Lafto woreda five prosperity

poletical organization

Photos from Lafto woreda five prosperity's post 18/04/2024

የብረት ምርትን ማሳደግ የኢንዱስትሪ ልማት ፖሊሲያችን አካል ነው። የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን በመጠቀም፣ ጥራት ያላቸው ከፍተኛ ኃይል አስተላላፊ የኤሌትሪክ ገመዶችን እና የኤሌትሪክ ማማዎችን ለኤሌክትሪክ ብሎም ለቴሌኮም ዘርፎች በሀገር ውስጥ ማቅረብን እየሠራንበት እንገኛለን። በተጨማሪም የተሽከርካሪዎችን እና የመለዋወጫዎችን የምርት ሥራ በመመልከቴም ተደስቻለሁ። ሀገር በቀል ኩባንያዎች ተሽከርካሪዎችን እና መለዋወጫዎችን ሲያመርቱ መመልከትም በእጅጉ ያበረታታል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

18/04/2024

የመደመር ትውልድ ልዩነትን የሚያከብርና አንድነትን የሚያጠናክር ነው!!

የመደመር ትውልድ ጥላቻን በፍቅር፣ ቂምን በይቅርታ፣ ግጭትን በውይይት የሚተካ ትውልድ ነው።

የመደመር ትውልድ ልዩነትን የሚያከብርና አንድነትን የሚያጠናክር ፤ ጽንፈኝነትን የሚጸየፍ ትውልድ ነው።

የመተማመን ክበቡ በብሄርና በመንደር ሳይታጠር ኢትዮጵያዊነትን በአርበኝነት መንፈስ የሚያፀና ነው።

በመሆኑም ከራስ ወዳድነት የፀዳ፣ ለሌሎች የሚራራ፣ ሀላፊነት የሚሸከም ፣ እውነተኛና የሌላው ህመም የሚያመው ትውልድ መቅረጽ የጋራ ሀላፊነት ሊሆን ይገባል።

በመደመር ትውልድ ተሠናስለን ተከባብረንና ተባብረን ለጋራ ግብ ቋሚ ተሰላፊ በመሆን ኢትዮጵያን እናበለጽጋለን።

18/04/2024

የብልጽግና ፕሮግራም‼️

1.የፖለቲካ ፕሮግራም ፦ጠንካራና ቅቡልነት ያለው ዘላቂ ሀገረ-መንግስት መገንባት።
2.የኢኮኖሚ ፕሮግራም ፦ልማትና ኢፍትሃዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ
አካታች የኢኮኖሚ ስርዓት መገንባት።

3.ማህበራዊ ፕሮግራም ፦ሁለንተናዊ ብልጽግናን የሚያረጋግጥ አካታች ማህበራዊ ልማት ማረጋገጥ።
4.የውጭ ግንኙነት ፕሮግራም ፦
ሀገራዊ ክብርን ማዕከል ያደረገ የውጭ ግንኙነት መከተል።

ሚያዝያ 10/2016
/ከተማ_ወረዳ_5_ፓርቲ_ሚዲያ‼️

Photos from Nifas Silk Lafto Sub City Prosperity Party's post 17/04/2024
Photos from Lafto woreda five prosperity's post 17/04/2024

የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት “ሀገራዊ መግባባት እና የኮሙኒኬሽን ተቋማት ሚና” በሚል ርዕስ ለኮሙኒኬሽን ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ሥልጠና እየሰጠ ነው፡፡

ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ተቋማት፣ ከዞንና ክፍለ ከተሞች እንዲሁም ከፌዴራል ተቋማት የተውጣጡ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊዎችና ከፍተኛ ባለሙያዎች በመርሀ ግብሩ ላይ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

በሥልጠናዉ የመጀመሪያ ቀን ውሎ “የገዥ ትርክት ግንባታ እና የኮሙኒኬሽን ሚና” በሚል ርዕስ በሚንስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዐት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትር ክቡር አቶ አዲሱ አረጋ ለተሳታፊዎች ስልጠና ሰጥተዋል፡፡

ገዥ ትርክት የሀገር አንድነት መሠረት መሆኑን ያመላከቱት አቶ አዲሱ የኮሙኒኬሽን ዘርፉ ትርክቱን በመትከልና በማጽናት ጉልህ ሚና እንዳለዉ አስገንዝበዋል፡፡

ቀድሞ ተንባይ የኮሙኒኬሽን ሥርዐት በመከተል ገዥ ትርክትን መገንባት ላይ ሰፊ ትኩረት መስጠት እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡

በመርሐ ግብሩ መክፈቻ ላይ መልእክት ያስተላለፉት የአገልግሎቱ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ከበደ ዴሲሳ “ጠንካራ ሀገረ መንግሥት ለመገንባት ብሔራዊ ጥቅሞቻችን ላይ ወጥ የሆነ መረዳትና አስተሳሰብ መያዝ ያስፈልጋል” ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ የሚስተዋሉ ችግሮችን ከመሠረታቸዉ በመረዳት የሰላም ግንባታ ሂደቱን ለማፋጠን የኮሙኒኬሽን ዘርፉ ሚና ከፍ ያለ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

የሥልጠናው ዓላማ የኮሙኒኬሽንና የሕዝብ ግንኙነት ዘርፉን በሥልጠና በማገዝ ወቅታዊ፣ ትክክለኛ፣ የተናበበ እና የተቀናጀ መረጃ ተደራሽነትን ማረጋገጥና ሚዲያን በአጀንዳ ለመምራት ዐቅም ለመፍጠር ነው፡፡

ተሳታፊዎች እንዲህ ዓይነቱ ሥልጠና የሀገርን ብሔራዊ ጥቅሞች፣ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂ በመረዳት የሀገረ መንግሥት ግንባታውን በኮሙኒኬሽን ለመደገፍ፣ ለሕዝቡ ትክክለኛ መረጃ በፍጥነትና በጥራት ለመስጠት እንደሚጠቅማቸዉ ገልጸዋል፡፡

17/04/2024

ሰላም በሁሉም ኢትዮጵያዊ ቤት ያለ፤ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊጠብቀው የሚገባ ነው!

ሰላም ዋጋው ውድ ነው። አንዴ ከእጃችን ካመለጠ እንዲሁ በቀላሉ አይገኝም። የሁሉንም የዕለ ተዕለት ስራን፣ ትጋት እና ርብርብ ይጠይቃል።

ያለ ሰላም ነጋዴው አትርፎ፣ ገበሬው አምርቶ፣ መምህሩ አስተምሮ፣ ተማሪው ተምሮ መግባት አይችልም። ሰላም ከሌለ ልማትና ዲሞክራሲን ማረጋገጥ አይቻልም። ሰላም ከሌለ ወጥቶ መግባት፣ ተንቀሳቅሶ ሰርቶ መለወጥ አይታሰብም።

በሰላም እጦት ፈርሰው ህዝባቸው ከፊሉ ለሞት፣ ከፊሉ ለስደት የተዳረጉባቸውን ሃገራት እነ ሶሪያን፣ የመንን እና ሊቢያን መጥቀስ የሰላምን ዋጋ ለመረዳት ይጠቅማል። በሃገራችን የሰሜኑ ጦርነት በሰላም እጦት ምክንያት የደረሰው ሰብዓዊና ቁሳዊ ጉዳትም የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው። ከዚህ በመማር በእጃችን ላይ ያለውን አንፃራዊ ሰላም አጥብቆ በመያዝ ዘላቂ ሰላማችንን ማረጋገጥ አማራጭ የሌለው አንገብጋቢ ጉዳይ ነው።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ማህበራዊ ሚዲያው የፈጠረላቸውን ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም የኢትዮጵያን እድገት የማይመኙ ታሪካዊ የውጭ ጠላቶች እና ፅንፈኞች በመናበብ ብሄርን ከብሄር፣ ሃይማኖትን ከሃይማኖት የሚያጋጩ፣ ህዝብ በመንግስ ላይ እንዲነሳ የሚያደርጉ፣ መጠራጠርና አለመተማመንን የሚያነግሱ የተዛቡ መረጃዎችን በሰፊው ሲያሰራጩ ይስተዋላል። መላው የኢትዮጵያ ህዝብ የእነዚህን ፀረ _ሰላም ኃይሎች ህዝብን እርስ በእርስ የማባላት እና ሃገርን የማፍረስ ሴራ ተገንዝቦ በጋራ ሊታገላቸው ይገባል።

ሰላም በአንድ ወገን ስለተፈለገ ብቻ አይረጋገጥም። በሁለቱም በኩል አዎንታዊ ምላሽ ሲኖር እንጅ። ሰላም በመንግስትና በፀጥታ ኃይሉ ብቻ ጥረት ሊረጋገጥም አይችልም። ይልቁንም መላው የህብረተሰብ ክፍል የሰላምን ዋጋ ተረድቶ ከፀጥታ ኃይሉ ጋር በመቀናጀት አካባቢውን ነቅቶ መጠበቅ እና መንግስት ሰላምን ለማረጋገጥ የሚወስዳቸውን አወንታዊ እርምጃዎች መደገፍ ሲችል እንጅ። ስለሆነም ሰላማችንን መጠበቅ እና መንከባከብ አማራጭ የሌለው የሁላችንም ኃላፊነት ነው።

ስለዚህ በሰላም አብሮ ከመኖር ውጭ አማራጭ የሌለን ህዝቦች መሆናችንን በመረዳት አብሮነታችንን ከሚሸረሽሩ የፅንፈኝነት አጀንዳ ህብረተሰቡ እራሱን ጠብቆ ፅንፈኞችን በጋራ በመታገል የከተማችንን ብሎም የሀገራችንን የብልፅግና ጉዞ እውን ለማድረግ መረባረብ አለበት።

መልካም ቀን ይሁንልዎ!!!

17/04/2024

ቁልፍ የፖለቲካ ስብራታችንን ከመጠገን አንጻር የብሔራዊነት ትርክት ፋይዳ ምንድነው?

እኛ ኢትዮጵያዊያን የወል ብሔረ መንግስት (Nation) በመመስረት አሰባሳቢ ሀገረ መንግስት (State) መገንባት ከጀመርንበት ጊዜ አንስቶ በርካታ ዘላቂ ወረቶች በጋራ ያካበትን ህዝቦች ነን፡፡ በጋራ ያካበት ናቸው ወረቶች እንደተጠበቁ ሆነው እስካሁንም ያልተሻገር ናቸው የፅንፍ አስተሳሰቦች አሉ፡፡ እነዚህ የጽንፍ አስተሳሰቦች በአንድ አመራር ትውልድ የተፈጠሩ ሳይሆን ከብሔረ- መንግስታችን ምስረታ እና ከሀገረ - መንግስታችን ግንባታ ጀምሮ የነበሩና እስካሁንም ድረስ ከእኛ ጋር ያሉ ናቸው፡፡ ዳሩ ግን እነዚህ ዋልታ ረገጥ አተሳሰቦችና ከእነሱ የሚመነጩ ድርጊቶች የየራሳቸው ምንጮች ያላቸው ናቸው፡፡

ምንጮቻቸውም ፓርቲያችን በተለያዩ ጊዜያት በትላልቅ ሰነዶቹ ጭምር በግልፅ እንዳስቀመጣቸው ፍፁማዊ አንድነትና ፍፁማዊ ልዩነት የሚሰኙ የተቃርኖ ትርክቶች ናቸው፡፡ በብልፅግና እምነት ደግሞ ፍጹማዊ አንድነትም ሆነ ፍጹማዊ ልዩነት ሀገራችን ኢትዮጵያን የማይመስሉ ብቻ ሳይሆን የማይመጥኑም መሆናቸው ነው፡፡

እነዚህ የህዝቦች አንድነትና የሀገር ቀጣይነት ላይ ከፍተኛ አደጋ የደቀኑ ትርክቶችና ፅንፈኛ አስተሳሰቦችን ተሻግረን ሁሉም ህዝቦችና ዜጎች እኩል የሆኑበት ከተማና ሀገር እውን ለማድረግ ሁሉም ዜጋ ሃላፊነት አለበት።

የብሄራዊነት ትርክት በአንድ በኩል ሀገራችን ኢትዮጵያ ከመጣችባቸው አባጣ ጎርባጣ የሀገር ምስረታና ሀገረ መንግስት ግንባታ የሚነሱ የተቃርኖ ትርክቶችን ከስር መሰረታቸው በመግራት ሀይል ለማሰባሰብ ያግዛል፤ በሌላ በኩል ደግሞ በአርበኝነት መንፈስ የተቃኘ አንድነት፣ ወንድማማችነትና አብሮነት በመትከል የጠነከረችና ሰላማዊት የሆነች ሃገር እውን ለማድረግ ያስችለናል፡፡

ይሄን ማድረግ በመቻላችን በሃገራችን ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን፣ እኩልነት እንዲረጋገጥ፣ ወንድማማችነት እንዲያብብ፣ የዴሞክራሲ ባህል እንዲዳብርና ሁለንተናዊ ብልጽግና እውን እንዲሆን ያስችላል፡፡

Photos from Lafto woreda five prosperity's post 16/04/2024

በአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት የስራ አስኪያጅ ልዩ ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ምስረታ በየደረጃው የሚገኙ የሴት ሊግ አመራሮች ፣ በልዩ ወረዳው የሚገኙ የፓርቲያችን ሴት አባላት እንዲሁም ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት ተካሂዷል።

በምስረታ ፕሮግራሙ ላይ የሊጉ መተዳደሪያ ደንብ እና የኢትዮጵያን ሰላም እጠብቃለው ለልጆቼ ምንዳን አስረክባለው በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ሰነድ ቀርቦ የልዩ ወረዳው ሴት ሊግ መስራች አባላት ተወያይተውበታል።

16/04/2024

በኮሪደር ልማት ዝግ ሆነው የቆዩ መንገዶች ለተሽከርካሪ ክፍት ተደርገዋል::

በኮሪደር ልማት ምክንያት ከመጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከ4 ኪሎ እስከ ፒያሳ ያለው መስመር የራስ መኮንን ድልድይ እየተሰራ በመሆኑ ተዘግቶ የነበረው መንገድ በከፊል ክፍት ተደርገዋል፡፡

በዚህም መሰረት፡-

• ከደጃች ውቤ በአፍንጮ በር ወደ ራስ መኮንን ድልድይ

• ከባሻወልዴ ችሎት በቱሪስት ሆቴል ራስ መኮንን ድልድይ አፍንጮ በር

• ከዳኑ ሆስፒታል እስከ ቱሪስት ሆቴል በመውጣት ወደ ራስ መኮንን ድልድይ አፍንጮ በር

•ከአራዳ መስተዳደር ወደ ዳኑ ሆስፒታል መውረጃ በአንድ አቅጣጫ ብቻ አሽከርካሪዎች መጠቀም የሚችሉ እና ልዩ ልዩ የልማት ስራዎች እየተከናወኑ በመሆኑ ለአጭር ሆነ ለረጅም ጊዜ ተሽከርካሪን አቁሞ መሄድ ፍፁም ክልክል መሆኑን አሽከርካሪዎች ተገንዝበው የትራፊክ ምልክትና ማመላከቻዎች አክብረው እራሳቸውንና ሌሎችን ከትራፊክ አደጋ እየጠበቁ መንገዱን መጠቀም እንደሚችሉ እናስታውቃለን::

Photos from Lafto woreda five prosperity's post 16/04/2024

የቱሉ ኤጀርሳ ወረዳ የብሎክ አመራሮች ለሀገር ባለውለታዎችና ለአቅመ-ደካማ ዜጎች እየገነባ የሚገኘውን መኖሪያ ቤት ግንባታ ጎበኙ።

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የቱሉ ኤጀርሳ ወረዳ የብሎክ አመራሮች ለሀገር ባለውለታዎችና ለአቅመ-ደካማ ዜጎች እየተገነባ የሚገኘውን መኖሪያ ቤት ግንባታ ጎበኙ።

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሃኑ አበራ እንዳሉት ፕሮጀክቱ የህዝብ በመሆኑ በተቀናጀና በተናበበ መንገድ እየተሰራ ነው ብለዋል።

ዋና ስራ አስፈጻሚው አክለውም በፍጥነት፣ በጥራትና በተያዘለት ጊዜ በማጠናቀቅ ለአገልግሎት እንዲበቃ 7/24 እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለልኝ ወንዴ የማህበረሰቡን የቤት ችግር ለመቅረፍ ከመንግስታችን ጎን በመቆም ለሚደረገው ድጋፍ ሁሉንም ባለድርሻ አካላት እናመሰግናለን ሲሉ ተናግረዋል።

በመጨረሻም ጉብኝት ያደረጉ የብሎክ አመራሮች በፕሮጀክቱ ደስተኛ መሆናቸውን በመግለጽ ተሳትፏቸውን ለማጠናከር ቃል ገብተዋል።

ሚያዚያ 08/2016 ዓ/ም

Photos from Lafto woreda five prosperity's post 16/04/2024

ለሀገር ባለውለታዎችና ለአቅመ-ደካሞች የቤት ግንባታ በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ በፍጥነትና በጥራት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ለሀገር ባለውለታዎችና ለአቅመ-ደካሞች የቤት ግንባታ በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ በፍጥነትና በጥራት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።

የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ብርሃኑ አበራ በዛሬው የመስክ ስራ ምልከታ እንዳሉት በጥራትና በፍጥነት በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ የተጀመረው ቅንጅታዊ አሰራር ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።

በቀጣይም የቅርብ ድጋፍና ክትትልን በማጠናከር ግንባታውን ማጠናቀቅ እንደሚገባ የስራ አቅጣጫ ተቀምጧል።

ሚያዚያ 08/2016 ዓ/ም

16/04/2024

ስለ ሰላም እንዘምራለን፤ ደግሞም እንሰራለን!

የዴሞክራሲ ምህዳሩን በማስፋት ሲንከባለሉ የመጡ እና በየጊዜው ቅርፃቸውን የሚቀያይሩ ሳንግባባ ያደርንባቸውን አገራዊ ጉዳዮች ጭምር ህዝባችንን በማሳተፍ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ እልባት በመስጠት አገራዊ አንደነታችንን በማይናወጥ መሰረት ላይ ለመገንባት ከለውጡ ጀምሮ የተለያዩ እርምጃዎች እየተወሰዱ ይገኛሉ።

በእሳት ተፈትኖ ነጥሮ እየወጣ ያለው የለውጡ መሪ መንግስታችን እና ፓርቲያችን "ኢትዮጵያ አበቃላት" ያስባለውን ከውጭም ከውስጥም የተደቀነባትን ምናልባትም በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ውስብስብ ፈተና ህዝቡን ከጎኑ አሰልፎ እንደ ጉም ከመግፈፉ በተጨማሪ የቆመለትን ኢትዮጵያን የማበልፀግ ዓላማ ለአፍታም ሳይገታ አጠናክሮ አስቀጥሏል።

በሌላ በኩል ደግሞ የኢትዮጵያን መለወጥ የማይመኙ፣ በልፅጋ ማየት የማይፈልጉ የውስጥና የውጭ ፀረ-ሰላም ሀይሎች ፍላጎታቸው የሚሳካው እርስ በእርስ ስንጣላ እንጅ ስንፋቀር ባለመሆኑ 24 ሰዓት በታዛቢነት ከዳር ሆነው የሚመለከቱትን የጦርነት ፊሽካ መንፋታቸውንና ከእሳት ላይ ቤንዚን ማርከፍከፋቸውን አላቆሙም።

ኢትዮጵያዊያን የጦርነትን እና የግጭትን አስከፊነት በየጊዜው የህይወት መስዋዕትነት እና የንብረት ውድመት ውድ ዋጋ እያስከፈለን እያለፍንበት ያለ የአስከፊ ታሪካችን ገፅታ ጭምር እንጂ ከርቀት የምንሰማው ጉዳይ አይደለም።

የግጭት አትራፊዎች ያልተቋረጠ የገቢ ምንጭ በሬ ወለደ የሚሉ የሀሰት ወሬዎች በመሆናቸው ሳያረጋግጡና ሳያመዛዝኑ የሚያዳምጡ ግለሰቦችን ወደ እኩይ መረባቸው ለማስገባት ጠዋት ማታ ያሰራጫሉ።

ከሀሰተኛ መረጃዎች ራስን መጠበቅ እንዲሁም በዘመኑ የሚዲያ አማራጮች ውሸታቸውን ማጋለጥም ከእያንዳንዳችን ይጠበቃል።

የአገር ዋልታ የሆነው መከላከያ ሰራዊታችን እና ሌላውም የፀጥታ ሀይላችን አስተማማኝ ሰላማችንን ለማረጋገጥ ለሚወስዳቸው አጥፊዎችን ወደ ህግ የማቅረብና ህግን የማስከበር እርምጃዎች እንደተለመደው ደጀንነታችንና ድጋፋችንን ማጠናከርም ይገባል።

የግጭት አትራፊዎች ስለሰላም ማውራትን፣ ስለሰላም ነገሮችን በትዕግስት ማለፍን እንዲሁም የሀይማኖት አባቶችን የሰላም ምክር እንደ ሞኝነት ቢቆጥሩትም የኢትዮጵያን አስተማማኝ ሰላም ለማረጋገጥ እንዲሁም ሁለንተናዊ ብልፅግናዋን እውን ለማድረግ ቆርጠን በመነሳታችን ዛሬም ሆነ ነገ ስለ ሰላም እንዘምራለን፤ ደግሞም እንሰራለን!

Photos from Lafto woreda five prosperity's post 15/04/2024

የውጤት ዜና
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት አስተዳደር ጽ/ቤ ዕውቅና ተሰጠ

በ2016 በጀት ዓመት በተደረገ ምዘና የወረዳ 05 ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት አስተዳደር ጽ/ቤት ከክፍለ ከተማው ካሉ 13 ወረዳዎች የ2ኛ ደረጃ በመውጣት በክፍለ ከተማው የዕውቅና ፕሮግራም የዋንጫና የሰርተፍኬት ተሸላሚ ሆኗል

የተገኘውን ውጤት አስመልክተው መልዕክት ያስተላለፉት የወረዳው ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዳምጤ ወርቅነህ ውጤቱ የተገኘው በመላው አመራር እና ባለሙያዎች ርብርብ በመሆኑ ለሪፎርም ተግባራት ስኬት የበኩላችሁን ሚና ለተወጣችሁ ሁሉ በጽ/ቤታችን ስም እያመሠገንን በቀሪ ወራት ያላከናወናቸው ቀሪ ተግባራት ላይ መረባረብ ይጠበቅብናል በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ሚያዚያ 07/2016

Photos from Lafto woreda five prosperity's post 15/04/2024

"ሰራተኛው በአቅሙና በእውቀቱ ልክ ምደባ ያገኘ በመሆኑ በአገልግሎት አሰጣጡ የተሻሉ ውጤቶች እየታዩ ነው"
አቶ ብርሃኑ አበራ

ሀገራዊ ሪፎርሙን ተከትሎ ሰራተኛው በአቅሙና በእውቀቱ ልክ ምደባ ያገኘ በመሆኑ የተሻሉ ውጤቶች እየታየ መሆኑን የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሃኑ አበራ ገለፁ።

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ጽ/ቤት የ2016 የግማሽ ዓመት እውቅና መርሃ ግብር አካሂዷል።

በእውቅና መርሃ ግብሩ የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ብርሃኑ አበራ፣ የክፍለ ከተማው አፈጉባኤ አቶ ወጋየሁ ኃይሉን ጨምሮ ሌሎች አመራሮች፣ የምክር ቤት አባላትና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ብርሃኑ አበራ እንዳሉት በሀገራዊ ሪፎርም ሰራተኛውን በአቅሙና በእውቀቱ ልክ ተገቢውን ሰው በተገቢው ቦታ በማሰራት ከፍተኛ ለውጥ እንዲመዘገብ ያስቻለ መሆኑን በአጽንኦት ተናግረዋል።

አቶ ብርሃኑ አክለውም በህብረተሰቡ ጥያቄ መሰረት የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፍታት፣ በመቀናጀት የተጣለበት ኃፊነት በአግባቡ በመወጣት ፐብሊክ ሰርቫንቱ እንደመከላከያ ሰራዊት ሁሉ የሀገሩ የበላይ ዘብ ነው ሲሉ አስምረውበታል።

በተጨማሪም የዓለማችን የዲፐሎማቲክ ከተማ የሆነችውን አዲስ አበባ የለማች፣ የበለፀገች እንዲሁም የአፍሪካ ሀገራት የስበት ማዕከል እንድትሆን ተባብረን በመስራትና የተጨበጠ ውጤት በማምጣት ብዙ ተግባራት ይጠበቅብናል ሲሉ አክለዋል።

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ጠረፍ ማሞ እንዳሉት በአገልግሎት አሰጣጥ፣ በግል ጥረትና አብሮ በመስራት በታየው የትብብር ስኬት እንዲሁም በሪፎርሙ አፈጻጸም እውቅና መሰጠቱን ገልጸው ለበለጠ ውጤት መትጋት እንደሚገባ አሳስበዋል።

ኃላፊዋ አክለውም ሽልማቶና እውቅና የተሰጣቸው ተቋማትና ባለሙያዎች ለተሻለ ስራ እንዲበረታቱና ለበለጠ ውጤት እንዲተጉ በማሰብ መሆኑን በአጽንኦት ተናግረዋል።

በመጨረሻም ተሸላሚ የሆኑ ሴክተር ተቋማትና ባለሙያዎች ሽልማታቸውን ከዕለቱ የክብር እንግዶች እጅ ተቀብለዋል።

ሚያዚያ 07/2016 ዓ/ም

15/04/2024

ኢትዮጵያውያን አንድም ብዙም ነን!!

በአንድነታችን ውስጥ ህብረ ብሔራዊነታችን፣ በህብረ ብሔራዊነታችን ውስጥ ደግሞ አንድነታችን አለ።

የኢትዮጵያ ድምቀትና ጥንካሬ ምንጩ ብዝሀነቷ ነው።

ፓርቲያችን ብልፅግና ከሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ እና ከእውነታው በመነሳት ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ በመከባበርና በመቻቻል ላይ የተመሰረተ ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነትን ለመገንባት ከምስረታው ጀምሮ የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል።

አካታች የዴሞክራሲ ስርዓትን ለመትከልና እና ፍትሃዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ያለሰለሰ ጥረት እያደረገ የሚገኘው ፓርቲያችን በቅርቡ በሀገራችን የተፈጠረውን አንፃራዊ የሰላም አየር ዘላቂ ለማድረግም ቁርጠኛ አቋም ሰንቋል።

የሁሉም ኢትዮጵያውያን ድምፅ የሚስተናገድበትና ያለፉ ቁርሾዎችን በይቅርታ በመዝጋት አዲስ የታሪክ ምዕራፍ እንደሚፈነጥቅ የሚጠበቀው ብሄራዊ ውይይታችንም ህብረ ብሄራዊ አንድነታችን በማጠናከር ለዘላቂ ሰላማችን የጎላ ሚና እንደሚኖረው ይጠበቃል።

Photos from Lafto woreda five prosperity's post 15/04/2024

የ60/90 ቀን እቅድ አፈጻጸም እና የፓርቲ መደበኛ ስራዎች ተገመገመ።

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 5 አስተዳደር የ60/90 ቀን እቅድ አፈጻጸም እና የፓርቲ መደበኛ ስራዎች በጠቅላላ አመራር ተገመገመ።

በ60 እና በ90 ቀን እቅድ ተይዞለት ከሚሰሩ የስራ እድል ፈጠራ፣ቤት እድሳት፣ሀብት ማሰባሰብ፣ልማት ትሩፋትና የተለያዩ ሰው ተኮር ተግባራቶች ተገምግሟል።በተጨማሪም ቀጣይ ለሚደረገው የማዕድ መጋራት ተዳስሷል።

የፓርቲ መደበኛ ስራ ጊዜውን የጠበቀ የህዋስ ውይይት፣ጠንካራ አባለትና ተቋም መፍጠር እንደሁም ወቅቱን የዋጀ ጠንካራ የአባላትና አመራር ስምሪት በደንብ ተገምግሞ የወደፊት አቅጣጫ ተቀምጧል።

ሚያዝያ 7/2016

15/04/2024

ቃልን በተግባር የሚያፀና ብልጽግናዊ ጉዞ በመዲናችን አዲስ አበባ እንደቀጠለ ነው!

የብልጽግና ፓርቲ ዋና መገለጫ የገባውን ቃል በተግባር በመፈጸም ለህዝብ ጥቅምና አገልግሎት ማዋል ነው። ፓርቲያችን የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ለውጥ ለማሳለጥና ከሚገባት የከፍታ ማማ ለማድረስ መደመርን መንገዱ አድርጎ በህብረብሔራዊ አንድነት የፀናች ሀገርን ለትውልድ ለማውረስ በመትጋት ላይ ይገኛል።

የፓርቲያችን መሰረት ሰው ነውና ለህዝብ ቃል የገባውን የለውጥ ጉዞ በሚታይና በሚጨበጥ ብርሃናማ ተስፋ ላይ ማስቀመጥ ችሏል። በተለይም አዲስ አበባ ከተማን ስሟንና ክብሯን በሚመጥን መልኩ የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ ዘርፈብዙ የሆኑ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያላቸው ስራዎች በመሰራት ላይ ናቸው።

በመዲናዋ እየተተገበረ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ከተማዋን ውብ፣ ፅዲና ማራኪ ከማድረግ ባሻገር ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ትስስርን በማሳለጥ ረገድ ሚናው የጎላ ነው። ፕሮጀክቱ የከተማዋን አጠቃላይ ገፅታ በመቀየር ዓለማቀፋዊ የቱሪዝም ማዕከልና መዳረሻ ለማድረግም ከፍተኛ ድርሻ አለው።

ብልጽግና ፓርቲ ቃሉን የሚያከብርና የሚፈጽም፣ የጀመረውንም በታሰበለት ጊዜና ዓላማ የሚያጠናቅቅ የሀገርንና የህዝብን ክብር የሚገነባ ዛሬና ነገን በወል ዕውነት የሚያስተሳስር የትውልድ ፓርቲ ነው። ለዚህም ነው በተግባራቱ ሁሉ የየዕለትን ብቻ ሳይሆን የነገውንም ዓቅዶና ዓልሞ ሀገራዊ ስብራቶችን በማረም ለትውልድ የሚተርፍ ምንዳን እየገነባ የሚገኘው።

ከዚህ አንፃር የኮሪደር ልማቱ የአዲስ አበባን አጠቃላይ ገፅታ በመቀየር ደረጃዋን የጠበቀች ውብና ማራኪ ዓለማቀፍ ተወዳዳሪ ከተማ ትሆን ዘንድ ከፍተኛ ሚናን ይወጣል። አድስ አበባ የቱሪስት መስብ፣ የኢኮኖሚ ማዕከል፣ የፖለቲካና ዲፕሎማሲ መናኸሪያ በመሆን ለነዋሪዎች ምቹና ተጨማሪ ገፀ-በረከት መሆን ትችላለች፤ እየሆነችም ነው።

በአጠቃላይ ፓርቲያችን በያዘው የኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማት የህዝብን ጥቅም ባረጋገጠ ሁኔታ ከተማዋን የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ እየተተገበሩ ያሉ ሰፋፊ ስራዎች ተጠናክረው የሚቀጥሉ ይሆናል። በዚህም ''ቃል በተግባር'' እየተገለፀ ሀገራዊ ሁለንተናዊ ብልጽግና የሚረጋገጥ ሲሆን ከተማችንም በሚመጥናት ስምና ክብር የምትቀመጥ ይሆናል።

14/04/2024

ሰላም፣ ይቅርታ እና ፍቅር ዕሴቶቻችን ናቸው፡፡ በፍቅር መደመርና በይቅርታ መሻገር ዋናው መርሐችን ነው፡፡ ታሪካዊ ስብራቶችን መጠገንና ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን ማጽናት ራእያችን ነው፡፡ መደመር መንገዳችን፣ ብልጽግና መዳረሻችን ነው፡፡

እነዚህ ዕሴቶች በለውጥ ዘመን የሚገጥሙንን ተግዳሮቶች የምንወጣባቸውና እስከቀጣዩ መዳረሻ የምንዳረስባቸው ናቸው፡፡ ያም መዳረሻ የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልጽግና ነው፡፡

የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ክቡር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

14/04/2024

ሰላማችንን በመጠበቅና ጽንፈኝነትን በጋራ በመታገል የሀገራችንን ብልፅግና እውን እናድርግ!

ሰላምን እውን የማድረግም ሆነ ሰላምን የማጣት ወሳኙ እኛው ራሳችን ነን። ዛሬ በእጃችን ያለው ሰላም ነገም በአስተማማኝ ደረጃ ሊቀጥል የሚችለው ሁሉም ለሰላም ተግቶ ሲሰራና ሰላምን የሚያፈርሱ ነገሮችን ያለ ምህረት ሲታገል ብቻ ነው፡፡

ሰላምን ከሚያደፈርሱ ነገሮች አንዱ ደግም ጽንፈኝነት ነው። ጽንፈኝነት ከመደመር ሳንካዎች ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ሲሆን የራስን ፍላጎት በሌሎች ላይ የመጫን ወይም የማስገደድ አባዜ የተጠናወተው ጫፍ የሚይዝ የኋላቀርነት መገለጫ ነው፡፡

መነሻው በተናጠል ፍላጎቷቶች ላይ የሚመሰረትና የሌሎችን መስተጋብሮች ለመቀበል የሚቸገር ነው።

ኢትዮጵያ ደግም ብዝሃ ሀሳብ፣ ብዝሃ ባህል፣ ብዝሃ ቋንቋና ብዝሃ ሃይማኖት ባለቤት ናት።

በመሆኑም የአዲሱ የብልፅግና እሳቤ መሰረት የሚያደርገው የመደመር ትውልድ አስተሳሰብ ትርክቱ የትስስር ትርክት፣ የአብሮነት ትስስር ነው፤ በማናቸውም የፖለቲካ፣ ማህበራዊ፣ የሀገር ደህንነትና ውጭ ጉዳይ ፖሊሲዎች እኔም፣ እኛም፣ በአጠቃላይ ሁላችንም በጋራ መጠቀም አለብን ማለት መቻል አለብን።

በመሆኑም ከጽንፈኝነት በመራቅ፣ ሰላማችንን መጠበቅ እና መንከባከብ አማራጭ የሌለው የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት ነው።

እኛ ኢትዮጵያዊያን ሀገራችን ሰላም ከሆነች የምንናፍቀውን ብልጽግና በአጭር ጊዜ እውን ከማድረግ የሚከለክለን ምድራዊ ሀይል አይኖርም።

ሰላማችንን በመጠበቅና ጽንፈኝነትን በጋራ በመከላከል የሀገራችንን ብልፅግና እውን እናድርግ!

Photos from Lafto woreda five prosperity's post 13/04/2024

የከተማችን ወጣቶች በሌማት ቱሩፋት ፕሮግራም የተፈጠረውን ምቹ ሁኔታ ሊጠቀሙበት እንደሚገባ ተጠቀሰ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ዘርፍ ሀላፊ አቶ የኋላሸት በቀለ እና የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ወጣቶች ሊግ ጽ/ቤት ሀላፊ ወጣት መለሰ አባተ
ከንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ወጣቶች ሊግ ጋር የሌማት ትሩፋትን የሚያጠናክር ፕሮግራም አስጀምረዋል።

በሌማት ቱፋፋት ማጠናከሪያ ፕሮግራሙ ላይ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ዘርፍ ሀላፊ አቶ የኋላሸት በቀለ እንደተናገሩት የሌማት ቱሩፋት እና የከተማ ግብርና ፕሮግራሞች የህዝባችንን የኑሮ ጫና ከማቃለል ባሻገር ለወጣቶች የስራ ዕድል ተጠቃሚነት ዕምቅ አቅም እንዳላቸው አስገንዘበዋል።

የሌማት ቱሩፋት ፕሮግራም ለህዝባችን ህይወት መሻሻል ጉልህ አስተዋፅዖ እንዳለው በመረዳት በሁሉም የከተማችን አካባቢዎች ሳያቆራርጡ ማስቀጠል እንደሚገባም አቶ የኋላሸት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ወጣት ሊግ ጽ/ቤት ሀላፊ ወጣት መለሰ አባተ አገራዊ በሆነው የሌማት ቱሩፋት ፕሮግራም በከተማችን አበረታች ውጤቶች እየተመዘገቡ መሆናቸውን ገልፀው በዛሬው ዕለት 200 የዶሮ ኬጅ እና አንድ ሺህ ዶሮዎች የተበረከተላቸው የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ወጣቶች የራሳቸውን ፈጠራ እና ጥረት ጨምረው ሀብት በመፍጠር ለሌሎችም ወጣቶች አርአያ ሊሆኑ እንደሚገባ ገልፀዋል።

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ወጣት ሊግ ጽ/ቤት ሀላፊ ወጣት አብዱልሀኪም ቡልጉ በበኩላቸው የክ/ከተማውን ወጣት በሌማት ቱሩፋት ፕሮግራም ተጠቃሚ ለማድረግ ብርቱ ጥረት እየተደረገ መሆኑንና ተጨባጭ ውጤትም መመዝገብን መጀመሩን አስረድተዋል።

ሚያዚያ 05/2016 ዓ/ም

13/04/2024

ሰው ተኮርነት ቃልን በተግባር

ዛሬ ረፋዱ ላይ መዲናችን በክብርት ከንቲባዋ አማካይነት ጉለሌ የተቀናጀ ልማት ስራዎችን ሪቫን ቆርጣለች : የእንጀራ ፋብሪካ: የመኖሪያ መንደር: መንገድ : የወተት ምርት :እንዲሁም 22ኛው የምገባ ማዕከል እንደ አንድ ፕሮጀክት ተሰርተው ተመርቀዋል ::

ይህ የተቀናጀ ልማት ጉስቁልና ያጎበጠውን የጉለሌ እናቶች ስብራት እንዲጠግን በክብርት ከንቲባችን ሀሳብ አመንጭነት ነበር ከስልሳ ቀናት በፊት የተጀመረው::

" ጭራሮን መሸከም የጀመርኩት ከእናቴ ሆድ ጀምሮ ነው " የምትል ጎልማሳ እናትን ስብራት መጠገን መቻል : ሰው ተኮርነት የፓርቲያችን ልክ እና መልክ መሆኑን የአረጋገጠም ነው::

የጉለሌ እናቶችን ጭራሮ ለቀማና ሸከማ ጀርባቸውን አጉብጦ :ተስፋቸውን አሟጥጦ ሳለ ዛሬ የደረሰላቸው የጉለሌ የተቀናጀ ልማት የመሪዎቻችንን ሁሉንም አቅም አስተባብሮ ሰውን ሰው የማድረግ ውጤት ነው።

የጉለሌ የተቀናጀ ልማት የእናቶችን ከጭራሮ እስከ ማእድ ዝግጅት የነበረውን መርግ የሚቀንስ ብቻ ሳይሆን በብልጽግና ተምሳሌትዋ አዲስ አበባችን የእናቶችን የኑሮ ፈተና መቅረፍ በጊዜና ሁኔታ ፈተናዎች ውስጥ ሳይንገራገጭ ዘላቂና ቀጣይ የከተማ አስተዳደሩ እና የፓርቲው አቅጣጫ መሆኑን አመላካችም ነው።

ይህ ደግሞ ከፓርቲያችን ሰው ተኮርነት ከመሪዎቻችን ትጋትና ብርታት ጋር የተሰናሰለም ነው።

ፓርቲያችን ሲመረጥ የታክቲክ እና የስትራተጂ ምንጩ ሰው ተኮርነቱ ነው፤ የገባውንም ቃል በፋታ የለሽ ርብርብ ሲመራና ሲሰራ ያረጋገጠውም ሰው ተኮርነቱን ነው ።

በጉለሌ የተቀናጀ ልማት ርብርብ ሌሊት ከጅብ ጋር እየተጋፉ መስራትና መምራት ልበ ቅን ባለሀብቶች በሚልየኖች የሚቆጠር ገንዘባቸውን ብቻ ሳይሆን እውቀትና ትጋታቸውን ጭምር በመለገስ ወገንተኝነታቸውን እንዲያስመሰክሩ የማድረግና የማነሳሳት ብቃት በእርግጥም ብልጽግና ለህዝብ የገባውን ቃል በተግባር ለማረጋገጥ ያለውን ቁርጠኝነት ዝግጅትና ብቃት ያረጋገጠም ነው።

ይህ ፕሮጀክት የእናቶችን ኑሮ ከዱር ጭራሮ ወደ እንጀራ ፋብሪካ ቀይሯል፤ ለምርት ግብዐትም ሆነ ለምርት ግብይት መገናኛ መንገድ ገንብቶላቸዋል፤ ከቤተሰባቸው ተርፎ ለገበያ ሊውል የሚችል የወተት ላሞች እርባታ አጎናጽፏቸዋል። ጣሪያውና ግርግዳ ፌስታልና ላስቲክስ ከሆነ ዳስ አውጥቶ ወደ መኖሪያ ህንጻዎች እመቤትነት አሸጋግሯቸዋል። 22ኛው የምገባ ማዕከል ጉለሌ መገንባቱም ፋይዳው ትልቅ ነው ።

የዚህ ሁሉ ድምር ምስል ደግሞ የብልጽግና ፓርቲ ሰው ተኮርነትንና ቃልን በተግባር የማረጋገጥ ስኬት የገለጸም ነው ።
ችግርን መሰረት አድርጐ በማቀድ : ያቀደውንም በጊዜና በጥራት በመፈጸም ሰው ተኮሩ ፓርቲያችን ብልጽግና ቃሉን በተግባር ሲገልጽ እንደመጣ ሁሉ በቀጣይነትም እየገለጸ እና እያረጋገጠ ይቀጥላል::

Photos from Lafto woreda five prosperity's post 13/04/2024

ይገርማል !
የዛሬው የአድዋ ድል መታሰቢያ ጎብኚዎች።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Photos from Lafto woreda five prosperity's post 13/04/2024

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር "ቃልን በተግባር" በሚል መርህ በመመራት የተቀናጁ የልማት ተግባራትን እያከናወነ ህዝቡን ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል!

ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ካስተላለፉት መልዕክት የተወሰደ ፦

የዛሬ ሁለት ወራት ገደማ የኢትዮጵያን የነፃነትና ሉዓላዊነት ታሪክ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚያስተላልፍና ሀገራዊ ትርክትን ለማፅናት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከት የሚችለውን የዓድዋ ድል መታሰቢያን መርቀን ስራ አስጀምረን ነበር።

ከሳምታት በፊት ደግሞ "የነገዋ" የተሰኘ የሴቶች ተሀድሶ እና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል በአቃቂ ቃሊቲ 11 ወራት ባልበለጠ ጊዜ ውሰጥ ገንብተን በማጠናቀቅ መርቀን ለአገልግሎት ክፍት አድርገን ነበር።

ዛሬ ደግሞ የጉለሌን እናቶች ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ሸክምን በመሰረታዊነት የሚያቃልል "የተቀናጀ የልማት ስራዎች ፕሮጀክት እያስመረቅን እንገኛለን። እነዚህን ሁሉ የተቀናጀ የልማት ንቅናቄዎች በመንግሥት አቅም ብቻ ሳይሆን በግሉ ዘርፍም ተሳትፎ እና ትብብር ነው እያከናወንን ያለነው።

የጀመርነው የሁለንተናዊ ብልፅግና ጉዞ እንዲሳካ ከትልሞቻችንና ግቦቻችን ላይ ለአፍታም አይናችንን አንነቅልም። የተጀማመሩ ስራዎች በተጨባጭ የህዝቡን ኑሮ እየቀየሩ ያሉ ቢሆንም አሁንም ያልሰራናቸው በርካታ የቤት ስራዎች ይጠብቁናል። በመሆኑም ባስመዘገብናቸው ውጤቶች ሳንዘናጋ ለላቀ ድል በትብብር መስራት ይገባናል።

Photos from Lafto woreda five prosperity's post 13/04/2024

በዛሬው እለት እንጦጦ አካባቢ ለሚገኙ የደሃ ደሃ ለሆኑ እና ጫካ ውስጥ በማይመቹ ቦታዎች ሲኖሩ ለነበሩ የተለዩ እናቶች የከተማ አስተዳደሩ ካስገነባቸው የጉለሌ የመኖሪያ ቤቶች ውስጥ 44 ቤቶችን በመግዛት ድጋፍ ካደረጉልን ውስጥ የሚከተሉት ተጠቃሽ ናቸው፦

1. ቲ ኤን ቲ ኮንስትራክሽን - በ16.8 ሚሊዮን ብር አሰር ስቱዲዮ

2. ቶኩማ ስታር ቢዝነስ - በ8.5 ሚሊዮን ብር ሁለት ስቱዲዮ እና ሁለት ባለ አንድ መኝታ

3. መሃመድ ሱጃጃ - በ8.5 ሚሊዮን ብር አምስት ስቱዲዮ

4. ጌታመሳይ ዘመድኩን - በ8.5 ሚሊዮን አምስት ስቱዲዮ

5. ኤም ደብልዩ ኤስ ትሬዲንግ - በ8.5 ሚሊዮን ብር አምስት ስቱዲዮ

6. ቲ ኤፍ ጂ ጀኔራል ትሬዲንግ- በ8.5 ሚሊዮን ብር አምስት ስቱዲዮ

7. ኖህ ሪልስቴት- በ5.3 ሚሊዮን ብር ሁለት ባለአንድ መኝታ ቤቶች

8. ዲሪባ ደፈርሻ - በ4.2 ሚሊዮን ብር አንድ ስቱዲዮ እና አንድ ባለ አንድ መኝታ

9. ማህደር ገብረመድህን ኃ/የተ/የግ/ ኩባኒያ - 4.2 ሚሊዮን ብር አንድ ስቱዲዮ እና አንድ ባለ አንድ መኝታ

10. አኮርዲያ ኢንቨስትመንት ግሩፕ- በ1.6 ሚሊዮን ብር አንድ ስቱዲዮ

ከላይ የተጠቀሱት ተቋማት እና ግለሰቦች በጠቅላላው 74.6 ሚሊዮን ብር የግንባታ ወጪ በመሸፈን 44 የመኖሪያ ቤቶችን ለአቅመ ደካማ የአካባቢው ነዋሪዎች ስላበረከቱ እያመሰገንን፣ በቀጣይም ድጋፍ ለማድረግ የምትፈልጉ ልበ-ቀና ባለሃብቶች የበኩላችሁን አስተዋፅዖ እንድትወጡ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Photos from Lafto woreda five prosperity's post 13/04/2024

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የ9 ወራት የፖለቲካና የድርጅት ስራዎች አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ፡፡

በግምገማ መድረኩም የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለልኝ ወንዴ፣ የፓርቲ ጽ/ቤት ምክትልና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ፍራኖል ሞሲሳ፣ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ መርክነህ ያዕቆብ እና ሌሎች የክፍለ ከተማና የወረዳ ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

በግምገማ መድረኩ በጽ/ቤቱ በ2016 በ9 ወራት ታቅደው የተከናወኑ የፖለቲካና የድርጅት ስራዎች አፈጻጸም፣ የነበሩ ጠንካራ ጎኖችና ጉድለቶች፣ የተወሰዱ የመፍትሔ እርምጃዎች እንዲሁም የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን የሚገልጽ የአፈጻጸም ሪፖርት በዝርዝር ቀርቦ ጥልቅ ውይይትና ግምገማ ተካሄዷል።

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለልኝ ወንዴ በየጊዜው ሲያጋጠሙ የነበሩ ችግሮች የተደራጀና ውጤታማ የአመራር ስምሪት በመስጠት በከፍተኛ ቅንጅትና በመናበብ በመስራት በርካታ ውጤታማ የፖለቲካና የድርጅት ስራዎችን መከናወናቸውን ገልፀዋል።

ኃላፊው አክለውም ህብረተሰብ ተጠቃሚ ያደረግንባቸው በርካታ ሰው ተኮር ተግባራት መከናወናቸውና የክፍለ ከተማችን ሰላምና ደህንነት አስተማማኝ እንዲሆን ህብረተሰቡን በማሳተፍ ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸው በማንሳት በጉድለት የተገመገሙ ጉዳዮች የቀጣይ የአጭር ጊዜ ዕቅድ አካል በማድረግ ወደ ውጤት በመቀየር ሁለንተናዊ ብልፅግናን ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል፡፡

የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ምክትልና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ፍራኖል ሞሲሳ ባለፉት 9 ወራት የተረጋጋ የአመራርና የመዋቅር ስምሪት ስርዓት በመፍጠር በርካታ ስኬቶች መመዝገባቸውን በመግለጽ በተለይም ያጋጠሙ የአመራር የውጤታማነት ችግር፣ የውሸት ሪፖርት፣ ጽንፈኝነትና ሌብነትን አምርረን በመታገል እርምጃ ወስደናል በቀጣይም በትኩረት ይሰራል ብለዋል፡፡

የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ መርክነህ ያዕቆብ በርካታ ውጤታማ የፖለቲካና የድርጅት ስራዎችን መፈጸማቸውን ጠቅሰው በቀጣይም የፓርቲ አሰራርና አደረጃጀት በመከተል ጠንካራ ተቋም በመፍጠር ጠንካራ ፓርቲን ለመገንባት ሁሉም ኃላፊነቱን በሙሉ የአመራር ዲስፕሊን መወጣት እንደሚገባው ገልጸዋል፡፡

በመድረኩም የፓርቲው አመራርና አባላት ለማብቃት የተከናወኑ የግንባታ ስራዎች፣ የከናወኑ የንቅናቄ ስራዎች፣ የአባል ምልመላ፣ የአባላት ወርሃዊ መዋጮ አሰባሰብ፣ የአባላት ዘመናዊ የመረጃ አያያዝና የማጥራት ስራ፣ ህዋሳትን የትግል ማዕከል የማድረግ፣ የሚዲያና የህዝብ ግንኙነት ተግባራት፣ የወጣቶችና የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆናቸው በመድረኩ ተገምግሞዋል፡፡

በመጨረሻም ከመድረኩ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት የቀጣይ አጭር የትኩረት አቅጣጫ በማስቀመጥ መድረኩ ተጠናቋል፡፡

ሚያዚያ 05/2016 ዓ/ም

Photos from Lafto woreda five prosperity's post 13/04/2024

የረዳን ፈጣሪ ይመስገን!

በዛሬው እለት በጉለሌ ክፍለ ከተማ እንጦጦ አካባቢ ለሚኖሩ ወገኖቻችን በገባነው ቃል መሰረት “ቃል በተግባር” ብለን የተቀናጁ ፕሮጀክቶች ጨርሰን አስረክበናል።
የዛሬ ዓመት ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር ባደረግነው ውይይት እንጨት በመልቀም ሲተዳደሩ ለነበሩ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የጉለሌ አካባቢ እናቶች እና የስራ እድል ያላገኙ ወጣቶች ጥያቄ መሰረት፦

1. ለከተማችን ሁለተኛ የእንጀራ ፋብሪካ የሆነው የጉለሌ እንጀራ ማዕከልን፣
2. ጉለሌ የመኖሪያ መንደርን ፣
3. ጉለሌ የወተት ምርት ማዕከልን ፣
4. የምገባ ማዕከልን እና ለአካባቢው ነዋሪዎች ግልጋሎት የሚሰጥ የመንገድ ስራን፣
እነሆ በቃላችን መሰረት በአጭር ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ ለ1533 ነዋሪዎች የስራ ዕድል በመፍጠር ዛሬ አገልግሎት አስጀምረናል።

ማህበራዊ ኃላፊነታችሁን በመወጣት የጉለሌ የተቀናጀ የልማት መንደር እውን እንዲሆን ድጋፍ ያደረጋችሁትን ሴንቸሪ ቢዝነስ ግሩፕ፣ ኢ/ር መታሰቢያ ታደሰ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ፣ ማህደር ገብረመድህን ኃ/የተ/የግ/ኩባኒያ እና ድሪባ ደፈርሻ ጄነራል ኮንስትራክሽን እንዲሁም ፕሮጀክቱን ላስተባበራችሁ አካላት በሙሉ በነዋሪዎቹ ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

12/04/2024

የተቀናጀ ልማት

ዛሬ ዕለተ አርብ ሚያዝያ 04/2016 ዓ.ም ምሽት ይጠብቁ።

Photos from Lafto woreda five prosperity's post 12/04/2024

ማህበሩ ያከናወነው የማጥራት ስራ የሴቶችን ፅናትና ቁርጠኝነት ያሳየ መሆኑ ተጠቆመ

የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ማህበር በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች እና ሰራተኞች የማህበሩን አባላት እና ንብረት ለማጥራት ሲያከናውኑት የነበረውን ውጤት ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የጋራ በማድረግ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን ለይተዋል።

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ /ፅ/ቤት የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ አቶ የኋላሸት በቀለ በውይይቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ማህበር የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከሌሎች ሴት አደረጃጀቶች ጋር እየተረባረበ እንደሚገኝ አስገንዝበዋል።

የማህበሩ ቦርድ የአሰራር ሪፎርም ካደረገ በኋላ ማህበሩ ጉድለቶችን እንዲሞላና የቆመለትን ሴቶችን ተጠቃሚ የማድረግ ዓላማ እንዲሳካ ሴቶችና ህፃናት ፣ ሴቶች ሊግ እና ሌሎችም አደረጃጀቶችና ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን አስተዋፅዖ ማበርከታቸውንም ገልፀዋል።

ማህበሩ በየደረጃው በሚገኙ መዋቅሮቹ ዴሞክራሲን በመትከል የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት እና የከተማችንን አስተማማኝ ሰላም ለማረጋገጥ ከባለድርሻ አካላት ጋር የሚያደርገውን አበረታች ጥረት እንዲያጠናክር አቶ የኋላሽት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ማህበር ፕሬዝዳንት ወ/ሮ እናታለም እንዳለ ማህበሩ በ1990 ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ለሴቶች ሁለንተናዊ ለውጥ ሲተጋ ቢቆይም ንብረቶቹን በአግባቡ ማስተዳደር ላይ እና ትክክለኛ የአባላቱን ቁጥር ማወቅ ላይ ጉድለቶች እንደነበሩበት አስረድተዋል ።

የማህበሩ ቦርድ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ማህበሩ ያሉትን ትክክለኛ የአባላት ቁጥር ለማወቅ እና ንብረቶቹን ለማጥራት ከባለድርሻ አካላት ባሉበት የጋራ ዕቅድ ተዘጋጅቶ ወደ ስራ በመገባቱ ለቀጣይ ስራዎች ፅኑ መሰረት የሚሆኑ ተግባራት መከናወናቸውን አስገንዝበዋል።

የማህበሩን ትክክለኛ የአባላት ቁጥር ለማወቅ በየክ /ከተሞች በተደረገው ጥልቅ የማጥራት ስራ አሁን ላይ የማህበሩ አጠቃላይ አባል 471 ሺህ 44 መሆናቸው መረጋገጡን ወ /ሮ እናታለም ገልፀዋል።

በሁለተኛ ደረጃ የተከናወነው የማህበሩን ንብረት የማጥራት ተግባር በርካታ ተግዳሮቶች ተደቅነውበት የነበረ ቢሆንም በሴትነት ፅናት እና ቁርጠኝነት ለውጤት መብቃቱ ተጠቅሷል።

ማህበሩ የሚያስተዳድራቸው ለሴቶች ተጠቃሚነት መዋል የነበረባቸውን የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶች እጅግ በዝቅተኛ ኪራይ በመከራየት እና ለሶስተኛ ወገን በማከራየት ውስን ግለሰቦች የሚጠቀሙባቸው ሆነው መቆየታቸው በማጥራት ሂደቱ መረጋገጡ ተመላክቷል።

ማህበሩ አሁን ላይ 71 የንግድ እና 48 የመኖሪያ ቤቶች እንዳሉት በማጥራቱ መረጋገጡን ያስረዱት የማህበሩ ፕሬዝዳንት ከአባላት በተጨማሪ የህግ ባለሙያዎችን እና የሎችንም ባለድርሻ አካላትን አስተዋፅዖ አድንቀዋል።

ከማጥራቱ በፊት ማህበሩ በሶስት ወር 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር ገቢ ብቻ ያገኝ እንደነበር የጠቆሙት ወ/ሮ እናታለም አሁን ላይ ቤቶቹ ያሉበትን አካባቢ መሰረት ባደረገ መልኩ በመከራየታቸው በየወሩ 1 ነጥብ 8 ብር ገቢ ማስገኘት መጀመራቸውን ገልፀዋል።

የከተማ የበላይ ጠባቂ የሆኑት ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና ባለድርሻ አካላት ማህበሩ ለሴቶች ተጠቃሚነት የሚያደርገው ጥረት እንዲጎለብት የሚያደርጉት አበረታች ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ወ/ሮ እናታለም ጥሪአቸውን አስተላልፈዋል።

የማህበሩ ም/ ፕሬዝዳንት ወ/ሮ አፀደ ሀበነ ለማህበሩ ሪፎርም በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላት ተገቢውን ድጋፍ ማድረጋቸውን ጠቅሰው ለከተማችን ሴቶች ተጠቃሚነት በቀጣይም በቅንጅት እንደሚሰራ አስረድተዋል።

የማህበሩ ዋና ፀሐፊ ወ/ሮ ኦድንግል ወሌ በበኩላቸው በማጥራት ሂደቱ ከተደረገው ርብርብ ባሻገር በዛሬው ውይይትም የአመራሩን እና የአባላትን ተነሳሽነትና አቅም ከፍ የሚያደረጉ ተጨማሪ ግብአቶች መገኘታቸውን ገልፀዋል።

ማህበሩ የተደቀኑበትን ችግሮች ፊት ለፊት በመጋፈጥ ያከናወነውን ጥልቅ የማጥራት ስራ ያደነቁት የውይይቱ ተሳታፊዎች በቀጣይም ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።

በፕሮግራሙ ማጠቃለያም የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ክ /ከተሞች እና ባለድርሻ አካላት የእውቅና እና የምስጋና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

Want your organization to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address

Addis Ababa
Other Political Organizations in Addis Ababa (show all)
African Union African Union
Addis Abeba
Addis Ababa, 1111

A UNITED & STRONG AFRICA

Qabsoo Bilisummaa Qabsoo Bilisummaa
Finfinne
Addis Ababa, 2560

Injifannoon Kan Abbaa dhugaati

GMN Grand Media Network GMN Grand Media Network
Addis Ababa

Manegment

Bole Wereda 1 Prosperity Party ብልጽግና Bole Wereda 1 Prosperity Party ብልጽግና
Bole Michael
Addis Ababa, G.P.O

ይህ በቦሌ ክ/ከተማ ስር በሚገኘው በወረዳ 1 ብልጽግና ፓርቲ የ?

Anwar Tuti Anwar Tuti
Somaliya
Addis Ababa, HADLIYAAAA

Addis Ketema Woreda 6 Prosperity Party-ብልፅግና Addis Ketema Woreda 6 Prosperity Party-ብልፅግና
Addis Ketema
Addis Ababa

ለሁሉም ዜጋ ብልፅግናን ለማረጋጋጥ እንሰራለን

Free state movement for Addis ababa Free state movement for Addis ababa
Addis Ababa

Political

Imala Haqaa Imala Haqaa
Addis Ababa

Kaayyoon Kenya haqaa dhokate basne baketi mulisudhaa kanafu nu hordofun haqaa cina dhabachun eru nun

Paartii Badhaadhinaa Kutaa Magaalaa Araadaa Paartii Badhaadhinaa Kutaa Magaalaa Araadaa
Belay Zeleke Street, Pissa Road
Addis Ababa, 251,56

providing facts of prosperity party

Abdallaa  Zeenu Abafogi .Follow Abdallaa Zeenu Abafogi .Follow
Jiimmaa
Addis Ababa