የቀድሞ የናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ተማሪዎች ማህበር /Nazareth St. Joseph Alumni Association

Nazareth St .Joseph School Alumni Association

Photos from የቀድሞ የናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ተማሪዎች ማህበር  /Nazareth St. Joseph Alumni Association's post 05/05/2024

መልካም የትንሣኤ በዓል ይሁንላችሁ !!!

Photos from የቀድሞ የናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ተማሪዎች ማህበር  /Nazareth St. Joseph Alumni Association's post 13/04/2024

ሱራፌል ስዩም እስከ 1972 ዓ.ም የቀድሞ የናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ተማሪ ነበር። 1972 ዓ.ም 5ኛ ክፍል ነበር ። በተለይ የ1979 ዓ.ም ባቾች በደንብ ያስታውሱታል። በአዳማ የእግር ኳስ ክለብ ውስጥም ጉልህ ሚና ነበረው ተወልዶ ባደገባት አዳማ/ናዝሬትም በስፖርቱ በተለይም በእግር ኳሱ ዘርፍ አቅሙ የቻለውን አስተዋፅኦ በማድረግ የራሱን ታሪካዊ አሻራ አኑሯል። ሱራፌል ስዩም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በገጠመው የኩላሊት ህመም በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የህክምና ጥረቶችን ያደረገ ቢሆንም ጤንነቱ ወደነበረበት መመለስ ባለመቻሉ እስከወዲያኛው አሽልቧል ። የቅዱስ ዮሴፍ ካቶሊክ ት/ቤት አዳማ/ናዝሬት የቀድሞ ተማሪዎች ማህበር በሱራፌል ስዮም ዜና ዕረፍት የተሰማውን ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰቡ ፣ አንደኛ ደረጃ አብረውት ለተማሩ፣ ለቀድሞ መምህራኖቹና ለወዳጅ ዘመዶቹ ፣እንዲሁም በተጫዋችነት ዘመኑ አብረውት ለሰሩ የአዳማ ከተማ መስተዳድር ወጣቶችና ስፖርት ባልደረቦች፣ ደጋፊና አድናቂዎቹ ለነበሩት ሁሉ መፅናናትን ይመኛል።
መልካም ዕረፍት !!

Photos from የቀድሞ የናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ተማሪዎች ማህበር  /Nazareth St. Joseph Alumni Association's post 09/04/2024

ዛሬ በተለያየ የህይወት መስመር ላይ ብንሆንም በተማሪነት ዘመናችን አብረውን ለተማሩ ሙስሊም እህትና ወንድሞቻችን የቀድሞ ተማሪዎች መምህራኖቻችን፣ አሁንም በመማር ላይ ያላችሁ ሙስሊም የሴንጆ ተማሪዎቸ እንዲሁም ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1445ኛው የኢድ-አልፈጥር በዓል በሠላም አደረሣችሁ !!! በዓሉ የሠላም ፣የደሰታና የፍቅር እንዲሆንላችሁ የቅዱስ ዮሴፍ ካቶሊክ ት/ቤት አዳማ/ናዝሬት የቀድሞ ተማሪዎች ማህበር መልካም ምኞቱን ይገልፃል።
ኢድ ሙባረክ !!!

Photos from የቀድሞ የናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ተማሪዎች ማህበር  /Nazareth St. Joseph Alumni Association's post 15/03/2024

ወንድም ዮሴፍ ልባብ (Bro. Yoseph Lebab) በ1976 እና በ1977 ዓ.ም በቅዱስ ዮሴፍ ካቶሊክ ት/ቤት አዳማ/ናዝሬት የእንግሊዘኛ ቋንቋ መምህር ነበር። በተለይ በእነዚያ ዓመታት የ7 እና 8ኛ ክፍል ተማሪ የነበሩ ጠንቅቀው ያውቁታል ፣ ጎበዝ መምህርም እንደነበረ ምስክርነታቸውን ይሰጡለታል ።
የቀድሞ መምህር ወንድም ዮሴፍ ልባብ ከቀናት በፊት ይኖርበት በነበረው አሜሪካን ሀገር ህይወቱ ማለፉንና የቀብር ስነ-ስርዓቱም በዛው በሀገረ አሜሪካ ተፈፅሟል። የቀድሞ የናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ተማሪዎች ማህበርም በቀድሞ መምህራችን ብራዘር ዮሴፍ ህልፈት የተሰማውን ሀዘን እየገለፅ ለወዳጅ ዘመድ ፣ ለቤተሰቡ ፣ ለቀድሞ ተማሪዎቹና አብረውት ለአስተማሩ የቀድሞ መምህራንና ለት/ቤቱ ማህበረሰብ መፅናናትን ይመኛል።

Photos from የቀድሞ የናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ተማሪዎች ማህበር  /Nazareth St. Joseph Alumni Association's post 08/03/2024

የቅዱስ ዮሴፍ ካቶሊክ ት/ቤት አዳማ/ናዝሬት ..በ1982 ዓ.ም በንግድ ሥራ የትምህርት ዘርፍ ካስመረቃቸው ተማሪዎች መካከል አንዷ የነበረችው እመቤት ይርጋ በገጠማት የጤና እክል በህክምና ስትረዳ ብትቆይም አርብ የካቲት 29/2016 ዓ.ም ከዚህ ዓለም ድካም አርፋለች ። የቀድሞ የናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ተማሪዎች ማህበርም በእህታች እመቤት ይርጋ ዜና ዕረፍት የተሰማውን ሀዘን እየገለፅ ለቤተሰቧ ለወዳጅ ዘመዶቿ፣ አብረዋት ለተማሩ የቀድሞ ተማሪዎች ጓደኞቿ ና ለቀድሞ መምህራኖቿ መፅናናትን ይመኛል !!!
መልካም ዕረፍት !!!

Photos from የቀድሞ የናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ተማሪዎች ማህበር  /Nazareth St. Joseph Alumni Association's post 05/03/2024

ONE FOR ALL ALL FOR ONE
የ1988ዓ ዓ.ም ባች ነው የቅዱስ ዮሴፍ ካቶሊክ ት/ቤት አዳማ/ናዝሬት !! ወንድማችን ተስፋዬ ፍቅሩ ይባላል። በደረሰበት ችግርና ህመም የሌሎችን ድጋፍና እርዳታ ይፈልጋል። ቀደም ሲል ቀና ልብ ያላቸው የቀድሞ የሴንጆ ተማሪዎች ድጋፍ እየተደረገለት የቆየ ቢሆንም አሁንም የጤናውና ያለበት ሁኔታ የሌሎችን ድጋፍና ዕርዳታ የሚሻ በመሆኑ አብራችሁ የተማራችሁ የቀድሞ ጓደኞቹ ፣ የቀድሞ የሴንጆ ተማሪዎች፣ የመስጠት ልብ ያላችሁ ቅን ወገኖች የበኩላችን በማድረግ እንድትደግፉት ፣በፀሎትና በዱአም እንድታስቡት ወገናዊ ጥሪው ይድረሣችሁ።
መርዳት ለምትፈልጉ
ተስፋዬ ፍቅሩ
0920366010
Commercial Bank of Eth.
1000256086038
የሚሰጡ እጆች የተባረኩ ናቸው !!

Photos from የቀድሞ የናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ተማሪዎች ማህበር  /Nazareth St. Joseph Alumni Association's post 29/02/2024

የቀድሞ የናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ት/ቤት ተማሪ ነው ። የ1982 ዓ.ም ባች ...ፎአድ አህመድ ። ዛሬ የካቲት 21/2016 ዓ.ም በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል ። የቀድሞ የናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ተማሪዎች ማህበር በወንድማችን ህልፈት የተሰማውን ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቹ ፣ አብረውት ለተማሩ የቀድሞ ተማሪዎች አብሮ አደግ ጓደኞቹና ለቀድሞ መምህራኖቹ መፅናናትን ይመኛል።
መልካም ዕረፍት .!!!

05/01/2024

አርብ ታህሣሥልዩነትምን016 ዓ.ም ..ጠዋት ላይ ከቀድሞ ት/ቤታችን ሴንጆ ቅጥር ግቢ ተገኝተን ነበር። በዕለቱ የነበረው የተማሪዎች የገና በዓል ዋዜማ ፕሮግራም የጥንት የተማሪነት ዘመናችንን ማስታወስ ብቻ ሣይሆን የዘመንና የትውልድ ልዩነትንም የተመለከትንበት ዝግጅት ነበር። በተማሪነት ዘመናችን የዘመርነውን
ቤተልሔም ዛሬ ለሊት
ተከባለች በታምራት
አምላክ ወሰን ተወልዶላት.....እና

የምሥራቹ ቃል በምድር ተሰማ
በከብቶች በረት ውስጥ ቤተልሔም ከተማ....
የሚለውን ዝማሬ ለማድመጥ ብንጓጓም የለም ...ያም ቢሆን ልጅነት ተማሪነት ደስ ይላል...በገና ዋዜማ ፕሮግራማቸው እጅግ ተደስተዋል ..የእነሱም ደስታ ተጋብቶብን እኛንም ደስ አሰኝቶናል.....እናም ለቀድሞ የሴንጆ ተማሪዎች፣ለቀድሞ መምህራኖቻችን፣ለአሁን ተማሪዎችና ለት/ቤቱ ማህበረሰብ እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሠላም አደረሣችሁ !!! መልካም የገና በዓል ይሁንላችሁ !! እያለ የቀድሞ የናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ተማሪዎች ማህበር መልካም ምኞቱን ይገልፃል ።
HAPPY CHRISTMAS !!!!

Photos from የቀድሞ የናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ተማሪዎች ማህበር  /Nazareth St. Joseph Alumni Association's post 21/10/2023

የ1983 ዓ.ም ባች ነው ኢንጂነር ስለሞን ጌታቸው የቅዱስ ዮሴፍ ካቶሊክ ት/ቤት አዳማ/ናዝሬት የቀድሞ ተማሪ ነው። ከአዲስ አበባ ዮኒቨርስቲ በመካኒካል ኢንጂነሪግ ተመርቋል። በቅድሚያ ወደ ጀርመን ከዛም ኑሮውን ወዳደረገባት እንግሊዝ ከማምራቱ በፊት በወንጃ ስኳር በፋብሪካና በሬስ ኢንጂነሪንግ በሙያው አገልግሏል። ባለትዳርና የአንድ ሴት ልጅ አባት የነበረው ኢ/ር ስለሞን ጌታቸው በገጠመው የጤና እክል በሚኖርበት እንግሊዝ ሀገር ሲረዳ ቆይቶ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። የቀብር ሥነ ሥርዓቱም ማክሰኞ ጥቅምት 13/2016 ---ኦክቶቨር 24/2023 ዓ.ም ለዓመታት በኖረባት እንግሊዝ --ማንችስተር ይፈፀማል። የቅዱስ ዮሴፍ ት/ቤት አዳማ/ናዝሬት የቀድሞ ተማሪዎች ማህበር በኢን/ር. ስለሞን ጌታቸው ህልፈት የተሰማውን ሀዘን እየገለፅ ለባለቤቱ ራሄል መኮንን ፣ ለልጁ ኤልሣቤጥ ስለሞን ፣ ለወንድምና እህቶቹ እንዲሁም ቀድሞ አብረው ለተማሩት ጓደኞቹ መፅናናትን ፣ ለሟች ወንድማችንም መልካም ዕረፍትን ይመኛል።

Photos from የቀድሞ የናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ተማሪዎች ማህበር  /Nazareth St. Joseph Alumni Association's post 10/10/2023

ቅዳሜ መስከረም 19/2016 ዓ.ም የቅዱስ ዮሴፍ ካቶሊክ ት/ቤት - አዳማ የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተማሪዎቹን ሲያስመርቅ ከተመራቂዎቹ አንዱ በሆነው ብሩክ ብርሀኑ ለዛች ቀን መድረስ ደስ ብሎን ደስታችንን ገልፀናል ። ዛሬ ደግሞ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ሲገለፅ እጥፍ ደስታ ተሰምቶናል ፣ ተማሪ ብሩክ ከት/ቤቱ ሴንጆ ሁለተኛ የሆነውን ውጤት 596 በማምጣት ለቤተሰቡና ለኛም ለቅዱስ ዮሴፍ ት/ቤት የቀድሞ ተማሪዎች ማህበር ኩራት ስለሆንከን እጅግ ደስ ብሎናል እንኳን ደስ አለህ !!
ONE FOR ALL ALL FOR ONE!

Photos from የቀድሞ የናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ተማሪዎች ማህበር  /Nazareth St. Joseph Alumni Association's post 30/09/2023

ተማሪ ብሩክ ብርሀኑ እንኳን ደስ ያለህ !!
የቅዱስ ዮሴፍ ካቶሊክ ት/ቤት አዳማ ..ዛሬ ቅዳሜ መስከረም 19/2016 ዓ.ም በሀይሌ ሪዞርት የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተማሪዎቹን አስመርቋል። ይህቺ ቀን ለተማሪ ብሩክ፣ አብረውት ለተማሩና ለተመረቁት እንዲሁም ለወላጆቻቸው ብቻ ሣይሆን ለቅዱስ ዮሴፍ ት/ቤት የቀድሞ ተማሪዎች ማህበርና አባላትም ልዩ ቀን ናት። ትውልድ ከሚቀረፅበት መንገድ አንዱ በሆነው ወገንን የማስተማር ሂደት የድርሻውን ማበርከትና ውጤቱንም ማየት መቻሉ ታሪካዊ ሀላፊነትን መወጣት ነውና በድጋሚ እንኳን ደስ ያላችሁ !!
ለተማሪ ብሩክና አብረውት ለተማሩ የዘንድሮ የሴንጆ ተመራቂዎች
CONGRATULATION !!
እንኳን ደሰ ያላችሁ !!!
ONE FOR ALL ALL FOR ONE !!

Photos from የቀድሞ የናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ተማሪዎች ማህበር  /Nazareth St. Joseph Alumni Association's post 23/09/2023

ONE FOR ALL ALL FOR ONE
በሚለው የቀድሞ የቅዱስ ዮሴፍ ት/ቤት ተማሪዎች ማህበር መሪ ቃል ጥላ ሥር "እኔም ወገኔን አሥተምራለሁ " በሚል ላለፉት ዓመታት ሲካሄድ የነበረው የበጎ ተግባር እንቅስቃሴ ...ሁለት ተማሪዎችን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና እንዲፈተኑ ያደረገ ሲሆን ዘንድሮም ይሄው የድጋፍ እንቅስቃሴ በመቀጠል ቅዳሜ መስከረም 12/2016 ዓ.ም የበጎ አድራጎት ልገሣው የትምህርት ቁሣቁስና የንፀህና መጠበቂያ ድጋፍ ለሚሹት በመስጠት ተከናውኗል ። ይህን መስሉ የመስጠትና የማካፈል መልካም ተግባር ተጠናክሮ ሊቀጥል የሚገባው ሰናይ ተግባር መሆኑን በፅኑ እናምናለን !
የሚሰጡ እጆች የተባረኩ ናቸው !!
እንቀጥላለን !!!!
ONE FOR ALL ALLFOR ONE!

Photos from የቀድሞ የናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ተማሪዎች ማህበር  /Nazareth St. Joseph Alumni Association's post 12/09/2023

ለቀድሞ የናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ተማሪዎች ፣ ለቀድሞ መምህራንና የት/ቤቱ ማህበረሰብ በሙሉ እንኳን ለ2016 ዓ.ም አዲስ ዓመት በሠላም አደረሣችሁ !!

Photos from የቀድሞ የናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ተማሪዎች ማህበር  /Nazareth St. Joseph Alumni Association's post 11/07/2023

ለNBC ETHIOPIA
የቅዱስ ዮሴፍ ካቶሊክ ት/ቤት -አዳማ የቀድሞ ተማሪዎች የመገናኛ ፕሮግራም አዘጋጅተው ፣ ለቀድሞ መምህራኖቻቸው የዕውቅናና የምሥጋና ሥጦታ ከማበርከት ባሻገር ይበል የሚያሰኝ ተግባር በዕለቱ ሲከውኑ ውለዋል ። ይህንን በአርያነት የሚጠቀሰ ተግባር ለሌሎችም ምሣሌ እንዲሆን ሚዲያቹ የፕሮግራም ሽፋን በመስጠት ለህዝብ እንዲደርስ በማድረጉ የቅ/ዮሴፍ ት/ቤት የቀድሞ ተማሪዎች ማህበር -አዳማ የተሰማውን ደስታ እየገለፀ በቀድሞ ተማሪዎች ሥም ምሥጋናውን ያቀርባል !!!
እ ና መ ሰ ግ ና ለ ን !!!

Photos from የቀድሞ የናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ተማሪዎች ማህበር  /Nazareth St. Joseph Alumni Association's post 06/07/2023

ብዙዎቹን ያስደሰተው የቀድሞ መምህራኖቻችንን ያስወደሰ፣የዕውቅናና የምሥጋና ሥጣታ ያስበረከተው የሰኔ25/2015ቱ የቅ/ዮሴፍ ካቶሊክ ት/ቤት የቀድሞ ተማሪዎች የመገናኛ ፕሮግራም
-ቅዳሜ ሀምሌ 1/2015 ከ7:00ሰዓት ጀምሮ በNBC ETHIOPIA TV
እሁድ ሀምሌ 2/2015 በFANA TV ፋና ቀለማት ከ7:00ጀምሮ የሚቀርብ በመሆኑ ፕሮግራሙን እንድትከታተሉ ከወዲሁ ለማሣወቅ እንወዳለን።
የቅ/ዮሴፍ የቀድሞ ተማሪዎች ማህበር

Photos from የቀድሞ የናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ተማሪዎች ማህበር  /Nazareth St. Joseph Alumni Association's post 02/07/2023

ሰኔ 25/2015 ልዮ ታሪካዊ ቀን ነበር በተለይ ለቅ/ዮሴፍ ካቶሊክ ት/ቤት አዳማ የቀድሞ ተማሪዎች ። ለበርካታ ዓመት የተለያዩ አብሮ አደግ ተማሪዎች የመገናኘት ፣ ትዝታቸውን የማውጋትና የመጨዋወት ሣይሆን ፣፣ ለዛሬው ማንነታቸው ትልቁን መሠረት የጣሉትን የዕውቀት አባት የሆኑ የቀድሞ መምህራንን እውና መስጠትና የማመስገንም ጭምር ነበር ። እጅግ ደማቅና ውብ ፕሮግራም ነበር ።

Photos from የቀድሞ የናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ተማሪዎች ማህበር  /Nazareth St. Joseph Alumni Association's post 27/06/2023

ለቀድሞ የቅዱስ ዮሴፍ ት/ቤት - አዳማ /ናዝሬት ሙስሊም እህት ወንድሞቻችን እንኳን ለኢድ አል አድሃ (አረፋ ) በዓል አደረሣችሁ እያለ የቀድሞ ተማሪዎች ማህበር መልካም ምኞቱን ሲገልፅ የሰኔ 25/2015 ዓም የመገናኛ ፕሮግራም አራት ቀን እንደቀረው በማስታወስም ጭምር ነው ።
መልካም በዓል !!
ሰኔ 25/2015 አይቀርም !!

Photos from የቀድሞ የናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ተማሪዎች ማህበር  /Nazareth St. Joseph Alumni Association's post 13/06/2023

19 ..ቀን ቀረው!!
የአሰራ አራት ዓመት የህይወት ምዕራፌ የሚነበበው ለዛሬው ማንነቴ ትልቁ መሠረት ከተጣለበት የናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ት/ቤት ሴንጆ ነው። በትዝታዬ ውስጥ ጎልቶ የሚታየው የልጅነት ዘመኔን ያጣጣምኩባት ፣ዕውቀት የገበየሁባት ፣ በግብረገብ የታነፅኩባት ፣ዛሬም ድረስ በፍቅር በአብሮነት የዘለቅን አብሮአደግ እህትና ወንድሞች ያፈራሁባት እናት ት/ቤቴ ሴንጆ ናት። ታዲያ ከበርካታ የመራራቅ ዓመታት በኋላ ያንን ጣፋጬን መልካም የተማሪነት ዘመን በትዝታ ለማውሣት ፣ ለባለውለተኛ መምህራኖቻችን ዕውቅናና ምሥጋና ለመቸርና ለተጨማሪ የተቀደሰ ዓላማ ሰኔ25/2015--July 2/2023 የቀድሞ የሴንጆ ተማሪዎች በሴንጆ ለመገናኘት የማይቀርበት ፕሮግራም አዘጋጅተዋል ። እናም ይህን 19ቀን የቀረውን ታሪካዊ ፕሮግራም ለመታደም ቀኑን በጉጉት እየጠበኩ ነው ።
በዕለቱ በሴንጆ ለመገኘት ወስኛለሁ
ሰኔ 25/ 2015-- July 2/ 2023
እኔ አልቀርም !!!

Photos from የቀድሞ የናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ተማሪዎች ማህበር  /Nazareth St. Joseph Alumni Association's post 05/06/2023

የዮኒቨርስቲ ትምህርቴን ጨርሴ በመምህርነት ወደሥራው ዓለም ስቀላቀል ማስተማር የጀመርኩት በቅዱስ ዮሴፍ ት/ቤት ነበር ናዝሬት--አዳማ። የዛሬ 35 ዓመት 1980ዓ.ም ። በአሁን ሰዓት በፕሮፌሰርነት ማዕረግ በመቀሌ ዮኒቨርስቲ በማስተማር ላይ እገኛለሁ። በሴንጆ በቆየሁባቸው ዓመታት በርካታ የዕውቀት ልጆችን አፍርቻለሁ። የሰኔ 25/2015--July 2/2023 የቀድሞ ተማሪዎችን የመገናኛ ፕሮግራም ስሰማ በዕለቱ ለመገኘት የወሰንኩት ምንም ሣላቅማማ ነው። ምክንያቱም ከሶስት አስርት አመታት በኋላ ለቁምነገር ከበቁ የቀድሞ ተማሪዎቼና እግዜአብሔር ፈቅዶ በህይወት ካሉ ጥቂት የቀድሞ መምህራን ባልደረቦቼ ጋር መገናኘትን የመሰለ ታላቅ ታሪካዊ ክስተት የለምና ማንኛውንም ዋጋ ከፍዬ ሰኔ25/2015---July 2/2023 ሴንጆ እገኛለሁ ። በፍፁም አይቀርም ።
ሰኔ25/2015--July 2/2023
እኔ አልቀርም !!!

Photos from የቀድሞ የናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ተማሪዎች ማህበር  /Nazareth St. Joseph Alumni Association's post 31/05/2023

ማምሻም ዕድሜ ነው ይሉትን አባባል አሰብኩት...የሰኔ 25/2015---July 2/ 2023 የሴንጆን ፕሮግራም ሰስማ።
መምህር ፍቅሩ ሽፈራው እባላለሁ በቅዱስ ዮሴፍ ካቶሊክ ት/ቤት አዳማ (ናዝሬት) ለአመታት አስተምሬያለሁ ፣ ብዙ የዕውቀት ልጆች ያፈራሁበት ፣ በርካታ የህይወት ገጠመኝ ያሣለፍኩበትም ነበር የሴንጆ ቆይታዬ ። ከአመታት በኋላ ዛሬ በጡረታ ዘመኔ ከቀድሞ ተማሪዎቼ ጋር ለመገናኘት ዕድል በር ከፍታልኛለች መስንበት ደጉ የቀድሞ የሴንጅ ተማሪዎች ሰኔ 25/2015--July-2/2023 የማይቀርበት ፕሮግራም አዘጋጅተዋል ለኔ ልዩና ትልቁ የህይወቴ አጋጣሚ ነውና ከዚህ ፕሮግራም በፍፁም አልቀርም !!
እኔ አልቀርም !!!

Photos from የቀድሞ የናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ተማሪዎች ማህበር  /Nazareth St. Joseph Alumni Association's post 26/05/2023

ከ1982ዎቹ መካከል እሽቱ ሀ/ወልድ ነኝ ። ዛሬ ለደረስኩበት ከፍተኛ ኃላፊነት የትናንት መሠረቴ ፣ በዕውቀት ያነፁኝና በግብረገብ የቀረፁኝ ት/ቤቴ ሴንጆና የቀድሞ መምህራኖቼ የአንበሣውን ድርሻ ይይዛሉ። እናም ለቀድሞ መምህራኖቼ ዕውቅናና ምስጋና ለመስጠት ፣ አብረውኝ ከተማሩ አብሮ አደግ ጓደኞቼ ጋር ናፍቆቴን ልወጣ ትዝታዬን ላወጋ ሰኔ 25/2015--July 2/2023 የተዘጋጀው ፕሮግራም በህይወት ዘመን የሚገኝ ድንቅ አጋጣሚ በመሆኑ በዕለቱ እኔ አልቀርም ።
ሰኔ 25/2015
እኔ አልቀርም !!

Photos from የቀድሞ የናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ተማሪዎች ማህበር  /Nazareth St. Joseph Alumni Association's post 12/05/2023

1988 ዓ.ም ..ነው ጥቁሩን ጋውን ለብሰን የተመረቅነውና ሴንጆን ተለይተን እኛም በተለያየ የኑሮ መስመር የተበታተነው ። መሰንበት ደግ ነው እንዲሉ ከ27 ዓመት በኋላ እውቀት ከገበየንባት ፣ በግብረገብ ከታነፅንባት እናት ት/ቤታችን ሴንጆ ሰኔ25/2015-- July2/2023 ለመገናኘት ቀን ተቆርጧል ። የቀድሞ መምህራኖቻችንን ለማግኘት ከሌሎች ባቾች ታላላቆቻችንና ታናናሾቻችን የቀድሞ ተማሪዎች ጋር ለመተዋወቅ ፣፣ትዝታዎቻችንን ማውጋት ብቻ ሣይሆን በቀጣይ ግንኙነታችንም ላይ ለመምከር ፣ በህይወት ዘመን የሚገኝ ታላቅ ዕድል በመሆኑ እኛ የ1988 ባቾች ሰኔ 25/2015--July 2/2023 ሴንጆ እንገኛለን።
እኛ አንቀርም !!!

11/05/2023

ላለፉት 38 ዓመታት በመምህርነት በቆየሁበትና ባስተማርኩበት ዘመን በርካታ የዕውቀት ልጆችን አፍርቻለሁ ። በተለያዬ ሙያና የሥራ መስክ ተሰማርተው ፣ኑሮአቸውን በሀገር ውሰጥና በውጭ ሀገራት አድርገው ይገኛሉ። ታዲያ ከበርካታ የመለያየት ዓመታት በኋላ ምንም ዓይነት እርቀት ሣይገድባቸው ሰኔ25/2015---July 2/2023 የቀድሞ የናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ተማሪዎች በቀድሞ ት/ቤታቸው ለመገናኘት የማይቀርበት ቀጠሮ ይዘዋል ። እኔም የቀድሞ ተማሪዎቼን ለማግኘት ዕለቱን ጓጉቼ እየጠበኩ ነው ። ሰኔ 25/2015--July 2/2023 አይቀርም ! የሴንጆ ጊቢ ዳግም በቀድሞ ተማሪዎቿ ትደምቃለች !!
ተማሪዎቼ እጠብቃችኋለሁ !!
እኔ አልቀርም !!!

27/04/2023

ሰኔ 30 አና ተማሪነት ልዮ ቁርኝት አላቸው ። ከየትኛውም የተማሪ ልብ ውስጥ የማይጠፋ ህያውነት የተላበሰ ...ዘንድሮ ግን ሰኔ 25/2015 ዓ.ም / July 2/ 2023/ በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ የሚኖሩ የቀድሞ የናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ተማሪዎች በቀድሞ ት/ቤታቸው ሊገናኙ ቀጠሮ ይዘዋል። በመሆኑም ለዓመታት የተለያዩ የቀድሞ ተማሪዎች የሚገናኙበት በርካታ ትዝታዎች የሚነሱበት ከተማሪነት በኋላ በህይወት ዘመንየሚገኝ ድንቅ አጋጣሚ በመሆኑ ይሄ ዕድል የትኛውም የቀድሞ ተማሪ ሊያመልጠው አይገባም በፕሮግራሙ መታደም ግድ ይላል። በመሆኑም ሁሉም የቀድሞ የሴንጆ ተማሪ እንዲገኝ ጥሪያችን ይድረሳችሁ። ቁም ነገርም ይመከርበታል ።
ሰኔ 25/2015--- July 2/2023

Photos from የቀድሞ የናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ተማሪዎች ማህበር  /Nazareth St. Joseph Alumni Association's post 20/04/2023

የቀድሞ የናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ተማሪዎች ማህበር ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ፣ ለቀድሞና ለአሁን ሙስሊም እህትና ወንድሞቻችን እንኳን ለ1444ኛው የኢድ አልፈጥር -- ረመዳን በዓል በሠላም አደረሣችሁ እያለ በዓሉ የሠላምና የደሰታ እንዲሆን መልካም ምኞቱን ይገልፃል ።
EID MUBARAK !!!

Photos from የቀድሞ የናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ተማሪዎች ማህበር  /Nazareth St. Joseph Alumni Association's post 15/04/2023

የቀድሞ የናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ተማሪዎች ማህበር እንኳን ለትንሣኤ የፋሲካ በዓል አደረሣችሁ እያለ ለመላው የክርስትና ዕምነት ተከታዮች ፣ ለቀድሞና ለአሁን ተማሪዎች ፣ እንዲሁም ለመምህራንና ለት/ቤቱ ማህበረሰብ በዓሉ የሠላምና የደስታ እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞቱን ይገልፃል ።
መልካም የፋሲካ በዓል !!!

Photos from የቀድሞ የናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ተማሪዎች ማህበር  /Nazareth St. Joseph Alumni Association's post 03/04/2023

የቀድሞ የናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ት/ቤት ተማሪ ነው ። የ1985 ዓ.ም ባች ፣ ዮናስ ዳንኤል ቫሩሽ ...ወንድማች ዮናስ ዳንኤል ቫሩሽን በድንገተኛ ህመም መጋቢት 25/2015 ዓ.ም በሞት አጥተነዋል ። አሣዛኙን የወንድማችንን ህልፈት የሰማነው በታላቅ ድንጋጤ ነው ፣ የቀድሞ የናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ተማሪዎች ማህበርም በወንድማችን ዮናስ ዳንኤል ቫሩሽ ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ፣ ለመላው ቤተሰቡ ፣ አብረውት ለተማሩ ለአብሮ አደግ ጓደኞቹ ፣ ለቀድሞ መምህራኖቹና ወዳጅ ዘመዶቹ መፅናናትን እንመኛለን።
መልካም ዕረፍት !!!!

Photos from የቀድሞ የናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ተማሪዎች ማህበር  /Nazareth St. Joseph Alumni Association's post 06/01/2023

በሀገር ውስጥና በመላው ዓለም ለምትገኙ የቀድሞ የናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ተማሪዎች ለቀድሞ መምህራንና አሁንም ላሉት የት/ቤቱ ማህበረሰብ እንኳን ለ2015
ዓ.ም የገና በዓል አደረሣችሁ እያለ በዓሉ የሠላም የደስታና የፍቅር እንዲሆንላችሁ የቀድሞ የናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ተማሪዎች ማህበር መልካም ምኞቱን ይገልፃል።
MERRY CHRISTMAS !!

Photos from የቀድሞ የናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ተማሪዎች ማህበር  /Nazareth St. Joseph Alumni Association's post 21/10/2022

የህይወት ምዕራፉ ተጠናቀቀ !
የብዙዎች የዕውቀት አባት የነበረውን የመምህር ሣሙኤል ከበደን ዜና ዕረፍት የሰማነው በታላቅ ድንጋጤ ነው ። በተማሪዎቹ ዘንድ ተወዳጅ የነበረው መምህሩ ከሃያ አመታት በላይ በቀድሞ የናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ት/ቤት በመምህርነት አገልግሏል ። በሽምግልና ዘመኑ በገጠመው አሰቸጋሪ የህይወት ፈተና በመቄዶኒያ የአረጋዊያን መርጃ ማዕከል ውስጥ የነበረው መምህር ሣሙኤል ከበደ ጥቅምት 8/2015 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተይቷል የቀብር ሥነ ሥርዓቱም በአያት ፀበል መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን ተፈፅሟል። የቀድሞ የናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ተማሪዎች ማህበር የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅ ለቀድሞ ተማሪዎቹ ፣ አብረውት በመምህርነት ላገለገሉ ወዳጆቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ ሁሉ መፅናናትን ይመኛል ።
መልካም ዕረፍት መምህር !!

Want your school to be the top-listed School/college in Adama?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Videos (show all)

አርብ ታህሣሥልዩነትምን016 ዓ.ም ..ጠዋት ላይ ከቀድሞ ት/ቤታችን ሴንጆ ቅጥር ግቢ  ተገኝተን ነበር።  በዕለቱ የነበረው የተማሪዎች የገና በዓል ዋዜማ ፕሮግራም  የጥንት የተማሪነት ዘመናች...

Category

Telephone

Website

Address


Picoke--Aboseto-buluko, Abebe Bikila Street
Adama
Other Schools in Adama (show all)
Kedirabuna Kedirabuna
Adama
Adama, 1000

Driver licence school Adama mm promotion kedirabunafacebook yutube instegetam telegerm imo facebook yuotube telegrok yuotube telegram okbarachuu nidanda'an

የሲቀላ ቀበሌ ታክስ ማዕከል የሲቀላ ቀበሌ ታክስ ማዕከል
Df
Adama

http://sikelataxadim.comአር

Ibn Abbas Training & Development Center Ibn Abbas Training & Development Center
Adama
Adama

Found by Abbas Ibrahim | Includes Quran lessons| Hadith of Prophet (saw)|and more courses

Simon Tesfaye Simon Tesfaye
Fichee
Adama, NO

Promo

Sena Yerosan School of Excellence Sena Yerosan School of Excellence
Ganda Hara & Bole
Adama

Sena Yerosan School provides quality education for all citizens.

Youtu.be/neeh5w1rxbw Youtu.be/neeh5w1rxbw
Saqalo
Adama, 7.46

Sami Sami
Gelan
Adama

School  life School life
Adama

Leyila mohammed

Homacho sabaa Homacho sabaa
Hinjiruu
Adama, ZIIPI

Awash  Academy Awash Academy
Adama

Awash Academy is a private organization.the school generates knowledgeble students that have a skill and it contributes to the country a good students .

Ifa boruu Ifa boruu
Alii Birraa
Adama

Ifa boruu like fi sher godhaa

Moke man Moke man
Arsi
Adama, MOK1212