ሲሳይ ደገፉ / Sisay degefu

Private

27/03/2024

#ዎላይታ #ዎርቃ #ማይዛና
#ዎላይታ #ሊቃ #ሚይያን #ኤቃና

Photos from ሲሳይ ደገፉ / Sisay degefu's post 26/03/2024
Photos from ሲሳይ ደገፉ / Sisay degefu's post 26/03/2024

* መልሱ 😓😓
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገንዘብ ወስደው አልመለሱም ያላቸውን ግለሰቦች ስም ዝርዝር ይፋ አደረገ

ገንዝብ ወስዳችሁ ያልመለሳችሁ
ኢትዮጵያውያን በሙሉ

ስም ዝርዝራችሁ ወጥቷል::😎

ሰው በተኛበት በለሊት ሰይጣን ብቻ በሚንቀሳቀስበት ስአት ገንዘቡን የወስዳችሁ ፎቶአቹን ከሚለቀቅ የወስዳችሁትን ገንዝብ

በቅርንጫፍ እየሄዳችሁ መልሱ::

እስቲ ስማችሁን ፈልጉት አለ እንዴ?

😎😎😎

🌴🌴🌴

26/03/2024

#ያልተኛ #ተጠቀመ
ከወጪ ቀሪ... 🤔

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሰሞኑ በተፈጠረው የሲስተም ችግር ሳቢያ ከ 9 ሚሊዮን ብር በላይ የወሰዱትን ወደ 567 የሚጠጉ ግለሰቦችን ማግኘት አለመቻሉን አስታወቀ ፦

ባንኩ መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም. ምሽት ላይ ከ 3:00 ጀምሮ እስከ ለሊቱ 8:45 ድረስ ባለው 25 ሺህ 761 ደንበኞች 801.4 ሚሊዮን ብር መውሰዳቸውን ገልጿል።

ባንኩ ባጋጠመው ችግር ምክንያት ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ በሂደቱ ውስጥ የተሳተፉ ግለሰቦችን ሂሳብ ልየታ ተከናውኗል የተባለ ሲሆን በዚህም 15 ሺህ 8 ያህል ሂሳብ ቁጥሮች መገኘታቸውን ባንኩ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል ።

በዚህም ጠቅላላ በተፈጠረው ችግር ያላግባብ የተወሰደ ገንዘብ መጠን በ25 ሺህ 716 ደንበኞች 801 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር በላይ መሆኑን የባንኩ ፕሬዝዳንት አ/ቶ አቤ ሳኖ ተናግረዋል።

ሆኖም በመጀመሪያው ቀን በተደረገ ጥረት ከ10 ሺህ 727 በአካውንታቸው ውስጥ በቂ ገንዘብ ከነበራቸው ደንበኞች 44 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር ተሰብስቧል። ጥረቱ ቀጥሎ በቀጣይ ቀናት ከ15 ሺህ 8 በአካውንታቸው ውስጥ ያለው ገንዘብ በቂ ባይሆንም የነበረን ገንዘብ በማካካስ 205 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር መሰብሰብ ተችሏል ተብሏል።

በተለይም ባንኩ ባቀረበው ጥሪ መሠረት 9 ሺ 2 መቶ 81 ያህል ግለሰቦች በፈቃደኝነት የወሰዱትን 223 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር መሉ በሙሉ መመለሳቸው ተገልጿል። እንዲሁም በጉዳዩ ላይ ተሳትፎ የነበራቸው 5 ሺ 1 መቶ 60 ያህል ግለሰቦች ከወሰዱት ገንዘብ በፈቃደኝነት ሙሉ በሙሉ ባይሆንም በከፊል 149 ሚሊዮን ብር መልሰዋል ተብሏል።

ጥፋተኞቹን ለመያዝ ብዙ አይነት መንገድ ባንኩ እንደተጠቀመ ያነሱት ፕሬዝዳንቱም ከዛ ውስጥ በሂሳባቸው ውስጥ በቂ ገንዘብ ያላቸውን እንዲሁም ያረጉት ግብይት ከ2 በላይ ያልሆኑ ከ10ቪ በላይ ደንበኞች ሌቦች እንዳልሆነ በማሰብ 44 ሚሊየን በላይ መሰብሰብ እንደተቻለ አንስተው ፤ ሁለተኛው እርምጃ ደግሞ በሂሳባቸው ውስጥ ገንዘብ አለ ነገር ግን ያላወጡ 15 ሺ ደንበኞች ወይም ከ1 ጊዜ በላይ ግብይት ያልፈፀሙ ሲኖሩ በዚህ መንገድ ሌላ ብር ሪከቨር ማድረግ እንደተቻለ ተነስቷል፡፡

አጠቃላይ በዛች ቅፅበት ከ14 ጊዜ በላይ ግብይት መፈፀሙ ሲነሳ ግብይቱን ከፈፀሙት ከ15‚000 በላይ ደንበኞች ውስጥ ሙሉ በሙሉ የከፈሉ ደንበኞች ቁጥር 9881 ሲሆን 5‚160 ሰዎች ደግሞ በከፊል እንዲከፍሉ እንደተደረጉ ተነስቷል፡፡

በዚህ ውስጥም 567 ደንበኞች ምንም አልመለሱም። የወሰዱት ገንዘብም ግን 9.8 ሚሊየን ብር እንደሆነ ፕሬዝዳንቱ ጨምረዋል።

በግብይቱ ወቅት ያራሳቸው ካልሆነው ውስጥ ትልቁ ገንዘብ የተወሰደው ውስጥ 334 ሺ ብር እንደሆነም ተገልጿል።

በአጠቃላይ በተደረገው ጥረት እስከ መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ.ም ባለ ሪፖርት መሠረት ከ622 ነጥብ 9 ወይንም 78 በመቶ ያክሉን ገንዘብ ወደ ባንኩ ተመላሽ መደረጉ ተገልጿል። ነገር ግን ቀሪ 567 ግለሰቦች ያላግባብ ከወሰዱት 9 ሚሊዮን 838 ሺህ 329 ብር ውስጥ እስከ አሁን ድረስ ምንም አይነት ክፍያ ወደ ባንኩ ቀርበው እንዳልፈፀሙ አ/ቶ አቤ ተናግረዋል።

ስለሆነም ባንኩ ባስቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ በፈቃደኝነት ምላሽ ያልሰጡ ግለሰቦችን በተመለከተ በጉዳዩ የተሳተፉ ግለሰቦችን ማንነት የሚገልፅ ማስታወቂያዎችን ፎቶግራፍን ጨምሮ በተመረጡ መገናኛ ብዙሃን ይፉ ይደረጋሉ ተብሏል። ይኸውም እስከ ሚቀጥለው ቅዳሜ ድረስ ተግባራዊ ከተደረገ በኋላ ደግሞ በህግ አግባብ ለመጠየቅ እንደሚሰራ ተገልጿል ።

ምንጭ፦ ካፒታል & ዳጉ ጆርናል & ኢትዮ FM

25/03/2024

በተሰቦቿ ተገኝቷል ስራዓተ ቀብሯም ተፈፅሟል ።
ለቤተሰቦቿ መፅናናት ይሁን ነብስ ይማር!!
😭

Photos from ሲሳይ ደገፉ / Sisay degefu's post 25/03/2024

ነብስ ይማር 😭

ልብ ይሰብራል😭

በአስቸኳይ ቤተሰቦቿን ፈልጉልን🙏

ይህች ሴት ስሟ ነፃነት ደሴ ቱጀሬ ነው!ቄራ አካባቢ የሚገኝ ምግብ ቤት ውስጥ በወጥ ሰሪነት ተቀጥራ እየሰራች ዛሬ ለሊት ድንገት የከሰል ጭስ አፍኗት ህይወቷ አልፏል😭

አስክሬኗ ዘውዲቱ ሆስፒታል የሄደ ሲሆን ቤተሰብ በአስቸኳይ ካልተገኘ መዘጋጃ እንደሚቀብራት ፖሊሶች አሳውቀዋል!

እህታችን ስራ የገባችው በደላላና መታወቂያዋ ብቻ ስለሆነ የቤተሰቦቿን አድራሻም ሆነ ስልክ ማግኘት አልተቻለም!!

መታወቂያዋ ላይ የእናቷ ስም አልማዝ_ላንጬ የትውልድ ቦታም ወላይታ ወረዳ ሆ/ቻ(ሆቢቻ) ይላል!!

ለቤተሰብ መርዶና ሀዘኑ ከባድ ቢሆንም ቢያንስ አስክሬኑን እንዲያገኙ ሼር በማድረግ ቤተሰቦቿን እንፈልግ🙏

* 0912852892

ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም"

ባይሽ ኮልፌ በጎ አድራጎት

😭

🌴🌴🌴

Photos from ሲሳይ ደገፉ / Sisay degefu's post 24/03/2024

* ከሀገረ ዎላይታ ጦና ቦክስ ክለብ እስከ ኢትዮጵያ እንድሁም የአፍሪካ መድረክ መሪነት*

| ኢትዮጵያዊቷ ድንቅ ቦክሰኛ ቤቴል ወልዴ፥ በ66 ኪ.ግ ከሞዛምቢኳ ቦክሰኛዋ ጋር ለፍፃሜ ተገናኝታ በሚገርም ብቃት 5 ለምንም በሆነ ውጤት በጋና አክራ ከተማ በተካሄደው በዘንድሮው የመላው አፍሪካ ጨዋታ ለኢትዮጵያ 2ኛ የሆነ የወርቅ ሜዳልያ በማስመዝገብና ለራሷ ደግም የወርቅ ሜዳልያ ቁጥር ከፍ በማድረግ ስሟን በደማቁ የታሪክ ማህደር መሰነድ ችላለች።

ከዎላይታ-ኢትዮጵያ እስከ አለምአቀፍ ቦክስ ስፓርት ውድድር ከ67 በላይ ወርቅ ተሸላሚ እንዲሁም ለአራት ዙር የቤልት ውድድር የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ቦክሰኛ ሻምፒዮና የሆነችው ቤቴል ወልዴ 68ኛውን የወርቅ መዳሊያ በመላው አፍሪካ የአትሌቲክስ ውድድር በማግኘት አዲስ ታሪክ ማስመዝገብ መቀጠሏን በአደባባይ አረጋግጣለች።

ቤቴል ወልዴ ውልደትና ዕድገቷ ዎላይታ ሶዶ ነው፥ በቦክስ ስፓርት የተመሰከረላት ወጣት ናት፣ አብዛኞቹን ተጋጣሚዎችን በበቃኝ ማሸነፏ ደግሞ ለየት ያደርጋታል፤ እስከአሁን ድረስ ባደረገችው በቦክስ፣ በኪክ ቦክስና ሞይንታይ ውድድሮች አሸናፊ በመሆን የ67 ሜዳሊያዎች ባለቤት ናት።

ለየት የሚያደርገው ደግሞ ከእነዚህ ሜዳሊያዎች አንዱ ብቻ የነሀስ ሲሆን ሌሎች በሙሉ የወርቅ ብቻ መሆኑንም ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ማረጋገጧ ይታወሳል።

መነሻውን የጦና ቦክስ ቡድን ያደረገችሁ ይህቺ ብርቷ ሴት ከዓመታት በፊት ዎላይታ ዞንን ወክላ በክልልና በአገርአቀፍ ደረጃ በሴቶች ቦክስ ስፖርት ሻምፒዮን በመሆን ትታወቃለች።

ቀጥሎ ባሉ ጊዜያት ለአካዳሚ፣ ለኒያላና ለአዲስ አበባ ፖሊስ ስፖርት ክለብ በመጫወትም በርካቶችን በበላይነት በማሸነፍ እንዲሁም የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት በመሆን እውቅና ያተረፈች እንቁ ወጣት ናት።

በቅርቡ መስከረም ወር 2015 ዓ.ም ኢትዮጵያን ወክላ በተሳተፈችበት የሞይንታይ ኢንተርናሽናል ውድድር የቤላሩሱዋን ተወዳዳሪ በበላይነት አሸንፋ የሀገሯን ስም ከፍ አድርጋ አስጠርታለች።

በጋና አክራ በተካሄደው 13ኛ መላው የአፍሪካ ጨዋታ ላይ ኢትዮጲያ በቦክስ ውድድር ከ37 ዓመት በኋላ አዲስ ታሪክ ለሀገራቸው የወርቅ ሜዳሊያ ካሸነፈችሁ ከሌላኛዋ ብርቱ ቦክሰኛ ቤቴሌሄም ገዛሃኝ አሁን በሚያሳዩት አስደናቂ አቋም ቀጣይ በአለምአቀፉ መድረክ ለኦሎምፒክ በማለፍ የመጀመሪያዋ ሴት ቦክሰኛ ይሆናሉ በሚል በርካቶች ይመሰክራሉ።

ላለፋት አምስት ቀናት በጋና አክራ ሲካሄድ የቆየው 13ኛው የመላ አፍሪካ የአትሌቲክስ ውድድር ከ50 የአፍሪካ ሀገሮች ከ640 በላይ አትሌቶች መሳተፋቸው የተገለፀ ሲሆን ኢትዮጵያ በ47 ወንድ፣ በ40 ሴት በድምሩ በ87 አትሌቶች የተወከለች ሲሆን 7 የወርቅ፣ 7 የብር እና 4 የነሐስ በድምሩ 18 ሜዳልያዎችን ማስመዝገብ ናይጄሪያን ተከትላ በሁለተኛነት ማጠናቀቋን ከአፍሪካ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለ

24/03/2024

ይታሰብበት!!
ባህርዛፍ ከማሳቸው ለሚያነሱት አርሶአደሮች የወላይታ ዞን መንግስት የተለያዩ የቡና እና የፍራፍሬ ችግኞች በነፃ በመስጠት ሊያበረታታ ይገባል።

Photos from ሲሳይ ደገፉ / Sisay degefu's post 23/03/2024

የቡና አብዮትም እንሰትን ይከተለው።
የእንሰት አብዮት በወላይታ ዞን፤ መልካም ጅማሮ ነው

የእንሰት ምርት በዞኑ አብዛኛው አከባቢዎች በስፋት የሚመረትና ለረጅም ዘመናት ለምግብነት እየዋለ የመጣ "አረንጓዴ ወርቅ" ነው፡፡

እንሰት ምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ የተመጣጠነ የሥነ ምግብ ስርዓትን ለመፍጠር ያግዛል፤ እንዲሁም ዘርፈ ብዙ ጠቃሜታዎችን እየሰጠ ያለ ተክል ነዉ።

እንሰት የጎጆዎች ግርማ ሞገስ፣ የጓሮዎች ማድመቂያና አረንጓዴ ሰገነት ከመሆን ባሻገር “ለግሉኮስ” ማቀነባበሪያ ግብዓት እንደሚሆን በጥናት ተረጋግጧል፡፡

እንሰት 20 ሚሊዮን የሚሆነው ህዝብ በቀን ሦስት ጊዜ መመገብ የሚያስችል እንደ ሀገር ያልተጠቀምንበት ሲሳይ፤ እስካሁን በጣም ያጣነው ትልቅ ሀብት ነው።

በዘመናዊ መንገድ አምርቶ ለገበያ የሚቀርብበት መንገድ ቢኖር ከሀገር አልፎ ለአፍሪካ ብሎም ለዓለም ገበያ መቅረብ የሚችል እምቅ ሀብት እንደሆነም ተጠቁሟል።

እንሰት ድርቅን የሚቋቋም፣ በውስን መሬት ላይ የሚለማ፣ ለምግብና ለሌሎች አገልግሎቶች የሚውል የተለያዩ ተዋፅኦዎቸን የሚሰጥ ተክል ነዉ።

የአየር ንብረት ሚዛንና የአካባቢን ለምነትን ጠብቆ ለማቆየትም ያግዛል የእንሰት ተክል። በምግብ ራስን ለመቻል በሚደረገው እንቅስቃሴም የበኩሉን እያበረከተ ይገኛል።

"ባህርዛፍን ከማሳ እንንቀል፤ እንሰትን እንትከል!!"

22/03/2024

አምባሳደር ተሾመ ቶጋ መልቀቂያ አስገብተው የኮሚሽነርነት ቦታቸው ለቀቁ።

ከመጋቢት 12/2016 ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን ለኮሚሽኑ አዳዲስ የአመራር ሹመቶች ተሰጡ። በበላይነት የሚመራዉ ቦርድም ተሰየመ።

ክቡር ኮሚሽነር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ በግል ጉዳያቸዉ ምክንያት በኮሚሽነርነት ላለመቀጠል ያቀረቡት ጥያቄ በመንግስት ተቀባይነት በማግኘቱ የኮሚሽነርነት ቦታቸዉን ከመጋቢት 3/2016 ጀምሮ ለቀዋል።

በምትካቸዉ ከመጋቢት 12/2016 ጀምሮ ክቡር አቶ ተመስገን ጥላሁን የብሄራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነዉ ተሹመዋል።

የኮሚሽኑ የሎጂስቲክስ እና አስተዳደር ዘርፍ ም/ኮሚሽነር በሆኑት በዶ/ር አትንኩት መዝገበ ምትክ ክቡር አቶ ተስፋዓለም ይህደጎ ከመጋቢት 12/2016 ጀምሮ ተሹመዋል ።

በተጨማሪም ኮሚሽኑን በበላይነት የሚመራ በፍትህ ሚኒስትሩ በክቡር ዶ/ር ጌድዮን ጢሞቲዎስ የሚመራ እና አምስት ከፍተኛ አመራሮች አባል እንዲሁም ክቡር ኮሚሽነር ፀሀፊ የሆኑበት ቦርድ ተሰይሞለታል።
***
በቴሌግራም መረጃ ማቅረብ ጀምረናል ተከተሉን
https://t.me/fastmereja
https://t.me/fastmereja

22/03/2024

ቅንነት?
በአንድ ወቅት በባቡር እየሄዱ ባቡሩ ላይ ለመግባት አንድ እግራቸው ሲገባ ባቡሩ ተንቀሳቀሰ ሲሄድ የአንድ እግራቸው ጫማ ወደቀ ወድያውኑ ባቡሩ መሄድ ስለጀመረ አንድ እግር ጫማቸውን ያልወለቀውን በማውለቅ ወደ ወለቀበት ወረወሩት አጠገባቸው ያለ ሰው እንዲህ ሲል ጠየቃቸው የ አንድ እግሮት ጫማ መውለቁ ሳያንስ እንዴት አንድ እግሩን ደገሙት ሲባሉ?
እኔ አንዱእግሩን ጫማ መቼም አላገኝውም ግን አንድ እግሩን ጫማ የሚያገኝው ሰው ለምን ሁለቱንም አያገኝም ብዬ ነው አሉ።
የመሀተበ ጋንዲ ቅንነት
ወንዱ ዘሐበሻ

ቅን እንሁን መልካም ቀን ይሁንልን ።

21/03/2024

በትግራይ ፤ የወንድ የዘር ፈሳሽ (ስፐርም) ለሚለግሱ ሰዎች 10ሺ ብር ስጦታ ይሰጣል ተባለ

'አዶ' በሚል ስም እሚታወቅ አንድ የግል የህክምና ማዕከል በተፈጥሮአዊ መንገድ ፅንስ ለመቋጠር ላልቻሉት ልጅ እእዲኖራቸው ለማድረግ እየሰራሁት ነው ባለው ስራ ሴት እንስቶች 'እንቁላል' ወንዶች ደግሞ 'የዘር ፍሬ (ስፐርም) እንዲለግሱ ጥሪውን አቅርቧል።

በትግራይ ክልል መቀለ ከተማ መቀመጫውን ያደረገው 'አዶ' የእናቶች፣ ሕጻናት እና የነቃ ሕይወት ሕክምና ማዕከል ይህንን ሕክምና ለመስጠት ዝግጅት የጀመረው ከትግራይ ጦርነት በፊት እንደሆነና ህክምናውን ለመጀመር የተደረገው ጥረት በጦርነቱ ምክንያት ቢቋረጥም ጦርነቱ ሲጠናቀቅ ግን ሂደቱ መቀጠሉን ይገለፃል።

ማዕከሉ በአሁኑ ሰዓት ታድያ ለስራው አስፈላጊ የሆኑ ቅድመ ዝግጅቶች በመከወን ስፐርም እና እንቁላል ለመለገስ ፈቃደኛ የሆኑ ሰዎችን እየጠበቀ ነውም መባሉን ዳጉ ጆርናል ታዝቧል።

የወንድ ዘር ለጋሾች የዘር ፍሬያቸው መጠን ከ 1.5 ሚ/ሊ በላይ መሆን አለበት፣በአንድ ሚ/ሊ ስፐርም ውስጥ ከ15 ሚሊዮን በላይ የወንድ የዘር ህዋስ (s***m cells) መኖር አለበት በተጨማሪም ለጋሾች ለኤችአይቪ፣ ለሄፐታይተስ ቫይረስ እና ሌሎች ተላላፊ በሽታዎች ምርመራ ማድረግ አለባቸውም ብለዋል።

እንቁላል ለሚለግሱ ሴቶች የእድሜ ገደብ እንዳለና እንቁላል ለመለገስ ብቁ የሆኑ ሴቶች በ 20 እና 30 አመት መካከል ናቸው በተጨማሪም ሴት ለጋሾች ቀደም ብለው የወለዱ መሆን አለባቸው ይላሉ ዶ/ር ሳምሶን። ይህ መስፈርት የተቀመጠው ለምን እንደሆነ ሲገልጹም “[የወለዱ ሴቶች] እንቁላሎቻቸው ተፈትነዋል ብለዋል።

የዘገባው የቢቢሲ አማርኛ ነው 👆

Photos from ሲሳይ ደገፉ / Sisay degefu's post 18/03/2024

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሳይበር ጥቃት እንዳልደረሰበት ተገለፀ፡፡
• ባንኩ ጠንካራ የሳይበር ደህንነት ስርዓት አለው ተብሏል፡፡
**********************

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መጋቢት 7 ቀን 2016 ዓ.ም በቅርንጫፍ እና በዲጂታል የባንክ አገልግልቶቹ ላይ ለተወሰኑ ሰዓታት የአገልግሎት መቋረጥ ማጋጠሙ ይታወቃል፡፡

ይህን በማስመልከት በዛሬው እለት ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ባንኩ ምንም አይነት የሳይበር ጥቃት እንዳልደረሰበት ገልፀዋል፡፡

ባንኩ ላይ የተለያዩ የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች በየጊዜው እንደሚደረጉ እና ባንኩ ባለው እጅግ ጠንካራ የሳይበር ደህንነት ስርዓት እንደሚመከቱ የገልፁት አቶ አቤ አሁን የተፈጠረው ችግር በሲቢኢ ብር እና በሞባይል ባንኪንግ አገልግሎቶች ላይ ተደርጎ በነበረ አዲስ የሲስተም ማሻሻያ ትግበራ ክፍተት መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ባንኩ የዲጂታል አገልግሎቶቹን ይበልጥ በማዘመን እና ለደንበኞች ይበልጥ ምቹ ለማድረግ በየጊዜው ማሻሻያዎችን ይተገብራል ያሉት አቶ አቤ፣ አሁን የተፈጠረውን ችግር በማጣራት ላይ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

አቶ አቤ በቅርንጫፎች እና በዲጂታል የባንኩ አገልግሎቶች ላይ መቋረጥ የገጠመው ሲስተሙ አልሠራ ባለማለቱ ሳይሆን፣ አዲስ ተግባራዊ ተደርጎ በነበረው የሲስተም ማሻሻያ ሳቢያ በተፈጠረ ክፍተት የተደረጉ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውሮችን በመለየት ለማገድ መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሳይበር ደህንነት በተለያዩ ዓለም አቀፍ መመዘኛዎች የደህነነት ማረጋገጫ እንዳገኘ አቶ አቤ ገልፀው፣ በዚህ ረገድ ደንበኞች ስጋት ሊገባቸው እንደማይገባ ገልፀዋል፡፡

18/03/2024

ኢትዮጵያ ትልልቅ ቀማኞች፥ እንኳን ቅጣት ግልምጫ ሳያገኛቸው፥ እንደ ልብ እየፋነኑ እሚኖሩባት አገር ሆናለች

(በእውቀቱ ስዩም)

ንግድ ባንክ በሌቦች ተጭበርብሮ፥ ወይም የኦንላይን ቅጽሩ ተሰብሮ ከሆነ ብዙ አይገርምም፤ እጅግ ታላላቅ የሚባሉ የአለም ተቋማት ሳይቀር እንዲህ አይነት አደጋ አጋጥሟቸው ያውቃል፤ እዚህ ሰፈር፥ ንቁ ዘበኛ ቢኖሮ እዚያ ማዶ ደግሞ የበለጠ ንቁ ሌባ ይኖራል፤ እያንዳንዱ ጽኑ በር ፥ ብርቱ መስበርያ አለው፤” ብርቅ አይደለም፤ ወደፊት በሌሎች ባንኮች ላይ ተመሳሳይ ነገር መፈጸሙ አይቀርም፤

በግሌ ያስገረመኝ ሌላ ነገር ነው፤

ስለዝርፍያው የተሰጠው ማህበራዊ ምላሽ እጅን ባፍ ብቻ ሳይሆን በጆሮም ያስጭናል፤ አብዛኛው ማህበራዊ ሚድያ ላይ ያለው መንፈስ ፥በቀልድም ቢሆን ሌቦችን የሚደግፍ ነው፤ ጨዋታ ቢሆንም የጨዋታው አቅጣጫ ያሳስባል፤ የሆነ ማህበራዊ በሽታ ምልክት ሊሆን ይችላል፤


የበሽታው መነሾ ምን ይሆን? የኔ ግምቶች እኒህ ናቸው፤

ሀ) “ ሰርቶ መብላት” የሚባለው ነገር ለብዙ ሰው ፥ለብዙ ሰው የትም የማያደርስ የዳገት መንገድ ሆኖበታል፤ ድሮ ‘ ያልሰራ አይብላ” የሚባል መፈክር ነበር፤ አሁን የሰራም የማይበላበት የኢኮኖሚ ጣቢያ ላይ ደርሰናል ፤ ለመኖር መስረቅ፥ ማጭበርበር ፥ መቆመር ወይ የሎተሪ እድለኛ መሆን ብቻ ነው የሚያዋጣው ‘ የሚል መንፈስ ነግሷል፤ ስለዚህ ውስጥ ውስጡን ፥ የሚዘርፉ ሰዎች እንደ አራዳ መቁጠር፥ ማድነቅ እየተለመደ ነው፤

ለ) ገዥዎችን እና ሀገረ መንግስትቱን ለያይቶ ማየት አለመቻል ሌላው ችግር ይመስለኛል ፤ ዋና ዋና የሀገር ተቋማትን እንደ ራስ መቁጠር እየቀረ ነው፤ ብዙዎቻችን፥ እኒህ ትልልቅ ተቋማት ቢወድሙ ወይም ቢዳከሙ ፥ የማታ የማታ፥ ጦሱ ለሁላችንም እንደሚተርፍ አናውቅም፤ ወይም ለማወቅ አንፈልግም፤


ሐ) የሕግ ተቋማት እና የጸጥታ ተቋማት ፥ የመንግስትን መዋቅር ተጠግተው የሚዘርፉ ሰዎችን ለመቅጣት ያላቸው ቸልተኝነት ወይም አቅመቢስነት ያሳስባል፤ መንግስት የሚደራጀው በዋናነት የዜጎችን ሕይወት እና በላባቸው ያፈሩትን ንብረት ለመጠበቅ ነው፤ አሁን አሁን፥ ኢትዮጵያ ትልልቅ ቀማኞች፥ እንኳን ቅጣት ግልምጫ ሳያገኛቸው፥ እንደ ልብ እየፋነኑ እሚኖሩባት አገር ሆናለች፤ ሕገ-ወጥነት አትራፊ ከሆነ ሁሉም የሕገ-ወጥነት ተቋዳሽ ለመሆን መጣሩ አይቀርም፤

Want your organization to be the top-listed Government Service in Sodo?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address


Wolaita
S**o
LULSEGED
Other S**o government services (show all)
Gesuba ketema  Agricultral office page Gesuba ketema Agricultral office page
S**o

Gov.t Office at Gesuba

Dddd Dddd
S**o

Dddd is an unknown political organization

የመንፈስ ፍሬዎች የመንፈስ ፍሬዎች
W/S**o, Gununo, Ethiopia።
S**o, TAMRMISRAKDESTA

በመፀሐፍ ቅዱስ ወደ ገላትያ ስዎች 5:22-23የስፈረ ቃል ነው።

ገሱባ ከተማ አስ/ር ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ዩኒቲ ገሱባ ከተማ አስ/ር ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ዩኒቲ
Gesuba
S**o

Gesuba town administration workers and social affairs

Happy yoghurt house Happy yoghurt house
S**o

Quality housing materials supply, interior design for homes, hotels and shopping rooms all for a fai

𝘏𝘢𝘲𝘢𝘢 𝘖𝘳𝘰𝘮𝘰𝘰 𝘏𝘢𝘲𝘢𝘢 𝘖𝘳𝘰𝘮𝘰𝘰
Walagaa
S**o, 01

I.m oromoo first