Bayra koysha woreda Health office

Bayra koysha woreda Health office

You may also like

Ethio news today
Ethio news today

Health for all

Photos from Bayra koysha woreda Health office's post 10/08/2024

የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የነበሩትና አሁን በፌዴራል የተሾሙት አቶ ተስፋዬ ይገዙ ማን ናቸው?

ወደ ፖለቲካው ዓለም የተቀላቀሉት ገና በወጣትነት የኮሌጅ ተማሪ እያሉ እንደ ሆነ ይነገራል። ወደ ፖለቲካው ዓለም ከገቡ በኋላ በአጭር ጊዜ ወደ አመራርነት መጥተዋል። የቀድሞ ደቡብ ኢትዮጵያ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ፣ ግብይት እና ህብረት ስራ ቢሮ በቢሮ ሀላፊነት ግብርና ቢሮን በምክትል ቢሮ ሀላፊነት ሰርተዋል።

በዚህ ወቅት የደቡብ ክልል ወጣቶች ሊግ ፕሬዝዳንት ሆነውም ያገለገሉ ሲሆን በሀገር ደረጃ ተመርጠው የኢትዮጵያ የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ ፕሬዝዳንት በመሆን ለሦስት ዓመታት አገልግለዋል።

እንዲሁም የዎላይታ ዞን አስተዳዳሪ ሆነው ለ3 ዓመታ የሚጠጋ ጊዜ ያገለገሉ ሲሆን በጊዜው የዎላይታ ዞን የተጀመሩ የልማት ሥራዎች እንዲጠናቀቁ፣ አዲዳስ የልማት ሥራዎችንም በመሥራት ውጤት አስገኝተዋል። በወቅቱ የዎላይታ ዞን በሁሉም ዘርፎች በክልሉ በላቀ አፈፃፀም ለ3 ተከታታይ ዓመታት ተሸላሚ እንዲሆን አብቅተዋል።

ከዎላይታ ዞን አስተዳዳሪነት ከተነሱ በኋላ የደቡብ ክልል ሕብረት ሥራ ቢሮ ኃላፊነት፣ እንዲሁም በውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊነት አገልግለዋል።

ከክልል ኃላፊነት ወደ ፌዴራል ተስበው የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ም/ዋና ዳይሬክተር፣ ቀጥሎም የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር ሚኒስቴር ደኤታ ሆነው አገልግለዋል።

በዚህ ወቅት የፌዴራል ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል እንዲሁም የዴኢህዴን ሥራ አስፈፃሚ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ነበሩ።

የተጀመረው ሀገራዊ ለውጥ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ወሳኝ ሚና የተጫወቱ ሰው ናቸው። በወቅቱ የሕ/ተ/ምክር ቤት አባል በነበሩ ጊዜ በጊዜው በድፍረት በሀገሪቱ የነበረውን ሙሰና በመተቸት በወቅቱ አይነከ የተባሉ አካላትንም በድፍረት ይገመግሙ ነበር።

አቶ ተስፋዬ ያመኑትን ነገር ፊት ለፊት የሚናገሩ፣ ገንዘብና ሥልጣን የማያንሰፈስፋቸው ግን ደግሞ ከውስጥ የጠለቀ የሕዝብ ለውጥ ፍላጎት ያላቸው፣ ለዚያም ሁሌም ያለመታከት የሚተጉ ሰው ናቸው። በዚህ ምክንያት በጊዜው የነበሩ አንዳንድ የደቡብ ባለሥልጣናት ሴራ በመጠንሰስ ሥራቸውን እንዳይከውኑ ብዙ ቢጋፈጧቸውም ተግባር ጥለው ተገምግመው አያውቁም።

የለውጡ መንግሰት ከተመሰረተ በኋላም በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት መልሶ ማቋቋሚያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ዋና ስራ አስፈፃሚ በመሆን ያገለግላሉ ሲሆን በኋላም የደቡብ ብ/ብ/ሕ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንትና የከተማ ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል።

የደቡብ ኢትዮጰሰያ ክልል ምክር ቤት አባልና የብልፅግና ፓርቲም ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ተስፋዬ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከተደራጀ በኋላ የክልሉ ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ሲያገለግሉ ቆይተው አሁን ወደ ፌዴራል በመሳብ የመስኖና ቆላማ ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ ሆነው ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር በዶ/ር አቢይ አህመድ ተሹመዋል።

አቶ ተስፋዬ በሰራባቸው ጊዜያት በርካታ ስኬቶች የተጎናፀፉ ሲሆን እንደ ሰው የራሱ የሆኑ ደካማ ነገሮችም ሊኖሩ ይችላሉና እሳቸውን በዚያ መንገድ ማየት ተገቢ የሚሉ ወገኖች አሉ።

የዎላይታ ክልል ጥያቄ ጋር በተያያዘ "የክልል ጥያቄን ያጨናገፈው እሱ" በሚል ስሙን አንስተው የሚከሱ ብዙዎች አሉ። በሌላ በኩል "የክልል ጥያቄ እንዲጨናገፍ ሳይሆን ሕግንና መርህን ተከትሎ እንዲሄድ ከጅምር ጀምሮ አብሮ የነበረ እንጅ የክልል ጥያቄ እንዲጨናገፍ ለአንድም ቀን ሲሰራ አላየንም እንዲያውም እሱ ባይሳተፍበት ኖሮ ክልል ጥያቄ ጋር በተያያዘ ብዙ ቀውስ ሊከሰት ይችል ነበር" የሚሉ አብረውት የሰሩ የሚመሰክሩ ብዙ ናቸው።

በዎላይታ ተፈጥሮ በነበረው አለ

Photos from Bayra koysha woreda Health office's post 20/07/2024
Photos from Bayra koysha woreda Health office's post 20/07/2024

18ቱን የጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጆችን በግለሰብ፣ በቤተሰብና በልማት ቡድን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ላደረጉ ለሁለት ቀበሌዎች የእውቅና አሰጣጥ ፕሮግራም ተካሄደ፣

በቅሎ ሰኞ፤ ሐምሌ 13/2016 ዓ ም በወላይታ ዞን ባይራ ኮይሻ ወረዳ 18ቱን የጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጆችን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ በማድረግ ሞዴል የሆኑ የሚኖ ዋራዛ እና የቡካማ ፈቀቃ ቀበሌዎች በዛሬው ቀን ሙሉ እውቅና በማግኘት በደማቅ ስነ-ስርዓት ተመርቋል።

ጤና ከሁሉም በላይ ለሰው ልጆች ቅድሚያ የሚሰጥ ጉዳይ በመሆኑ መንግስት በጤናው ፖሊሲ በሽታን አስቀድሞ ለመከላከል በሚያስችሉ ቅድሜ ጥንቃቄ ስራዎች ላይ ከአጠቃላይ ህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ተቀናጅቶ በመሰራቱ የተሻለ ውጤት እያመጣ እንደሆነ በምረቃ መድረክ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አዝማቹ ዳዊት ተናገሩ።

መንግስት ያስቀመጠውን የጤና ፖሊሲን ተግባራዊ በማድረግ እያንዳንዱ አባወራ በቤቱና በልማት ቡድኑ 18ቱን የጤና ኤክስቴሽን ፓኬጆችን ተግባራዊ በማድረጋቸውና ለጤና ስራ ልዩ ትኩረት በመስጠታቸው የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ጤና ለማረጋገጥ እየተቻለ መሆኑን ተናግሯል።

በቀበሌዎች ስር የሚገኙ አመራሮች፣ ባለሙያዎችና አጠቃላይ ህብረተሰብ ክፍሎች ያደረጉት ጥረትና አስተዋጽኦ እጅግ የላቀ ነው ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ይህንን ለማስቀጠልና ሁልጊዜ ንፅዕናው የተጠበቀ ቤተሰብ፣ አከባቢና ቀበሌ እንዲሆን እንዲሁም በየዓመቱ ፌስቲቫል ለማክበር ሁልጊዜ ክትትል ማድረግ ያስፈልጋል ብሏል።

ህብረተሰቡ የራሱንና የቤተሰቡን ጤና ለማረጋገጥ በመንግሥት በኩል የሚወርደውን የጤና ፖሊሲን የሁልጊዜ ተግባራዊ በማድረግና ዓመት ሙሉ ጠንካራ ስራ በማከናወን የተሻለ ውጤት እያስመዘገበ ነው ያሉት ደግሞ የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ ተወካይ አቶ ተመሰ ቴቃ ናቸው።

ጤናው የተጠበቀ ህብረተሰብ ማንኛውንም አይነት ልማትና የእድገት ስራዎችን ማከናወን ይችላል ያሉት አቶ ተመሰ ማህበራዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ በጤና ስራዎች ዘርፍ የተጀመሩ ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል ያስፈልጋል ብሏል።

ጤናው የተረጋገጠ ማህበረሰብ ለመፍጠር እያንዳንዱ ሰው ከፍተኛ የሆነ ኃላፊነት አለው በማለት በዞን ደረጃ የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ጤና ለማረጋገጥ በሁሉም ጤና ፓኬጆች አተገባበር ዙሪያ ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ እየተደረገ ይመራል ብሏል።

የወባ በሽታን ጨምሮ ሌሎች በወረርሽኝ መልክ የሚከሰቱ በሽታዎች ለመከላከል የህፃናት ክትባት፣ ኤች አይ ቪ ህክምና እና ሌሎችን በአግባቡ መከታተል እንደሚያስፈልግ በመግለፅ በህብረተሰቡ ዘንድ በሽታና ሞት እንዳይከሰት አመራሮች፣ የጤና ባለሙያዎችና የሴቶች ልማት ቡድን መሪዎች ድርሻቸውን ልወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በዛሬው ቀን የሞዴልነት እውቅና ያገኙት የሚኖ ዋራዛና የቡካማ ፈቀቃ ቀበሌዎች 18ቱን የጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጆችን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ማድረጋቸውን በተለያየ ጊዜ ከዞን የመጡ አጣሪ ቡድን ባረጋገጡት መሠረት ዛሬ በዞን ደረጃ ሞዴል ቀበሌ ማዕረግ በማግኘት ነጭ ባንድራ ልሰቀል መቻሉን የወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አበራ ባንጫ ተናግሯል።

ማህበረሰቡ በአጠቃላይ የእናቶች፣ የህፃናትና የሁሉም አባራዎች ሁለንተናዊ ጤና የተጠበቀ እንዲሆን የሽንት ቤት አጠቃቀም፣ የክትባትና የምግብ አመጋገብ፣ እንዲሁም በሌሎች 18 ጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጆች ላይ ጠንካራ ስራዎችን ማከናወን እንደሚያስፈልግ መልዕክት ተላልፈዋል።

በፕሮግራሙ ማጠቃለያ ላይ ቀበሌዎቹ ሞዴል ሆኖ እንዲመረቁ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላትና ተቋማት የእውቅና ምስክር ወረቀት ተሰቶላቸዋል።

Photos from Bayra koysha woreda Health office's post 12/07/2024

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በወላይታ ዞን የባይራ ኮይሻ ወረዳ ሞዴል የማህበረሰብ መድኃኒት ቤት ግንባታ 99.99% የተጠናቀቀ ሲሆን በቅርብ ቀን ከፌዴራል ጤና ሚንስቴር ጀምሮ በርካታ እንግዶች በተገኙበት ይመረቃል ተብሎ ይጠበቃል።
እንኳን ደስ አላችሁ።

Photos from Bayra koysha woreda Health office's post 11/05/2024

በበጀት ዓመቱ በ9 ወራት በጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጆች ሞዴል የሆኑ 6 ቀበሌዎች የሞዴልነት እውቅና መሰጠቱን የባይራ ኮይሻ ወረዳ አስታወቀ።

በቅሎ ሰኞ፤ግንቦት 03/2016 ዓ፤በወላይታ ዞን ባይራ ኮይሻ ወረዳ 18ቱን የጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጆችን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ በማድረግ ሞዴል የሆኑ የጋሌ ዋርጎ እና የበቅሎ ሰኞ ከተማ ቀበሌዎች በዛሬው ቀን እውቅና አገኙ።

ጤና ከሁሉም በላይ ለሰው ልጆች ቅድሚያ የሚሰጥ ጉዳይ በመሆኑ መንግስት በጤናው ፖሊሲ በሽታን አስቀድሞ ለመከላከል በሚያስችሉ ቅድመ መከላከል ስራዎች ላይ ህብረተሰቡን በማሳተፍ በመሰራቱ የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ እንደሆነ በምረቃ መድረክ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አዝማቹ ዳዊት ተናገሩ።

ቀበሌያት ሞዴል እንዲሆኑ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች፣ ባለሙያዎችና አጠቃላይ ህብረተሰብ ክፍሎች ያደረጉት ጥረትና አስተዋጽኦ እጅግ የላቀ ነው ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ይህንን ለማስቀጠልና ሁልጊዜ ሞዴል የሆነ ቤተሰብ፣ አከባቢና ቀበሌ እንዲሆን እንዲሁም በየዓመቱ ፌስቲቫል ለማክበር ሁልጊዜ ክትትል ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።

የጤናው ሴክተር የዜጎችን ሁለንተናዊ ጤናን ለማረጋገጥ በሚያስችሉ ተግባራት ላይ ቅድሚያ በመስጠት እየሰራ ነው ያሉት የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ ተወካይ አቶ አንበሳው ወልዴ ህዝቡም ይህንን በተግባር ላይ እንዲያውል በሴቶች ልማት ህብረት እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ከፍተኛ ስራ እየተሰራ መሆኑንና የተሻለ ውጤትም እየተመዘገበ መሆኑን ተናግረዋል።

የሞዴልነት እውቅና ያገኙት የጋሌ ዋርጎና የበቅሎ ሰኞ ከተማ ቀበሌዎች 18ቱን የጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጆችን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ማድረጋቸውን በተለያየ ጊዜ ከዞን የመጡ አጣሪ ቡድን ባረጋገጡት መሠረት ዛሬ በዞን ደረጃ ሞዴል ቀበሌ እውቅና በማግኘት ነጭ ባንድራ ልሰቀል መቻሉን የወረዳ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አበራ ባንጫ ተናግሯል።

በመጨረሻም ለሥራው መሳካት አስተዋጽኦ ላበረከቱት ተቋማት፣ አደረጃጀቶች እና ግለሰቦች የእውቅና ሰርትፍኬት የተሰጠ ስሆን በወረዳው ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ በግንባታ ላይ ያሉ መሰረታዊ ጤና ኬላ እና የማህበረሰብ ፋርማሲ ቤት ግንባታ ጉብኝትም ተደርጓል።

11/05/2024

በበጀት ዓመቱ በ9 ወራት በጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጆች ሞዴል የሆኑ 6 ቀበሌዎች የሞዴልነት እውቅና መሰጠቱን የባይራ ኮይሻ ወረዳ አስታወቀ።

በቅሎ ሰኞ፤ግንቦት 03/2016 ባይራ ኮይሻ ወረዳ 18ቱን የጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጆችን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ በማድረግ ሞዴል የሆኑ የጋሌ ዋርጎ እና የበቅሎ ሰኞ ከተማ ቀበሌዎች በዛሬው ቀን እውቅና አገኙ።

ጤና ከሁሉም በላይ ለሰው ልጆች ቅድሚያ የሚሰጥ ጉዳይ በመሆኑ መንግስት በጤናው ፖሊሲ በሽታን አስቀድሞ ለመከላከል በሚያስችሉ ቅድመ መከላከል ስራዎች ላይ ህብረተሰቡን በማሳተፍ በመሰራቱ የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ እንደሆነ በምረቃ መድረክ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አዝማቹ ዳዊት ተናገሩ።

ቀበሌያት ሞዴል እንዲሆኑ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች፣ ባለሙያዎችና አጠቃላይ ህብረተሰብ ክፍሎች ያደረጉት ጥረትና አስተዋጽኦ እጅግ የላቀ ነው ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ይህንን ለማስቀጠልና ሁልጊዜ ሞዴል የሆነ ቤተሰብ፣ አከባቢና ቀበሌ እንዲሆን እንዲሁም በየዓመቱ ፌስቲቫል ለማክበር ሁልጊዜ ክትትል ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።

የጤናው ሴክተር የዜጎችን ሁለንተናዊ ጤናን ለማረጋገጥ በሚያስችሉ ተግባራት ላይ ቅድሚያ በመስጠት እየሰራ ነው ያሉት የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ ተወካይ አቶ አንበሳው ወልዴ ህዝቡም ይህንን በተግባር ላይ እንዲያውል በሴቶች ልማት ህብረት እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ከፍተኛ ስራ እየተሰራ መሆኑንና የተሻለ ውጤትም እየተመዘገበ መሆኑን ተናግረዋል።

የሞዴልነት እውቅና ያገኙት የጋሌ ዋርጎና የበቅሎ ሰኞ ከተማ ቀበሌዎች 18ቱን የጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጆችን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ማድረጋቸውን በተለያየ ጊዜ ከዞን የመጡ አጣሪ ቡድን ባረጋገጡት መሠረት ዛሬ በዞን ደረጃ ሞዴል ቀበሌ እውቅና በማግኘት ነጭ ባንድራ ልሰቀል መቻሉን የወረዳ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አበራ ባንጫ ተናግሯል።

በመጨረሻም ለሥራው መሳካት አስተዋጽኦ ላበረከቱት ተቋማት፣ አደረጃጀቶች እና ግለሰቦች የእውቅና ሰርትፍኬት የተሰጠ ስሆን በወረዳው ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ በግንባታ ላይ ያሉ መሰረታዊ ጤና ኬላ እና የማህበረሰብ ፋርማሲ ቤት ግንባታ ጉብኝትም ተደርጓል።

Photos from Bayra koysha woreda Health office's post 29/03/2024

ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከካምባታ ዞን ሀንጋጫ ወረዳ የተወጣጡ ሉዑካን ቡድን በወላይታ ዞን ባይራ ኮይሻ ወረዳ በማህበረሰብ ተሳትፎ የተሰሩ ጤና ፓኬጆች ዙሪያ ልምድ ልውውጥ አድርገዋል

በቅሎ ሰኞ፤ መጋቢት 19/2016 ዓ ም፤ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከካምባታ ዞን ሀንጋጫ ወረዳ የተወጣጡ ልዑካን ቡድን በወላይታ ዞን ባይራ ኮይሻ ወረዳ ተገኝቶ በማህበረሰብ ተሳትፎ የተሰሩ የጤና ኤክስቴሽን ፓኬጆች አተገባበርና ሌሎች የጤና ስራዎች ዙሪያ ልምድ ልውውጥ አድርገዋል።

የባይራ ኮይሻ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አዝማቹ ዳዊት እንግዶችን እንኳን በደህና መጣቹ መልእክት በማስተላለፍ ወረዳው የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ጤና ለማረጋገጥ እየተሰራ ባለው ተግባራት ዙሪያ ልምድ ልውውጥ ለማድረግ ስለመጣችሁ በወረዳ ህዝብ ስም አመሰግናለሁ ብሏል።

ሉዑካን ቡድኑ በወረዳ ውስጥ ካሉ ቀበሌያት መካከል በጋሌ ዋርጎ ቀበሌ በዋርጎ ጤና ኬላ በመገኘት በቤተሰብ ደረጃ እየተተገበሩ ያሉ የጤና ፕሮግራሞችን ቤት ለቤት ተዟዙሮ ጉብኝት አድርገዋል።

በጉብኝት ወቅትም የወረዳ አስተዳደር የጤና ፕሮግራሞችን የአመራር ፕሮጀክት በማድረግ ለስራው የሰጠው ትኩረት ከፍተኛ በመሆኑ ከዘርፉ ከፍተኛ ትምህርት አግኝተናል ብሏል።

እያንዳንዱ አባ/እማወራ በጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጆች አተገባበር ላይ የሰጠው ትኩረትና ተግባር ላይ ያዋሉበት መንገድ አስደናቂ መሆኑን የጠቆሙት የቡድኑ አባላት ይህንን በቀጣይ በራሳቸው አከባቢ ለመትግበር ትልቅ ትምህርት ወስደናል ብለዋል።

Photos from Bayra koysha woreda Health office's post 10/03/2024

በባይራ ኮይሻ ወረዳ 18ቱን የጤና ኤክስቴሽን ፓኬጆችን ተግባራዊ ያደረጉ ሁለት ቀበሌዎች ዓመታዊ ፌስቲቫል አከባበርና የሴሬ አታላቻ የኮምፕሬንስብ ጤና ኬላ ግንባታ መሠረት ድንጋይ የማስቀመጥ ስነስርዓት ተካሂዷል፣

በቅሎ ሰኞ፣ የካቲት 30/2016 ዓ ም በወላይታ ዞን ባይራ ኮይሻ ወረዳ የሴሬ አታላቻ እና አማቾ ኮዶ ቀበሌዎች በ18ቱ የጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጆችን በግለሰብ፣ በቤተሰብና በልማት ቡድን ተግባራዊ በማድረጋቸው የሞዴልነት እውቅና አሰጣጥና የሴሬ አታላቻ ቀበሌ ኮምፕሬንስብ (ሁሉ አቀፍ) ጤና ኬላ ግንባታ መሠረት ድንጋይ የማስቀመጥ ፕሮግራም ተካሂዷል።

የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ፀጋዬ ኤካ በምረቃ ፕሮግራም ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ሞዴል በመሆን የሚመረቀው ቀበሌ 18ቱን የጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጆችን በቤትና በአከባቢ እንዲሁም በልማት ቡድን ላይ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ በመደረጉና የህብረተሰቡን ጤና በዘላቂነት ለማረጋገጥ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ አመርቂ ውጤት ልመዘገብ በመቻሉ እንደሆነ ገልጿል።

ህብረተሰቡ በእያንዳንዱ እለት በጤናው ስራ ዘርፍ ያከናወናቸው በርካታ ስራዎች ከእያንዳንዱ ቤተሰብ አልፎ በልማት ቡድንና በቀበሌ ደረጃ ትልቅ ለውጥ እያመጣ በመሆኑ የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ ለቀበሌዎቹ ሙሉ እውቅና ለመስጠት መምጣቱን በመግለፅ የተጀመረው ስራ ከመቸውም ጊዜ በላይ በተሻለ ሁኔታ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪውን አስተላልፏል።

ሰው ለመኖር ምቹ የሆነና ለጤና ተስማሚ የሆነ አከባቢን ለመፍጠር በመንግሥት በኩል የተጀመሩ ስራዎች በብዙ አከባቢዎች ላይ ተጨባጭ ለውጥ እያመጡ መሆኑን የገለፁት አቶ ፀጋዬ አጠቃላይ የህብረተሰብ ክፍሎች ለጤናው ስራ ልዩ ትኩረት በመስጠት ለተግባራዊነቱ ቁርጠኛ መሆን ያስፈልጋል ብሏል።

በዛሬው እለት መሠረት ድንጋይ የተጣለው አዲሱ ኮምፕሬንሲብ (ሁሉ አቀፍ) የጤና ኬላ ግንባታ ለህዝብ ከፍተኛ አገልግሎት የሚሰጥና ፈጣን የህክምና አገልግሎት የሚሰጥ በመሆኑ ህብረተሰቡ በሙላት እንዲሳተፉና ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪውን በማስተላለፍ እንደ ዞን ጤና መምሪያ የጤና ኮላ ግንባታው ስጠናቀቅ ለህክምና አገልግሎት የሚውሉ ማቴሪያል እና የመድኃኒት ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልጿል።

የወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አዝማቹ ዳዊት በበኩላቸው የቀበሌዎቹ ማህበረሰብ በጤና፣ በግብርና፣ በትምህርት፣ በሌሎች መሠረተ ልማት ስራዎች ላይ ጠንካራ ስራ በመስራት የህዝብን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ መንግስት ከህዝብ ጋር በትብብር እየሰራ ያለው ስራ ከመቸውም ጊዜ በላይ እየተሻሻለ መምጣቱን ገልጿል።

በጤና ስራ ዙሪያ እየተሰሩ የሚገኙ ስራዎች ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመከላከል ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው በግልፅ እየታየ መምጣቱን የገለፁት አቶ አዝማቹ ለህዝብ ጤና መረጋገጥ ጠቀሜታ ባላቸው ዘርፎች ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥተን መስራት አለብን ብሏል።

ጤናው የተጠበቀ ማህበረሰብን ለመፍጠር መንግስት ያመቻቸውና ተግባራዊ እያደረገ የሚገኘው የጤና ፓኬጆች ህብረተሰቡ በበሽታ እንዳይጠቁና ለአደጋ እንዳይጋለጡ ከማድረግ ረገድ ከፍተኛ ለውጥ እያመጣ እንደሚገኝ በመግለፅ የጤና ስራ ሁልጊዜ ትኩረት የሚሻ በመሆኑ ህዝቡ ልዩ ትኩረት በመስጠት ከጤና ባለሙያዎች ጋር ተባብሮ መስራት ያስፈልጋል ብሏል።

ዛሬ መሠረት ድንጋይ የተቀመጠው አዲሱን ኮምፕሬንስብ(ሁሉ አቀፍ) ጤና ኬላ ግንባታ በህብረተሰብ ተሳትፎ የሚከናወን በመሆኑ ህዝብን በማመስገን የወረዳ መንግስት በበኩሉ የራሱን ድርሻ በመወጣት አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያስፈልግ አረጋግጠዋል።

በዛሬው ቀን የሞዴልነት እውቅና ያገኙት የሴሬ አታላቻ እና አማቾ ኮዶ ቀበሌዎች 1

Photos from Bayra koysha woreda Health office's post 22/02/2024

በወላይታ ዞን ባይራ ኮይሻ ወረዳ የአማቾ ኮዶ መሠረታዊ ጤና ኬላ ግንባታ የደረሰበት ደረጃ የመስክ ምልከታ ተደርገዋል።

Photos from Bayra koysha woreda Health office's post 15/02/2024

Fistula በሽታ እና ዶ/ር ሀምልን

የሃምሊን ታሪክ
ፌስቱላንን ሙሉ በሙሉ እስክናጠፋ ድረስ ይህ ቦታ ለብዙ እና ለብዙ ዓመታት ይቆያል - በኢትዮጵያ ያለች እያንዳንዷ ሴት ደህና መውለዷ እና ሕፃን እንደምትወልድ እስክታረጋግጥ ድረስ።

- ዶክተር ካትሪን ሃምሊን
ዶክተር ካትሪን እና ሬግ ሃምሊን
ከ60 ዓመታት በፊት በአውስትራሊያ አቅኚ ዶክተር ካትሪን ሃምሊን እና የቀዶ ጥገና ሀኪም ባለቤቷ ዶ/ር ሬግ ሃምሊን የተመሰረተው ሃምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ እጅግ አሰቃቂ የሆነ የወሊድ ጉዳት የደረሰባቸውን ኢትዮጵያውያን ሴቶች ለማከም ቁርጠኛ ነው፡ የማህፀን ፌስቱላ።

የማህፀን ፊስቱላ በወሊድ ወቅት እፎይታ በሌለው ምጥ ምክንያት የሚከሰት የውስጥ ጉዳት ነው። የማኅጸን ፌስቱላ አንዲት ሴት ራሷን የማትቸገር፣ የተዋረደች እና ልጇን በማጣቷ ያዝናለች። ስለ የወሊድ ፊስቱላ እዚህ የበለጠ ይረዱ።

ዶ/ር ሬጅ እና ካትሪን ሃምሊን ተገናኝተው ያገቡት ሁለቱም በሲድኒ አውስትራሊያ በሚገኘው የክራውን ስትሪት የሴቶች ሆስፒታል የሕክምና መኮንን በነበሩበት ጊዜ ነበር። የጀብደኝነት መንፈሳቸው ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር የሦስት ዓመት ውል ተቀብለው በጽንስና ማህፀን ሐኪምነት እንዲሠሩና በአዲስ አበባ አዋላጅ ትምህርት ቤት እንዲመሠርቱ አነሳስቷቸዋል።

እ.ኤ.አ. በ1959 ኢትዮጵያ በገቡበት ምሽት አንድ የማህፀን ሐኪም “የፊስቱላ ታማሚዎች ልባችሁ ይሰብራል” ብለው ነበር። እና በእርግጥም አደረጉ።

ካትሪን እንዲህ ብላለች:- “የመጀመሪያው የፊስቱላ በሽተኛችን በሚያሳዝን ሁኔታ ልባችን ተነካ እና አስደንግጦናል፡ አንዲት ቆንጆ ወጣት ሴት በሽንት የተጨማለቀች የተቦጫጨቀ ልብስ ለብሳ፣ ብቻዋን በተመላላሽ ታካሚዎቻችን ክፍል ተቀምጣ ከሌሎች ተጠባባቂ ታካሚዎች ርቃለች። እሷ ከሌሎቹ የበለጠ እንደሚያስፈልጋት እናውቅ ነበር። እናም ከብዙ የፌስቱላ ታማሚዎች መካከል የመጀመሪያውን አይተናል።

ከአውስትራሊያ የመጡት እነዚህ ፈር ቀዳጅ ዶክተሮች ከኢትዮጵያ ወጥተው አያውቁም። ይልቁንም ካትሪን እና ሬግ ህይወታቸውን ለኢትዮጵያውያን ሴቶች እና ሀገር ቤት ብለው በጠሩት ሀገር የእናቶች ጤናን ለማሻሻል ህይወታቸውን ሰጥተዋል።

በአቀራረባቸው ያልተቋረጡ እና ለኢትዮጵያ ሴቶች ጀርባቸውን ለመስጠት ፈቃደኛ አልነበሩም። በወታደራዊ አመፅ፣ ረሃብ እና አረመኔያዊ የእርስ በርስ ጦርነት ሰርተዋል - ይህ ሁሉ ሲሆን ለኢትዮጵያ ሴቶች የማይናወጥ ቁርጠኝነት ነበራቸው።

በአዲስ አበባ ልዕልት ፀሐይ መታሰቢያ ሆስፒታል በመሥራት ላይ ያሉት ካትሪን እና ሬጅ የማህፀን ፌስቱላ ጉዳቶችን ለመጠገን የቀዶ ጥገና ቴክኒኮችን በማጣራት የተለያዩ የማህፀን ህክምና ጉዳዮችን ቀጥለዋል። በመጀመሪያዎቹ ሶስት ዓመታት ውስጥ ሬጅ እና ካትሪን ለ300 የፊስቱላ ታካሚዎች ቀዶ ጥገና አድርገዋል። የፈውስ ዜና ሲሰራጭ፣ ብዙ ታካሚዎች መጡ።

በማህፀን ፌስቱላ የሚሰቃዩትን በርካታ ህሙማንን ፍላጎት ለማሟላት ካትሪን እና ረግ የገንዘብ ማሰባሰብ ጀመሩ እና የአዲስ አበባ ፊስቱላ ሆስፒታል በ1974 ዓ.ም.

ዶር ሬግ ሃምሊን እ.ኤ.አ. በ1993 እስኪሞት ድረስ በሆስፒታሉ ውስጥ ሰርታለች። ከሬጅ ሞት በኋላ ካትሪን ለመልቀቅ ፈቃደኛ አልሆነችም። እሷም ቆየች እና በፌስቱላ ለሚሰቃዩ ሴቶች የተሟላ ህክምና አዘጋጅታለች። የቀዶ ጥገና ጥገና፣ ማማከር፣ ማገገሚያ እና መልሶ ማዋሀድ ሁሉም የሃምሊን ሞዴል እንክብካቤ አካል - ለቅድመ-ቀዶ እና ከቀዶ በኋላ የፊስቱላ ህክምና ግንባር ቀደም አቀራረብ።

ካትሪን እና ቡድኗ ሌሎች አምስት የሃምሊን ክልል የፊስቱላ ሆስፒታሎችን፣ የመልሶ ማቋቋሚያ እና የመልሶ ማቋቋም ማዕከልን እንዲሁም

Photos from Bayra koysha woreda Health office's post 19/01/2024

Congratulation
ባይራ ኮይሻ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት በክልል ደረጃ የተሻለ ጤና መዲህን አፈጻጸም ተሸላሚ ሆነዋል።
በአንድ ዓመት ብቻ አራት የዞን እና የክልል ዋንጫ ባለቤት ሆነናል።
congratulation

Photos from Bayra koysha woreda Health office's post 05/01/2024

"
congratulations congratulations
እንኳን_ደስ_አላችሁ፣ ባይራ ኮይሻ

የባይራ ኮይሻ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት በ2016 በጀት ዓመት በማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት የእስካሁን አፈፃፀም የላቀ ውጤት በማስመዘገብ የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።

በወላይታ ዞን ባይራ ኮይሻ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት በ2016 በጀት ዓመት በማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት (ማዐጤመ) በግማሽ ዓመት አፈፃፀም የላቀ ውጤት በማስመዘገብ በዞን ደረጃ 1ኛ ደረጃ በመውጣት የዋንጫና የምስክር ወረቀት ሽልማት ተቀብሏል።

ወረዳው ሽልማቱን ያገኘው የ2016 ዓ.ም የግማሽ ዓመት አፈፃፀም የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት ግምገማና በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ በሚመክር ጉባዔ ላይ ነው።

በግማሽ ዓመት አፈፃፀም የላቀ አፈጻጸም ያስመዘገበው ባይራ ኮይሻ ወረዳ ከዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ከአቶ ሳሙኤል ፎላ እና የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊ ከአቶ ፀጋዬ ኤካ እጅ ሽልማታቸውን ተረክበዋል።

Photos from Bayra koysha woreda Health office's post 28/12/2023

18ቱን የጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጆችን በግለሰብ፣ በቤተሰብና በልማት ቡድን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ላደረጉ ለሁለት ቀበሌዎች የእውቅና አሰጣጥ ፕሮግራም ተካሄደ፣

በቅሎ ሰኞ፤ ታህሳስ 18/2016 ዓ ም በወላይታ ዞን ባይራ ኮይሻ ወረዳ 18ቱን የጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጆችን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ በማድረግ ሞዴል የሆነው የወይዴ መሠና እና የሴረ ባላካ ቀበሌዎች በዛሬው ቀን ሙሉ እውቅና በማግኘት በደማቅ ስነስርዓት ተመርቋል።

በምረቃ ፕሮግራም ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አዝማቹ ዳዊት እንደገለፁት ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች የራሳቸውንና የአካባቢያቸውን ንፅህና በመጠበቅ በሽታን ለመከላከል የሚያስችል ቅድመ ጥንቃቄ ስራዎች ላይ ተሳታፊና ተባባሪ ሆኖ ሞዴል ቀበሌ እንዲመረቅ በመቻሉ እንኳን ደስ አላችሁ በማለት ምስጋና አቅርቧል።

በቀበሌዎች ስር የሚገኙ አመራሮች፣ ባለሙያዎችና አጠቃላይ ህብረተሰብ ክፍሎች ያደረጉት ጥረትና አስተዋጽኦ እጅግ የላቀ ነው ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ይህንን ለማስቀጠልና ሁልጊዜ ንፅዕናው የተጠበቀ ቤተሰብ፣ አከባቢና ቀበሌ እንዲሆን እንዲሁም በየዓመቱ ፌስቲቫል ለማክበር ሁልጊዜ ክትትል ማድረግ ያስፈልጋል ብሏል።

ደረጃውን የጠበቀ ሽንት ቤት መገንባት፣ የቤትና የአከባቢ ንፅህና መጠበቅ፣ እንዲሁም ሌሎችን የጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጆችን ተግባራዊ ማድረግ የራሱንና የቤተሰቡን ጤና ለማረጋገጥ የሚያስችል በመሆኑ ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመከላከል ሁሉም አካል ለጤና ስራ ተባባሪ መሆን ያስፈልጋል።

እንደወረዳ በጤናው ዘርፍ ለማሳካት ከተያዙ ዕቅዶች አንዱና ዋነኛው ሞዴል ቀበሌና ሞዴል ወረዳን መፍጠር ስሆን ለዚህ ደግሞ ህዝቡ በማዐጤመ አገልግሎትና በሌሎች ጤና ስራዎች ላይ ግንባር ቀደም መሆን ያስፈልጋል ብሏል።

መንግስት የዜጎችን ሁለንተናዊ ጤናን ለማረጋገጥ በሚያስችሉ ተግባራት ላይ ቅድሚያ በመስጠት እየሰራ ያለ ስሆን ህዝቡም ይህንን በተግባር ላይ እንዲያውል በሴቶች ልማት ቡድን በኩል ከፍተኛ ስራ እየተሰራ መሆኑንና የተሻለ ውጤትም እየተመዘገበ እንደሆነ የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ ተወካይ አቶ መሳይ ሳሙኤል ገለፁ።

በኢትዮጵያ ከ80% በላይ በሽታዎች በቅድመ ጥንቃቄ ትምህርቶችና ግንዛቤ ሊንከላከል የሚንችላቸው ስሆን ይህ ደግሞ ደረጃውን የጠበቀ ሽንት ቤት አጠቃቀም ጀምሮ ሁሉንም የጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጆችን በቤተሰብ፣ በአከባቢና በልማት ቡድን ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል ብሏል።

በአንዳንድ አከባቢዎች ላይ በወረርሽኝ መልክ የሚከሰቱ በሽታዎችን ለመከላከል የህፃናት ክትቫትን ጨምሮ ሌሎችን በአግባቡ መከታተል እንደሚያስፈልግ በመግለፅ በህብረተሰቡ ዘንድ በሽታና ሞት እንዳይከሰት አመራሮች፣ የጤና ባለሙያዎችና የሴቶች ልማት ቡድን መሪዎች ድርሻቸውን ልወጡ ይገባል ብሏል።

ጤና በእያንዳንዱ ሰው እጅ ያለ ስሆን የራሱንና የቤተሰቡን ጤና ለማረጋገጥ በጤና ስራዎች ላይ የሚሰጠውን ትምህርት ተግባራዊ በማድረግ በጤናው ዘርፍ የተቀመጠውን ብልፅግና ማረጋገጥ ጠንክሮ መስራት ያስፈልጋል ብሏል።

በዛሬው ቀን የሞዴልነት እውቅና ያገኙት የወይዴ መሠናና ሴረ ባላካ ቀበሌዎች 18ቱን የጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጆችን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ማድረጋቸውን በተለያየ ጊዜ ከዞን የመጡ አጣሪ ቡድን ባረጋገጡት መሠረት ዛሬ በዞን ደረጃ ሞዴል ቀበሌ ማዕረግ በማግኘት ነጭ ባንድራ ልሰቀል መቻሉን የወረዳ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አበራ ባንጫ ተናገሩ።

አቶ አበራ አክሎም የእናቶች፣ የህፃናትና የአጠቃላይ ህዝብ ሁለንተናዊ ጤና የተጠበቀ እንዲሆን በጋራ እየተሰራ ይቀጥላል ብሏል።

Photos from Bayra koysha woreda Health office's post 02/11/2023

Healing hands of joy የተሰኘ ግብረ ሠናይ ድርጅት በባይራ ኮይሻ ወረዳ የእናቶች ቅድመ ወሊድ ማቆያ ማዕከል ግንባታ አጠናቅቆ የግብዓት አቅርቦት ኮሚቴ በመሰየም ስራ አስጀምሯል፣

በቅሎ ሰኞ፣ ጥቅምት 22/2016 ዓ ም Healing ealing of Joy የተሰኘው በእናቶች ጤና ዙሪያ የሚሰራ ግብረ ሠናይ ድርጅት ከባይራ ኮይሻ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር የፊስቱላ በሽታ መከላከል ረገድ አንፃር የቅድመ ወሊድ እናቶች ማቆያ ማዕከል ግንባታ በማጠናቀቅ ርክክብና የግብዓት አቅርቦት ኮሚቴ በማዋቀር ስራ አስጀምሯል።

በእናቶች ጤና አጠባበቅ ዙሪያ የመውለጃ ጊዜ የደረሰባቸው እናቶች የሚቆዩበት ስፍራ በተግባር ላይ ለማዋልና የምግብ አቅርቦት ለማሟላት የተለያዩ ኮሚቴዎች ተቋቁሞ የማቆያ ቦታ ርክክብ የተደረገ ስሆን የግብዓት አቅርቦት ኮሚቴ ተቋቁመው ወደ ተግባር ገብቷል።

ድርጅቱ የእናቶች ጤና አጠባበቅ ዙሪያ፣ የፊስቱላ ህክምና እድል ያላገኙና ከፊስቱላ ጋር የሚኖሩ ሴቶችን የመለየትና ህክምና መስጠት፣ እንዲሁም ለተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች የግንዛቤ ሥራዎች ከመስራት ባለፈ ህክምና ያገኙ ሴቶች በእናቶች ጤና፣ በሥነ አእምሮ የምክር አገልግሎት እና የገቢ ማስገኛ ሥራ ርዕሶች ላይ ሥልጠና በመስጠት ከነበሩበት ችግር እንዲያገግሙ ከፍተኛ ስራን ያከናውናል።

የወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ከሂልንግ ሃንድስ ኦፍ ጆይ ከተሰኘው ድርጅት ጋር በመተባበር የእናቶች ማቆያ ግንባታ ያጠናቀቀ ስሆን እናቶች በቅድመ ወሊድና በድህረ ወሊድ ወቅት የሚመገቡበትን የምግብ አቅርቦት በሙሉ ሌሎች ግብዓቶችን ለሟሟላት በወረዳና በቀበሌ የተለያዩ ስራዎችን የሚያከናወኑ ኮሚቴዎችን በማዋቀር ወደ ተግባር ተገብቷል።

በአንድነትና በህብረት ከተሰራ የማይሳካ ነገር የለምና በየዘርፉ የተሰማሩና ኃላፊነትን የተቀበሉ አካላት ድርሻቸው በአግባቡ ለመወጣት በትጋት፣ በታማኝነትና በቁርጠኝነት በመስራት የእናቶችን ሁለንተናዊ ጤናን ለማረጋገጥና ሞትና ስቃይ ለማስቀረት በልዩ ትኩረት ልሰራ እንደሚገባ ጥሪ ቀርቧል።

በመድረኩ የወረዳ ፊት አመራሮች፣ የዞን ጤና መምሪያ ከፍተኛ ባለሙያዎች፣ የሂልንግ ሃንድስ ኦፍ ጆይ አስተባባሪዎች፣ የወረዳ ጤ/ጥ/ጽ/ቤት አመራሮችና ባለሙያዎች፣ የጤና ጣቢያ ባለሙያዎች፣ የቀበሌ አመራሮች፣ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎችና ሌሎች ባለድርሻ ሴ/መ/ቤት አመራሮችና ተወካዮች ተሳትፈዋል።

Photos from Bayra koysha woreda Health office's post 27/10/2023

የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ የ2016 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸም የግምገማ እና የድንገተኛ አደጋዎች ቅኝት ምላሽ የምክክር መድረክ በባይራ ኮይሻ ወረዳ ቡካማ ቅዱስ ፈረንስሰኮስ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ መካሄድ ጀመረ።

Photos from Bayra koysha woreda Health office's post 19/10/2023

በባይራ ኮይሻ ወረዳ የአይን ቆብ(ትራኮማ) በሽታ መከላከያ ክትባት በዘመቻ ለመስጠት የኦሬንተሽን መድረክ ተካሄደ፣

በወላይታ ዞን ባይራ ኮይሻ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ከOrbis International Ethiopia ጋር በመተባበር የአይን ቆብ(ትራኮማ) መከላከያ ክትባት ዘመቻ ማስጀመሪያ ኦሬንተሽን መድረክ አካሂዷል።

መድረኩ የትራኮማ በሽታ መከላከያ ክትባት ዘመቻና ህክምና ለመስጠት በሁሉም ቀበሌ የክትባት ቹመስጠትና በበሽታው የተጠቁ ሰዎችን ልየታ ለማድረግና ህክምና ለመስጠት የታለመ ነው።

በመድረኩ የወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ዋና ኃላፊ አቶ አበራ ባንጫን ጨምሮ ሌሎች የጽ/ቤትና የጤና ጣቢያ አመራሮችና ባለሙያዎች፣ እንዲሁም የዞን ጤና መምሪያ ባለሙያ በተገኘበት ተካሂዷል።

ማህበረሰብ አቀፍ የትራኮማ መድሃኒት ስርጭትና ክትባት ዘመቻው ከቀን 08/02/2016 ዓ ም ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት ከ6 ወር ጀምሮ ላሉ ሰዎች በሙሉ በዘመቻ መልክ እንደሚሰጥ ተገልጿል።

በዘመቻው ወቅት ቲቭና ወባ በሽታን ጨምሮ ሌሎች ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ልየታና ህክምና እንደሚሰጥ ተገልጿል።

በመድረኩ የወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት አመራሮች፣ የጤና ጣቢያ አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎችና የልማት ቡድን አመራሮች ተሳትፈዋል።

Photos from Bayra koysha woreda Health office's post 13/10/2023

በዳሞት ጋሌ ወረዳ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን / ማዐጤመ / ሀብት አሰባሰብ እና ሌሎች መዋጮ ገቢ ማሰባሰብያ ወረዳዊ ንቅናቄ በሻክሾ ሾኔ ቀበሌ በይፋ ተጀመረ

ዳሞት ጋሌ ፤ ጥቅምት 2/2016 በዳሞት ጋሌ ወረዳ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን / ማዐጤመ / ሀብት አሰባሰብ እና ሌሎች መዋጮ ገቢ ማሰባሰብያ ወረዳዊ ንቅናቄ በሻክሾ ሾኔ ቀበሌ በይፋ ተጀምሯል ።

የዳሞት ጋሌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ተወካይ አቶ አለማየሁ ቄልታ እንደገለጹት ህብረተሰቡ በትንሽ ክፍያ ብዙ የጤና አገልግሎት ማገኘት የሚችሉበት አጋጣሚ መሆኑን አስረድቷል።

አክለውም በተሰጠው ጊዜ ገደብ በመረባረብ ሁሉም ክፍያውን በጊዜ በመክፈል መታወቂያ እንዲያሳድሱና ከዚህ በፊት የማዐጤመ አባል ያልሆነ ወደ ጤና ተቋም በመቅረብ የማዐጤመ መታወቂያ አዲስ በመውሰድ አባል እንዲሆኑም ጭምር አሳስቧል ።

የዳሞት ጋሌ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘዉዱ ላቤና በበኩላቸው በጤና ሴክተር እያጋጠመ ያለው የጤና ክብካቤ የፋይናንስ አስተዳደር / ችግር ለመቅረፍ የማዐጤመ ገቢ ማሰባሰብ ለጤና ክብካቤ ፋይናንስ ሥራ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።

አክለውም ዛሬ የተጀመረው ወረዳዊ የማዐጤ ገቢ ማሰባሰብያ ንቅናቄ ሥራ እሰከ ህዳር 30/2016 ዓ/ም ድርስ የሚቀጥል መሆኑን አስረድቷል።

በተጨማሪም የወረዳ አስተባባሪ አካላት ተወካዮችና የጤና ጽ/ቤት ኃላፊ በጋራ በመሆን በቡጌ ጤና ጣቢያ የህዝብ አገ/ት እንድሁም በጤና ጣቢያ ግቢ ውስጥ ያሉ 30-40-30 ፍራፍሬ አትክልት ያለበት ደረጃ ጉብኝት አድርገዋል።

የወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት

08/10/2023

የሀዘን መግለጫ

የባይራ ኮይሻ ወረዳ አፈጉባኤ ጽ/ቤት ማህበራዊ ዘርፍ ቋሚ ኮምቴ ሰብሳቢ ሆና ስታገለግል የነበረችዉ ወዘሮ ዘርቱ ኡታሎ ከባታቸዉ ከአቶ ኡታሎ ኡነ እና ከእናታቸዉ ከወ/ሮ አፋመ አርድደዶ በወላይታ ዞን ባይራ ኮይሻ ወረዳ ሴሬ አታላቻ ቀበሌ በ1968ዓ.ም ተወልዳ መስከረም 27/01/2016ዓ.ም ባጋጠማት ህመም በህክምና ስትረዳ ቆይታ በ48ዓመቷ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች።

ወ/ሮ ዘርቱ ኡታሎ ለረጅም ዓመታት ጤና አክስተንሽን ባለሙያ ሆና በታማኝነትና በትጋት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትል ህብዝበን ስታገለግል ቆይታ ከ2012ዓ.ም ጀምሮ የባይራ ኮይሻ ወረዳ አፈጉባኤ ጽ/ቤት ህግና ፍትህ ዘርፍ ቋሚ ኮምቴ ሰብሳቢ ሆና በታማኝነትና በትጋት ስታገለግል ቆይታለች።

ወ/ሮ ዘርቱ ኡታሎ የጤና አክስተሽን ባለሙያ ሆና ባገለገችባቸዉ ጊዜያት በስራዋ ፊት በመዉጣትና የተሻለ ዉጤት በማስመዝገብ ከፈደራል፣ከዞንና ከወረዳ የተለያዩ ሽልማቶችን አግንታለች።

ወ/ሮ ዘርቱ ኡታሎ በስራዋ ተሸላሚ፣ለደሃ ሳትሰስት የምትሰጥ የደሃ እናት፣ታታሪና ትጉ ሰራተኛ ነበረች።

ለዘመድ አዝማዶቿ፣ለስራ ባልደረቧቿ እና ለወዳጆቿ መፅናናትን እንመኛለን።

ባይራ ኮይሻ ወረዳ ጤናው ጽ/ቤት

Photos from Bayra koysha woreda Health office's post 04/10/2023



የባይራ ኮይሻ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት በ2015 በጀት ዓመት በማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን የላቀ አፈጻጸም በማስመዘገብ የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።

በወላይታ ዞን ባይራ ኮይሻ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት በ2015 በጀት ዓመት በማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን የላቀ አፈጻጸም በማስመዘገብ በዞን ደረጃ 1ኛ ደረጃ በመውጣት የዋንጫና የምስክር ወረቀት ሽልማት ተቀብሏል።

ወረዳው ሽልማቱን ያገኘው የ2015 ዓ.ም የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አፈጻጸም ግምገማና የ2016 ዓ.ም ንቅናቄ መድረክ በተካሄደበት ነው።

በዓመቱ አፈፃፀም የላቀ አፈጻጸም ያስመዘገበው ባይራ ኮይሻ ወረዳ ከዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ከአቶ ሳሙኤል ፎላ እና ከዞኑ የመንግስት ዋና ተጠሪ ከአቶ አሳምነው አይዛ እጅ ሽልማታቸውን ተረክበዋል።

Photos from Wolayta Zone Health Department /ወላይታ ዞን ጤና መምሪያ's post 08/09/2023
Photos from የወላይታ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት- Wolaita Prosperity Party office's post 08/09/2023
Photos from Bayra Koysha Woreda Government Communication/የባይራ ኮይሻ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን's post 26/08/2023
Want your organization to be the top-listed Government Service in Sodo?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address

S**o
Other Government Organizations in S**o (show all)
Wolaita Zone Youth Association/ ወላይታ ዞን ወጣቶች ማህበር Wolaita Zone Youth Association/ ወላይታ ዞን ወጣቶች ማህበር
Ligaba
S**o

በብቃት እና በጥረት የተካኑ ወጣቶችን ለማፍራት እንተጋለን !

Gesuba ketema  Agricultral office page Gesuba ketema Agricultral office page
S**o

Gov.t Office at Gesuba

Tare Tare
Tarekegn Mathewos
S**o, 4500

ገሱባ ከተማ አስ/ር ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ዩኒቲ ገሱባ ከተማ አስ/ር ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ዩኒቲ
Gesuba
S**o

Gesuba town administration workers and social affairs

𝘏𝘢𝘲𝘢𝘢 𝘖𝘳𝘰𝘮𝘰𝘰 𝘏𝘢𝘲𝘢𝘢 𝘖𝘳𝘰𝘮𝘰𝘰
Walagaa
S**o, 01

I.m oromoo first

Wolaita S**o City Fana womba Kebele Administration Wolaita S**o City Fana womba Kebele Administration
Wolaita S**o
S**o, WOLAITAWOLAITASODOFANA

Wolaita zone agri .department Wolaita zone agri .department
Wolaita Soddo
S**o

Wolaita S**o Agricultural College Wolaita S**o Agricultural College
S**o, 120

Home of Agricultural Vocation!