Kawo koysha woreda water irrigation and energy development office

gov'tal organization

Photos from Kawo koysha woreda water irrigation and energy development office's post 10/03/2023

በወላይታ ዞን ካዎ ኮይሻ ወረዳ ውኃ መስኖና ማዕድን ልማት ጽ/ቤት የስድስት ወር ሥራ አፈጻጸምን በተመለከተ የሶስትዮሽ ምክክር መድረክ እና የመስክ ሥራ ጉብኝት ተደረገ::
☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆

የካቲት30/2015 ዓ.ም.
ላሾ

በወላይታ ዞን ካዎ ኮይሻ ወረዳ ውኃ መስኖና ማዕድን ልማት ጽ/ቤት የስድስት ወር ሥራ አፈጻጸምን በተመለከተ የሶስትዮሽ ምክክር መድረክ እና የመስክ ሥራ ጉብኝት ተደረገ::በምክክር መድረኩ የተገኙት እና ተወካዮች በባለፉት ስድስት ወራት በዞኑ ውስጥ በድርጅቱ ከታቀፉት ወረዳዎች ግንባር ቀደም ውጤት በዚህ ወረዳ በመመዘገቡ ደስተኛ መሆናቸውን ጠቅሰው ለወረዳው ሁለንተናዊ ድጋፍ እናደርጋለን አሉ::

የካዎ ኮይሻ ወረዳ ውኃ መስኖና ማዕድን ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ድርጅቱ ለወረዳው ህዝብ ለሚያደርገው ድጋፍ ከፍተኛ ምስጋና ካቀረበ ቦኇላ "ከዚህ ቦኇላ የተገኙ ውጤቶችን አጠናክረን በማስቀጠል ከዚህ በፍት የተሠሩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን በመጠበቅና በተደራሽነት ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥተን በመሥራት የህብረተሰቡን ጥያቄ በአጭር ጊዜ መመለስ እንችላለን" አሉ::

በመድረኩ ድንበር ተሻጋር ውኃ ግንባታ÷የጥገና ሥራ ያለበት ደረጃ እና ፌዴሬሽኖቹ ዘመናዊ የፋይናንስ አሠራር እንድከተሉ በሚደረግበት ሁኔታ ላይ ጠለቅ ያለ ውይይት ተደርጎ በስተመጨረሻ በመያድ ለናሙና በተመረጠው አንድ ቀበሌ ውኃ ፌዴሬሽን ላይ የመስክ ሥራ ምልከታ በማድረግ ተጠናቅቋል::

Photos from Kawo koysha woreda water irrigation and energy development office's post 07/03/2023

የካቲት 27/2015 ዓ.ም
ከ2.6 ቢሊየን ብር በላይ ተመድቦለት በወላይታ ዞን ቦሎሶሶሬ ወረዳ እየተገነባ ያለው የወይቦ ግድብ መካከለኛ መስኖ ፕሮጀክት የተጠቀሚ አርሶ አደሮችን ተስፋ ያለመለመ መሆኑ ተገለፀ ፡፡
***************************************************************************************
የደቡብ ክልል መስኖ ተቋማት ልማትና አስተዳደር ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ካሣሁን ወልደጊዮርጊስ ፡- ኤጀንሲው በክልሉ 42 ፕሮጀክቶችን እያስገነባ እንደሚገኝና ባለፉት ስድስት ወራትም 2696 ሄክታር ማልማት የሚችሉ 16 ፕሮጀክቶች መጠናቀቃቸውን ጠቁመው፣
ከ2.6 ቢሊየን ብር በላይ ተመድቦለት በመገንባት ላይ የሚገኘው የወይቦ መስኖ ፕሮጀክት በፌዴራል መንግሥት እየተገነቡ ካሉት አራት ፕሮጀክቶች አንዱ መሆኑንና እስካሁን ባለውም የግንባታ ሂደት አፈፃሙ 12% ላይ እንደሚገኝና መድረስ ከሚገባው አፈፃፀም አኳያ መዘግየቶእንደሚስተዋሉ አልሸሸጉ፡፡
የወይቦ ፕሮጀክት ተጠናቆ ወደ ሥራ ሲገባ ከ4000 ሄክታር በላይ መሬት በማልማት በሁለት ወረዳዎች በ11 ቀበሌዎች የሚገኙ ከ63000 በላይ ሰዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ገልፀው፣ ከመስኖ ልማቱ ጎን ለጎን አሳ ልማትና ለተለያዩ የመናፈሻ ዘርፎች መፈጠር ትልቅ ዕድል ስለሚፈጥር፣ ለአከባቢው ሕብረተሰብ ተጨማሪ የኢኮኖሚ ዕድገት በመፈጠር የተለያዩ በረከቶችን እንደሚያመጣ ዘርዝረዋል፡፡

በደቡብ ውሃ ሥራዎች ድርጅት የፕሮጀክቱን ኮንትራት አስተዳደር ወኪል እንደ አቶ ብሩክ ናስር ገለፃ የፕሮጀክቱን አተገባበር ሂደት በሶስት የተለያዩ ክፍሎች ሊገለፅ እንደሚችል፤ ለሠራተኞች የካምፕ ግምባታና የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ፣ የግድቡ ዋና ቁፋሮና ለግድቡ ግንባታ አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን የማምረት ሥራዎችን እንደሚያጠቃልልና የተለያዩ ግብአቶች የማምረቱ ተግባር 34% መድረሱ ጠቅሰዋል፡፡
ፕሮጅከቱን ከተያዘለት ጊዜ አኳያ ለተከሰቱት ውስንነቶች ዲዛይኑን ከነባራዊ የሳይት ሁኔታ የማስታረቅ ሥራ፣ የወሰን ማስከበርና የዝናብ ወቅት ተጠቃሽ መሆናቸውን ያስታወሱት አቶ በሩክ፣ በነዚህ ምክኒያቶች የባከነውን ጊዜ ለማካካስም ምሽትን ጨምሮ ተጨማሪ ጊዜን፣ ማሽኖችንና የሰው ኃይል በማሰማራት እየተሰራ መሆኑን አክለዋል፡፡

የቦሎሶሶሬ ወረዳ ም/አስተዳደርና የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አማን ከበደ በበኩላቸው:- የአከባቢው ሕብረተሰብ ከዚህ በፊት የተለያዩ የጓሮ አትክልቶችንና ፍራፍሬዎችን በመስኖ የማልማት ልማድ ቢኖረውም ስንዴ የማምረት ልምድ እንዳልነበረው ተናግረው ፣ አሁን ግን በተፈጠረለት ግንዛቤ ኩታገጠም የበጋ መስኖ ልማት ተግባርን እየተላመደና እያስፋፋ መምጣቱን ገልፀዋል፡፡
የመጣላ ሂምቤቾ ቀበሌ ነዋሪ አርሶአደር ፍቃዱ ጊዴቦና ቶማስ ዳንሳ ከዚህ ቀደም የነበረው አነስተኛ መስኖ በመጠቀም የተለያዩ ሰብሎችን፣ ፍራፍሬዎችና የጓሮ አትክልቶችን የማምረት ልምድ እንደነበራቸውና በአሁኑ ሰዓት ኩታ ገጠም የበጋ ስንዴ ምርት ላይ ተሳታፊ በመሆን ካገኙት ጥቅም አኳያ ከዚህ በፊት የባከኑትን ጊዘያት በከፍተኛ ቁጭት እንደሚመለከቱት ተናግረው፣ የወይቦ ፕሮጀክት ተጠናቆ ወደ ሥራ ሲገባ በቂ ውሃ ስለሚያገኙ ከአሁኑ በብዙ እጥፍ ለማምረት እንደሚያስችላቸው ታላቅ ተስፋ እንዳላቸው ገልፀዋል፡፡

11/01/2023

CROPS AND CROP LAND ALLOCATION
1. Crop Selection
Selecting suitable crop in relation to the available water supply and climatic condition of an area is very essential step in crop water demand assessment. Generally crop selection is based on the following variables:-
 Suitability of soil: – the selected crops should give a maximum possible yield with little or no additional inputs which will increase the soil nutritive value and provide adequate drainage facility during high impoundment.
 Method of irrigation
 Climate:– the climate should be suitable for crops
 Availability of labor & farm machineries
 Water requirement:– It should be considered so that availability of water to meet the plant needs is ensured
 Market & profit: – priority should be given to those high markets.
 Socio economic aspect value
 Farmers preference
 Yield response factor and water utilization efficiency.
Taking the above variables into consideration, maize crop is selected for Konso Iyanda Irrigation Project.
2. Cropping Pattern
It is the sequence in which plants (crops) are grown on the total area. The cropping pattern of the project (e.g. Crops, crop rotation and intensity) is essential input consideration in the overall project planning. The overall objective of cropping pattern is maximizing the utilization of land water in order that the beneficiaries are capable of implementing the proposed program in terms of supplying the labor & other inputs required to increase the percentage of the total cropped area. Cropping pattern depends on the following factors:-
Availability of water: - The cropping pattern should be planned such that the crops can be irrigated during the critical irrigation demand.
Type of soil: - Detail soil survey should be conducted to determine the suitable type of crop for a particular land.
Climatic conditions: - Crops requiring more water should be grown when rainfall is available.
Value of crop: - As far as possible, the crops which ha

Photos from Kawo koysha woreda water irrigation and energy development office's post 23/12/2022

የድንጋይ ከሰል ማዕድን ጥቅም ላይ ለማዋል የተቀናጀ እንቅስቃሴ መጀመሩን ተገለጸ

ለሾ:- ታህሳስ 13/2015 የክልሉ ውሃ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ኃላፊዎችና የማኔጅመንት አባላት እና የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች በወላይታ ዞን ኪንዶ ዲዳዬ ወረዳ እየተመረተ ያለ የድንጋይ ከሰል ምርትን ጎብኝተዋል።

የደቡብ ክልል ውሃ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር አክሊሉ አዳኝ እንዳሉት በክልሉ በየዓመቱ 500 ስኩዌር ኪሎሜትር ስፋት ማዕድን ያሉባቸው አከባቢዎች ከተለያዩ ተቋማት ጋር በመተባበር ጥናት እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።

አያይዘውም ጥናቱ በክልሉ ምን ያህል ማዕድናት እንዳሉ ለማወቅና ለመለየት የሚያስችል እንደሆነ አስገንዝበዋል።

ከዚህ በፊት ለማዕድን ያለው ግንዛቤ ዝቅተኛ በመሆኑ ብዙ ስራ አለመስራቱ የገለፁት ኃላፊው በለውጡ መንግስት ለማዕድን ዘርፍ በሰጠው ትኩረት ብዙ ስራዎች እየተሰራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።

በክልሉ የተለያዩ ማዕድን ሀብት በስፋት መኖሩ በጥናት አረጋግጠናል ያሉት ኃላፊው ያሉ ማዕድናትን በመለየት በዘርፉ የተሰማሩ ባለሀብቶች ወደ ስራ እንዲገቡ ሰፊ ስራዎች እየተከናወነ ይገኛልም ብለዋል።

በዘርፉም የአከባቢው ማህብረሰብ ተጠቃሚ እንዲሆን እየተሰራ ነው ያሉት ኃላፊ በዘርፉ የተሰማሩ ባለሀብቶች ከአከባቢው ማህበረሰብ ጋር ተቀናጅቶ መስራት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

የክልሉ ማዕድንና ኢነርጂ ኤጀንሲ ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ አጸደ አይዛ ከውጭ ሀገር በከፊል የሚገባውን የድንጋይ ከሰል ማዕድን በሀገር ውስጥ ለመተካት እየተሰራ ነው ብለዋል።

በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የግንባታ ማዕድናትን ሳይጨምር ከ25 በላይ ማዕድናት መኖራቸው በጥናት መረጋገጡን ተናግረዋል።

በክልሉ ሀገርቷ የምትፈልገውን ለስምንቶና ሌሎች ግብዓትነት እንደሀይል ማመንጫ የሚጠቅም በቂ የማዕድናት ክምችት መኖሩን አስታውቀዋል።

ማዕድኑ ለአልምውና ለወረዳው ህብረተሰብን ተጠቃሚ የሚያደርግ እና ለስራ አጥ ወጣቶች ስራ ዕድል የሚፈጥር እንደሆነም ገልጸዋል።

ለማምረት ፈቃድ የተሰጣቸው የድንጋይ ከሰል አምራቾች በውላቸው መሠረት ወደ ሥራ እንዲገቡ የዞኑ እና የወረዳው መንግስት ያበረከቱት ድጋፍ አመስግነዋል።

የወላይታ ዞን ውሃ መስኖና ማዕድን ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ተስፋሁን ታድዮስ ዞኑ ከክልሉ ውሃ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮና የክልሉ ማዕድንና ኢነርጂ ኤጀንሲ ጋር በማቀናጀት ትላልቅ ስራዎችን እየሰራ መቆየቱን ገልጸዋል።

በዞኑ የከሰል ድንጋይ ክምችት በሁለት ወረዳዎች በኦፋና ኪንዶ ዲዳዬ እንደሚገኝ ገልጾ በዚህ ዘርፍ አራት ባለሀብቶችን ወደ ስራ የማስገባት ስራ መሰራቱንና ሌሎች በሂደት ላይ እንደሚገኙም አስታውቀዋል።

በኪንዶ ዲዳዬ ወረዳ የሚገኘው የድንጋይ ከሰል የውጭም የሀገር ውስጥም ስታንዳርዱን የሚያሟላና ጥራቱን የተጠበቀ መሆኑን አስረድተዋል።

በቀጣይ ለምርት ሂደቱ የሚገቡ ባለሀብቶች መኖራቸውን የገለፁት አቶ ተስፋሁን ለዚህም ምቹ የስራ ሁኔታዎች ለመፍጠር ባለድርሻ አካላት አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ እንዳለባቸውም አመላክተዋል።

እንንደዞን የኦፋልና ሌሎች ጥናት ሂደት ላይ የሚገኙ በርካታ ማዕድናት ክምችት በበቂ ሁኔታ መኖሩን ተናግረዋል።

ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች ከጉብኝቱ ጎን ለጎን ከአከባቢው ማኅበረሰብ እና ከድንጋይ ከሰል አምራቾች ጋር ተወያይተዋል።

Photos from Kawo koysha woreda water irrigation and energy development office's post 16/12/2022

የላሾ ከተማ አዲስ ውኃ ግንባታ ተጠናቅቆ ዛሬና ነገ የሙከራ ስርጭት ስለሚደረግ የመሐል ከተማ ውኃ በሙከራ ስርጭት ምክንያት ለሁለት ተከታታይ ቀናት ዝግ ይሆናል::
ከዚህ በፊት ከመሐል ከተማ ቦኖ ስቀዱ የነበሩ ሥራው እስከሚጠናቀቅ ከጫቴ ላሾ,ናዝሬት ላሾ እና ጫሬ ቦሎላ ለመቅዳት የሚችሉ መሆኑን እናሳስባለን::

Photos from South Ethiopia Regional State Water, Mines And Energy Bureau's post 16/12/2022
Photos from የዎላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉ/ጽ/ቤት's post 15/12/2022
Photos from Kawo koysha woreda water irrigation and energy development office's post 13/12/2022

በሕገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ የተለያየ አይነት እና መጠን ያላቸው ማዕድናት እና የቁም እንስሳት በቊጥጥር ስር ዋሉ

ወላይታ ሶዶ፤ ታህሳስ 3/2015(ወቴቪ)

አጠቃላይ ክብደታቸው ስምንት ኪ.ግ የሚመዝኑ ማእድናት በሰመራ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በብዬ ቆቢ መቆጣጠሪያ ጣቢያ በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ መያዙን የጉመጁሩክ ኮሚሽን አስታወቀ።

በተመሳሳይ በጅግጅጋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሁለት ሚሊዮን ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የቁም እንስሳት በህገወጥ መንገድ ወደ ሱማሌ ላንድ ሊወጡ ሲሉ በቶጎዉጫሌ መቆጣጠሪያ ጣቢያ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

የጉምሩክ ኮሚሽን በሂደቱ ለተሳተፉ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቶቹ ሠራተኞችና አመራሮች እንዲሁም ለጸጥታ ተቋማት አመራሮች እና አባላት ምስጋናውን አቅርቧል።

የኮንትሮባንድ እና ህገወጥ ንግድ የአፈጻጸም ስልቱ ተለዋዋጭ በመሆኑ ድርጊቱን ለመግታትና በሀገር ኢኮኖሚ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተጽእኖ ለመከላከል ጉምሩክ ኮሚሽን ብቻ የሚያደርገው እንቅስቃሴ በቂ ባለመሆኑ ሁሉም ባላድርሻ አካላትና ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የጉምሩክ ኮሚሽን ጥሪውን አቅርቧል።ዘገባው ኢፕድ ነው።

አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ



ከኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን

Photos from Kawo koysha woreda water irrigation and energy development office's post 13/12/2022

ታህሳስ 04/2015 ዓ.ም
የደቡብ ክልል ብሔራዊ አሀዳዊ ፕሮግራም በ2015 በጀት ዓመት ከ808 ሚሊየን ብር በላይ በመመደብ ወደ ሥራ መግባቱ ተገለፀ፡፡
***********************************************************************************************************
ብሔራዊ አሀዳዊ ዋሽ ፕሮግራም በክልሉ በሚገኙ የውሃ፣ መስኖና ማዕድን ልማትቢሮ፣ ጤና ቢሮ ፣ ትምህርትና ፋይናንስ ቢሮዎች በቅንጅት የሚያከናውኑ ፕሮግራም ሲሆን፣ በንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፣ ሳኒቴሽንና ሀይጅን ሥራዎችን በፕሮግራሙ በታቀፉ በገጠርና አነስተኛ ከተሞች ላይ የሚያከናውን ፕግራም ነው፡፡
ከክልል፣ከዞን ፣ከልዩ ወረዳዎችና ወረዳዎች የተውጣጡ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ባለድርሻ መስሪያቤቶች በተገኙበት የፕሮግራሙ የ2014 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀምና የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ የሚመክር ጉባኤ በሀላባ ዞን ቁሊቶ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
በጉባኤው በፕሮግራሙ ሁለተኛ ምዕራፍ የተከናወኑ የፊዚካልና ካፒታል ተግባራት አፈፃፀም አስመልክቶ ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በመገምገም በቀጣይ መከናወን ስለሚገባቸው ተግባራት የጋራ መግባባት ላይ እንደሚደረስ ይጠበቃል፡፡

Photos from Kawo koysha woreda water irrigation and energy development office's post 12/12/2022

ታህሳስ 01/2015 ዓ.ም
።።።።።።።።።።።።።።።።።
የደቡብ ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ውሃ ፤መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ለዞንና ለልዩ ወረዳ የሰው ሀብት ልማት ሥራ አመራር አስተዳደር ቡድን መሪዎች በሴክተር ተኮር ሪፎርም ሥራዎችና በአፈፃፀም ሥራ አመራር ሥርዓት በተመለከተ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

በስልጠናውመድረክ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት አቶ ሰለሞን ውድነህ በምክትል ቢሮ ኃላፊ ማዕረግ አስተዳደርና ፋይናንስ ዘርፍ ኃላፊ እንደገለጹት ፡ በሁለቱም ርዕሶች እየተሰጠ የሚገኘው ስልጠና ከክልል እስከ ወረዳ ያሉትን የሰው ሀብት ሥራዎች ደንብና መመሪያን መሠረት አድርጎ ተግባራዊ ለማድረግ አዎንታዊ አስተዋፅኦ ስለሚያበረክት ለዚህ ደግሞ ሴክተር ተኮር የሪፎርም መሣሪያዎችን መተግበርና የአፈፃፀም ሥራ አመራር ማኑዋል ተግባራዊ ማድረግ ፤ በዚህ ወቅት የህዝብን ጥያቄ በአግባቡ ምላሽ ለመስጠት አስፈላጊና ወሳኝ መሆኑን አብራርተዋል።

ወ/ሮ መሰለች አለማየሁ የቢሮው ሰው ሀብት ልማት ሥራ አመራርና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ተወካይ የስልጠናውን ዓላማ በተመለከተ ስገልጹ፡-እንደሌሎች ስልጠናዎች በተለየ ሁኔታ ትኩረት ተሰጥቶት ውጤቱ በተግባር መገለፅ ያለበት እንደሆነና ለሰልጣኞች ከሥራቸው ጋር ቀጥታ ግኑኝነት ያለው በመሆኑ በጥንቃቄ ተግባራዊ ሊያደርጉት እንደሚገባ እንዲሁም የሪፎርም መሣሪዎች የሴክተሩን ተጨባጭ ሁኔታ መሠረት በማድረግ በሁሉም ዞኖችና ልዪ ወረዳዎች በየአስራምስት ቀኑ ውይይት እየተደረገ ሪፖርትና ግብረመልስ መስጠት እንደሚገባም አስገንዝበዋል ፡፡
ስልጠናው ከክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ በመጡ በከፍተኛ የሪፎርም አማካሪዎች የተሰጠ ሲሆን ከሰልጣኞች አስተያየት ና ጥያቄ ተነስቶ በቢሮውሰው ሀብት ልማት ሥራ አመራርና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ተወካይ በወ/ሮ መሰለች አለማየሁ እና በአሰልጣኞቹ በዝርዝር ምላሽና ማብራሪያ ተሠጥቷል፡፡

08/12/2022

GOOD LUCK FOR MULUWORK MARU

07/12/2022

እንኳን ለኢትዮጵያ ብሄሮች ፣ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል አደረሳችሁ፡፡
ህዳር 29/2015 ዓ/ም “ህብረ-ብህራዊ እንድነታችን ለዘላቂ ሰላም” በሚል መሪ ቃል በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሃዋሳ ከተማ ለሚከበረው 17ኛው የብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር እንኳን አደረሳችው ይላል ፡፡
የብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ለመጀመርያ ጊዜ መከበር የጀመረው በ1999 ዓ.ም ነበር፡፡ በወቅቱ በዓሉ የተከበረውም በፌዴሬሽን ምክር ቤት አዘጋጅነት በአዲስ አበባ ከተማ ሲሆን መሪ ቃሉም “ሕገ-መንግስታዊ ቃል ኪዳን የአብሮነታችን መገለጫ ነው” የሚል ነበር።
የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በየዓመቱ ህዳር 29 በደማቅ ሁኔታ ይከበራል:: ይህ ቀን በኢትዮጵያ ታሪክ ጉልህ ስፍራ ያለው ሲሆን የኢፌዴሪ ህገ-መንግስት የፀደቀበትና የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፌዴራላዊ ስርዓት መከተል የጀመረችበት ጊዜ ነው፡፡ ይህ ማለት ህዳር 29 ቀን 1987 ዓ.ም የፀደቀው የፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ኢትዮጵያ ህገ-መንግስት የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦችን ከዳር እስከዳር በማሳተፍ የፀደቀ በመሆኑ በዓሉ በየአመቱ ሲከበርም የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች በጋራ የሚያከብሩት ቀን ነው፡፡
በዓሉ የሚከበረው ሃገራዊ አንድነትንና ህብረ -ብሄራዊነትን ለማጠናከር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ነው፡፡ ከዚያ ባሻገር በዓሉ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትና ለፌዴራሊዝም ስርዓት መጠናከር ፋይዳው የላቀ ነው፡፡ በእለቱ የሚካሂዱ ሲምፖዚሞች፣ ኢግዚብሽኖችና የባህል ልውውጥ መድረኮችና ትዕይንቶች ሀገራዊ አንድነትን በማጠናከር ረገድ አስተዋጾአቸው ከፍተኛ ነው፡፡

Photos from Kawo koysha woreda water irrigation and energy development office's post 07/12/2022

ሚኒስቴሩ ለኦሮሚያ ብሄራዊ ክልል 900 የውሃ መሳቢያ ፓምፖች ድጋፍ አደረገ

የመስኖና ቆላ አካባቢ ሚኒስቴር በዛሬው ዕለት ለኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት 900 የውሃ መሳቢያ ፓምፖች ድጋፍ አድርጓል፡፡ የውሃ መሳቢያ ፓምፖቹን ክብርት ኢንጂነር አይሻ መሃመድ ለኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ ሽመልስ አብዲሳ አስረክበዋል፡፡
ክብርት ሚኒስትሯ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት ‹‹የኦሮሚያ ክልል በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ላለው ሥራ ያላቸውን አድናቆት ገልፀው የውሃ መሳቢያ ፓምፖቹም ክልሉ እያከናወነ ላለው የበጋ የስንዴ ልማት ትልቅ እገዛ እንደሚኖረውና ድጋፉም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡
ክቡር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በበኩላቸው ሚኒስቴሩ ከተቋቋመበት አጭር ጊዜ አኳያ እያከናወናቸው ያሉ ተግባራት አገሪቱ በግብርና እያሳየችው ባለው እመርታ ውስጥ በጉልህ የሚታይ መሆኑንና ‹‹ለዚህም ትጋታችሁ አክብሮታችንን እንገልፃለን ›› ብለዋል፡፡
የውሃ መሳቢያ ፓምፖቹም ለአርሶ አደሩና አርብቶ አደሩ ትልቅ ትርጉም ያላቸውና ህይወት የሚቀይሩ ናቸው ያሉት አቶ ሽመልስ ሚኒስቴሩ ላደረገላቸው ድጋፍ አመስግነዋል፡፡
በሚኒስቴሩ የመስኖ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ብርሃኑ ሌንጂሶ በበኩላቸው ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ዘንድሮ ሚኒስቴሩ አራት ሺህ ያህል የውሃ መሳቢያ ፓምፖችን ለሁሉም ክልሎችና ለሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች ማቅረቡን ተናግረው በዛሬው ዕለት የተደረገው ድጋፍም በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡

Photos from Kawo koysha woreda water irrigation and energy development office's post 04/12/2022

የውሃ አገለግሎት ክፍያ ለመወሰን በተዘጋጀው ረቂቅ ደምብ ላይ ውይይት ተካሄደ ፡፡

20/3/2015 (ው.ኢ.ሚ) የውሃ አገልግሎት ክፍያን ለመወሰን በተዘጋጀ ረቂቅ ደንብ ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡

የምክክር መድረኩን በንግግር የከፈቱት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የውሃ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር ዶ/ር አብርሃ አዱኛ እንደገለጹት ባለፈው ዓመት የተተገበረውን ተቋማዊ ለውጥ ተከትሎ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በሀገሪቱ ያሉ የውሃ ሀብቶችን ለማስተዳደር እና በአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚን ለመገንባት አስቻይ ሁኔዎችን በሚፈጥር መልኩ የህግና የትግበራ ማእቀፎች በማዘጋጀት ወደ ተግባር እንቅስቃሴ መግባቱን ገልጸዋል፡፡

ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው አክለው ሲገልጹ፤ ተቋዘሙ በተሰጠው ስልጣንና ኃላፊነት መሰረት የውሃ ሀበታችንን የመጠቀም ብቻ ሳይሆን የመጠበቅና የመንከባከብ ስራዎች በስፋት ማከናወን ስለሚጠበቅ፤ የውሃ ፈቃድ መስጠት ብቻ ሳይሆን ክፍያ ስርአት መዘርጋት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የስልጣንና ኃላፊነት አንድ አካል ነው ብለዋል፡፡ የውሃ ሀብት አስተዳደር ሁሉም ውሀ ተጠቃሚዎች ውሀን የሚጠቀሙበት ፈቃድ መውሰድ ብቻ ሳይሆን የአጠቃቀም ክፍያ እንዲከፍሉ የሚጠይቅ በመሆኑ የረቂቅ ደንቡ ፋይዳ ከማስከፈል ባሻገር የውሃ ሀብታችንን ጥራትና መጠን ላይ እንድንሰራ ያደረግል፡፡

የተዘጋጀው ደንብ በዋነኛነት የውሀ ሀብትን ከምንጩ ለመጠበቅ ያለመ ሲሆን በዚህ የክፍያ ስርአት የሚካተቱት ከአንድ ሄክታር በላይ የመስኖ ተጠቃሚዎች፣ አሳ በማስገር ላይ ተሰማሩ፣ ኢንዱስሪዎች፣ የውሃ ሀይል ማመንጨት ላይ ተሰማሩ አካላት፣ የውሃ የመዝናኛ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ላይ ነው፡፡

ረቂቅ ደንቡ ላይ የግንዘቤ ፈጠራ ለማናከወን ሂልቪታስ ኢትዮጵያና ሰክሰስ ፕሮጀክት ድጋፍን እንደሚያደርጉ በመድረኩ ተገልጿል፡፡

04/12/2022

''Ethiopia’s power export fosters regional integration"

ADDIS ABABA – Ethiopia’s power export to neighboring states manifested the country’s desire to connect the East African region through electricity besides satisfying the local demand, the Ministry of Water and Energy said.

Speaking to the Ethiopian Press Agency (EPA) Water and Energy Minister Habtamu Itefa (PhD. Eng.) stated that Ethiopia believes in electricity interconnection will help to integrate and transform the economies of the East African countries. Ethiopia’s interconnectivity with neighboring countries in electricity has many benefits for the former.

“Ethiopia cannot stand alone without making connections with its neighbors and we need to be connected by physical infrastructure including electricity for the benefit of our people and economies. In doing so, due attention has been given to the electricity export will not cause a significant harm in the domestic demand.”

Ethiopia’s export of electricity to neighboring states could boost its economy besides generating a sizable foreign currency and easing the forex crunch that the country has faced. The finance will also have a pivotal role in speeding up the ex*****on of ongoing projects, and fostering regional integration and investment as well as strengthening relationships
As to the minister, Ethiopia’s aspiration to electricity interconnectedness is a good example for the world and the experience can be expanded to other countries and will bring immense economic benefits. The move also nurtures Ethiopia’s diplomatic ties with neighboring countries. Meanwhile, Habtamu highlighted that the ministry’s “Dam on my Yard” initiative has brought a commendable result helping communities in drought-prone and low-rainfall areas.

An office is implementing such initiatives in selected areas of the Oromia State including Borena Zone and Gondar City in the Amhara State by retaining rainfall water in house roofs and water tankers that are used for drinking a

Photos from Kawo koysha woreda water irrigation and energy development office's post 02/12/2022

የዓለም ዕጅ መታጠብ ቀን በጉራጌ ዞን በሶዶ ወረዳ በጥያ 1ኛ ደረጀ ትምህረት ቤት ተከበረ ፡:
************************************
በክልሉ ዋሽ ሴክተሮችና በተባባሪ ተቋማት ድጋፍ ለወራት የግንዛቤ ማስጨበጫ ተግባራት እየተከናወኑበት የቆየው የእጅ መታጠበ ቀን በጥያ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተከናወነ ደማቅ ሥነሥርዓት መቋጫውን አግኝቷል፡፡
በማጠቃለያ በዓሉ ላይ የዋሽ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ተወካዮች የእጅ መታጠብን የጤና በረከቶችን በመዘርዘር መልዕክቶቻቸውን አስተለልፈዋል፡፡ በዚህም፣ የእጅ መታጠብ ቀን ሲከበር ለአንድ ቀን ሥነሥርዓት የሚከናወን ተግባር ብቻ ሳይሆን እጃችንን ዘወትር ወሳኝ በሆኑ ጊዜያት በመታጠብ የዳበረ ልምድ ልናደርገው እንደሚገባም ተገልጿል፡፡
እጅን በውሃና በሳሙና በተገቢ ሁኔታ መታጠብ ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለውም ተገልጿል፡፡

Photos from Kawo koysha woreda water irrigation and energy development office's post 02/12/2022

DRIP IRRIGATION

Photos from Kawo koysha woreda water irrigation and energy development office's post 25/11/2022

በወላይታ ዞን ካዎ ኮይሻ ወረዳ ከሁሉም ቀበሌያት ለመጡ ጥገና ባለሙያዎች የመጠጥ ውኃ ተቋማት ደህንነት አጠባበቅ ስልጠና የወረዳው ውኃ መስኖና ማዕድን ልማት ጽ/ቤት ከRCBDIA ጋር በመሆን ለሁለት ተከታታይ ቀናት እየሰጠ ነው::

22/11/2022

የተሰጠን እውቅናና ሽልማት ለተሻለ ሥራ የሚያነሳሳን ነው:: የካዎ ኮይሻ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤትን እናመሰግናለን!!!

Photos from የካዎ ኮይሻ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት/kawo koisha woreda prosperity party office/'s post 11/11/2022
Photos from Kawo koysha woreda water irrigation and energy development office's post 17/10/2022

በካዎ ኮይሻ ወረዳ ዉኃ መስኖና ማዕድን ልማት ጽ/ቤት የሰንደቅ ዓላማ ቀን ተከበረ!!

፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠

ዛሬ ማለትም በቀን 07/02/2015 ዓ.ም በካዎ ኮይሻ ወረዳ ዉኃ መስኖና ማዕድን ልማት ጽ/ቤት የ15ኛው ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን "ሰንደቅ ዓላማችን የብዝሃነታችን መገለጫ የሉዓላዊነታችን ምሶሶ ነው!!!" በሚል መሪ ተከበረ::

Photos from Kawo koysha woreda water irrigation and energy development office's post 05/09/2022

የብልፅግና ፓርቲ አባላት ግምገማ መድረክ ፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ዛሬ ማለትም በቀን 30/12/2014 ዓ.ም በወላይታ ዞን በካዎ ኮይሻ ወረዳ ዉኃ መስኖና ማዕድን ልማት ጽ/ቤት የብልፅግና ፓርቲ የ2014 በጀት ዓመት የፓርቲና መንግስታዊ ተግባራት አፈጻጸም እንድሁም አመለካከትን መሠረት ያደረገ ሂስና ግለ-ሂስ መድረክ አባላት ራሳቸውን በሚገባ ያዩበትና ለቀጣይ ተግባራት በተለየ ሁኔታ የተዘጋጁበት ሆኖ ተጠናቅቋል ::

Photos from Kawo koysha woreda water irrigation and energy development office's post 26/08/2022

ዛሬ ማለትም በቀን 20/12/2014 ዓ.ም በወላይታ ዞን በካዎ ኮይሻ ወረዳ ዉኃ መስኖና ማዕድን ልማት ጽ/ቤት "አሁንም ትኩረት ለህዝባችን" በሚል መሪ ቃል የ2014 በጀት ዓመት አፈጻጸም እና የ2015 በጀት ዓመት ጠቋሚ ዕቅድ ዙሪያ የግምገማ መድረክ የተደረገ ሲሆን የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ሥራ ሂደቶችና ግለሰቦች የማበረታቻ ሽልማት በመስጠት ተጠናቅቋል::

23/08/2022

# # # # እንኳን ደስ አላችሁ/ን!!!! # # # #

የካዎ ኮይሻ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት በቀን 16/12/2014 ዓ.ም ባደረገው በ2014 በጀት መንግስተዊና ድርጅታዊ ሥራ አፈጻጸም ግምገማ መሥሪያ ቤታችን በሁሉም ተግባራት የተሻለ አፈጻጸም በማስመዘገቡ ተሸላሚ ሆኗል::

Photos from Kawo koysha woreda water irrigation and energy development office's post 15/08/2022

የካዎ ኮይሻ ወረዳ ዉኃ መስኖና ማዕድን ልማት ጽ/ቤት የወረዳዉ ህዝብ ንጹህ መጠጥ ዉኃ እጥረት ለመቅረፍ ትኩረት ሰጥተዉ እየሠራ ነዉ:- ቦጋለ ቡቼ
*****************************************
*****************************************
#ላሾ:-ነሐሴ 9/2014 የካዎ ኮይሻ ወረዳ ዉኃ መስኖና ማዕድን ልማት ጽ/ቤት የወረዳዉ ህዝብ ንጹህ መጠጥ ዉኃ እጥረት ለመቅረፍ ትኩረት ሰጥተዉ እየሠራ እንደሚገኝ የካዎ ኮይሻ ወረዳ ዉኃ መስኖና ማዕድን ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ቦጋለ ቡቼ አስታወቁ::
#የካዎ ኮይሻ ወረዳ ዉኃ መስኖና ማዕድን ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ቦጋለ ቡቼ በወረዳው ዉስጥ ተሠርተው ያለቁ 2 እና እየተሠሩ ያሉ 4 ፕሮጀክቶችን እየተጎበኙ ነዉ::
በ2014 በጀት ዓመት በላሾ እና ዋሙራ ከተሞቻችን በወረዳዉ መንግስትና በህብረተሰብ ተሳትፎ ከ250,000 በላይ ብር ወጪ የተደረገበትና ከ2,000 በላይ ህዝብ ተጠቃሚ የሚያደርግ የንጹህ መጠጥ ዉኃ ፕሮጀክት አስመርቆ ለህብረተሰቡ ማስረከቡን ያስታወሱት ጽ/ቤት ኃላፊ ባሁኑ ሰዓት በመንግስታዊ ባልሆኑ ደርጅቶች ደግሞ ከ6,700 በላይ ህዝብ ተጠቃሚ የሚያደርጉ 4 የንጹህ መጠጥ ዉኃ ፕሮጀክቶች በሶስት ቀበሌያት እየተሠሩ እንዳሉ አስታዉቀዋል::

#የላሾ ከተማ ንጹህ መጠጥ ዉኃ ፕሮጀክቶች ማስፋፊያና የ50,000 litre Reserviour Retaining wall በወላይታ ልማት ማህበር የሚሠራ ሲሆን የዋሙራ ቦርኮሼ እና የኮይሻ ላሾ ቀበሌያት 3ቱ ፕሮጀክቶች በRCBDIA እና በህብረተሰብ ተሳትፎ የሚሠሩ ናቸው ያሉት ኃላፊ ለጥቅት ሳምንታት የዲዛይን ክለሳ በማስፈለጉ ምክንያት ተቋርጦ የነበረ የላሾ ከተማ ዉኃ ሥራ በሚቀጠልበትና ህብረተሰባችን ይበልጥ ተጠቃሚ በሚያደርግ ዲዛይን ክለሳ ዙሪያ ከልማት ማህበሩ ጋር በመነጋገር ወደ መስማማት ለመድረስ እንደተቻለ ገልጸዋል::
በ2015 በጀት ዓመት በተደራሽነት ላይ ልዩ ዕቅድ በማዘጋጀት በአብዘኛው ቀበሌያት የንጹህ መጠጥ ዉኃ ችግር ያለባቸውን አከባቢዎችን በመለየት እና የሚፈታበትም መንገድ በማዘጋጀት መ/ቤቱ እየሠራ እንደሆነ የገለጸው ጽ/ቤት ኃላፊ ጠንካራ የባለድርሻ አካላት ድጋፍ እና የህብረተሰብ ተሳትፎ ካለ በበጀት ዓመቱ የወረዳ ውኃ ሽፋን አሁን ካለበት በ10% ማሳደግ እንደሚቻልም ጭምር ነው ያሳወቀው::

በሌላ በኩል በሳለፈነው በጀት ዓመት አገልግሎት ያቋረጡ የመጠጥ ዉኃ ተቋማትን ወደ አገልግሎት ለመመለስ በተደረገዉ ከፍተኛ ርብርብ ከ11 በላይ ተቋማትን ለመጠገን ከመቻሉም ባለፈ የኮይሻ ላሾ- ጨራቼ እና ጫውካሬ-ዋሙራ-ፓታታ net work መስመሮችን በመጠገን የኪንዶ ኮይሻ እና የኪንዶ ዲዳዬ ወረዳ ህዝም ጭምር ተጠቃም ማድረግ መቻሉን በማንሳት :ውኃ ንጹህ ነው ስለንጹህ ዉኃ ስናስብም ሆነ ስንናገር አስተሳሰባችም ጭምር ንጹህ መሆን ስላለበት እና ለውኃ ማረፊያ እንጅ ድንበር የለሌው ስለሆነ ለኪንዶ ዲዳዬ÷ለኪንዶ ኮይሻ እና ኦፋ ወረዳ ህዝብ የሚሄዱ የመጠጥ ውኃ ተቋማት ቢያንስ በአከባቢያችን እንዳይበላሹ ሁሉም ባለድርሻ አካል ኃላፊነት በመውሰድ ለተቋማት ደህንነት ድርሻችን መወጣት አለበት በማለት ጥሪ አቀርበዋል::

15/08/2022
Photos from Kawo koysha woreda water irrigation and energy development office's post 10/06/2022

በዛሬዉ ዕለት የካዎ ኮይሻ ወረዳ ው/መ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ምክትል ኃላፍ ሆኖ ከተሾሙት ከአቶ ፋልተ ፋንታ ጋር ትዉዉቅ አደርገናል::መልካም የሥራ ዘመን ይሁንልህ ወንድማችን!!!

Photos from Kawo koysha woreda water irrigation and energy development office's post 10/06/2022

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋልያዎቹ ባሳዩት አስደናቅ ጨዋታና አኩሪ ውጤት እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን!!!!!!!

Want your organization to be the top-listed Government Service in Sodo?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address

S**o
Other Government Organizations in S**o (show all)