SHEGER FM 102.1 RADIO

SHEGER 102.1FM 'Yenanetew Radio' is the first private radio station in Ethiopia. We are proud to be Ethiopian and we love our country more than anything!

Hear us live on www.ShegerFM.com, dedicated phone numbers, and mobile Apps. ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬዲዮ መስከረም 23፣2000 ዓ.ም ሥራ የጀመረ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ የግል ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያ ነው፡፡

ይህ ከአዲስ አበባ በ250 ኪሎ ሜትር ክበብ ውስጥ ፕሮግራም እንዲያሰራጭ ፈቃድ አግኝቶ የረጅም ጊዜ የሬዲዮ ሥራ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች የተቋቋመው ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬዲዮ በአጭር ጊዜ ውስጥ በአድማጮች ዘንድ ተወዳጅነትን ሊያተርፍ ችሏል፡፡

ሸገር 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡

Sheger FM Tintane ኢራን በእስራኤል ላይ የፈፀመችው ጥቃት ለዓለም ምን አሳየ ? በእሸቴ አሰፋ Eshete Assefa 17/04/2024

ሸገር ዓለም አቀፍ ትንታኔ - ሚያዝያ 9፣2016

ላለፉት አስርት አመታትም ካብ ለካብ ሲተያዩ የቆዩት እስራኤልና ኢራን ከሰሞኑ ደግሞ የጥላቻ ደረጃቸው ከፍ ብሎ ጦር እስከመማዘዝ ደርሰዋል፡፡

ኢራን በእስራኤል ላይ የፈፀመችው ጥቃት ለዓለም ምን አሳየ?

እሸቴ አሰፋ

https://youtu.be/oHYuQIm-Y5s

#

Sheger FM Tintane ኢራን በእስራኤል ላይ የፈፀመችው ጥቃት ለዓለም ምን አሳየ ? በእሸቴ አሰፋ Eshete Assefa ,sheger fm news,sheger maleda,sheger,sheger sport,shegernews,shegercafe,shegerradio,shegershelf,shegerfmyoutube,shegermeaza,shegermek...

17/04/2024

ሚያዝያ 9፣2016

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲን አጸደቀ፡፡

በሀገሪቱ በተለያዩ ዘመናት የተከሰቱ እና የቀጠሉ ተደራራቢ እና ሰፊ የተጎጂና የአጥፊ ወሰን ያላቸው የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ የእርስ በእርስ ግጭቶች፣ ያልጠሩ ትርክቶች እና በደሎችን ለመፍታት የተለያዩ ሙከራዎች መደረጋቸውን ም/ቤቱ አስታውሷል፡፡

ሆኖም እነዚህ አሰራሮች በእውነት፣ በዕርቅ፣ በምህረት እና በፍትሕ ላይ የተዋቀረ እና በግልፅ ፖሊሲ የሚመራ ሁለንተናዊ የሽግግር ፍትሕ ስልትን አካታች፣ ሰብአዊ መብት ተኮር በሆነ እና በተሰናሰለ መንገድ ባለመተግበራቸው የሚፈለገውን ዘላቂ መፍትሔ ማምጣት አልቻሉም ብሏል።

ስለሆነም የሽግግር ፍትሕ ሂደቱን በተደራጀ፣ በተቀናጀ እና ውጤታማ በሆነ መልኩ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመምራትና ለመተግበር እንዲቻል ረቂቅ ፖሊሲ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቧል፡፡

ምክር ቤቱም በዛሬው እለት ባደረገው ስብሰባ በረቂቅ ፖሊሲው ላይ ከተወያያ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ መወሰኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ተናግሯል፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከዚህ በተጨማሪም የመንግስት ሠራተኞች አስተዳደርን ነጻ፣ ገለልተኛ፣ ቀልጣፋ፣ ተደራሽነት እና ተጠያቂነት ላይ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት፤ እንዲሁም ከጊዜው ጋር የሚራመድ የአስራር ስርአት ለመዘርጋት የሚያስችል ረቂቅ አዋጅ ተወያይቶ ለህዝብ አንደራሴዎች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ መወሰኑ ተሰምቷል፡፡



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram:

Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio

ሚያዝያ 9፣2016 - በኢትዮጵያ የኤች አይ ቪ የሥርጭት ምጣኔ 0.9 ቢሆንም በቦታ፣ በእድሜ፣ በጾታና በሌሎችም ምክንያቶች ከፍተኛ የስርጭት ልዩነት እየታየ ነው ተ 17/04/2024

ሚያዝያ 9፣2016

በኢትዮጵያ ያለው አጠቃላይ የኤች አይ ቪ ኤድስ የሥርጭት ምጣኔ 0.9 ቢሆንም በቦታ፣ በእድሜ፣ በጾታ እንዲሁም በሌሎችም ምክንያቶች ከፍተኛ የስርጭት ልዩነት እየታየ ነው ተባለ፡፡

የኤች አይ ቪ መከላከል ስራ ተጋላጭ ዜጎች እና ከፍ ያለ የሥርጭት ምጣኔ የሚታይባቸውን አካባቢዎች በመለየት የኤች አይ ቪ ኤድስ በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚደረጉ ጥረቶች አሁንም ሊቀጥሉ እንደሚገባ የጤና ሚኒስቴር ተናግሯል።

ሀገር አቀፍ የኤች አይ ቪ ኤድስ ፕሮግራም የዘጠኝ ወራት አፈጻጸም የጋራ ግምገማ በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ ነው።

ኢትዮጵያ ኤች አይ ቪ ኤድስ አሁን ያለበትን ስርጭት መጠን ለመቀነስ በመጪዎቹ አራት አመታት የሚተገበር ስትራቴጂክ እቅድ አዘጋጅታ በስራ ላይ እንደምትገኝ በጤና ሚኒስቴር የኤች አይ ቪኤድስ መከላከልና መቆጣጠር መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ፍቃዱ ያደታ ተናግረዋል።

በሀገሪቱ ያለው የኤች አይ ቪ የስርጭት ምጣኔ 0.9 ቢሆንም በቦታ፣ በእድሜ፣ በጾታ እንዲሁም በተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ከፍተኛ ልዩነቶች እንደሚታይ አቶ ፍቃዱ ጠቅሰዋል፡፡

የኤች አይ ቪ ዘርፈ ብዙ https://tinyurl.com/5fnap95f



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram:

Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

ሚያዝያ 9፣2016 - በኢትዮጵያ የኤች አይ ቪ የሥርጭት ምጣኔ 0.9 ቢሆንም በቦታ፣ በእድሜ፣ በጾታና በሌሎችም ምክንያቶች ከፍተኛ የስርጭት ልዩነት እየታየ ነው ተ በኢትዮጵያ ያለው አጠቃላይ የኤች አይ ቪ ኤድስ የሥርጭት ምጣኔ 0.9 ቢሆንም በቦታ፣ በእድሜ፣ በጾታ እንዲሁም በሌሎችም ምክንያቶች ከፍተኛ የስርጭት ልዩነት እየታየ ነው ተባለ፡፡ የኤች አ...

በምስራቅ አፍሪካ የድንበር አካባቢዎች በመጪዎቹ ወራት የሚኖረው የአየር ጠባይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርስ ስለሚችል ተነገረ 17/04/2024

ሚያዝያ 9፣2016

በምስራቅ አፍሪካ የድንበር አካባቢዎች ጭምር በመጪዎቹ ወራት የሚኖረው የአየር ጠባይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርስ ስለሚችል ተነገረ፡፡

ለእዚህም ጠንካራ ትብብርና አስቀድሞ የአየር ጠባይ ሁኔታ ትንተናን የሚፈልግ ነው ተብሏል፡፡

https://tinyurl.com/268xjzc4

የኔነህ ሲሳይ



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram:

Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

በምስራቅ አፍሪካ የድንበር አካባቢዎች በመጪዎቹ ወራት የሚኖረው የአየር ጠባይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርስ ስለሚችል ተነገረ ሚያዝያ 9፣2016 በምስራቅ አፍሪካ የድንበር አካባቢዎች ጭምር በመጪዎቹ ወራት የሚኖረው የአየር ጠባይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርስ ስለሚችል ተነገረ፡፡ ለእዚህም ጠንካራ ትብብርና አስቀድሞ የ....

Photos from SHEGER FM 102.1 RADIO's post 17/04/2024

ሚያዝያ 9፣2016

በኢትዮጵያ በተለያየ ምክንያት እርዳታ ከሚያስፈልጋቸው በ10 ሚሊዮን ለሚቆጠሩ ሰዎች ድጋፍ ለማቅረብ እስከ መጪው ጥር ወር ድረስ 3.24 ቢሊየን ዶላር ያስፈልጋል ተባለ፡፡

በመጪዎቹ 5 ወራት የነፍስ አድን እርዳታ ለማቅረብ እና ምግብ ነክ ድጋፍም ለማድረግ 1 ቢሊየን ዶላር እንደሚያስፈልግ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተናግሯል፡፡

የኢትዮጵያ አለም አቀፍ አጋር ድርጅቶች ከዚሁ አላማ ጋር በተገናኘ በስዊዘርላንድ ጄኔቫ ትናንት ፈንድ ማሰባሰቢ ስብሰባ አካሄዷል፡፡

በዚህም በመጭዎቹ 5 ወራት ያስፈልጋል ከተባለው 1 ቢሊየን ዶላር መካከል 630 ሚሊየን ዶላር ቃል መገባቱን በስብሰባው ላይ የተሳተፉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ በኤክስ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስፍረዋል፡፡

ይህም ከሚያስፈልገው የተገኘው 5 በመቶ ብቻ መሆኑን ያሳያል ብሏል የተባበሩት መንግስት ድርጅት በድረ ገፁ ባወጣው መረጃ፡፡

የገቢ ማሰባሰቢ ፕሮግራሙን የኢትዮጵያና የእንግሊዝ መንግስት በጋራ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጋር በመተባበር የተካሄደ ነው ተብሏል፡፡

በድርቅ፣ በጎርፍና በግጭት ምክንያት የምግብ እጥረት አጋጥሟቸው እርዳታ የሚያስልጋቸው ሰዎች ቁጥር እስከመጪው መስከረም ወር ወደ 10.8 ሚሊየን https://tinyurl.com/ysam7w5b

#ድጋፍ #እርዳታ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram:

Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Photos from SHEGER FM 102.1 RADIO's post 17/04/2024

ሚያዝያ 9፣2016

የአማራ ክልላዊ መንግስት ሕወሃት በወረራ ከያዛቸው አካባቢዎች ለቆ እንዲወጣ አሳሰበ፡፡

የክልሉ ሕዝብም ሕወሃት የከፈተውን ጥቃት እንዲመክት ጥሪ አስተላልፏል፡፡

የአማራ ክልላዊ መንግስት ይህን መግለጫ ያወጣው ሕወሃት የማንነት ጥያቄ ያለባቸውን የራያ አላማጣ፣ የራያ ባላ፣ ኦፍላ፣ የኮረም እና ዛታ አካባቢዎች ላይ ወረራ ፈፅሟል ብሎ ነው፡፡

የሕወሃት የወረራ ድርጊት፣ የፕሪቶሪያውን ስምምነት የጣሰ፣ ከጊዜያዊ አስተዳደሩ እና ከፌዴራል መንግስቱ የተደረገውን የሰላም አማራጭ ውይይት የገፋ ነው ብሎታል፡፡

ሕወሖትና ለአራተኛ ጊዜ የጀመረውን ደም አፋሳሽ ጦርነት ከማድረግ እንዲታቀብና የፕሪቶሪያውን ስምምነት አክብሮ፣ በወረራ የያዛቸውን አካባቢዎች ለቆ እንዲወጣ የአማራ ክልል መንግስት ጠይቋል፡፡፡

ያ ካልሆነ፣ የክልሉ መንግስትና ሕዝቡ ከሌሎች ኢትዮጵያዊን ጋር ሆነው፣ አገርን ከመፍረስ ሕዝብንም ከጥቃት ለመከላከል እንደሚገደድ በመግለጫው ላይ ጠቅሷል፡፡

በየደረጃው ያሉ የክልሉ የፖለቲካና የፀጥታ መዋቅር አባላትም እንዳለፈው ጊዜ ሁሉ ሕዝቡን በቁርጠኝነት እንዲያደራጁና እንዲጠብቁ ጥሪ አስተላልፏል፡፡

የክልሉ ሕዝቡም ከየአካባቢው ከሚገኙት የአስተዳደር መዋቅሮች ጋር የጠበቀ ቁርኝነት እንዲፈጠርና እንዳለፈ ጊዜ ሁሉ የተከፈተውን ጥቃት እንዲመክት ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

የፌዴራሉ መንግስትም ሕወሃት ከወረራቸው አካባቢዎች ለቆ እንዲወጣ በማድረግ፤ https://tinyurl.com/yz8npp9a

#ራያ #አላማጣ #ግጭት

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram:

Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

ለመረጃ ጥበቃና ደህንነት የሚሰሩ የመረጃ ተቋማት እየበረከቱ ሲሆን መንግስትም አስፈላጊውን መሰረተ ልማት አሟልቻለሁ እያለ ነው 17/04/2024

ሚያዝያ 9፣2016

አሰራሮችና የመረጃ ቋቶች ሁሉ ዲጂታል ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ፤ የግለሰቦች እና የመንግስት መረጃዎች ደህንነት ጉዳይ ይነሳል፡፡

ለመረጃዎቹ ጥበቃና ደህንነት የሚሰሩ የመረጃ ተቋማት እየበረከቱ ሲሆን መንግስትም እስፈላጊውን መሰረተ ልማት አሟልቻለሁ እያለ ነው፡፡

https://tinyurl.com/m9yrh7cz

ፍቅሩ አምባቸው



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram:

Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

ለመረጃ ጥበቃና ደህንነት የሚሰሩ የመረጃ ተቋማት እየበረከቱ ሲሆን መንግስትም አስፈላጊውን መሰረተ ልማት አሟልቻለሁ እያለ ነው ሚያዝያ 9፣2016 አሰራሮችና የመረጃ ቋቶች ሁሉ ዲጂታል ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ፤ የግለሰቦች እና የመንግስት መረጃዎች ደህንነት ጉዳይ ይነሳል፡፡ ለመረጃዎቹ ጥበቃና ደህንነት የሚሰሩ የመ....

17/04/2024

ሚያዝያ 9፣2016

በግጭቶችና ጦርነቶች ምክንያት የኢትዮጵያ ቱሪዝም መቀዛቀዙ ይነገራል፡፡

ለ2 አመት በዘለቀው የሰሜኑ ጦርነት ምክንያት የቱሪስት ማረፊያዎች ሁሉ የፈረሱበት የአፋር ክልል የቱሪስት እንቅስቃሴ አንዲያንሰራራ እየሰራሁ ነው ብሏል፡፡

በዚህም በ8 ወራት ውስጥ ከሁለት ሺህ በላይ የውጭ ቱሪስቶች ጉብኝት አድርገዋል ተብሏል፡፡

https://tinyurl.com/mr3e38rr

በረከት አካሉ



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram:

Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

በገንዘብ ችግር ምክንያት ህክምናቸውን የሚያቋርጡና ለሌሎችም ቀውሶች የሚዳረጉት ሴቶች ብዙዎች ናቸው ተባለ 17/04/2024

ሚያዝያ 9፣2016

በኢትዮጵያ ህክምና ለማግኘት ወደ ጤና ተቋማት ከሚሄዱ ሴቶች ውስጥ በገንዘብ ችግር ምክንያት ህክምናቸውን የሚያቋርጡና ለሌሎችም ቀውሶች የሚዳረጉት ብዙዎች ናቸው ተባለ፡፡

ይህንንም ለማገዝ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም የህክምና ኮሌጅ ህክምና ባለሞያዎች ስብስብ የበጎ አድራጎት ድርጅት መመስረቱ ተነግሯል፡፡

https://tinyurl.com/6k4uz45c

ምህረት ስዩም



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram:

Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

በገንዘብ ችግር ምክንያት ህክምናቸውን የሚያቋርጡና ለሌሎችም ቀውሶች የሚዳረጉት ሴቶች ብዙዎች ናቸው ተባለ ሚያዝያ 9፣2016 በኢትዮጵያ ህክምና ለማግኘት ወደ ጤና ተቋማት ከሚሄዱ ሴቶች ውስጥ በገንዘብ ችግር ምክንያት ህክምናቸውን የሚያቋርጡና ለሌሎችም ቀውሶች የሚዳረጉት ብዙዎች ናቸው ተባለ፡....

ከኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በደብረ ብርሃን የሚገኙ ተፈናቃዮች በሺዎች የሚቆጠሩ ናቸው 16/04/2024

ሚያዝያ 8፣2016

ከኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በደብረ ብርሃን የሚገኙ ተፈናቃዮች በሺዎች የሚቆጠሩ ናቸው፡፡

እነዚህ ተፈናቃዮች ወደ ቀድሞ ቀያቸው ይመለሳሉ ቢባልም እንደታሰበው አልሆነም፡፡

ተፈናቃዮቹ በአሁኑ ሰዓት በከፍተኛ ችግር ውስጥ መሆናቸው ተሰምቷል፡፡

የፌዴራል መንግስት በበኩሉ የድጋፍ ጥያቄ ከክልሎች ሲቀርብልኝ እሰጣለሁ፤ እያደረኩ ያለሁትም ይህንኑ ነው ብሏል፡፡

ተፈናቃዮቹ ለአራት ወራት ምንም አይነት የምግብም ሆነ ሌሎች ድጋፎች እንዳልተደረገላቸው እና በዚህም የሞቱ ሰዎች እንዳሉ ሰምተናል፡፡

በአንድ የመጠለያ ጣቢያ ብቻ ከ 12 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች ተጠልለው እንደሚገኙ እና ከነዚህም ውስጥ አብዛኛው ህፃናት፣ አዛውንት እንዲሁም የሚያጠቡ እናቶች እንደሆኑ ተነግሯል፡፡

መንግስት ‘’የእነዚህ ተፈናቃዮች ሀላፊነት እኔ እወስዳለሁ’’ ቢልም ለተከታታይ አራት ወራቶች ግን ምንም የእህል ዘር አይተው እንደማያውቁ በሶስት የመጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ ተፈናቃዮች ነግረውናል፡፡

ችግሩ ከከፋ ረሃብም አልፎ ለሞት እየተዳረጉ እንደሆነ እና ግብረሰናይ ድርጅቶች ቦታው ድረስ በመምጣት ድጋፍ ለማድረግ ቢሞክሩም እንዳልሆነላቸው ሸገር ከተፈናቃዮች ለማወቅ ችሏል፡፡

‘’ሶስት አመት ሙሉ ያለምንም ዘላቂ መፍትሄ እየተሰቃየን ነው መንግስት ሊያየን ይገባል’’ም ይላሉ ተፈናቃዮቹ፡፡

በክልሉ ተጠልለው የሚገኙ ተፈናቃዮች ወደ ቀድሞ ቀያችሁ ትመለሳላችሁ ተብለው በከፊል ቢመለሱም በድጋሚ ተመልሰው ወደ ደብረብርሃን ቻይና ካምፕ ለመግባት ቢሞክሩም መመለስ እንደማይችሉ እና ስማችሁ መሰረዙን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

አረጋዊያን ህፃናት እንዲሁም ሴቶች ወጥተው መስራት ስለማይችሉ ወጣቶች ወጥተን እንዳንሰራ የመታወቂያ ጉዳይ ሌላ እንቅፋት ሆኖብናል ብለዋል፡፡

https://tinyurl.com/ymkzwfc8

ማርታ በቀለ

#ተፈናቃዮች

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram:

Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

ከኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በደብረ ብርሃን የሚገኙ ተፈናቃዮች በሺዎች የሚቆጠሩ ናቸው ሚያዝያ 8፣2016 ከኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በደብረ ብርሃን የሚገኙ ተፈናቃዮች በሺዎች የሚቆጠሩ ናቸው፡፡ እነዚህ ተፈናቃዮች ወደ ቀድሞ ቀያቸው ይመለሳሉ ቢባልም እ....

የሞቃዲሾው ጥልማሞት - በእሸቴ አሰፋ 16/04/2024

ሚያዝያ 8፣2016

የሞቃዲሾው ጥልማሞት - በእሸቴ አሰፋ

https://youtu.be/nspYKTHN29s

#ዲፕሎማት

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram:

Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

የሞቃዲሾው ጥልማሞት - በእሸቴ አሰፋ የሞቃዲሾው ጥልማሞት - በእሸቴ አሰፋየፖሊስ መኮንኑ፣ መምህሩ፣ ዲፕሎማቱ እንዲሁም የመረጃ እና ደህንነት ባለሞያው የዶ/ር አስማማው ቀለሙ ማን ነበሩ? (ተያያዥ ዘገባ)https://tinyurl.com/mx5t93uuሚ.....

ይስሐቅ ኦቲዝም ማዕከል የአዕምሮ እድገት ውሱንት ላለባቸውን ህፃናት ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ተናገረ 16/04/2024

ሚያዝያ 8፣2016

በጄኔራል ዊንጌት ት/ቤት አካባቢ የሚገኘው ይስሐቅ ኦቲዝም ማዕከል የአዕምሮ እድገት ውሱንት ላለባቸውን ህፃናት ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ተናገረ፡፡

https://tinyurl.com/ynhfsvsy

ወንድሙ ሀይሉ



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram:

Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

ይስሐቅ ኦቲዝም ማዕከል የአዕምሮ እድገት ውሱንት ላለባቸውን ህፃናት ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ተናገረ ሚያዝያ 8፣2016 በጄኔራል ዊንጌት ት/ቤት አካባቢ የሚገኘው ይስሐቅ ኦቲዝም ማዕከል የአዕምሮ እድገት ውሱንት ላለባቸውን ህፃናት ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ተናገረ፡፡ ወንድሙ ሀይሉ ...

ወደ ተለያዩ ሀገራት ለመሄድ በጅቡቲ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ መታሰቡ ተሰምቷል 16/04/2024

ሚያዝያ 8፣2016

ጅቡቲን እንደመሸጋገሪያነት በመጠቀም ወደ ተለያዩ ሀገራት ለመሄድ፤ በዚያ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ መታሰቡ ተሰምቷል፡፡

በኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎ ዋና ዳይሬክተር የተመራ የልዑክ ቡድን ለዚሁ ጉዳይ ጅቡቲ መሆኑ ተሰምቷል፡፡

https://tinyurl.com/ye2y3x33

ንጋቱ ሙሉ ያሰናዳውን በያሬድ እንዳሻው

#ጅቡቲ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram:

Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

ወደ ተለያዩ ሀገራት ለመሄድ በጅቡቲ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ መታሰቡ ተሰምቷል ሚያዝያ 8፣2016 ጅቡቲን እንደመሸጋገሪያነት በመጠቀም ወደ ተለያዩ ሀገራት ለመሄድ፤ በዚያ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ መታሰቡ ተሰምቷል፡፡ በኢሚግሬሽን እና ዜግነት...

ሚያዝያ 8፣2016 - በማህበራዊ የትስስር ገፆች ላይ የሚተላለፍ የጥላቻ ንግግር መጠኑ ጨምሯል ተባለ 16/04/2024

ሚያዝያ 8፣2016

በኢትዮጵያ በማህበራዊ የትስስር ገፆች ላይ የሚተላለፍ የጥላቻ ንግግር እና የሀሰተኛ መረጃ መጠኑ ጨምሯል ተባለ።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ይህንን ያለው፤ ዛሬ በማህበራዊ የትስስር ገጾች የጥላቻ ንግግር እና ሀሰተኛ መረጃ ሀገራዊ ሪፖርትን ይፋ ባደረገበት ወቅት ነው።

ጥናቱ የተካሄደው 5 የማህበራዊ ገፆችን ትኩረት አድርጎ መሆኑ የተነገረ ሲሆን ፌስቡክ፣ ዩቲዩብ፣ ኤክስ፣ ቴሌግራም እና ቲክቶክ ላይ ጥናቱ እንደተካሄደ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሲናገር ሰምተናል።

በሪፖርቱም የጥላቻ እና ሀሰተኛ መረጃ ስርጭቱ ካለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር ብሄር ተኮር እና የፖለቲካ ጉዳዮች ይበዙ እንደነበር የተናገው ባለስልጣኑ በ2016 ግማሽ አመት ከብሄር ጉዳዩች ይልቅ የፖለቲካ ሀሰተኛ መረጃ ስርጭቶች እንደጨመረ ጥናቱ ያሳያል ተብሏል።

በኤክስ ገፅ 66 በመቶ፣ በፌስቡክ 63 በመቶ፣ በቴሌግራም 59 በመቶው በፅሁፍ የተሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎች ሲሆኑ በምስል እና በፅሁፍ የተላለፉት ደግሞ በኤክስ 12 በመቶ እና በቴሌግራም 18 በመቶ መሆኑ ተነግሯል።

በቪዲዮ ከተላለፉ ሀሰተኛ መረጃዎች መካከል ደግሞ በቲክቶክ https://tinyurl.com/32xf9a45



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram:

Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

ሚያዝያ 8፣2016 - በማህበራዊ የትስስር ገፆች ላይ የሚተላለፍ የጥላቻ ንግግር መጠኑ ጨምሯል ተባለ በኢትዮጵያ በማህበራዊ የትስስር ገፆች ላይ የሚተላለፍ የጥላቻ ንግግር እና የሀሰተኛ መረጃ መጠኑ ጨምሯል ተባለ። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ይህንን ያለው፤ ዛሬ በማህበራዊ...

16/04/2024

ሚያዝያ 8፣2016

የፖሊስ መኮንኑ፣ መምህሩ፣ ዲፕሎማቱ እንዲሁም የመረጃ እና ደህንነት ባለሞያው የዶ/ር አስማማው ቀለሙ የቀብር ሥነ ሥርዓት በዛሬው ዕለት ይፈፀማል፡፡

ዶ/ር አስማማው ቀለሙ ማን ነበሩ?

እሸቴ አሰፋ

https://tinyurl.com/mx5t93uu

#ዲፕሎማት

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram:

Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

በዩኔስኮ የተመዘገበው የሸዋል ኢድ በዓል ከዛሬ ጀምሮ በሀረሪ ክልል መከበር ይጀምራል 16/04/2024

ሚያዝያ 8፣2016

በዩኔስኮ የተመዘገበው የሸዋል ኢድ በዓል ከዛሬ ጀምሮ በሀረሪ ክልል መከበር ይጀምራል፡፡

እንግዶችም ወደ ሀረር እየገቡ ነው ተብሏል፡፡

https://tinyurl.com/mtfhbedt

በረከት አካሉ

#ሀረር

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram:

Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

በዩኔስኮ የተመዘገበው የሸዋል ኢድ በዓል ከዛሬ ጀምሮ በሀረሪ ክልል መከበር ይጀምራል ሚያዝያ 8፣2016 በዩኔስኮ የተመዘገበው የሸዋል ኢድ በዓል ከዛሬ ጀምሮ በሀረሪ ክልል መከበር ይጀምራል፡፡ እንግዶችም ወደ ሀረር እየገቡ ነው ተብሏል፡፡ በረከት አካሉ #ሸዋ....

ሚያዝያ 8፣2016 - በአማራ ክልል በአማካኝ አንድ መፅሐፍ ለ70 ተማሪዎች የደረሰበት አካባቢዎች መኖራቸዉን፤ እንባ ጠባቂ ተቋም አረጋግጫለው አለ 16/04/2024

ሚያዝያ 8፣2016

በአማራ ክልል በአማካኝ አንድ መፅሐፍ ለ70 ተማሪዎች የደረሰበት አካባቢዎች መኖራቸዉን፤ የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም አረጋግጫለው አለ፡፡

የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የባህርዳር ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት፤ ክልሉ የትምህርት ጥራትን በተመለከተ ያደረገውን የክትትል ሪፖርት ለሸገር ራድዮ ተናግሯል፡፡

በዚህም በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተማሪዎች የመፅሐፍ ጥምርታ በአማካኝ አንደ መፅሐፍ ለ60 ተማሪ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ደግሞ አንድ መፅሐፍ ለ70 ተማሪ ነው የሚሰጠው ያሉን የህዝብ እንባ ጠባቂ የባህር ዳር ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ጋሻነው ደሴ ናቸዉ፡፡

ለተማሪዎች የመማሪያ መጽሐፍት በሶፍት ኮፒ ቢሰጥም ተማሪዎች ማንበብያ ማለትም እንደ ስልክ ፣ ታብሌት እና ላፕቶፕ ሰለሌላቸው እየተቸገሩ ነው፤ ይህም በትምህርት ጥራት ላይ ችግር እያስከተለ ነው ተብሏል፡፡

ጽህፈት ቤቱ ሌላው ግኝቴ ነው ያለው፤ በባህርዳር ዙሪያ በ71 የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ ባረደኩት ክትትልም ከ71ዎቹ ትምህርት ቤቶች 50ዎቹ ምንም ዓይነት መጸዳጃ ቤት የሌላቸው ሲሆን https://tinyurl.com/327mzxp5

#ተማሪዎች #ባህርዳር

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram:

Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

ሚያዝያ 8፣2016 - በአማራ ክልል በአማካኝ አንድ መፅሐፍ ለ70 ተማሪዎች የደረሰበት አካባቢዎች መኖራቸዉን፤ እንባ ጠባቂ ተቋም አረጋግጫለው አለ በአማራ ክልል በአማካኝ አንድ መፅሐፍ ለ70 ተማሪዎች የደረሰበት አካባቢዎች መኖራቸዉን፤ የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም አረጋግጫለው አለ፡፡ የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የባህርዳር ቅርንጫፍ ...

15/04/2024

ሚያዝያ 7፣2016

የኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ከእንግዲህ የተለያዩ ማህበራዊ ውይይቶችን ስትጠቀሙ አንዳች ክፍያ የማትጠየቁበትን አገልግሎት ጀምሮላቹሀል ተባለ።

ይህ የተባለው ዛሬ ኢትዮ ቴሌኮም ፅሁፍ ለመላላላክ ቪዲዮና ሌሎችንም ማህበራዊ ጉዳዮች የሚያበረታ አገልግሎት መጀመሩን በተናገረበት ጊዜ ነው ።

ስልካችሁ ውስጥ ሳንቲም ኖረም አልኖረም ክፍያ ሳትጠየቁ ከወዳጅ ቤተሰብ ጋር ወግ ለመሰለቅ የቀጥታ ውይቶችንም(online chat) ለማድረግ እንደሚቻል ዛሬ የተጀመረው አገልሎት ይፈቅዳል ተብሏል።

ኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞቹ ማህበራዊ ውይቶችን እና ወጎችን ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ የሚገናኙበትን አገልግሎት በቴሌ ብር ሱፐር አፕ ምንም አይነት ተጨማሪ የኢንተርኔት ክፍያ ሳይጠይቅ ጀምሯል።

ደንበኞች መረጃዎችን መቀባበል የሚችሉበትና ማህበራዊ ወጎቻቸውን የሚያቀላጥፉበት አገልግሎት ለደንበኞች መቅረቡንም ሰምተናል።

አገልግሎቱም "ቴሌ ብር ኢንጌጅ" ተብሏል።

በዚህ አገልግሎት ደንበኞች ከቴሌብር አገልግሎት ባለፈ ስለ ቢዝነስ፣ ስለማህበራዊ ጉዳይና ሌሎችንም ወግ ማድረግ የሚችሉበት ነው ተብሏል።

በ ቴሌ ብር ኢንጌጅመንት ፅሁፍ ለመላላክ፣ ቪዲዮና የድምፅ ፉይሎችን ለመቀባበል እንዲሁም ሰነዶችን ለመጋራት የሚያስችል እንደ ማህበራዊ ትስስር ገፅ አይነት አመቺ አገልግሎት መሆኑን ኩባንያው አስረድቷል።

የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ይህ አገልግሎት ኢትዮዽያ በራሷ ልጆች ያዘጋጀችው ፣ከቴሌ ብር እና አገልግሎቱ ባለፈ መረጃና አብሮነትን ፣ማህበራዊ ህይወትን የሚያበረታ ነው ብለዋል ።

የቴሌ ብር ኢንጌጅ ግለሰብም ሆኑ የቢዝነስ ደንበኞች የተናጠል ወይም የቡድን የቀጥታ ውይይቶችን
(online chat) ለማድረግ ያስችላል ተብሏል ።

የግብይት መረጃ ለመቀባበል በውይይት ወቅት ደንበኞች ከመተግበርያው ሳይወጡ ስልክ ሳይደውሉ እዛው ገንዘብ ለመጠየቅ ለመላክና ለመቀበል ሂሳብም ለመጋራት ያስችላል ተብሎለታል።

ይህ አገልግሎት መረጃን ከመለዋወጥ ባለፈ ማህበራዊ ህይወትን የሚያጠነክር መሆኑም ተሰምቷል።

ኢትዮ ቴሌኮም በዲጅታል አለም የትብብር ባህል እንዲዳብር ፣ክህሎትና ሌላውም ለሁሉ እንዲደርስ የዴቨሎፐሮች ማህበረሰብ እንዲፈጠሩ የሚያግዝ የዴቨሎፐር ፖርታል ማዘጋጀቱን ተናግሯል።

ኩባንያው የዲጅታል ስነ ምህዳሩን ለማስፋት ዴቨሎፐሮች ከቴሌ ብር ሱፐር አፕ ጋር ሲስተሞቻቸውን በማስተሳሰር ምርትና አገልግሎቶች ባጠረ ግዜ ተደራሽ ለመማድረግ የዴቨሎፐር ፖርታል ጀምሯል ተብሏል።

ተህቦ ንጉሴ



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram:

Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Mekoya - ቅስቀሳ የዘራው ጥላቻ እና ጥላቻ ያጋጋለው እልቂት! Rwandan Genocide በእሸቴ አሰፋ Eshete Assefa 15/04/2024

መቆያ - ቅስቀሳ የዘራው ጥላቻ እና ጥላቻ ያጋጋለው እልቂት! በእሸቴ አሰፋ ሚያዝያ 5፤2016.

https://youtu.be/lY9dLv2q-yM



ውድ የሸገር ቤተሰቦች፣ ሌሎች ማራኪ የመቆያ መሰናዶቻችን ይመልከቱ…👇👇👇👇👇👇👇

https://www.youtube.com/watch?v=Cq676-5oCak&list=PLep9COCl9DsZHLRzElVug3fSDuMJwYujJ

Mekoya - ቅስቀሳ የዘራው ጥላቻ እና ጥላቻ ያጋጋለው እልቂት! Rwandan Genocide በእሸቴ አሰፋ Eshete Assefa Mekoya - ቅስቀሳ የዘራው ጥላቻ እና ጥላቻ ያጋጋለው እልቂት! Rwandan Genocide በእሸቴ አሰፋ Eshete Assefa በሩዋንዳ የዘር ማጥፋት የተፈፀመበትን 30ኛ ዓመት she...

15/04/2024

ሚያዝያ 7፣2016

ኢትዮጵያ በውሀ ሀብቷ አጠቃቀም ዙሪያ ከነግብፅና ሱዳን ጋር የገባችበት ውዝግብ በሀገር ውስጥም በክልሎች መካከል ሊነሳ የሚችልበት እድል እንደሚኖር ባለሞያዎች ይናገራሉ፡፡

የውሃ አስተዳደር ስራን በተቀናጀ መንገድ መምራት ካልተቻለ በክልሎች መካከል ያመግባባት ምክንያት ሊሆን ይችላል ተብሏል፡፡

https://tinyurl.com/yaffjufk

ቴዎድሮስ ወርቁ



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram:

Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

በኦሮሚያ 240 ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸው ተሰማ 15/04/2024

ሚያዝያ 7፣2016

በኦሮሚያ ክልል ባለው የሰላም እጦር ምክንያት 240 ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸው ተሰማ፡፡

ትምህርት ቤቶቹ፤ ከ131 ሺህ በላይ ተማሪዎች ይማሩባቸው የነበሩ መሆናቸውን ሰምተናል፡፡

https://tinyurl.com/2k7cpc6p

ፋሲካ ሙሉወርቅ



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram:

Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

በኦሮሚያ 240 ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸው ተሰማ ሚያዝያ 7፣2016 በኦሮሚያ ክልል ባለው የሰላም እጦር ምክንያት 240 ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸው ተሰማ፡፡ ትምህርት ቤቶቹ፤ ከ131 ሺህ በላይ ተማሪዎች ይማሩባቸው የነበሩ መሆናቸውን ሰምተናል፡...

ሀይማኖቶች፤ ለሰላም፣ ለሰብአዊ ክብርና ነፃነት መጠበቅ የድርሻቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ 15/04/2024

ሚያዝያ 7፣2016

ሀይማኖቶች፤ ለሰላም፣ ለሰብአዊ ክብርና ነፃነት መጠበቅ የድርሻቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ፡፡

ሁለተኛው አለም አቀፍ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡

https://tinyurl.com/r3dxh25b

ያሬድ እንዳሻው

#ሀይማኖት

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram:

Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

ሀይማኖቶች፤ ለሰላም፣ ለሰብአዊ ክብርና ነፃነት መጠበቅ የድርሻቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ ሚያዝያ 7፣2016 ሀይማኖቶች፤ ለሰላም፣ ለሰብአዊ ክብርና ነፃነት መጠበቅ የድርሻቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ፡፡ ሁለተኛው አለም አቀፍ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው.....

የተፈራው እየደረሰ ነው! - ዓለም አቀፍ ትንታኔ 15/04/2024

ሚያዝያ 7፣2016 - ዓለም አቀፍ ትንታኔ

ኢራን በእስራኤል ላይ ጥቃት መክፈቷ ለአሜሪካ የፈሩት ይደርሳል ሆኖባታል፡፡

ኢራን በእስራኤል ላይ የሚሳየል እና የድሮን ዶፍ አዝንባባታለች፡፡

የአሜሪካ ጦርም እስራኤልን ከጥቃት ለመጠበቅ በአየር መከላከያው ከጎኗ ተሰልፋለች፡፡

https://youtu.be/t6NssY5CRpk

የኔነህ ከበደ

#አሜሪካ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram:

Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

የተፈራው እየደረሰ ነው! - ዓለም አቀፍ ትንታኔ ሚያዝያ 7፣2016 ኢራን በእስራኤል ላይ ጥቃት መክፈቷ ለአሜሪካ የፈሩት ይደርሳል ሆኖባታል፡፡ኢራን በእስራኤል ላይ የሚሳየል እና የድሮን ዶፍ አዝንባባታለች፡፡ የአሜሪካ ጦርም እስራኤል.....

15/04/2024

ሚያዝያ 7፣2016

ደመናን ተጠቅሞ ዝናብ የማዝነብ ቴክኖሎጂ በኢትዮጵያ መሰራት ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡

መላውን በሀገሪቱ ለማስፋፋት እና ችግር ፈቺ ለማድረግ የተለያዩ ተቋማት በጋራ እየሰሩ ነው ተብሏል፡፡

https://tinyurl.com/yjvckpm8

ምንታምር ፀጋው



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram:

Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

በየፍትህ ተቋማት መካከል ተግባብቶ መስራት ፈተና እየሆነ መምጣቱ ይነገራል 15/04/2024

ሚያዝያ 7፣2016

በኢትዮጵያ የፍትህ ተቋማት መካከል ተግባብቶ መስራት ፈተና እየሆነ መምጣቱ ይነገራል፡፡

ከዚህም ውስጥ በፍርድ ቤቶች የተወሰኑ ጉዳዮች በፖሊስ ተፈፃሚ አለመደረጋቸው አንዱ ነው፡፡

ይህም በተለይ በፍ/ቤቶች አሰራር ላይ ጫና መፍጠሩን የክልል ፍ/ቤቶች ተናግረዋል፡፡

https://tinyurl.com/y5etuc9t

በረከት አካሉ



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram:

Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

በየፍትህ ተቋማት መካከል ተግባብቶ መስራት ፈተና እየሆነ መምጣቱ ይነገራል ሚያዝያ 7፣2016 በኢትዮጵያ የፍትህ ተቋማት መካከል ተግባብቶ መስራት ፈተና እየሆነ መምጣቱ ይነገራል፡፡ ከዚህም ውስጥ በፍርድ ቤቶች የተወሰኑ ጉዳዮች በፖሊስ ተፈፃሚ አለመደረጋቸው አን....

ኢትዮጵያዊያን ሴት ባለፀጎች በአለም ገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆኑና ጥራት ያለው ምርት እንዲያመርቱ ድጋፍ እየተደረገላቸው ነው ተብሏል 15/04/2024

ሚያዝያ 7፣2016

ኢትዮጵያዊያን ሴት ባለፀጎች በአለም ገበያ በሚፈለገው ልክ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ እንዲሁም በተገቢው መንገድ ጥራት ያለው ምርት እንዲያመርቱ ድጋፍ እየተደረገላቸው ነው ተብሏል፡፡

https://tinyurl.com/42vmfjrm

ፋሲካ ሙሉወርቅ

#ሴቶች #ድጋፍ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram:

Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

ኢትዮጵያዊያን ሴት ባለፀጎች በአለም ገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆኑና ጥራት ያለው ምርት እንዲያመርቱ ድጋፍ እየተደረገላቸው ነው ተብሏል ሚያዝያ 7፣2016 ኢትዮጵያዊያን ሴት ባለፀጎች በአለም ገበያ በሚፈለገው ልክ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ እንዲሁም በተገቢው መንገድ ጥራት ያለው ምርት እንዲያመርቱ ድጋፍ እየተደረገላቸው ነው ተብ....

ዘረፋ እና ቃጠሎ የደረሰባቸው የአበባ እርሻዎች ወደ ስራ አልገቡም ተብሏል 15/04/2024

ሚያዝያ 7፣2016

በባህር ዳር አካባቢ ዘረፋ እና ቃጠሎ የደረሰባቸው የአበባ እርሻዎች ወደ ስራ አልገቡም ተብሏል፡፡

https://tinyurl.com/mr2786ux

ያሬድ እንዳሻው

#ቃጠሎ #ዝርፊያ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram:

Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

ዘረፋ እና ቃጠሎ የደረሰባቸው የአበባ እርሻዎች ወደ ስራ አልገቡም ተብሏል ሚያዝያ 7፣2016 በባህር ዳር አካባቢ ዘረፋ እና ቃጠሎ የደረሰባቸው የአበባ እርሻዎች ወደ ስራ አልገቡም ተብሏል፡፡ ያሬድ እንዳሻው #ቃጠሎ #ዝር...

Sheger cafe - የትውስታ ፖለቲካ በወቅታዊት ኢትዮጵያ/ተግባሩ ያሬድ እና ዮናስ አሽኔ ከመዓዛ ብሩ ጋር …@ShegerFM1021Radio 14/04/2024

ሸገር ካፌ፦ የትውስታ ፖለቲካ በወቅታዊት ኢትዮጵያ ተግባሩ ያሬድ እና ዮናስ አሽኔ ከመዓዛ ብሩ ጋር - ሚያዝያ 6፤2016

https://youtu.be/f5VrEPY8ia4

#ፖለቲካ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram:

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Sheger cafe - የትውስታ ፖለቲካ በወቅታዊት ኢትዮጵያ/ተግባሩ ያሬድ እና ዮናስ አሽኔ ከመዓዛ ብሩ ጋር …@ShegerFM1021Radio የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…Telegram: t.ly/ShegerWebsite: t.ly/ShegerFM YouTube: t.ly/SHEGERTiktok: https://bit.ly/44Dd6Il Sheger FM 102.1 Radio is The F...

Yechewata Engida -“ለስዕል ነፍስ የሚሰጠው የእያንዳንዱ ሰው እውነታ ነው”Artist Tibebe Terffa With Meaza Birru Part 2 13/04/2024

የጨዋታ እንግዳ፦ ለጥበብ ታማኝ ሆኖ የኖረው ሠዓሊ ጥበበ ተርፋ መታሰቢያ!

ከመዓዛ ብሩ ጋር ያደረጉት ጨዋታ ክፍል 2 - ሚያዝያ 5፣2016

https://youtu.be/CY_aq2Pj5zw

#ጥበብ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram:

Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

Yechewata Engida -“ለስዕል ነፍስ የሚሰጠው የእያንዳንዱ ሰው እውነታ ነው”Artist Tibebe Terffa With Meaza Birru Part 2 Yechewata Engida -“ለስዕል ነፍስ የሚሰጠው የእያንዳንዱ ሰው እውነታ ነው”Artist Tibebe Terffa With Meaza Birru P...

Sheger Tizita ze Arada - ባለቅኔው መንግስቱ ለማ ወደ ኪነ-ጥበብ ያመላከታቸውን የልጅነት ህይወት! Mengistu Lemma በተፈሪ ዓለሙ 13/04/2024

ትዝታ ዘ አራዳ - ባለቅኔው መንግስቱ ለማ ወደ ኪነ-ጥበብ ያመላከታቸውን የልጅነት ህይወት! በተፈሪ ዓለሙ - ሚያዝያ 5፣2016

https://youtu.be/nt4FrGZ1u-A

Sheger Tizita ze Arada - ባለቅኔው መንግስቱ ለማ ወደ ኪነ-ጥበብ ያመላከታቸውን የልጅነት ህይወት! Mengistu Lemma በተፈሪ ዓለሙ Sheger Tizita ze Arada - ባለቅኔው መንግስቱ ለማ ወደ ኪነ-ጥበብ ያመላከታቸውን የልጅነት ህይወት! Mengistu Lemma በተፈሪ ዓለሙ...

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Videos (show all)

#የቅዳሜ_ጨዋታነገ ጥር  18፣2016 ከሰዓት በኋላ ከሸገር ጋር ከሆናችሁ በእነዚህ የቅዳሜ ጨዋታ መሰናዶዎቻችንን እንጠብቃችኋለን! የቅዳሜ ጨዋታችን፤ ከቀኑ 7:00 ሲሆን በሟሟሻ ይጀመራል፡፡...
#የቅዳሜ_ጨዋታነገ ጥር  11፣2016 በጥምቀት በዓል ከሰዓት በኋላ ከሸገር ጋር ከሆናችሁ በእነዚህ የቅዳሜ ጨዋታ መሰናዶዎቻችንን እንጠብቃችኋለን! የቅዳሜ ጨዋታችን፤ ከቀኑ 7:00 ሲሆን በሟ...
#የቅዳሜ_ጨዋታነገ ጥር 4፣2016 ከሰዓት በኋላ ከሸገር ጋር ከሆናችሁ በእነዚህ የቅዳሜ ጨዋታ መሰናዶዎቻችንን እንጠብቃችኋለን! የቅዳሜ ጨዋታችን፤ ከቀኑ 7:00 ሲሆን በሟሟሻ ይጀመራል፡፡ እ...
#የቅዳሜ_ጨዋታ_ልዩ_የበዓል_መሰናዶነገ ታህሳስ 27፣2016  በገና በዓል ዋዜማ ከሰዓት በኋላ ከሸገር ጋር ከሆናችሁ በእነዚህ የቅዳሜ ጨዋታ መሰናዶዎቻችንን እንጠብቃችኋለን! የቅዳሜ ጨዋታችን...
#የቅዳሜ_ጨዋታየነገው ቅዳሜ ታህሳስ 13፣2016 ከሰዓት በኋላ ከሸገር ጋር ከሆናችሁ እነዚህን መሰናዶዎችን ታደምጣላችሁ፡፡ከቀኑ 7:00 ሲሆን  ማሟሻ፣ የቅዳሜ ጨዋታችን ማስጀመሪያ ይሆናል፡፡...
#የቅዳሜ_ጨዋታ የነገ ታህሳስ 6፣2016 የቅዳሜ ጨዋታ መሰናዶዎቻችንን እናሳውቃችሁ!የቅዳሜ ጨዋታችን፤ ከቀኑ 7:00 ሲሆን በማሟሻ ይጀመራል፡፡በመቀጠል፤ እሸቴ አሰፋ በመቆያ መሰናዶው፤ ስለ ...
ወደ ብሔራዊ ባንክ  የሚገባው የወርቅ መጠንም  ቀንሷል ተባለ!
#የቅዳሜ_ጨዋታ የነገ ህዳር 15፣2016 የቅዳሜ ጨዋታ መሰናዶዎቻችንን እናሳውቃችሁ!የቅዳሜ ጨዋታችን፤ ከቀኑ 7:00 ሲሆን በሟሟሻ ይጀመራል፡፡በመቀጠል፤ እሸቴ አሰፋ በመቆያ መሰናዶው፤ ስለ ...
#የቅዳሜ_ጨዋታ የነገ ሕዳር 1፣2016 የቅዳሜ ጨዋታ መሰናዶዎቻችንን እናሳውቃችሁ!የቅዳሜ ጨዋታችን፤ ከቀኑ 7:00 ሲሆን በሟሟሻ ይጀመራል፡፡በመቀጠል፤ እሸቴ አሰፋ በመቆያ መሰናዶው፤ የፍልስ...
#የቅዳሜ_ጨዋታ ነገ ጥቅምት 24፣2016 ከሰዓት በኋላ ከሸገር ጋር ከሆናችሁ እነዚህን የቅዳሜ ጨዋታ መሰናዶዎቻችንን ታደምጣላቹ፡፡ ከቀኑ 7:00 ሲሆን የቅዳሜ ጨዋታችን፤ በሟሟሻ ይጀመራል፡፡...
መስከረም 10፣2016በጋምቤላ ክልል በወንዞች ሙላት ምክንያት እስከ አሁን 25 ሺህ ሰዎች ከመኖሪያ መፈናቀላቸው ተነገረ።የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ለእነዚሁ ተፈናቃዮች የሚሆን ም...
የጨዋታ እንግዳ መዓዛ ብሩ ከአዲስ አበባ የፅዳት ሰራተኞች ጋር ያደረገችው ልዩ የበዓል ጨዋታ…  ልዩ የበዓል ጨዋታ… 9፡00 ይጠብቁን... #YechewataEngida #MeazaBirru #Sh...

Category

Telephone

Address


Addis Ababa Bahirdar Road
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:00 - 00:00
Tuesday 08:00 - 00:00
Wednesday 08:00 - 00:00
Thursday 08:00 - 00:00
Friday 08:00 - 00:00
Saturday 08:00 - 01:00
Sunday 08:00 - 00:00
Other Radio Stations in Addis Ababa (show all)
HYPNOTIZED Afro FM 105.3 HYPNOTIZED Afro FM 105.3
Piazza
Addis Ababa

The official page for the Afro FM Hypnotized show Listen live on www.afro105fm.com

The Vibe Afro FM 105.3 The Vibe Afro FM 105.3
Bole
Addis Ababa

Welcome To The Official Fan Page for The ViBE(The French Hr) Afro FM 105.3 - 10am - 11am Weekdays 11

Abresh Saddam Digital entertainment Ethiopia Abresh Saddam Digital entertainment Ethiopia
Addis Ababa

Man proposise, God disposise.

Arada FM 95.1 - አራዳ ኤፍኤም 95.1 Arada FM 95.1 - አራዳ ኤፍኤም 95.1
Kazanchis, Bloom Tower Building, 4th Floor, Addis Abeba
Addis Ababa

This is the official page of AradaFm 95.1 Infotainment Radio station.

Awal show Awal show
Addis Ababa

Like tuqi

Hodan Media Hodan Media
Hodan@gmail. Com
Addis Ababa

ከሀ እስከ ፐ  Ke Ha Eske Pe ከሀ እስከ ፐ Ke Ha Eske Pe
Addis Ababa

ስፖርታዊ ክንውኖችን በቀጥታ የሚስተላልፍ ፕሮግራም

ሐበሻ ጣዕም/Habesha Taem ሐበሻ ጣዕም/Habesha Taem
Addis Ababa

ሐበሻ ጣዕም ስለ ሁሉም የሚያወራ ስለ ሁሉም የሚያነሳሳ #የመዝናኛ ,#የመረጃ ,እና, #የቁምነገር ሬዲዮ ፕሮግራም ነው