Mewedah International

Mewedah International

Every single act of kindness is considered charity! We believe that Ulemmas play a crucial role in guiding and educating the Muslim community.

Our mission is to create a strong and supportive network within the Muslim diaspora community, fostering unity, empowerment, and a sense of belonging among individuals and families. We work to protect and defend the rights and freedoms of Ulemmas (Islamic scholars) from government interference and persecution. We believe that by connecting and collaborating, we can strengthen our community, preser

08/14/2024

አሳዛኝ ዜና
ሸይኽ ሚቅባሰኑር ተሻግረዋል::
انا لله وانا اليه راجعون

Photos from Mewedah International's post 07/06/2024

የአዲስ አበባ አህሉሱና ወልጀማአ የዑለሞች ቅሬታ አቅራቢ ኮሚቴ ተቋቋመ

ባለፉት ጊዜያት ለአንድ አመት ያህል ሀገር አቀፍ እና የክልል ቅሬታ አቅራቢ ኮሚቴ ተቋቁሞ በተለያዩ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች በመገኘት አቤቱታዎች እያቀረበ ከፍተኛ ጫና ሲፈጥር እንደነበር ይታወቃል።

ቀደም ሲል የነበረውን ታስክ ፎርስ የበለጠ ለማጠናከርና ህዝባዊ ለማድረግ ዑለማኦች በዋናነት የሚሳተፉበት የኦሮሚያ አህለሱና ወልጀማዓ የዑለማ ቅሬታ አቅራቢ ኮሚቴ ባለፈው ሳምንት የተመሰረተ ሲሆን በዛሬው ዕለት ሰኔ 27/2016 ዓ•ል የአዲስ አበባ አህለሱና ወልጀማዓ የዑለሞች ቀሬታ አቅራቢ ኮሚቴ ተቋቁሟል።

ኮሚቴው 11 ዑለማኦችን በአባልነት ያቀፈ ሲሆን ቀደም ሲል ከተቋቋመው ሀገር አቀፍ ታስክ ፎርስ ጋር በመናበብ የተጀመረውን ሰላማዊ ትግል አጠናክሮ በመቀጠል በአዲስ አበባ ውስጥ በህገወጡ መጅሊስ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ የሚፈፀሙ በደሎችን በማጋለጥ ዘላቂ ለውጥ እንዲመጣ በትጋት ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን ዛሬ በነበረው የምስረታ ስብሰባ ላይ ኮሚቴው ይፋ አድጓል።

ህዝበ ሙስሊሙ ከዑለሞቹ ጎን በመሰለፍ የተጀመረውን ሰላማዊ ትግል አጠናክሮ እንዲቀጥል እና የመሻይኾቹን መንገድ አጥብቆ እንዲይዝ ጥሪ አቅርበዋል።

Photos from Mewedah International's post 07/03/2024

መልካም የፖለቲካ ንግድ
*********************************
በሃይማኖት በመጠለል የፖለቲካ አጀንዳ አስፈጻሚ ድርጅቶች እዚህም አሜሪካ መልተዋል:: በእስልምና ስም የፕለቲካ ጫወታ ከሚጫወቱ ድርጅቶች አንዱ በድር ነው:: በመጀመሪያ ድርጅቱ የሚያዘጋጀውን ስብሰባ/convention[ቢዳአም መውሊድም ነው:) ] ሙስሊሞች ለመገናኛ እና ለመተዋወቂያ ይጠቀሙበታል። በዛውም የተዘጋጀበትን እስቴት ለመጎብኘት ዕድል ያገኛሉ። አብዛኛው ተሳታፊ ይህንን በማሰብ ልጆቹን ለማዝናናት፣ ወዳጅ ዘመድ ለመጠይቅ እግረ መንገዱን በስብሰባው ይካፈላል።

ይህ ድርጅት ይህንን የተሳታፊ/ታዳሚ ማስያዣ በማድረግ የተለያዩ የፖለቲካ ቁማሮችን ለመጫወት ይሞክራል። እንዳየሩ ፀባይ፣ እንደ ወቅቱ የፖለቲካ ሁኔታ ይከረባበታል። እንደፖለቲካው የአየር ፀባይ አንዳንዴ ተለሳላሽ፣ አንዳንዴ ተሞጋች፣ አንዳንዴ ተለጣፊ፣ አንዳንዴ ሳይመረጥ ተወካይ እየሆነ ይቀያየራል።
በዘመነ ኢህአዲግ passive ነበር። ድምፃችን ይሰማ መነሻው አከባቢ የድምጻችን ይሰማ ተቃዋሚ ወይም መሃል ሰፋሪ ነበር የኢሃዲግ ደጋፊ ስለነበር። የድምፃችን ይሰማ መንጋ ሲያይል የድምጻችን ይሰማ ደጋፊ ሆነ። በዚህ ወቅት የኢትይጵያ ሙስሊሞች ተጨቁነዋል የሚል ታፔላ ለጥፎ ሲንቀሳቀስ ነበር። ብልጥግና ሲመጣ ከብልግና ጋር ተጣበቀ። የፕልጥግና ወንበር እንዲፅና እና መንግስት በሙስሊሞች ተቀባይነት እንዳለው ለሙስሊሙ ባለውለታ መሆኑን ለማሳየት መውሊዱን ማነው ስብሰባውን ኢትጵያ ወስጥ አድርጎ፣ በአፈሙዝ የተሰበርን መጅሊስ ልክ ሕግ እና ደንብ የተከተ ነው በማለት እንታገልለታለን የሚሉትን የኢትይጵያ ሙስሊም ላይ አላግጠው፣ እነዚ የሃይማኖት ነጋዴዎች ከአፈሙዙ መጅሊስ ሹመኞች ፎቶ ተንስተው ከሃገር ወጡ።

በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል ሙስሊሞች ሲጨፈጨፉ የበላ አፍ ሆነና ዝምታን መርጠው፣ ሎሎች አትራፊ አጋጣሚውን ሲያገኙ ለብልጥግና ትማኝነታቸውን ለማሳየት በቅ ጥለቅ ሲሉ ቆዩ። መስጂድ በገፍ ሲፈርስ ባላየ ዝም ብለው፣ ንፁሃን የብልግና ስናይፐር የጥይት ሐሩር ስለባ ሲሆኑ፣ ይህንንም ዝምብለው ያለወትሮዋቸው እንደ ትያትር ትእይንቱን ሲኮመኩሙ ቆይተው የህዝቡን ማጉረምረም እና የተቃውሞ ድምፅ ሲያዩ ነገር አብርዱ ብለው ለመንግስት poletical cricis managment ሰርተው ወደ አፎታቸው ተመለሱ።

ይህ ድርጅት በሕዙቡ የቅቡልነት ድርቅ የተመታውን፣ በአፈሙዝ በሙስሊሙ ላይ የተጫነው የብልግና መጅሊስ ቅቡልነት እንዲኖረው ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል። በመሆኑም በመንግስት የአዲስ አበባ እና የፌደራል መጅሊስን በታጣቂ የተቆጣትሩትን ሐጂ ቱፋን እናከጀርባ የሚሾፍሩትን የድምፃችን ይሰማ ቡድን የህዝብ ገፅታ በሃገረ አሜሪካ ለመገንባት ያላሰለሰ ጥረት ያደርጋል። የዘንድሮውን ዳላስ ላይ የሜደረገውንም ስብሰባ ለዚሁ አጀንዳ ማስፈጸሚያ ለመጠቀም የመጅሊስ ፈንቃዮችን ኢድሳተፉ አመቻችቶላቸውል። በተከታታይ የዚህን ድርጅት ዝግጅቶቹ ካየነው የድምፃችን ይሰማ/የውሃብያ ተውካዮችን ገፅታ ለመገንባት ከነሱ ውጭ በሃገራችን አሊም የለም ይመስል ከነሱ ውጭ ለሃገሩ የሰራ የለ ይመስል ከነሱ(ወሃብያ፣ ድምጻችን ይስማ፣ መጅሊስ ፈንቃይ) ውጭ አንድ የረባ በኢትየጵያ ወስጥ ጉልህ ሚና የተጫወተ ግለሰብ ሲጋብዝ አይተነው አናውቅም፣ምክንያቱም ከፖለቲካ አንፃር አያዋጡም። ወይም የመንግስት አጀንዳ አይደሉም.​ የተከበሩ የኢትይጵያን ኡለሞችን መድረክ ላይ ማቅረብ ቀርቶ ዛሬ በየክፍለሀገሩ ከየመስግዶቻቸው የሚባረሩ የሚታሰሩ ኡለሞች ለአለቆቻቹ(ለብልግና እና ብልግና ላቋዋቋመው መጅሊስ ) ሲታሰሩ ከመጂድ ሲባረሩ ጆሮ ዳባ ልበስ ያል የቆማሪውች ስብስብ ነው።

የዘንድሮ ስብሰባ በዳላስ ቴክሳስ በሚገኘው የቢላል ኮሚኒቲ የሚደረ ሲሆን፣ ይህ ድርጀት እየሰራ ለሚገኘው የመስጂድ ቦታ ገቢ ማሰባሰቢያ ይህንን ዝግጅት እንደሚጠቀምበት ይታሰባል. ይህ ድርጅት ለመስራት የሚጥራቸው የሚበረታቱ ኮሚኒቲውን የሚያገለገሉ ተግባራት ይበል የሚያስብል ሲሆን ነገርግን ሁሉንም የአባላቱን ፍላጎት ያልጠበቀ ይህን የመሰለ የⶒለቲካ መነገጃ እንዳይሆን መጠንቀቅ ይኖርበታል! በተለይም በአመራር ቦታ ላይ የተቀመጡ ጥቂት ግለሰቦች በፍላጏታቸው እና በፖለቲካዊ እሳቤያቸው ድርጅቱን ሲዘውሩት ይስተዋላል. የድርጅቱን የወደፊት ህልውና ለማቃናት በሃገራችን የተካሄደውን መፈንቅለ መጅሊስ ከመደገፍ በመታቀብ የቀጣይ ትውልዱን የማቃናት በጎ ተግባር ላይ ቢያተኩር እንላለን.

በተረፈ መልካም የፖለቲካ ንግድ

06/16/2024

Eid Mubarek for all Ethiopians wherever you are.

06/16/2024
05/31/2024

"እኛ የአላህ ነን ወደ አላህም ተመላሾች ነን"
إنا لله وإنا إليه راجعون
በሐርቡ ከተማ አቅራቢያ የጀበሉ ኑር ሐሪማ ሸይኽ የነበሩት ሸይኽ ኢብራሂም ኢማም ሲራጅ ጣጢሳ ወደ አኺራ ተሻገሩ።
ሸይኽ ኢብራሂም ሙሉ ህይወታቸውን ለዲን የሰጡና አያሌ የዒልም ሰራዊትን ለኡማው ያበረከቱ በተጨማሪም ሙስሊሙ ማህበረሰብ ዚክርን የዘወትር ተግባሩ ያደርግ ዘንድ ጦሪቃ በመስጠት ዘክረው ያስዘክሩ እጅግ ታላቅ ሸይኽ ነበሩ።....................................................................
إن العلماء ورثة الأنبياء وإن الأنبياء لم يورثوا دينارا ولا درهما إنما ورثوا العلم
ዑለማዎች የነብያቶች ወራሾች ናቸው ነብያቶችም ዕውቀትን እንጂ ለዑመቶቻቸው ገንዘብን አላወረሱም። የሁሉም ነብያቶች እምነት የሆነዉን ኢስላምን በማስፋፋትና በማስተማር አይነተኛና የማይተካ ሚና ያላቸው ዑለማዎች ናቸው። ወደ አኼራ ያለፉትን የአሏህ እዝነት አይለያቸው ያሉትንም አሏህ ያቆይል አሚን።

04/09/2024

EID MUBARAK for all Ethiopians in the Diaspora
***********************************************

All Praise is due to Alláh, We praise Him, and we seek help from Him. We ask forgiveness from Him. We repent to Him, and we seek refuge in Him from our own evils and our own bad deeds.
During Ramadan, we fasted for Allah, not for ourselves. We fasted not just with our stomachs, but also with our ears, our eyes, our tongue, and our heart. We fasted so that Allah would count us amongst His obedient, beloved servants. Fasting has trained us and has given us more discipline.

Now that Ramadan is over we should have cultivated a heightened sense of taqwa, [a cautious, awe-inspired awareness of Allah]. In this higher spiritual state, it’s crucially important that we do not slip back into the bad old habits we had before Ramadan. We have to try hard to prolong this blissful state of nearness to Allah. For one whole month, we’ve controlled our nafs al amara bis sow, the ego that inclines us towards evil. We’ve learned to tame our lower passions, we’ve subdued our attachments to food, drink, and s*x; we’ve restrained anger, and backbiting, and cleansed ourselves of the diseases of the tongue and diseases of the spiritual heart.

Let’s continue to cultivate Taqwa, to be cautiously Allah-aware in everything we do. Let’s continue to do the good Ramadan things throughout the year. Let’s fast the 6 days of Shawwal.
In one hadith, Prophet Muhammad said that “The best of deeds are small ones, repeated often.” (repeat) Small good actions repeated often, grow into good habits, and good habits cultivate good character. A good character produces a sound heart, the Qalb Saleem that guarantees our place in Al Jannah. Therefore, my dear sisters and brothers, let’s not ever belittle even the smallest good action. Allah takes account and magnifies every good deed.

As we enjoy Eid, our hearts and our minds must also be with our brothers and sisters who suffer all manner of hardships in our home country Ethiopia as well as around the world. Much of this suffering is avoidable; it’s man-made, not natural only natural disasters.

During our Eid celebrations, let us not forget how differently Eid is being celebrated right now in a different part of our country Ethiopia, Palestine, Syria, Yemen, Kashmir, and other places of conflict around the world. We can donate generously to help others and alleviate their suffering. Our efforts may seem so small and insignificant. But Allah puts His barakah into those efforts. Our tiny efforts can grow, just as little drops of water make a stream, a river, a flood, an ocean; and little snowflakes can become an avalanche, an irresistible force of nature that sweeps away everything in its path. One of the great lessons our beloved Prophet Muhammad sws taught us is that we should work hard to fulfill the needs of others.

Allah will always care for us as long as we care for His creation. We can and must help our brothers and sisters in Islam, as well as our brothers and sisters in humanity, i.e. not only Muslims, but anyone in need, anywhere. May Allāh protect us and our families

**Mewedah International wishes you all a joyous Eid Mubarak! **

04/08/2024

ሱዑዲ ላይ ጨረቃ ስላልታየች ነገ 30ኛው የረመዷን ፆም ይሆናል።

ከሀገር አቀፍ የሙስሊሞች አቤቱታ አቅራቢ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ || ሚዛን ሚዲያ አዲስ አበባ 03/09/2024

‼️ሰበር ‼️

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሀገር አቀፍ አቤቱታ አቅራቢ ኮሚቴ የመጀመሪያው የሆነዉን መግለጫ በይፋ ሰጠ

ኮሚቴዉ በርካታ ጉዳዮችን አንስቷል ሚዛን በስፍራው በመገኘት መግለጫዉን አሰናድቶላችሗል ።

ሼር. እና ሰብስክራይብ በማድረግ ማዳረስ አይርሱ

https://youtu.be/RQTCpVvu6rM?si=QBwEIyPdGmrJ9Kst

https://youtu.be/RQTCpVvu6rM?si=lSzvjPDmQKXWG7vY

ከሀገር አቀፍ የሙስሊሞች አቤቱታ አቅራቢ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ || ሚዛን ሚዲያ አዲስ አበባ -amharicnews3005 ...

03/08/2024

📌መልካም ረመዷን
==============

በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የሙስሊም ህዝብ ቁጥር ወደ 3.45 ሚሊዮን ገደማ ሲሆን ይህም ከ 1% በላይ የሚሆነውን ህዝብ ቁጥርን ይይዛል።

በተለያዩ የአሜሪካን ግዛት የሚገኙ መስጅዶች ለማህበረሰቡ ከኢባዳ ባለፈ የተለያዩ አገልግሎትችን በመስጠት ይጠመዳሉ።

እንደ Fiqh Council of North America በስነፈልክ መሰረት ለሚቆጥሩ/ለሚሄዱ ሙስሊሞች በስነፈለክ ቀመር መሰረት የዘንድሮ ረመዳን የመጪው ስኞ ሲጀምር ተረዊህ እሁድ ምሽት ይጀምራል። የጨረቃን በሰው መታየት ለሚከተሉ በተለመደው መንገድ ጨረቃ በምትታይበት ወቅት ይሆናል።

“The Astronomical New Moon is on Sunday, March 10, 2024, at 9:00 Universal Time. On that day, the elongation is more than 8 degrees and moon is more than 5 degrees above the sun everywhere in North America. Therefore, the first day of Ramadan 1445 is on Monday, March 11, 2024, insha’Allah. Tarawih prayer will start on Sunday night.”
ሙሉውን የሚከተለውን ተጭነው ይመልከቱ: https://fiqhcouncil.org/announcement-for-ramadan-shawwal-1445

በሀገር ውስጥም ውጭም የምትኖሩ ሙስሊም ኢትይጵያውያን ይህ የረመዷን ወር የሰላም፣ የኢባዳ እና የበረካ ወር እንዲሆንላቹ መወዳህ ኢንተርናሽናል ምኞቱን ይገልፃል‼️

02/26/2024

Open Letter
*************
ከዚህ በፊት በተለያዩ ግዜያት ሃይማኖት ነክ በሆኑ ጎዳዮች የኢትይጵያ ሙስሊም ዲያስፖራ አባላት በኢትየጵያ ለሚኖሩ ወንድም እህቶቻቸው በጭቆና ጊዜ ድምፅ፣ በችገር ጊዜ መፍትሄ በመሆን ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክተዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመንግስት ድጋፍ እና በመሳሪያ ሃይል መጅሊስን የተቆጣጠረው አካል የተለያዩ መስጅዶችን በራሱ ተላላኪዎች ለመተካት በማሰብ በተለያዩ መስጅዶች ላይ የማተራመስ፣ ረብሻ የማስነሳት፣ የማዋከብ እና ሙስሊሞችን በገፍ እና በግፍ ወህኒ የመወርወር ተግባር እያከናወነ ይገኛል። ከዚህ በፊት የሙስሊሙ ልሳን የነበሩ ሚዲያዎችን በጥቀማጥቀም በመደለል ጆሮ ዳባ ልበስ እንዲሉ ተደርገዋል። የኢትይጵያ ሙስሊም ዲያስፖራ አባላት ይህንን አይን ያውጣ ግፍ እንዳያወግዝ መንግሥትንም መፍትሄ እንዳይጠይቅ፣ ጉዳዩ ተድበስብሶ እንዲያልፍ በተለያዩ የኢትይጵያ ሙስሊም ዲያስፖራ ማህበራት ወስጥ የተቀመጡ የመጅሊስ ደጋፊዎች ሰምቶ እንዳልሰማ ለማለፍ የሚያደጉት ጥረት የሚያስተዛዝብ፣ ለወከሉትም ማህበረሰብ ያላቸውን ያነሰ ግንዛቤ ያሳያል። ሆኖም ሀቅን እየአንድ አንዱ ማህበራት ደጃፍ በግልፅ እንዲደርስ ይህንን Open Letter ለሁሉም ተደራሽ እንዲሆን በእንግሊዝኛ አዝጋጅተን ለድርጅቶቹ እንዲደርስ ለቀናል። ይህ ተደራሽ እንዲሆን እርሶ በሚገኙበት ሀገር ለሚገኙ ድርጅቶች እንዲደርስ ፕሪንት አድርጎ በመስጠት፣ በሶሻል ሚዲያችው ላይ በመላክ ብቻ በየትኛውም መልኩ እንዲደርስ በማድረግ ይተባበሩን። እናመሰግናለን!

02/24/2024

Mewedah International Every single act of kindness is considered charity!

02/05/2024

የአቋዋም መግለጫ
******************
በአሜሪካ፣ በካናዳ እንዲሁም በተለያዩ የውጭ ሃገራት የሚገኙ የኢትይጵያ ሙስሊም ዲያስፖራ አባላት በሀገራችን ኢትየጵያ በተለያዩ መስጅዶች እየተደረገ ያለውን ኢ-ህገመንግስታዊ ጫና በመቃወም ባደርጉት ስብሰባ ያወጡት የአቋዋም መግለጫ

02/04/2024

ስብሰባችን ጀምሮዋል!

Photos from Mewedah International's post 01/25/2024

የሙስሊም ዲያስፖራ አባላት ከተበደሉት ሙስሊሞች ጎን እንዲቆሙ ስለመጠየቅ
**********************************************************************

ከጊዜ ወደ ጊዜ በሀገራችን በህገወጥ መንገድ መጅሊስን የተቆጣጠረው ቡድን አመለካከቴን አይቀበሉም የሚላቸውን የሙስሊም መሃበረሰብ፣ ኢማሞች፣ መስጊዶች፣ መድረሳዎች እና የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን ማሸበር፣ ማዋከብ፣ እነዚህን ተቅዋማት ለመቆጣጠር እና የራሱን ሰዎች ለመሾም በማለም ከመንግስት አካላት ጋራ በመቀናጀት የሙስሊሙን ማህበረሰብ እያሸበረ፣ እያሳሰረ እና ከኢማምነት እያፈናቀለ ይገኛል።
ለምሳሌ ያህል በዚህ ሳምንት በአዲስ አበባ አሊ መስጅድ ሕዝቡ የመረጣቸውን የኮሚቴ አባላት ሽሬያለው በማለት የመስጂዱ ማህበረሰብ እዉቅና ያልሰጣቸዉ አካላትን ሾሜያለው በማለት ረብሻ በማስነሳት ብዙ ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሶዋል። አንድ እናት እና ሌሎች መታሠራቸዉ ለመታዘብ ችለናል:: በመንግስት አካላት አመልክቱ ተብለው በሕግ ለመሄድ ሲሞክሩ በመንግስት አካላት ሸፍጥ እንደተሰራባቸው እና የሙስሊሙ ማህበረሰብ ለማን አቤት ማለት እንዳለብን ግራ ገብቶናል ሲሉ አምርረዉ ገልፀዋል።
በተመሳሳይ በዚሁ ሳምንት በኦሮሚያ ክልል ነቀምት ከተማ የሚገኘዉ ፈትህ መስጂድ ለአዲሱ መጅሊስ አስረክቡ ሲል የዞኑ ፖሊስ ኮሚሽን አስተዳደር በተደጋጋሚ ጫና እያሳደረ እንደሚገኝ የአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀዋል ። የነቀምት ፈትሒ መስጂድ ኮሚቴና ማህበረሰብ ለአዲሱ መጅሊስ አናስረክብም መስጅዳችንን እራሳችን እናስተዳድራለን፣ ከዚህ በፊት መጅሊሱ በኃይል የተቆጣጠራቸውን መስጅዶች ከአከባቢው ማህበረሰብ በመንጠቅ በራሱ አስተሳሰብ እና ፍላጎት መሰረት የራሱን አጀንዳ የሚያስፈፅሙለት ሰዎችን በመሾም የራሱን አጀንዳ ማስፈፀሚያ አድርጎዋቸዋል ሲሉ የሚደረግባቸውን ማዋከብ አስረድተዋል።

በ ጥር ወር 2016 ሆሳዕና የሚገኘው ኑር የቁርአን የሂፍዝ ማእከል መጅሊስን በኃይል የተቆጣጠሩት ሰዎች፣ አመለካከታቸውን ስለማይቀበል ወደራሳቸው ቁጥጥር ለማስገባት አሊያም ለማዘጋት ጥረት ሲያደርጉ ነበር። እነዚሁ ወገኖች የመንግስት የፅጥታ አካላት በመጠቀም የተሳሳተ መረጃ በመስጠት በርካታ የሂፍዝ ተማሪዎች እንዲታሰሩ ማድረጋቸውን እንዲሁም ፖሊስ በኋይል ቁርአንኖችን፣ ኪታቦችን፣ ደረሳዎች የሚተኙበትን አልጋዎችና ልብሶቻቸውን ውጭ ሜዳ ላይ እንዲጣል ማድረጉ የቅርብ ጊዜ ክስተት ነበር። የአከባቢው ነዋሪ ባደረገው ያላሰለሰ ጥረት እስከፍርድ ቤት በመሄድ መብታቸውን በትግል ማስከበር ችለዋል።

በታህሳስ ወር በቂርቆስ ክፍለከተማ ካዛንቺስ ወረዳ 08 የሚገኘዉ ተዉባ መስጂድ ላይ ከህዝብ እዉቅና እና ይሁንታ ዉጪ ኮሚቴ አዋቅሬያለሁ በማለቱ እና የራሱ ያደራጃቸውን ሰዎች በግድ ተቀበሉ በማለቱ ተቃዉሞ መነሳቱ እና በዚህም ምክንያት ግርግር ተነስቶ እንደነበር መስጂ ውስጥ ሁከት ማስነሳቱ የሚታወስ ነው።

በመንግስት ድጋፍ መጅሊስ ላይ የተሾመው እና ሁሉን መስጅዶች እና የእምነት ተቅዋማት ጨፍልቆ በራሱ አስተሳሰብ ለመጥመቅ እየሰራ የሚገኘው ይሄው መጅሊስ ከነዚህ ክስተቶች በፊት የትየለሌ ተመሳሳይ ሁከቶችን እና የማሸበር ስራዎችን ሲሰራ ነበር። ለምሳሌ
- በመቱ ከዚህ በፊት ሲከበር እንደነበረው የአከባቢው ሙስሊሞች መውሊድ በእስታድየም እንዳያከብሩ በመጅሊስ ሰዎች እና በመንግስት አካላት ጥምረት መከልከሉ፣
- በተለያዩ በአዲስ አበባ የሚገኙ መስጊዶች መስጅዳችን በራሳችን በመረጥነው ሰው ነው የሚተዳደረው ባሉ የመስጅዱ አከባቢ ነዋሪዎች ላይ የመንግስት የጽጥታ አካላትን በጥቅም በመደለል የሚያጠቡት ሴቶችን እስከ ልጆቻቸው መታሰራቸው።
- በኮምቦልቻ መጅሊስ በመንግስት አካላት በአፈሙዝ መቀማቱ እና ለብልፅግና መጅሊስ መሰጠቱ።
- የፍሉሃ መስጂድ ኢማን ለማፈናቀል ምንም ደሞዝ እናዳያገኙ በማድረግ እንዲሁም የአከባቢውን ማህበረስብ በተለያየ ጊዜያት ማዋከቡ።
- በአዲስ አበባ ላፍቶ መስጅድ ጨምሮ በተለያዩ የሀገራች ክፍል የተለያዩ መስጂድ ኢማሞች እና ሙአዚኖች በነፅነት ማስተማር አለመቻላቸው፣ የተለያዩ ተልካሻ ምክንያቶችን በመጠቀም መታሰራቸው፣
-በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኙ ከተሞች ውስጥ ወደ 40 የሚጠጉ መስጅዶች ያለ አግባብ መፍረሳችውን ተከትሎ በተነሳ ተቃውሞ በአንዋር መስጂድ ሙስሊሞች በመንግስት ስናይፐሮች ሆን ተብለው መገደላቸው እና ለዚህ ዘግናኝ ጭፍጨፋ ምንም አይነት የሕግ ተጠያቂነት ስይገኝለት ደማቸው ደመ ከልብ ሆኖ መቅረቱ፣ የመጅሊስ ባለሙዋሎች ይህ ጉዳይ ተድበስብሶ እንዲቀር ማድረጋቸው
- የሙስሊሙ አንድነት በሙስሊም ሊቃውንትቁርአን፣ ሐዲስ፣ ኢጅማእ እና ቂያስን መሰረት ባደረገ ውይይት እና ዑልሞች በተስማሙበት ረቂቅ ደንብ መሆን ሲገባው በአሻጥር፣ በፖለቲካዊ አካሄድ የመንግስት ድጋፍ እና ይሁኝታ በመመስረት በመንግስት አፈሙዝ ወደ መጅሊስ መግባታቸው ታዝበናል።

የአወሊያ ተቃውሞ እንደ መፈክር ካነሳቸው አበይት ጉዳዮች መሃከል የሚከተሉት ይገኙበታል።
1- የእምነት(የአመለካከት) ነፅነት
2- በመረጡት የመተዳደር/የመገለገል
3- መንግስት ከሃይማኖት እጁን እንዲያነሳ
4-ወዘተ

ከላይ የጠቀስናቸው ኡነታዎችን እንደ ናሙና ስንመለከት የአዎሊያ ተቃውሞ የመጅሊስ ስልጣን ላይ እስከሚደረስ ድረስ እንጂ እውነት ለእምነት ነፃነት እንዳልነበረ ያሳያል።

ሀገር ወስጥ ለነበረው የእምነት ነፃነት ሀገርም ወስጥ በተለይ ከሀገር ውጭ የሚኖሩ የኢትይጵያ ዲያስፖራ አባላት በያሉበት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርገው ነበር። በአብዛኛው የተሳተፉ ወንድምና እህቶች የእምነት ነፃነት እንዲከበር በማለም እንጂ እስምናን በጊዜው ከነበረው የገዢ ፓርቲ ተፅዕኖ አላቀው አሁን ላለው ገዢ ፓርቲ የሚያሸረጉድ መጅሊስ፣ ከበፊቱ በባሰ ሁኔታ ኢማሞች፣ ወንድም እና እህቶች የሚታሰሩበት ደማቸው ደመከልብ የሚሆንበት ስርዓት ለመፍጠር አልነበረም ትግሉ። ትላንት በእምነታችን ታሰርን ተገረፍን የሚሉ ሰዎች ዛሬ ላይ ደርሰው አሳሳሪ እና አሳዳጅም እንዲሆኑ አልነበረም። በዲያስፖራው የሚገኙ የተለያዩ የሙስሊም ተቅዋማት አሁን ያለውን መጅሊስ ደጋፊ የሆኑ ሰዎች ስለተቆጣጠሩዋችው የሙስሊሙ ጭቆና ተድበስብሶ እንዲቀር ለማድረግ ረጅም ርቀት ሲሄዱ ተስተውለዋል። የእነዚህ ተቅዋም አመራሮች ሙስሊሞች በሚሰበሰቡበት ስበሰባዎች የገዢን ፓርቲ እና መጅሊሱን ቅቡልነት ለማሰጠት የፖለቲካ ሥራ ሲሰሩ ይስተዋላል።

የዲያስፖራው ማህበረሰብ ከዚህ በፊት ለእምነቴ ነፅነት ብሎ፣ ለሙስሊም ወንድም እና እህቶች ድምፅ እንደሆነው ሁሉ የዚህ መጅስሊስ እና የገዢ ፓርቲ ጭቆና በትር ቀማሽ ለሆኑት እህት እና ወንድሞች ድምፅ መሆን፣ መንግስት ከእመንተት ተቅዋም እጁን እንዲያነሳ፣ መጅስሊስ በትክክለኛው የእመነት መሰረት ላይ እንዲቆም ጥሪ እና ትግል ማድረግ እስላማዊ ግዴታ ነው። የአሏህ እርዳታ ከተበዳዮች ጋር ነው! ፍትህ ከፍጡር ሳይሆን ከአሏህ ነው! ከሃቅ ጋር መቆም ለራስ ነው!
በሃሳቡ ከተስማሙ ለሌሎች እንዲደርስ ላይክ ወይም ሼር በማድረግ የበኩሎን ይወጡ።

"ሁለት ቁርዓን ባይኖረንም ቁርዓን የሚቀሩትን ማፈናቀል ነዉ እየተሰራ ያለዉ" 01/18/2024

https://youtu.be/nNpWoUP59CI?si=j8hes659vzGvWPcS

"ሁለት ቁርዓን ባይኖረንም ቁርዓን የሚቀሩትን ማፈናቀል ነዉ እየተሰራ ያለዉ" በሚዛን ሚዲያ ያልተሰሙ ድምፆች የተበደሉ የተጮቆኑ ሁሉ ይቀርባሉ ተመልካቹ አድማጩ ለህሊናዉ ይፈርዳል ።(ይቀጥላል)

01/16/2024

******ስለ ጋዛ በተመለከተ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የተሳተፉበት ዲሲ ላይ ተደረገ ******

ዩናይትድ ስቴትስ ለእስራኤል የምትሰጠውን ዕርዳታ እንድታቆም እና በጋዛ የተኩስ አቁም እንዲደረግ በሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች በመሀል ከተማ ዲሲ ቅዳሜ ከሰአት በኋላ ሰልፍ ላይ ተሰብስበው ነበር።

ተቃዋሚዎቹ “ነፃ ፍልስጤም” እያሉ እና “ተኩስ አቁም” የሚሉ መልእክቶችን የያዙ ምልክቶችን ይዘው ነበር። አሁን” እና “በጋዛ ያለውን ጦርነት አቁም እና የእስራኤልን መንግስት አፓርታይድ አገዛዝ እንዲቆም የጠየቁ ሲሆን። የአሜሪካ መንግስት ተባባሪ ነው በማለት የከሰሱ ሲሆንፕሬዚዳንት ባይደንን የዘር ማጥፋት ወንጀል ክሰዋል።

ሰልፉ በለንደን፣ ሮም፣ ፓሪስ፣ ደብሊን ጨምሮ ተመሳሳይ የፍልስጤም ደጋፊ ሰልፎች የተካሄዱበትየአለም አቀፍ የተቃውሞ ቀን አካል ነበር። ጆሃንስበርግ እና ኩዋላ ላምፑር፣ ማሌዥያ።
በአውቶቡሱ ተጭነው የሚጎርፉ ሰልፈኞች በበቀጠለው ጦርነት እና አሜሪካ ለእስራኤል ባደረገችው ድጋፍ ቁጣቸውን ገለፀዋል። የጋዛ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እንደገለጸው ከ23,000 በላይ ጋዛውያንን ሲገድልና ወደ 60,000 የሚጠጉ ቆስለዋል።

ዲሲ ብዙ የኢትይጵያውያን ኮሚኒቲ የሚኖርባት እንደመሆኑ ብዙ ኢትይጵያውያን ሙስሊሞች በዚህ ታሪካዊ የተቃውሞ ሰልፍ ለመሳተፍ እና ለሙስሊሞ ወንድሞቻቸው ያላቸውን ድጋፍ ለማሳየት በቅተዋል።

"አላማቸዉ የዳዕዋ ስራን ማጥፋት ነዉ" 01/15/2024

https://youtu.be/o3mCh3rxM7Q?si=4WOnKO6yBhnq_Nug

"አላማቸዉ የዳዕዋ ስራን ማጥፋት ነዉ" የሎሚ ሜዳ አሊ መስጂድ እናቶች (ያልተሰሙ ድምፆች )ጋር ያደረጉት ቆይታ

ያልተሰሙ ድምፆች || ያልተሰማዉ የእናቶች ለቅሶ || በሚዛን ሚዲያ ሰኞ ማታ ይቀርባል ። 01/12/2024

https://youtu.be/GR2jNn1mcA4?si=NWbj6RPNpDGK4YK5

ያልተሰሙ ድምፆች || ያልተሰማዉ የእናቶች ለቅሶ || በሚዛን ሚዲያ ሰኞ ማታ ይቀርባል ። ያልተሰሙ ድምፆች ከሚዛን ሚዲያ ፕሮግራሞች ዉስጥ አንዱ ሲሆን በዚህ ፕሮግራም ድምፅ ያጡ ድምፅ የተነፈጉ ሰሚ ላጡ የተበደሉ ድምፃቸዉ የሚያሠሙበት የሚተነፍሱበት መድረክና ፕሮግራም ነ.....

ኢትዬጵያ መንዙማ @ነቢ ዘይኔ @ibrahimwazir2 commemoration of mawlid al nebi iseattle USA 10/04/2023

ነቢዘይኔ መንዙማ - ከሲያትል ዋሽንግተን መውሊድ የተቀነጨበ d🙌🙏​👌
**********************************************************

ኢትዬጵያ መንዙማ @ነቢ ዘይኔ @ibrahimwazir2 commemoration of mawlid al nebi iseattle USA

Seattle Harari Mawlid (Pt.3) - Asiyrun Nafsi + Ya Rabbi hayyi'lana 10/04/2023

መውሊድ በየዓመቱ የሚናፈቅ የነብዩን ማንነት እንዲሁም የተላኩበትን አላማ የሚያንፅባርቅ ከብረ በዓል ነው! ዘንድሮ በተለያዩ የአሜሪካ ስቴቶች በኢትዮጵያውያን የሚደረጉ መውሊድ ዝግጅቶች እንደቀጠሉ ናቸው።

በዚህ ሳምንት ከተደረጉት የመውሊድ ዝግጅት በሲያትል ዋሽንግቶን የተደረገው መውሊድ ተጠቃሽ ነው። ከታች እንደምተመለከቱት ሞቅ ደመቅ ብሎ ተከናውኖዋል።

በዝግጅቱ የተለያዩ ትምህርቶች፣ ሰለዋት እና መንዙማ የነበረ ሲሆን። ብዙ ከወንድም ከሴትም ተሳታፊዎች የነበሩት ሲሆን በሰፍዋ በኢሽቅ ተጠናቆዋ።

በቀጣይ የተለያዩ እስቴቶች መውሊድ እንደሚኖር ሲታወቅ በተለይ በአትላንታ እና በዳላስ የሚጠበቅ ነው።

መልካም መውሊድ!!

Seattle Harari Mawlid (Pt.3) - Asiyrun Nafsi + Ya Rabbi hayyi'lana A Harari Mawlid on September 29th, 2023 CE (15th of Rabi'ul Awwal 1445 AH). Hosted by the Abadiriyyah of Seattle, this is Part 1 breaking down how a Harari M...

Want your organization to be the top-listed Non Profit Organization in Dallas?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Videos (show all)

Eid Mubarek for all Ethiopians wherever you are.
#መወዳየኮምበልቻ ሙስሊሞች በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ካደረጉ ውይይት የተቀነጨበ ‼️‼️‼️ሼር በማድረግ ተደራሽ እናድርገው ‼️‼️#ፍትህ_ለኮምበልቻ_ሙስሊሞች!#ፍትህ_በግፍ_ለታገቱት_ዑለሞች!#እንቀ...

Address

Dallas, TX

Opening Hours

Monday 8am - 6pm
Tuesday 8am - 6pm
Saturday 11am - 6pm
Sunday 11am - 6pm
Other Dallas non profit organizations (show all)
Mustard Seed Generation Mustard Seed Generation
539 W. Commerce Street Ste. 3036
Dallas, 75208

Mustard Seed Generation (MSG) is a faith-based 501(c)(3) non-profit organization that exists to eradicate barriers to mental health that increase life dissatisfaction, family dysfu...

Tom Joyner Foundation Tom Joyner Foundation
13760 Noel Road
Dallas, 75240

The Tom Joyner Foundation supports Historically Black Colleges and Universities (HBCU’s) with scholarships, endowments, and capacity building enhancements. http://tomjoynerfoundati...

International Society of Bassists International Society of Bassists
14070 Proton Road , Suite 100
Dallas, 75244

The ISB page is a non-commercial forum dedicated to promoting bass-focused events, please do not post items for sale. Visit www.isbstore.com

KERA Arts KERA Arts
Dallas, 75201

North Texas arts, culture & entertainment. Part of the KERA newsroom. Formerly Art&Seek.

Promise House Promise House
224 W Page Avenue
Dallas

Promise House embraces homeless, runaway, and at-risk teens, giving them skills, support, encouragement, and hope for a better life.

TITAS TITAS
2403 Flora Street
Dallas, 75201

TITAS/DANCE UNBOUND is the foremost presenter of internationally touring dance in North Texas. Buy t

Rainbow Days Rainbow Days
12221 Merit Drive, Suite 1700
Dallas, 75251

Helps children and youth in adversity build coping skills and resilience to create positive futures

Human Rights Initiative of North Texas, Inc. Human Rights Initiative of North Texas, Inc.
2801 Swiss Avenue
Dallas, 75204

Promoting international human rights through local service to refugees and immigrants who have suffered human rights abuses. http://www.hrionline.org *HRI cannot give legal advic...

Rescuties Animal Rescue Rescuties Animal Rescue
Dallas

We are a 501(C)(3) nonprofit. Our mission is to stop the killing of sheltered animals in the city, state and nation. We do TNR and disaster relief also.

Wings Foundation Wings Foundation
Dallas, 75261

Welcome to Wings Foundation, a 501 (c)(3) supporting American Airlines flight attendants with vital financial aid during hardships due to illness, injury, disability or natural dis...

White Rock Young Life White Rock Young Life
Dallas, 75214

Out there in the world of kids, meeting them where they are, accepting them as they are, with a visio

AT&T Performing Arts Center AT&T Performing Arts Center
2403 Flora Street
Dallas, 75201

Immerse yourself in a world of live performing arts, right here in downtown #Dallas.