Burru woradi eote B/s/b/mine

Giwire yannatenni baate qansichima'ya qeecha fuleemmo!!

Photos from Sidaamu Dagoomu Qoqqowi Mootimma Eote Biilloonye የሲ/ብ/ክ/መ/ገቢዎች ባለሥልጣን's post 22/06/2024
Photos from Burru woradi eote B/s/b/mine's post 21/06/2024

በተሻሻለዉ የገጠር መሬትና የእርሻ ምርት ግመታ ግብር አዋጅ ትግበራን አስመልክቶ የፓናል ዉይይት ማድረጉን የሲዳማ ብ/ክ/መ/ገቢዎች ባለስልጣን አስታወቀ።
ሰኔ 13/2016ዓ.ም
***********************************************
የባለሥልጣን ተቋሙ በተዘጋጀዉ ረቂቅ አዋጅ አፈጻፀምና ትግበራ ላይ ዘርፈ ብዙ ለግብዓት የሚሆን ሀገርንና ህብረተሰብን ማዕከል ያደረገ ትምህርት አዘል ለሚዲያ ሽፋን አጀንዳ አጋርቷል።
የፓናል ዉይይቱን የመጀመሪያ ንግግር ያደረጉት የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኃይሉ ጉዱራ እንደተናገሩት በፊት የነበረዉ የገጠር መሬት መጠቀሚያ ግብር አዋጅ እንዲሻሻል አስገዳጅ የሆነዉ ጉዳይ፣
1 የነበረዉ አዋጅ የሀገሪቱን ማህበራዊና ክልላዊ ተጨባጭ ሁኔታ ታሳቢ ያላደረገና ተለዋዋጭ የዓለም ኢኮኖሚ ባህሪያት ጋር የማይመጣጠን መሆኑን በጥናት ስለተረጋገጠ፣
2 መንግስት በእርሻዉ ዘርፍ ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ አስፈላጊ ግብዓትና የግብርና ቴክኖሎጂ ለአ/አደሩና ለአርብቶ አደሩ በዉድ ዋጋ እያቀረበ ተገቢ ገቢ ስላጣ፣
3 የማይቆም የግብርና እና የእርሻ ምርት ግብዓት በስፋትና በጥራት እያቀረበ አርሶ አደሩ ሠርቶ ምርታማ ሆነዉ ቤተሰቡን በምግብ ራሱን ብቁ እንዲያደርግ ለማስቻል፣
4 የመንግስትና የሕዝብ የመሠረተ ልማት ፍላጎትና ጥማት የተግባር ምላሽ ለመስጠት የገቢ መሠረቶችን ማጠናከሩ የጋራ አማራጭ ስለሆነ፣ እንዲሁም ያልተዘረዘሩ የሀገር በቀል ጉዳዮችና ፍጆታ ወጪዎችን ለመሸፈን አዋጅ መሻሻሉ ለሀገርና ለሕዝብ የበለጠ ዕድገትና ልማት ሀብት እንደሚያመነጭ ታምኖበት መሆኑን አስረድተዋል።
በማስቀጠልም የሲ/ብ/ክ/መ/ፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዳዊት ሀዬሶ በበኩላቸዉ በመንግስት በኩል ለእርሻ ልማት የሚቀርበዉ ግብዓት አ/አደሩ ተጠቃሚ ሆኖ ለምርታቸዉም የግብይት ሰንሰለት ተበጅቶላቸዉ የተሻለ ገቢ እያገኙ መሆናቸዉን ገልጸዉ፣
ከምርትና ከግብር የሚሰበሰበዉ ገቢ አናሳ በመሆኑ እስከ አሁን በሀገር ደረጃ ከግብርና ዘርፍ የሚሰበሰበዉ ገቢ ዝቅተኛ መሆኑን ተናግረዋል።
እንዲሁም ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዶ/ር በኃይሉ ጡቄላ ሲናገሩ በኢትዮጵያ ከምስራቅ አፍሪካ ሀገራት በገቢ ዕድገትና በልማት ወደኋላ መቅረቷን ገልጸዉ ህብረተሰቡ ከድህነት ችግር ምክንያት ያጡትን የመሠረተ ልማት ፍላጎቶችን ለማግኘት የገቢ እና ግብር አዋጅ መሻሻሉ ወቅቱንና ለክልል ኢኮኖሚ ከፍ ለማድረግ አስፈላጊ መሆኑን አብራርተዋል።
በዕለቱ ፓናል ዉይይት አጀንዳ አስመልክተዉ ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዶ/ር ወንድሙ አክልሉ ሀሳባቸዉን ሲገልጹ በዓለም ደረጃ መንግስት ከሕዝብ የሚሰበስበዉ ገቢ የላቀ ልማት መልሶ ለሀገርና ለሕዝብ ስለሚሰራ የወጣዉ አዋጅ ተግባራዊ ሆኖ ህብረተሰባችን ለልማታዊ መንግስት ከጎን በመቆም ልማት እንዲፋጠን የበኩላቸዉን እንዲወጡ አሳስበዋል።
በመጨረሻም የረቂቅ አዋጅ አፈጻፀሙን አስመልክተዉ የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኃይሉ ጉዱራ አዋጅ ተግባራዊ ሲሆን የመሬት ስፋት፣ለምነት፣ምርትና ምርታማነት እንዲሁም አርሶ አደሩን መብት ታሳቢ ተደርገዉ የሚተገበሩ መሆኑን አዉስተዉ፣
የገቢ ጉዳይ የሀገርና የሕዝብ ልማት ጉዳይ መሆኑን አዉቀዉ ሁሉም ግንዛቤ ያላቸዉ ዜጎች የበኩላቸዉን እንዲወጡ ጥሪ አስተላልፈዉ የእለቱን ፓናል ዉይይት አጠናቀዋል።
የሲዳማ ብ/ክ/መ/ገቢ/ባለስ /ኮሚኒ/ጉዳዮች።

27/05/2024

በሲዳማ ክልል ከ8 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዳማ ክልል ባለፉት 10 ወራት ከ8 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የክልሉ ገቢዎች ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡

የቢሮው ሃላፊ አቶ ሃይሉ ጉዱራ እንደገለጹት÷ በክልሉ ለመሰብሰብ የታቀደውን ከ13 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ከማሳካትና የክልሉን ገቢ ከማሳደግ አንፃር የሚሰሩ ቀሪ ሥራዎች አሉ።

በበጀት ዓመቱ 10 ወራት የተሰበሰበው ከ8 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ብልጫ እንዳለው ጠቁመዋል።

ይህም ከቀጥታ ታክስ፣ ቀጥታ ካልሆነ ታክስ፣ ታክስ ነክ ካልሆነ ገቢ እንዲሁም ከማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ የተሰበሰበ መሆኑን አስረድተዋል።

ቅንጅታዊ አሰራርን በማጎልበት በቴክኖሎጂ የተደገፈ አሰራር መዘርጋቱ፣ ውዝፍ እዳዎችን አሟጦ መሰብሰቡ እንዲሁም የቅሬታ አፈታት ሥርዓት በመሻሻሉ ለገቢው ማደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል ብለዋል።

በ40 ግብር ከፋዮች ፋይል ላይ በተደረገ የማጣራት ስራ በ29ኙ ላይ ከግብር ሕግ ተገዥነት አንፃር ጥሰት እንደተገኘ መግለጻቸውንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡

09/04/2024

Ayidde cambalaalla!
የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የገቢዎች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀይሉ ጉዱራ ለሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ ፊቼ ጫንባላላ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ/አደረሰን መልዕክት አስተላልፈዋል::

ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ሀይሉ ጉዱራ በመልዕክታቸው ለመላው የሀገራችን ሕዝቦች'ለበዓሉ ባለቤት ለሆነው ለሲዳማ ሕዝብ'ለባለሥልጣኑ ማናጅመንት' ለመላው ሠራተኞች በየደረጃው ለሚገኙ የቻችኛው መዋቅሮቻችን እና ለበዓሉ ታዳሚዎች በሙሉ ለ2017 የሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ ፊቼ ጫንባላላ በዓል እንኳን አደረሳችሁ/አደረሰን ብለዋል::

በዓሉን ሲናከበር ፊቼ ጫንባላላ ውስጥ ያሉትን ዕምቅ እሴቶች ማለትም መከባበርን ወንድማማችነትን እኩልነትን በጋራ መሰባሰብን ይቅር ባይነትን እያሰብን ስለሆነ ሁሉ ሕብረተሰብ ይህንን ዘመን መለወጫ በዓል ሲያከብረ አነዚህን ድንቅና ብርቅ እሳቤዎችን ከግምት ውስጥ የማስገባት አስፈላጊነትን በመልዕክታቸው ጠቁመዋል::

የዘንድሮ የፊቼ ጫንባላላ በዓል የአካባቢያችንን ፀጥታ በመጠበቅ ነዳያንን በመርዳት' የታመሙትን በመጠየቅ' የተቸገሩትን በመደገፍ' መልካም የሆነውን ሁሉ በማድረግ'ፍቅራችንን የምንገልጽበት እንዲሆን በመመኘት ቀጣዩን ጊዜ የውስጥ ገቢያችንን አሟጦ በመብሰብ' የሕዝባችንን የመልማት ፍላጎት በማሟላት የጋራ የቤተሰብ ብልፅግና በተባበረ ክንድ በመሥራት ከድህነት አረንቋ የምንላቀቅበት እንዲሆን ጭምር በማሳሰብ 'መጪው ዘመን ለመላው ሕዝባችን የዕድገት'የብልፅግና'የደስታና የሰላም እንዲሆን ምኞታቸውን ገልጸዋል::

“ግብር ለሀገር ክብር!!” የዓመቱ መሪ ቃላችን ነው !
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገቢዎች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር፡፡
27/7/2016

Photos from Burru woradi eote B/s/b/mine's post 26/03/2024
22/11/2023
Photos from Burru woradi eote B/s/b/mine's post 30/09/2023

Burra albira !!
Burru woradi daganna burru quchumi teesaano hawalle hagidhitini

03/09/2023

ከ30 ቢሊየን ብር በላይ የታክስ ጉዳት አድርሷል የተባለው ግለሰብ ላይ ተደራራቢ ክስ ተመሰረተ

ነሐሴ 27፣ 2015 ዓ.ም ( የገቢዎች ሚኒስቴር)

በመንግስት ላይ ከ30 ቢሊየን ብር በላይ የታክስ ጉዳት አድርሷል የተባለው ተከሳሽ በረከት አለኸኝ ላይ 7 ተደራራቢ ክስ እንደተመሠረተበት ተገለፀ።

ተከሳሹ ለ339 ግብር ከፋዮች 1 ሺህ 663 ደረሰኞችን በማሰራጨት በ15 የገቢዎች ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች የ25 ቢሊየን 989 ሚሊየን 943 ሺህ 223 ብር ከ.83 ሳንቲም የግብአት ታክስ ተመላሽ የተጠየቀበት እና በንግድ ትርፍ ወጪነት የቀረበ በመሆኑ ሌሎች ግብር ከፋዮች ሀሰተኛና አሳሳች ሰነዶችን መጠቀሙም በክሱ ተመላክቷል።

ተከሳሹ በተጨማሪም ያተመውን ደረሰኝ በማሰራጨት የንግድ ትርፍ ፣ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ማለትም በአጠቃላይ 13 ቢሊየን 147 ሚሊየን 368 ሺህ 295 ብር ከ.35 ሳንቲም ጉዳት ያደረሰ መሆኑም በክሱ ተጠቅሷል።

ለሙሉ ዘገባውን የሚከተለውን ሊንክ ይጫኑ፣

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid02e9vmW3Sscez4BbjFfMXjK5iNKzzie44soTNiHAqewLNVgZEdDwLdLRUaafPAJUC2l&id=100069672641659&mibextid=Nif5oz

Photos from Burru Woradi Jireenyu Paarte Dagate Xaadooshshi Qoola/ የቡራ ወረዳ ብ/ፓ/ህ/ግ/ገጽ's post 04/08/2023

Hawalle hagidhitinonni

Photos from Burru woradi eote B/s/b/mine's post 31/08/2022

የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የኦሮሚያ ልዩ ሀይል ዩኒፎርሞች በሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ መመረት ጀመሩ

ነሐሴ 25/2014 ዓ.ም ሲ/ብ/ክ/መ/ፕሬስ ሴክሬታሪያት፡ ሀዋሳ

የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የኦሮሚያ ክልል ልዩ ሀይል ወታደራዊ ዩኒፎርም (መለዮ) በሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ መመረት ጀምረዋል፡፡

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሳንዶካን ደበበ፣ የትራንስፎርሜሽንና ዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ፍፁም ከተማ እንዲሁም የኮርፖሬሽኑ ሌሎች የስራ ሀላፊዎች የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የስራ እንቅስቃሴን ተመልክተዋል፡፡

በጉብኝታቸውም ኢፒክ አፓረል የተሰኘ አምራች ኩባንያን የሀገር መከላከያ ሰራዊት ዩኒፎርምን እንዲሁም የኦሮሚያ ክልል ልዩ ሀይል ዩኒፎርሞችን የሚያመርት ኩባንያን የስራ እንቅስቃሴ ተዟዙረው ቃኝተዋል፡፡ ኢፒክ አፓረል የተሰኘው ኩባንያ እነዚህን ዩኒፎርሞች ከሁለት ሳምንት በፊት ማምረት የጀመረ ሲሆን በምርት ሂደቱ ላይ ያሉ እንቅስቃሴዎችንም ከኮርፖሬሽኑ ከፍተኛ ሀላፊዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡

በሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክም የሚገኘው ኢፒክ የተሰኘው አምራች ኩባንያ ከ177 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ፈሰስ በማድረግ ኢንቨስትመነቱን ስራ የጀመረ ሲሆን አሁን ላይ የጨርቃጨርቅ ዘርፉ ላይ በመሰማራት ከ2500 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል መፍጠሩን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ገልጿል፡፡

ሀዋሳ ኢንዱስተሪ ፓርክ በአሁን ሰዓት ከ20 በላይ አምራች ኩባንያዎችን በውስጡ የያዘ ሲሆን በኢትዮጵያ ካሉ ኢንዱስትሪ ፓርኮችም ቀደምት ከሚባሉት የሚጠቀስ ነው፡፡

ምንጭ፡ ደ.ሬ.ቴ.ድ

Want your organization to be the top-listed Government Service in Awassa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address

Awassa
Other Government Websites in Awassa (show all)