Addis Ababa Revenue Bureau Lideta Branch

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Addis Ababa Revenue Bureau Lideta Branch, Government Organization, leghar, Addis Ababa.

23/08/2021

#ከደረሰኝ አጠቃቀም ጋር የሚፈፀሙ ወንጀሎች ላይ የሚያስከትለው ቅጣት**
============================
#በገቢ ግብር አዋጅ 979/2008 መሰረት ከደረጃ "ሐ" ግብር ከፋዮች በስተቀር የደረጃ "ለ" እና "ሀ" ግብር ከፋዮች የሂሳብ መዝገብ፣ አስፈላጊ መረጃዎችን የመያዝና ህጋዊ ደረሰኞችን የመጠቀም ግዴታ ተጥሎባቸዋል፡፡ በእርግጥ የደረጃ "ሐ" ግብር ከፋዮች የሂሳብ መዝገብ እንዲይዙ በህግ ባይገደዱም በፍላጎታቸው ግን እንዲይዙ ይበረታታሉ፡፡ የደረጃ "ሀ" እና "ለ" ግብር ከፋዮች የንግድ ስራቸውን በሚያከናውኑበት ወቅት ግብይታቸውን በደረሰኝ እንዲደገፍ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ያለደረሰኝ ግብይት መፈፀም በመንግስት ገቢና በህጋዊ ነጋዴዎች ላይ አሉታዊ ተጽእኖ የሚያሳድር መሆኑን ይታወቃል፡፡ ከደረሰኝ ጋር በተያያዘ ወንጀል ተፈጽመው ሲገኙ በአዋጁ መሰረት የሚጣልባው ቅጣት አለ፡፡ በዚህ መሰረት፡-
• ማንኛውም ደረሰኝ የመስጠት ግዴታ ያለበት ግብር ከፋይ ያለ ደረሰኝ ግብይት ካከናወነ ከብር ሃያ አምስት ሺ እስከ ብር ሃምሳ ሺ የሚደርስ የገንዘብ መቀጫ እና ከሦስት እስከ አምስት ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፤
• በአንድ ግብይት በተሰጡ ተመሳሳይ የደረሰኝ ኮፒዎች ላይ የተለያዩ ዋጋዎችን በመመዝገብ የሽያጭ ዋጋን ያሳነሰ ማንኛውም ግብር ከፋይ ብር 100 ሺህ እና ከአምስት ዓመት እስከ ሰባት ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፤
• የሽያጩ ትክክለኛ ዋጋ ከብር 100 ሺህ የሚበልጥ ከሆነ የሚጣለው ቅጣት በደረሰኞቹ ላይ ከተመለከቱት ከፍተኛው የገንዘብ መጠን ይሆንና ከሰባት ዓመት እስከ አስር ዓመት የሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፤
• ግብይት ሳይፈጸም ደረሰኝ የሰጠ ወይም የተቀበለ ሰው ከብር 100 ሺህ እስከ ብር 200 ሺህ በሚደርስ የገንዘብ ቅጣት እና ከሰባት ዓመት እስከ አስር ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፤
• ደረሰኙ ከብር 200 ሺህ የሚበልጥ የገንዘብ መጠን የያዘ እንደሆነ የሚጣለው ቅጣት በደረሰኙ ከተገለጸው የገንዘብ መጠን ጋር እኩል በሆነ የገንዘብ ቅጣት እና ከአስር ዓመት እስከ አስራ አምስት ዓመት የሚደረስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፤
• በባለሥልጣኑ ሳያስፈቅድ ደረሰኝ ያተመ ሰው ከብር 300 ሺህ እስከ ብር 500 ሺህ በሚደርስ የገንዘብ ቅጣት እና ከሁለት ዓመት እስከ አምስት ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፤
• ጥፋተኛ የተባለ የደረሰኝ አታሚ ወንጀሉን ለሁለተኛ ጊዜ ፈጽሞ ጥፋተኛ መሆኑን ከተረጋገጠ የህትመት መሣሪያው እና የማተሚያ ድርጅቱ ይወረሳል፣ የንግድ ፈቃዱም ይሰረዛል፤
ስለሆነም ማንኛውም ደረሰኝ የመጠቀም ግዴታ ያለበት ግለሰብ ወይም ድርጅት የሚፈፅመውን ማነኛውም ግብይት በህጋዊ ደረሰኝ ላይ የተመሰረተ በማድረግ ራሱን ከህግ ተጠያቂነት ሊያድን ይገባል፡፡
ምንጭ፡- አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ

23/08/2021

ለልደታ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ፅ/ቤት የደረጃ ‹‹ለ›› ግብር ከፋዮች በሙሉ

በገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 979/2008 መሰረት የደረጃ ‹‹ለ›› ግብር ከፋዮች የ2013 የግብር ዘመን ግብርን አሳውቆ የመክፈያ ጊዜ ከሐምሌ1/2013 እስከ ጳጉሜ 05/2013 ዓ.ም መሆኑ ይታወቃል፡፡ በዚሁ መሰረት ቀደም ብላችሁ ግብራችሁን አሳውቃችሁ የከፈላችሁትን ግብር ከፋዮቻችንን እያመሰገንን፤ እስካሁን ያላሳወቃችሁ ግብር ከፋዮች ግን በቀሩት ጥቂት ቀናት ከኮሮና ቫይረስ ራስዎን በመጠበቅ የሚጠበቅባችሁን ግብር አሳውቃችሁ በመክፈል መጨረሻ ቀናት ላይ ከሚፈጠር የወረፋ መጨናነቅ እንዲሁም ቅጣት ራሳችሁን እንድታድኑ ስንል እናሳስበባለን፡፡

የልደታ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት!!!

17/08/2021

ለልደታ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ፅ/ቤት የደረጃ ‹‹ለ›› ግብር ከፋዮች በሙሉ

በገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 979/2008 መሰረት የደረጃ ‹‹ለ›› ግብር ከፋዮች የ2013 የግብር ዘመን ግብርን አሳውቆ የመክፈያ ጊዜ ከሐምሌ1/2013 እስከ ጳጉሜ 05/2013 ዓ.ም መሆኑ ይታወቃል፡፡ በዚሁ መሰረት ቀደም ብላችሁ ግብራችሁን አሳውቃችሁ የከፈላችሁትን ግብር ከፋዮቻችንን እያመሰገንን፤ እስካሁን ያላሳወቃችሁ ግብር ከፋዮች ግን በቀሩት ጥቂት ቀናት ከኮሮና ቫይረስ ራስዎን በመጠበቅ የሚጠበቅባችሁን ግብር አሳውቃችሁ በመክፈል መጨረሻ ቀናት ላይ ከሚፈጠር የወረፋ መጨናነቅ እንዲሁም ቅጣት ራሳችሁን እንድታድኑ ስንል እናሳስበባለን፡፡

የልደታ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት!!!

Want your organization to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address


Leghar
Addis Ababa
0

Opening Hours

Monday 08:00 - 17:00
Tuesday 08:00 - 17:00
Wednesday 08:00 - 17:00
Thursday 08:00 - 17:00
Friday 08:00 - 17:00
Saturday 08:00 - 17:00
Sunday 08:00 - 17:00
Other Government Organizations in Addis Ababa (show all)
Addis Ketema woreda 5 Communication Addis Ketema woreda 5 Communication
Addis Ababa
Addis Ababa

This is woreda 5 communication office .

Addis Ketema Woreda12 Communication Addis Ketema Woreda12 Communication
Addis Ketema
Addis Ababa

በዚህ ወሳኝ ወቅት ከመንግስት ተቋማት የሚተላለፉትን መረጃዎ�

የቦሌ ሥራ፤ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ፅ-ቤት የቦሌ ሥራ፤ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ፅ-ቤት
Addis Ababa

የቦሌ ሥራና ክህሎት ፅ-ቤት Official የፌስቡክ ገፅ ነው፤ እኛን የሚመለከት ጉዳይ ካለዎት ያግኙን።

Addis Ababa City Administration Trade Bureau Addis Ababa City Administration Trade Bureau
Addis Ababa
Addis Ababa

News

Addis Ababa City Admin. Landholding Registration and Information Agency Addis Ababa City Admin. Landholding Registration and Information Agency
604 Equatorial Guiene Avenue
Addis Ababa

Serving reliable cadastral services and information

Lafto woreda 05 Communication Lafto woreda 05 Communication
Addis Ababa

peace for Ethiopia

Ethio-engineering Group Ethio-engineering Group
Bole Sub City, Gerji, Amora Building
Addis Ababa

Ethio-engineering Group is a governement owned industrial enterprise established under the laws of the Federal Democratic Republic of Ethiopia /FDRE/ by the decree of the council o...

Yeka Sub city Small Tax payers branch Office Yeka Sub city Small Tax payers branch Office
Addis Ababa

Revenue for societal infrastructure and facilities

Ministry of Irrigation & Lowlands - Ethiopia Ministry of Irrigation & Lowlands - Ethiopia
Kasanchis
Addis Ababa

The Ministry of Irrigation & Lowlands (MILLs) is FDRE's Ministry established in 2021.

Ambassade du Cameroun en Ethiopie/ Embassy of Cameroon in Ethiopia Ambassade du Cameroun en Ethiopie/ Embassy of Cameroon in Ethiopia
2Q29+FQP
Addis Ababa

Permanent Representation of the Republic of Cameroon to the African Union and the United Nations Economic Commission for Africa.