Demtsachen Yesema Atlanta Support Group
Support Demtsachen Yesema
ዋ! እንዳትሳሳቱ!
-----
ሕዝበ ሙስሊሙ በዛሬው ጁምዓ ተቃውሞውን ያላሰማው ኡስታዞች ፌስቡክ ላይ እንደሚጽፉት የመጅሊስን ጥሪ አክብሮ ነው? ባለፉት ጁምዓዎችስ Protest ሊባል የሚችል ተቃውሞ ተደርጎ ነበር እንዴ? ምንም ዓይነት ተቃውሞ በሌለበት ሁናቴ ነው የጸጥታ ኃይሎች ህዝቡን በዱላና በጥይት የደበደቡት። የተቃውሞ ሰልፍ የሚመስል ዓይነት እንቅስቃሴ ከህዝቡ አልተነሳም። ሕዝቡ ስሜቱንና ንዴቱን እየገለጸ ያለው በሶሻል ሚዲያ ብቻ ነው።
-----
የሆነው እንዲህ ነው!!
በመጀመሪያው ሳምንት የጸጥታ ኃይሎች ለExcuse ይመቻቸው ዘንድ ቅጥረኞቻቸውን በመስጂድ በሮች ላይ አሰማሩ። ነገሩ ያልገባቸው ጥቂቶች በእነርሱ ተወናብደው ድምጻቸውን አሰሙ። ይህንኑ ይጠብቁ የነበሩት የጸጥታ ኃይሎች መስጂድ ድረስ ገብተው ምእመናንን በጥይት ገደሉ። (እዚህ ላይ ልብ በሉ!! ተቃውሞ ቢኖር እንኳ የጸጥታ ኃይሎች የተቃውሞ ሰልፍን ለመበተን ጥይት መጠቀማቸው በህግ የተከለከለ ነው። ይሁን እንጂ ዛሬ "ጸሐይ ወጥቷል፣ ለውጥ መጥቷል" በሚባልበት ዘመን ጭምር ተቃውሞን ለመበተን ውሃ መርጨት፣ የጎማ ጥይት መተኮስ፣ አስለቃሽ ጪስ መጠቀም ቅንጦት ሆኗል)።
በሁለተኛው ሳምንት ደግሞ ቅጥረኞቹ ቢመጡም ሕዝቡ ነቄ በማለቱ ከእነርሱ ጋር አልጮኸም። በመሆኑም የቅጥረኞቹ ድምጽ ታፍኖ ቀርቷል። ሕዝቡም ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ ውስጥ አልገባም። በዚያን ጊዜ አንዳንዶች ከበሩ ራቅ ብለው መስጂድ ውስጥ ቆመዋል። አንዳንዶችም ከመስጂድ ወጥተው በሰላም ወደ ቤታቸው እየሄዱ ነበር።
ሆኖም ለኢስላም እና ለሙስሊሞች ጥላቻ ያላቸው ኃይሎች ያሰማሯቸው የጸጥታ ኃይሎች ሌላ ሰበብ አልጠበቁም። የተላኩት ከሰጋጆቹ መካከል ቀረብ ያሉትን ገድለው በሙስሊሙ ሕዝብ ላይ ሽብር እና ፍርሓት ለመፍጠር ነበርና እነርሱ በከፈቱት ተኩስ ብዙ ምእመናን አለቁ። ከዚያ ወዲህ ደግሞ መጅሊስ እና መንግሥት ትርኢታቸውን የሚተውኑበት ሌላ መጋረጃ ተከፈተ።
በዚህ ደረጃ በቁጥር የበዙ ሙስሊሞች በአንዋር መስጂድ የተገደሉት በ1987 እና በቀይ ሽብር ዘመን ብቻ ነው። ከዚህ ውጪ ያለፈው የኢህአዴግ መንግሥት በዱላ ብዙዎችን ቢፈነክትም ምእመናኑን እንደዚህ በጭካኔ አልገደለም። በተለይም በድምጻችን ይሰማ ዘመን በየሳምንቱ ተቃውሞ ይደረግ የነበረ ሲሆን ፖሊሶች ከመስጂዱ አጥር አልፈው ወደ ውስጥ አልገቡም።
------
ዛሬም እንደ ባለፈው ሳምንት ከሙስሊሙ ሕዝብ የተነሳ ተቃውሞ አልተነሳም። ተቃውሞ ማድረጉም አስፈላጊ አልነበረም። ሕዝቡ ቢያንስ የመንግሥት የልብ ትርታ ምን ያህል እንደሚመታ በትንሹም ቢሆን አውቋልና ለጊዜው ተቃውሞውን ውጦታል።
አሁን እንደምናየው ከሆነ ሕዝቡ እርስ በራሱ እየተነጋገረ ነው። የመንግሥትንም መግለጫ እየገመገመው ነው። ሁሉም በየጀመዓው "የመንግሥት ባለስልጣናት ትናንት የገቡት ቃል ተአማኒነት ያለው ነው? የሕዝቡን attention ለማስቀየስ ያስወሩት ቢሆንስ? ለወደፊቱ መስጂዶች እንዳይፈርሱ ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?" እየተባባለ ነው። ከዚህ ውጪ ማሕተሙን እንኳ አስተካክሎ ማሰራት ያልቻለ እና ከውስጣዊ ውዝግብ እና ንትርክ ራሱን ያላጸዳ መጅሊስ የለቀቀው መግለጫ በሕዝቡ ዘንድ ተቀባይነት አግኝቷል ብሎ መዘብዘብ ውሃ የማይቋጥር ወሬ ነው።
------
መፍትሔው!!
የኢትዮጵያ መንግሥት ከአሁኑ crisis ለመውጣት ከፈለገ መፍትሔው ቀላል ነው።
1. የሕዝብን ድምጽ መስማት
2. መስጂዶች ከተገነቡ በኋላ "ህገ ወጥ ናቸው" እያሉ ማፍረስን ማቆም
3. መስጂዶችን ከከተሞች ዘመናዊ ማስተር ፕላን ጋር እንዲጣጣሙ አድርጎ ለማሰራት ከተፈለገ መንግሥት መሸፋፈኑን ትቶ ከሕዝበ ሙስሊሙ ጋር በቀጥታ ተነጋግሮ የሕዝቡን ይሁንታ ማግኘት፣ መስጂዶቹ ከፈረሱ በኋላ በድጋሚ ተገንብተው እስኪያልቁ ድረስ ደግሞ ሕዝቡን ማሳተፍ
4. እስከ ዛሬ ለተፈጸሙት ጥፋቶች ኃላፊነቱን መውሰድ፣ ለሞቱትና አካላቸው ለገደለው ሁሉ ካሳ መክፈል፣ አላግባብ የታሰሩትን በአስቸኳይ መፍታት፣ ከመጠን በላይ የሆነ ኃይል የተጠቀሙ የጸጥታ አካላትን ለፍርድ ማቅረብ፣
5. ለወደፊቱ ከተለመደው የክፍለ ከተማ ደንብ አስከባሪዎች ውጪ የታጠቁ የጸጥታ ኃይሎችን በመስጂድም ሆነ በሌሎች ቤተ እምነቶች አቅራቢያ አለማሰማራት
-----
ይህ በኔ እይታና ግምገማ የደረስኩበት አስተያየት ነው። በርካታ ሰዎችም የኔ ዓይነት አስተያየት አላቸው። መንግሥት ሁሉንም ማድመጥ አለበት።
-----
ድል ለሰፊው ሕዝብ!
አላሁ አክበር!!
10 አመት በፊት የሙስሊሙ ትግል ትውስታ
http://sndup.net/n9v4
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
600 Means Street NW, Ste 100
Atlanta, 30313
Hands On Atlanta mobilizes the Atlanta community to tackle our city's most pressing needs.
PO Box 724325
Atlanta, 31139
Our Gift & DREAM? "Atlanta: City of Peace - A Global Capital of Peace" [Please "Like" & "Share"]
Atlanta
All volunteer membership organization, based in Atlanta,GA
1201 Peachtree Street NE Ste. 200
Atlanta, 30361
HGA is an international membership association created to encourage excellence, inspire creativity,
8601 Dunwoody Place, Ste 318
Atlanta, 30350
GAA Annual Meeting: September 5-7 Hyatt Regency Savannah
Atlanta, 30308
Like Modern Architecture?So do we! Become a fan of DOCOMOMO Georgia Chapter - learn about DOcumentati
1447 Peachtree Street NE Ste 900
Atlanta, 30309
The focus of the ADE North Carolina Digital Empowerment Summit will be to focus on “The JET Agenda” (Jobs, Education and Training) in underserved communities. For more information...
1 Dunwoody Park, Ste 200
Atlanta, 30338
The Atlanta Sales and Marketing Council (SMC) is a 300-member council comprised of sales and marketing professionals in the homebuilding industry focused on education, programs, m...