Sidama National Regional State Ethics and Anti Corruption Commission

Sidam natinal rigional state stablished by proclamation number 10/2012 to fight against corruption

13/09/2024

ሙስና የሀገር ሰላምን የሚያደፈርስ ፣በዜጎች መካከል የነበረን መተማመን የሚሸረሽር ፣የዴሞክራሲ እድገትን የሚያቀጭጭ እንዲሁም ቤተሰብን የሚያናጋ ጠላት እንደመሆኑ መጠን ለትግሉም የሁሉንም አካላት ቁርጠኛ ትግል ይጠይቃል።

Photos from Sidama National Regional State Ethics and Anti Corruption Commission's post 11/09/2024

Hawalle 2017 M.D haaru diro soorro ayyaanira keerunni iillishi'ne/iillishinke. Haaru diri baxillunniha, keeruniha, alte atootunnihanna gumunniha ikka'nera/ikkankera halcheemma!

Dancha Ayyaana

እንኳን ለ2017 ዓ.ም ዘመን መለወጫ በዓል በሰላም አደረሰን /አደረሳችሁ አድሱ ዓመት የሰላም፣ የፍቅር፣የበረከትና የስኬት ዓመት እንዲሆንልን/እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።
መልካም በዓል

Photos from Sidama National Regional State Ethics and Anti Corruption Commission's post 05/09/2024

ኮሚሽኑ ለባለሙያዎች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና እየሰጠ ነዉ።

ነሀሴ 30/2016 ዓም
ቱላ
===================================

የሲዳማ ክልል ሥነምግባር እና ፀረሙስና ኮሚሽን ለኮሚሽኑ ሰራተኞች በእቅድ አዘገጃጀት እና በስራ ሥነ-ምግባር ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫና የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና በቱላ ከተማ እየሰጠ ይገኛል።
ኮሚሽኑ ሥልጠና ለመስጠት የክልሉን የፕላንና የልማት ቢሮ፣ የሲ/ሰ/የሰ/ሀ/ቢሮንና የኮሚሽኑን የሥልጠና ዳይረክቶሬት በመጋበዝ ሲሆን ስልጠናዉ የስራ ሥነ ምግባር፣ አገልግሎት አሰጣጥ፣ እስትራቴጂያዊ የልማት እቅድ አዘገጃጀት ፣ የሥነምግባር ኮድና በስራ ሥነምግባር ግድፈቶች ዙሪያ ትኩረት ተደርጎ እየተሰጠ ይገኛል።

ስልጠናዉ ዓላማም በስራ ሥነምግባር እና እቅድ አዘገጃጀት ላይ ልታዩ የሚችሉ ችግሮችን ለመቅረፍ እንድቻልና በቀጣይነት የሚሰራዉን ስራ በታማኝነት፣ በተጠያቂነትና በግልጽነት ለመስራት ግንዛቤ ለመፍጠር እንደሆነም ተገልጿል።

03/09/2024

ለልጆቻችን ከሙስና የፀዳች ሀገር ለማስረከብ ለሚደረገዉ ትግል አካል እንሁን።

02/09/2024

ሙስና የልማትና የዴሞክራሲ እንቅፋት እንዲሁም ከወንጀሎች ሁሉ የከፋ ወንጀል በመሆኑ በቁርጠኝነት በመታገል ልማትና መልካም አስተዳደርን እናፋጥን።

Photos from Sidama National Regional State Communication Affairs Bureau's post 29/08/2024
Photos from Sidaama Regional State Livestock Resource Development Bureau's post 27/08/2024
Photos from Sidama National Regional State Ethics and Anti Corruption Commission's post 27/08/2024

Si/Da/Qo/Mo/Am/Ts/Mu 2016 M.D loosu jeefishsha keenatenni 2017 M.D qummeessancho mixo timo eliidi amanyotu harunso dayrekterootira dirrissu.

Woxawaajje 21/2016 M.D
Tuula
===================================
Si/Da/Qo/Mo/Am/Ts/Mu/Ko 2016 M.D loosu jeefishsha keenatenni 2017 M.D qummeessaancho mixo qoqqowunna zoonnate tantanante loossano amanyootu harunso dayrektrrootira shiqishsheenna Tuulate quchumira hasaawa assitino.

Barete leelte sokkase sayissinoti qoqqowu Am/Ts/Mu/Ko Komishiinere Dukko Zelaalemi Lammiti coydhanni, mussinnu bikkamino manni jirote birxera fulanno gede assatenni hala'lado daga kayinni buximate giddo tuganno latishshu diinati yitino.

Komishiineri Zelaalemi suffeno, gobbate deerrii ikko kalqete batinyu manni loosikkinni wolu jiro adhate halchanno; konne gargarre gatisanna dagate amandoonni latishshu mixo hafanfarre nookkiha coicha ikkino garinni baatto kaxxitanno gede safo tugginannire ikka'ne bikkinni konni handaarinni kaayyo afidhine loossinanni massagaano, amanyootu harunso dayrekterootinna deskete massagaano wo'mu xukinni sharramate murccidhinoonnirenna bushu assootinni coicha ikkitinoonnire ikka hasiissanno'ne yitino.

Mussinnu loosi kalaqamate albaanni balaxote gargarooshshi aana illacha tunge loosa hasiissannota qummi assitinoti ayirrado komishinere, balaxote gargarooshshinni sa'ino haja wolootu hajo la'annonsa bissara harancho yanna giddo shiqisha hasiissannota xawissino

Mootimmate loosu uurrinsha giddo loossanno ogeeyyenna massagaano moorunna bainchu assooti giddora e'anno gede assannohu amanyootu ba'ne ikkitinota kulte qajeelshunninna harunsotenni tiiu soorro abbate illacha tunge loosa hasiissannotano lede huwachishshino.

Amanyootu ha'runso dayrektoreete Dayrekterichi Kalaa Asaffi Worqinehu isi widoonni coyiranni, 2016 M.D giddo tiiu soorro aana illacha tunge loonsoonnita xawise konniino xaaddote qajeelsha aate ragaanni hala'ladu loosi loosamino yino.

Photos from Desta Ledamo- ደስታ ለዳሞ's post 24/08/2024
Photos from Sidama National Regional State Ethics and Anti Corruption Commission's post 23/08/2024

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሥነምግባርና ፀረሙስና ኮሚሽን አመራርና ሰራተኞች የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃግብር አካሄዱ።

ነሀሴ 17/2016 ዓም
ሀዋሳ
=====================================
"የሚትተክል ሀገር የሚያፀና ትዉልድ" በሚል መሪ ሀሳብ በሀገር ደረጃ በአንድ ጀምበር 600 ሚልዮን ችግኝ የመትከል መርሀግብር እየተካሄደ የሚገኝ ስሆን የሲዳማ ክልል ሥነምግባርና ፀረሙስና ኮሚሽን አመራርና ሰራተኞችም በዛሬዉ እለት በሀዋሳ ከተማ በ ጋራ ሪቃታ ቀበሌ ተገኝተዉ ችግኝ በመትከል አረንጓዴ አሻራቸዉን አኑረዋል፡፡

በችግኝ ተከላ መርሀግብሩ ላይ ተገኝተዉ ንግግር ያደረጉት የሲዳማ ክልል ኮንስትራክሽን ቢሮ ሀላፊ አቶ አሻግሬ ጀምበሬ እንደተናገሩት አለማችን በአየር ንብረት ለዉጥ ከፍተኛ ተግዳሮት እየገጠማት በሚትገኝበት በዚህን ወቅት ሀገራችን ይህንን ተግዳሮት መሻገር የሚትችልበትን ስልት በመንደፍ ባለፉት አራት አመታት ወዲህ የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም ተይዞ ትልቅ ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ በመግለጽ ይህም እንደሀገር ልደርስብን የሚችለዉን ተፈጥሯዊ አደጋዎች ለመከላከል የሚያበረክተዉ አስተዋፅኦ የጎላ እንደሆነ ተናግረዋል ።

ዛሬ እየተከልን ያለነዉ የችግኝ ተከላ መርሃግብሩን ከማስፈጸም ባለፈ ሀገራችንን ከተለያዩ ተፈጥሯዊ አደጋዎች ተጽእኖ የሚከላከል፣ በምግብ እራሳችንን ለመቻል የሚደረገዉን ትግል የሚያሳካና እንዲሁም ለመጪው ትዉልድ የተሻለ አከባቢ የማሻገር ጉዳይ ነዉ ብለዋል።

በዚህ መርሃግብር የተሳተፍን ሁላችንም ችግኝን ከመትከል ባሻገር መጽደቃቸዉንም የማረጋገጥ ሀላፊነት አለብን ያሉት ሀላፊዉ ይህንን በመረዳት የተተከሉትን መንከባከብና ይህን መልካም ተግባር ለቀጣይ ትዉልድ በማሸጋገር የፀናች ሀገር መፍጠር ይጠበቅብናል ስሉ አሳስበዋል።

በመርሃግብሩ የሀገር ሽማግሌዎች ፣የሀይማኖት አባቶች፣ከወረዳና ከክልል ቢሮ የተወጣጡ አመራርና ሰራተኞች እንዲሁም የፌደራል ፖሊሲ አባላትና አመራሮች ተሳትፈዋል።

የኮሚሽኑ የኮሚንኬሽን ጉዳዮች ዳይረክቶሬት

Photos from Sidama National Regional State Ethics and Anti Corruption Commission's post 19/08/2024

የሲዳማ ክልል ሥነምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ከኮሚሽኑ አመራርና ሰራተኞች ጋር ዉይይት አካሄደ።

ነሀሴ 13/2016ዓም
ሀዋሳ
==============================
ኮሚሽኑ በዛሬዉ እለት "ሰዉ ተኮር አገልግሎት ለሀገር ግንባታ" በሚል ርዕስ ላይ በተዘጋጀው ሰነድ ዙሪያ አጠቃላይ የኮሚሽኑ አመራርና ሰራተኞች በተገኙበት ወይይት አድርጓል። የመወያያ ሰነድን የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር አቶ መልካሙ መንገሻ ያቀረቡ ስሆን በቀረበዉ ሰነድ መነሻነት ዉይይት የተካሄደ ሲሆን እንደሀገር ስምንት የክልል ተቋማትን እና ሁለት የፌዴራል ተቋማትን ናሙና በመዉሰድ የተካሄደው ይኸው የዳሰሳ ጥናት በየተቋማቱ በሚሰጡ አገልግሎቶች ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ፍንትው አድርጎ ያሳየ መሆኑ ተመላክቷል።

እንደሀገር የመንግስት ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ እና መሠል የህዝብ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተደረጉ ጥረቶች ቢኖሩም፤ በአገልግሎት አሰጣጡ ዙሪያ ከሚስተዋሉ ችግሮች ስፋትና ጥልቀት አንፃር ጉዳዩ ፈጣን የማስተካከያ እርምጃ የሚጠይቅ መሆኑን የዳሰሳ ጥናቱ አመላክቷል።

በተጨማሪም ጥናቱ በመልካም አስተዳደር ዘርፍ በየደረጃው ያሉ ተቋማት ራሳቸውን እንዲፈትሹ የሚያደርግ መሆኑን ነዉ ም/ኮሚሽነር አቶ መልካሙ የገለፁት።

በመጨረሻም በጥናቱ ሰነድ ላይ በተጠቀሱት ችግሮች እና የመፍትሔ አቅጣጫዎች ዙሪያ ሰፊ ውይይት የተካሄደ ሲሆን፤ በቀጣይ ተግባራዊ ንቅናቄ በማድረግ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚዘጋጁ የውይይቱ ተሣታፊዎች ገልፀዋል።

የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ዳይረክትሬት

19/08/2024

ዛሬ የተተከለ ችግኝ ለትውልድ የሚያብብ የውርስ ቃል ኪዳን ነው!!

ነሀሴ 13/2016 የሲዳማ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ

ዛሬ ላይ ችግኞችን የምንተክለው ለመጪው ትውልድ የማይረሳ አሻራን እና የበለፀገች ሀገር ለማኖር ነው።

መጪው አርብ ነሐሴ 17/2016 የምንወዳት ሀገራችን በአንድ ቀን 600 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ታሪካችንን ዳግም የምናድስበትን ልዩ ቀን ነው።

በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶ/ር አብይ አህመድ ጥሪ የተያዘው ይህ ታላቅ ተነሳሽነት የከባቢ አየር ለውጥን ከማስጠበቅ በላይ ኢትዮጵያውያን ሀገራቸው በአለም አዳባባይ በአረንጓዴ ልማት የጀመረቻቸውን የአየር ንብረት ለውጥን የማስጠበቅ ሚናዋን አጠናክራ ማስቀጠሏን የምታረጋግጥበት ፣ የራሷን ታሪካዊ አሻራ ደግማ የምታድስበት አስደናቂ ተግባር ነው። ለሀገራችን ትልቅ ስጦታ እና ለመጪው ትውልድም የማይረሳ ትሩፋት ነው።

የዚህ ተግባር አስፈላጊነት በቀላሉ ሊገለጽ የማይችል ፤ ችግኞችን በመትከል በአየር ንብረት ለውጥ ሊመጡ የሚችሉ ችግሮችን በመታገል ጎን ለጎን ተፈጥሯዊ መልክዓ ምድራችንን በማስፋት ስነ-ምህዳሮችን ወደነበረበት ለመመለስ እና ለራሳችን እና ለሚመጣው ትውልድ ጤናማ አካባቢን እያረጋገጥን መሄድ ነው።

እያንዳንዱ ችግኝ ለመጪው ትውልድ ተስፋን ፣ ጽናትን እና ለምንወዳት ሀገራይን ኢትዮጵያ ደህንነት ያለንን የጋራ ቁርጠኝነት የሚያመላክት ይሆናል ፤ እናም ይህ ታላቅ ተግባር የእያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ ተሳትፎ ይመለከታል። የአንድነታችንን ጥንካሬ እና የጋራ ራዕያችንን ለማሳካት የተሻለ ጊዜ ላይ መሆናችንንም ያሳየናል።

ይህ ቀን ለአካባቢያችን ለውጥ እና ብልፅግና ያለን ቁርጠኝነት እና ለጋራ ጥቅም በጋራ ለመስራት ያለን ፈቃደኝነት ማሳያ ይሆናል። ለዚህ ታሪካዊ ቀን ስንዘጋጅ ጥረታችን ችግኞችን ከመትከል ያለፈ ፥ ብሔራዊ አርበኝነታችንን የምናመላክትበት መሆኑንም እናስታውስ።

የሀገራችን ኢትዮጵያ የለውጥ መሪዎች ፣ የወደፊቷን ኢትዮጵያ የተሻለች ለማድረግ የሚታትሩ ፣እና ለቁጥር የሚታክቱ ትውልድን የሚጠቅሙ ትሩፋት ተሸካሚዎች እና አብሳሪዎች በመሆን ኃላፊነታቸውን እየተወጡ ሲሆን ፥ የጠቅላይ ሚኒስትራችን የአረንጓዴ ልማትም የብልፅግና እና የኢትዮጵያ ራዕይ ፖሊሲ ብቻ አለመሆኑን እና ለልጆቻችን እና የእኛን ፈለግ ለሚከተሉ ሁሉ ቃል ኪዳን መሆኑን ያመላከተ ተግባር ሆኗል።

አርብ ነሐሴ 17/2016 ማንም ሰው እንዳይቀር። እያንዳንዱ ግለሰብ ፥ እንዲሁም ቡድን በጉጉት እና በቁርጠኝነት ለዚህ አጋጣሚ ይነሳ። ለዚህ ታላቅ ስራ ሁላችንም የበኩላችንን እናበርክት፣ ይህንንም በማድረግ ለዘላቂና ለበለፀገች ኢትዮጵያ እውን መሆን ያለንን ቁርጠኝነት እናረጋግጥ።

በጋራ፣ ይህንን ያልተለመደ ግብ ማሳካት እና ለዘመናት የሚዘልቅ ትሩፋት መገንባት እንችላለን። ችግኝ ስንተክል የእድገት ተምሳሌት ብቻ ሳይሆን የጋራ ተስፋችንን እና የቁርጠኝነታችን ተምሳሌት እና ህያው ማስታወሻ ይሆናል።

ዛሬ የተተከለ ችግኝ ለትውልድ የሚያብብ የውርስ ቃል ኪዳን ነው!! ( የሲዳማ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት)

Photos from Sidama National Regional State Ethics and Anti Corruption Commission's post 19/08/2024

Sidaamu Da/Qo/Mo/A/Tse/Mu/ Komishiine loosaasine "Mancho Illachishshino Owaante Gobbate Ijaarshira" (ሰዉ ተኮር አገልግሎት ለሀገር ግንባታ) yitanno sanade aana konni garinni hasaawa hanaffino.

Photos from Sidama National Regional State Agriculture Bureau's post 06/08/2024
05/08/2024

የከንቲባዋ ታናሽ ወንድም እና የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ነኝ በማለት ከአራት ግለሰቦች ላይ ከ900 ሺ ብር በላይ ያታለለ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለ

************

(የፌ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ ሐምሌ 29/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) አንድ በድለላ ስራ ላይ የተሰማራ ግለሰብ የከንቲባዋ ታናሽ ወንድም እና የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ነኝ በማለት ከአራት ግለሰቦች ላይ ከ900 ሺ ብር በላይ ያታለለን ተጠርጣሪ ከግብረ አበሮቹ ጋር ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን አዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ተጠርጣሪው ግለሰብ ታደለ ጌታነህ ይባላል፡፡ ሆኖም ስሙ ታደለ አቤቤ እንደሚባል ሐሰተኛ መታወቂያ አሰርቶና የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ታናሽ ወንድምና የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ነኝ በማለት ሰዎችን በሀሰት ጉዳያችሁን እጨርስላችኋለው ብሎ ከተዋወቀ በኋላ ከአራት ግለሰቦች ላይ 970 ሺ ብር በማታለሉ ተጠርጣሪውን ጨምሮ ሁለት ግብረ አበሮቹን ይዞ ምርመራው መቀጠሉን አዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የግል ተበዳይ አቶ ልዑል ኪሮስን የከንቲባዋ ወንድም እንደሆነና መንግስት ለቤት መስሪያ 140 ካሬ ሜትር ቦታ ስለሰጠው ለሊዝ የሚክፍለው 800 ሺ ብር እንዲያበድሩት ይጠይቃቸዋል፡፡

የግል ተበዳይም የተባሉትን በማመን 600 ሺ ብሩን አስናቀ ጌታነህ ቀሪውን 200 ሺ ብር ደግሞ በላይ ጣሰው በተባሉት ግብረ አበሮቹ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢ እንዲያደርጉ በነገራቸው መሰረት ብሩን ገቢ ያደርጋሉ፡፡

በተመሳሳይ የማታለያ ዘዴ አቶ ፈለቀ ሃይሉ የተባሉትን ግለሰብ በመቅረብ ቤት ለመገንባት 4ሚሊዮን ብር እንደሚያስፈልገው እና 500ሺ ብር ብድር እንዲሰጡት ጠይቆ 105 ሺ ብር መቀበሉን በማስረጃ ማረጋገጡን ፖሊስ ገልጿል፡፡

በተመሳሳይ አዳማ ከተማ የተዋወቃቸውን አቶ ለገሰ ሲሳይን ደግሞ የከንቲባዋ ወንድም ስለሆነኩ በቀላሉ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ መሬት አሰጥሃለሁኝ ብሎ 10 ሺ ብር የወሰደ ሲሆን እንዲሁም ለቤተሰባቸው ፓስፖርት ለማውጣት ኢሚግሬሽን ያገኛቸውን አቶ ፈለቀ ዝናቡን የከንቲባዋ ወንድም ነኝ በተጨማሪም “እኔም ዳኛ ነኝ ምናልባት ያለ አግባብ የሚያጉላሉህ ካሉ አሳውቀኝ ሰብስቤ አሳስራቸዋለሁኝ” የሚል የማታለያ ቃል በመናገር ጉዳያቸው በፍጥነት እንዲያልቅል 80 ሺህ ብር እንዲሰጠው ጠይቆ 10 ሺ ብር አታሎ መውሰዱን አዲስ አበባ ፖሊስ ባሰባሰበው ማስረጃ መረጋገጡን አስታውቋል፡፡

ግለሰቡ ከከንቲባዋ ጋር ምንም አይነት ዝምድና የሌለውና በድለላ ስራ የተሰማራ መሆኑን ፖሊስ አስታውቆ ግለሰቡን ጨምሮ በዚህ ወንጀል ተሳትፎ ያላቸው ሦስት ተጠርጣዎችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራውን መቀጠሉን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የመንግስት አገልግሎት ተገቢ ባልሆነ መንገድ ወይም በአቋራጭ ለማግኘት የሚደረጉ ማንኛውም ህገወጥ ተግባር ላልተገባ ወጪ የሚዳርግ መሆኑን ህብረተሰቡ ተገንዝቦ ድርጊቱን እንዲከላከል እና በዚህ ህገ ወጥ ድርጊት የሚሳተፉ ግለሰቦችን ህብረተሰቡ የማጋለጥ ሐላፊነት እንዳለበት አዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክት አስተላልፏል፡፡

ከሙስና የፀዳች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ዕውን እናድርግ!

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የጥቆማ ሶፍትዌሮች፦ https://ncrs.feacc.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/
ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc
የጥቆማ ኢሜል፡- [email protected]
ዩትዩብ፡- https://youtube.com/-corrupti149
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/?_t=8jEyU0ouURa&_r=1
ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን።

Photos from Sidama National Regional State Ethics and Anti Corruption Commission's post 05/08/2024

ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ የመንግስትና የህዝብ ሀብት ከምዝበራ ማዳን መቻሉን የሲዳማ ክልል ሥነምግባርና ፀረሙስና ኮሚሽን ገለፀ።

ሐምሌ 29/2016 ዓ.ም
ቱላ
=====================================
ኮሚሽኑ የ2016 በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀም በመገምገም በ2017 ዓ.ም ትኩረት ተሰጥቶ በሚሰራባቸዉ ጉዳዮች ዙሪያ የኮሚሽኑ አመራር፣ የማናጅመንት አባላትና ባለሙያዎች በተገኙበት በቱላ ክፍለ ከተማ ዉይይት አድርጓል፡፡

የዉይይት መድረኩን የመሩት የክልሉ ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ወ/ሮ ዘላለም ለማ እንደገለፁት በ2015 የታዩ ጉድለቶችን በማረም የተሻለ የአፈፃፀም ዉጤት መታየቱን ተናግረዋል፡፡ አያይዘዉም የማናጅመንት አባላትንና ባለሙያዎችን ተባብረዉ ላመጡት እጅግ በጣም ከፍተኛ ዉጤት በማመስገን ለቀጣይ በጀት ዓመት እቅድም እጅ ለእጅ ተያይዘዉ በመስራት ይህንን ዉጤት እንዲያስቀጥሉ መልእክታቸዉን አስተላልፈዋል። ኮሚሽነሯ አክለዉም የመንግስት በጀትን በቀጣይ የሚሰሩ ስራዎችን መሰረት ባደረገ መልኩ መጠቀምና የሚጠብቅብንን ስራ በቁርጠኝነት መወጣት ይገባናል ስሉም አሳስበዋል።

የ2016 ዓም የስራ አፈፃፀም ሪፖርትና የ2017 ዓ.ም መሪ እቅድ ያቀረቡት የኮሚሽኑ በጀት ዝግጅት፣ ክትትልና ድጋፍ ዳይረክቶሬት ዳይረክተር አቶ በላይ ባንጋሳ እንደገለፁት፣ ኮሚሽኑ ትዉልድን በመልካም ሥነ-ምግባር የማነጽ ስራዎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሰራ ገልፀዉ በዚህም ወቅታዊ የስልጠና ሞጁሎችን በማዘጋጀት የፊትለፊት ስልጠና ተሰጥቷል ብለዋል። ከመንግስትና ከግል ሚዲያዎች ጋር በመቀናጀት እየተሰራ ነዉ ያሉት ዳይረክተሩ በሬዲዮና በቴሌቪዥን ትምህርታዊ ይዘት ያላቸዉ ፕሮግራሞችን ለማስተላለፍ መታቀዱንና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ ከእቅዱ በላይ መስራት መቻሉንም ጨምረዉ አብራርተዋል።

አያይዘውም የሀብት ማሳወቅ፣ ማስመዝገብና ግልጽነትንና ተጠያቅነትን ከማጠናከር እንዲሁም ትክክለኛነትን ከማረጋገጥ አኳያም ከእቅዱ በላይ ማሳካት መቻሉን አብራርተዋል። አቶ በላይ አክለዉም በ2016 በጀት ዓመት ዉስጥ 508 ጥቆማዎች መቅረባቸዉን ገልፀዉ በዚህም 20,458,942.59 የመንግስትና የህዝብ ሀብት ከምዝበራ ማዳን መቻሉን አመላክተዋል ፡፡

በመጨረሻም በቀረበዉ የስራ ክንዉን ሪፖርትና የ2017 ዓም መሪ እቅድ ዙሪያ ተሳታፊዎቹ አስተያየትና ጥያቄ አንሰተዉ በኮሚሽኑ አመራር ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

Photos from Sidama National Regional State Ethics and Anti Corruption Commission's post 31/07/2024

የፌ/ሥ/ፀ/ሙ/ኮ/ የጀመረዉን አቻ ለአቻ ድጋፋዊ ክትትል አጠናቀቀ ።
ሐምሌ 24/2016 ዓ. ም.
ሲዳማ
ሀዋሳ

የኮሚሽኑ ድጋፋዊ ክትትል ቡድኑ ሐምሌ 20/2016 ዓ.ም. በክልላችን ኮሚሽን በመገኘት የጀመሩትን ድጋፋዊ ክትትል በኮሚሽኑ ታቅዶ በዕቅዱ መሠረት የተከናወኑ ክንዉኖችን በጥልቀት ፈትሾ በመገምገም ችግር ፈቺ ድጋፍ በማድረግ በሂደቱ ያገኙትን ጠንካራና ደካማ ጎን ለማነጅሜቱ ግብረ መልስ አቅርበዋል።

ከቀረበዉም ግብረ መልስ መነሻ ኮሚሽኑ በበጀት ዓመቱ አቅዶ ያከናወናቸው ተግባራት እጅግ አመርቂና ተስፋ ሰጪ መሆኑን ቡድኑ አንስቷል።
በዉይይቱ ላይ ለቀረበዉ ግብረ መልስ ምላሽ ስሰጡ ክብርት ኮሚሽነር ዘላለም ለማ እኛ ሥራዎችን የሚንሠራዉ የሕዝባችንን ተጠቃሚነት ግምት ዉስጥ በማስገባት ሌት ተቀን ደከመን ሰለቸን ሳንል ነዉ በማለት በቀጣይም ጥንካሬአችንን በማስቀጠል ክፍቶቻችንበማረም ከዚህ የበለጠ እንሠራለን ብለዋል።
በመጨረሻም ቤቱ የተለያዩ አስተየቶችን ሰጥቶ ቡድኑ ስላደረገው ቀና ድጋፋዊ ክትትል አመስግኖ መድረኩ ተጠናቅቋል።

የሲዳማ ክ/የሥ/ፀ/ሙ/ኮ/የሕዝብ ግንኙነት ዳይረክቶሬት

Photos from Sidama National Regional State Ethics and Anti Corruption Commission's post 29/07/2024

የፌደራል የሥ/ም/ፀ/ሙ/ኮሚሽን የክልል ኮሚሽኖችን ሱፐርቫይዝ ማድረግ ጀመረ።
ሐምሌ 22/2016 ዓ ም
ሀዋሳ
ከፌደራል ሥ/ም/ፀ/ኮ/ ለሲዳማ ክልል የተመደቡ አካላት 1ኛ አቶ በቃሉ አትርሳዉ የኮምሽኑ የሥልጠና ጥራትና ተገቢነት ባለሙያ 2ኛ አቶ አሰፋ ቶላ የአዲስ አበባ ከተማ ፀ/ሙ/ኮ/ ምክትል ኮሚሽነር በሲዳማ ክ/ፀ/ሙ/ኮ/ቢሮ ተገኝተዉ ከኮሚሽኑ ማኔጅመንት ገር በመተዋወቅ የሱፐርቪዥኑን ዓላማ ካስረዱ በኋላ በያዙት ቸክሊስት መሠረት የመጀመሪያ ምዕራፍ የሥልጠና ዳይረክቶሬትን ጨርሰዉ ከምሳ ዕረፍት በኋላ እንደሚቀጥሉ ተረገግጧል። ቀጣዩን ቀጥለን የሚናቀርብ ይሆናል።

የሲ/ክ/ፀ/ሙ/ኮ/የሕዝብ ግንኙነት ዳይረክቶሬት
ሐዋሳ

Photos from Federal Ethics and Anti-Corruption Commission's post 28/07/2024
Photos from Sidaama National Regional State Urban development and Construction Bureau's post 06/07/2024
Want your organization to be the top-listed Government Service in Awassa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address


Awassa
Other Government Organizations in Awassa (show all)
Sidaama Region Bureau of Justice/ሲብክመ ፍትሕ ቢሮ Sidaama Region Bureau of Justice/ሲብክመ ፍትሕ ቢሮ
Awassa

Sidama Region Bureau of Justice is Governmental Institution that strives for law, justice and equity

Daayye Quchumu Gashshooti Mootimate komunikeeshiine Hajjubba Borro Mine Daayye Quchumu Gashshooti Mootimate komunikeeshiine Hajjubba Borro Mine
Woldamanuel Dubale Street
Awassa, GOVERNMENTALORGANIZATION

Non profit

በታቦር ክ/ከተማ የሂጣታ ቀበሌ አስተዳደር የህዝብ ግንኙነት ጽ/ቤት Hitata Kebele በታቦር ክ/ከተማ የሂጣታ ቀበሌ አስተዳደር የህዝብ ግንኙነት ጽ/ቤት Hitata Kebele
Hawassa
Awassa

አብረን ሠርተን አብረን እንደግ በጋራ አቅደን በህብረት እንሩ

Hawaasi Qooxeessi Aliidi Yoo Mine የሀዋሳ አከባቢ ከፍተኛ ፍ/ቤት Hawaasi Qooxeessi Aliidi Yoo Mine የሀዋሳ አከባቢ ከፍተኛ ፍ/ቤት
Infront Of Meskel Square
Awassa

This page is governmental organization which delivers timely information for court community and its customers

Arbegoonu Woradi Budu ,Turizimetenna Ispoortete Borro Mine Arbegoonu Woradi Budu ,Turizimetenna Ispoortete Borro Mine
Arbegona, Sidama
Awassa, YAYESIDAMAETHIOPIA

Garamba mountain