Soddo Zuria Wereda Health Office

Soddo Zuria Woreda Health Office is governmental Sector which woks to promote Health & prevent disea

Photos from Soddo Zuria Wereda Health Office's post 07/08/2021

እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን!
⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️⌛️
የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ጤና ጥ/ጽ/ቤት በ2013 ዕቅድ አፈጻጸም በዞኑ ዉስጥ ካሉት ወረዳዎች 3ኛ ደረጃ በመዉጣቱ የዕዉቅና ሴርቴፍኬትና ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡
የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ጤና ጥ/ጽ/ቤት መከላከልን መሠረት ያደረገዉን የጤና ፖሊሲ ለመፈጻም ለትተቀን እየሠራ መሆኑ ና የህክምና አገ/ሎት ጥራትና ፍትሐዊነትን ለማሻሻል፣ ህብረተሰብን የጤና አገ/ሎት ተጠቃሚ ለማድረግ የማዐጤመ አባል እንዲሆኑ ማድረግ፣ ሞዴል ቀበሌ መፍጠር፣ የእናቶችና ህጻናት ጤና መሻሻል ወ.ዘ.ተ ዙሪያ ሰፊ ሥራዎችን መሥራቱ ይታወቃል፡፡
በመሆኑም የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ በአጠቃላይ ጤና ሥራ ዙሪያ ባዘጋጀዉ መመዘኛ መስፈርት ተመዝኖ በዞኑ ዉስጥ ካሉ ወረዳዎች መካከል በ3ኛ ደረጃ በመዉጣቱ የዕዉቅና ሴርቴፍኬት ፣ ዋንጫ እና ደስክቶፕ ኮሚፒዉተር ተሸላሚ ሆኗል፡፡ በተጨማሪ በ2013 ዓ.ም የኮቪድ 19 በሽታ መከላከል ዙሪያ ለሠራዉ አኩሪ ተግባር የዕዉቅና ሴርቴፍኬት ተበርክቶለታል፡፡
ይህ የዕዉቅና ና ሽልማት ለ2014 ዓ.ም ካሉበት ደረጃ ለማሻሻልና ህብረተሰብን ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ እጅግ የሚያነሳሳ እንደሆነ ና ጤና ተቋማትም ለቀጣይ ተሸላሚ ለመሆን ቁርጠኝነታቸዉንና ቁጭታቸዉን ገልጸዋል፡፡
በዋናነት ህብረተሰባችንን ተጠቃሚ ለማድረግ ሞዴል ጤና ተቋማትን ፣ ሞዴል ትም/ቤትን፣ ሞዴል ቀበሌን፣ ሞዴል ወረዳ ለመፍጠር ካሁኑኑ ወደ ተግባር በመግባት ዉጤት ለማስመዝገብ ትኩረት እንደሚሰጡም ገልጸዋል፡፡
በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን!

Photos from Soddo Zuria Wereda Health Office's post 29/04/2021

የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ጤና ጥ/ጽ/ቤት የ2013 የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በማስመልከት በወረዳ ዉስጥ ላሉ ወላጅ አጥ ህጻናትና ቫይረሱ በደማቸዉ ዉስጥ ላሉባቸዉ ወገኖች የእህል ድጋፍ አድርጓል፡፡
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
በዓሉን በማስመልከት አጠቃላይ 86 ሰዎች እያንዳንዳቸዉ 25 ኪ.ግ የበቆሎ እህል ድጋፍ ያገኙ ሲሆን ከእነሱ 60 ወላጅ አጥና 26 ቫይረሱ በደማቸዉ ዉስጥ ያሉባቸዉ ወጌኖች ናቸዉ፡፡
በቦታዉ የተገኙ ባለድርሻ አካላትየጤና ጥ/ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ጳዉሎስ ሙሴ፣ የወረዳዉ ሴቶች ወጣቶችና ህጻናት ጉ/ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ወ/ሪት ዝናሽ በቀለ፣የጽ/ቤታችን የኤች አይ ቪ ዘርፈ ብዙ ቅኝት ና ምላሽ ዳይሬክቶሬት ቡድን መሪ አቶ ሀብታሙ ብርሃኑና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ነዉ፡፡

Photos from Soddo Zuria Woreda Health Office/ሶዶ ዙሪያ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት's post 09/04/2021
Photos from Ministry of Health,Ethiopia's post 02/04/2021
Photos from Lia Tadesse, Minister of Health's post 01/04/2021
31/03/2021
Photos from Wolayta Zone Health Department /ወላይታ ዞን ጤና መምሪያ's post 30/03/2021
Photos from Soddo Zuria Wereda Health Office's post 25/03/2021

የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ጠ/ጥ/ጽ/ቤት የዚጋ ቦርኮሼ ቀበሌን በ18ቱ ጤና ኤክስተንሽን ፓኬጅ ሞዴል አድርጎ ለማስመረቅ በዞን ጤና መምሪያ ቨርፍኬሽን ቲም ቨርፋይ ተደርጎ የታዩ ጥቅት ክፍተቶች ታርመው መመረቅ እንደሚችል ተወስኗል።

22/03/2021

መጋቢት 13/2013

በኢትዮጵያ በቲቢ ምክንያት በየቀኑ 57 ሰዎች ይሞታሉ፡- የጤና ሚኒስቴር
****************

የጤና ሚኒስቴር በቲቢ በሽታ ምክንያት በኢትዮጵያ በየቀኑ 57 ሰዎች በየሰአቱ ደግሞ 2 ሰዎች ህይወታቸውን እንደሚያጡ አስታወቀ።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በቲቢ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር ዙሪያ የተሰሩ ስራዎች አበረታች ውጤቶች የታዩ ቢሆንም አሁንም ትኩረት የሚሹ ችግሮች መኖራቸውን ገልጿል።

በማሳያነትም የቲቪ በሽታ ይገኝባቸዋል ተብለው ከሚታሰቡ ሰዎች 29 በመቶው ወደ ህክምና ተቋማት አለመምጣታቸውንና የቲቢ መድሀኒቶችን የተላመዱ ተዋህስያን መፈጠርና መዛመቱን ገልጿል።

የዓለም የቲቢ ቀን በዓለም ለ39ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ24ኛ ጊዜ እየታሰበ ይገኛል።

18/03/2021

የዛሬው የኮሮና ቫይረስ ሁኔታ መግለጫ እስከዛሬ ከታየው ከፍተኛውን የስርጭት መጠን 25% positive rate ያሳየ ነው::

Photos from Soddo Zuria Wereda Health Office's post 17/03/2021

የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ጤና ጥ/ጽ/ቤት በላሾ ከተማ ቀበሌ ሞዴል ቬርፍኬሽን ተደርጎ በታዩ ክፍተቶች ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር በጥልቀት ተወያይቶ በአጭር ጊዜ ተሻሽሎ በዞን ቬርፍኬሽን ቲም እንደሚታይ ተቀምጧል።

Photos from Soddo Zuria Wereda Health Office's post 17/03/2021

የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት የሞዴል ቀበሌ ቨርፍኬሽን በወረዳ ደረጃ የላሾ ከተማን ቨርፋይ በማድረግ በተለዩ ክፍተቶች ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደርጎ በአጭር ቀናት ውስጥ ተሻሽሎ የዞን ቨርፍኬሽን ቲም መጥቶ እንደሚጣራ በመስማማት ውይይቱ ተጠናቅቋል።

የኮሮና ወረርሽኝ ከአንድ አመት በኋላ በአፍሪካ | DW | 16.03.2021 16/03/2021

የኮሮና ወረርሽኝ ከአንድ አመት በኋላ በአፍሪካ | DW | 16.03.2021 ከአንድ አመት በፊት መጋቢት 2 ቀን 2012 ዓ.ም. የዓለም ጤና ድርጅት ኮሮና ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ሆኗል ብሎ ሲያውጅ በአፍሪካ በተሕዋሲው የተያዙ ሰዎች ቁጥር 47 ብቻ ነበር። ከአንድ አመት በኋ.....

Photos from Wolaita S**o University's post 14/03/2021
14/03/2021

ዳግም ትኩረት ለኮቪድ -19

በዓለም አቀፍ ደረጃ ስጋት የነበረው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ኢትዮጵያ ላይ ልክ የዛሬ አመት በዚህ ቀን አንድ ብሎ አሁን ያለበት ደረጃ ላይ ደርሷል።

የጤና ሚኒስትር ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች እና ከማህበረሰብ ጋር በመቀናጀት ወረርሽኙ የከፋ ቀውስ እንዳያስከትል የቅድመ መከላከል እና የድህረ መከላከል ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል፤ በመስራት ላይም ይገኛል።

በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከገባ አንድ ዓመቱን ባስቆጠረበት ዕለት የኮቪድ-19 ቫይረስ ክትባትንም በዛሬው ቀን መስጠት ጀምራለች። ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ቫይረስ የተገኘበት ግለሰብ የ48 አመት የጃፓናዊ ዜግነት ያለው ሲሆን ከቡርኪና ፋሶ አገር የጉዞ ታሪክ የነበረው እንደሆነ ይታወሳል፡፡በኢትዮጵያ ለ 2‚214‚180 ግለሰቦች የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 172‚ 571 ግለሰቦች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ 141‚195 ግለሰቦች ያገገሙ ሲሆን የ2‚510 ግለሰቦች በቫይረሱ ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል የሚገቡ ግለሰቦች ቁጥርም እየጨመረ የሚገኝ ሲሆን፤እስከ ትላንትናው እለት ብቻ 454 ግለሰቦች በፅኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ ይገኛሉ፡፡ኮቪድ-19 ወደ ኢትዮጵያ ከገባ እለት ጀምሮ ይሄ ቁጥር ከፍተኛ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ወደ ኮቪድ- 19 የህክምና ማዕከል ከሚገቡት 100 ግለሰቦች 61 የሚሆኑት በተለያየ መጠን ኦክስጅን የሚያስፈልጋቸው ሲሆን፤ በዛሬው እለት በደረሰን መረጃ ብቻ 7 ያህል ግለሰቦች ሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መሳሪያ በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ።

ከጊዜ ወደ ጊዜ የሕብረተሰቡን መዘናጋት እና የመከላከያ መንገዶችን በአግባቡ አለመተግበር ተከትሎ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በሀገሪቱ በሁሉም ክልሎች አስደንጋጭ እና አስከፊ በሆነ መንገድ በወረርሽኙ ስዎች እየተያዙ እና ህይወታቸው እያለፈ ይገኛል። የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የሚያስከትለው የተለያዩ ማሕበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውሶች እየጨመረ ስለመጣ ችላ ሳንል የመከላከያ መንገዶችን በአግባቡ በመተግበር ልንከላከል ይገባል።

የኮሮና ቫይረስ በአገራችን ከተከሰተበት በአንድ አመት በዚህ ዕለት የኮቪድ 19 ክትባት ይበልጥ ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን በመለየት የጤና ባለሙያዎችና ሰራተኞች፣ እድሜያቸው የገፉ እና ተጓዳኝ ህመም ያላቸው እንዲሁም ሌሎች ለቫይረሱ ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ክትባቱን እንዲያገኙ ደረጃ በደረጃ ለመከተብ መርሀግብር ተዘጋጅቶ ስራ መጀመሩ ትልቅ እምርታ ሲሆን ክትባቱን ለሁሉም የማህበረስብ ክፍል ማዳረስ የማይቻል መሆኑን በመገንዘብ የኮቪድ 19 የመከላከያ መንገዶችን ተግራዊ ልናደርግ ይገባል፡፡

የጤና ሚኒወቴር እና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ኮቪድ-19 በኢትዮጵያ የተከሰተበትን አንድ አመት በምናስታውስበት እለት ለኮቪድ-19 መከላከል እና ቁጥጥር የበኩላቸውን ሲያበረክቱ የነበረውን ሁሉንም የማህበረሰብ አባላት፣ አጋር ድርጅቶች፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፤ የሐይማኖት ተቋማት፣ ሲቪክ ማህበራት፤ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፤ የጤና ባለሙያዎች፤ መምህራንና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ምስጋና እያቀረብን፤ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በተለይ ባለፉት ሁለት ወራት የስርጭት አቅሙን አጠናክሮ ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል የሚገቡ ፤ በቫይረሱ ህይወታቸውን የሚያጡ ግለሰቦች ቁጥር እየጨመረ ይገኛል፡፡ ስለሆነም ከዚህ የከፋ ማሕበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውሶችን ሳያስከትል መጀመሪያ ላይ እንደነበረው ሁሉም የሕብረተሰብ ክፍል የጥንቃቄ እና የመከላከያ መንገዶችን በአግባቡ እንዲተገብር ኮቪድ-19 ከዚ በላይ ዋጋ ሳያስከፍለን ቀድመን እንድንጠነቀቅ የጤና ሚኒስቴር ጥሪውን ያቀርባል።

የደቡብ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ

13/03/2021

∆ ፕ/ር ታከለ ታደሰ አዳፍሬ (የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት)-በዛሬው እለት የኮቪድ ክትባት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ ተገኝተው ካስተላለፉት መልዕክት የተወሰደ👇

"በዛሬው እለት ከደቡብ ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር በተዘጋጀው እና በዩኒቨርሲቲው ኦቶና ህክምና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በተካሄደው የኮቪድ-19 በሽታ መከላከያ ክትባት የማስጀመሪያ መርሐ ግብር ላይ ተግኝተን የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን የመጀመሪያውን ዙር ክትባት ወስደናል።"

"ይህ ክትባት በሳይንሳዊ ጥናትና ምርምር ተፈትሾ በሽታውን የመከላከል አቅሙ ተረጋግጦ እንዲሰጥ ቢወሰንም፤ በመጀመሪያው ዙር ክትባቱን ቀድመው የሚወስዱት ለበሽታው ተጋላጭነት ያላቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች እና የጤና ችግር ውስጥ የሚገኙ የህብረተሠብ ክፍሎች መሆናቸው ተገልጿል።"

"በሽታው እንደ ወረርሽኝ የሚያስከትለው ጉዳት ከፍተኛ ነውና ሁላችንም መከላከሉ ላይ ትኩረት በማድረግ እንደከዚህ ቀደምት ማስክ በማድረግ፣ አካላዊ እርቀት በመጠበቅ እንዲሁም ባለመጨባበጥና እጅን አዘውትሮ በመታጠብ የኮቪድ በሽታን ልንከላከል ይገባል።"

"ውድ የሀገራችን ሕዝቦች ኮሮናን በመከላከል በሀገራችን የተጀመረው ፈጣን ልማት እንዲረጋገጥ ሁላችንም በየተሰማራንበት የሥራ መስክ ለውጤታማነት መስራት ይጠበቅብናል። በዩኒቨርሲቲያችንም ኮቪድን በመካላከል ሠላማዊ መማር ማስተማርን ለማረጋገጥ የጀመርነውን ስራ እጅ ለእጅ ተያይዘን ዳር እንደምናደርሰው እምነቴ ጽኑ ነው። ፈጣሪ ሀገራችንንና ሕዝባችንን ይባርክ!!"🙏🙏

Photos from SNNP Prosperity Party - ብልፅግና's post 13/03/2021
Photos from Ethiopian News Agency's post 12/03/2021
11/03/2021

የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና በሰላም ተጠናቀቀ
🚹🚺🚹🚺🚹🚺🚹🚺🚹🚺🚹🚺
በኮሮና ምክያንት ተራዝሞ የነበረው የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና በሰላም ተጠናቀቀ። እንደ ሶዶ ዙሪያ ወረዳ በመዋቅራችን ዉስጥ ባሉ መሰናዶ ትም/ት ቤቶች ፈተናዉ በሰላም ተጀምሮ በሰላም መጠናቀቁን የሶዶ ዙሪያ ትም/ት ቤቶች ጽ/ቤት አስታወቀ።
ለሁሉም ተፈታኞች መልካም ውጤት እንዲሆንላቸው የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ዋና አስተዳደር መልካም ምኞቱን ይገልጻል።

Photos from Soddo Zuria Adminstration Office's post 10/03/2021
Photos from Soddo Zuria Wereda Health Office's post 10/03/2021

የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ጤ/ጥ/ጽ/ቤት የሴክተሩን የ2013 ዓ.ም. የ7 ወር ዕቅድ ክንውን አየገመገመ ይገኛል። በስብሰባው ሁሉም ጤና ኤክስተንሽ ሠራተኞች፣ የጤና ጣቢያ ሃላፊዎች፣ የጤና ጣቢያ ጤና ኬላ ትስስር ፎካሎች ፣ የጤና ጣቢያ የላቦራቶሪ ባለሙያዎች፣ የጤና ጣቢያ ክትባት ፎካሎች፣ የጽ/ቤት ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

10/03/2021

የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ጤና ጥ/ጽ/ቤት የሴክተሩ የ2013 ዓ.ም የ7 ወር ዕቅድ ክንዉን ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት እየገመገመ ይገኛል፡፡

የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ጤና ጥ/ጽ/ቤት የሴክተሩ የ2013 ዓ.ም የ7 ወር ዕቅድ ክንዉን ሁሉም ባለድርሻ አካላት ማለት ሁሉም የጤና ኤክስተንሽን ሠራተኞች፣ የጤና ጣቢያ ኃላፊዎች፣ የጤና ጣቢያ ጤና ኬላ ትስስር ፎካሎች፣ የጤና ጣቢያ የላቦራቶሪ ባለሙያዎች ፣ የጤና ጣቢያ የክትባት ፎካሎች፣ የጽ/ቤት ባለሙያዎች ተሳታፊዎች ናቸዉ፡፡
በስብሰባዉ ላይ የሚቀርቡ ሰነዶች፡-
1. የ7 ወር ዕቅድ ክንዉን ግምገማ ሰነድ
2. የክትባት የጥራት ማሻሻያ ሰነድ
3. በወባ መከላከልና መቆጣጠር ዙሪያ የተዘጋጁ ሰነዶች ናቸዉ፡፡
መክፈቻ ንግግር ያደረጉ የጤ/ጥ/ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ጳዉሎስ ሙሴ መሻሻል ያለባቸዉን ተግባራት ጠቅሰዉ ሁሉም ባለሙያዎች የድርጊት መርሃ ግብር አዘጋጅተዉ ማሻሻል እንዳለባቸዉ አስቀምጠዋል፡፡
የሶዶ ዙሪያ ወረዳ አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ኃይሌ ስላስ ሁሉም ባለሙያ በባለቤትነት መሥራት እንዳለባቸዉና በቀበሌ ደረጃም ያሉ የጤና ልማት ሠራዊት Fanctional በማድረግ ቀበሊያትን ሞዴል ማድረግ እንዳለባቸዉ በአጽንኦት አስቀምጠዋል፡፡ የመረጃ ሥርዓት መጠናከር እንዳለበት ጨምረዉም አስቀምጠዋል፡፡

Want your organization to be the top-listed Government Service in Sodo?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address

S**o
Other Government Organizations in S**o (show all)