ትንሣኤ ለኢትጵያ

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ትንሣኤ ለኢትጵያ, Government Organization, Awassa.

19/08/2023

የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ለደቡብ ኢትዮጵያና ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ይፋዊ የክልል አደረጃጀትን አስመልክቶ የሰጡት መግለጫ እና የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት

ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ በመልዕክታቸው የሲዳማ ህዝብ ከጥንት ጀምሮ ከአጎራባች ወንድምና እህቶቹ ጋር በመልካም ግንኙነት የሚኖር ህዝብ ነው ብለዋል።

ሌሎቹም እንዲሁ እርስ በርስ በመልካም ጉርብትና ይኖራሉ። ግጭትና መገፋፋት በደቡባዊ ሀገሪቷ ክፍል በሚኖሩ ህዝቦች ዘንድ የተለመዱ ድርጊቶች አይደሉም። ዘመናትን ባስቆጠረ መልካም ግንኙነት እነዚህ ህዝቦች ክልል መስርተው ለሦስት አስርት ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ በጋራ የኖሩም ናቸው በማለት ተናግረዋል።

በእነዚህ ዓመታት ቀደም ቢሎ የነበረው ግንኙነት የበለጠ ተጠናክሯል የትውውቅ ዕድል ሰፍቷል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ የወንድማማችነት የጋራ ስነልቦናም ተፈጥሯል ብለን እናምናለን በማለት እና በመግለፅ ነው።

እነዚህ የማይበጠሱ የአብሮነታችን እሴቶች እንዳሉ ሆነው ለህዝባችን ልማት መፋጠንና በቅርበት አገልግሎት ለመስጠት የህዝቡን ፍላጎት መነሻ በማድረግ በተሠራ አዳዲስ ክልሎች የማዋቀሩ ሥራ ያለምንም ችግር ክልሎቹ በተሳካ ሁኔታ በመመስረቱ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንገሥት እንኳን ደስ አላችሁ ይላል ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው።

የተከበሩ አቶ ጥላሁን ከበደ እና የተከበሩ አቶ እንደሻው ጣሰው አዳዲሶቹን ክልሎች ለመምራት በፈጣሪና በህዝቡ ይሁንታ አግኝታችሁ ርዕሰ መስተዳድር ሆናችሁ በመሾማችሁ ደስ ብሎናል። እንኳን ደስ አላችሁ እያልኩኝ የስልጣን ዘመናችሁ ለህዝባችሁ የብልጽግና ለእናንተ የስኬት እንድሆንላችሁ እመኝላችኋለሁም ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ።

ከዚህ ቦኃላ ከአዳድሶቹ ክልሎች ጋር እጅ ለእጅ ተያይዘን በመሥራት የህዝቦቻችን አንድነት አጠናክረን ለማስቀጠልና የክልል ወሰን ሳይገድበን የጋራ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ዝግጁ መሆናችንን በዚህ አጋጣሚ መግለጽ እወዳለሁ በማለትም ኢትዮጵያዊ ወንድማማችነታቸውን አስረድተዋል።

11/08/2023
Photos from Ethiopian Cities Association's post 28/07/2023
Photos from ትንሣኤ ለኢትጵያ's post 27/07/2023

የጠቅላይ ሚንስተር አብይ አህመድ ዶ/ር ሐምሌ 6 ቀን 2015ዓ.ም በግብጽ ያደረጉትን ጉብኝት መነሻ በማድረግ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ኋላፊ ክብርት ወ/ሮ አለምጸሀይ በተመራዉ የፌዴራል ከፍተኛ የስራ ኋላፊዎችና ከተመረጡ ከንቲባዎች ጋር በመሆን በጎሮቤት ሀገር በግብጽ የስራ ጉብኝት አድርገናል።

በጉብኝቱ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣ የጠቅላይ ሚኒስተሩ የማህበራዊ ጉዳይ አማካሪ ሚኒስትር ዳንኤል ክብረት(ዲ)፣ የባህርዳር ከተማ ከንቲባ ክቡር ድረስ ሳህሉ(ዶ/ር)፣ የአዳማ ከተማ ከንቲባ አቶ ሀይሉ ጃልዴና ሌሎችም የስራ ኋላፊዎች የታደሙበት ሲሆን በግብጽ ካይሮ ከተማ አቅራቢያ የተገነባዉ አዲሱ የካይሮ ከተማ(NAC/ New Administrative Capital) መጎብኘታችን ለሀገራችን ከተሞች ተጨባጭ የሆኑ ልምዶችን እንድንወስድ የሚያስችለን ነዉ።

በልምድ ልዉዉጡ ያገኘናቸዉ አዳዲስ ሀሳቦች፣ ተሞክሮዎችና፣ ከግብጽ ከጥንታዊ የኪነ-ህንጻ ጥበብ የተቀዱ ዘመን ተሻጋሪ ስራዎችን ለመጪዉ ትዉልድ በማሰብ የተሰሩ በመሆኑ እኛም ካገኘነዉ እዉቀት በመነሳት አልህቀንና አተልቀን የኢትዮጲያን ከተሞች ለአለም ምሳሌ ማድረግ በሚያስችል መልኩ እንድንሰራ የተሻለ እዉቀት የቀሰምንበት ነዉ ማለት እንችላለን።

ይህን እድል ያመቻቸልንን የጠቅላይ ሚኒስተር ጽ/ቤትን በራሴና በከተማ አስተዳደራችን ስም ከልብ የመነጨ ምስጋናዬንና አድናቆቴን ላቀርብ እወዳለሁ።

ቀጣዩ ዘመን ለኢትዮጲያና ለህዝቦቿ ብሩህ ነዉ!

Photos from Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)'s post 26/07/2023
Photos from Tsegaye Tuke Kia- ፀጋዬ ቱኬ ክአ's post 26/07/2023
Photos from ትንሣኤ ለኢትጵያ's post 25/07/2023

የሲዳማ መግቢያ በሩ የሐዋሳ ከተማ ነው ስንል በምክንያት ነው!!!

ከተሞች የራሳቸው መገለጫ (City Branding) አላቸው። ይህ ደግሞ በቀላሉ በሁሉም አዕምሮ ውስጥ ቦታ እንዲኖረው እና አይረሴ ትውስታን እንዲጭሩ እድል የሚፈጥርላቸው ትልቅ አቅም ይሆናል ተብሎ ይታሰባል።

አንዳዶች ታዲያ ይህን እድል ተጠቅመው በመስራት በርግጥም አትርፈዋል ሳይሆን ከተማቸውን ለብዙሀኑ መሸጥ ችለዋል።

ይህ ነው እይግዲህ (City Marketing ) የከተማ ግብይት ተብሎ ከማጠቀሰው ውስጥ አንዱ ሆኖ የሚቀመጠው።

ለዚህም በዚህ መግቢያ የሚያልፍ ሁሉ ዳዎቡሹን ይረዳል። ሲዳማነት የልብ ኢትዮጵያዊ ማንነት ስለመሆኑ ያውቃል። ማወቅም ብቻ አይደለም ቤታችሁ ቤቴ ነው በሚል እሳቤ ያለውን ከማካፈል ባለፈ ሰጥቶ ያኖራልን ያስተውላል።

በዚህ ረገድ ከተማችን ሐዋሳ ብዙ እራሷን መቀጥ የሚያስችላትን አቅም ፈጥራ በብዙ መልኩ ጥረት ከድርጋለች። ከዚህ አንፃር ማንም ሐዋሳን ሲመለከት በተለይም ከየትኛውም አቅጣጫ ወደ ከተማዋ የሚገባን ጎብኚም ይሁን ለሌላ አላማ የሚመጣ እንግዳን በልዩነት ማሰብ እንዲችል በመግቢያ በሯ በኩል ያሰናዳችው እና በጥናት ላይ የተመረኮው gateway አንዱ ነው።

በዚህ መግቢያ ታዲያ ሐዋሳና የሲዳማ ትሩፋተ ሀብት መሆኗን ብሎም ማንም ወደ ከተማዋ ሲገባ ቀድሞ አዕምሮው ዘንድ የሚደርስ መልዕክት ከማስተላለፈ አንፃር ጉልህ ሚና አለው።

እንግዶች በዚህ መግቢያ (gateway) ሲያልፍ አሊያም ሲደርሱ የሲዳማን ባህል እና ትሩፋቱን ይረዳሉ፣ የሰላም ተምሳሌትነቷን ያውቋሉ፣ በሻፌታ አብሮነትን ያውቃሉ እንዲሁም እንግዳን 'ዳዎቡሹ ብለው መቀበልን ያውቁበት ዘንድ ባህላዊ ትውፊቱን ይረዳሉ።

ከዚህ ባለፈም በዚህ ፕሮጄክት ሐዋሳ የተለየ አንድ እንግዳ ተቀባይ ህዝብ በፍፁም ኢትዮጵያዊ ማንነት እየተቀበላቸው እንደሆነ ያውቃሉ።

ይህም ብቻ አይደለም በዚህ መግቢያ (gateway) እንግዶች አረፍ ብለው ስለ ሲዳማ ባህል እውቀቱ ኖሯቸው ህዝባቸውን ለመጎብኘት የእረፍት ጊዜ የሚወስዱበትም ጭምር ሆኖ ነው የተዘጋጀው።

በዚህ ስፍራ ባህላዊ ምግቦቻችን ይተዋወቃሉ። ሰላማዊነት ክብር ሆኖ በሲዳማ ባህል ይደምቃል። ጎብኚ ነገን ናፍቆ ይመጣ ዘንድ በልዩነት ውስጥ ሐዋሳን ያስባል። ከዚህ ባለፈም ለበርካቶች የስራ እድል እስከመፍጠር ድረስ ማህበራት ከበቂ የከተማቸው ግንዛቤ ጋር ይገናኛሉ።

ይህ ሲሆን ሐዋሳን ለሲዳማ፣ ሰዳማን በሐዋሳ ውስጥ አጥርቶ ማሳየት ያስቻለ አቅም ይፈጥራል። ነጋሪ ሳያሻው ጎብኚ ጠያቂ ይሆናል። በመጠየቅ ውስጥ ደግሞ ሐዋሳን ከመግቢያው ይረዳል።

እኛም እንላለን በሐዋሳ መግቢያ ከተማችን ማናትን ታውቁ ዘንድ እነሆ ብለናል በማለት።

ኑ! ወደ ሐዋሳ! ከመግቢያችን ጀምሮ ህዝብ ኢትዮጵያዊ ስነምግባርን ተላብሶ የፍቅር ከተማነቷን ያሳያችኋል ።

Photos from ትንሣኤ ለኢትጵያ's post 22/07/2023

Ayiino qase uge
Diafaahe tuge
Goxannolla muge
Mataateewa xiixay
Heeraalla yammuuge
Buxanete anna
Latishshu janna
Heerattolla ati
Gibaaheri la'anna
Albikki ba'anna

Pr Tsegish Tuke

(Tarku Toshe)

Photos from ትንሣኤ ለኢትጵያ's post 19/07/2023

በአንጋፋዉ የሐዋሣ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ከመጀመርያ እስከ ሶስተኛ ድግሪ ሰልጥናችሁ በነገዉ ዕለት የምትመረቁ ዕጩ ምሩቃን በሙሉ እንኳን ደስ ያላችሁ ለማለት እወዳለሁ !!

በዩንቨርስቲዉ በነበራችሁ የትምህርት ቆይታ በእዉቀት፣ በክህሎትና በአመለካከት ከመታነጽ ባለፈ ለቀጣይ ሀገራችንንና ህዝባችንን በምታገለግሉበት መልካም ስብዕና፣ በጥሩ ማህበራዊ መስተጋብርና በህይወት ዉጣ ዉረድ ተፈትናችሁ ያለፋችሁ በመሆኑ ለቀጣይ ህይወታችሁ ስምረት በግቢ ቆይታችሁ የተሻለ ነገር ያገኛችሁበት እንደሆነ አልጠራጠርም።

ዉድ ተመራቂዎች የኢትዮጲያ የብልጽግናዋ መጻኢ-ተስፋ በእናንተ እጅ በመሆኑ በምትሔዱበት ሁሉ የሀገራችሁን እድገትና ብልጽግና ከዳር ለማድረስ በአዳዲስ ሀሳብ፣ በቴክኖሎጂና በፈጠራ በመታገዝ ለህዝባችሁ የለዉጥ ሀዋርያ እንደምትሆኑ እምነቴ የጸና ነዉ።

እናንተ ያበቃ ይህ ታላቅ ተቋም ከዚህ በኋላ ያለዉ ጊዜም የምርምርና የልህቀት ማዕከል እንደመሆን የናንተን ፈለግ የሚከተሉ ዜጎችን የሚያፈራ እንደመሆኑ በመልካም ምሳሌ የምትጠቀሱ አልሙነስ(Alumnus) እንደምትሆኑ አምናለሁ።

በመጨረሻም በዩኒቨርሲቲ የነበራችሁ ቆይታ በክፍልና በተግባር ከቀሰማችሁት እዉቀት ባልተናነስ ከከተማችን ማህበረሰብ የሸመታችሁት የእንግዳ ተቀባይነት፣ አብሮ የመኖር፣ የመተሳሰብና የመደጋገፍ እሴታችንን በምትሔዱበት ሁሉ በመመስከር ብሎም የከተማችሁ ዉበትና ማራኪነት በማስተዋወቅ የሐዋሳ እዉነተኛ አንባሳደሮች እንደምትሆኑ በመተማመን፤ ቀሪ ዘመናችሁ የፍሰሃና የተድላ እንዲሆን በራሴና በከተማ አስተዳደር ስም መልካም ምኞቴን ለመግለጽ እወዳለሁ።
ከንቲባ ፀጋዬ ቱኬ (ረ/ፕ)

Photos from ትንሣኤ ለኢትጵያ's post 17/07/2023
Photos from ትንሣኤ ለኢትጵያ's post 14/07/2023

የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ የተመራ ድጋፍ ሰጪ ቡድን በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር በመገኘት ከከተማው ከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይትና የመስክ ምልከታ እያካሄዱ ይገኛሉ።

ውይይቱና የመስክ ምልከታው በከተማው በክረምት ወራት በሚተገበሩ በተመረጡ የትኩረት መስኮች ላይ መሠረት የሚያደርግ ነው ።

Photos from ትንሣኤ ለኢትጵያ's post 14/07/2023

ዛሬ ከተማችን ሐዋሳ ከፖርቹጋሏ መቶዚኒዮስ (Matosinhos) ከተማ ጋር የእህትማማቾች ስምምነት ተፈራርማለች!

በስምምነታችንም ከተማችን ሐዋሳንና የፖርቹጋሏ መቶዚኒሆስ ከተማ የእህትማማች ከተማ እንዲሆኑ ስምምነት ተፈራርመናል።

መቶዚኒዮስ የፖርቹጋል ስሜናዊ ግዛት ዉስጥ የምትገኝ በባህር ዳርቻ የተከተመች ውብ፣ ምቹ የቱሪዝምና የኢንቨትመንት መዳረሻ መሆኗን ብዙዎች ይመሰክሩላታል።

ከተማዋ ከሐዋሳችን ጋር የሚያመሳስላት በርካታ ተፈጥርዊና ሰው ሰራሽ የሆኑ ጸጋዎች አሏት።

በሁለቱ ከተሞች መካከል ልምድ ለመለዋጥ፣ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት፣ በድጋፍና በትብብር ለመስራት፣ የቴክኖሎጂ፣ የእዉቀትና የክህሎት ሽግግር ለማድረግ ትልቅ እድል ያለውም ነዉ።

ሐዋሳም ያላትን ተፈጥሮአዊ ጸጋና ባህላዊ ትሁፊቷን ለአውሮፖዊያን እንድታስተዋዉቅና ብሎም የውጪ ኢንቨስትመንትን እንድትስብ ትልቅ አቅም ይፈጥርላታል።

የከተማዋ ከንቲባ ከርሎስ ማውታ(ደ/ር ) (Dr.Carlos Mouta) በኢትዮጵያ የፖርቹጋል አንባሳደር ሉእሴ ፍራንጎሶ (Luisa Fragoso) ሌሎች የስራ ኃላፊዎች በእህትማማችነት ስምምነቱ ወቅት የተገኙ ሲሆን ለሁሉም ለነበራቸዉ ሚና በራሴና በከተማ አስተዳደራችን ስም ምስጋናዬን ላቀርብ እወዳለሁ!!

Photos from ትንሣኤ ለኢትጵያ's post 10/07/2023

ዛሬ ከኢዱሱቱሪ ፓርኮች ኮርፖሬሽን ስራ አስፈጻሚዎች፣ የድሬደዋ ከንቲባና ከሌሎች የስራኋላፊዎች ጋር በመሆን አዉሮፖዊቷ ሀገር ፖርቹጋል- ሊዝበን ላይ በሚካሔደዉ የኢንቬስመንት ፕሮሞሽን፤ የከተማና ኢንዱስቱሪ ትስስር መድረክ ላይ ተሳትፈናል።

መድረኩ በኢንዱስቱሪ ፖርኮችና በከተሞች መካከል የተሻለ ትስስር በመፍጠር ለከተሞችና ለነዋሪዎች የተሻለ ተጠቃሚነት በመፍጠር ዙርያ ላይ የታሻለ ልምድና ተሞክሮና ልምድ ለመገራት ያለመ ሲሆን፤ ከተማችን ሐዋሳ፣ ብሎም ሌሎች የኢዱስቱሪ ፖርኮች በአቅራቢያቸዉ የሚገኙ ከተሞች የተሻለ የኢንቬስትመንት አማራጮቻቸዉን እንዲያሰፉና ያሉንን ምቹ ሁኔታዎችን በማስተዋወቅ የዉጪ ባለሀብቶችን መሳብ እንድንችል የተሻለ መደላድል የሚፈጥርልን ነዉ። በዚህ ረገድ ከተማችንም የተሻለ ተጠቃሚ እንድትሆን የተሻሉ እዉቀቶችንንና ነዋሪዎቻችንን ተጠቃሚ ያሚያደርጉ አዳዲስ ልምዶችን ያገኘንበት ነዉ።

Photos from ትንሣኤ ለኢትጵያ's post 07/07/2023

#ሀዋሳ
የለውጥና ብልጽግና ማሳያ፣ የሠላም እና የፍሠሀ ተምሳሌት ከተማ

Photos from ትንሣኤ ለኢትጵያ's post 07/07/2023

Hawassa City new projects

Photos from ትንሣኤ ለኢትጵያ's post 04/07/2023

የሐዋሳ የመበልጸግና የማማር ምክንያቶች እናንተ ናችሁ። ድካማችሁ ሁሌም በስኬትና በዉጤት ስለታጀበ በጋራ ያቀድናቸዉ ወደ ስራም የገባንባቸዉ ስራዎች በዛሬ እለት በስኬት ተጠናቀዉ ለምረቃ ስለበቁ ክብር ይገባችኋል። ነገም የስራ ፤የስኬትም ቀን ነዉና በመፍጠርና በመፍጠን ለከተማችን እድገትና ብልጽግና የድርሻችንን እንዋጣ!

Photos from ትንሣኤ ለኢትጵያ's post 03/06/2023

ዛሬ በከተማችን የህክምና ቁሳቁስ ማምረቻ ፋብሪካ ለመገንባት በክቡር ኘሬዘዳንታችን አቶ ደስታ ሌዳሞ የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧል።

ፋብሪካዉ በሻሎም ሔልዝ ኬር ሶሉሸን ኩባንያ መስራችና ኘሬዘዳንት ዶ/ር ዊንታ መሐሪ የሚገነባ ሲሆን ይህ ግዙፍ ኢንቬስትመንት በከተማችን መገንባት ሀገራችን የህክምና ቁሳቁስ ለማስገባት የምታወጣዉን የዉጪ ምንዛሪ ከማስቀረቱ ባሻገር ሐዋሳን የሜዲካል ቱሪዝም ሁነኛ መዳረሻ ለማድረግ ላስቀመጥነዉ ግብ ምቹ መደላድል ይፈጥርልናል።

ፋብሪካዉ ከግንባታ ሒደት ጀምሮ ለበርካታ ዜጎቻችን ቋሚና ግዜያዊ የስራ እድል እንደሚፈጥርም እምነቴ የጸና ነዉ።
የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ረ/ፕ ፀጋዬ ቱኬ

Photos from ትንሣኤ ለኢትጵያ's post 01/05/2023

የኢትዮጲያ አርተፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ለከተማችን ለደህንነት አገልግሎት የሚዉሉ ግምታቸዉ ከ20 ሚልዮን ብር በላይ የሚሆኑ ዘመናዊ ካሜራዎችንና ተዛመጅነት ያላቸዉ ቁሳቁሶችን ለከተማችን ድጋፍ አድርገዉልናል።

ኢንስቲትዩት በሀገራችን ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በማስተዋወቅና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ላይ የፈጠራ ስራዎች እንዲስፋፉ እየተጫወተ ከሚገኘዉ ሚና ባሻገር መሰል ድጋፎችን ለከተማችን ማድረጉ ስማርት ሀዋሳን ለመገንባት በምናደርገዉ ጥረት ውስጥ ትልቅ አቅም የሚፈጥርልን በመሆኑ የኢንስቲትዩቱን ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ኢንጅነር) እና የስራ ሀላፊዎችን በራሴና በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ስም እጅግ ላመሰግን ወዳለሁ::

ከድጋፉ ባሻገር ኢንስቲትዩቱ ጋር በቀጣይ ስማርት ሀዋሳን ለመገንባት በምናደርገዉ ጥረት ውስጥ በስዉ ሃይል ግንባታ፣ በቴክኖሎጂና በእዉቀት ሽግግር ላይ በርካታ ስራዎች ለመስራት የሚያስችለንን የመግባቢያ ስምምነቶችን ተፈራርመናል።

20/04/2023

እንኳን ለ1444ኛው የኢድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም በጤና አደረሳችሁ! በዓሉ የፍቅር፣ የአብሮነትና የመተሳሰብ እንዲሆንላችሁ ከልብ እመኛለሁ!

ኢድ ሙባረክ!

Photos from Abiy Ahmed Ali's post 20/04/2023
20/04/2023

የኢስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለዒድ አልፈጥር በአል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ።

አንድ ተብሎ የተጀመረው ቅዱሱ የረመዳን ወር ተጠናቆ ነገ ህዝበ ሙስሊሙ የኢድ አልፈጥርን በዓል ያከብራል፣ ለዚህም ፈጣሪን ማመስገን ያስፈልጋል። አላሁ ሱባነሁ ወተኣላም በቅዱስ ቁርአን ውስጥ ላረኩለችሁ ነገር ያመሰገናቹኝ ከሆነ እጨምርላቿለሁ ብሏል።

የረመዳን ወር ለህዝበ ሙስሊሙ የዕዝነት የመተሳሰብ የመረዳዳት ለከይር ስራ የመሽቀዳደም እና ከፈጣሪው ጋር ያለውን ቅርበት የሚያጠናከርበት ነው::

በመሆኑ የፍቅር የመቻቻልና የአንድነት ተምሳሌት የሆነችው ከተማችን በቀናት ልዩነቶች ውስጥ የትንሣኤን በዓልና የፊቼ ጨምበላላ በዓላትን ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መልኩ ያስተናገደች ሲሆን ነገ ደግሞ የኢድ አልፈጥር በዓል በታላቅ ድምቀት ይከበራል። ለዚህም የከተማችን ነዋሪዎች ሚና የማይተካ ነው።

በድጋሚ መልካም በዓል እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።

ኢድ ሙባረክ።

Photos from ትንሣኤ ለኢትጵያ's post 19/04/2023

-Cambalaalla

19/04/2023

Ayidde Cambalaalla!

18/04/2023

የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ለሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ ፍቼ ጫንባላላ በአል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
******************
(ኢ ፕ ድ)

የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ ለሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ ፍቼ ጫንባላላ በአል በሰላም አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል ፊቼ ጫምባላላን አስመልክተው ያስተላለፉት መልዕክት እንደሚከተለው ቀርቧል።

ፍቼ ጫንባላላ የአዲስ ዘመን ብስራት ነዉ፤ የሲዳማ አባቶች (አያንቶች) በከዋክብትና በጨረቃ ዉደት የዘመን ቀመር በማበጀት አሮጌዉን ዓመት ሸኝተዉ፣ አዲሱን አመት በፍሰሃና በተድላ እንድንቀበል ያበጁልን ታላቅ የአስትሮኖሚያዊ እዉቀት የሚገለጥበት ታላቅ በዓል ነው ብለዋል ከንቲባው በመልዕክታቸው።

በሲዳማ ብሄር ባህላዊ ስርዓት መሰረት፣ ፍቼ- ጫንባላላ የሰዉ ልጆች ሚያከብሩት በአል ብቻም ሳይሆን ፍጥረታትም ጭምር የሚከበሩበት እጅግ ታሪካዊ የእኩልነት በዓል ነዉ። በዓሉ ለስነ-ምህዳር ካለዉ ትልቅ ቦታ በመነሳት፣ በበዓሉ ወቅት የእንስሳት እርድ፣ የእጽዋት መቆረጥ እና የመሬት እርሻ ፈጽሞ የማይፈቀዱ ተግባራት ናቸውም ብለዋል ከንቲባው።

በዓሉ አዲሱን ዓመት በትልቅ ፀጋ፣ ዕቅድ፣ ተስፋና መልካም ምኞት የሚንቀበልበት፤ ባሳለፍናቸዉ ጊዜያት ሁሉ ስለ ሰራናቸው ስራዎች የፈጣሪን ምህረት አብዝተን የምንለምንበት፤ ይቅርታ እርቅና ፍቅር የሚወርድበት፤ ያለዉ ለሌለዉ አካፍሎ የሚበላበት፥ የአዲስ እሳቤና የመልካም ስራ እንደመሆኑ ባህልን ከሀይማኖታዊ አስተምሮዎች አስተሳስሮ የያዘ የሁሉም እኩል በዓል ስለመህኑም ነው ከንቲባው የገለፁት።

ከሁሉም በላይ ፍቼ ጫንባላላ የአብሮነት በአል ነዉ። በቄጣላዉ ስረአት አብሮነትን፣ በማዕድ ማጋራቱ አብሮነትን በሆሬ ዳንባርዮ ጫወታ አብሮነትን፣ በሶሬሳ ጉዱማሌዉ አብሮነትን በፋሮ ረገጣዉ አብሮነትን በሁሉቃዉ ስረአት አብሮነትን ያስተምረናል። አክባሪነት፣ አቃፊነትና ወንማማችነት ልዩ መገለጫዎቹ እንደሆኑም አስረድተዋል።

በመጨረሻም ከንቲባው ለከተማዋ ነዋሪ ይህንን የአለም የማይዳሰስ ቅርስ፤ በመን ተሻጋሪ የሆነ ባህላችንን ስናከብር የሶሬሳ ጉዱማሌያችን መገኛ የሆነችዉ ከተማችን ሀዋሳ ልጆቿንና እና እንግዶቿን ከአራቱም ማዕዘናት ተቀብላ በክብር የምታስተናግድበት ልዩ ቀን እንደመሆኑ የሚመጡ እንግዶችን ተቀብሎ በክብር መሸኘት የቱሪስት ፍሰታችን አይነተኛ ሚና ስለሚኖረዉ በክብር ተቀብለን እንድናስተናግድ የአደራ መልክቴን እያስተላለፍኩ ለመላዉ የከተማችን ማህበረሰብ መልካም በአል በአል እንዲሆን እመኛለሁ በማለት አስረድተዋል። ።

Want your organization to be the top-listed Government Service in Awassa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address

Awassa
Other Government Organizations in Awassa (show all)
Sidaama Region Bureau of Justice/ሲብክመ ፍትሕ ቢሮ Sidaama Region Bureau of Justice/ሲብክመ ፍትሕ ቢሮ
Awassa

Sidama Region Bureau of Justice is Governmental Institution that strives for law, justice and equity

Daayye Quchumu Gashshooti Mootimate komunikeeshiine Hajjubba Borro Mine Daayye Quchumu Gashshooti Mootimate komunikeeshiine Hajjubba Borro Mine
Woldamanuel Dubale Street
Awassa, GOVERNMENTALORGANIZATION

Non profit

በታቦር ክ/ከተማ የሂጣታ ቀበሌ አስተዳደር የህዝብ ግንኙነት ጽ/ቤት Hitata Kebele በታቦር ክ/ከተማ የሂጣታ ቀበሌ አስተዳደር የህዝብ ግንኙነት ጽ/ቤት Hitata Kebele
Hawassa
Awassa

አብረን ሠርተን አብረን እንደግ በጋራ አቅደን በህብረት እንሩ

Hawaasi Qooxeessi Aliidi Yoo Mine የሀዋሳ አከባቢ ከፍተኛ ፍ/ቤት Hawaasi Qooxeessi Aliidi Yoo Mine የሀዋሳ አከባቢ ከፍተኛ ፍ/ቤት
Infront Of Meskel Square
Awassa

This page is governmental organization which delivers timely information for court community and its customers

Arbegoonu Woradi Budu ,Turizimetenna Ispoortete Borro Mine Arbegoonu Woradi Budu ,Turizimetenna Ispoortete Borro Mine
Arbegona, Sidama
Awassa, YAYESIDAMAETHIOPIA

Garamba mountain

Sidama National Regional State Ethics and Anti Corruption Commission Sidama National Regional State Ethics and Anti Corruption Commission
Awassa

Sidam natinal rigional state stablished by proclamation number 10/2012 to fight against corruption