Health and medicine

this page is to provide general knowledge about health,diseases,and treatment especially drug related

16/07/2023

የኮሌራ በሽታ!!!
የኮሌራ በሽታ መተላለፊያ መንገዶች፣ የሚያሳያቸዉ ምልክቶች እና የበሽታው መከላከያ መንገዶች
ኮሌራ ከሰዉነት ዉስጥ ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችንና ፈሳሽን በብዛት እና በአጣዳፊ ሁኔታ በተደጋጋሚ ተቅማጥና ትውከት በማስከተል ሰዉነትን አድርቆ የሚገል በሽታ ነዉ፡፡
በሽታዉ የሚያሳያቸዉ ምልክቶች፡-
የሰውነት ድርቀት፣
የአፍ መድረቅ፣
የአይን መሰርጎድ፣
የእንባ መድረቅ፣
የሽንት መቀነስ፣
የቆዳ መሸብሸብና አጠቃላይ የሆነ የድካም ስሜት ያስከትላል፡፡
መተላለፊያ መንገዶች:- በአካባቢና የግል ንጽህና መጓደል አማካኝነት ነው። ማለትም:-
• በሽታው በተበከለ ምግብና ውሃ አማካኝነት ከሰው ወደ ሰው በከፍተኛ ፍጥነት ይተላለፋል፡፡
• ንጹህ ባልሆኑ እጆች ምግብን በማዘጋጀት፣ በማቅረብና በመመገብ፣
• በበሽታ አምጪ ተህዋስያን የተበከለ የምንጭ፣ የጉድጓድ፣ የወንዝ፣ የዝናብ፣ የቧንቧና ወዘተ ውሃን መጠቀም፣
• በበሽታ አምጪ ተህዋስያን የተበከለ የውሃ ማጠራቀሚያና መገልገያ እቃዎችን በመጠቀም፣
• ክዳን የሌላቸውና ለዝንቦች የተጋለጡ የምግብ ማስቀመጫና መመገቢያ እቃዎችን በመጠቀም፣
• በበሽታ አምጪ ተህዋስያን የተበከሉ ምግቦችን፣ አትክልቶችንና ፍራፍሬዎችን በመመገብ፤ወዘተ ይተላለፋል፡

የኮሌራ በሽታ መከላከያ መንገዶች:-
• ሁልጊዜ ውሃን አፍልቶ እና አቀዝቅዞ መጠጣት ወይም በውሃ ማከሚያ ኬሚካል የታከመ ውሃ መጠቀም፤
• ምግብን በሚገባ አብስሎ በትኩስነቱ መመገብ፤
• የምግብ እቃዎችን በንጹህ ወይም በኬሚካል በታከመ ውሃ ማጠብ እና መጠቀም፣
• መጸዳጃ ቤትን አዘጋጅቶ በአግባቡ መጠቀም፤
• እጅን በሚከተሉት ወሳኝ ጊዜያት በንጹህ ውሃና በሳሙና ሳሙና ከሌለ በአመድ በሚገባ መታጠብ፣
• ከመጸዳጃ ቤት መልስ፣
• ምግብ ከማዘጋጀት በፊት
• ምግብ ከማቅረብ በፊት፣
• ምግብ ከመመገብ በፊት፣
• ሕጻናትን ካጸዳዱ በኃላ፣
• ሕጻናትን ጡት ከማጥባት በፊት ፣
• በበሽታው ለተያዙ ሰዎች እንክብካቤ ካደረጉ በኃላ፣
• በበሽታው የሞቱ ሰዎችን አስክሬን በድንገት ከነኩ፣
• ማንኛውንም ከቤት የሚወጣ ደረቅ ወይም ፈሳሽ ቆሻሻን ውሃንና አካባቢን እንዳይበክል በአግባቡ በተመደበለት ስፍራ ማስወገድ፣
• በኮሌራ በሽታ የታመመን ሰው ልብስ በፈላ ውሃ መቀቀል ወይም በበረኪናና በልብስ ማጽጃ ሳሙና ዘፍዝፎ ማጠብ፣
• በበሽታው የተያዘን ሰው በፍጥነት ወደ ሕክምና ተቋም በመዉሰ የህክምና እርዳታ እንዲያገኝ ማድረግ ናቸው።
• የግልና የአካባቢን ንጽህና በመጠበቅ ዝንቦች እንዳይራቡ ያድርጉ፣
• ፈሳሽና ደረቅ ቆሻሻን በአግባቡ በተመደበለት ስፍራ ያስወግዱ
• ሽንት ቤት በመገንባት በአግባቡ ይጠቀሙ እንዲሁም በንጽህና ይያዙ፣
• በተቅማጥና ተውከት የተነካካ እቃን፣ ወለልና መሬትን ከማጽዳትዎ በፊት በረኪና በማፍሰስ ብክለትን ይከላከሉ።
የበሽታ ምልክት ሲታይ መከናወን ያለባቸው ተግባራት:-
- በሽታው የሰውነትን ፈሣሽና ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን በብዛት ከሰውነት የሚያስወጣ ስለሆነ የሚከተሉትን እርምጃዎች በፍጥነት በመውሰድ እንዲተኩ ያድርጉ።
-በመጀመሪያ ቤት ውስጥ የሚገኘውን ማንኛውም ንጽህናው የተጠበቀ ፈሣሽ የሚችሉትን ያህል ይጠጡ።
-ህይወት አድን ንጥረ ነገር ወይም ኦ.አር.ኤስ በቤት ውስጥ ካለ አንድ ፓኬት ተፈልቶ በቀዘቀዘ አንድ ሊትር ውሃ በመበጥበጥ ይጠጡ፤ የተበጠበጠ ኦ.አር.ኤስን መጠቀም የሚቻለው በተበጠበጠ በ24 ሰዓት ውስጥ ነው።
- ኦ.አር.ኤስ በቤት ውስጥ ከሌለ 8 የሻይ ማንኪያ ስኳር እና ግማሽ የሻይ ማንኪያ ጨው በአንድ ሊትር ንጹህ ውሃ በመበጥበጥ ባስቀመጥዎ ቁጥር ይጠጡ።

06/07/2023

አስም ምንድን ነው?
አስም በመተንፈሻ አካላት (የአየር መተላለፊ ቱቦዎች) ጊዜያዊ እብጠት ወይም መጥበብ የሚመጣ ህመም ነው።
በሁሉም የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሰዎችን የሚያጠቃ የተለመደ በሽታ ነው ÷ ነገር ግን ብዙውን ጊዜ በልጅነት ይጀምራል::
የአስም በሽታ ተጋላጭነቶች እና የአደጋ ምክንያቶች
• ለአለርጂ የመጋለጥ ዝንባሌ (የአበባ ብናኝ ÷ አቧራ ÷ የቤት እንስሳት ፀጉር)÷
• የመተንፈሻ ቱቦ መቆጣት (በጭስ ÷ በጠንካራ ሽታ)÷
• የአየር ብክለት÷
• የመተንፈሻ አካላት ኢንፌክሽን÷
• ከፍተኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ÷
• ትምባሆ÷
• ከመጠን ያለፈ ውፍረት÷
• አመጋገብ÷
• ቀዝቃዛ አየር ÷
• ጭንቀት÷
• መድሃኒቶች÷
• የሙያ መጋለጥ÷
• የሆርሞን ለውጦች::
የአስም በሽታ ዋና ዋና ምልክቶች:- በሚተነፍስበት ጊዜ የሚያፏጭ ድምፅ(Wheeze)፣ የትንፋሽ ማጠር /ለመተንፈስ መቸገር ፣ ማሳል፡- ብዙ ጊዜ በሌሊት ወይም በማለዳ ይባባሳል፣ የደረት መጨናነቅ(Chest thightness)፣ የድካም ስሜት፣ በፍጥነት መተንፈስ፣ በአተነፋፈስ ችግር ምክንያት መጨነቅ ወይም መደናገጥ፣ ማስነጠስ፣ የአፍንጫ ፍሳሽ እና የአይን ማሳከክ
ወዘተ....
• አስም እንዳለብዎ ከተጠራጠሩ ለትክክለኛ ምርመራ እና የሕክምና አማራጮች የጤና ባለሙያ ማማከር ይኖርብዎታል::
የአስም በሽታ ምርመራ:-
• የሕክምና/የህመም ታሪክ ማዎቅ ፣
• የአካል ምርመራ ማድረግ፣
• የሳንባ ተግባር ምርመራዎች (Spirometry) ፣
• አንዳንድ ጊዜ የአለርጂ ምርመራ።
የአስም ሕክምና
አጋላጭ የሆኑትን/አስምን የሚቀሰቅሱ ነገሮችን መቀነስ ወይም ማስወገድ::
1.1 ራስን ከአለርጂ መጠበቅ/መከላከል
- ቀስቃሾችን መለየት እና ማስወገድ የአስም ምልክቶችን ለመከላከል ይረዳል ፡- የተለመዱ ቀስቃሾች የአበባ ብናኝ፣ አቧራ፣ የቤት እንስሳት ብናኝ፣ ሻጋታ እና አንዳንድ ምግቦችን ያካትታል።
1.2 የአኗኗር ዘይቤን ማሻሻል፡-
1.2.1 መደበኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፡- የአስም በሽታ ያለባቸውን ሰዎች የሳንባ አሰራርና አጠቃላይ የአካል ብቃት ደረጃን ያሻሽላል።
1.2.2 ጤናማ አመጋገብ፡-በፍራፍሬ፣ አትክልት ፕሮቲን... የበለፀገ የተመጣጠነ አመጋገብ አጠቃላይ ጤናን ሊያስተካክል እና የአየር መተላለፊ ቱቦ እብጠትን ሊቀንስ ይችላል።
1.2.3 የበዛ ጭንቀትን ማስወገድ
[ ] አስፈላጊ ሲሆን ደግሞ መድኃኒቶችን መጠቀም።
የአስም መድሐኒቶች:
1. የጠበበ የመተንፈሻ ቱቦን የሚያሰፉ (Reliever) መድሃኒቶች :-የመተንፈሻ ቱቦ ጡንቻን የሚያዝናኑ እና ለድንገተኛ ምልክቶች ፈጣን እፎይታ የሚሰጡ;
1.1. β2-agonists
• Salbutamol(Albuterol) ብዙ ጊዜ የምንጠቀመው::
• Salmeterol÷ formoterol÷Indacaterol...
1.2. Anticholinergics ÷Theophylline
2. ተቆጣጣሪ መድሃኒቶች(Controllers):- እብጠትን ወይም /መቆጣትን የሚያክሙ;
2.1.Corticosteroids
• በአፍ የሚነፉ:-Beclomethasone....
• በደም ስር የሚሰጡ:-Hydrocortisone...
• በአፍ የሚዋጡ:- predinson/lone...
• ጡንቻ ላይ የሚዎጉ:-
2.2.Leukotriene Modifiers:
• Montelukast
• Zafirlukast......
[ ] የአስም ግላዊ የህክምና እቅድ ማዘጋጀት፡-
• የእርስዎን ልዩ ፍላጎቶች የሚያሟላ እና ጥሩ የአስም መቆጣጠርን ለማግኘት የሚረዳ ግላዊ የህክምና እቅድ ማዘጋጀት÷
• ይህም በጤና ባለሙያዎ አጋዥነት ስለ መድሃኒት አጠቃቀም፣ ስለ ምልክቶችን ማወቅ(የቀን÷የማታ÷በሳምንት ውስጥ) እና ስለ የድንገተኛ ህክምና መመሪያዎችን ያካትታል።
የአስም ህክምና ዓላማ:-
• በቀን የሚከሰት የምልክት ድግግሞሽን በሳምንት ሁለትና ከዚያ በታች ማድረግ÷
• በወር ውስጥ ሌሊት ላይ የሚከሰት ህመምን ሁለትና ከዚያ በታች ማድረግ÷
• የማስታገሻ(Reliever) መድሃኒት አጠቃቀምን በሳምንት ሁለትና ከዚያ በታች ማድረግ÷
• በአመት ከአንድ ጊዜ ያልበለጠ አጣዳፊ ህመም መከሰት÷
• የሳንባ አሰራርን ማሻሻል÷
• የተለመዱ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎችን ያለምንም ችግር ማከናወን÷
• በትንሹ ወይም ምንም የጎንዮሽ ጉዳት ሳይኖር በአስም ህክምና መደሰት÷
ስለ አስም ህክምና የተሳሳቱ ግንዛቤዎች
1.አልሜታሚን (Almetamine ) ያክመዋል ብሎ ማሰብ፣
2. ምስር የምታክል ሮዝ/ነጭ ታብሌት መድሃኒት (Predinsolone) ያለ ሃኪም ትዛዝ ለረጅም ጊዜ መውሰድ በዚህም ለጎንዮሽ ጉዳት መጋለጥ፣
3.በአፍ የሚነፉ መድሃኒቶች (puffs) ይለምድብኛል ብሎ አለመውሰድ፣
4.የሚነፋ መድሃኒትን በትክክል ወደ የአየር መተላለፊ ቱቦዎች ከትንፋሽ ጋር ከማስገባት ይልቅ መዋጥ(...የቴክኒክ ችግር)÷
5.የሚነፋ መድሃኒትን ከወሰዱ በሗላ አፍን አለመታጠብ::

• በትክክለኛ አያያዝና የሕክምና ዕቅዶችን በመተግበር ፣አብዛኞቹ አስም ያለባቸው ሰዎች ያለአንዳች ገደብ መደበኛ ህይወት መምራት ይችላሉ።

30/06/2023

ሾተላይ (Rh-isoimmunization)

💥 ሾተላይ የሚባለው በሽታ ከሁለተኛ ጀምሮ የሚወለዱ ህፃናትን የሚያጠቃ በሽታ ሲሆን ይህም በእናትና በፅንሱ መሀከል የደም አይነት አለመጣጣም(Rh incompatability) ምክንያት የሚከሰት ነው።

💥 ሾተላይ የሚከሰተዉ የሴቲቱ የደም አይነት Rh negative ፣ የባል የደም አይነት Rh positive እና የፅንሱ ደግሞ Rh positive ከሆነ ሲሆን በተጨማሪም በተለያዩ ምክንያቶች Rh positive ደም ወደ ሴቲቱ ደም ከገባ ወይም ከወሰደች ነው።

ነጥብ

💥 ሚስት Rh negative መሆን ይኖርባታል እና ፅንሱ Rh positive መሆን ይኖርበታል
💥 ባል Rh negative ከሆነ ሾተላይ አይከሰትም

🌟 ሾተላይ ለምን ይከሰታል?

👉 የሰው ልጅ ከወላጆቹ ዘረመል ተነስቶ ከ4 የደም አይነቶች ውስጥ አንዱን ሊይዝ ይችላል። እነኝህም
1. “A”
2. “B”
3. “AB”
4. “O” ተብለው ይጠራሉ።

👉 በሰውነት ውስጥ የሚገኙ ቀይ የደም ህዋሶች(RBCs) የላይኛው ሽፋናቸው ላይ Rh የተባለ ፕሮቲን (protein) ካላቸው ሴቲቱ Rh positive ናት ማለት ሲሆን እነኚህ ፕሮቲኖች ከሌሉ ደግሞ Rh negative ናት ማለት ነው።

ለምሳሌ:- ሴቲቱ የደም አይነቷ B ቢሆንና ቀይ የደም ሴሎቿ ላይ Rh ፕሮቲን ካለ B Positive ናት ማለት ነው፤ እነኚህ Rh ፕሮቲኖች ከሌሉ ደግሞ B Negative ናት ይባላል።

👉 አንዲት ሴት ሾተላይ የሚባለው ችግር ሊከሰትባት የሚችለው እሷ Rh negative ሆና በተለያዩ አጋጣሚዎች Rh positive የሆነ ደም ወደሰውነቷ ሲገባ ሰውነቷ እነኚህን Rh positive የደም አይነቶች የሚያጠፉ(የሚገሉ) ንጥረ ነገሮች (Antibodies) ሲያመነጭ (ሲያመርት) ነው። እነኚህም እስከ እድሜልክ በሰውነቷ ይቆያሉ።

👉 እነኚህ የተመረቱት ተከላካይ ንጥረ ነገሮች(Antibodies) የመጀመሪያው ልጅ ላይ ምንም ተፅዓኖ ሳይኖራቸው ልጁ በሰላም ሊወለድ ይችላል ነገር ግን የሁለተኛው ፅንስ የደም አይነቱ Rh positive ከሆነ ወደ ፅንሱ በማለፍ የፅንሱን Rh positive የቀይ የደም ህዋሶች ያጠቃሉ ማለት ነው፤ ይህም ፅንሱን ለተለያየ አደጋዎች ሊያጋልጠው ይችላል።

👉 ይህም ችግር ፅንሱ ላይ የተለያዩ ጉዳቶችን ሊያመጣ ይችላል ፤ እነኚህም

☘️ በፅንሱ የተለያዩ የአካል ክፍሎች ውሀ መቋጠር - Fetal hydrops
☘️ በተደጋጋሚ የፅንስ መውረድ - Miscarriage
☘️ የፅንሱ የደም ማነስ - Fetal anemia
☘️ ፅንሱ በማህፀን ውስጥ እንዳለ ጊዜው ሳይደርስ ህይወቱ ማለፍ
☘️ ህፃኑ ከተወለደ በውሃላ ቆዳው ቢጫ መሆን እና የጨረር ህክምና ማስፈለግ(phototherapy)
☘️ በከፍተኛ ደም ማነስ ምክንያት ደም ለመውሰድ መጋለጥ

🌟 ሾተላይ እንዴት ይታከማል?

👉 Rh negative የሆነችው እናት ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩት ነገሮች ከገጠሟት
☘️ ባለቤቷ Rh positive ከሆነ
☘️ ውርጃ ካጋጠማት
☘️ ከማህፀን ውጭ እርግዝና ካጋጠማት
☘️ ከእንግዴ ልጅ ላይ የሚነሳ እጢ(Gestation trophoblastic disease) ካጋጠማት
☘️ በእርግዝና ወቅት አደጋ ከደረሰባት፤
☘️ በክትትል ወቅት ከእንግዴ ልጅ ወይም ከሽርት ዉሃ በመሳሪያ ናሙና ከተወሰደ

👉👉 Anti D የተባለ ኢሚውኖግሎቡሊን (immunoglobulin) መድሀኒት በመውሰድ ሾተላይን መከላከል ይቻላል።

💥☘️ በእርግዝና ጊዜ Anti D የተባለውን መድሃኒትን በ 7 ወር(28 ሳምንት) ላይ እና ህፃኑ በተወለደ ቢቻል እስከ 72 ሰዓት ውስጥ በመስጠት የሾተላይ በሽታን መከላከል ይቻላል።

👉 Rh negative የሆነች እናት(ባል Rh positive) የእርግዝና ክትትሏ ከሌሎች እናቶች ለየት ያለ እና የሚሰጣትም ቀጠሮ በዛ ያለ ይሆናል።

👉 ይህም በልጇ ላይ ሊከሰቱ የሚችሉትን የሰውነት ውሀ መቋጠር(መጠራቀም) እና የፅንሱ ደም ማነስ ካለ ቀድሞ በማወቅ ህክምናውን በቶሎ ዘመኑ በደረሰበት ቴክኖሎጂ እዛው ማህፀን ውስጥ እንዳለ ደም በመለገስ እና ወቶ ለመኖር ብቁ በሆነበት ጊዜ ቀድሞ እንዲወለድ በማድረግ ተጨማሪ የሆኑ የህክምና እርዳታዎች እንዲደረግለት ማድረግ ይቻላል።

Photos from Health and medicine's post 04/11/2022

⚽️⚽️⚽️⚽️⚽️ሄፓታይተስ ኤ⚽️⚽️⚽️⚽️

🍇 ሄፓታይተስ ኤ የምንለው ምግብ ወለድ በሽታ ከምላቸው ውስጥ አንደኛው እና ተጠቃሽ ነው፡፡
🍇 ሄፓታይተስ ኤ ያለምንም የበሽታ ምልክት ከ 15-45 በአማካይ እስከ 30 ቀን በሰውነት ውስጥ ሊቆይ ይችላል በተጨማሪም ቫይረሱ በሰገራ ከሰውነት ይወገዳል፡፡
🍇አጣዳፊ ምንለው ሄፓታይተስ ኤ በሽታ ህጻናት ላይ በተደጋጋሚ የሚከሰት እና አብዛኛውን ጊዜ የህመም ምልከት የማይኖረው ሲሆን አዋቂዎች ላይ ግን ከባድ የህመም ምልክት ሊታይ ይችላል ከህጻናት ጋር ሲነጻጸር የመግደል አቅሙ ከፍ ያለ ነው፡

⚽️⚽️⚽️⚽️መንስኤዎቹ ⚽️⚽️⚽️⚽️

🍇​አብዛኛውን ጊዜ ዋና መነሻ ተደርጎ ሚወሰደው የምግብ እና መጠጥ ንጽህና ጉድለት ሲሆን ይሄንንም በምንመገብበት ጊዜ ከበሽተኛው ቫይረሱ ወደ እኛ ሰውነት ይገባል ( faeco-oral route)በቫይረሱ ​የተጠቁ ሰዎች የጥንቃቄ ጉድለት የሚያዘጋጁትን ምግቦች መመገብ
​በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ጋር የሚኖር ልቅ የሆነ የግብረ-ስጋ ግንኙነት​፣የተበከለ የ መጠጥ ውሃ
🍇 አንድ በበሽታው የተጠቃ ሰው ምንም አይነት የበሽታ ምልክት ባያሳይም እስከ 2 ሳምንት ድረስ በሽታውን ወደሌሎች ያስተላልፋል ነገር ግን የበሽታውን ምልክት ባሳየ በሳምንት ጊዜ ውስጥ ወደሰዎች የማስተላለፍ እድሉ ዝቅተኛ ነው::

⚽️⚽️⚽️⚽️ ተጋለጭ የሆኑት የህብረተሰብ ክፍሎች ⚽️⚽️⚽️⚽️

🍇​ማንኛውም የሽታ መከላከል አቅሙ የደከመ ሰው
🍇​መኖሪያ ቤት የሌላቸው እና በተጨናነቀ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ሰዎች
🍇​የፍቅር ወይም የትዳር አጋር በበሽታው ከተጠ
🍇​የ ሄፓታይተስ ኤ ስርጭት ከፍተኛ የሆነባቸው ሀገራት ወይም አካባቢዎች ላይ ጉዞ ታሪክ ያላቸው ሰዎች
🍇​ግብረሰዶማውያን (homo-sexual)
🍇​ህጻናት ማሳደጊያ ላይ ያሉ ህጻናት
🍇 ​ያልበሰሉ ምግቦችን መመገብ

⚽️⚽️⚽️⚽️ምልክቶቹ ምድናቸው⚽️⚽️⚽️⚽️

አንድ በዚህ በሽታ የተያዘ ሰው ከ15 ቀን እስከ 30 ቀን ባለው ጊዜ ውስጥ እነዚህን የበሽታውን ምልክቶች ያሳያሉ
🍇​ከፍተኛ የሆነ ድካም ስሜት
🍇​የምግብ ፍላጎት መቀነስ
🍇​የጡንቻ ህመም
🍇​ማቅለሽለሽ እና ትውከት
🍇​መጠነኛ ትኩሳት
በሽታው ከተከሰተ ከብዙ ቀናት በኋላ አንዳንድ የጉበት በሽታ ምልክቶች መታየት ይጀምራ
🍇​የሽንት መጥቆር
🍇​የሰገራ መንጣት
🍇​ቢጫ ቆዳ( jaundice ) ይሄ ከ 6 አመት በታች ያሉ ህጻናት ላይ ብዙ አይከሰም
🍇​ነጩ የአይን ክፍል ወደ ቢጫ መቀየር
🍇​የላይኛው ሆድ ክፍል ላይ የሚኖር ህመም
🍇​ቆዳን ማሳከክ
ሌላው ህጻናት ከሆኑ
🍇​ብርድ ብርድ ማለት፣ ​ሳል፣ ​የጉሮሮ ህመም ሊኖር ይችላል

⚽️⚽️⚽️⚽️የሚስከትለው ጦስ⚽️⚽️⚽️⚽️

🍇አብዛኛውን ጊዜ በራሱ ጊዜ የሚድን ቢሆንም አንዳንድ ጊዜ ግን የጉበት መጎዳት ያመጣል (liver failure) አዋቂዎች ላይ እድሜአቸው ከ 50 አመት በላይ የሆኑት ላይ ሌላ አይነት የጉበት በሽታ ሊስከትል ይችላል፡፡
🍇ስኳር ታማሚዎች፣ ደም ማነስ ያለባቸው እና የልብ ድካም ታማሚዎች ከበሽታው በቶሎ ማገገም አይችሉም፡፡

⚽️⚽️⚽️⚽️እንዴት ይመረመራል⚽️⚽️⚽️⚽️

🍇​የጤና ባለሞያው የኋላ ታሪክ በመውሰድ አጋላጭ ምክንያቶችን በመለየት
🍇​የደም ምርመራ ጉበት ያለበትን የጤና ሁኔታ ለማወቅ ያግዛል
🍇​Antibody test for Hepatitis C and B ታማሚው እነዚህ ምርመራዎች ተሰርተውለት ነጻ ከሆነ ሊሆን የሚችለው ሄፓታይተስ ኤ ወይም ሄፓታይተስ ኢ እነዚህ ደግሞ በራሳቸው የሚድኑ ናቸው፡

⚽️⚽️⚽️⚽️ህክምናው⚽️⚽️⚽️⚽️

እራሱን የቻለ ይህ ተብሎ የተዘጋጀ መድሃኒት የለውም ነገር ግን ህመሙን እና ሌሎች ተያያዥ ቀውሶችን ለመቀነስ የሚሰጡ ህክምናዎች አሉ
🍇​የፈሳሽ መጠኑን ማስተካከል
🍇​አልኮል እንዲያቆም ማድረግ
🍇​እረፍት እንዲያደርግ መምከር
🍇​የህመም ማስታገሻዎችን አንዲጠቀሙ ይመከራል
🍇​በሽተኛው ከፍተኛ የሆነ ማስመለስ እና ማቅሽለሽ ካለ አልጋ ይዞ እንዲታከም ሊደረግ ይችላል።

⚽️⚽️⚽️⚽️ክትባት (vaccine)⚽️⚽️⚽️⚽️

ሄፓታይተስ ኤ የራሱ የሆነ ክትባት አለው ምን አይነት ሰዎች ይሄን ክትባት እንዲወስዱ ይመከራል
🍇​እድሜአቸው ከ 1 አመት በታች የሆኑ ህጻናት
🍇​የበሽታው ስርጭት በብዛት የሚስተዋልባቸው ሀገራት እና ካቢዎች የሚጓዙ ሰዎች
🍇​ግብረሰዶም የሚፈጽሙ ሰዎች
🍇​ደስታን የሚሠጡ መድሃኒቶችን በመርፌ የሚጠቀሙ
🍇​ቤት አልባ የሆኑ እና ኑሮአቸውን ጎዳ ላይ ያደረጉ ሰዎች
🍇​ስር የሰደደ የጉበት በሽታ ላለባቸው ሰዎች ከ ሄፓታይተስ ኤ ውጪ ለምሳሌ ሄፓታይተስ ሲ ወይም ሄፓታይተስ ቢ
🍇​የደም መርጋት ችግር ያለባቸው ሰዎች ምክንያቱም ጉበት ለደም መርጋት የሚገለግሉ ነገሮችን ያዘጋጃል።

Telegram: Contact @HakimEthio 26/10/2022

Iron በእርግዝና ጊዜ
በዶ/ር ዳዊት መስፍን፤ የማህፀንና ፅንስ ስኜሻሊስት

✍️ አንድ በእርግዝና ወቅት ላይ ያለች ሴት 1 ግራም Iron ለመላ የእርግዝና ጊዜዋ ያስፈልጋታል።

📌 500ሚ.ግ - ቀይ የደም ህዋሶችሽን ለመጨመር
📌 300ሚ.ግ - ወደ ህፃንሽ የሚሄድ
📌 200ሚ.ግ - በተለያየ ምክንያት ከሰውነትሽ ለምታጪው Iron የሚተካ ይሆናል

✍️ 💊 ስለዚህ በእርግዝናሽ ጊዜ ከ 30-60 ሚ.ግ elemental Iron በቀን ያስፈልግሻል ማለት ነው።

✍️ ብዙውን ጊዜ በእርግዝናሽ ሰዓት የሚከሰተው የደም ማነስ ከIron እጥረት የመጣ ሲሆን እሱም Iron deficiency Anemia እንለዋለን።

✍️ እሱም የሚታወቀው የደም መጠንሽን የሚለካው Hgb (Hemoglobin) የተባለው ቀይ የደም ህዋስሽ ላይ የሚገኝ መጠኑ ከ 10gm% በታች ሲሆን ነው።

✍️ ስለዚህ በመጀመሪያው እንዲሁም በሁለተኛው የቅድመ ወሊድ ክትትል ሂደትሽ ላይ የሚሠጡሽን ሠላሳ ሠላሳ የIron እንክብሎች (Tablets) ,አንድም ሳታስቀሪ ተጠቀሚ ።

👌🤰🏻ላንቺ የሚሰጠው ጥቅም

- ከእርግዝና ጋር ተያይዞ ለሚመጣ የደም ማነስ ለመከላከል
- የሰውነትሽን የIron መጠን ለመጨመር

👌👼 ለፅንሱ የሚሰጠው ጥቅም

- የደም ማነስን ይከላከላል
- በቂ የ ኦክስጅን አቅርቦት ይጨምራል
- ለፅንሱ የጭንቅላት እድገት ጠቃሚ ነው

💊አወሳሰድ💊

✍️ Iron Tablets በባዶ ሆድ ቢወሰድ ወደ ደምሽ የሚገባው የIron መጠን ከፍተኛ ይሆናል ።

✍️ ነገር ግን የማቅለሽለሽ እንዲሁም ጨጓራሽን የማቃጠል ስሜት ካለሽ ምግብ ከተመገብሽ በኋላ ብትወስጅው መጠኑ ይቀንስ እንጂ ጥቅሙ እጅጉን የላቀ ነው።

✍️ ከፍተኛ የሆነ ማቅለሽለሽ እና ማስታወክ ካለ እንክብሉ(Tablet) ወደ ሽሮፕ(Syrup) ሊቀየር ይችላል።

⚠️⚠️ሳልወስድ ብተወው ካልሽ የሚከሰቱ ጉዳቶች⚠️⚠️

🩸በእርግዝና ጊዜ የደም ማነስ (ላንቺም ለፅንሱም)
🩸በቂ የIron መጠን ስላሌለሽ ከወሊድ በኋላ የደም ማነስ በተለይ በወሊድ ጊዜ ደም ከፈሰሰ
🩸 የደም ማነሱ መጠኑ በጣም ከፍተኛ ከሆነ ደግሞ የልብ ድካምን(Cardiac Failure) ሊያስከትልብሽ ይችላል።

Telegram: Contact @HakimEthio

Photos from Health and medicine's post 19/10/2022

Constpiton(የሆድ ድርቀት) "የምንለው የሰገራ(f***s) የሚይዘው የ ፈሳሽ መጠን መቀነስ እና ከመጠን ያለፈ የሰገራ ድርቀት አና በቀላሉ ለመፀዳዳት መቸገር ማለት ነው በተለምዶ የሆድ መድረቅ እንለዋለን በተጨማሪም ይሄ የገጠማቸው ሰዎች የተለያዩ ምልክቶች ይኖራቸዋል
1.የሆድ ህምም(abdominal pain)
2.የሆድ መነፋት (bloating)
3.ተፀዳድተው እንደጨረሱ ያለመረዳት ስሜት (loss of filling to complete f***s)
የሚያስከትለው ችግር (complications)
1.የፊንጢጣ ኪንታሮት (hemorrhoids)
2.የፊንጢጣ መሰንጠቅ(anal fissure)
3. ሬብ (re**um) ላይ ከፍተኛ የሆነ የሰገራ ክምችት መኖር (f***l impaction) ይሄም ከፍየኛ ህመም ስሜት ይፈጥራል
አንድ ጤነኛ ሰው በቀን ሶስት ጊዜ እስከ በሳምንት ሶስት ጊዜ መፀዳዳት መቻል አለበት ተብሎ ይታሰባል።

የሆድ ድርቀት አይነቶች (Types of Constipation)

1. አጣዳፊ የሆድ ድርቀት (acute constipation) ስሙ እንደሚያመለክተው በድንገት የሚከሰት ሲሆን መንስኤውን በማወቅ አፋጣኝ የሆነ ህክምና እርዳታ መስጠት ያስፈልጋል። ሳይኮሶማቲክ የሆድ ድርቀት (psychosomatic constipation) ብዙውን ጊዜ ከፍተኛ የሆነ ጭንቀት በሚኖር ሰአት ይከሰታል ለምሳሌ ከፍተኛ የስራ ጫና ሲኖር ወይም ጉዞ ላይ ወዘተ. የተከሰተበት ምክንያት ከታወቀ ይታከማል።

ሃይፖቶኒክ የሆድ ድርቀት፡ ሥር የሰደደ የሆድ ድርቀት(chronic type of constipation) ነው እንዲህ ዓይነቱ የሆድ ድርቀት የሚከሰተው የሆድ ጡንቻዎች መጠንከር አለመቻል ሲሆን በዚህም ምክንያት የ አንጀት ጡንቻዎች በትክክል ለመሥራት ይቸገራሉ (muscles are too weak to work properly in the intestines.)በተለመደው መልኩ መፀዳዳት አለመቻል እንዲኖር ያደርጋል በዚህም ከፍተኛ መጠን ያለው የሰገራ መጠራቀም(unable to defecate normally) እንዲኖር ያደርጋል። በአመጋገብ ውስጥ በቂ ፋይበር አለመኖሩ እና በቂ ውሃ ባለመኖሩ ምክንያት ሊከሰት ይችላል።

ስፓስቲክ ኮንስትፔሽን(Spastic constipation): ከላይ ከጠቀስነው በተቃራኒ የሚከሰት ሲሆን ከፍተኛ የሆነ የጡንቻ መኮማተር (muscle spasm) ምክንያት ይከሰታል በዚህም ከፍተኛ የሆነ ሆድ ቁርጠት እና ህምም ይኖራል ነገር ግን የሰገራ መጥን አይቀንስም እና የሰገራ መውጣት (defecation) ላይ ችግር አይኖርም ::

ሬክታል ኮንስትፔሽን (re**al constipation ):አንድ ሰው በተደጋጋሚ የሰገራ መምጣት ስሜት እያለው ዝም ማለት ወይም ስሜቱን ተቀብሎ አለመፀዳዳት ሲኖር እና ሲደጋገም ሰውነታችን ለአእምሮ መልክት ማስተላለፍ ሲያቆም ወይም ሲቀንስ ይከሰታል በዚህም bowel movement ይቀንሳል አንጀት ላይ የተጠራቀመ ሰገራ የያዘወን የርጥበት መጠን እየቀነሰ ሰገራ እየደረቀ ይምጣል በዚህም ሆድ ድርቀት ይከሰታል።

Risk factors (አጋላጭ ምክንያቶች)

The American Academy of Family Physicians mentions these risk factors:

• አትክልት እና ፍራፍሬ አለመጠቀም

• የምንወስደው የፍሳሽ መጠን ዝቅተኛ መሆን

• በቂ የሆነ እንቅስቃሴ አለማድረግ

• የመፀዳዳት ስሜትን ተቀብሎ አለመፀዳዳት

• አንዳንድ መድሃኒቶች opoids የሚባሉ የህመም ማስታገሻዎች ሱስ ስለሚያመጡ በተደጋጋሚ መጠቀም በነዚህ መድሃኒቶች የሚመጣውን ድርቀት ለማስቆም ግዴታ መድሃኒቶቹን ማቆም ይመከራል

• አንዳንድ በሽታዎች ወይም ሁኔታዎች ለምሳሌ የስኳር በሽታ፣lupus (የራሳችን የበሽታ መከላከያ መንገድ የራሳችንን የተለያዩ የሰውነት ክፍሎቻችንን የሚያጠቃ በሽታ ነው) ወይም multiple sclerosis (አእምሮን እና ሰረሰርጌ አንጎልን የነርቭ ሽፋኖች የሚያጠቃ በሽታ ነው)

Causes of Constipation (መንስኤዎች)

The most common cause is an irregular intake of food, especially junk food.ዋነኛ መንስኤ ተደርጎ የሚወሰደው ያልተስተካከለ የአመጋገብ ስርአት መኖር በተለይ ምንም አይነት የንጥረነገር ጥቅም የሌላቸው ምግቦችን(junk food) መመገብ ዋነኛ መንስኤ ተደርጎ ይወሰዳል

• በቂ የሆነ እንቅስቃሴ አለማድረግ

• ለረጅም ሰአት መቀመጥ የሚያበዙ ከሆነ ከስራ ጋር ተያይዞም ሆነ በሌላ ምክንያት

• ማጨስ፣ መቃም እና አልኮል መጠቀም

• በቂ የሆነ እንቅልፍ አለማግኘት

• የምንወስደው የፈሳሽ መጠን መቀነስ

• ጉዞ ለረጅም ሰአት መጓዝ

• እርግዝና

Symptoms (ምልክቶቹ)

• አልፎ አልፎ መፀዳዳት

• ማማጥ በግድ መጸዳዳት ሰገራ በቀላሉ አለመውጣት

• ጠንከሰራ እና አነስተኛ ሰገራ መኖር

• ተፀዳድተው ከጨረሱም በኋላ ያለመጨረስ ስሜት ይኖራል በዚህም መፀዳጃ ቤት መመላለስ ይኖራል

• የታችኛው የሆድ ክፍላችን ላይ ምቾት አለመሰማት

• የሆድ መነፋት እና መወጠር ሊያጋጥም ይችላል

• በሚፈጠረው የሰገራ መድረቅ የሚመጠሰ የፊንጢንጣ መሰንጠቅ እና መድማት ሊኖር ይችላል

• አንዳንዴም የ ወፍራም አንጀት በሰገራ ከተዘጋ አንዳንድ ጊዜ ተቅማጥ ሊከሰት ይችላል

• የመከሰት እድሉ ዝቅተኛም ቢሆን ግን የ ወፍራም አንጀት መቦርቦር ሊከሰት ይችላል

• ወደ መፀዳጃ ቤት ሲሄዱ ውጥረት ውስጥ መግባት እና መፀዳጃ ቤት የመሄድ ፍርሃት

Complications of Constipation (የሚያስከትለው ጦስ)
የሆድ ድርቀት አብዛኛውን ጊዜ አጣዳፊ እና ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ነው

አስከፊ ከሚባሉት ችግሮች ውስጥ:

• Hemorrhoids (swollen, inflamed veins in the re**um or around the a**s that may cause re**al pain and bleeding) የፊንጢጣ ኪንታሮት የምንለውን ሊያመጣ ይችላል በፊንጢጣ የሚገኘው የደም ስር ማበጥ እና መቆጣት ይሄም ከፍተኛ ህመም እና መድማት ሊያመጣ ይችላል

• A**l fissures (small tears in the skin around the a**s that are often accompanied by itchiness, pain, and bleeding) የፊንጢጣ መሰንጠቅ ማሳከክ፣ህምም እና መድማት ሊያመጣ ይችላል

• F***l impaction (inability to push stool out because it has hardened and packed in the colon and re**um too tightly)በጣም የሰገራ ከመጠን በላይ መድረቅ እና ለመፀዳዳት መቸገር

• Re**al prolapse ፊንጢጣን አልፎ ሬብ ወደ ውጪ መውጣት

Diagnosis and test (ምርመራ)

ጠቅላላ የሰውነት ምርመራ ( Digital re**al exam) የምንለው አለ ይሄም መንስኤውን ለማወቅ ይጠቅማል

የደም ምርመራ ይሄም ውስጣዊ ችግር ካለ የ ሆርሞን መዛባት ከተከሰተ በተለይ የ thyroid ሆርሞን ማነስ ጋር ተያይዞ

በተለያዪ መሳሪያዎች በመታገዝ የሚሰራ ጠቅላላ የ ወፍራም አንጀት እና የሬብ (re**um) ምርመራ

Treatment and medications (ህክምናው እና መድሃኒቶች)

ህክምናው እንደ እንደ መንስኤው ይለያያል

የተለያዩ የሆድ ማለስለሻ መድሃኒቶችን በመጠቀም(laxatives and stool softeners) የተጠራቀመውን የደረቀ ሰገራ እንዲለሰልስ እና በቀላሉ እንዲወገድ ማድረግ

አመጋገብን ማስተካከል ይሄም ፋይበር የበዛባቸው ምግቦችን መመገብ እንደ ጥራጥሬ፣ፈርራፍሬ፣ ያልተፈተጉ ምግቦችን እና አትክልት ይመከራል ነገር ግን ወተት እና የወተት ተዋፅዖዎች፣ ሩዝ፣ፉርኖ ዱቄት፣ ቀይ ስጋ መቀነስ ወይም ማቆም

ብዙ ፈሳሽ መውሰድ ይመከራል ነገር ግን ቡና አልኮል አይመከርም

በየቀኑ ለ 30 ደቂቃ አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ይመከራል

ድርቀት እንዲከሰት ምክንያት የሆኑ ነገሮችን ከመሰረቱ ማከም ( hormone replacement therapy surgery )

laxative (የ ሆድ ማለስለሻ መድሀኒትዎች)
እነዚህ መድሀኒቶች የሰገራን የውሃ መጠን እንዲጨምር በማድረግ ሰገራ እንዲለሰልስ ያደርጋሉ።
ሌሎች ደግሞ የ አንጀት ጡንቻዎች እንዲኮማተሩ በማድረግ ሰገራ በቶሎ እንዲወጣ ያግዛሉ እነዚህ ግን ሆድ ቁርጠት ሊያስከትሉ ይችላሉ።

18/10/2022

ሱስ እየሆነ የመጣው Tramadol
ዶክተር ናሆም ግሩም

ከቀናት በፊት አንድ እድሜዋ በአስራዎቹ መገባደጃ አከባቢ ሚገኝ ታካሚዬ ለመጣችበት ህመም መፍትሄ ይሆናል ብዬ ያሰብኩትን መድሃኒት ሰጥቼያት ተሰናብታኝ ልትወጣ ስትል "አንድ ነገር ላማክርህ ነው እባክህ እርዳኝ" እያለች ማልቀስ ጀመረች። ጉዳዩን በአንዴ ለማስረዳት ፍቃደኛ ባትሆንም ከስንት ግዜ ውትወታ በኋላ ችግሯን ነገረቺኝ።

Tramadol ሚባል መድኋኒት በቀን ብዙ ፍሬ እንደምትወስድ እና አሁን እሱም አልበቃ ብሏት በመርፌ ሚወጋ መውሰድ መጀመሯን፣ ይሄን መድሃኒት እሷ ብቻ ሳትሆን ብዙ ጓደኞቿ እንደሚወስዱት እና ትምህርት ቤት ውስጥ ጭምር ተዋቂ መሆኑን ጭምር አጫወተቺኝ። "መድኀኒት ቤቶች ብር ከተሰጣቸው ያለ ጤና ባለሙያ ትዕዛዝ ይሸጣሉ። አንዳንዶቹ ገና ሲያዩን ምን ፈልገን አንደመጣን ያውቃሉ" አለች።

ከዚ በፊት አንድ መኪና ማጠቢያ ቦታ ማውቀው ልጅ መኪና ውስጥ የስራ ቦታ መታወቂያዬን አይቶ ሀኪም መሆኔን ካወቀ በኋላ "እባክህ በጣም ስላመመኝ Tramadol ሚባል መድኋኒት በርከት አርገህ እዘዝልኝ" ብሎኝ ያውቃል። በኋላ በደንብ ቀርቤው ስጠይቀው መውሰድ ከጀመረ 2 አመት እንደሞለው እና ያለሱ ስራውን መስረት አንደማይችል አጫወተኝ። ማረሚያ ቤት ያሉ ታካሚዎች ህክምና ቦታ ከመጡ ብዙዎቹ ለባለሙያው "Tramadol ካልሆነ ሌላ መድሃኒት አያሽለኝም" ሲሉ ብዙ ግዜ ገጥሞኝ ያውቃል። የሌሎቹን ታሪክ ቤት ይቁጠረው!

Tramadol ለመካከለኛ እና ከበድ ላለ ህመም ሚወሰድ የህመም ማስታገሻ ሲሆን በተደጋጋሚ እና የለ አግባብ ከተወሰደ የመድሃኒቱ ሱስ ውስጥ ሊያስገባ ይችላል። በዚህም ምክንያት በተለይ እድሜያቸው በአፍላ ወጣትነት አከባቢ ሚገኝ እጅግ ብዙ ወጣቶች abuse ያረጉታል። አንዴ የዚ መድሃኒ ሱስ ውስጥ ከገቡ ሌላ ተጨማሪ መድኋኒቶች እና አደንዧዥ እፅች አብሮ የመውሰድ እድሉ ከፍ ያለ ይሆናል። ይሄ ለትውልዱም ለሀገርም ትልቅ ክስረት እና አሳሳቢ ነገር ነው።

መድሃኒቶችን ያለ በለሙያ ትዕዛዝ ሚሸጡ ሰዎች ከትውልድ ገዳይ ተግባር ማታቀብ አለባቸው። በህግም መጠየቅ አለባቸው! ጉዳዩ ሚመለከታቸው በጤናው ዛርፍ ያሉ አካላት እንደዚ አይነት መድሃኒቶች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ማረግ አለባቸው። የጤናው ባለሙያም መድኋኒቶችን ለታካሚ ሲያዝ ሀላፊነት በተሞላበት መንገድ አርጎ ሙያዊ ሀላፊነቱን መወጣት አለበት!

17/10/2022

የእንቅልፍ አተኛኘት አቅጣጫ ጥሩ እና መጥፎ ጎናቸው!

1. በጀርባቸው የሚተኙ!
✔ ጥቅሙ

በጀርባ መተኛት ትራስ አከርካሪን የመደገፍ ሥራውን በትክክል እንዲወጣ ይረዳዋል። በትክክለኛው አለም ሁሉም ሰው ትራስ ሳይጠቀም በጀርባው መተኛት ይፈልጋሉ፤ ይህም አቅጣጫ አንገታችን ነፃ አቅጣጫ ላይ እንዲሆን ይረዳዋል። ከመጠን በላይ/ ብዙ ትራስ መጠቀም የአተነፋፈስ ሥርዓትን አስቸጋሪ ያደርገዋል።

በጀርባ መተኛት ውበትን ከመጠበቅ አንፃር ይመከራል፤ ሌሊቱን ሙሉ ፊታችን ለንጽህ አየር እንዲጋለጥ በማድረግ ይረዳል። የተጠቀምነው የውበት መጠበቂያ ኮስሞቲክስ በትራሱ እንዳይጠረግ ከማድረጉ በተጨማሪ የፊት መሸብሸብን ወይም መጨማደድን ይቀንሳል።

✔ ጉዳቱ

ማንኮራፋት እና የእንቅልፍ እጦት በጀርባ ተንጋሎ ከመተኛት አቅጣጫ ጋር ይያያዛሉ። በነገራችን ላይ በጀርባ መተኛት ከእንቅልፍ እጦት ጋር በቅርበት የተገናኘ ነው ለዚህም ነው ዶክተሮች በጎን አቅጣጫ በኩል መተኛትን እንደመፍትሄ የሚመክሩት።

በጀርባችን በምንተኛበት ወቅት የመሬት ስበት ሃይል የምላሳችን ሥር ወደ አየር ቧንቧ አቅጣጫ እንዲታጠፍ ያስገድደዋል ይህም ሥርዓተ ትንፈሳን በማስተጓጎል ጎረቤትን እንቅልፍ የሚነሳ አስቀያሚ ማንኮራፋት እንዲፈጠር ያደርጋል።

ጥሩ እንቅልፍ የሚተኙ እና ጥሩ ያልሆነ እንቅልፍ የሚተኙ ሰዎችን በማነፃፀር የተደረገ ጥናት እንደሚያሳየው፦ ጥሩ ያልሆነ እንቅልፍ የሚተኙ ሰዎች አብዛኛውን የመኝታ ጊዜ የሚያሳልፉት በጀርባቸው እንደሆነ አረጋግጠዋል።

2. በጎናቸው የሚተኙ!

✔ ጥቅሙ

በጎናቸው የሚተኙ ሰዎች በአንድ ላይ! ማህፀን ውስጥ እንዳለ ጽንስ እግራቸውን እጥፍጥፍ አድርገው የሚተኙ እና እግራቸውን ዘርግተው የሚተኙ ሰዎች፤ አብዛኛው ማህበረሰብ በጎን በኩል እንደሚተኙ ሪፓርት ተደርጓል።

በእርግዝና ወቅት በግራ ጎን በኩል እንዲተኙ ዶክተሮች ይመክራሉ፤ ምክንያቱም ወደ ልብ ያለውን የደም ፍሰት ስለሚጨምር ነው ይህም ለእናት እና ልጅ እጅግ በጣም ጠቃሚ ነው። በእርግዝና ወቅት በጎን በኩል እንድትተኚ ይመከራል ምክንያቱም በጀርባ በኩል መተኛት የታችኛው ጀርባ ላይ ግፊት ይፈጥራል (በአብዛኛው ፌንት እንድታደርጊ አስተዋጽዎ ያድርጋል)። እንደሚታወቀው በእርግዝና ወቅት በሆድ በኩል መተኛት አይቻልም።

✔ ጉዳቱ

በተመሳሳይ ሁኔታ በግራ ጎን በኩል መተኛት ሆድ እና ሳንባ ላይ ጫና እንዲፈጠር ያደርጋል። ሁሉም በጎናቸው የሚተኙ ሰዎች እንደሚያውቁት በዚህ አቅጣጫ በሚተኙበት ወቅት የእጅ መደንዘዝ ሊያጋጥም ይችላል።

ጭንቅላትን እጅ ላይ አስደግፎ መተኛት የተለመደ አቅጣጫ ነው። ነገር ግን በጡንቻ እና ነርቭ ላይ ተጨማሪ ጉዳት ያስከትላል። ጭንቅላትን (አጠቃላይ ሰውነትን) በአንድ እጅ ላይ ማሳረፍ የደም ፍሰትን ይከለክላል በተጨማሪም ነርቭን ወደታች ይጫናል።

3. በሆዳቸው የሚተኙ!

✔ ጥቅሙ

በሆድ በኩል መተኛት ማንኮራፋት እና የእንቅልፍ ችግርን ያስቀራል። ነገር ግን በጣም ጥሩ የሚባለው ጎኑ በሌሊት ሠዓት ቦርጫችን ወደ ውስጥ እንዲገባ ያደርጋል።

✔ ጉዳቱ

በሆድ በኩል መተኛት በአብዛኛው እንደሚታወቀው በጣም አስቀያሚ የሚባል የአተኛኘት አቅጣጫ ነው። የአከርካሪ የተፈጥሮ መንጋደድን በማዛባት ቀጥ እንዲል ያደርገዋል ይህም የታችኛው ጀርባ ህመምን ያስከትላል።

ሌሊቱን ሙሉ ጭንቅላትን ወደ አንድ አቅጣጫ አድርጎ መተኛት የአንገት ህመምን ያስከትላል።

16/10/2022

ቡግር (Acne)

ቡግር የረጅም ጊዜና በብዙ ሰዎች ላይ የሚከሰት እና የፀጉር መውጫ ቀዳዳዎች በተለያዩ ነገሮች በሚዘጋበት ጊዜ የሚመጣ የሰውነት ቆዳ ህመም ነው።

• ይህ ህመም በፊት ላይ ከሚገኙ አነስተኛ ነጫጭ እና ጥቋቁር ነጥብጣቦች እስከ ሁሉንም የሰውነት ክፍል እስከሚያዳርስ መግል የቋጠሩ እብጠት ይደርሳል።

• ምንም እንኳ እስከሞት የሚያደርስ ችግር ባይሆንም የሰውነት ቆዳን በማበላሸት የስነ ልቦና ችግር ፣ ድብርት ፣ በራስ መተማመንን ይቀንሳል እንዲሁም የረጅም ጊዜ የቆዳ ለምጥ ያስከትላል ።
• 80% በሚሆኑ ሰዎች ላይ ቀለል ያለ ሰሆን 20% የሚሆኑ ሰዎች ላይ ከባድ ቡግር ይኖራቸዋል ።

ማንን ያጠቃል
• ምንም እንኳ በየትኛውም የእድሜ ክልል የሚገኝ ቢሆንም በብዛት በአስራዎቹ እድሜ ክልል ያሉ ሰዎችን በብዛት ያጠቃል ።
• ይህም በጉርምስና እና ኮረዳነት ጊዜ በሚጀመረው የሆርሞን በከፍተኛ መጠን መመረት ጋር የተያያዘ ነው።
• ከ14-30 ዓመት 80% የሚሆኑ ሰዎችን ሲያጠቃ ከ30-40 ዓመት 15% የሚሆኑ ሰዎችን ያጠቃል ።

እንዴት ይከሰታል
• በሰውነታችን ላይ ትንንሽ ቀዳዳዎች ሲኖሩ እነዚህ ቀዳዳዎች ከስራቸው ፀጉር ሊበቅልበት የሚችልበት ከመሆኑ በተጨማሪ በስራቸው የሚገኙትን የወዝ ዕጢዎች የሚያመርቱት ወዝ ወደ ላይኛው የቆዳ ክፍል የሚወጡበት ሲሆን ይህ ቀዳዳ ከመጠን በላይ በሆነ ስብ መመረት እና በሞቱ የቆዳ ሴሎች በሚደፈኑበት ጊዜ በሰውነታችን ላይ የሚገኝ ኩኒባክቴሪየም አክኒ ውስጥ ላይ እንዲራባ እና ቁስለት እንዲፈጠር ያደርጋል ።

የሚያጋልጡ ሁኔታዎች
• ለቡግር በዋናነት የሚያጋልጠው የዘረ-መል ሲሆን ይህም በቤተሰብ በብዛት እንዲገኝ ያደርገዋል ።
• ከሆርሞን ጋር የተያያዘ ይህም በአስራዎቹ እድሜ የመብዛት እና በወር አበባ ጊዜ የመጨመር ሁኔታ ያሳያል
• ከፍተኛ የሆነ የሆነ የወዝ መመረት
• የሰውነት የቆዳ ሴሎች የመመረት እና የመወገድ ሁኔታ አለመመጣጠን
• ሰውነት ላይ የሚደረጉ እንደ የጀርባ ሻንጣ፣ እራስ ላይ የሚደረጉ ኮፍያዎች እና ጥምጣም ፣ የጡጥ ማስያዣ ፣ ሄልሜት የመሳሰሉት የውዝ መውጫውን በመድፈን
• መድሀኒቶች ለምሳሌ ሊትየም፣ አንዳንድ ለመጣል በሽታ የሚሰጡ

የትኛውን የሰውነት ክፍል ያጠቃል
• ቡግር በብዛት የፀጉር መውጫ ቀዳዳዎች በሚገኙበት ቦታ ማለትም በፊት ፣ በደረት አካባቢ እና በጀርባ ላይ ቢገኝም በሁሉም የሰውነት ቆዳ ላይ ሊወጣ ይችላል።

አይነቶቹ
• አነስተኛ ቡግር በቁጥር ከ30 በታች የሚሆኑ ነጫጭ እና ጥቋቁር ነጠብጣቦች
• መካከለኛ ቡግር በቁጥር ከ100 በታች የሆኑ ነጫጭ እና ጥቋቁር ነጠብጣቦች እና ቀያይ እብጠቶች
• ከፍተኛ ቡግር ተለቅ ያሉ ጠጣር ህመም ያላቸው እብጠቶች እና ህመም ያላቸው መግል የያዙ ከቆዳ ስር ያሉ እባጮች የያዘ

ምልክቶች
• ነጭ አናት ያላቸው ነጠብጣቦች
• ጥቁር አናት ያላቸው ነጠብጣቦች
• ትናንሽ ቀያይ ህመም ያላቸው ነጠብጣቦች
• ቀያይ ጫፍ ላይ ትንሽ መግል ያላቸው ነጠብጣቦች
• ተለቅ ያሉ ጠጣር ህመም ያላቸው እብጠቶች
• ህመም ያላቸው መግል የያዙ ከቆዳ ስር ያሉ እባጮች

• ከእነዚህ ቆዳ ላይ ከሚታዩት ምልክቶች በተጨማሪ ከበድ ባሉ የቡግር አይነቶች ትኩሳት ፣ ብርድ ብርድ ማለት እና የመገጣጠሚያ ህመም ሊኖር ይችላል ።

ህክምናው
• በብዛት የሚመከር ቡግር ያለበት ቦታ ላይ የሚቀቡ ረቲኖል እና የሚቀቡ ፀረ-ተህዋስያን (ክሊንዳማይሲን፣ ኢሪትሮማይሲን) በአንድ ላይ ለሁሉም የቡግር አይነቶች እንደ መጀመሪያ ደረጃ ህክምና ነው።

06/08/2022

የእናት ጡት ወተት ጥቅሞች
📌 በአሁኑ ወቅት በተለይ በከተሞች አካባቢ አንዳንድ እናቶች ልጆቻቸዉን የሚያጠቡት ከራሳቸው የጡት ወተት ይልቅ የጣሳ ወተትን ስመርጡ ይስተዋላሉ::

📌 በእርግጥ ሁሉም እናቶች የራሳቸው ምክንያት አላቸው::

📌ሆኖም ግን እስካሁን በተጠኑት ጥናቶች መሰረት የእናትን ወተት የሚተካ ሌላ አይነት ወተት ወይም ምግብ እስካሁን አልተገኘም ‼️

📌የእናት ጡት ወተት ጥቅሙ ልጇ ብቻ ሳይሆን ለእናትም ለቤተሰብም ለማህበረሰብም ከፍ ሲልም ለሀገር ነው:: እስኪ በዝርዝር እንየዉ፦

1. ጡት ማጥባት ለእናት ያለው ትቅም ፦

✍️ ከ ወሊድ በዋላ ማህፀን ቶሎ እንዲኮማተር እና ወደ ቦታ እንዲመለስ ያረጋል ይሄም የደም መፍሰስ እንዳይከሰት ይከላከላል
✍️ ከወሊድ በዋላ ክብደትን ለመቀነስ ይረዳል
✍️ የጡት እና የእንቁላል ማኩረቻ ካንሰርን ይከላከላል
✍️ በ እድሜ የሚመጡ በሽታዎችን ለምሳሌ ስኳር ደም ግፊት እና የመሳሰሉትን በሽታዎችን ይከላከላል
✍️ በ እናት እና በልጅ መሃል ያለውን ፍቅር ይጨምራል
✍️ በተፈጥሮ ስለሚገኝ ወጪ ቆጣቢ ነው
✍️ ለአጭር ጊዜ ቢሆንም እርግዝናን ይከላከላል

2. የእናት ጡት ወተት ለህፃናት ያለው ጥቅም:

👉 ትክክለኛ እና በቂ የሆኑ ንጥረ ነገሮች በውስጡ ስለያዘ ህፃናት በተገቢው ሁኔታ እንዲያድጉ ይረዳል
👉 የብሩህ አይምሮ(Higher IQ) ባለቤት ያረጋቸዋል
👉 የተለያዩ የህፃናት ኢንፌክሽኖችን ይከላከላል ለምሳሌ የ ጆሮ፣የሳምባ፣ የአንጀት ፣የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን
👉 የልጆች አለርጂን ይከላከላል
👉 ልጆች ከመጠን ያለፈ ውፍረት እንዳይኖራቸዉ ይከላከላል
👉 የመጀመርያዉ አይነት የስኳር በሽታ(Type 1 Diabetus Mellitus) ይከላከላል
👉 ድንገተኛ የሆነ የጨቅላ ህፃናትን ሞት ይከላከላል

3. የእናት ጡት ወተት ማጥ ባት ለቤተሰብ እና
ለ ማህበረሰብ ያለው ጥቅም

📌 የተለያዩ የህፃናት በሽታ በመከላከል የሀገሪቱን የ ጤና ወጪ ይቀንሳል
📌 ልጆች ባለ ብሩህ አይምሮ ሆነው እንዲያድጉ በመርዳት በትምህርትም ዉጤታማ እንዲሆኑ ከዛም እንደ ሀገር ጥሩ አበርክቶ እንዲኖራቸዉ ቀላል የማይባል አስተዋፆ አለው::

እባክዎን ካነበቡ በኋላ ሼር ያድርጉት !

ዶክተር ፋሲል መንበረ
በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ የህጻናት ስፔሻሊስት ሐኪም

Photos from Hakim's post 18/07/2022
Want your practice to be the top-listed Clinic in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address

Addis Ababa
Other Medical & Health in Addis Ababa (show all)
Janmeda Health Center Janmeda Health Center
Addis Ababa

Janmeda primary Health Care Unit

DXN_addis Amanuel DXN_addis Amanuel
Addis Ababa

Holistic Medicine and Supplementary Products Selling Platform.....All Herbal&Organic Products

DR Mitiku Medium Clinic DR Mitiku Medium Clinic
Amfo Square
Addis Ababa

our patients are our family

South Sudanese future pharmacists South Sudanese future pharmacists
Addis
Addis Ababa, 2023

Our major aim is to brightening the future of upcoming generations.

Tesfa  home care nursing Tesfa home care nursing
Bole
Addis Ababa, 1000

Our company provides ultimately medical care with mobility and with senior nursing abilities from minor to severe cases with a reasonable price.

Shalom Medical Consultancy Shalom Medical Consultancy
Swazeeland Street
Addis Ababa, 1271

This page is created to promote helath realted issues and provide medical consultation for pateints

Ethiopian anesthetists voice Ethiopian anesthetists voice
Addis Ababa

Here we are for better Health care

Health info and vaccancy news Health info and vaccancy news
Addis Ababa
Addis Ababa, 0000

HIVN media adresses health related news, vacancies and health educational topics

Xarunta dhireedka Yemen Xarunta dhireedka Yemen
بولي ميكائيل . فندق ومسجد جعفر
Addis Ababa

Ethio medical Ethio medical
Bole
Addis Ababa, 1056

Duko medicine Duko medicine
Addis Abeba
Addis Ababa