ዳሞት ወይዴ ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት-Damot Woyde Urban dev.t & construction

damot woyde woreda urban development and construction office

Photos from ዳሞት ወይዴ ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት-Damot Woyde Urban dev.t & construction's post 19/10/2022

የዳሞት ወይዴ ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት "አካታች ከተማ ለሀገራችን ብልፅግና "በሚል መሪ ቃል የ2014 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሄደ

ዳሞት ወይዴ፣ጥቅምት 8/2015 ዓ/ም የዳሞት ወይዴ ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት "አካታች ከተማ ለሀገራችን ብልፅግና "በሚል መሪ ቃል የ2014 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሄዷል።

በምክክር መድረኩ ላይ የተገኙት የዳሞት ወይዴ ወረዳ የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ አሰራት ወልደጊዮርጊስ እንደገለፁት በ2014 በጀት ዓመት ታቅዶ ያልተሠሩት የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች የተስተዋሉ ደካማ ጎኖችን በመለየት ዕቅድ አካል በማድረግ ለተግባራዊነቱ መረባረብ ይገባል ብለዋል።

ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች በተለያዩ መሰረተ ልማት ሥራዎች በመሳተፍ ከተማን ውብና ጽዱ የማድረግ ሥራ መስራት እንደሚጠበቅበትም ገልጸዋል።

ለከተማችን ለውጥና ዕድገት የአመራሩና የባለድርሻ አካላት ሚና ከፍተኛ መሆኑን የገለጹት አቶ አሥራት ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፏቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳሰበዋል።

የዳሞት ወይዴ ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን በየነ በበኩላቸው በ2014 በጀት ዓመት የታዩት ጉድለቶችን በማረምና በአዲሱ ዓመት የዕቅድ አካል በማድረግ ጽ/ቤቱ ልዩ ትኩረት ሰጥተው ይሠራል ብለዋል።

አቶ ተስፋሁን አያይዘውም በ2015 በጀት ዓመት ለተገልጋዩ ህብረተሰብ ክፍሎች ቀልጣፋና ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት ከባለድርሻ መስሪያ ቤቶች ጋር በቅንጅትና በቅርበት እንደሚሠራ አረጋግጠዋል።

በከተማችን የተጀመሩ መሠረተ ልማት ሥራዎች እንዲጠናቀቁና አዲስ ሥራ እንዲጀመር ትኩረት በመስጠት ከሚመለከተው አካላት ጋር በመናበብ ለአፈጻጸሙ ቅድሚያ እንደሚሰጥ አቶ ተስፋሁን አስታውቋል።

በምክክር መድረኩ ላይ የዳሞት ወይዴ ወረዳ የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ አሰራት ወልደጊዮርጊስና ፊት አመራሮች ፣የዳሞት ወይዴ ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን በየነ፣የወረዳው አጠቃላይ አመራሮች ፣ የጽ/ቤቱ አጠቃላይ ባለሙያዎች እና ባለድርሻ መስሪያ ቤቶች ተገኝተዋል።

Photos from ዳሞት ወይዴ ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት-Damot Woyde Urban dev.t & construction's post 12/10/2022

ዛሬው ዕለት ማለትም ቀን 02/02/2015 ዓ.ም የበዴሳ ከተማ ሁለቱም ቀበለያት ነዋሪዎች በነቂስ ወጥቶ የመንገድ ዳር ችግኝ አጥር የማጠር ፤ችግኝ የመትከል ና የመኮትኮት ሥራ ተሠርቷል።

Photos from ዳሞት ወይዴ ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት-Damot Woyde Urban dev.t & construction's post 24/08/2022

ዛሬ በቀን 18/12/2014 ዓ.ም የሣኬ ማዘጋጃ ቤት የ10 ዓመት ፕላን ዕድሣት ዙሪያ ከዞን ከተማ ልማት መምሪያ የመጡ ፕላነር ሶሽዮ ባለሙያዎች እና የወረዳው ከተማ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊዎች እንዲሁም የዘርፉ ባለሙያዎች እና የዳዌ ሣኬ፤ሙንዳጃ ሣኬ፤ጋልቻ ሣኬ ቀበሊያት የመጡ ሊቀመንበሮችእና ከቀበሌው የተካለሉት አርሶ አደሮች እና የጋልቻ ማዘጋጃ አጠቃላይ ህብረተሰብ በተገኙበት ፕረዘንቴሽን አድርገው አዲሱ ፕላንን በማስማማት ወደ ውሳኔ ተደርሷል።

Photos from ዳሞት ወይዴ ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት-Damot Woyde Urban dev.t & construction's post 08/08/2022

በዳሞት ወይዴ ወረዳ የክረምት ወጣቶች በጎ አገልግሎት ሥራ ህብረተሰቡን በማሳተፍ የከተማ ውበትና ጽዳት ሥራ ተከናወነ

ዳሞት ወይዴ፣ነሐሴ 2/2014 ዓ/ም በዳሞት ወይዴ ወረዳ የበዴሳ አድስ ከተማና ቴሌ 01 ቀበሌ ህዝብና የክረምት በጎ ወጣቶች በጋራ በመሆን ከተማውን ውብና ጽዱ የማድረግ ሥራ አከናውኗል።

ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች የከተማውን ውበትና ጽዳት ከመጠበቅ ባሻገር የየራሳቸውን አካባቢን ለማጽዳትና ለማስዋብ ትኩረት መስጠት ይገባል።

በቀጥታ ሆነ በተዘዋዋሪ የሚደርሰውን የጤና ጉዳትን ለመከላከልና ለመጠበቅ እያንዳንዱ ግለሰብ የራሱንና የአከባቢውን ጤንነት ለመንከባከብ ጽዳትና ውበት ስራ አስፈላጊ መሆኑን ህብረተሰቡ ተረድተው ዲርሻውን በተገቢው መወጣት አለበት።

የወረዳው ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ከበዴሳ ከተማ ማዘጋጃና 3ቱ አደረጃጀት ጋር በጋራ በመቀናጀት የውበትና ጽዳት ሥራው በተገቢው እንዲመራ ተደርጓል።

በከተማ ውበትና ጽዳት ሥራ ቦታ የወረዳው ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት፣የበዴሳ ከተማ ማዘጋጃ ፣3ቱ አደረጃጀት እና የሁለቱ ቀበሌያት ህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።

Photos from ዳሞት ወይዴ ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት-Damot Woyde Urban dev.t & construction's post 05/07/2022

የኢትዮጵያ የከተሞች የአረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር በለገጣፎ፣ ለገዳዲ ከተማ በይፋ ተጀመረ።

የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በለገጣፎ፣ ለገዳዲ ከተማ ከፌዴራልና ከክልል የተውጣጡ የዘርፉ አመራሮችና የከተሞች ከንቲባዎች በተገኙበት በዛሬው ዕለት ሰኔ 28/2014 ዓ.ም በይፋ ተጀምሯል።
ፕሮግራሙን በይፋ ያስጀመሩት የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ ሲሆኑ ሚኒስትሯ በመክፈቻ ንግግራቸው በአገር አቀፍ ደረጃ ለአራተኛ ዙር ከተያዘው የ6 ቢሊዮን የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ውስጥ በሁሉም የሀገራችን ከተሞች 196.8 ሚሊዮን ችግኝ ለመትከል እቅድ መያዙን ጠቁመው በተያዘው እቅድ መሰረት በዛሬው ዕለት በለገጣፎ፣ ለገዳዲ ከተማ የተካሄደው የማስጀመሪያ መርሃ ግብር በሁሉም ከተሞች እውን ይሆናል ብለዋል።
እስካሁን በተካሄደው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ስኬታማ ስራዎችና አበረታች ውጤቶች እንደተመዘገቡ የጠቆሙት ክብርት ሚኒስትሯ ከአገራችን ኢትዮጵያ አልፎ ለምስራቅ አፍሪካ ሀገራት አንድ ቢሊዮን ችግኝ መላክ በመቻላችን የአገራችን ተሞክሮ ለዓለም ሀገራት በዓርአያነት የሚጠቀስ መሆኑን በፖላንዷ ካቶቬስ ከተማ በተካሄደው 11ኛው የዓለም ከተሞች ፎረም ላይ መጠቀሱን አስታውሰዋል።
ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ በማጠቃለያ ንግግራቸው እያንዳንዱ ከተማ በከተማው ውስጥ የሚገኙ ክፍት ቦታዎችን በሙሉ በአትክልትና ፍራፍሬ በመሸፈን መንግስት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያደርገውን ጥረት ሊያግዝ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል። የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ በፕላን ታግዞ መመራት እንዳለበት ጠቁመው በአረንጓዴ አሻራውም የከተማ ግብርናን ታሳቢ ያደረጉ ስራዎች ሊሰሩ ይገባል ብለዋል። የአረንጓዴ አሻራው ዘላቂነት እንዲኖረው ንቅናቄውን ተቋማዊ አድርገን ልንሰራ ይገባል ያሉት ሚኒስትሯ ለዚህ ደግሞ አመራሩ ግንባር ቀደም በመሆን ሚናውን ሊወጣ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

በመድረኩ ተገኝተው የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ያስተላለፉት የለገጣፎ፣ ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ በሪሶ ተመስገን በበኩላቸው እንደሀገር የተያዘውን የአረንጓዴ አሻራ እቅድ ለማሳካት በከተማዋ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡
በመርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙት የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒን ጨምሮ ክብርት ወ/ሮ ሄለን ደበበ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ዲኤታ ፣ ከፌዴራልና ከክልል የተውጣጡ የዘርፉ አመራሮችና የየከተሞቹ ከንቲባዎች ችግኝ ተክለዋል።

Photos from ዳሞት ወይዴ ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት-Damot Woyde Urban dev.t & construction's post 05/07/2022

የደቡብ ክልል ኮንስትራክሽንና ከተማ ልማት ቢሮ በወላይታ ሶዶ ለአቅመ ደካማ እናት ቤት ለመሥራት አስጀመረ

ዳሞት ወይዴ፣ ሰኔ 28/2014 የደቡብ ክልል ኮንስትራክሽንና ከተማ ልማት ቢሮ ከወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በወላይታ ሶዶ ድ/በጌረራ ቀበሌ ለአቅመ ደካማ እናት ቤት ለመሥራት ጀምሯል።

ቢሮ ከዩኒቨርስቲው ጋር በመተባበር ለ45 ቀናት ሲሰጥ የቆየውን ስልጠና ማጠቃለያ ላይ ነዉ የቤት የማስጀመር መርሃ ግብር ያደረገው።

ከደቡብ ክልል ከተለያዩ ዞናችና ከልዩ ወረዳዎች ለመጡ ከተማ መሬትና ፕላን ላይ የተሰጠውን ስልጠና መነሻ በማድረግ ዩኒቪርስቲ ማናጅመንት ጋር ተወያይቶ የተለያዩ ቁሳቁሶችንን ቆርቆሮና አልባሳትን ድጋፍ አድርገዋል።

በሚቀጥለው በጥቅት ወራት ውሰጥ ቤቱን ሰርተው ለማስረከብ ቃል ገብቷል።

Photos from Damot Woyde Woreda Prosperity Party- ብልጽግና  ፓርቲ's post 23/06/2022
Want your organization to be the top-listed Government Service in Sodo?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address

South
S**o
Other S**o government services (show all)
Wolaita Zone Youth Association/ ወላይታ ዞን ወጣቶች ማህበር Wolaita Zone Youth Association/ ወላይታ ዞን ወጣቶች ማህበር
Ligaba
S**o

በብቃት እና በጥረት የተካኑ ወጣቶችን ለማፍራት እንተጋለን !

ሲሳይ ደገፉ / Sisay degefu ሲሳይ ደገፉ / Sisay degefu
Wolaita
S**o, LULSEGED

Private

Gesuba ketema  Agricultral office page Gesuba ketema Agricultral office page
S**o

Gov.t Office at Gesuba

Dddd Dddd
S**o

Dddd is an unknown political organization

የመንፈስ ፍሬዎች የመንፈስ ፍሬዎች
W/S**o, Gununo, Ethiopia።
S**o, TAMRMISRAKDESTA

በመፀሐፍ ቅዱስ ወደ ገላትያ ስዎች 5:22-23የስፈረ ቃል ነው።

Bayra koysha woreda Health office Bayra koysha woreda Health office
S**o

Health for all

Tare Tare
Tarekegn Mathewos
S**o, 4500

ገሱባ ከተማ አስ/ር ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ዩኒቲ ገሱባ ከተማ አስ/ር ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ዩኒቲ
Gesuba
S**o

Gesuba town administration workers and social affairs