Commercial Bank of Ethiopia Trade Union

Commercial Bank of Ethiopia Trade Union

Nearby finance companies

CBE NOOR
CBE NOOR

ማኅበሩ የተመሠረተበት ዓመት :- ታኅሣስ 2 /1960 ዓ ም
የአባላት ብዛት:- ከ 35,000 በላይ

Photos from Commercial Bank of Ethiopia's post 13/06/2024
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማህበር ከትናንት እስከ ዛሬ:: 05/06/2024

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማህበር ከትናንት እስከ ዛሬ::
*********************************************

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማህበር ከትናንት እስከ ዛሬ በሚል ሃሳብ የተዘጋጀዉን የማሕበሩን ታሪክ በቴሌቭዥን ያመለጣችሁ እንድትከታተሉ በድጋሚ ጋብዘናል::

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማሕበር
በተባበረ ክንድ ለተሻለ ሕይወት እንተጋለን!

Telegram https://t.me/CBETUOfficial
Facebook https://www.facebook.com/Tradeunion2018
Website https://cbetradeunion.cbe.com.et
ስልክ ቁጥር፡- 0906570000 ዘወትር በሥራ ሰዓት ይደዉሉ፡፡

https://youtu.be/T9JlAhV5NW0?si=0jFCnJJZY5bcNkVs

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማህበር ከትናንት እስከ ዛሬ:: #የንግድ ባንክ #ሠራተኛ ማኅበር #የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ #ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!Copyright © CBE (Commercial Bank of Ethiopia)Follow us on:☞Facebook: https://www.facebook.com/combanket...

Photos from Commercial Bank of Ethiopia Trade Union's post 03/06/2024

የውስጥ ስፖርት ውድድር ተጀመረ
******************

የሰራተኞችን ማህበራዊ ትስስር ማጠናከርና ብቁና ጤናማ ሠራተኞችን ለማፍራት ዓላማ በማድረግ የሚከናወነዉ የዉስጥ ዉደድር ተጀምሯል፡፡

ከዉድድሩ መክፈቻ ቀደም ብሎ ግንቦት 23 ቀን 2016 ዓ.ም ከሠራተኛ ማሕበሩና አና ከባንኩ የተወከሉ የስፖርት ዉድድሩ ኮሚቴ፤ የማሕበራችን ፕሬዝደንትና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስፖርት ለሁሉም ተወካይ በተገኙበት ስለ ዉድድሩ አካሄድ መግለጫ በመስጠት፣ የዲስትሪክቶች ዕጣ ድልድል እና የስፖርት ትጥቅ ሥርጭት ተደርጓል፡፡

ዉድድሩም ግንቦት 25 ቀን 2016 ዓ.ም በአበበ ቢቂላ ስታዲየም የባንካችን ፕሬዝደንት እና ማኔጀመንት አባላት፤ የማሕበራችን ፕሬዝደንት እና ሥራ አስፈፃሚዎች እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ የአዲስ አበባ ከተማ ስፓርት ለሁሉም ኮሚቴ ፕሬዘዳንት እና ተወዳዳሪዎች ማለትም የአስሩ ዲስትሪክቶች፣ የዋናዉ መ/ቤት እና የኮሜርሻል ኖሚኒስ ተጫዋቾች እና ደጋፊዎች በተገኙበት ዉድድሩን በድምቀት የተከበሩ አቶ አቤ ሳኖ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት ከተጋባዥ እንግዶች ጋር በመሆን አስጀምረዉታል፡፡

በዉድድሩ መክፈቻ ዕለትም ሁለት ጨዋታዎች የተካሄዱ ሲሆን የዋናው መስሪያ ቤት ማኔጅመንት ቡድን ከ አራዳ እና የካ ዲስትሪክት ጥምረት ማኔጅመንት ቡድን ጋር ግጥሚያ አድርጎ ዋናው መስሪያ ቤት ማኔጅመንት ቡድን በአቶ አቤ ሳኖ መክፈቻ ጎል መምራት ቢችልም የአራዳ እና የካ ጥምረት ጎል በማስቆጠር ጨዋታው በአቻ ውጤት ተጠናቋል። በሠራተኞች መካከል በተደረገዉ ጨዋታ ደግሞ የዋናው መስሪያ ቤት ሰራተኞች ቡድን ከጨዋታ ብልጫ ጋር 6 ለ 2 የኮሜርሻል ኖሚኒስ ቡድንን ማሸነፍ ችሏል።

ዉድድሩም ለ1 ወር ከ 15 ቀን የሚቆይ ሲሆን ዲስትሪክቶች እና የዋና መ/ቤት ሠራተኞችም በዉድድር ቦታዉ በመገኘት ዉድድሩን እንዲመለከቱ እና ድጋፍ እንዲሰጡ ተጋብዘዋል፡፡ ከአዲስ አበባ ዉጪ ላሉ ዲስትሪክቶችም የስፖርት ትጥቅ ተመርቶ እንዳለቀ በቅርቡ የሚላክ ይሆናል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማሕበር
በተባበረ ክንድ ለተሻለ ሕይወት እንተጋለን!

Telegram https://t.me/CBETUOfficial
Facebook https://www.facebook.com/Tradeunion2018
Website https://cbetradeunion.cbe.com.et
ስልክ ቁጥር፡- 0906570000 ዘወትር በሥራ ሰዓት ይደዉሉ፡፡

02/06/2024

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሲስተም ማሻሻያ ሥራ ጋር በተገናኘ መጋቢት 7 ቀን 2016 ዓ.ም. በተፈጠረ ችግር ምክንያት ያለአግባብ ተወስዶ ከነበረው ብር 801.4 ሚሊየን ገንዘብ ውስጥ 98.9 በመቶ ወይም ብር 792.71 ሚሊየን የሚሆነውን ማስመለስ ችሏል፡፡ ቀሪውን የማስመለስ ሥራውን ቀጥሏል።

CBE Trade Union 01/06/2024

ዶክዩመንተሪይ ክፍል ሁለት ያመለጣችሁ
********************

ዛሬ ቅዳሜ 24/09/2016 ዓ.ም ከቀኑ 11:30 በአማራ ቴሌቪዥን እንዲሁም
ነገ እሁድ 25/09/2016 ዓ.ም ከምሽት 2፡30 በፋና ቴሌቪዥን ስለሚተላለፍ እንድትከታተሉ በድጋሚ ገብዘናል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማሕበር
በተባበረ ክንድ ለተሻለ ሕይወት እንተጋለን!

Telegram https://t.me/CBETUOfficial
Facebook https://www.facebook.com/Tradeunion2018
Website https://cbetradeunion.cbe.com.et
ስልክ ቁጥር፡- 0906570000 ዘወትር በሥራ ሰዓት ይደዉሉ፡፡

CBE Trade Union CBE Trade Union is one of the few long ageded trade unions in Ethiopia and has been working diligently more than 56 years.

CBE Trade Union 30/05/2024

#ክፍል ሁለት #

ስለ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማሕበር ከምስረታ ጀምሮ ያለዉን ታሪክ የሚገልፅ ዶክዩመንተሪይ ክፍል ሁለት እንዲትከታተሉ በአክብሮት ጋብዘኖታል፡፡

ክፍል ሁለት የሚተላለፈዉ
23/09/2016 ዓ.ም አርብ ምሽት 2፡00 ሰዓት በEBS ቴሌቪዥን
24/09/2016 ዓ.ም ቅዳሜ ከቀኑ 11:30 በአማራ ቴሌቪዥን
25/09/2016 ዓ.ም እሁድ ምሽት 2፡30 በፋና ቴሌቪዥን የሚተላለፍ ይሆናል፡፡

ክፍል ሁለትን በድጋሚ ለመመልከት
26/09/2016 ዓ.ም ሰኞ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት በፋና ቴሌቪዥን
27/09/2016 ዓ.ም ማክሰኞ ምሽት 1፡00 ሰዓት በEBS ቴሌቪዥን
27/09/2016 ዓ.ም ማክሰኞ ምሽት 2፡30 በአማራ ቴሌቪዥን

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማሕበር
በተባበረ ክንድ ለተሻለ ሕይወት እንተጋለን!

Telegram https://t.me/CBETUOfficial
Facebook https://www.facebook.com/Tradeunion2018
Website https://cbetradeunion.cbe.com.et
ስልክ ቁጥር፡- 0906570000 ዘወትር በሥራ ሰዓት ይደዉሉ፡፡

CBE Trade Union CBE Trade Union is one of the few long ageded trade unions in Ethiopia and has been working diligently more than 56 years.

CBE Trade Union 27/05/2024

ስለ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማሕበር ከምስረታ ጀምሮ ያለዉን ታሪክ የሚገልፅ ዶክዩመንተሪይ ክፍል አንድ በድጋሚ ስለምተላለፍ እንዲትከታተሉ በአክብሮት ጋብዘኖታል፡፡

ዶክዩመንተሪዉ በድጋሚ የሚተላለፈዉ፡-
• ዘሬ 19/09/2016 ዓ.ም ሰኞ ቀን 6፡00 ሰዓት በፋና ቴሌቪዥን
• ነገ 20/09/2016 ዓ.ም ማክሰኞ ምሽት 2፡30 በአማራ ቴሌቪዥን
• ነገ 20/09/2016 ዓ.ም ማክሰኞ ምሽት 1፡00 ሰዓት በEBS ቴሌቪዥን

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማሕበር
በተባበረ ክንድ ለተሻለ ሕይወት እንተጋለን!

Telegram https://t.me/CBETUOfficial
Facebook https://www.facebook.com/Tradeunion2018
Website https://cbetradeunion.cbe.com.et
ስልክ ቁጥር፡- 0906570000 ዘወትር በሥራ ሰዓት ይደዉሉ፡፡

CBE Trade Union CBE Trade Union is one of the few long ageded trade unions in Ethiopia and has been working diligently more than 56 years.

CBE Trade Union 25/05/2024

ዶክዩመንተሪይ እንድትመለከቱ ስለመጋበዝ

ዉድ የባንካችን ማሕበረሰብ እና የማሕበራችን አባላት በሙሉ ስለ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማሕበር ከምስረታ ጀምሮ ያለዉን ታሪክ የሚገልፅ ዶክዩመንተሪይ ተዘጋጅቶ በቴሌቭዥን በሁለት ክፍል ስለሚተላለፍ እንድትከታተሉ በአክብሮት ተጋብዛችሁዋል፡፡ ዶክዩመንተሪዉ የሚተላለፍባቸዉ ቀናትና የቴሌቪዥን ጣቢያዎች

ክፍል አንድ የሚተላለፈዉ
ዛሬ ቅዳሜ 17/09/2016 ዓ.ም ከቀኑ 11:30 ሰዓት በአማራ ቴሌቪዥን
እሁድ 18/09/2016 ዓ.ም ምሽት 2፡30 በፋና ቴሌቪዥን የሚተላለፍ ይሆናል፡፡

ክፍል አንድን በድጋሚ ለመመልከት
19/09/2016 ዓ.ም ሰኞ ቀን 6፡00 ሰዓት በፋና ቴሌቪዥን
20/09/2016 ዓ.ም ማክሰኞ ምሽት 2፡30 በአማራ ቴሌቪዥን
20/09/2016 ዓ.ም ማክሰኞ ምሽት 1፡00 ሰዓት በEBS ቴሌቪዥን የሚተላለፍ ይሆናል፡፡

ስለሆነም ሁሉም ፕሮግራሞች የሚተላለፉት በመደበኛ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቴሌቪዥን ፕሮግራም ሰዓት ላይ መሆኑን ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማሕበር
በተባበረ ክንድ ለተሻለ ሕይወት እንተጋለን!

Telegram https://t.me/CBETUOfficial
Facebook https://www.facebook.com/Tradeunion2018
Website https://cbetradeunion.cbe.com.et
ስልክ ቁጥር፡- 0906570000 ዘወትር በሥራ ሰዓት ይደዉሉ፡፡

CBE Trade Union CBE Trade Union is one of the few long ageded trade unions in Ethiopia and has been working diligently more than 56 years.

CBE Trade Union 15/05/2024

ድጋፍ ዓይነት ስምንት
********************

ሠራተኛ ጡረታ ሲወጣ የሚደረግ ድጋፍ

ይህ ድጋፍ የሚደረገዉ አባል ሠራተኛ ወይም የሥራ መሪ በጉብዝና ጊዜዉ ባንኩን ሲያገለግል ቆይቶ ጡረታ ሲወጣ ለዚህ አስተዋፅዖ ዕዉቅና ለመስጠት ታስቦ የሚደረግ ድጋፍ ነዉ፡፡

ይህ ድጋፍ የሥራ መሪ ከመሆናቸዉ በፊት የማህበሩ አባል ያልነበሩ ወይም አባልነታቸዉን በመሃል ላቋረጡ ሠራተኞች ጡረታ ሲወጡ አይከፈላቸዉም፡፡

የድጋፉ ዓይነት እና መጠን

• የምስጋና ደብዳቤና የምስክር ወረቀት
• በአባልነት እያሉ ጡረታ ለሚወጡ ሠራተኞች 15,000.00ብር
• አባል የነበሩ እና ከሥራ መሪነት ጡረታ የሚወጡ ሠራተኞች 7,500.00ብር

መሟላት ያለባቸዉ መስፈርቶች

• ጡረታ ስለ መዉጣቱ የሚገልፅ ከባንኩ የሚሰጥ ማስረጃ
• የጡረታ መታወቂያ ደብተር
• ሁለት ጉርድ ፎሮግራፍ

የጥያቄ አቀራረብ

ሠራተኛዉ በአካል ወደ ማህበሩ ጽ/ቤት ቀርቦ ለዚህ ጉዳይ የተዘጋጀ ቅፅ በመሙላት ጥያቄዉን ያቀርባል፡፡

የጊዜ ገደብ

ይህ ጥያቄ ተቀባይነት የሚኖረዉ አባል ሠራተኛዉ ከባንኩ ጋር ያለዉ የሥራ ግንኙነት ከተቋረጠበት ቀን ጀምሮ ባለዉ አንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ብቻ ነዉ፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማሕበር
በተባበራ ክንድ ለተሻለ ሕይወት እንተጋለን!

Telegram https://t.me/CBETUOfficial
Facebook https://www.facebook.com/Tradeunion2018
Website https://cbetradeunion.cbe.com.et
ስልክ ቁጥር፡- 0906570000 ዘወትር በሥራ ሰዓት ይደዉሉ፡፡

CBE Trade Union CBE Trade Union is one of the few long ageded trade unions in Ethiopia and has been working diligently more than 56 years.

CBE Trade Union 09/05/2024

የድጋፍ ዓይነት ሰባት
*****************

አባል ሠራተኛ በገዛ ፈቃዱ ሥራ ከለቀቀ የሚደረግ ድጋፍ
------------------------------------------------------------
ይህ ድጋፍ አባል ሠራተኛ በማንኛውም ምክንያት በገዛ ፈቃዱ ከባንኩ ጋር ያለውን የሥራ ውል በቋሚነት ሲያቋርጥ የሚደረግ የመሸኛ ድጋፍ ነው፡፡

የድጋፍ መጠን

• ከጀማሪ እስከ 3 ዓመት ባለዉ ጊዜ ዉስጥ በገዛ ፈቃድ ለለቀቀ ምንም ድጋፍ አይደረግም
• 3 ዓመት አገልግሎ በገዛ ፈቃድ ለለቀቀ 2,000ሺ ብር ድጋፍ ይደረጋል
• 4 ዓመት አገልግሎ በገዛ ፈቃድ ለለቀቀ 2,500 ብር ድጋፍ ይደረጋል
• 5 ዓመት አገልግሎ በገዛ ፈቃድ ለለቀቀ 3,000ሺ ብር ድጋፍ ይደረጋል
• 6 ዓመት አገልግሎ በገዛ ፈቃድ ለለቀቀ 3,500 ብር ድጋፍ የሚደረግ ይሆናል፡፡

መሟላት ያለባቸዉ መስፈርቶች

• የአባልነት መዋጮውን ሳያቆራርጥ የከፈለ፣
• በገዛ ፈቃድ መልቀቁን የሚገልፅ ከባንኩ የተሰጠ ማስረጃ
• የባንኩን መታወቂያ (ማንነቱን የሚያረጋግጥ ሌላ መታወቂያ) ኮፒ

የጥያቄ አቀራረብ

አባል ሠራተኛዉ በአካል ወደ ማህበሩ ጽ/ቤት ቀርቦ ለዚህ ጉዳይ የተዘጋጀዉን ቅፅ በመሙላት ጥያቄዉን ያቀርባል፡፡

የጊዜ ገደብ

ይህ ጥያቄ ተቀባይነት የሚኖረዉ አባል ሠራተኛዉ ከባንኩ ጋር ያለዉ የሥራ ግንኙነት ከተቋረጠበት ቀን ጀምሮ ባሉት ሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ ብቻ ነዉ፡፡
ይቀጥላል………….

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማሕበር
በተባበራ ክንድ ለተሻለ ሕይወት እንተጋለን!

Telegram https://t.me/CBETUOfficial
Facebook https://www.facebook.com/Tradeunion2018
Website https://cbetradeunion.cbe.com.et
ስልክ ቁጥር፡- 0906570000 ዘወትር በሥራ ሰዓት ይደዉሉ፡፡

CBE Trade Union CBE Trade Union is one of the few long ageded trade unions in Ethiopia and has been working diligently more than 56 years.

04/05/2024

እንኳን አደረሳችሁ!

ለመላዉ የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ በሰላም አደረሳችሁ፡፡

መልካም በዓል!!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማሕበር
በተባበራ ክንድ ለተሻለ ሕይወት እንተጋለን!

Telegram https://t.me/CBETUOfficial
Facebook https://www.facebook.com/Tradeunion2018
Website https://cbetradeunion.cbe.com.et
ስልክ ቁጥር፡- 0906570000 ዘወትር በሥራ ሰዓት ይደዉሉ፡፡

30/04/2024

በኢትዮጵያ ለ49ኛ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ135ኛ ጊዜ ለሚከበረው የሠራተኞች ቀን እንኳን አደረሳችሁ!

መልካም የላባደሮች ቀን!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማሕበር
በተባበራ ክንድ ለተሻለ ሕይወት እንተጋለን!

Telegram https://t.me/CBETUOfficial
Facebook https://www.facebook.com/Tradeunion2018
Website https://cbetradeunion.cbe.com.et
ስልክ ቁጥር፡- 0906570000 ዘወትር በሥራ ሰዓት ይደዉሉ፡፡

Photos from Commercial Bank of Ethiopia Trade Union's post 30/04/2024

ድጋፍ ተደረገላቸዉ፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማሕበር ለክበብ ሠራተኞች ድጋፍ አደረገ፡፡

በአዲስ አበባ የሚገኙ የክበብ ሠራተኞች በእጅግ ዝቅተኛ ደመወዝ ለረዥም ጊዜ ያገለገሉ መሆናቸዉን ከግንዛቤ በማስገባት በቂ ባይባልም ለበዓል ጥቂትም ነገር ቢሆን ወጪ እንዲሸፍን በማሰብ የተዘጋጀ ድጋፍ ነዉ፡፡

በዚህም መሠረት ክበቡን ከ 30 ዓመት በላይ ላገለገሉ ሠራተኞች 15ሺ ብርና የቁሳቁስ ድጋፍ ከ 20 ዓመት በላይ ላገለገሉ ሠራተኞች 10 ሺ ብርና የቁሳቁስ ድጋፍ እንዲሁም ከ 15 ዓመት በላይ ላገለገሉ ሠራተኞች 5ሺ ብርና የቁሳቁስ ድጋፍ ተበርክቶላቸዋል፡፡

የዚህ ድጋፍ ዋናዉ ዓላማ ሠራተኛ ማሕበሩ ማሕበራዊ ሃላፊነት መወጣት እና የክበብ ሠራተኞቹ በክበባቱ የሚጠቀሙ የባንኩን ሠራተኞች ደስተኛ ሆነዉ እንዲያገለግሉ ማበረታቻ እንዲሆን ያለመ ነዉ፡፡

በዕለቱም የማሕበራችን ፕሬዝደንት እና ሥራ አስፈፃሚዎች ተገኝተዉ ለክበብ ሠራተኞች ይህንን ድጋፍ እና እዉቅና የሰጡ ሲሆን አጠቃላይ በ 7 ክበባት የሚሰሩ ከ 136 በላይ ሠራተኞች የድጋፉ ተጠቃሚ መሆን ችለዋል፡፡

በመጨረሻም የክበባት ሠራተኞቹም ይህ ድጋፍ አዲስና ከዚህ በፊት ተደርጎላቸዉ የማያዉቁት በመሆኑ ደስተኛ መሆናቸዉን ገልፀዉ አመስግነዋል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማሕበር
በተባበራ ክንድ ለተሻለ ሕይወት እንተጋለን!

Telegram https://t.me/CBETUOfficial
Facebook https://www.facebook.com/Tradeunion2018
Website https://cbetradeunion.cbe.com.et
ስልክ ቁጥር፡- 0906570000 ዘወትር በሥራ ሰዓት ይደዉሉ፡፡

Photos from Commercial Bank of Ethiopia Trade Union's post 29/04/2024

ዜና ስፖርት
*********

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 3 ሙገር ሲሚንቶ 1

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች እግር ኳስ ቡድን ሙገር ሲሚንቶ ሠራተኞች እግር ኳስ ቡድንን 3 ለ 1 አሸነፈ፡፡

በኢትዮጵያ ሠራተኞች ማሕበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) አዘጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘዉ የበጋ ስፓርት ዉድድር ላይ በአጠቃላይ ዘጠኝ እግር ኳስ ቡድኖች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

በዚህ ዉድድር እየተሳተፈ የሚገኘዉ የባንካችን ሠራተኞች እግር ኳስ ቡድን እስከ አሁን ሰባት ጨዋታ ያደረገ ሲሆን ከዚህም ስድስቱን በማሸነፍና አንዱን አቻ በመዉጣት በጥቅሉ አሥራ ዘጠኝ ነጥብ
በመሰብሰብ ወድድሩን እየመራ ይገኛል፡፡

የስፖርት ዉድድሩ ከአንድ ጨዋታ በኋላ ይጠናቀቃል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማሕበር
በተባበራ ክንድ ለተሻለ ሕይወት እንተጋለን!

Telegram https://t.me/CBETUOfficial
Facebook https://www.facebook.com/Tradeunion2018
Website https://cbetradeunion.cbe.com.et

ስልክ ቁጥር፡- 0906570000 ዘወትር በሥራ ሰዓት ይደዉሉ፡፡

CBE Trade Union 27/04/2024

የድጋፍ ዓይነት ስድስት
********************

አባል ሠራተኛ ከሥራ ከተሰናበተ የሚደረግ ድጋፍ
---------------------------------------------------
ይህ ድጋፍ አባል ሠራተኛዉ ከራሱ ፈቃድ ውጪ ማለትም በባንኩ ዉሳኔ ከሥራ እንዲሰናበት ከተደረገ የሚሰጥ የስንብት ክፍያ ነዉ፡፡

የድጋፍ መጠን
1. ሠራተኛዉ ታስሮ ወይም ታግዶ በነበረ ጊዜ ድጋፍ ተደርጎለት ከሆነ
• ከጀማሪ እስከ 3 ዓመት 3,000.00 ብር
• ከ3 በላይ እስከ 7 ዓመት 5,000.00 ብር
• ከ7 በላይ እስከ 15 ዓመት 10,000.00 ብር
• ከ15 ዓመት በላይ 15,000.00 ብር

2. ሠራተኛዉ በመታሰር ወይም በመታገድ ምክንያት ምንም የገንዘብ ድጋፍ ያልተደረገለት ከሆነ
• ከጀማሪ እስከ 3 ዓመት 7,000.00 ብር
• ከ3 በላይ እስከ 7 ዓመት 10,000.00 ብር
• ከ7 በላይ እስከ 15 ዓመት 15,000.00 ብር
• ከ15 ዓመት በላይ 20,000.00 ብር

መሟላት ያለባቸዉ መስፈርቶች

•የሙከራ ጊዚውን የጨረሰ፣
•የአባልነት መዋጮውን ሳያቆራርጥ የከፈለ
•ከባንኩ ስለ መሰናበቱ የሚገልፅ ከባንኩ የተሰጠ ማስረጃ
•መታወቂያ ኮፒ (ወደ ባንኩ የተመለሰ ከሆነ ማንነቱን የሚያረጋግጥ ሌላ መታወቂያ)

የጥያቄ አቀራረብ
ሠራተኛዉ በአካል ወደ ማህበሩ ጽ/ቤት ቀርቦ ለዚህ ጉዳይ የተዘጋጀ ቅፅ በመሙላት ጥያቄዉን ያቀርባል፡፡

የይርጋ ጊዜ
ይህ ጥያቄ ተቀባይነት የሚኖረዉ አባል ሠራተኛዉ ከባንኩ ጋር ያለዉ የሥራ ግንኙነት ከተቋረጠበት ቀን ጀምሮ ባሉት 2 ወራት ጊዜ ውስጥ ብቻ ነዉ፡፡
ይቀጥላል………….

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማሕበር
በተባበራ ክንድ ለተሻለ ሕይወት እንተጋለን!

Telegram https://t.me/CBETUOfficial
Facebook https://www.facebook.com/Tradeunion2018
Website https://cbetradeunion.cbe.com.et
ስልክ ቁጥር፡- 0906570000 ዘወትር በሥራ ሰዓት ይደዉሉ፡፡

CBE Trade Union CBE Trade Union is one of the few long ageded trade unions in Ethiopia and has been working diligently more than 56 years.

CBE Trade Union 23/04/2024

የድጋፍ ዓይነት አምስት
**********************

አባል ሠራተኛ በጊዜያዊነት ከሥራ ከታገደ የሚደረግ ድጋፍ
---------------------------------------------------------
ይህ ድጋፍ አባል ሠራተኛዉ በማንኛዉም ምክንያት ከመደበኛ ሥራው በሚታገድበት ወቅት የሚደረግ ድጋፍ ሆኖ ይህ ድጋፍ ሊደረግ የሚችለዉ ሠራተኛዉ ማረሚያ ቤት በመቆየት ምክንያት ድጋፍ ያልተደረገለት ከሆነ ብቻ ነዉ፡፡
በተጨማሪም ይህ ድጋፍ ለአንድ አባል ሠራተኛ ሊሰጥ የሚችለዉ በሦስት ዓመት ውስጥ አንድ ጊዜ ብቻ ነዉ፡፡

የድጋፍ ዓይነት እና መጠን
ሀ. የሕግ ድጋፍ፡
ማህበሩ በጽ/ቤቱ ቀጥሮ የሚያሰራዉን ወይም ሌላ የሕግ ባለሙያ በመጠቀም የሕግ ምክር አገልግሎት ይሰጣል፡፡

ለ. የገንዘብ ድጋፍ፡
ዕግድ የሚቆየዉ ለአንድ ወር ብቻ በመሆኑ ሠራተኛዉ ለፍ/ቤት ክርክርም ይሁን ለሌላ ጉዳይ ሊያዉለዉ የሚችል
• ከ15 ቀን እስከ 45 ቀን ለታገደ ብር 3,000 (ሦስት ሺህ ብር) እና
• ከ45 ቀን በላይ ለታገደ አባል ሠራተኛ ብር 7,000 (ሰባት ሺህ ብር) ይከፈላል፡፡

መሟላት ያለባቸዉ መስፈርቶች

• የሙከራ ጊዚውን የጨረሰ፣
• የአባልነት መዋጮውን ሳያቆራርጥ የከፈለ
• ከባንኩ የተሰጠው የእግድ ደብዳቤ፣
• ከእግዱ በኋላ በባንኩ የተሰጠው የውሳኔ ደብዳቤ፡ ማለትም ወደ ሥራ የተመለሰበት ወይም የተሰናበተበት ወይም ውሳኔ ያልተሰጠዉ እና ዕግድ ላይ ያለ መሆኑን የሚገልፅ የባንኩ ወይም የፍ/ቤት ማስረጃ
• የባንኩ መታወቂያ ኮፒ (ወደ ባንኩ የተመለሰ ከሆነ ማንነቱን የሚያረጋግጥ ሌላ መታወቂያ)

የጥያቄ አቀራረብ
አባል ሠራተኛዉ በተጠሪ ጽ/ቤቶች ወይም በማህበሩ ዋና ጽ/ቤት በአካል በመገኘት/ህጋዊ ወኪል እና መስፈርቶችን በማሟላት ለዚህ ጉዳይ የተዘጋጀ የድጋፍ መጠየቂያ ቅፅ በመሙላት ጥያቄዉን ያቀርባል፡፡

ጥያቄዉ የቀረበዉ ለተጠሪ ጽ/ቤቶች ከሆነ በሸኚ ደብዳቤ ወደ ዋናዉ የማህበሩ ጽ/ቤት ይልካሉ፤ ክፍያዉ የሚፈፀመዉ በማህበሩ ዋና ጽ/ቤት ነዉ፡
የጊዜ ገደብ
የዚህ ድጋፍ ጥያቄ ከመጀመሪያዉ ጀምሮ መቅረብ የሚችል ሆኖ ሠራተኛዉ ወደ ሥራ ከተመለሰ በኋላ በማንኛዉም ሁኔታ ከ3 ወራት በላይ ከቆየ ተቀባይነት የለዉም፡፡
ይቀጥላል………….

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማሕበር
በተባበራ ክንድ ለተሻለ ሕይወት እንተጋለን!

Telegram https://t.me/CBETUOfficial
Facebook https://www.facebook.com/Tradeunion2018
Website https://cbetradeunion.cbe.com.et ይቀላቀሉ
ስልክ ቁጥር፡- 0906570000 ዘወትር በሥራ ሰዓት ይደዉሉ፡፡

CBE Trade Union CBE Trade Union is one of the few long ageded trade unions in Ethiopia and has been working diligently more than 56 years.

21/04/2024

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሲስተም ማሻሻያ ሥራ ጋር በተገናኘ መጋቢት 7 ቀን 2016 ዓ.ም. በተፈጠረ ችግር ምክንያት ብር 801.4 ሚሊየን ያለአግባብ ተወስዶ ከነበረው ገንዘብ 96.3 በመቶ ወይም 771.3 ሚሊየን የሚሆነውን ማስመለስ ቻለ፡፡ ቀሪውን 3.7 በመቶ የማስመለስ ሥራውን አጠናክሮ ቀጥሏል።

CBE Trade Union 19/04/2024

የድጋፍ ዓይነት አራት፡-
*********************

ማረሚያ ቤት ለሚቆይ አባል የሚደረግ ድጋፍ
----------------------------------------------
ይህ ድጋፍ አንድ አባል ሠራተኛ በማንኛዉም ምክንያት ከታሰረ ወይም ማረሚያ ቤት ከቆየ የሚደረግ ድጋፍ ነዉ፡፡ ይህ ድጋፍ ለአንድ አባል ሠራተኛ ሊሰጥ የሚችለዉ በሦስት ዓመት ውስጥ አንድ ጊዜ ብቻ ነዉ፡፡

የድጋፍ ዓይነት እና መጠን

ሀ. የሕግ ድጋፍ
ማህበሩ በጽ/ቤቱ ቀጥሮ የሚያሰራዉን ወይም ሌላ የሕግ ባለሙያ በመጠቀም የሕግ ምክር አገልግሎት ይሰጣል፡፡

ለ. የገንዘብ ድጋፍ፡
ሠራተኛዉ ለፍ/ቤት ክርክርም ይሁን ለሌላ ጉዳይ ሊያዉለዉ የሚችል፡-
• ከ15 ቀን እስከ 30 ቀን ለታሰረ አባል ብር 1,000 (አንድ ሺህ ብር) መጠየቂያ፣
• ከ አንድ ወር በላይ እስከ ሦስት ወር ለታሰረ ብር 5,000 (አምስት ሺህ ብር)
• ከሦስት ወር በላይ ለታሰረ አባል ሠራተኛ ተጨማሪ ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) ይከፈላል፡፡

አባል ሠራተኛዉ ማሟላት ያለባቸዉ መስፈርቶች

• የሙከራ ጊዚውን የጨረሰ፣
• የአባልነት መዋጮውን ሳያቆራርጥ የከፈለ እና ማህበሩ ላይ ማናቸውንም አሉታዊ ድርጊቶች ፈጽሞ የማያውቅ ፣
• መታሰሩን እና ማረሚያ ቤት የቆየበትን ጊዜ የሚገልፅ የፖሊስ ማስረጃ
• መታሰሩን እና ማረሚያ ቤት የቆየበትን ጊዜ በማስመስከር ሦስቱ የቅርንጫፍ/የክፍል ተወካዮች የፈረሙበት እና የቅርንጫፉ ማህተም ያረፈበት ማስረጃ
• የባንኩ መታወቂያ ኮፒ

የጥያቄ አቀራረብ

• ጥያቄዉ የቀረበዉ አባል ሠራተኛዉ ከማረሚያ ቤት ከወጣ በኋላ ከሆነ ሠራተኛዉ እራሱ ለዚህ ጉዳይ የተዘጋጀዉን ቅፅ ሞልቶ ጥያቄዉን ያቀርባል፤
• ጥያቄዉ የቀረበዉ አባል ሠራተኛዉ ማረሚያ ቤት እያለ ከሆነ ግን ቤተሰቡ ወይም የቅርንጫፍ/የክፍል ተወካዮች ለተጠሪ ጽ/ቤት ተወካዮች ያሳዉቃሉ፤
• የተጠሪ ጽ/ቤት ተወካዮች ጉዳዩን ካጣሩ በኋላ መሟላት ያለባቸዉ መስፈርቶች እንዲሟሉ ያደርጋሉ፤
• ክፍያዉ የ 1000 (አንድ ሺህ) ብር ከሆነ በተጠሪ ጽ/ቤት ደረጃ ይፈፅማሉ፤
• ክፍያዉ ከ1000 (አንድ ሺህ) ብር በላይ ከሆነ በሸኚ ደብዳቤ በመደገፍ ለማህበሩ ጽ/ቤት ይላካል

የጊዜ ገደብ

የዚህ ድጋፍ ጥያቄ አባል ሠራተኛዉ ከታሰረበት ጊዜ ጀምሮ መቅረብ የሚችል ሆኖ ሠራተኛዉ ከማረሚያ ቤት ከወጣ በኋላ በማንኛዉም ሁኔታ ከ3 ወራት በላይ ከቆየ ተቀባይነት የለዉም፡፡

ሌሎች ድጋፍ አይነቶች ይቀጥላል………….
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማሕበር
በተባበራ ክንድ ለተሻለ ሕይወት እንተጋለን!

Telegram https://t.me/CBETUOfficial
Facebook https://www.facebook.com/Tradeunion2018
Website https://cbetradeunion.cbe.com.et ይቀላቀሉ
ስልክ ቁጥር፡- 0906570000 ዘወትር በሥራ ሰዓት ይደዉሉ፡፡

CBE Trade Union CBE Trade Union is one of the few long ageded trade unions in Ethiopia and has been working diligently more than 56 years.

CBE Trade Union 16/04/2024

የድጋፍ ዓይነት ሦስት፡-
***************

በህመም ፈቃድ ምክንያት ደመወዝ ለተቋረጠበት አባል የሚደረግ ድጋፍ
-------------------------------------------------------------------
ይህ ድጋፍ አባል ሠራተኛዉ በሕመም ምክንያት ለረጅም ጊዜ ከተኛ እና ወደ ሥራዉ መመለስ ባለመቻሉ ባንኩ የሠራተኛዉን ደመወዝ እየቆራረጠ የሚያስቀረዉን መጠን ማህበሩ እስከ አንድ ዓመት ድረስ የሚሸፍነዉ የድጋፍ ዓይነት ነዉ፡፡

በተጨማሪም አባል ሠራተኛዉ ወይም የሥራ መሪ በሕመሙ ምክንያት ወደ ሥራ የማይመለስ ከሆነ ለአንድ ጊዜ የሚደረግ ድጋፍን ይጨምራል፡፡

የድጋፍ መጠን

ሀ. አባል ሠራተኛዉ በህመም ከሥራዉ ከተስተጓጎለበት ቀን ጀምሮ እስከ አንድ ዓመት ድረስ የሚዘልቅ ሆኖ ባንኩ የሠራተኛዉን ደመወዝ 1/2ኛ፣ 1/3ኛ እና 2/3ኛ እያለ ወይም በሌላ ስሌት ቆርጦ የሚያስቀረዉን መጠን ማህበሩ የሚሸፍን ይሆናል፡፡

ለ. በዚህ አንቀፅ ከላይ የተጠቀሰዉ እንደ ተጠበቀ ሆኖ ከአንድ ዓመት በኋላም አባል ሠራተኛዉ በሕመሙ ወይም በአካል ጉዳት ምክንያት ወደ መደበኛ ሥራዉ የማይመለስ ከሆነ ለአንድ ጊዜ ብቻ የሚከፈል ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) ብር ድጋፍ ይደረጋል፡፡

ከላይ አንቀፅ (ለ) የተጠቀሰዉ ድጋፉ ለሥራ መሪ ከሆነ ብር 25,000 (ሃያ አምስት ሺህ ብር) ይሆናል፡፡

አባል ሠራተኛዉ ማሟላት ያለባቸዉ መስፈርቶች

•የህመም ፈቃድ ከባንኩ ከሚመለከተው ክፍልና ጤና ተቋም ማስረጃ ማቅረብ፣
• የምስክር ወረቀት ከታወቀ የህክምና ተቋም፣
• ባንኩ ይከፍለው የነበረው ሙሉ ደመወዝ እና ከተቆረጠበት በኋላ እየተከፈለው ያለውን የደመወዝ መጠን የሚገልጽ ፔሮል ወይም ደብዳቤ፣
• ወደ ሥራ መመለስ የማይችል ከሆነ ይህንኑ የሚገልፅ ሙሉ የህክምና ማስረጃ፣
• የባንኩን መታወቂያ ኮፒ

የጥያቄ አቀራረብ

ሠራተኛዉ የሚያስፈልጉ ዶክመንቶችን በማሟላት የማህበሩ ጽ/ቤት በአካል ወይም ህጋዊ ወኪል በመቅረብ ለዚህ ጉዳይ የተዘጋጀዉን ቅፅ በመሙላት ጥያቄዉን ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡

የጊዜ ገደብ

አንድ አባል ሠራተኛ ይህንን መብቱን መጠየቅ የሚችለዉ ችግሩ ከደረሰበት ወይም ከሥራዉ ከተስተጓጎለበት ጊዜ አንስቶ ባንኩ ሙሉ ደመወዙን መክፈል ካቋረጠበት ቀን እስከ 3 ወራት ባለው ጊዜ ውስጥ ብቻ ነዉ፡፡ ሆኖም ግን ከአቅም በላይ በሆነ ችግር ምክንያት ብቻ እስከ 6 ወራት የይርጋ ጊዜዉ ሊራዘም ይችላል፡፡
ሌሎች ድጋፍ አይነቶች ይቀጥላል………….

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማሕበር
በተባበራ ክንድ ለተሻለ ሕይወት እንተጋለን!

Telegram https://t.me/CBETUOfficial
Facebook https://www.facebook.com/Tradeunion2018
Website https://cbetradeunion.cbe.com.et ይቀላቀሉ
ስልክ ቁጥር፡- 0906570000 ዘወትር በሥራ ሰዓት ይደዉሉ፡፡

CBE Trade Union CBE Trade Union is one of the few long ageded trade unions in Ethiopia and has been working diligently more than 56 years.

Photos from Commercial Bank of Ethiopia Trade Union's post 15/04/2024

ዜና ስፖርት

*********

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ስፖርት ቡድን አዲስ አበባ ከተማ ባስ ስፖርት ቡድንን 4 ለ 2 ድል አደረገ፡፡

የባንካችን ሠራተኞች ስፖርት ቡድን በኢትዮጵያ ሠራተኞች ማሕበራት ኮንፌዴሬሽን አዘጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘዉን የበጋ ስፓርት ዉድድር ሁሉንም በማሸነፍ እና አንዱን ብቻ አቻ በመዉጠት ምድቡን እየመራ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማሕበር
በተባበራ ክንድ ለተሻለ ሕይወት እንተጋለን!

Telegram https://t.me/CBETUOfficial
Facebook https://www.facebook.com/Tradeunion2018
Website https://cbetradeunion.cbe.com.et ይቀላቀሉ

ስልክ ቁጥር፡- 0906570000 ዘወትር በሥራ ሰዓት ይደዉሉ፡፡

CBE Trade Union 13/04/2024

የድጋፍ ዓይነት ሁለት፡-
****************
ለውጭ ሀገር ሕክምና የሚደረግ ድጋፍ

ይህ ድጋፍ አባል የሆነ ሠራተኛ ወደ ውጭ ሀገር ሄዶ በሚታከምበት ወቅት ድርጅቱ/ባንኩ ከሚሰጠው የሕክምና ወጪ 20,000 ዶላር በተጨማሪ ታካሚው ተጓዳኝ ጥቃቅን ወጪዎችን እንዲሸፍንበት በማሕበሩ የሚደረግ ድጋፍ አይነት ነዉ፡፡

የድጋፍ መጠን

• ድጋፉ የሚደረገዉ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሆን በአንድ ጊዜ የሚከፈል ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)
• ድጋፉ የሚደረገዉ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን በአንድ ጊዜ የሚከፈል ብር 25,000.00 (ሃያ አምስት ሺህ ብር) ሲሆን በጥቅሉ 75,000 ብር ይደገፋል ወይም ይደጎማል፡፡

ድጋፍ የሚጠይቅ አባል ሠራተኛ ማሟላት ያለበት መስፈርቶች

• የሙከራ ጊዚውን የጨረሰ፣
• የአባልነት መዋጮውን ሳያቆራርጥ የከፈለ እና ማህበሩ ላይ ማናቸውንም አሉታዊ ድርጊቶች ፈጽሞ የማያውቅ፣
• በተጨማሪም ማህበሩ አስፈላጊ ናቸዉ ብሎ ያመነባቸውን ሌሎች ማስረጃዎችን ማቅረብ መቻል አለበት፤
• ሠራተኛዉ ወደ ውጭ ሀገር ሄዶ እንዲታከም በሀኪሞች ቦርድ የተረጋገጠበት የህክምና ማስረጃ ማቅረብ መቻል አለበት፤
• ባንኩ ለውጭ ሀገር ሕክምና ክፍያ የፈጸመበት ሰነድ ወይም የውጭ ምንዛሪ የተፈቀደበት ማስረጃ ማቅረብ መቻል አለበት፤
• የሚሄዱበት ሀገር ቪዛ እና የባንኩ መታወቂያ ኮፒ፣

የጥያቄ አቀራረብ

ሠራተኛዉ የሚያስፈልጉ ዶክመንቶችን በማሟላት የማህበሩ ጽ/ቤት በአካል ወይም ህጋዊ ወኪል በመቅረብ ለዚህ ጉዳይ የተዘጋጀዉን ቅፅ በመሙላት ጥያቄዉን ያቀርባል፡፡

የጊዜ ገደብ

ይህን ድጋፍ መጠየቅ የሚቻለው ህክምናው ከመጠናቀቁ በፊት ወይም የህክምና ማስረጃው ከተሰጠ በኋላ እስከ 6 ወራት ባለዉ ጊዜ ውስጥ ብቻ ነው፡፡

ሌሎች ድጋፍ አይነቶች ይቀጥላል…………

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማሕበር
በተባበራ ክንድ ለተሻለ ሕይወት እንተጋለን!

ማህበራዊ ትስስር ገፆቻችንን
Telegram https://t.me/CBETUOfficial
Facebook https://www.facebook.com/Tradeunion2018
Website https://cbetradeunion.cbe.com.et ይቀላቀሉ
ስልክ ቁጥር፡- 0906570000 ዘወትር በሥራ ሰዓት ይደዉሉ፡፡

CBE Trade Union CBE Trade Union is one of the few long ageded trade unions in Ethiopia and has been working diligently more than 56 years.

CBE Trade Union 12/04/2024

እንድታዉቁት
*********

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማህበር ከባንኩ ጋር በሚያደርጋቸዉ ድርድሮች የሁሉንም የአባል ሠራተኞችን መብት እና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ከማስከበር ባሻገር አባላት ችግር ሲደርስባቸዉ ከጎናቸዉ መቆም አስፈላጊ በመሆኑ፤አባል ሠራተኞች ከማህበራቸዉ የሚጠብቁት ፋይዳ እየሰፋ እና እየጨመረ ስለመጣ ከሌሎች አባል ካልሆኑ ሠራተኞች በተለየ መልኩ አባል በመሆናቸዉ ብቻ ከማህበሩ የሚያገኙት የተለያየ ጥቅም መኖር ስላለበት፤እንዲሁም የማህበሩ ተደራሽነት ለመስፋት እና አባሎቹ ማህበሩ ላይ ያላቸዉ እምነት መጎልበት ስላለበት በማህበራችን ሕገ ደንብ መሠረት የአባላቱን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይህ የአባላት ድጋፍ መመሪያ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል፡፡

የመመሪያዉ ተፈፃሚነት ወሰን

ይህ የአባላት ድጋፍ መመሪያ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማህበር አባላት ላይ ሙሉ በሙሉ ተፈፃሚ ሲሆን፤ የተወሰኑ የድጋፍ ዓይነቶች በድጋፍ ዓይነቱ ትርጉም ስር በተቀመጠዉ መሠረት አባል ያልሆኑ ሠራተኞችን እና የሥራ መሪዎችንም ሊመለከት ይችላል፡፡

አንድ ድጋፍ የሚጠይቅ አባል ሠራተኛ ማሟላት ያለበት መስፈርት፡፡

-የሙከራ ጊዚውን የጨረሰ፣
-የአባልነት መዋጮውን ሳያቆራርጥ የከፈለ እና ማህበሩ ላይ ማናቸውንም አሉታዊ ድርጊቶች ፈጽሞ የማያውቅ፣
-በተጨማሪም ማህበሩ አስፈላጊ ናቸዉ ብሎ ያመነባቸውን ሌሎች ማስረጃዎችን ማቅረብ መቻል አለበት፤

የድጋፍ ዓይነት፡-
1.የታካሚ መጠየቂያ
-ይህ ድጋፍ አባል ሠራተኛዉ ከአንድ ወር በላይ ታሞ ከተኛ በተጠሪ ጽ/ቤት ተወካዮች የሚፈፀም የመጠየቂያ ድጋፍ አይነት ነዉ፡፡
-ይህ ድጋፍ ታሞ ለተኛ አባል ሠራተኛ የሚከፈል ሳይሆን ለጥየቃ የሚሄዱ ባልደረቦች ባዶ እጃቸዉን እንዳይሄዱ ቢያንስ ፍራፍሬ ገዝተዉ እንዲጠይቁ ማድረጊያ ሲሆን መጠኑም 2,000 ብር ነዉ፡፡

አባል ሠራተኛዉ ማሟላት ያለባቸዉ መስፈርቶች
-የሕክምና ፈቃድ ላይ መሆኑን የሚገልፅ ማስረጃ ከህክምና ተቋምና ከባንኩ
-እንዲሁም የባንኩን መታወቂያ ኮፒ

የጥያቄ አቀራረብ
-ታማሚዉ ወይም ቤተሰቡ ወይም የቅርንጫፍ/የክፍሉ ሠራተኛ ተወካይ ለተጠሪ ጽ/ቤት ተወካዮች ለዚህ ጉዳይ የተዘጋጀውን ቅፅ በመሙላት ጥያቄ ያቀርባሉ፣
-የተጠሪ ጽ/ቤት ተወካዮች ጉዳዩን በማጣራት በራሳቸዉ ወይም በቅርንጫፍ/ክፍሉ ተወካይ መሠረት ድጋፉ ለሠራተኛዉ እንዲደርስ ይደረጋል፤

የጊዜ ገደብ
ድጋፉ የታካሚ መጠየቂያ ስለሆነ አንድ አባል ሠራተኛ ሕክምናውን ጨርሶ ወደ ሥራ ገበታው ከተመለሰ በኋላ ሊጠይቅ አይችልም፡፡

ሌሎች ድጋፍ አይነቶች ይቀጥላል………….

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማህበር
በተባበረ ክንድ ለተሻለ ሕይወት እንተጋለን!

ማህበራዊ ትስስር ገፆቻችንን ይቀላቀሉ ይከታተሉ
Telegram https://t.me/CBETUOfficial
Facebook https://www.facebook.com/Tradeunion2018
Website https://cbetradeunion.cbe.com.et ይቀላቀሉ

ስልክ ቁጥር፡- 0906570000 ዘወትር በሥራ ሰዓት ይደዉሉ፡፡

CBE Trade Union CBE Trade Union is one of the few long ageded trade unions in Ethiopia and has been working diligently more than 56 years.

09/04/2024

እንኳን አደረሳችሁ!
*****************************

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማሕበር ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1445ኛው ዒድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሰላም፣የጤና፣የፍቅር እና የመተሳሰብ እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞቱን ይገልጻል፡፡

ኢድ ሙባረክ - EID MUBARAK !

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማህበር
በተባበረ ክንድ ለተሻለ ሕይወት እንተጋለን!

ማህበራዊ ትስስር ገፆቻችንን ይቀላቀሉ ይከታተሉ

Telegram https://t.me/CBETUOfficial
Facebook https://www.facebook.com/Tradeunion2018
Website https://cbetradeunion.cbe.com.et ይቀላቀሉ
ስልክ ቁጥር፡- 0906570000 ዘወትር በሥራ ሰዓት ይደዉሉ፡፡

Photos from Commercial Bank of Ethiopia Trade Union's post 08/04/2024

የቅርንጫፍ ጉብኝት ተጠናቀቀ
*****************************
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማህበር የዲስትሪክት ተጠሪ ፅ/ቤት ተወካዮች ለአንድ ሳምንት ሲያካሄዱ የነበረ የቅርንጫፍ ጉብኝት በአብዛኘዉ ተጠናቋል፡፡

በጉብኝት እና ምልከታ ወቅትም የሠራተኛ ማህበሩ የዲስትሪክት ተጠሪ ፅ/ቤት ተወካዮች ከቅርንጫፍ ሠራተኞቹ ጋር ዉይይት ያከሄዱ ሲሆን ከሠራተኞቹም ሰፊ ጥያቄ እና አስተያየት ተነስቷል፡፡

ከሠራተኞቹ ለተነሱ ጥያቄዎችም በየደረጃ ካሉ ባለድርሻ አካላት ጋር በመነጋገር በቅርንጫፍና በዲስትሪክት ደረጃ መፍትሄ እንዲያገኝ እየተደረገ ሲሆን፤በቅርንጫፍ ማነጀሮችና በዲስትሪክት ምላሽ ያልተሰጡ የሠራተኞችን ጥያቄ ለዋና መስሪያ ቤት ሠራተኞች ማህበር ተወካዮች እያሳዉቁ ይገኛሉ፡፡

ለአብነትም የቦሌ ዲስትሪክት ይጠቀሳል፡፡በቦሌ ዲስትሪክት በተካሄደዉ የማጠቃለያ ዉይይት ላይም የማህበራችን ፕሬዝደንትና ስራአስፈፃሚ ተገኝተዉ ከተወካዮች ጋር ዉይይት አካሄደዋል፡፡
በዕለቱም ማብራሪያ ለሚፈልጉ ጉዳዮች ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን በማህበሩ ደረጃ የማይፈቱ የሠራተኞችን ጥያቄ ጉዳዩ ከሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት ጋር በመነጋገር ምላሽ እንደሚሰጥም የማህበራችን ፕሬዝደንት ገልፀዋል፡፡

በመጨረሻም የዲስትሪክት እና ቅርንጫፍ ተወካዮቹ የማህበራችን ፕሬዝደንትና ስራአስፈፃሚዎች የሠራተኞችን ጥያቄ ለማዳመጥ ስለተገኙ በማመስገን የዕለቱ ዉይይት ተጠናቋል፡፡

ለበለጠ መረጃ ከታች ያሉ ማህበራዊ ትስስር ገፆቻችንን ይቀላቀሉ ይከታተሉ
Telegram https://t.me/CBETUOfficial
Facebook https://www.facebook.com/Tradeunion2018
Website https://cbetradeunion.cbe.com.et
ስልክ፡- 0906570000 ዘወትር በሥራ ሰዓት ይደዉሉ፡፡

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማህበር

****በተባበረ ክንድ ለተሻለ ሕይወት እንተጋለን!****

Photos from Commercial Bank of Ethiopia Trade Union's post 02/04/2024

ሀሰተኛ የFacebook ገፅ ሰለማሳወቅ
*************************
ይህ በምስል የምትመለከቱት የFacebook ገፅ በማህበራችን ስም የተከፈተ ሀሰተኛ ገፅ ነው፡፡ በዚህ ገፅ ላይም የስራ ፤የንግድና ሌሎችም ሀሰተኛ ማስታወቂያዎች ስዘዋወር ደርሰንበታል።
በመሆኑም የማህበራችንን ትክክለኛ የማህበራዊ ትስስር ገፆች ብቻ በመከተል ትክክለኛ እና ወቅታዊ መረጃ እንድታገኙ እንጠይቃለን፡፡
የማህበራዊ ትስስር ገፆቻችንን
Telegram :- https://t.me/CBETUOfficial
Website:- https://cbetradeunion.cbe.com.et
Facebook:- https://www.facebook.com/Tradeunion2018

ለማንኛውም ሃሣብና አስተያየት በስልክ ቁጥር 0906570000 ዘወትር ሥራ ሰዓት ላይ ይደውሉ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማህበር
***በተባበረ ክንድ ለተሻለ ሕይወት እንተጋለን!****

Want your business to be the top-listed Finance Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Videos (show all)

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰራተኞች ማኅበር የባንኩን ራዕይ እና ስትራቴጂዎች ለማስፈጸምና ሰላማዊ የሥራ ኢንዱስትሪ እንዲኖር አበክሮ መሥራት እንዳለበት ተገለጸ፡፡********  ከተመሰረተ 55 ...
የኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ሠራተኞች ማኅበር የተመሰረተበትን 55ኛ ዓመት አከባበርን በከፍል የሚያሳይ ቪዲዮ፡፡

Category

Address

Addis Ababa
2176

Opening Hours

Monday 08:00 - 16:30
Tuesday 08:00 - 16:30
Wednesday 08:00 - 17:00
Thursday 08:00 - 17:00
Friday 08:00 - 16:30
Saturday 08:00 - 18:00
Other Commercial banks in Addis Ababa (show all)
ባንኪ ንግዲ  ኢትዮጵያ ባንኪ ንግዲ ኢትዮጵያ
Ras Desta Damtew Street
Addis Ababa

አብ 1942 ዓ.ም ዝተጣየሸ ፈላማይ ዘመናዊ ባንኪ ሃገርና፣ወናኒ ልዕሊ 1900 ጨናፍር ባንኪ ንግዲ ኢትዮጰያ

Afro Bank S.C. Afro Bank S.C.
Addis Ababa

The mission of Afro Bank is to be the new face of banking in Ethiopia. We strive to establish a bank

አማራ ባንክ አክሲዮን ማህበር አማራ ባንክ አክሲዮን ማህበር
Addis Ababa

Amhara Bank share company (under formation)

Tensae Fita Tensae Fita
Addis Ababa

Obey God First!

Berhan Bank Berhan Bank
Addis Ababa

Established in October 2009, Berhan is noted for providing integrity driven fully fledged banking services. Experience Stress Free Banking with Berhan!

Amhara Bank Share Market Amhara Bank Share Market
Addis Ababa

Amhara Bank and other banks and insurances Share sales! call us: 0918040000 0940599595

Desale Bayuh Desale Bayuh
Addis Ababa

Commercial Bank of Ethiopia Shiromeda Branch Commercial Bank of Ethiopia Shiromeda Branch
Shiro Meda, Entoto Park
Addis Ababa

Commercial Bank of Ethiopia Shiromeda Branch የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሽሮሜዳ ቅርንጫፍ

Bank of Abyssinia Bank of Abyssinia
Bank Of Abyssinia Head Office, 2Q73+4C7, Ras Desta Damtew Street
Addis Ababa

Bank of Abyssinia is the fastest-growing bank in Ethiopia serving more than 10.2 million customers.

Lion International Bank S.C. Lion International Bank S.C.
Lex Plaza, Haile Gebre Silase St
Addis Ababa

LIB - KEY TO SUCCESS!!

Awash Bank Awash Bank
Awash Tower, Ras Abebe Aregay Street
Addis Ababa

The First Private Bank in Ethiopia

Dashen Bank Dashen Bank
Sudan Street, In Front Of The National Bank Of Ethiopia
Addis Ababa, 12752

Dashen Bank is one of the leading banks in Ethiopia with over 860 branches and banking outlets.