አባኮራን ሚሲዮና አብሮአደግ ማኅበር Abakoran Misiyona Friendship Association
ይህ ስብስብ ለብዙ ዘመናት አብረው ያደጉና በተለያዩ የህይወት አጋጣሚዎች ተራርቀው የነበሩ የአባኮራን ሚሲዮና አካባቢ ወጣቶች ለመገናኘትና ለመረዳዳት ያቋቋሙት
መላው የማህበራችን አባላት ከነቤተሰቦቻችን በያላችሁበት እንኳን ለ2016 አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ/አደረሰን
አዲሱ ዓመት የተሟላ ሰላም፤ የጤና፤ የፍቅር፤ የመተሳሰብና የእድገት እንዲሆንልን መልካም ምኞታችን ነው፡፡
ዕሁድ ነሃሴ 14-2015
ማህበራችን ከልጅነት ክብር ሚኒስተሪ ጋር በመተባበር ከ450 በላይ ለሚሆኑ ኑሯቸው ዝቅተኛ ለሆነ እና ከፍለው መታከም ለማይችሉ የአካባቢያችን ነዋሪ ወገኖች፥ ነፃ የዓይን፣ የጥርስ፣ የውስጥ ደዌ የቆዳና የህፃናት ህክምና እንዲሁም የመድኃኒት ዕደላ እጅግ በተሳካና ባማረ ሁኔታ ያጠናቀቀ ሲሆን፣ ይህ መርሀ-ግብር እንዲሳካ ገንዘባችሁን፣ዕውቀታችሁን፣ጊዜያችሁንና ጉልበታችሁን ያለስስት ለሰጣችሁ አጠቃላይ የህክምና ባለሙያዎች፣ ተቋማት እና ጽ/ቤቶች እንዲሁም ለመላው የማህበራችን አመራሮች እና ተሳታፊ አባላት በሙሉ እጅግ ከፍ ያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን።
ማህበራችን በአካባቢያችን ነዋሪ ለሆኑ አቅማቸው ዝቅተኛና ከፍለው መታከም ለማይችሉ ወገኖቻችን በዓመት አንድ ጊዜ ነጻ የህክምናና የመድሃኒት እደላ ለማካሄድ በያዘው ዕቀድ መሰረት ከፈጣሪ ጋር በመጪው ነሃሴ 14 ቀን 2015 ዓ.ም በዕለተ ዕሁድ በቁጥር 350 ለሚሆኑ ታካሚዎች የዓይን፤ የጥርስ፤ የውስጥ ደዌና የቆዳ ህክምና ለመስጠት ዝግጅት እያደረገ ይገኛል፡፡
ዝርዝር ጉዳዮች በቀጣይነት የሚገለጹ ይሆናል፡፡
አርብ ግንቦት 11-2015
የአመራር አባላት በቀጣይ (2ኛ ዙር ) የበጎ ሥራ (የነፃ ህክምና አገልግሎት) ዙሪያ ሰፋ ያለ ውይይት አድርገዋል። ዝርዝር ጉዳዮችንና ውሳኔዎችን በሚቀጥለው የማህበራችን የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ላይ እናሳውቃለን እንወያያለን።
የአብሮነት እሴትን በማጎልበት ችግርን በጋራ መፍታት ይቻላል፣ይገባልም!
የአዲሰ አበባ ከተማ አስተዳደር ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን የ2015 ዓ.ም የበጋ በጎ ፈቃድ ማደስጀመሪያ፣ የበጎ ፈቃደኞች ስምሪትና የማነቃቂያ (Mindset) ስልጠና ፕሮግራም ላይ ለማህበራችን አመራርና አባላት በተደረገው የክብር እንግድነት ጥሪ ላይ ከአመራርና አባላት መካከል መገኘት የቻልነው ማህበራችንን ወክለን በስፍራው የተገኘን ሲሆን፤ ከፕሮግራሙም ጠቃሚ ልምድና ተነሳሽነትን ቀስመናል፡፡
እንደተለመደው ይህን ፕሮግራም ለተካፈላችሁና ላስተባበራችሁ አመራርና አባላት ከፍተኛ ምስጋናችን ይድረሳችሁ እንላለን፡፡
ዕለተ ዕሁድ ጥቅምት 06-2015
ማህበራችን ነሃሴ 29-2014 አድርጎት በነበረው የነጻ ህክምና ላይ፣ የዓይን ህክምና ካገኙና መነፅር ከታዘዘላቸው በርካታ ታካሚዎች መካከል ብዛታቸው 15 ለሚሆኑና ተገኝተው መረከብ ለቻሉት የዓይን መነፅር ዕደላ ተካሂዷል፡፡ ቀሪ ታካሚዎች ከ 15 ቀናት በኋላ እንደሚደርስላቸው ቃል ተገብቶልናል፡፡
ከመካከላቸውም የተወሰኑ ታካሚዎች የሰጡንን አስተያየት ከዚህ በታች ባሉ ቪዲዮዎች በጥቂቱ እንድትመለከቱ ጋብዘናል፡፡
በድጋሚ ይህ እንዲሳካ ለተባበራችሁ በሙሉ ምስጋናችን ይድረሳችሁ፡፡
ነሃሴ 29 2014 በነጻ ህክምና ላይ ከነበረው የመጨረሻ ፕሮግራም በከፊል
https://www.youtube.com/watch?v=RJogv69cjnM
ነሃሴ 29 በነጻ ህክምና ላይ ከነበረው የመጨረሻ ፕሮግራም በከፊል ነሃሴ 29 2014 በነጻ ህክምና ላይ ከነበረው የመጨረሻ ፕሮግራም በከፊል
🕊🕊🕊🕊🕊
ለመላው አባላትና ወዳጆቻችን እንዲሁም ለመላው ኢትዮጵያውያን እንኳን ለ2015 አዲስ ዓመት አደረሰን፡፡
2015 ከሁሉ አስቀድሞ የሰላም ቀጥሎ የደስታና የብልጽግና እንዲሆን ማህበራችን ከልብ ይመኛል፡፡
መልካም አዲስ ዓመት 🕊🕊🕊🕊🕊
ፈጣሪ እጅግ የተመሰገነ ይሁን።
ዕለተ ዕሁድ ነሃሴ 29-2014፤ ከ250 በላይ ለሚሆኑ ኑሯቸው ዝቅተኛ ለሆነ እና ከፍለው መታከም ለማይችሉ የአካባቢያችን ነዋሪ ወገኖች፥ ነፃ የዓይን፣ የጥርስ፣ የውስጥ ደዌ ህክምና እንዲሁም የመድኃኒት ዕደላ እጅግ በተሳካና ባማረ ሁኔታ ተጠናቋል።
ይህ ዕውን እንዲሆን ወሳኙን ሚና ለተጫወታችሁ፦
* አጠቃላይ የህክምና፣ የላቦራቶሪና የፋርማሲ ባለሙያዎች
* የወረዳ 02 አስተዳደር ጽ/ቤት
* የኢትዮጵያ ካ/ቤ/ክ የበጎ ሥራ ወንድሞች መርጃ ማህበር (የቀድሞው ሚስዮና ክሊኒክ)
* ራስ ዕምሩ ጤና ጣቢያ
* ዞይ ክሊኒክ
* ህሊና የጥርስ ህክምና
* ለመላው የማህበራችን አመራሮች እና ተሳታፊ ዓባላት
* እንዲሁም በትዕግስትና በስርዓት ስትስተናገዱ ለነበራችሁ ታካሚዎቻችን በሙሉ እጅግ የላቀ ምስጋናችንን እናቀርባለን።
https://www.youtube.com/watch?v=RJogv69cjnM
በጎ ተግባር ከበጎ ሃሳብ ይመነጫል።
ነሐሴ 18, 2014፤ በሂልተን ሆቴል በመጪው ዕሑድ 29/12/2014 ለሚደረገው የነፃ ህክምና የተሰሩ ስራዎች ሪፖርት የቀረበበት፣ ያልተሰሩ ስራዎች የተከፋፈልንበት እዲሁም በዛ ቀን የስራ ድርሻችንን የወሰድንበት ስብሰባ ይህን ይመስል ነበር ::
ይህን ላስተባበሩና ወጪውን በግል ለሸፈኑ የአመራር አባላት ከፍተኛ አድናቆትና ምስጋና እናቀርባለን።
አስኪ ይህን ለትውስታ ተመልከቱ ኮማንደር ማያ ቶኒ…….
የፊታችን ዕሁድ (ነሐሴ 29) ግማሽ ቀን የአካባቢያችን ነዋሪዎች ለሆኑ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ላሉና ከፍለው መታከም ለማይችሉ 200 ለሚደርሱ ወገኖቻችን በስፔሻሊስት ሀኪሞች የዓይን፣ የጥርስ፣ የውስጥ ደዌ ነጻ ህክምናና የመድሀኒት እደላ ይሰጣል። ለዚህ አገልግሎት በዋናነት ውሳኔ ሰጪዎች ለሆኑት አመራሮች ላቅ ያለ ምስጋና እናቀርባለን ::
Click here to claim your Sponsored Listing.
Videos (show all)
Contact the organization
Telephone
Website
Address
Abakoran
Addis Ababa
Office Addis Ababa
Addis Ababa, P.O.BOX21261,CODE1000
We are working for/with the most poorest and potentialy vulnerable elders in Ethiopia!
EiABC, Dej. Baltcha Aba Nefso Street
Addis Ababa
Welcome to the AIESEC in Ethiopia Official Fan Page! AIESEC is the World's largest student‐run organi
Akaki Kality, Wereda 01
Addis Ababa
L'ESPERANCE-ETHIOPIA is a humanitarian and non-making institution.
Addis Ababa
MHDI is a humanistic and development initiative working for Social Minority Groups!!
Addis Abeba
Addis Ababa
አፍሮ የሚለውን ቃል ከአፍሪካዊ ቅፅል የተዋስን ሲሆን ፔጁ በስፔን የባርሴሎና ክለብ ደጋፊዎች ማህበር (ፔንያ) እውቅና ያለው የአፍሮ ባርሳ ደጋፊዎች ልሳን ነው
City Center
Addis Ababa
The word ‘Bana’ (ባና) is a Tigrinya word meaning ‘a light emanating hopefulness’, literally ‘the dawn’
WelloSefer K-12 Building, Ethio China Street
Addis Ababa
REACH Ethiopia is local non-profit organization works to improve the health & well-being of Ethiopian
Addis Ababa
KHCO is non profit, non political and voluntary youth serving organization working for children and families, which aims to see a transformed community using a holistic approach.
Bole Subcity
Addis Ababa
Gezuyad Foundation is an emerging NGO founded with a long-sited vision & clear objective.
Gurd_shola
Addis Ababa, 355
AEID’s main programmatic interventions include: WASH/ Health and Nutrition/ Education/ Emergency Shelter/NFIs/ Youth Empowerment/Infrastructures/Child Care, Empowerment of Women an...