ኮልፌ ወረዳ 07 ወሳኝ ኩነት ፅ/ቤት

ህብረተሰቡን በፍጥነት በቅልጥፍና በፍትሃዊነት ማገልገል ተ?

17/01/2023

አባት እናቱ ከአላንድ አልወለዱ
አባታጠቅ ካሳ ያዉ አንዱ ያዉ ወንዱ።

እጅ አልሰጥም ብሎ ለፈረንጅ ካቴና

ወድቆ ተሰበረ ሽጉጡን ጠጣና።

የአባ ፈንቅል ልጅ ወሬሳዉ ካሳ
አባቱ ነበር እናቱ አንበሳ
ዞብል ላይ ሁኖ ይታያል አዉሳ

ከቱርክ ይዋጋል እንኳን ከወሬሳ
ያባ ፈንቅል ልጅ መይሳው ካሳ

ሱሪህ አረንጓዴ ጎራዴህ ባለወርቅ
ያምርብሀል ካሳ አንተ ብቻ ታጠቅ

ይላል መሰንቆኛው የካሳ ኢትዮጵያን ታልቅና ገናና ለማድረግ ከሌት የሚባዝነውን ንጉስ ራዕይ በመሰንቆ ሲያናግረው ።

አፄ ቴዎድሮስን ስናነሳ ጥር 6 ቀን 1811 ዓ.ም ጎንደር ይወለዱ እንጂ፤ ጀግንነታቸዉ በአጠቃላይ የሰሩት ነገር ሁሉ ለሃገራቸዉ ለአንዲት ኢትዮጵያ ነዉ።

እንደሚታወቀዉ በመሳፍንት ተከፋፍላ የነበረች ኢትዮጵያን በዉድም በግድም አስገብረዉ፤ አንድ አድርገዉ፤ አሁን ያለቸዉን ኢትዮጵያን ያወረሱ ታላቅ ንጉስ ናቸዉ ።

በትውልድ ስማቸው ካሳ ሃይሉ
በፈረስ ስማቸው አባ ታጠቅ

በወታደራዊ ስማቸው መይሳው ካሳ ወይም አንድ ለናቱ በንግስና ስማቸዉ አፄ ቴዎድሮስ የ19ኛው ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት፤ ወታደርና ፖለቲከኛ ነበሩ።

መይሳው ካሳ ገና በጉብና ዘመናቸዉ በዘመነ መሳፍንት ተከፋፍላ የነበረችውን ኢትዮጵያን አንድ የማድረግ ታላቅ ራዕይ ይዘው በመነሳት
በጦር አበጋዞች ፉክክር ምክንያት የዘመነ መሳፍንት በጎጥና በመንደር ተበታትና የነበረችዉን ኢትዮጵያን አንድ በማድረግ ጠንካራ ማዕከላዊ መንግስት ባልነበረበት ወቅት ጠንካራ መሪ ላልነበራት ኢትዮጵያ ጠንካራ መሪ የሆኗት የሀገራዊ አንድነት ትልም አመንጭተዉ የተስፋ ብርሃንን የፈነጠቁ ።

ታላቋን ኢትዮጵያ ለመገንባት ከመድፍ መስራት መንገድ መጥረግ የተናቁ ሙያዎችን ያስከበሩ ጋፋት አካባቢ የብረት ማቅለጫ፤ ከዝያም በራሳቸዉ ጥረት በጣና ላይ የባሕር ሐይል ለመስራት የሞከሩ
ባርነትን የሚያግድ አዋጅ በማወጅ ሰዉ በሰዉነቱ እኩል መሆኑን ያስከበሩ የመጀመሪያው መንገድ ግንባታ፣ የሥርዓተ ንዋይና የፖለቲካ ሥርዓቱን በማዕከላዊ መንገድ በማዋቀር ለወታደሩ ደሞዝ በመክፈል የዘመናዊ ኢትዮጵያን ጉዞ ታሪክ “ሀ” ብለዉ የጀመሩ በቀይባህር አድርጎ ወደኢትዮጵያ በመግባት የአባይን ምንጭ ለመያዝ ያሰፈሰፈዉን ጠላት ለመመከት የጦር መሳሪያ ማምረት አስፈላጊ መሆኑን በመገንዘብ ከጎንደር ከወሎ ከጎጃም ሽዋ ሞረቴ ደንቢያ አንጥረኞችንና ሙያተኞችን በማሰባሰብ በቴክኖሎጂን በማሸጋገር በራስ አቅም ነፃነትን አስጠብቆ የመቆም ለትውልድ ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ ታላቅ ራዕይ የነበራቸው ንጉስ ።

ሀገር 1 አርጎ የመግዛት ህልም ከሃገር አልፎ እየሩሳሌምን ነጻ ለማውጣት ቀን ከሌት የሚባዝኑ ታላቅ ባለ ራዕይ በዕርዳታ እና በድጋፍ የቆመች ሀገር ሃያል ሀገር እንደማትሆን ቀድመው በመረዳት
ሀገራቸውን በዘመናዊ ጦር ለማደራጀት የነበራቸው ጉጉት የባህር በር ለማስከበር የነበራቸው ትልቅ ህልም ለማሳካት ያለእርፈት ከሰሜን እስከ ደቡብ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ የማሰኑ እረፍት የማያዉቁ ሩህሩህነት ቁርጠኝነት ለጋስነት ኩራት መገለጫቸው የነበሩ ባለ አንበሳ ግርማ በኢትዮጵያ ጉዳይ እንደነብር ቁጡ ጀግና ነበሩ ።

የታላቁ ንጉስ ህዝቤን አሰልጥኑልኝ አስተምሩልኝ መሳሪያ አትርዱኝ መሳርያ እንዴት እንደሚበጅ አሳዩኝ እንጂ ብለው የጠየቁት ጥያቄ ሀገራቸውን በዘመናዊ ጦር ለማደራጀት የነበራቸው ጉጉት እየሩሳሌምን ነጻ ለማውጣት የነበራቸው ትልቅ ህልም ሀገራችን በቅኝ ግዛት ለመያዝ አሰፍስፈው ለነበሩት እንግሊዛውያን የሚዋጥ አልነበረም እና በጀኔራል ናፒየር የሚመራ ወታደር ከሀገረ እንግሊዝ እና በቅኝ ግዛት ከያዟቸው ሀገራትም ሳይቀር አሰባስበው ሚሊዮን ፓውንድ መድበው ጦር ሰብቀው ደንበራት አቋርጠው የቋረኛውን ክንድ ሊጨብጡ የሀበሻውን ንጉስ ሊወጉ መቅደላ አንባ ድረስ መጡ በራሳቸው ንድፍ ያሰሩት ታላቅ ተስፋ እና ዕምነት የጣሉበት መድፋቸው ሴባስቶፖል ጥቂት ካታገላቸው በኋላ ከጥቅም ውጭ ሆኖ ተስፋቸውን ሲያጨልም ወንድ ሲጨብጥ የነበረ ክንዴን ለማንም አላስነካም ብለው መቅደላ አንባ ላይ ራሳቸውን ገደሉ እንጂ

ለባርነት ለጭቆና እጅ አልሰጡም
ገደልን እንዳይሉ ሞተው አገኟቸው
ማለክን እንዳይሉ ሰው የለ በጃቸው
ምናሉ እንግሊዞች ሲገቡ ሀገራቸው

ሲሉ የጠየቁ ነበሩ ምክኒያቱም የሀበሻን ንጉስ ማርከው ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ስር ሊያስተዳድሩ በብዙ ደክመው ነበርና፡፡
የእንግሊዝ ሰራዊት ፋሲካ በዋለ ማግስት ሰኞ ሚያዝያ 7/1860ዓ.ም ራሳቸውን ከሰው በኋላ ሀገር የመውረር ምኞቱ ሲከሽፍበት ሽንፈቱን የሚሸፍንበት ምንም አጣ ውርደቱን የሚያላክክበት ኪሳራውን የሚያካክስበት ምንም አልተረፈውም ዕቅዱ የውንዱን ክንድ መጨበጥ ዓላማውም ጤዎድሮስን መማረክ ቃለ ኪዳናቸውም ቴዎድሮስን መያዝ ነበር ግን አልሆነም መይሳው በሰው እጂ አልወድቅም ብሎ ሽጉጡን ጠጥቶ ወድቋል ንዴት እና ሽንፈት የተናነቃቸው ወታደሮች ለላኳቸው ሹማመንት ምን መመለስ እንዴት መመለስ ግራ እንደተጋቡ ከአስከሬናቸው ላይ ጸጉራቸውን ላጭተው ወሰዱት ሲል በወቅቱ የነበረ እና በኋላም የጉዞ ማስታወሻ የጻፈው ሰው ክሊማንትስ ማርካም በጉዞ ማስታወሻው አስፍሮታል፡፡

መቅደላ አፋፉ ላይ ጩኋት በረከት
የሴቱን አናዉቅም ወንድ አንድ ሰዉ ሞተ


ዛሬም ልደታቸውን ስናከብር አፄ ቴዎድሮስ ጀግንነት ታሪክና ዝናንን ከማስታወስ በተጨማሪ
ለአንድ ኢትዮጵያ አንድ በሚያደርገን ነገር ላይ አንድ ሆነን ሃገራችንን ለማሳደግ ካወረሱን ጠንካራ የስነ ልቦና ልዕልና
ወርሰን ታላቅ ሃገራዊ ራዕዩን በማዬት ሌላ አኩሪ ታሪክ ልንሰራ ይገባል ።

መዩ የወንዶች ቁና መልካም ልደት !💚💛❤️

Photos from Ghion Maleda ግዮን ማለዳ's post 17/01/2023
Want your organization to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address


Addis Ababa

Opening Hours

Monday 02:30 - 11:30
Tuesday 02:30 - 11:30
Wednesday 02:30 - 11:30
Thursday 02:30 - 11:30
Friday 02:30 - 11:30
Saturday 02:30 - 06:30
Other Government Organizations in Addis Ababa (show all)
Addis Ketema woreda 5 Communication Addis Ketema woreda 5 Communication
Addis Ababa
Addis Ababa

This is woreda 5 communication office .

Addis Ketema Woreda12 Communication Addis Ketema Woreda12 Communication
Addis Ketema
Addis Ababa

በዚህ ወሳኝ ወቅት ከመንግስት ተቋማት የሚተላለፉትን መረጃዎ�

የቦሌ ሥራ፤ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ፅ-ቤት የቦሌ ሥራ፤ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ፅ-ቤት
Addis Ababa

የቦሌ ሥራና ክህሎት ፅ-ቤት Official የፌስቡክ ገፅ ነው፤ እኛን የሚመለከት ጉዳይ ካለዎት ያግኙን።

Addis Ababa City Administration Trade Bureau Addis Ababa City Administration Trade Bureau
Addis Ababa
Addis Ababa

News

Addis Ababa City Admin. Landholding Registration and Information Agency Addis Ababa City Admin. Landholding Registration and Information Agency
604 Equatorial Guiene Avenue
Addis Ababa

Serving reliable cadastral services and information

Lafto woreda 05 Communication Lafto woreda 05 Communication
Addis Ababa

peace for Ethiopia

Ethio-engineering Group Ethio-engineering Group
Bole Sub City, Gerji, Amora Building
Addis Ababa

Ethio-engineering Group is a governement owned industrial enterprise established under the laws of the Federal Democratic Republic of Ethiopia /FDRE/ by the decree of the council o...

Yeka Sub city Small Tax payers branch Office Yeka Sub city Small Tax payers branch Office
Addis Ababa

Revenue for societal infrastructure and facilities

Ministry of Irrigation & Lowlands - Ethiopia Ministry of Irrigation & Lowlands - Ethiopia
Kasanchis
Addis Ababa

The Ministry of Irrigation & Lowlands (MILLs) is FDRE's Ministry established in 2021.