love action armi

ሰዉ ሰራሽ ሆነ ተፈጥሮ አደጋ ስይከሰት ሴቶች ህፃናት አቅመ ደካማ አካል ጉዳተኞች ቅድሚያ በመሰጠት መረዳት/help all

13/11/2023

እኔና የካፌዋ አስተናጋጅ!

ትናንት አንድ ካፌ ቁጭ ብዬ አንድ መጽሐፍ እያነበብኩኝ ሳለሁ ከአስተናጋጆቹ አንዷ ቀረብ ብላ “ምን ላምጣልህ” አለችኝ፡፡ ሃሳቤ በማነበው ነገር ተወስዶ ስለነበረ ለመልስ ዘግየት ስላልኩባት በትእግስት ከጠበቀችኝ በኋላ “ምን አይነት ሃሳብ እያነበብክ ቢሆን ነው እንደዚህ ትኩረትህን የሳበው?” አለችኝ፣ በፈገግታ፡፡ እኔም ለጥያቄዋ መልስ ከሰጠኋት በኋላ፣ “መጽሐፍ ታነቢያለሽ?” ብዬ ጠየኳት፡፡

የልጅቷ መልስ፡- “ሰዎች ከሚሰጡኝ “ቲፕ” የማገኘውን ገንዘብ በመለቃቀምና በማጠራቀም የየእለት ኑሮዬን ለማሸነፍ ከጠዋት እስከማታ ስለፋ ስለምውል ለማንበብም ጊዜ የለኝም” የሚል ነበር፡፡ ይህ መልሷ በወቅቱ አጠር ያለች ሃሳብ እንድለግሳት፣ ቤቷ ስትሄድ ደግሞ የምትሰራውን የቤት ስራን እንድሰጣት አነሳሳኝ፡፡

ይህቺ ሴት የዘነጋችው ነገር ቢኖር በየእለቱ የማንበብን ልማድ ብታዳብር፣ በምትለቅመው “ቲፕ” የየእለት ኑሮዋን ለማሸነፍ ከመታገልና ማለቂያ የሌለው ዑደት ውስጥ ከመቅረት አልፋ በምታነበው ሃሳብ ደግሞ የነገ ኑሮዋን የተሻለ የማድረግ አመራጩ እንዳላት ነው፡፡

ከዚህ በፊት አንብቤው ያነቃቃኝ አንድ ሃሳብ ትዝ አለኝና እሱን አሳብ በአጭሩ አጋራኋት፡-

በቀን ውስጥ ካለን ጊዜ አንድ በመቶውን (1%) ብቻ ከዓላማችን አንጻር እድገት-ተኮር የሆኑ ጽሑፎችን ብናነብ በሌላ መልኩ ልናመጣ የማንችለውን ለውጥና እድገት እናመጣዋለን፡፡ ይህ ማለት በቀን ውስጥ ካሉን 1,440 ደቂቃዎች ውስጥ አንድ በመቶውን (1%) ማለትም 14.4 ደቂቃዎችን (15 ደቂቃ የማይሞላ) ጊዜያችንን ለንባብ መጠቀም ማለት ነው፡፡

ሰዎች በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዓታትን በጥናት አሳልፈው በጥቂት ገጾች ውስጥ ያሰፈሩልንን እውቀት እኛ በቀን 15 ደቂቃዎችን ብቻ በማሳለፍ፣ በማንበብና ተግባራዊ በማድረግ ታላቅ የሆነ እድገት ውስጥ መግባት እንችላለን፡፡

አንድ ጥናት እንደሚነግረን በቀን ውስጥ በአማካኝ ከ60 ጊዜ በላይ ጊዜ ስልካችንን እናነሳለን፡፡ ይህ ልማድ በቀን ውስጥ ከ3 ሰዓታት በላይ ስልካችን ላይ የማሳለፍን ሁኔታ ይፈጥራል፡፡ ከዚህ አንጻር ሲታይ ለ15 ደቂቃዎች መጽሐፍን ማንሳት አስቸጋሪ አይደለም፣ የልማድ ጉዳይ ሆኖ ነው እንጂ!

የልጅቷ መልስ ከዚህ ስሌት አንጻር ሲተረጎም፣ “ለማደግ ጊዜ የለኝም” የሚል ይሆናል፡፡ በየቀኑ የእለት ኑሮዋን ለመግፋት ሰዓታት በማሳለፍ የምትለቅመው “ቲፕ” አስፈላጊነት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በየቀኑ የወደፊት ኑሮዋን ለመለወጥ አስራ አምስት ደቂቃዎች በመውሰድ ሕይወት ለዋጭ እውቀት “የመለቃቀምን” ልማድ ብትጨምርበት ደግሞ እጅግ የተሻለ ነው፡፡

ካላት የማስተናገድ ስራ ሩጫ ሰረቅ በማድረግ የሰጠችኝን ትኩረቷን በመጠቀም ከላይ የዘረዘርኩትን ሃሳብ ጠቆምኳትና እንዳጋጣሚ በቦርሳዬ ውስጥ የያዝኩትን በራሴው ከተጻፉት መጽሐፎች አንዱን ሰጠኋት፡፡

የመጨረሻ ጥያቄዋ እንዴት የንባብን ልማድ ላዳብር ነበረና የሚከተሉትን ለእኔ የጠቀሙኝን ልምምዶች አጋራኋት፡፡

1. የምታነቢውን የመጽሐፍ ርእስ ለማምጣት ከምትፈልጊው ለውጥ አንጻር ምረጪ፡፡

2. የማንበብን ልማድ በደንብ እስከምታዳብሪ ገጻተቸው አነስ ያሉ መጽሐፎች ላይ አተኩሪ፡፡

3. በቀን ውስጥ ለ15 ደቂቃዎች የምታነቢበትን ንቁ ሰዓት ለይተሽ መድቢ፡፡

4. በዚያን ጊዜ ሌሎች ማድረግ የምትፈልጊያቸው ነገሮች ብቅ ቢሉም፣ ሆን ብለሽ ከእነሱ ይልቅ ማንበብ ላይ አተኩ፡፡

5. ማንበብ ካስቸገረሽ የማንበብ ልማዱ ያላቸው የንባብ አጋሮችን በማዘጋጀት የጋራ ነገር በማንበብ ተበረታቱ፡፡

6. በቀን ውስጥ የማንበቢያ ክፍተቶችን ለይተሽ ተጠቀሚባቸው፡፡ የማንበቢያ ክፍተቶች ማለት፣ ሰውን ስትጠብቂ፣ በታክሲ ውስጥ ስትጓዢ፣ በስራ መካከል ያለ እረፍት፣ ከመተኛትሽ በፊት እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡

አንብቡ! እናንብብ! እንደግ! የወደፊታችንን እኛው እንወስን!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

13/11/2023

በራስ መተማመን (Self Confidence) (ክፍል አንድ)

ጤናማ በራስ-መተማመን አላችሁ? ራሳችሁን መዝኑት!

የተወደዳችሁ ተከታታዮቼ፣ በዚህ ሳምንት በራስ ስለመተማመን ጥቂት ነጥቦችን አብረን እናያለንና ቀበቷችሁን ጠበቅ አድርጉ፡፡

ሰዎችን ማመን ማለት በሰዎቹ መተማመን ማለት ነው፡፡ በአንድ ነገረ ላይ አንድን ሰው ስናምነው ያ ሰው ያመንነውን ነገር ያሟላል ብለን በድፍረትና በመተማመን ስለምንኖር ሳንፈራና ሳንጨናነቅ እንሰማራለን፡፡

በተያያዘ ሁኔታ፣ በአንድ ሰው ላይ ከልክና ከጠርዝ ያለፈ መተማመን ውስጥ ስንገባ፣ ማመን ከሚገባን ሚዛናዊነት አልፈን በዚያ ሰው ላይ ስለምንደገፍ ሰውዬው የጠበቅነውን ነገር በማያሟላበት ጊዜ ቀውስ ውስጥ እንገባለን፡፡ ስለዚህ፣ በሰዎች ላይ ያለንን መተማመን ሚዛናዊ ማድረግም አስፈላጊ ነው፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ በራስ መተማመን ማለት ራስን "ማመን" ማለት ነው፡፡ በራሳችን ስንተማመን በማሕበራዊ ሕይወታችን በድፍረትና በመተማመን እንኖራለን፡፡ ተራ ሰዎች እንደሆንን፣ ከሌሎች ጋር የማንመጥን እንደሆንን፣ የአለም ሩጫ አልፎንና አምልጦን እንደሄደ፣ በዙሪችን ካሉ ሰዎችና ቡድኖች መመጠንና መግጠም የማንችል አድርገን ራሳችንን የምንቆጥር ከሆነ በራስ መተማመናችን የወረደ ነው ማለት ነው፡፡

ባለን ማንነትና አቅም የምንችለውን በማድረግ ቀና ብለን መኖር የምንችል ሰዎች እንደሆንን በማሰብ ሁለንተናዊ ማንነታችንን መቀበል በራስ የመተማመን የመጀመሪያው ደረጃ ነው፡፡

ሆኖም፣ በራስ መተማመንን ስናነሳ ከጠርዝ ያለፈ ደፋርነት፣ አጉል አውቃለሁና እችላለሁ ባይነትና ማንም አይደርስብኝም ባይነት እንዳልሆነ ከወዲሁ ተስማምተን እንለፍ፡፡ ይህ ሚዛን-ዘለል በራስ መተማመን (Overconfidence) አደገኛና ወደትእቢተኛነትና ትምክህተኛነት ቀጠና ስለሚወስደን ሊታረም የሚገባው ዝንባሌ ነው፡፡

በተቃራኒ ግን ጤናማ በራስ መተማመን በርካታ ጥቅሞች አሉት፡፡ እነዚህን ጥቅሞች በሚቀጥለው ጽሑፌ ከመዳሰሴ በፊት ለዛሬ አንባቢዎቼ ያላችሁን በራስ የመተማመን ደረጃ እንድትመዝኑት በተለያዩ ቦታዎች ለወጣቶች ስልጠና ስሰጥ የምጠቀምበትን አንድን ቀላል የሙከራ መጠይቅ (Questionnaire) ከዚህ በታች አስፍሬያለሁና በእሱ እንጀምር፡፡ መጠይቁ ሳይንሳዊና መቶ በመቶ ትክክለኛ ውጤታችንን አመልካች ባይሆንም ያለንበትን ሁኔታ ይጠቁምናል፡፡

ፈቃደኛ የሆናችሁ መጠይቁን ከሰራችሁና ጥያቄዎቹን ከመለሳችሁ በኋላ ውጤታችሁን ከአንድ ሰው ጋር ተወያዩ፡፡ በነገራችን ላይ በመነጋገር ላይ ስላለነውና ስለመሰል ሁኔታዎቻችን ያለንበትን ወቅታዊ ደረጃ በግልጽነት መወያየት ያለንን ማሕበራዊ ድፍረትና ሁኔታችንን ለመጋፈጥ የሚኖረንን መነሳሳት ይጨምረዋል፡፡

የመተማመንና የድፍረት መመዘኛ

1. በማንነትህና ባለህበት ሁኔታ የረካህና ደስተኛ የመሆንህን ሁኔታ ከአስር ስንት ትሰጠዋለህ?

2. በፍቅር፣ በትዳር ወይም “በብቸኝነት” ሕይወትህ ያለህን ደስተኛነት ከአስር ስንት ትሰጠዋለህ?

3. ሰዎች የተቃወሙህ ወይም የናቁህ ሲመስልህ ሁኔታውን አልፎ የመሄድ አቅምህን ከአስር ስንት ትሰጠዋለህ?

4. ሰዎች ስህተትህን ሲነግሩህ ካለ ምንም ስሜታዊነት ራስህን ለማየት ሃሳቡን የማስተናገድና የመቀበልህን መረጋጋት
ከአስር ስንት ትሰጠዋለህ?

5. ነገሮች በፈለካቸው መንገድ አልሄድ ሲሉህ አሁንም ከመሞከር ያለማቆምህን ሁኔታ ከአስር ስንት ትሰጠዋለህ?

6. ሎሎች ሰዎች ሲሳካላቸው ስታይ ስለተሳካላቸው ደስተኛ የመሆንህን ሁኔታ ከአስር ስንት ትሰጠዋለህ?

7. እርዳታ መጠየቅ በሚያስፈልግህ በማንኛውም ነገር ላይ እርዳታን ለመጠየቅ ያለህን ክፍትነት ከአስር ስንት ትሰጠዋለህ?

8. አዳዲስ ነገሮችን ከመጀመር ጋር የሚመጣን ተግዳሮትና ግፊያ በደስታና በይቻላል ስሜት የመጋፈጥህን ሁኔታ ከአስር ስንት ትሰጠዋለህ?

9. አዳዲስ ሰዎችን በማግኘትና በመተዋወቅ ጊዜ ያለህን ምቹ ስሜት ከአስር ስንት ትሰጠዋለህ?

10. ለራስህ ግብን በምታወጣበት ጊዜ ያንን ግብ ለመፈጸም ያለህን መነሳሳት ከአስር ስንት ትሰጠዋለህ?

ለእያንዳንዱ ጥያቄዎች የሰጠሃቸውን መልስ ቁጥር ደምራቸውና ውጤትህን ፍታው፡፡ አጠቃላይ ውጤትህ . . .

ከ10 እስከ 20 ከሆነ በራስ የመተማመንህ ደረጃህ እጅግ የወረደ ነው፡፡

ከ21 እስከ 30 ከሆነ በራስ የመተማመን ደረጃህ ዝቅተኛ ነው፡፡

ከ31 እስከ 40 ከሆነ በራስ የመተማመን ደረጃህ መጠነኛ ነው፡፡

ከ41 እስከ 60 ከሆነ የመተማን ደረጃህ አማካኝ ነው ነው፡፡

ከ60 በላይ ከሆነ የመተማን ደረጃህ ከፍተኛ ነው፡፡
. . ይቀጥላል!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

12/11/2023

ውድ የላብ አክሽን አባላት አመራር
በሙሉ አዳድስ መልዕክቶች በዚህዉ
ላይ ስለሚገኙ እንድተትከታተሉ
Dar love action army all mebers
This page is the orgnaztion servics
centr! your create and invet look at
love action army new messge in centr all servic

Want your organization to be the top-listed Non Profit Organization in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address


Ethiopa
Addis Ababa
Other Charity Organizations in Addis Ababa (show all)
imagine1day imagine1day
2Q3W+XV2 Imagine1day, Gabon Street
Addis Ababa, 1000

Educating people to transform themselves, their communities, and the world.

Bana Development and Humanitarian Aid Bana Development and Humanitarian Aid
City Center
Addis Ababa

The word ‘Bana’ (ባና) is a Tigrinya word meaning ‘a light emanating hopefulness’, literally ‘the dawn’

ናድቢስ ትዉልድ ናድቢስ ትዉልድ
Adiss Abeba
Addis Ababa

Organization for Welfare & Development in Action - OWDA Organization for Welfare & Development in Action - OWDA
Meskel Square , Lion Building , 9th Floor
Addis Ababa, 1502A.A

OWDA is a charity organization that Promotes conditions of sustainable human development through implementing programs on basic service delivery, economic opportunities, livelihood...

Women and Children Empowerment Organization-WCEO Women and Children Empowerment Organization-WCEO
Addis Ababa. Ethiopia
Addis Ababa

WCEO is Charity Society Organization (CSOs) founded to engage in empowering the community particularly women and children through designing different interventions that create econ...

Jaldu Page Jaldu Page
Addis Ababa, ###X

This page is where Jaldu Woreda people will share their ideas, views and discuss on what ever agendas raised

Relief Organization for South Sudan Addis Ababa, Ethiopia Relief Organization for South Sudan Addis Ababa, Ethiopia
Addis Ababa

To coordinate humanitarian assistance to save lives, restore dignity through psycho-socio rehabilita

waldah qurana waldah qurana
Addis Ababa, 1000

الجمعية الخيرية لخدمة القرآن في إثيوبيا �

ኑስራ የበጎ አድራጎት ድርጅት/ Nusra Charitable organization ኑስራ የበጎ አድራጎት ድርጅት/ Nusra Charitable organization
Mesalemia
Addis Ababa

በበጎነት ማህበረሰቡን እናብቃ!!

Spiritan Community Outreach Ethiopia - SCORE Spiritan Community Outreach Ethiopia - SCORE
SCORE A. A Office
Addis Ababa

We are part of 3000 Spiritans working in over 57 countries. We have been Serving in Ethiopia since 1972. We minister in areas for which the Church has difficulty in finding workers...