) እንዲሁም ኤች.ኤስ.ቪ -2 (HSV2) ከጨቅላ ህጽፃናት እስከ የእድሜ ባለፅጋ የእድሜ ክልል ኢንፌክሽን መፍጠር የሚችሉ ሲሆን ኤች.ኤስ.ቪ- 1 (HSV-1) በምች አምጪ ባህሪዉ ይታወቃል።

ኤች.ኤስ.ቪ -1 (HSV-1) ከሰዉ ወደሰዉ በቆዳ-ቆዳ እና በቆዳ-የሚውከስ ሽፋን (የአፍ ዉስጥ ለስላሳ ሸፍን መሰል) ንክኪ የሚተላለፍ ሲሆን ኤች.ኤስ.ቪ -2 (HSV-2) ደግሞ በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት እንዲሁም ከመራቢያ አካላት-ፊት በሚደረግ ንክኪ ይተላለፋል።

የኸርፒስ (Herpes) ቫይረስ ዝርያዎች በነጭ የደም ሴሎቻችን ተጠቅተዉ ከሰዉታችን ሙሉ በሙሉ በመወገድ ፈንታ በሰዉነታችን የነርቭ አካላት ዉስጥ በመሸሸግ የሰዉነታችን ዉስጣዊ ሁኔታዎች ምቹ እስኪሆኑ በመጠባበቅ ከተሽሽጉበት በመዉጣት በድጋሜ የምቸ በሽታን ያስከትላሉ።

☑️ የምች በሽታ ምልክቶች ምንድን ናቸዉ

የምች በሽታ ተህዋስያን ለመጀመርያ ጊዜ በሰዉነታችን ኢንፌክሽን ስያስከስቱ በአብዛኛዉ ምንም ምልክት አይኖራቸዉም ነገር ግን በሚከተሉት ጊዜያት ሲከሰቱ የሚከተሉትን የመሳሰሉ ምልክቶች ሊያሳዩ ዪችላሉ።

የላይኛዉን ወይም የታችኛዉን የከንፈር ጠርዝ በ ቀኝ ወይም ግራ በበኩል ከፊት ቆዳ ጋ የሚያገናኘዉ ቦታ አካባቢ የመለብለብ፣የማሳከክ ወይም ጨምድዶ የመያዝ ስሜት ሊሰማዎት ይችላል። ከዚህም ከ 24 ሰአታት በኋላ ከስራቸው ቀልተዉ ዉሃ የቋጥሩ ጥቃቅን የቁስለቶች ስብስብ ይፈጠራል።

በምች የሚመጡ ቁስለቶች ከተፈጠሩበኋላ በቀላሉ በመፈንዳት ፈሳሽ ሊያፈልቁ ይችላሉ ከዛም ወድያዉ በመድረቅ በቅርፊት ይሸፈናሉ።

ከላይ ከተጠቀሱት ምልክቶች በተጟዳኘ የራስ ምታት፣ ትኩሳት፣ የድካም ስሜት እንዲሁም በአንገት ወይም በብብት ውስጥ የሚገኙ ሊምፍ ኖድ የሚባሉ እጢዎች እብጠት ሊያስከትል ይችላል። ቁስለቶቹም በተለምዶከ2-4 ሳምንታት ጊዜ ውስጥ ያለ ጠባሳ ይድናሉ።

🗣 የህመም ማስታገሻ

በምች በሽታ ሚመጡን ቁስለቶች በተያያዘ የሚሰማዎትን ህመም ለመቀነስ ያለ ሃኪም ትዛዝ በፋርማሲ የምናገኛችውን አይቡፐሮፈን (Ibuprofen) እና አሴታሚኖፈን (Paracetamol) በፋርማሲ ባለሙያው ትዕዛዝ መሰረት መጠቀም። ለበለጠ መረጃ Website: tiritahome.com
Telegram: https://t.me/tiritahome
Twitter:
Instagram: tiritahome
Phone No.: 0965500000/0902200002

Photos from Tirita Home-Healthcare and Ambulance Service P.L.C's post 25/01/2023

አስም (የመተንፈሻ አካል ህመም )

አስም ለረጅም ጊዜ የሚቆይ የመንፈሻ አካል ህመም ሲሆን በማቁሰል ፣በማሳበጥና በማጥበብ ለመተንፈስ አሰቻጋሪ አስቸጋሪ ያደርጋል ።
አስም ተላላፊ ካልሆኑ በሽታዎች አነዱ ሲሆን እንደ የአለም ጤና ድርጅት ግምት በፈረንጆቹ አቆጣጠር 2016 አመተ ምህረት 339 ሚሊየን ሰዎች የአስም ህመም ተጠቂዎች ሲኖሩ 417,918 ሰዎች ደግሞ በዚህ ህመም ህይወታቸውን አጥተዋል ።

የአስም ምልክቶች
የአስም ምልክቶች በአሰም በሽታ ከሚከሰቱ ሶስት የአየር ቱቦ ሂደቶች ምክንያት የሚመጡ ናቸው
1.የአየር መመላለሻ ቱቦዎች መጥበብ ፦ በአስም ያልተጠቃ ሰው በአየር ቱቦ ዙሪያ ያሉ ጡንቻዎች ላላ ያሉና የአየር ዝውውር በቀላሉ ይካሄዳል ነገር ግን አስም በሚኖርበት ጊዜ እነዚህ ጡንቻዎች ይጠብቁና የአየር ቱቦዎችን እንዲጠቡ በማድረግ የአየር ዝውውሩን ከባድ ያደርጉታል ።
2.የአየር ቱቦዎች ቁስለት ፦በሌላ በኩል አስም የአየር ቱቦዎችን እብጠት፣ቁስለትና ቁጣን በማስከተል ሳንባን ይጎዳል ።
ይህን ማከምም በረጅም ጊዜ አስምን ለመቆጣጠር ይረዳል።
3.የአየር ቱቦ ቁጣ፦ ሌላው ምክንያት የአስም ተጠቂ የሆኑ ሰዎች የአየር ቱቦ በጣም ቁጡና ቀላል እና አነስተኛ ለሆኑ የአስም ህመም ቀስቃሾች የሚቆጣና ከተገቢው በላይ የሆነ መልስ ይሰጣል ።

በእነዚህ ምክንያቶች የተነሳ የሚከተሉት ምልክቶች ይታያሉ፦
•ሳል፦በተለይም ጧትና ማታ ላይ የሚጨምር
•በሚተነፍሱበት ጊዜ ከሳንባ የሚነሳ በተለይም አንገት አካባቢ የፉጨት ድምፅ መስማት
•ለመተንፈስ መቸገር
•ደረት አካባቢ ጥብቅ አድረጎ መያዝ ፣የደረት ህመም
•ቶሎ ቶሎ መተንፈስ
•በትንፋሽ ማጠር ምክንያት ለመተኛት መቸገር
ህክምና
የአስም ህክምና የታካሚውን ሙሉ ተሳትፎ የሚጠይቅ ስለሆነ ከሀኪምወ ጋር በመሆን የህመሙን የመቆጣጠር እቅድ ያውጡ።

1.አስምንን የሚቀሰቅሱ/የሚያስነሱ ነገሮችን ማስወገድ (Avoidance Measures )
•ከድመት፣ከውሻ ጋር ያለውን ንክኪ ያስወግዱ
•አያጭሱ፣ከሚያጨስ ሰው ይራቁ
•የአበባ ብናኝ ፣የቤት ቆሻሻ ብናኝ ያስወግዱ
•ሳኒታይዘር ፣ ሽቶ ያስወግዱ
•ክብደትን መቆጣጠር
•እንቅስቃሴ አዘውትሮ መስራት ለበለጠ መረጃWebsite: tiritahome.com
Telegram: https://t.me/tiritahome
Twitter:
Instagram: tiritahome
Phone No.: 0965500000/0902200002

23/01/2023

የቪያግራ ለምን ? ጥቅም እና ጉዳቱስ ?

Want your business to be the top-listed Health & Beauty Business in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Videos (show all)

እንኳን ለአዲሱ አመት በሰላም አደረሳችሁ ። አዲሱ አመት የሰላም ፣የፍቅር እና የመተሳሰብ እንዲሆን ድርጅታችን ይመኛል።
ነጻ የምክር አገልግሎት በ ቲክቶክ ላይቭ ዘወትር ማክሰኞ እና አርብ ምሽት ከ 3-4 ስዓት
happy eid
የፊንጢጣ ኪንታሮት
Hemorrhoids
ፅንስ ማስወረድ #Ethiopia #health #AddisAbeba
የእርግዝና መከላከያ #health #ethiopianfood #AddisAbeba #tiritahome
ስለ እርግዝና መከላከያ ማወቅ ያሉብን ነገሮች
የአፍንጫ አስም/allergic rhinitis/
HIV virus
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች መልካም የረመዳን ጊዜ እንዲሆንላችሁ ትርታ ሆም ኬር ይመኛል።Happy Ramadan 🌙🌙🌙
ስለ የደም ማነስ መረዳት ያሉብን ነገሮች ።

Telephone

Address


Megenagna, Bethlehem Plaza, 5th Floor, Office Number 503
Addis Ababa
Other Addis Ababa health & beauty businesses (show all)
Efoy Physiotherapy Specialty Clinic Efoy Physiotherapy Specialty Clinic
Togo Street
Addis Ababa

Strictly professional clinic with high quality physiotherapeutic and medical rehabilitatiotion servic

Berhan Yehun Project , Ethiopia Berhan Yehun Project , Ethiopia
Addis Ababa

Our vision is to see a community where no child is left behind for lack of nutrition, health care, an

Dagi's Day Spa Dagi's Day Spa
1/Atlas Branch, Yoly Hotel 3rd Floor, 2/Imperial Branch , Alfoz Plaza 1st Floor
Addis Ababa

No 1 Day Spa in Addis Ababa. Located @Yoly Hotel 3rd Floor around Bole Atlas and 2nd branch is located at Alfoz Plaza 1st floor. Dagi's is open 24/7

Ethiopian Cumin Seed Oil / Nigella Sativa Ethiopian Cumin Seed Oil / Nigella Sativa
Bole
Addis Ababa, 00251

We're producers and suppliers of pure Black cumin seed oil ( Nigella Sativa) based in Ethiopia. We've been supplying our products to the world especially Middle East and Europe.

Janmeda Health Center Janmeda Health Center
Addis Ababa

Janmeda primary Health Care Unit

DXN_addis Amanuel DXN_addis Amanuel
Addis Ababa

Holistic Medicine and Supplementary Products Selling Platform.....All Herbal&Organic Products

DR Mitiku Medium Clinic DR Mitiku Medium Clinic
Amfo Square
Addis Ababa

our patients are our family

South Sudanese future pharmacists South Sudanese future pharmacists
Addis
Addis Ababa, 2023

Our major aim is to brightening the future of upcoming generations.

Tesfa  home care nursing Tesfa home care nursing
Bole
Addis Ababa, 1000

Our company provides ultimately medical care with mobility and with senior nursing abilities from minor to severe cases with a reasonable price.

Shalom Medical Consultancy Shalom Medical Consultancy
Swazeeland Street
Addis Ababa, 1271

This page is created to promote helath realted issues and provide medical consultation for pateints

Ethiopian anesthetists voice Ethiopian anesthetists voice
Addis Ababa

Here we are for better Health care